… ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ንገሩልን:: በእናትህ! በወለደችህ! ድረስልን በሉልን:: … አንዲት ነፍሰጡር ከሱሉልታ ከተማ

“… ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ንገሩልን:: በእናትህ! በወለደችህ! ድረስልን በሉልን:: በምትወዳት ኢትዮጵያ ይዘንሃል:: በባንዲራዋ ይሁንብህ…. በሉልን … ህቅ ህቅ ህቅ…”

የሱሉልታ አካባቢ ነዋሪዎች ቤታችሁ በ7 ቀናት ውስጥ ይፈርሳል ተብለን ስጋት ውስጥ ነን ይላሉ፡፡

ጠዋት ሸገር FM 102.1 እያዳመጥኩ ነበር:: (ዝርዝሩን ከታች ያዳምጡት) የሱሉልታ ከተማ አስተዳደር “ሕገ ውጥ” በማለት እንዲፈርስ ቤቶቻቸው ላይ በቀይ ቀለም “X” ምልክት የተደረገባቸው ዜጎች አንጀት ስፍስፍ በሚያደርግ ሁኔታ እያለቀሱ ችግራቸውን ለጣብያው አመልክተዋል::

ሸገሮች ስለጉዳዩ ለማጣራት ከንቲባዋ ወ/ሮ ሮዛ ዑመርንም ሆነ የኦሮሚያ የመሬት አስተዳደር ዶ/ር ሚልኬሳን ለማንጋገር ያደረጉት ጥረት ስልኮቻቸው በመዘጋቱ ሊያገኟቸው እንዳልቻሉ ነግረውናል::

ሬዲዮ ጣቢያው የተወሰኑ ነዋሪዎችን ድምፅ ቀርጾ ያቀረበ ሲሆን አንዲት ነፍሰጡር ነኝ ያለች እናት ሳግ በሚያቆራርጠው ልቅሶ እንዲህ አለች…

“… ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ንገሩልን:: በእናትህ! በወለደችህ! ድረስልን በሉልን:: በምትወዳት ኢትዮጵያ ይዘንሃል:: በባንዲራዋ ይሁንብህ…. በሉልን … ህቅ ህቅ ህቅ…”

በእናትህ !!!… ከዚህ በላይ ማዳመጥ አልቻልኩም::

የመጽሐፍ ቅዱሷ ራሔል ትዝ አለችኝ:: ግብጻዊውን አለቃ እንዲሁ ነበር የለመነችው:: “…በእናትህ! ነፍሰጡር ነኝ! አንድ ጊዜ ጽንሱን እስክገላገል ታገሰኝ! …” ልዩነቱ ራሔል የሰው ሀገር ግብፅ ሄዳ ነው:: የእኛዋ ግን በገዛ ሀገሯ ነው::

የሱሉልታ አካባቢ ነዋሪዎች ቤታችሁ በ7 ቀናት ውስጥ ይፈርሳል ተብለን ስጋት ውስጥ ነን ይላሉ፡፡

ቤቱ የሚፈርስበት ምክንያት ለመንገድ ግንባታ ነው ቢባልም እንዲፈርሱ ምልክት የተደረገባቸው ቤቶች እዚህም እዚያም መሆናቸው ለመንገድ እንዳልሆነ እንገምታለን ብለዋል፡፡

እንዲፈርሱ ምልክት የተደረገባቸው ቤቶች ከአንድ መደዳ አልፈው አልፈው ነው ይላሉ ነዋሪዎቹ፡፡ ይህን ልዩነት ያመጣው ምንድነው ? ለሚለው መልስ የሚሰጥ አልተገኘም፡፡

ሸገር ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የሱሉልታ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ ሮዛ ኡመርን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ አሁንም ለነዋሪዎቹ ጥያቄዎች መልስ ይዘን ለመመስ ጥረት እናደርጋለን…

ቅሬታቸውን ከነገሩን ነዋሪዎች የተወሰኑትን እንድታዳምጡ ጋብዘናል…


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE