በፍቅር – በሕብረት መቆም ሲቻል ውጤቱ ምን መሆን እንደሚቻል ያሳየንበት ነው። – ታማኝ በየነ

“እንደ እምነቴ ይሄ የሆነው በእግዜብሔር ነው። በዚህ ደረጃ ሕዝብ ይንቀሳቀሳል ብዬ የሚል ግምት አልነበረኝም። በፍቅር – በሕብረት መቆም ሲቻል ውጤቱ ምን መሆን እንደሚቻል ያሳየንበት ነው። እስካሁን አንድ ሚልዮን ሁለት መቶ ሃምስ ሺህ ሶላር ደርሷል።”

በምዕራብ ጉጂና ጌድዎ ዞኖች ግጭት ቀዬውን ጥሎ እንዲበተን የተገደደው ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ዛሬም ደራሽ ዕርዳታ ይሻል።

ለግጭቶቹ ዘላቂ መፍትሔና ተፈናቃዩን ሕዝብ መልሶ ለማቋቋም የአካባቢውና የፌድራል መንግስት ሊወስዱ ከሚገቡ እርምጃዎች ባሻገር ዜጎች በሕይወት አድኑም ሆነ በሃገር ደረጃ ብጥብጥን በሚያርቁና ሰላም በሚያመጡ ጥረቶች ዜጎች ያላቸውን ሁነኛ ድርሻ የሚያመላክት ምግባር ነው።

የዋሽንተን ዲሲው “ዓለምቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት” የተሰኘው የጋራ ግብረ-ኃይል መሰንበቻውን ለጌድዎ ተፈናቃዮች እርዳታ አሰባስቧል።