በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡

Image may contain: textበሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡

ሱዳን ለሦስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ ማወጇን ተከትሎ በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳሰበ፡፡

በሱዳን ከምሽቱ 4፡00 በኋላ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ በትናንተናው ዕለት የሰዓት እላፊ መታወጁ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ በአገሪቱ የሚስተዋለው የፀጥታ ችግር እስኪረጋጋ ድረስ ሕዝባዊ ተቃውሞ ወደሚደረግባቸው አካባቢዎች ከመሄድ እንዲቆጠቡ ኤምባሲው አሳስቧል፡፡

ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚያጋጥሟቸውን ድንገተኛ ሁኔታዎች በተከታዮቹ ስልክ ቁጥሮች ለኤምባሲው ሪፖርት እንዲያደርጉም ተጠይቀዋል፡፡

0912534834፣ 0911646547፣ 0900410075፣ 0121111465፣ 0900368617፣ 0183471156

ምንጭ፡- ኢቢሲ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE