የህወሃት አብዮታዊ ዴሞክራሲ በራሱ በድርጅቱ ውስጥ የነበሩ አመራሮች እንኳን ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ እንዳይችሉ የሚያሸማቅቅ ነው።- ዛዲግ አብርሃ

“ህወሃት ‘መስርቸዋለሁ (ፈጥሬዋለሁ)’ የሚለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ አይደለም ለህዝብ፣ ለኢህአዴግ አመራሮች እንኳን አልጠቀመም። የህወሃት አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ በራሱ በድርጅቱ ውስጥ የነበሩ አመራሮች እንኳን ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ እንዳይችሉ የሚያሸማቅቅ ነው። በተግባር ደረጃ፣ ህወሃት ራሱንም ሆነ ሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ አልቻለም። ከዚህ ይልቅ፣ ህዝብ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በበጎ ጎኑ የሚመለከቱ አመራሮችን ከስልጣናቸው ማንሳት ዋነኛ ተግባሩ ነበር፤ አሁንም በዚያ ቀጥሏል። …..

….በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውስጥ የሚደረጉ ተሃድሶዎች ዋነኛ ዓላማም ቢሆን፣ ለህወሃት ተፎካካሪ የሆኑ እህት ድርጅቶች እንዳይፈጠሩ መከላከል ነበር። ይፈለግ የነበረው ጠንካራ ህወሃት እንጂ፣ ጠንካራ ኢህአዴግ አልነበረም። …

…..ህወሃት ባደረጋቸው ተሃድሶዎች ችግሮችን የሚቀርፍ ለውጥ ማምጣት አልቻለም። ህወሃት የሚያነሳቸው ‘ዴሞክራሲን አመጣለሁ’ የሚሉ። ፉከራዎች፣ የአንድ ወቅት ጮኸት ይሆኑና ተግባራዊ ሳይደረጉ ይቀራሉ። በ1993 ዓ.ም ህወሃት ዴሞክራሲን ለማስፈን በአንጻራዊነት የተሻለ ተሃድሶ ያደረገ ቢሆንም፣ በ1997 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ስልጣኑን ለማጣት የተቃረበ በመሆኑ፣ እውነተኛ ባህሪው ወጥቶ፣ ሰዎችን በግላጭ ለማፈንና ለመጨቆን ተገድዷል፤ ሁሌም ቢሆን የህወሃት አመራሮች ከስልጣን በላይ የሚያስቀድሙት ነገር የላቸውም፤ ዋናው ጉዳያቸው እዚህ ላይ የተንጠለጠለ ነው። ….

….ዴሞክራሲ ስልጣንን ለመልቀቅ፣ ስልጣንን ለማጋራት እንዲሁም ከሃላፊነት ለመውረድ ዝግጁ መሆንን ይጠይቃል። የህወሃት አመራር ግን ዝግጁ አይደለም፤ ምርጫን የሚቀበለው ስልጣኑን ካላስጠበቀለት ብቻ ነው፤ ለእሱ ምርጫ ማስመሰያ ነው። …

…..አሁን ባለው ሁኔታ፣ ህወሃት በኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን፣ በትግራይም ሳይቀር ተቃውሞ እየገጠመው ይገኛል፤ ተቃውሞው ፊት ለፊት የማይታይ ቢሆንም፣ ውስጥ ውስጡን ግን እየተንተከተከ ነው። የህወሃት ማብቂያ እዛው (ትግራይ) እንደሆነ ይሰማኛል። ከትግራይ ህዝብ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የማግኘት እድሉ እየጠበበ ነው። …

…እኔ የህወሃት አባል በነበርኩበት ወቅት በሚኒስትርነት አገልግያለሁ። በህወሃት ውስጥ ከነበሩት ተጽእኖ ፈጣሪና አንጋፋ አምስት ሚኒስትሮች መካከል አንዱ ነበርኩ። በነበረኝ የሚኒስትርነት ሹመት በእርካታ ተጽእኖዎችን በመፍጠር ድርጅቱን አግለግያለሁ። ዛሬ ላይ ሆኜ፣ በህወሃት ውስጥ በነበረኝ የሃላፊነት ዘመን፣ ተጽእኖ ፈጣሪ ነበርኩ? ወይንም አልነበርኩም? ብዬ ራሴን መጠየቅ አልፈልግም። ምክንያቱም፣ ድርጅቱ በስልጣን ላይ ለዓመታት ሲያስቀምጠኝ፣ ለቦታው እንደምመጥን አምኖብኝ ነው። ከዚህ ባለፈ የድርጅቱ አባላትም የትግራይ ህዝብ ተጽእኖ ፈጣሪነቴን ይመሰክሩልኛል።” …..

[ዛዲግ አብርሃ፣ ትናንት ለንባብ በበቃችው ኢትዮጲስ ጋዜጣ ላይ ካደረገው የመጀመሪያ ክፍል ቃለ ምልልስ ላይ ከሰጠው ምላሽ ውስጥ የተወሰደ ነው።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE