የኖርዌይ አየርመንገድ የቦይንግ ኩባንያን ካሳ ጠየቀ

የኖርዌይ አየርመንገድ የቦይንግ ኩባንያን ካሳ ጠየቀ

የኖርዌይ አየር መንገድ ከበረራ ላገዳቸው ቦይንግ 737 Max 8 አውሮፕላኖች ካሳ እንዲከፍለው ቦይንግን ጠየቀ።

አሜሪካን ጨምሮ የብዙ ሀገራት አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ከበረራ ውጭ ያድርጉ እንጂ የካሳ ጥያቄ አላነሱም ነበር ።

የኖርዌይ አየርመንገድ ግን የካሳ ጥያቄ በማቅረብ የመጀመርያው ሆኗል። ይህን ተግባር ሌሎቹም እንደሚከተሉት እየተገለፀ ነው።

የአየር መንገዱ ስራ አሰፈፃሚ ቦጆርን ጆስ ጉዳዩ እስ ኪጣራ ላቆምናቸው አውሮፕላኖች እኛ ተጠያቂ ልንሆን በሱ ሳቢያም ኪሰራ ልንገባ አይገባም ፤ አውሮፕላኑ ከበረራ ውጭ በመሆኑ ሳቢያ እየደረሰ ያለውን እያንዳንዷን ኪሳራ ያመረተው ኩባንያ ሊያካክስልን ግድ ይለዋል ብለዋል ለሲኤንኤን።

በዚህ ሳቢያ በደንበኞች ላይ በደረሰው መጉላላትም ስራ አስፈፃሚው ይቅርታ ጠይቀዋል።

ይህ ሂደት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 MAX 8 አውሮፕላን አደጋ ከደረሰበት በኋላ በቦይንግ ላይ እየደረሰ ያለውን የአክስዮን ድርሻ ማሽቆልቋል ይበልጥ ከፍ እንዲል ያደርገዋል ኪሳራም ያስከትላል ተብሏል።

ምንጭ፦ ሲኤን ኤን


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE