የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ቢከናወን በሃገሪቱ ላይ ሌላ ቀውስ መጋበዝ መሆኑ ታምኖበታል

ቆጠራው እንዲራዘም ሲወሰን ሰፊ ክርክር ተደርጎና በወቅቱ ቢከናወን በሃገሪቱ ላይ ሌላ ቀውስ መጋበዝ መሆኑን ሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም ፌዴራል መንግስት አምነውበት መወሰኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ተናግረዋል፡፡

ከአንድም ሁለት ጊዜ የተራዘመውና መች እንደሚከናወን ገና በውል ውሳኔ ያላገኘው 4ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ምንም እንኳን በጊዜ ገደቡ መከናወን ባይችልም አመኔታ ያለው ሆኖ እንዲከናወን ይሰራል ሲል ማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለ« DW » ተናግሯል፡፡ ቆጠራው እንዲራዘም ሲወሰን ሰፊ ክርክር ተደርጎና በወቅቱ ቢከናወን በሃገሪቱ ላይ ለሌላ ቀውስ መጋበዝ መሆኑን ሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም ፌዴራል መንግስት አምነውበት መወሰኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ተናግረዋል፡፡ ከምንም በላይ ግን በሃገሪቱ የጸጥታ መጓደል በየቦታው ከቀያቸው የተበተኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረግ አለመቻሉ ቆጠራውን ለማራዘም ገፊ ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል፡፡ቆጠራው መራዘሙ ሲሰማ የቆጠራ መሳሪያውን ወደየ ቤታቸው ይዘው ሄደው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚደርሱ ሰራተኞችም አሁን ንብረቶችን መልሰው ገቢ አድርገዋል ብለዋል ሃላፊው፡፡