ኢህአዴግ ውይይትና ግምገማ በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል ።

የኢህአዴግ ምክር ቤት ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት ከዛሬ ጀምሮ ማለትም ሚያዝያ 7 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን የሚካሂድ መሆኑን ምክር ቤቱ አስታውቋል ።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስበሰባውም በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ የሚመክር መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

በዚህ መሰረትም ምክር ቤቱ ያለፉት ወራት የድርጅት ስራዎች አፈጻጸም እንዲሁም በሌሎች ሀገራዊና ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይትና ግምገማ በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል ።