ሰብዓዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋል የተባሉ 13 የአፋር የጸጥታ ሐይሎች አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ለብዙዎች መሰቃየትና መብት ረገጣ ምክንያት የሆኑ የአፋር ክልል የፀጥታ አስከባሪ ሐይሎች አመራሮች ማለትም 13 የሚሆኑ ኮማንደሮች ለህግፊት እንዲቀርቡ ወሳኔ ተላላፈ።

ከእነዚህ መካከል፦
1) ኮማንደር ዘይኑ እ/ም የልዩ ዋና አዛዥ የነበሩ
2) ኮማንደር ማህሙድ መሀመድ የልዩ ምትክል አዛዥ
3)ም/ኮማንደር አህመድ መሀመድ
4)ም/ኮማንደር አብዱ ኑሩ
5)ም/ኮማንደር አብዱ ማርቶሌ
6)ም/ኮማንደር ኑርሳ መሀመድ
7)ም/ኮማንደር ደርሳ አህመድ
8)ም/ኮማንደር ጋዱ ሱብሃቶ
9)ም/ኮማንደር ማህሙድ አሊ
10)ም/ኮማንደር መሃመድ ኢብራሂም
11)ም/ኮማንደር ኡመር ካበኤ
12)ም/ኮማንደር አመር መሀመድ
13)ም/ኮማንደር አብዱ ኡመር


ከነበሩበት ሐላፊነት ተሰናብተው ለፈፀሙት ቀንጀል በህግፊት እንዲጠየቁ በአዋሽ አርባ ስደረግ የቆየው ግምገማ መወሰኑን ተማኝ ምንጮች ይገልፃሉ። በአፋር ታሪክ ይህ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። እስከዛሬ ተጠያቂነት የታየበት ውሳኔ በአፋር ታይቶ አይታወቅም። የተጠቀሱ ኮማንደሮች ላለፉት በርካታ አመታት ህግና ህገመንግስት አልፎም የዜጎች መብት ከማስከበር ይልቅ የግለሰቦችና የቡዱኖች ጥቅም ለማስከበርና የወያኔ ሚሊሺያ የነበሩ የአፋር (የትዓዴ) አመራሮች ዙፋን ለማስቀጠል የበርካቶችን መብት የተጋፉ ከአካል ጉዳት እስከ ህይወት መጥፋት የደረሰ ውሳኔ በንጹሃን ላይ የወሰኑ የአንባገነን ስርዓት አቀንቃኞች ናቸው። በህግፊት ቀርበው የእጃቸውን እንደየጥፋታቸው ሊቀጡና ለሌሎች ማስተማሪያ ሊሆኑ ይገባል።

በአንድ ጎን የተወሰነው ውሳኔ እደግመዋለሁ። በሌላ በኩል ግን ጥቂቶች ላይ ብቻ ትኩረት የተደረገ ውሳኔ መሆኑንና ብዙዎች ከላይ በሥም የተጠቀሱ የአምባገነን ዙፋን ጠባቂዎች ጋር እኩል የተሳተፉ አመራሮች ተጠያቂ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ሳይ አሁንም በአፋር ሰማይ ላይ የፍትህ ጀንበር በወጉ አለመውጣቷን የሚያመለክት በመሆኑ ሂደቶች ላለፉት 26 አመታት የመጣንበት የሗላቀርነት አይነት የቂም በቀል ፖለቲካ አካሄድ ይዘት እያራመድ ይሁን? የሚል ስጋት አሳድሮብኛል።

እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባ ነገር ቢኖር ተዛዦችን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በአንድ ሪሞት አፋርን በእነዚህ ኮማንደሮች እጅ ሲያስጨፈጭፉ የኖሩ ጌቶቻቸውን ካለምንም ቅደመ ሁኔታ ከግብረአበሮቻቸው ጋር የትዓዴ አመራሮች በአስቸኳይ በህግፊት ሊቀርቡ ይገባል። ከዚህ ቡሗላ አንዱን ደፍሮ አንዱን ፈርቶ አይነት የፈሪ ፖለቲካ ሊቆም ይገባል። ካጠቡ አይቀር ከራስ መጀመር ነው።

እነ አጅሬን ሚኒስተርና አማካሪን አድርጋችሁ በV-8 ሽሩጉድ እያስባላችሁ ተጠያቂነት ከታች መጀመሩ የፈሪዎች ዱላ ይመስላል። ለማንኛውም ይህ የመጀመሪያ እርምጃ በመሆኑ የሚደነቅ ቢሆንም ገና ያልተያዙ፣ ያልተፈተሹ በርካታ አፋኞች በፀጥታ ሐይሎች ስር የቀሩ በመሆናቸው እነሱን በፍጥነት ማየት የግድ ይላል።በመጨረሻ ግን የዛሬ ውሳኔ በሁለት ልብ የተወሰነ ውሳኔ ነውና ወጥመዱን በመዘርጋት ዋና አሳነባሪውን በመያዝ ደስታችንን ሙሉ አድርጉት ነው የምንለው።

Allo Yayo Abu Hisham


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE