መንግሥት በየአካባቢው ቁጥራቸው እየተበራከቱ የመጡትን የጎበዝ አለቆችና ታጣቂዎችን በህግ አግባብ ሊያስታግሳቸው ይገባል – ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና

“መንግስት ጊዜ በማራዘም ፖለቲካዊ ቀውሱን ሊወጣው እንደማይችለው ተገንዝቦ …በየአካባቢው ቁጥራቸው እየተበራከቱ የመጡትን የጎበዝ አለቆችና ታጣቂዎችን በህግ አግባብ ሊያስታግሳቸው ይገባል።”
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
Image may contain: 1 person, sitting and indoor
(ኢ.ፕ.ድ)

መንግሥት ጊዜ በማራዘም ፖለቲካዊ ቀውሱን ሊወጣው እንደማይችለው ተገንዝቦ በየአካባቢው ቁጥራቸው እየተበራከቱ የመጡትን የጎበዝ አለቆችና ታጣቂዎችን በህግ አግባብ ሊያስታግሳቸው ይገባል ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተናገሩ።

መንግስት ለውጡ ወደታች ወርዶ ህዝቡን የሰላሙ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ ሊያስቀምጥም እንደሚገባ ነው የገለጹት።

«በአሁኑ ወቅት ስልጣን ላይ ያለው መንግሥት ችግሮችን በእቅድና በጊዜ ለክቶ ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ አይታይም» ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፤ ይህም ቀውሱን የተሻለ መልክ ለማስያዝ ለሚፈልጉ ኃይሎች በር እየከፈተ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህንን በአፋጣኝ ማድረግ ካልተቻለ አሁን አለ የሚባለውም መፍትሄ ከእጅ ሊያመልጡበት የሚችሉበት እድል መኖሩን ጠቁመዋል። የህዝብና ቤት ቆጠራውም ሆነ ለምርጫው ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጥ ከተወሰነ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚታየው ፖለቲካዊ ትርምስ ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ሊዛመት ይችላል የሚል ብርቱ ስጋት እንዳላቸውንም አመልክተዋል።

ከአዲስ ዘመን ቅዳሜ መጋቢት 14/2011 የተወሰደ

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://www.press.et/Ama/?p=7322