ይቅርታ እንዴት እንጠይቅ ?? ( ምህረት ደበበ )

ይቅርታ እንዴት እንጠይቅ ?? ( ምህረት ደበበ )
 
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሌላውን ሰው አስቀይመው ወይም ጥፋት አጥፍተው ይጸጸታሉ፡፡ ነገር ግን መጸጸትና ይቅርታ መጠየቅ ይለያያሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ይቅርታቸውን ከአንገት በላይ ያደርጉና ተበዳዩን አዛኝ መስለው በከንፈር መጠጣ (lips service) ይሸነግሉታል፡፡ አልያም መልሰው እንደሚያጠፉ እርግጠኛ እየሆኑ እንኳን የይስሙላ ይቅርታ ይጠይቃሉ፡፡ ሺህ ግዜ እያጠፋ ከስህተቱ ለማይማር ሰው ይቅርታ ትርጉም የለውም፡፡ እንዲሁም ይቅርታን ለጥፋቱ መሸሸጊያ የመጨረሻ ምሽግ ያደርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የሌላውን ሰው ልብ ያደማል፡፡ ይቅርታው በተግባር ለውጥ ስለማይታጀብ ከአፍ አይዘልም፡፡ የዚህ ስሜት በእራሳችን ደርሶ ካላየነው በስተቀር ህመሙ አይሰማንም፡፡
 
ታዲያ አሳማኝ ይቅርታ እንዴት መጠየቅ ይቻላል
 
አንድሪያ ብራንድ የተባለች ሳይኮሎጂስት ከዚህ የሚተሉት ስድስት ነጥቦች ይቅርታን ለመጠየቅ ጠቃሚዎች ናቸው በማለት ትመክራለች ፡-
 
#ከልብ የመነጨ ይቅርታ መጠየቅ
 
የተበዳይ የመንፈስ ስብራት እኛም በግለሰቡ ቦታ ብንሆን ምን ያህል እንደሚሰማን በማሰብ ከውስጥ በመነጨ ስሜት ይቅርታን መጠየቅ፡፡
 
#ስለበደሉት ነገር ዕውቅና መስጠትና ዳግመኛ ላለመበደል ኃላፊነትን+መውሰድ ፡-
 
ስለአጠፉት ጥፋት እቅጩን መናገር “አውቃለሁ እንዲህ ማድረግ አልነበረብኝም ፤ እኔ በአንተ ቦታ ብሆን ምን ያህል እንደሚሰማኝ እረዳለሁ፡፡ እባክህን ይቅር በለኝ!” በማለት ጥፋትን ለማረም ዝግጁ መሆንን ማሳየት፡፡
 
#ዳግመኛ ላለመበደል ቁርጠኛ መሆን ፡-
 
የበደላችሁት ሰው ከጥፋታችሁ እንደተማራችሁ እንዲያውቅ ማድረግ፡፡ ይህንንም ዕለት ተዕለት በሚደረግ አግባቦትና ተግባር በግልጽ ማሳየትና ምንም ለውጥ ያላሳየን እንደሆን ወዳጆቻችን በግልጽ ቅሬታቸውን እንዲገልጹ ማድረግ፡፡
 
#ይቅርታ የምትጠይቁት ሰው ለእናንተ ምን ያህል እንደሆነ መግለጽ ፡-
 
ከበደላችሁት ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በማድነቅ መግለጽ፡፡
 
#ይቅርታ_መጠየቅ ፡-
 
ይቅርታ መጠየቅ በሁለታችው መሃል ስላለው ግንኙነት አስፈላጊነት የሚያስረዳ ሲሆን፤ በምላሹ ተበዳይ ይቅርታ ለማድረግ ጊዜን ይፈልግ ይሆናል እንደ ጉዳቱ መጠን፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ሁኔታዎች ይቅር የሚባሉ ነገር ግን በደሉ ሊረሳ የማይችል ስለሚሆን፡፡ “Forgiven but never forgotten” እንዲል የባህር ማዶ ሰው፡፡
 
#ለውጥን_በተግባር_ማሳየት
 
“የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” እንደሚባለው በአገረኛው ዘይቤ፤ ያጠፉትን ጥፋት ዳግመኛ ላለመተግበር ለእራስ ቃል ታማኝ መሆን፡፡ ይህም የአእምሮ ደውል በመውስጣችን በማቃጨል “እንዲህ ላለማድረግ እኮ እንዲህ ብለህ ቃል ገብተሃል” በተግባር ቃልህን አሳይ በማለት፡፡
በደል ያቆስላል ልብንም ይሰብራል #ይቅርታ_ግን_ቁስልን_ይሽራል_የተሰበረ_ልብንም_ይጠግናል ፡፡
 
#ይቅርታ እንታረቅ!
 
ቅን ከሆኑ ለሌሎች ያጋሩ ።
www.fb.com/Dr.Mehret.Debebe

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE