ሁለት የደቡብ አፍሪካ ሂሊኮፕተሮች ኢትዮጵያ ገብተዋል፤ ማጥፋቱን ነገ ጠዋት ይጀምራሉ

ሁለት የደቡብ አፍሪካ ሂሊኮፕተሮች ኢትዮጵያ ገብተዋል፤ ማጥፋቱን ነገ ጠዋት ይጀምራሉ ረዥም ጊዜ የፈጀው ረዥም በረራ ለማድረግ የሚችል ሂሊኮፕተር ሲፈለግ ነው፡፡ ማጥፊያው በሌላ ተጭኖ ነው የመጣው” ተብሏል።

ከሳምንታት በፊት በሰሜን ብሔራዊ ፓርክ የተነሣውን እሳት ለማጥፋት በፌዴራል መንግሥት ደረጃ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ከአማራ ክልላዊ መንግሥት ጋር ሲተባበሩ ቆይተዋል:: ይኸውም የእሳት ማጥፋት ስራው ከዉጭ የእሳት አደጋ ሄሊኮፕተሮች የፌዴራል መንግስት በማስመጣት ላይ በነበረት ግዜ በሀገር ሰው ርብርብ እሳቱን ለማቆም ተችሎ ነበር::

በአሁኑ ወቅትም እስካውቶች፣ ልዩ ሕይል አባላትና በጎ ፈቃደኞች ሲረባረቡ ቆይተው ከረቡዕብ ወዲህ ግን እሳቱ በሰው ለመድረስ ከማይቻልበት ረባዳ ቦታ ገብቷል:: በመሆኑም በጠሚ/ር ጽ/ቤት አመቻችነት የፌዴራልና የክልሉ መንግስት አካላት ባደረጉት ጥረትና ጥሪ ከዉጪ ሀገሮች የተገኙ የእሳት አደጋ ሄሊኮፕተሮች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች የእሳት ማጥፋት ሥራውን ለመጀመር ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል::

PMOEthiopia


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE