Blog Archives

መንግሥት: በቅ/ሥላሴ ካቴድራል አድሏዊና መዝባሪ አስተዳደር ላይ ምርመራ እንዲያደርግ ተጠየቀ፤ ፓትርያርኩ፣ “አስተዳዳሪው አይነሣም፤ በአንገቴ ገመድ ይገባል” አሉ

“ለሰላም አደፍራሾች ምቹ ኹኔታ እንዳይፈጥር ፈጣን ርምጃ ይወሰድልን፤”/ካህናትና ሠራተኞች/ አድልዎውንና ምዝበራውን መንግሥት ጣልቃ ገብቶ እንዲመረምር ለጠ/ሚሩ አመለከቱ፤ ሊቀ ሥልጣናቱ(አስተዳዳሪው)፣ ጸሐፊውና ሒሳብ ሹሙ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ጠየቁ፤ በአስተዳደሩ የተዳከመው ሰበካ ጉባኤ፣ በካህናትና በምእመናን ምርጫ እንዲዋቀር አሳሰቡ፤ *** የሀገር ክብር መገለጫና የሀገር ባለውለታዎች የመጨረሻ ማረፊያ የኾነው ታሪካዊው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ በጎሠኞች አድሏዊ አስተዳደርና ምዝበራ፥ ቅርሱ እየተራቆተ፣ አገልጋዮቹ እየተንገላቱ፣ ገንዘቡና ንብረቱ እየተዘረፈ መኾኑን የገለጹ ካህናትና ሠራተኞች፣ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ምርመራ እንዲያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠየቁ፡፡ ካህናትና ሠራተኞች፣ ትላንት ማክሰኞ የካቲት 12 ቀን፣ በአድራሻ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ባደረሱትና ለሰላም ሚኒስቴር፣ ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በግልባጭ ባስታወቁት ደብዳቤአቸው፣ የአስተዳደሩን የአሠራር ብልሽቶችና መዛባቶች ከክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በየደረጃው ቢያቀርቡም መፍትሔ ባለማግኘታቸው፣ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ምርመራ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቁም ያሉት ዘረኝነትና ምዝበራ በቤተ ክህነት ተባብሶ እየቀጠለ በመኾኑ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ጉዳዩን ይመርምርልን፤” ያሉት ካህናቱና ሠራተኞቹ፥ በልማት ስም በካቴድራሉ የቅርስ ይዘትና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ታሪካዊው የቅ/ሥላሴ ካቴድራል: በልማት ስም ቅርስ ሕንፃዎቹ እየወደሙ፣ ጥንታዊ ዐጸዶቹ እየተጨፈጨፉ፣ ገንዘቡና ንብረቱ እየተዘረፈ ነው፤ የአባ ገብረ ዋሕድ ጎሠኛ አስተዳደር እንዲወገድ ተጠየቀ!

አስተዳዳሪው ሊቀ ሥልጣናት አባ ገብረ ዋሕድ ገብረ ኪዳን(ግራ)፤ ሒሳብ ሹሟ ወ/ሮ ሣራ ገብረ ሥላሴ(ቀኝ) በጎሠኛ አደረጃጀት ሰበካ ጉባኤውን አዳክመው ያሻቸውን የሚወስኑት አስተዳዳሪው አባ ገብረ ዋሕድ ገብረ ኪዳንና አራት የጽ/ቤት ሓላፊዎች እንዲነሡ፣ ሠራተኞችና ሰንበት ት/ቤቱ ቋሚ ሲኖዶሱን እየጠየቁ ነው፤ ፓትርያርኩ፣ “በአንድ ወገን ላይ የተነጣጠረ አቤቱታ ነው፤” በማለት ለአስተዳዳሪው በማድላታቸው በአቋም የተከፋፈለው ቋሚ ሲኖዶሱ ለመወሰን ተቸግሯል፤ ፓትርያርኩን ተቃውመው የአባ ገብረ ዋሕድ አስተዳደር መነሣት እንዳለበት አቋም የያዙት የቋሚ ሲኖዶስ አባላት፣ አቤቱታ አቅራቢዎቹን፣ “ውሳኔ ሊሰጣችሁ ወደሚችል አካል ኹሉ ሒዱ፤” ብለዋቸዋል፤ *** በመቃብር ቦታ ጥያቄና በግለሰብ ሠራተኞች ምደባና ዝውውር ሳይቀር ፓትርያርኩ ቀጥተኛ መመሪያ የሚሰጡበት አካሔድ ካቴድራሉን ለከፋ ጉዳት እያጋለጠው ነው፤ “የበቁ አባቶች ሕንፃ እንድገነባ በራእይ ታይቷቸው ነግረውኛል፤” ለሚሉት ቢትወደድ ባሕሩ አብርሃም ፈቃድ በመስጠታቸው፣ 25 ዕድሜ ጠገብ ሀገር በቀል ዐጸዶች ተጨፍጭፈዋል፤ ግንቡና ታሪካዊ ሐውልቶች ተንደዋል፤ ባለሀብቱ የአብነት ት/ቤት ለመሥራት ቢጠይቁም ሽፋን እንጂ፣ የሕንፃ ቤተ መቅደሱን ደኅንነትና ውበት፣ የምእመናንን ማስቀደሻና መጠለያ የሚጎዳ ባለ5 ፎቅ የግል መቃብር ቤት/ፉካ/
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞች የለውጥ ማነቃቂያ ሥልጠና ተሰጠ፤ “በመሪ ዕቅድ ለታገዘው ኹለንተናዊ ለውጥ ማዳረሻ ይኾናል፤”/ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ/

የኹሉም መምሪያዎች እና ድርጅቶች ዋና እና ምክትል ሓላፊዎች እንዲሁም መላው ሠራተኞች የተሳተፉበት መኾኑ ልዩ ያደርገዋል፤ “ሓላፊዎችና ሠራተኞች፥ ከውሸት፣ አሉባልታና መወነጃጀል ተጠብቀው ራሳቸውን በትምህርትና ሥልጠና ሊያሻሽሉ ይገባል፤” “ያዳከሙንንና ያስነቀፉንን ድክመቶች ለይተን የለውጡን መሰናክሎች ለማስወገድና ሒደቱን ለመለካት የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ያስፈልገናል፤” “ከፖሊቲካ ራቅን እያልን ቤተ ክርስቲያንን ከተጽዕኖ ፈጣሪነትና ተጠቃሚነት ወደ ኋላ ያስቀረንበትን አካሔድ በማረም መሪነትንና ቀድሞ መገኘትን ማጎልበት ይኖርብናል፤” “የአሁኑ ሥልጠና በዐይነቱ ልዩና ሠራተኛውን ያነቃቃ ነው፤ ጠቅላይ ጽ/ቤቱን ያስመሰግናል፤ ቀጣዩም ኹሉም በየድርሻውና በሚመጥነው ደረጃ የሚሠለጥንበት ቢኾን፤” *** ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ለውጥና ዕድገት፣ የቤተ ክርስቲያንን ስም አስጠብቆ በአንድነት፣ በፍቅርና በመከባበር ሓላፊነትን መወጣት እንደሚያስፈልግ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ አሳሰቡ፡፡ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና የድርጅት ሓላፊዎችና ሠራተኞች፣ ከየካቲት 4 ጀምሮ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ አዳራሽ ሲካሔድ የቆየው የሦስት ቀናት ሥልጠና ትላንት ከቀትር በኋላ ሲጠናቀቅ፥ ከውሸት፣ አሉባልታና መወነጃጀል ተጠብቆ የድርሻን መወጣት፣ በመሪ ዕቅድ ለታገዘው የቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ለውጥ ወሳኝ እንደኾነ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቁልቢ ቅ/ገብርኤልን ለዓመታት የመዘበሩት ዓምባገነኑ አስተዳዳሪ ተነሡ፤ የናዝሬቱ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለ ሃይማኖት ወልዱ ተተኩ

በጡረታ የተገለሉት አማሳኙ አስተዳዳሪ፣ ለ27 ዓመታት የገዳሙን ወርኀዊ ገቢ ከሌሎች ሓላፊዎች ጋራ ለምዝበራና ብክነት በመዳረግ ራሳቸውን አበልጽገዋል፤ ከ4 ተወዳዳሪዎች በብልጫ የተመረጡት ተተኪው አስተዳዳሪ፣ በየዓመቱ እየጨመረ ያለውን የክብረ በዓል ገቢ ከምዝበራና ብክነት እንደሚጠብቁ ታምኖባቸዋል፤ በተመሰከረለት ትምህርታቸውና ሞያቸውም፣ የማኅበረሰብ ልማትና ረድኤት ተልእኮውን የሚወጣ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል እንደሚያደርጉት ተስፋ ተጥሎባቸዋል፤ ስብከተ ወንጌሉ በመዳከሙና እና የሰንበት ት/ቤቱ ባለመጠናከሩ፣ የአካባቢው ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ለተለያዩ ሱሶች እና ለቅሠጣ ተጋልጠዋል፤ በኹለቱ ዓመታዊ ክብረ በዓላት በስእለት የሚገባው ጥሬ ገንዝብና ንዋያተ ቅድሳት፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ግንባር ቀደም የበጀት ምንጭ ኾኖ ይገኛል፤ ለአብነት መምህራን፣ ለመንፈሳውያን ኮሌጆች፣ ለሰባክያነ ወንጌል፣ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች ደመወዝ ይከፈልበታል፤ ድንገተኛ ወጪዎችን ይሸፍናል፤ የቁልቢ ከተማ አስተዳደርና የዙሪያው አብያተ ክርስቲያንም፣ከወርኀዊ ገቢው የመሠረተ ልማት ችግሮችን የሚፈታ ድጋፍና ድጎማ ለማግኘት(ልዩ ጥቅም እንዲከበር) ሲጠይቁ ቆይተዋል፤ *** ላለፉት 27 ዓመታት የርእሰ አድባራት ደብረ ኀይል ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን በምዝበራና ብልሹ አሠራር ሲበድሉት የኖሩት መልአከ ኀይል አባ ወልደ ጊዮርጊስ ከአስተዳዳሪነት ሓላፊነታቸው በጡረታ የተገለሉ ሲኾን፣ በምትካቸው፣
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቁልቢ ቅ/ገብርኤልን ለዓመታት የመዘበሩት ዓምባገነኑ አስተዳዳሪ ተነሡ፤ የናዝሬቱ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለ ሃይማኖት ወልዱ ተተኩ

በጡረታ የተገለሉት አማሳኙ አስተዳዳሪ፣ ለ27 ዓመታት የገዳሙን ወርኀዊ ገቢ ከሌሎች ሓላፊዎች ጋራ ለምዝበራና ብክነት በመዳረግ ራሳቸውን አበልጽገዋል፤ ከ4 ተወዳዳሪዎች በብልጫ የተመረጡት ተተኪው አስተዳዳሪ፣ በየዓመቱ እየጨመረ ያለውን የክብረ በዓል ገቢ ከምዝበራና ብክነት እንደሚጠብቁ ታምኖባቸዋል፤ በተመሰከረለት ትምህርታቸውና ሞያቸውም፣ የማኅበረሰብ ልማትና ረድኤት ተልእኮውን የሚወጣ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል እንደሚያደርጉት ተስፋ ተጥሎባቸዋል፤ ስብከተ ወንጌሉ በመዳከሙና እና የሰንበት ት/ቤቱ ባለመጠናከሩ፣ የአካባቢው ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ለተለያዩ ሱሶች እና ለቅሠጣ ተጋልጠዋል፤ በኹለቱ ዓመታዊ ክብረ በዓላት በስእለት የሚገባው ጥሬ ገንዝብና ንዋያተ ቅድሳት፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ግንባር ቀደም የበጀት ምንጭ ኾኖ ይገኛል፤ ለአብነት መምህራን፣ ለመንፈሳውያን ኮሌጆች፣ ለሰባክያነ ወንጌል፣ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች ደመወዝ ይከፈልበታል፤ ድንገተኛ ወጪዎችን ይሸፍናል፤ የቁልቢ ከተማ አስተዳደርና የዙሪያው አብያተ ክርስቲያንም፣ከወርኀዊ ገቢው የመሠረተ ልማት ችግሮችን የሚፈታ ድጋፍና ድጎማ ለማግኘት(ልዩ ጥቅም እንዲከበር) ሲጠይቁ ቆይተዋል፤ *** ላለፉት 27 ዓመታት የርእሰ አድባራት ደብረ ኀይል ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን በምዝበራና ብልሹ አሠራር ሲበድሉት የኖሩት መልአከ ኀይል አባ ወልደ ጊዮርጊስ ከአስተዳዳሪነት ሓላፊነታቸው በጡረታ የተገለሉ ሲኾን፣ በምትካቸው፣
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የድሬዳዋ ሀ/ስብከት: በጅምላ የታሰሩ ወጣቶች በፍትሕና ዕርቅ እንዲፈቱ ጠየቀ፤ በቤተ ክርስቲያን ላይ ቀጣይ የትንኮሳና ጥቃት ስጋቶች እንዳሉት ጠቆመ

የጥምቀትን በዓል ያደመቁ በርካታ ወጣቶች ጭምር ያለጥፋታቸው እየታፈሱ ታስረዋል፤ በታቦታትና በምእመናን ላይ ድንጋይ የወረወሩ ነውጠኞች ያልተለዩበት ጅምላ ርምጃ ነው፤ “ምእመናን፥ ምን አጠፋን፣ ማንንስ ጎዳን በማለት በኀዘንና በልቅሶ ፍትሕ እየጠየቁ ነው፤” ከእምነት አባቶችና ከሀገር ሽምግሌዎች ጋራ፣ በፍትሕና በዕርቅ መንገድ እንዲፈቱ ጠየቀ፤ *** በቤተ ክርስቲያንና በምእመናን ላይ ቀጣይ የትንኮሳና የጥቃት ስጋቶች እንዳሉት ጠቆመ፤ ከጉዳት በፊት ክትትሉ እንዲጠበቅና ጉዳት ሲደርስም ርምጃው ፍትሐዊ እንዲኾን አሳሰበ፤ አስተዳደሩ፣ለአብያተ እምነትና ለማኅበረሰብ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ አመለከተ፤ ድሬዳዋ፣ በእምነትና በትውልድ የማይሸማቀቁባትና የማይሰደዱባት እንድትኾን ተማፀነ፤ *** በድሬዳዋ፣ በቤተ ክርስቲያንና በምእመናንዋ ላይ ቀጣይ የሁከት ፈጣሪዎች ትንኮሳና ጥቃት ስለ መኖሩ ስጋት የገባው የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት፣ አስተዳደሩ ጥበቃ እና ክትትል እንዲያደርግ ለከተማ መስተዳድሩ ያሳሰበ ሲኾን፤ የጥምቀት ክብረ በዓል ማብቂያን ተከትሎ በተከሠተው ሁከትና ብጥብጥ ያለጥፋታቸው በአፈሳ ለታሰሩ ወጣቶች ፍትሕ እንዲሰጥና አጠቃላይም ችግሩም ሰላማዊ በኾነ የዕርቅ መንገድ እንዲፈታ ጠየቀ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉሃን ማትያስ በቀለ፣ “ወቅታዊ በኾኑ ጉዳዮች ላይ ፍትሕ ስለ መጠየቅ”
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በቋሚ ሲኖዶስ የተመደቡት የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሓላፊዎች ዛሬ ከጽ/ቤቱ ሠራተኞች ጋራ ይተዋወቃሉ፤ ትኩረትንና ፈጣን ማስተካከያን የሚሹ ተግባራት ይጠብቋቸዋል

አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ለምደባው ፍላጎት ባለማሳየታቸው በማግባባት ዘግይቷል፤ መልአከ ሕይወት ቀለም ወርቅ ዓለሙ፣ የሰው ኀይል አስተዳደር ሓላፊ ኾነዋል፤ መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነ ብርሃን፣ለሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ሓላፊነት ተመደቡ፤ ያገረሸው ምዝበራና የተጓተቱ ሥራዎች ትኩረትንና ፈጣን ማስተካከያን ይሻሉ፤ *** ቋሚ ሲኖዶስ ባለፈው ሳምንት የመደባቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ እና ሥራ አስኪያጅ፣ ዛሬ ዓርብ፣ የካቲት 1 ቀን ከጽ/ቤቱ ሠራተኞች ጋራ ትውውቅ የሚያደርጉ ሲኾን፣ በተፈጠረው የአስተዳደር ክፍተት ሳቢያ ትኩረትንና ፈጣን ርምጃዎችን የሚሹ በርካታ ጉዳዮች እንደሚጠብቋቸው ተገለጸ፡፡በልዩ ሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ጳጳስ ኾነው የተመደቡት የጉራጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ እና ሥራ አስኪያጁ መ/ር አባ ሞገስ ኀይለ ማርያም፣ ትላንት ተሲዓት በኋላ ከአስተዳደር ጉባኤ አባላት ጋራ ተገናኝተው በምክትል ሥራ አስኪያጁ መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወልደ ሐና አማካይነት የምደባቸው ደብዳቤ ከተነበበ በኋላ፣ ከመላው የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ጋራ የሚካሔደው የዛሬው የትውውቅ መርሐ ግብር መመቻቸቱ ታውቋል፡፡ በንባብ በተሰማው የቋሚ ሲኖዶሱ ደብዳቤ፣ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከትን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ልዩ ሀ/ስብከት አ/አበባ: የመጀመሪያው መነኰስ ሥራ አስኪያጅ መ/ር አባ ሞገስ ኀ/ ማርያም

መምህር አባ ሞገስ ኀይለ ማርያም በድጓ እና ቅዳሴ አስመስክረዋል፤ ቅኔን ተምረዋል፤ በነገረ መለኰት የመጀመሪያ ዲግሪ ከመንፈሳዊ ኮሌጅ በማዕርግ ተመርቀዋል፤ በተለያዩ ጊዜያት የአስተዳደር ሥልጠናዎችን ወስደዋል፤ ከአዲስ አበባ 30 ኪ.ሜ ርቀት በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ወልመራ ወረዳ የሚገኘውን የመናገሻ ዓምባ ማርያም እና የጋራው መድኃኔዓለም የአንድነት ገዳምን፣ ከሐምሌ ወር 2004 ዓ.ም. ጀምሮ በመምህርነት እንዲሁም የኮሎቦ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን በአስተዳዳሪነት እየመሩ ይገኛሉ፤ ቀደም ሲል ገዳሙን በዲቁና እና በቅስና ለኻያ ዓመታት አገልግለዋል፤ ጎን ለጎንም በጸሐፊነት ሠርተዋል፤ ለዚህም የምስጋና ወረቀት አግኝተዋል፤ በብሕትውና እየኖሩ በደብረ ሊባኖስ ገዳም አርዑተ ምንኵስናን ተቀብለዋል፤ ባለአምስት ጉልላቱ የጋራ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ፣ ባለአንድ ደርብ/ፎቅ የገዳሙ ተግባር ቤት እንዲሁም የልማት ሥራዎች ከሥራዎቻቸው በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፤ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ፣ በ1908 ዓ.ም. ያሳነጿት የመናገሻ ዓምባ ማርያም ገዳም 100ኛ የምሥረታ በዓሏን ግንቦት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ያከበረች ስትኾን፣ መ/ር አባ ሞገስ ኀይለ ማርያም 22ኛው አስተዳዳሪ ናቸው፤ በአዳ በርጋ ወረዳ ዱብቲ ቀበሌ ገበሬ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ: በአ/አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ጳጳስ፤ የመናገሻ ቅ/ማርያም አበምኔት አባ ሞገስ ኃ/ማርያም ሥራ አስኪያጅነት ተመደቡ

ብፁዕነታቸው፣ የጉራጌ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ እስከ መጪው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ድረስ እየመሩ ይቆያሉ፤
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቋሚ ሲኖዶስ: ለአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ይመድባል፤ ተቀባይነት የሌለው እንዳይኾን ሊጠነቀቅ ያስፈልጋል!!!

“ለቦታው የሚመጥን ሰው የሚያስገኝ የተሟላ የመመዘኛ መስፈርት አልተዘጋጀም፤”  “አንዱ ለሌላው ሰው እየላከ ሁሉም የእኔ የሚለውን ለማስመደብ እየተሯሯጠ ነው፤” “ከቡድነኝነት ይልቅ መዋቅራዊ መፍትሔ የሚሻው ሀ/ስብከት ገና ብዙ መሥዋዕት እንደሚጠይቅ ያመለክታል፤” *** ቋሚ ሲኖዶስ፣ በዛሬ ዓርብ፣ ጥር 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው እየተነጋገረባቸው ከሚገኙ ዐበይት አጀንዳዎች ቀዳሚው፣ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ለኾነው አዲስ አበባ፥ ጊዜያዊ ረዳት ሊቀ ጳጳስ፣ ሥራ አስኪያጅ እና የሰው ሀብት አስተዳደር ዋና ሓላፊ መመደብ ነው፡፡ በተለይ የሥራ አስኪያጅ እና የሰው ሀብት አስተዳደር ዋና ሓላፊ ምደባዎች፣ አስቀድሞ መመዘኛ መስፈርት በማዘጋጀት የሚከናወን እንጂ በቲፎዞና በወገንተኝነት እንደማይኾን በተወሰነው መሠረት ከተባለው ቀን ቢዘገይም ሲጠበቅ ሰንብቷል፡፡ ዘግይቶም ቢኾን ግና፣ የትምህርት ዝግጅትን፣ አግባብነት ያለው የሥራ ልምድንና ሥነ ምግባርን ያገናዘበ የመመዘኛ መስፈርት ባልወጣበት ኹኔታ ነው ቋሚ ሲኖዶሱ ዛሬ በምደባው ላይ ለመወሰን የተቀመጠው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለዋልታ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት፣ “ከምንም ነጻ የኾነ፣ ገለልተኛ የኾነ፣ ንክኪ የሌለው፣ ጥሩ ማስተዳደር
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቋሚ ሲኖዶስ: በተሐድሶ ኑፋቄ የተጠረጠሩትን አቡነ ያዕቆብን ከአትላንታ አብያተ ክርስቲያን አገደ! “ከሲኖዶሳዊ አንድነት ወደ ሲኖዶሳዊ ማጥራት?!”

