ሀዋሳ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ላይ ናት ።

ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ በመላው ሲዳማ አከባቢዎች ተግባራዊ እየሆነ ነው!!

Image may contain: outdoor

ሀዋሳ የስራ ማቆም አድማ ላይ ናት ። መንግስት የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ችላ ብሎታል በሚል ለ3 ቀን የስራ ማቆም አድማ ተጠርቷል ባንኮችና አንዳንድ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም ትላንት ማታ በተበተነ ወረቀት በዛሬው ዕለት ትምህርት አቁሟል ።

በሀዋሳ የስራ ማቆም አድማ ውስጥ ያልተሳተፈ የነበረው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ነበር አሁን ጃዋር ከሲዳማ ወንድሞቻችሁ ጎን ቁሙ ባንኩን ዝጉ የአድማው ተባባሪ ሁኑ በማለቱ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክም የአድማው አኳል ሆኗል ።

Image may contain: one or more people, crowd, stadium and text

በሀዋሳ ከተማ በኤጄቶ የታወጀውን የ3 ቀናት የስራ ማቆም አድማ ተግባራዊነት እየተከታተልን ሲሆን አብዛኛዎቹ ባንኮች አዋጁን አክብረው ዘግተዋል። ነገር ግን በሀዋሳ ከተማ 4 ቅርንጫፍኡን ከፍቶ ከአዋጁ ውጪ የሆነው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ብቻ ነው። ስለዚህ የሚመለከታቸው አካላት ጉዳዩ ወደ ሌላ ነገር ሳይለወጥ ባስቸኳይ ባንኮቹን እንዲያዘጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን።( Sidama page)

Image may contain: outdoor

ጥቆማችንን ተቀብላችሁ ከባንኩ ማናጀሮች ጋር በመነጋገር የስራ ማቆም አድማው አካል እንዲሆኑ ላደርጋችሁ የኦሮሞ አክቲቪስቶች እና የኦሮምያ ህብረት ስራ ባንክ አመራሮች። አሁን ላይ በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ባንኮች ሁሉም በስራ ማቆም አድማው ተሳታፊ ሆነዋል!! ( Sidama page)


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE