የአራት ኪሎዎቹን መንትያ ሕንፃዎች ለቤተ ክርስቲያን መመለሱን የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ፤“ተከራዮች ባሉበት ይቀጥላሉ”

ለመኖሪያና ለንግድ የተከራዩ ኹለት ባለ12 ፎቅና ኹለት መለስተኛ ሕንፃዎች ናቸው፤ በመኖሪያነት የሚጠቀሙበትም ኾነ በንግድ የተሠማሩት ተከራዮች ባሉበት ይቀጥላሉ፤ በልዩ ፖሊቲካዊ ውሳኔ እንዲመለሱላት መወሰኑን፣ የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፤ እንዲመለሱላት፣ ያለፉትና ያሉት ቅዱሳን ፓትርያርኮች በተደጋጋሚ ሲጻጻፉ ኖረዋል፤ በአቡነ ቴዎፍሎስ አመራር፣ እስከ 10ኛ ፎቅ ከገነባች በኋላ ነበር በደርግ የተነጠቀችው፤ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 10ሺሕ ቤቶች አንዱ ኾኖ ቆይቷል፤ *** …