አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።

የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ «መኢአድ» ባካሄደዉ ስምንተኛ መደበኛ ድርጅዊ ጉባዔ የድርጅቱ ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረን የድርጅቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም ጌጡን ፤ ምክትል ፕሬዚዳንት ደግሞ አቶ ሙሉጌታ አበበን አድርጎ ሾምዋል። የፓርቲዉ የቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር በዛብህ ደምሴ በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት መካተታቸዉ ን የድርጅቱ የሥራ አስፈፃሚዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል።

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE