በባልደራሱ ስብሰባ መልስ የታሰሩ ቀሪ ወጣቶች ዛሬ ተፈቱ

በባልደራሱ ስብሰባ በኋላ የታሰሩ ወጣቶች ሁሉም ተፈተው ማለቃቸው ተረጋግጧል፡፡
——
ባሳለፍነው እሁድ ዕለት በባልደራስ አዳራሽ በተጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ፣ በሰላማዊ መንገድ በነቂስ የወጣው የአዲስ አበቤ ወጣት ለልዩ ጥቅም ተቧዳኝ እራስ-ምታት እንደሆነ እሙን ነው፡፡ በዚህ የተነሳ፣ ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ በአንዳንድ የስብስባው ታዳሚዎች ላይ የተሰማው የመታሰር ዜና ከተነገረ ወዲህ፣ አስተባባሪ ኮሚቴው በተለያዩ ጣቢያዎች ባደረገው አሰሳ የተወሰኑት ወጣቶች ወዲያው ከእስር መፈታታቸው ተሰምቷል።

የዝግጅት ኮሚቴው ይህን ለመቀበል ተጨማሪ ማረጋገጫ በመፈለጉ እና ፈለጋው. ተጠናክሮ በመቀጠሉ ቀሪ እስረኞች ከአራዳ ፖሊስ መምሪያ ወረዳ 9 ችሎት አካባቢ መፈታታቸው ከደረሰን ጥቆማ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመሆኑም በአሁን ወቅት፣ ከስብሰባው ጋር በተያያዘ የታሰሩ ወጣቶች አለመኖራቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Image may contain: one or more people and people standing


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE