ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ ከባድ የሙስና ወንጅሎች የተጠረጠሩ ባለስልጣናትን በቁጥጥር ስር አዋለ!

ፌደራል ፖሊስ ከ 61 በላይ ባለስልጣናትን በቁጥጥር ስር አዋለ!

ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ ከባድ የሙስና ወንጅሎች የተጠረጠሩ የመንግስት ባለስልጣኖችን ከትላንትና ጀምሮ በቁጥጥር ስር ማዋል ጀመረ፡፡ እስካሁንም ከ61 በላይ በተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ከ3ወራት በላይ በፈጀው ምርመራ በተለይም የመድሃኒት ግዢ፣ የመንገድ ግንባታና የተለያዩ የኮንስትራክሽን ስራዎች እንዲሁም ከሌሎች ከተለያዩ ዘርፎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች መኖራቸውም ጭምር ተረጋግጧል፡፡ በጉዳዩ ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ብርሃኑ ፀጋዬም ዛሬ ከሰአት በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እነደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩን አቶ ይገዙ ዳባንና ምክትላቸው አቶ ሰለሞን አይንማርን ጨምሮ የመስሪያ ቤቱ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች ትናንት ረፋድ ላይ ከቢሮአቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ኤጀንሲና ከሌሎችም መስሪያ ቤቶች እስካሁን ከ60 በላይ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰምተናል፡፡ጉዳዩ ከሙስና ጋር ሳይያያዝ እንደማይቀር ምንጮቻችን ነግረውናል፡፡

በቁጥር ስር ያሉት የመንግስት የስራ ሀላፊዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ለመጠየቅ ወደ ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ደውለናል፡፡

አጠቃላይ መግለጫ እንሰጥበታለን በሚል መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡በፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የመንግስትንና የህዝብን ሀብት ማባከናቸው የተረጋገጠባቸው ገንዘቡን እንዲመልሱ ተጠይቀዋል፡፡

ገንዘቡን ያልመለሱትም ክስ እንዲመሰረትባቸው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በአፈ ጉባኤው የተቋቋመው የኦዲት ግኝቶችንና የተወሰዱ ማስተካከያዎችን የሚከታተለው ልዩ ቋሚ ኮሚቴ ከሁለት ሳምንት በፊት ለዐቃቤ ህግ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

Fed Police Arrest 61 Government Officials  http://ow.ly/anOP30op9QD

Federal Police have arrested Yigezu Daba, director general of the Public Procurement & Property Disposal Service and 60 other government officials on suspicion of corruption and economic sabotage.

Officials from the then Ministry of Finance, Economics & Cooperation, the Public Procurement & Property Disposal Service, the Food & Drug Administration Agency, the Pharmaceuticals Fund & Supply Agency and the Ethiopian Water Works Construction Enterprise were also arrested yesterday, April 11, 2019, by a police operation that began early in the morning.

The Office of the Attorney General is expected to give a press conference late in the afternoon today.

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE