መረጃ የማግኘት ችግር ተባብሷል ሲሉ ጋዜጠኞች አማረሩ

በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከመንግሥት መረጃ ማግኘት አዳጋች እየሆነ መምጣቱን ጋዜጠኞች ተናገሩ። በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን የተለያዩ እድሎች እና ተግዳሮቶች ላይ አትኩሮ ትንንት እና ዛሬ በአፍሪቃ ኤኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በተካሄደው ዐውደጥናት ላይ የተሳተፉ ጋዜጠኞች በተለይ የቀድሞው የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ከፈረሰ ወዲህ ችግሩ መባባሱን ለዶቼቬለ DW ተናግረዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ስለ ወቀሳው የቀድሞውን የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ የወሰደው ፣የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክረታርያት አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠይቅም ለዛሬ መልሱ አልደረሰውም።

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE