መንግስት በአስመራ ከጋምቤላና አፋር ነፃ አውጪ ንቅናቄዎች ጋር የእርቅ ስምምነት ተፈራረመ

መንግስት ከጋምቤላና አፋር ነፃ አውጪ ንቅናቄዎች ጋር የእርቅ ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ መንግስት ከጋምቤላና ከአፋር ነፃ አውጪ ንቅናቄዎች ጋር የእርቅ ስምምነት ላይ ተፈራረመ።

ከሁለቱ ፓርቲዎች ጋር ስምምነት ላይ የተደረሰው ትናንት በአስመራ በተደረገው ውይይት ነው ተብሏል።

ስምምነቱን የደረሱት የአገር መከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሀመድና የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ኡስማን መሀመድ ሁመዳ፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ፣ በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የድርጅቶቹ ተወካዮች በተገኙበት ነው።

ከጋምቤላና ከአፋር ነፃ አውጪ ንቅናቄዎች ጋር በተናጠል ተደረሰው በዚህ ስምምነት መሰረት ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ይሆናል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE