ኢትዮጵያዊቷ ስራ ፈጠሪ ፍሬወይኒ መብራህቱ የሲ ኤን ኤን የአመቱ ˝ጅግና˝ ተብላ ተመርጣለች፡፡

Image may contain: 1 person, standing

የሲ ኤን ኤን የ2019 ˝ጀግና˝ ኢትዮጵያዊት ፍሬወይኒ መብራህቱ

ኢትዮጵያዊቷ ስራ ፈጠሪ ፍሬወይኒ መብራህቱ የሲ ኤን ኤን የአመቱ ˝ጅግና˝ ተብላ ተመርጣለች፡፡

https://edition.cnn.com/videos/world/2019/05/02/cnnheroes-mebrahtu-mixed.cnn

ፍሬወይኒ መብራህቱ በአሜሪካን ሀገር የኬሚካል ኢንጅነሪንግ ትምህርቷን የተከታተለች ሲሆን፥ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉ የሴቶች የፅዳት መጠበቂያዎችን ዲዛይን ያደረገች እና የፈጠረች ናት፡፡

ማሪያም ሰባ የተሰኘ የፅዳት መጠበቂያ ምርት የሚያመርት ፋብሪካ በመቐለ ያቋቋመቸው ፍሬወይኒ መብርሃቱ ፥ ለዚህ ስራዋ የሲ ኤን ኤን የ2019 ጀግና በመሆን ተመርጣለች፡፡

ከህይወት ልምዷ በመነሳት የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ማምረቻ ያቋቋመቸው ሰናይት፥ በፈረንጆቹ 2006 በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የንፅህና መጠበቂያው የባለቤትነት ማረጋገጫ በኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተሰጥቷታል፡፡

ይህ የንፅህና መጠበቂያ ማምረቻ ፋብሪካ ለ42 የአካባቢው ሴቶች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፥ በየአመቱ የወር አበባ መጠበቂያን ጨምሮ 600 ሺህ የንፅህና መጠበቂያ እና 300 ሺህ የውስጥ ሱሪዎችን ያመርታል፡፡

ፋብሪካው ሴቶች በኢኮኖሚው ራሳቸውን እንዲችሉ ወሳኝ ነው ያለችው ፍሬወይኒ መብራህቱ፥ ለሴት ሰራተኞቿ ነፃ ስልጠና፣ የቴክኒካል ስልጠና ክፍያ እና ሌሎች እድሎችን ይጠቀማሉ ብላለች፡፡

ከዚህ ባለፈ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የንፅህና መጠቢያ መጠቀም እንዳለባቸው በማስተማር የወር አበባ መጠበቂያ ድጋፍ ታርጋላቸው፡፡

በፋብሪካው ከሚመረቱ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ 80 በመቶውን ለሴቶች በነፃ ለሚያከፋፍሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንደምትሸጥም ተነግሯል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት መረጃ እንደሚያመላክተው 75 በመቶ የሚሆኑ ኢትጵያውያን ሴቶች የወር አበባ ሲከሰትባቸው የንፅህና መጠበቂያ አይጠቀሙም።

ማሪያም ሰባ በተባለው የንፅህና መጠበቂያ ፋብሪካ የሚመረተው ይህ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ሙሉ በሙሉ የሚታጠብ እና ፈሳሽን መጦ ያመያዝ አቅም ያለው መሆኑ ከThis is Africa የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)