በርሃብ ከተጎዱት ወገኖች መካከል ግማሽ ያህሉ በኦሮሚያ ክልል ነዋሪ ናቸዉ።

የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሺን ይፋ ባደረገዉ ሪፖርት መሰረት ፣ በያዝነዉ የአዉሮፓዉያን አመት 8.3 ሚልየን ኢትዮጵያዉን የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ለዚህም የሚሆን $ 1.3 billion በላይ ያስፈልጋል።

በርሃብ ከተመቱና እርዳታ ከሚያስፈልጋቸዉ ወገኖች መካከል ግማሽ ያህሉ በኦሮሚያ ክልል ነዋሪ ናቸዉ።

እንደ ኮሚሽነሩ አቶ ምትኩ ካሳ ገለጻ በርሃብ ከተጎዱት ዉስጥ

46 % በኦሮሚያ ክልል
20 % በሶማሊ ክልል
12 % በአማራ ክልል
10 % በደቡብ ክልል
4 % በትግራይ ክልል
4 % በአፋር ክልል የሚኖሩ ናቸዉ።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE