በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የተቋቋመው ኮሚቴ የህግ ድጋፍ አለው ወይ ?

የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ አባል የሆነው የኦሮሞ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኦዴፓ) የአዲስ አበባ አስተዳደር ገንዘባቸውን ለቆጠቡ ነዋሪዎች የጋራ ቤቶችን ማስተላለፉን እንደማይቀበለው እና በአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይም መግለጫ ከወጣ በኋላ ውዝግብ ተቀስቅሷል፡፡

ውዝግቡን አርግቦ መፍትሄ ለማፈላለግ ጠቅላይ ሚኒስሩ በአዲስ አበባ አስተዳደርና በኦሮሚያ ክልል መካከል አለ የተባለውን የወሰን ችግር ለመፍታት፤ የሚሰሩ 8 አባላት ያለው ኮሚቴ ማቋቋማቸው ይታወሳል፡፡ በሌላ በኩል ለአስተዳደር ወሰን ችግር፣ እልባት ይሰጣል ተብሎ የተሰየመው አዲሱ ኮሚቴ፣ ከመቋቋሙ በፊት፣ በተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ ያገኘና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮችን አጥንቶ የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባል የተባለ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡

ታዲያ አዲስ የተሰየመው ኮሚቴ የህግ ድጋፍ አለው ወይ ? ፓርላማው ከሰየመው ኮሚሽን የተለየ ስልጣን ካለው የተጣረሰ አሰራር አይሆንም ወይ ? የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው፡፡