በአገሪቱ ከሚታየው አለመረጋጋት አንፃር ቦርዱ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን የመቀየር ስልጣን የለውም ተባለ።

የሥራ ጫናም ሆነ በአገሪቱ ከሚታየው አለመረጋጋት አንፃር ቦርዱ የምርጫው የጊዜ ወደፊት መገፋት እንለበት ቢያምን ይህን የማድረግ ሥልጣን አለው ወይ በሚል የተጠየቁት የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥልጣን “የለውም” ብለዋል አያይዘውም ሊደረግ የሚችለውን አብራርተዋል።”ምርጫ ለማድረግ ያህል አናደርግም።ምርጫ በዜጎች ደህንነትና ሕይወት ላይ የተባባሰ ነገር ለማምጣት ብለን አናደርግም። ምርጫ የተሻለን ነገር ለማምጣት ነው መደረግ ያለበት። እስካሁን ከተደረጉ ምርጫዎች በአብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል ተአማኒነት ያገኘ እንዲሆን አድርገን ለሱ የሚያስፈልጉንን ነገሮች በኛም ፣ በተሳታፊዎችና በሰላሙ ሁኔታ መሬት ላይም መኖራቸውን አረጋግጠን ነው የምናደርገው። “ ብለዋል ….

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

 

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE