ከንቲባዋ የለገጣፎ አካባቢ ተወላጅ አይደለችም፤ ከለገጠፎ ምክር ቤትም አይደለም የመጣችው፤ ይህ በራሱ ህገ ወጥ ነው።(አበበ አካሉ)

መምህር አበበ አካሉ ይባላል። በቀድሞው አንድነት ፓርቲ ከዚያም በኋላ በሰማያዊ ፓርቲ ባለፉት አመታት በተለያዩ የአመራርነት ቦታ ያገለገለ እውቅ ሰው ነው። በተለያየ ግዜ ለእስር እና እንግልት ተዳርጓል ፤ በLTV በተዘጋጀው የሰፊው ምህዳር ውይይት ላይ ተገኝቶ ታጋይነቱንና ሃቀኝነቱን ያሳየ ብርቱ ሰው ነው።

መምህር አበበ አካሉ ምን አለ?
1ኛ. 27 አመት ሙሉ ስንታገለው የነበረው ህወሃት እንኳን በሎደር ቤት አላፈረሰም፤ ያሁኑ የለውጥ መሪ ተብዬ መንግስት ግን ተጎጅዎች የቤታቸውን ፍራሽ ቆርቆሮ እንኳን እንዳይሸጡ አድርጎ ምንም ሃላፊነት በማይታይበት መንገድ በሎደር አፍርሷል።

2ኛ.የለገጣፎ ህዝብ የቤት ባለቤት እንዲሆን ላለፉት አመታት ታግለናል። የቤት ባለቤቶቹ ህጋዊ ስለመሆናቸው መረጃውን ማቅረብ እችላለሁ። እነዚያ የተፈናቀሉ ህዝቦች በመድሃኒያለም፣ በገብርኤልና በማርያም ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ነው ያሉት። የሚያሳዝነው ደግሞ የኦዴፓ ባለሳጣናት ቤታቸውን ማፍረሳቸው ሳያንስ በተጠለሉበት ቦታ እርዳታ እንዳያገኙ እየተደረጉና ከተጠለሉበት የእምነት ቦታ እንዲወጡ እያደረጉ ነው።

3ኛ.ዜጎችን ህገ ወጥ ናችሁ ብለው የሚያፈናቅሉት ባለስልጣናት አይደለም ህጋዊ ሰብዓዊ እንኳን አይደሉም። ብዙዎቹ በእጅ በጅ ሙስና የተጨመላለቁ ናቸው፤ መረጃ የሚፈልግ አካል ካለ እኔ ጋር ማግኘት ይችላል። ለምሳሌ ከንቲባዋ የለገጣፎ አካባቢ ተወላጅ አይደለችም፤ ከለገጠፎ ምክር ቤትም አይደለም የመጣችው፤ ይህ በራሱ ህገ ወጥ ነው።

4ኛ.ልዩ ጥቅም የሚለው ሃሳብ የጤነኞች ሃሳብ አይመስለኝም። የሁሉም ችግር ምንጩ ህገ መንግስቱ ነው። እኛ ህገ መንግስቱ እንዲሻሻል እንፈልጋለን፤ እንታገላለን። ልዩ ጥቅም የሚለው በራሱ ዝርዝር ነገሮችን እያስቀምጥም።ይህ በራሱ አንድ ክፍተት ነው። ልዩ ጥቅም የሚባልም አያስፈልግም፤ የተለዬ ዜግነት የሚባል አለ እንዴ ኢትዮጵያ ውስጥ?!

5ኛ.አሁን እንደምናዬው ልዩ ጥቅም የሚለው ሃሳብ እየተቀነቀነ ያለበት ሁኔታ ዱላና ገጀራ ይዞ ይህ አካባቢ የኦሮሞ ነው፤ ከኦሮሞ ውጪ ያለው ህዝብ አያገባውም ይውጣ በሚመስል ሁኔታ ነው። ኦዴፓ/ODP ይህን መሰል እኩይ እንቅስቃሴ ባየ ምሽት ላይ እንቅስቃሴውን የሚደግፍ መግለጫ ማውጣቱ ያሳዝናል። ኦዴፓ ጤናማ መሆን ከፈለገ መግለጫውን revise ማድረግ አለበት።