በሃዋሳ በቀጠለው የስራ ማቆም አድማ በኤጄቶ እና በፀጥታ ኃይሎች መሐል ግጭት መከሰቱ ተሰማ

በሀዋሳ ከተማ እና በመላ ሲዳማ ከዕሮብ እስከ አርብ ለ3 ቀናት በኤጀቶ የተጠራው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዞ ቀጥሏል፡፡ትናንት ተዘግተው የዋሉት አንዳንድ ሱቆች እና የህዝብ መገልገያ ተቋማት በተወሰኑ መልኩ ዛሬ ተከፍተዋል፡፡ አድማው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል፡፡ ሆኖም በኤጄቶ እና በፅጥታ ኃይሉ መሐል ግጭት እንደሚታይ ነው የደረሰኝ መረጃ የሚያመለክተው፡፡ ትናንት የተወሰኑ ወጣቶች ተጎድተው ሆስፒታል እንደገቡ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል፡፡

Image may contain: outdoor
ባለፈው ሐሙስ ስብሰባ ጀምረው አርብ ዕለት በኤጄቶ ተደብድበው ወደየመጡበት የፈረጠጡት የደኢህዴን አባላት ከማክሰኞ ጀምረው በድጋሚ ሀዋሳ በመግባት በዝግ እየመከሩ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ምክሩን ከጀመሩ ዛሬ 3ኛ ቀኑን ይዘዋል፡፡ ባለፈው ለኤጄቶ ረብሻ ምክንየት የሆነው በተለይ በሲዳማ አመራሮች በኩል ከድርጅቱ አቅጣጫ በወጣ መንገድ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ እና ተከታዮቻቸው የሚፈፅሙትን ድርጊት በኃይል በማውገዛቸው ምክንያት የሲዳማ ተወካዮች አዳራሹን ረግጠው መውጣታቸው ነበር፡፡ በተለይ ሚሊዮን ማትዮስ ከክልል አስተዳዳሪነት እንዲወርድ የሁሉም ዞን ተወካዮች አጥብቀው ጠይቄዋል፡፡

በክልሉ ውስጥ ከፅዳት እና ጥበቃ ሰራተኞች እስከ ርዕሴ መስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ የአንድ ብሔር የበላይነት አለ በማለት ሁሉም አባላት እነ ሚሊዮንን ተችተዋል ፡፡ በዛም ምክንያት የሲዳማ ተወካዮች ስብሰባ በተጀመረበት ዕለተ ሐሙስ ስብሰባውን ረግጠው ሲወጡ ሌሎቹ ሐሙስ ሲገማገሙ ውለው አርብ ዕለት ልቀጥሉ አዳራሹ በገቡበት ነው ወከባው የገጠማቸው፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ይህን ድርጊት አጄቶ እንድፈፅም በግልፅ ጥሪ ቀርቦ ነበር፡፡ “እንደትላንቱ ዛሬም የሲዳማ ተወካዮች በሌሉበት በሀዋሳ መሸገን ሲዳማ ህዝብን እንሰድባለን ካላችሁ ኤጄቶ የስብሰባ አዳራሻችሁን ይከባል” በማለት ነበር ጉዳዩን ያሳወቀችው፡፡ ከስብሰባ መደፍረስ ቦኃላም በ8:00 በሀዋሳ ከተማ ኤጄቶ እንዲሰባሰብ ጥሪ አድርጋ ነበር፡፡ ተሳክቶላታልም፡፡ በአሁኑ ስብሰባ ሚሊዮን ከክልሉ አስተዳዳሪነት ይወርዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE