ትጥቅ የፈቱ የኦነግ ወታደሮች የረሃብ አድማ ላይ ናቸው፡፡

ትጥቅ የፈቱ የኦነግ ወታደሮች የረሃብ አድማ ላይ ናቸው፡፡

Image may contain: 2 people, people standing and outdoor

በአባ ገዳዎች ማግባባት ትጥቅ ፈትተው ወደተዘጋጀላቸው መጠለያ የገቡ አንድ ሺህ የሚሆኑ የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ወታደሮች የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ የሚገኙት እነዚህ የቀድሞ የኦነግ ወታደሮች በካምፑ ለአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ መጋለጣቸውን ተናግረዋል።

አንድ የቀድሞ የኦነግ ወታደር “የተያዝንበት ሁኔታ በጣም አስከፊ ነው። ብዙ ጓደኞቻችን በምግብ እጥረትና በንፅህና መጠበቂያ አገልግሎት ችግር ታመዋል” ሲል ሁኔታውን ገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ በቀጣይ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ይመለሱ ዘንድ ይሰጣችኋል የተባለው ስልጠናም ሆነ ሌሎች የተገቡላቸው ቃሎች አለመፈፀማቸውን ገልፀዋል።

የኦነግ ወታደሮች ትጥቅ ፈትተው ወደ ካምፕ እንዲገቡ ኦነግን እና መንግስትን ሲያሸማግል የነበረው ኮሚቴ አባል የሆኑት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው አቶ በቀለ ገርባ ወታደሮቹ ችግሮች እንዳሉባቸው የሰሙ ቢሆንም በካምፑ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት የክልሉን መንግሥት ፍቃድ እየጠበቁ እንደሆነ ተናግረዋል።

ምንጭ – ቢቢሲ አማርኛ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE