የቦይንግ ኩባንያ የአክስዮን ድርሻ ዋጋ በዓለም የገበያ ሠንጠረዦች ላይ አሽቆለቆለ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የነበረውና በበረራ ቁጥር 302 ተመዝግቦ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ሲነሳ ከትናንት በስተያ ቢሾፍቱ አካባቢ የወደቀውን 737 ማክስ ኤይት አደጋ ተከትሎ የቦይንግ ኩባንያ የአክስዮን ድርሻ ዋጋ በዓለም የገበያ ሠንጠረዦች ላይ ማሽቆልቆሉን ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል።ቦይንግ ደግሞ አሁን ሥራ ላይ ያለውን የአሠራር መመሪያ እንደማይለውጥ አስታውቋል።

ተጨማሪ ሃገሮች ማክስ ኤይትን ከአየር ላይ እያወረዱ ሲሆን የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎችም ከአሜሪካ በረራዎች ለጊዜው እንዲታገዱ እየጠየቁ ናቸው።

የአቪዬሽን ቴክኖሎጂው እጅግ መዘመንና በኮምፕዩተር አሠራር መራቀቅ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን እምብዛም የሚያስደስታቸው አይመስል። “አልበርት ኧንሽታይን እንዲያበርረኝ አልፈልግም” ብለዋል። በሌላ በኩል ግን የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ኀዘናቸውን ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመድን ኩባንያዎች በዋስትና ክፍያ ጥያቄ እየተጨናነቁ ናቸው።

ቦይንግ ደግሞ አሁን ሥራ ላይ ያለውን የአሠራር መመሪያ እንደማይለውጥ አስታውቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE