ሻሸመኔ ከተማ ላይ አንድ ግለሰብን ደብድበው ሕይወቱ ሲያልፍ በአደባባይ ዘቅዝቀው የሰቀሉ ተፈረደባቸው

የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለፈው ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓም ሻሸመኔ ከተማ ላይ አንድ ግለሰብን ደብድበው ሕይወቱ ሲያልፍ በአደባባይ ዘቅዝቆ በመስቀል በከባድ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉ በሁለቱ ተከሳሾች ላይ የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ፈረደ።

የሻሸመኔ ከተማ የፍትሕ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጀልዶ በዳሶ ማምሻውን ለDW እንደገለፁት ቀደም ሲል በጉዳዩ ተጠርጥረው የተያዙት ስምንት ሲሆኑ ስድስቱ በመከላከያ ማስረጃ ነፃ ወጥተዋል።

እንዲያም ሆኖ በዕለቱ በቦታው ተረኞች ነበርን በማለት የሃሰት ምስክርነት ሰጥተዋል የተባሉ የፖሊስ አባላት በቦታቸው መታሠራቸውንም አመልክተዋል።

የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ገመዲ ሹሚ እና ደዋሮ ሁሴን ሲሆኑ እስካሁን የሟች ቤተሰብ ነን ወይም እናውቀዋለን የሚል አካል እንዳልተገኘም ገልጸዋል።

(ፎቶው ከሻሸመኔ የወቅቱን ሁኔታ የሚያመልክት ነው።)


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE