ቤተ ክርስቲያንን ከጥቃት ለመታደግ: ቅዱስ ሲኖዶስ የእረኝነት፣ መንግሥት የሕግ አስጠባቂነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ደቀ መዛሙርቱ ጠየቁ፤ “ለዝምታም ኾነ ትዕግሥት መጠንና ልክ አለው!”

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለቤተ ክርስቲያን ሉዓላዊነት መከበር ድምፁን አላሰማም፤ አላወገዘም፤ መንግሥት፣ አገር የተባለችውን ቤተ ክርስቲያንና ምእመናኗን ከጥቃት አልጠበቀም፤ የቅዱስ ሲኖዶሱ ዝምታ ይሰበር፤ ለመንጋው አለመጨነቅ ሊያበቃ ይገባል፤ መንግሥት፣ ከቃላት ባለፈ ችግሮች እንዳይደገሙ ግዴታውን ይወጣ! ቋሚ ሲኖዶሱ፣ ፓትርያርኩንና ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን በመሸምገል ላይ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱን ያነጋገረ ሓላፊም ኾነ አባት የለም፤ *** በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች፣ በቤተ ክርስቲያን፣ በካህናትና …