በኢትዮጵያ እያታዩ ያሉ ቀውሶች ትኩረት ስለተነፈጋቸው በሀገሪቱ የተስተዋለውን የፖለቲካ ለውጥ ጥላ አጥሎበታል

የጌዴኦ ተወላጆችን ከጉጂ መፈናቀልን በተመለከተ የThe Guardian ጋዜጠኛ የሆነው ቶም ጋርድነር ሰፊ ሀተታ ፅፏል። ፅሁፉ ሰፊ ቢሆንም ሰብሰብ አድርጌ ለመተርጎም ሞክሪያለሁ። 👇👇👇 በ ጥላሁንፅጌ


“በኢትዮጵያ እያታዩ ያሉ ቀውሶች ትኩረት ስለተነፈጋቸው በሀገሪቱ የተስተዋለውን የፖለቲካ ለውጥ ጥላ አጥሎበታል”
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ዜጎች በርሃብና በሽታ ተጠቅተዋል። ጠሚ አብይ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ብቻ ያሰቡ ይመስላል።

በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ የርዳታ ሰራተኞች በክልሉ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ ቀውስ መከሰቱን ተናገርዋል። ይሁን እንጂ አዲሱ የአብይ አህመድ መንግስት በችግሩ ላይ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ወደስልጣን ከመጡበት የባለፈው ሚያዝያ ወር ወዲህ የፖለቲካ ምህድሩን አስፍተዋል፣ በኢትዮጵያ እና ኤርትራን ሰላማዊ ግንኙነት መስርተዋል። ጠሚ አብይ የኖቤል ሽልማት እጩ መሆናቸም ይታወሳል። መንግስታቸው የርህራሄ እና ተራማጅ አስተሳሰብ ምሳሌ የተባለለትን አዲስ የስደተኞችን ፖሊስም ተግባራዊ አድርጓል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሀገሪቱ በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀልና አስከፊ ህይወት መንግስት እየሰጠ ባለው ትኩረት ምክንያት ብዙዎች በመንግስት ላይ ጥርጣሬ አሳድረዋል።


ጎቲቲ በተባለው አካባቢ የተጠለሉ ከ20-30 ሺህ የሚሆኑ የጌዴኦ ተፈናቃዮች ከባለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ የሰብዓዊ በዋናነት የምግብ ርዳታ ተከልክለዋል።
በኢትዮጵያ ባለፈው አመት (2018) ከአንድ ሚሊየን በላይ ዜጎች በብሔር ተኮር ግጭቶች ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለመፈናቀል ተገድደዋል። ይህም ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገሮች በላይ በሀገር ውስጥ ብዙ ዜጎቿ የተፈናቀሉባት ቀዳሚ ሀገር ያደርጋታል። በጣም አስከፊው መፈናቀል የተከሰተውና በ2017 በማይናማር ሮሂንጋዎች ከተከሰተው በላይ የሆነው በደቡብ ኢትዮጵያ የተከሰተው የጌዴኦ ተወላጆች ከምዕራብ ጉጂ መፈናቀል ነው።
ጌዴኦዎችና የጉጅ ኦሮሞዎች በኢትዮጵያ ሰፊ ህዝብ የሰፈረበትን የእርሻ ቦታ ይጋራሉ። በህዝብ ብዛትም እያደጉ ነው። ከአካባቢው የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ዘግናኝ ግያዎች፣ አስገድዶ መድፈርና አንገት መቅላት ተፈፅሟል። የአካባቢው ባለስልጣናት፣ የፖሊስና ሚሊሺያ አባላት ከላይ የተጠቀሱ ወንጀሎችን አስተባብረዋል። በዚህም ምክንያት በጌዴኦ ተወላጆች ላይ ከተራ የጎሳ ግጭት ይልቅ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል ወደሚል ድምዳሜ ይወስደናል።
ከጉጅ ተፈናቅለው በጌዴኦ ዞን የተጠለሉት ብዙዎች የጌዴኦ ተወላጆች ወደተፈናቀሉበት ቦታ መመለስ ያስፈራቸዋል። ለመመለስ የሚያስችል ምንም ነገር የላቸውም። ቤታቸው በሙሉ ተቃጥሎባቸዋል። ማሳቸው (በሰፊው የቡና ማሳቸው) ተዘርፎና ወድሞ አሁን ምንም የለም። ተፈናቃይዮቹ ከቅርብ ሳምታት በፊት ወደ ተፈናቀሉበት ቦታ ለመመለስ ጥረት ያደረጉትን የጌዴኦ ተወላጆች ያሸበረውን በምዕራብ ጉጅ በንቃት እየተንቀሳቀሰ ያለውን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አማፂያንን እንደሚፈሩም ተናግረዋል።
ዜጎች እንዲህ ባለ አስከፊ ሁኔታ ላይ ሆነው ባለበት ሰዓት መንግስት በተደጋጋሚም ወደተፈናቀሉበት ቦታ እንዲመለሱ ሲያስስገደዳቸው ቆይቷል። መንግስት መጀመሪያው ከተፈናቀሉበት የሚያዝያ ወር በኋላ በሰኔ ወር እንዲመለሱ አድርጎ የነበረው ቢሆንም ግጭት ከበፊቱ ተባባሰ። ይህ እየሆነ ባለበት ሁኔታ መንግስት በነሐሴ ወር በባስና በጭነት መኪና በግድ ወስዶ ድንበር ላይ ጣላቸው። የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ በማቋረጥ ወደተፈናቀሉበት እንዲመለሱ የማድረግ ስራ መሰራቱን ሳይቀር በአካባቢው የተሰማሩ የእርዳታ ሰራተኞች ተናግረዋል። በታህሳስ ወር ከ15 ሺህ በላይ የጌዴኦ ተወላጆች በድጋሚ የጉጂን አካባቢ ለቅቀው ወጥተዋል።
መንግስት የሰብዓዊ እርዳታን በመከልከል ጌዴኦዎች ወደተፈናቀሉበት ቦታ እንዲመለሱ የማድረግ ስራን አሁንም እየሰራ ነው። ባሳለፍነው የካቲት ወር በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የእርዳታ ሰራተኞች በሌሎች የሰብዓዊ እርዳታ በሚያስፈልጋቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከመንቀሳቀስ እንታገዳለን ብለው በመፍራታቸው ማንነታቸው እንዳይታወቅ በመሆን በአካባቢው ምንም አይነት እርዳታ እንዳናቀርብ ለወራት ተከልክለናል ብለዋል። ለብርድ የሚሆን አልባሳትን በጥቂቱም ቢሆን ለማቅረብ ሙከራ ተደርጓል። ምግብ የለም፣ ማልኒውትሪሽን በየቦታው ነው ያለው። ተፈናቃዮቹ የተጠለሉበት ቦታ ሌላው ቢቀር በፕላስቲክ እንኳን ያልተከፋፈለ በመሆኑ ዝናብ በሚመጣ ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች አሳሳቢ መሆናቸውን ተናግረዋል።
መንግስት ባወጣው የሁለት ወር Action Plan መሰረት ባለፈው ወር ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በኢትዮጵያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደተፈናቀሉበት አካባቢዎች መመለሱን አስታውቋል። ይህ የመንግስት ፕላን ወደ ኦሮሚያ ለመመለስ በእጅጉ የሚፈሩትን ጌዴኦዎች የሚያካትት ይመስላል።
የእርዳታ ሰራተኞች እንደሚሉት ከሆነ መንግስት በደንብ ሳይዘጋጅ (ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል ተብሎ እየተሰጋ ላለው) በቀጣይ ለሚከሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ ሲባል ብቻ የጌዴኦ ተወላጆችን የመመለስ ስራ ሊሰራ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልፀዋል። ተፈናቃዮችን ያለፍላጎታቸው እንዲመለሱ ማድረግ እና ለዚህም የሰብዓዊ እርዳታን መገደብ የሰብዓዊ እርዳታ መርሆዎችን ይጥሳል።
ይህ ፖሊስ ለምንና በማን ስልጣንና ሀላፊነት እየተሰራ እንደሆነ ምንም ግልፅ የሆነ ነገር የለም። ዘርን መሰረት ያደረገው የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ነገሮች በማን ሀላፊነት እየተከወኑ እንደሆኑ ለማወቅ አዳጋች ያደርጋል። ለምሳሌ የእርዳታ ሰራተኞች የሰብዓዊ እርዳታ እንዳይዳርስ በተደጋጋሚ የሚከለክለውን የደቡብ ክልላዊ መንግስት ሲወቅሱ ሌሎች ደግሞ ይሄንን ያደረገው የበላይ አካል ነው ይላሉ። (የፌደራል መንግሥት ግን ተፈናቃዮችን ያለፍላጎታቸው እንዲመለሱ የማድረግም ሆነ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች እርዳታ እንዳይደረግላቸው
ብዬ አላውቅም ብሏል)።
የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሳዛኙ ተግባር በጉዳዩ ላይ ዝምታን መምረጡና ትኩረት አለመስጠቱ ነው። ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በጌዴኦም ይሁን በጉጂ ወይም በኢትዮጵያ ባሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች የሚገኙበትን የስደተኞች ካምፕ ሄዶ አልጎበኘም። ከእሱ በፊት የነበሩ መሪዎች ያደርጉ የነበረውን የፈላጭ ቆራጭነት ባህሪ ያስወገደ ቢመስልም በሀገሪቱ የሚስተዋሉትን ሰብዓዊ ቀውሶች ግን ትኩረት ነፍጓቸዋል። ያነጋገርኳቸው የእርዳታ ሰራተኞች እንደገለፁልኝ ከሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩና በእሱ ዙሪያ ያሉ ባለስልጣናት የተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ የመንግስትን ገፅታ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ከማበላሸቱ በፊት የዜጎችን መፈናቀል ትኩረት ባለመስጠት ችግሩን ረግጦ ስለማጥፋት እንደሚጨነቁ ገልፀውልኛል።
አንድ ከፍተኛ የሰብዓዊ እርዳታ ባለሙያ “በጌዴኦና ጉጂ አካባቢ ያለው ቀውስ እጅግ አስከፊ ነው። በአካባቢው የሰብዓዊ እርዳታ ስራዎችን ለመስራት አልቻለም። በጠቅላላ ሀገሪቱ ተመሳሳይ ችግር እንዳይገጠመን ስጋት አለኝ” በማለት የችግሩን አሳሳቢነት ገልፆልኛል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE