የሱዳን ወታደራዊ ሃይል ፕሬዝዳንቱን አውርዶ ስልጣን መቆጣጠሩን አወጀ።

የሱዳን ወታደራዊ ሃይል ፕሬዝዳንቱን አውርዶ ስልጣን መቆጣጠሩን አወጀ። የሱዳኑ ፕሬዚዳንትና ረዳቶቻቸው ከስልጣን ወርደው በቤተመንግስት ውስጥ በቁም እስር እንደሚገኙ ተነግሯል ለሶስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ለሶስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። የመከላከያ ሚኒስትሩ የሽግግር መንግስቱን እኔ እመራዋለሁ ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።የፖለቲካ እስረኞች ሙሉ በሙሉ እንደሚፈቱ ሚኒስትሩ ቃል ገብተዋል።

የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሺር ከስልጣን መውረዳቸውን ለማሳወቅ ጠብቁኝ ማለቱን ሮይተርስ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ ዘግቧል።የሁለት አመት የሽግግር ወቅት እንደሚደረግ የመከላከያ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህንን ቢሉም ተቃዋሚው ሕዝብ በፍጹም ፈቃደኛ ባለመሆኑ የተቃውሞ ሰልፉ እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።

Image may contain: 1 person, sitting
ወታደራዊ ኃይሉ በርካታ ወታደሮችን በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በማሰማራት አውራ ጎዳናዎችና ድልድዮችን ዘግቶ ቤተመንግስቱን እንደከበበ የሱዳን ቴሌቪዥን በዘገባው ጠቅሷል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ከታህሳስ ወር ጀምሮ የአል በሺርን አስተዳደር በመቃወም ሰልፍ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።
የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ለ30 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩትን ፕሬዚዳንት አል በሺርን ከስልጣን በማውረድ የሽግግር ጊዜ ምክር ቤት ማቋቋሙን እንደሚገልፅ ይጠበቃል።በአሁኑ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን በዋና ከተማዋ ካርቱም ማዕከላዊ ቦታዎች ደስታቸውን እየገለጹ ጸረ አል በሺር መፈክሮችን እያሰሙ ነው ተብሏል።

የሀገሪቱ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች የአርበኝነት ሙዚቃዎችን እያሰሙ መሆኑንም መረጃዎች አመላክተዋል።

https://platform.twitter.com/widgets.js


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE