በጦላይ ስልጠና ላይ ባሉ የኦነግ አባላት የጤና እክል ገጠማቸው

በጦላይ ስልጠና ላይ ባሉ የኦነግ አባላት ላይ ምንም አይነት የከፋ ጉዳት አለመድረሱን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ
የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ስልጠና ላይ ያሉ የኦነግ አባላት የገጠማቸውን የጤና እክል መነሻ ምን እንደሆነ ፖሊስና የሚመለከታቸው አካላት ምርመራ እያደረጉ ነው።ውጤቱ ሲታወቅም ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ብለዋል ።

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ከሰሞኑ በአባላቱ ላይ የምግብ መመረዝ አጋጥሟል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑንም አቶ አድማሱ ገልፀዋል።

የጤና እክል የገጠማቸው 136 የሚሆኑ የሰራዊቱ አባላት በወሊሶ ሉቃስ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ምንም አይነት የከፋ የጤና ችግር እንደሌለባቸውም ተረጋግጧል ብለዋል።

መንግስት በስልጠናው ላይ የምግብ የመኝታና የጤና እንዲሁም ሌሎች አቅርቦቶችን ማሟላቱንም የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊው ገልፀዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ በሰራዊቱ አባላት ላይ የምግብ መመረዝ ደርሶባቸዋል ሰራዊቱ ላይም ይህ ነገር እንዲደርስ ተደርጓል በሚል አየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች ውሸት መሆናቸውን ሀብረተሰቡ ተገንዝቦ ትክክለኛውን መረጃ ከመንግስት ሊያገኝ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ በስልጠና ላይ የሚገኙ የኦነግ ሰራዊት አባላት ከ1ሺህ በላይ እንደሆኑ ተገልጿል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE