በሶማሊያ አንድ የፌዴራሉ ዓባል የሆነ ግዛት ከማዕከላዊ መንግሥት ጋራ ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ተከትሎ በሃገሪቱ የሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ተባብሷል።
በሶማሊያ ከሚገኙ ስድስት የፌዴራሉ ዓባል ግዛቶች ውስጥ አንዷ የሆነችው በደቡብ የምትገኘው ጁባላንድ ከፌዴራል መንግሥቱ ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን በይፋ አስታውቃለች፡፡
ይላል የግዛቲቱ ካቢኔ ስብሰባን ተከትሎ ዛሬ ከኪሲማዮ የወጣው መግለጫ…