  የግዛቲቱ ካህናትና ምእመናን፣ከጥቅምቱ ምደባ በፊትና በኋላ አቤቱታ ሲያሰሙ ቆይተዋል፤ እመቤታችንን ከሚነቅፉና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ከሚጥሱ ጋራ ግዴለሽና ተባባሪ ኾነዋል፤ በቅዳሴ መካከል የጳጳሱንና የደጋፊዎቻቸውን ጭፈራ የሚያሳይ ቪዲዮ በማስረጃነት ተካቷል፤ ከደጋፊቻቸው ጋራ ምእመኑን እየከፋፈሉ ባነፀው ቤተ ክርስቲያን እንዳይገለገል አውከውታል፤ *** ችግሩ ከአትላንታ ጆርጂያ አልፎ በአምስት ግዛቶች አብያተ ክርስቲያንም ዘንድ ተስፋፍቷል፤ ቅደስ ሲኖዶስ፣ በእውነት የሚጠብቅ ርቱዕ አባት እንዲመድብ ካህናቱና ምእመናኑ ጠይቀዋል፤ በአ/አበባ የሚገኙት ሊቀ ጳጳሱ፣“በአንድ ወገን አቤቱታ የተላለፈ ነው፤” በሚል ተቃውመዋል፤ በኑፋቄው አራማጅነት የሚጠረጠሩ ሌሎች ጳጳሳትም ጉዳይ ክትትልና እርምት ያስፈልገዋል፤ *** በሰሜን አሜሪካ የጆርጂያ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ የእምነት አቋማቸውን በተመለከተ ከካህናትና ምእመናን በተደጋጋሚ በቀረበባቸው አቤቱታ፣ ከአትላንታ ጆርጂያ ግዛት ከሚገኙ አድባራት እስከ መጪው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ድረስ ታግደው እንዲቆዩ ቋሚ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ፣ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ የአትላንታ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ቦርድ አገልጋይ ካህናት እና ማኅበረ ምእመናን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የባሕረ ጥምቀት ይዞታዎቻችን በልማት ሰበብ እየተሸራረፉና እየተጣበቡ ነው፤ በበዓሉ ትውፊት፣ ማኅበራዊ ሚና እና በቱሪዝሙ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ይታሰብበት!

ከበዓል ማክበር ባለፈ የቤተ ክርስቲያን ልማትን የማይፈቅዱ የመንግሥት አካላት አሉ፤ የቤተ ክርስቲያን አመራር፣ በጥቃቅን ሥራ እየተጠመደ መብቷን ሊያስከብር አልቻለም፤ በዘላቂነትም መንቀሳቀስ እንጂ ለበዓል ማጽዳት፣ማስዋብና መጠቀም ብቻ በቂ አይደለም፤ ቤተ ክርስቲያን በቋሚ ይዞታነት ልትረከባቸው፣ልትጠብቃቸውና ልትከባከባቸው ይገባል፤ አካባቢን ያገናዘበ የማስዋብና የመጠበቅ ሥራ ለመሥራት ዝግጁነቷን ማሳየት አለባት፤ በዓሉን የሚያደምቀው የምእመኑና የወጣቱ ተነሣሽነት በይዞታ ማስከበሩም ይጠናከር፤ *** ጃንሜዳ፣ በየአቅጣጫው ሊባል በሚችል መልኩ ልዩ ልዩ ግንባታዎች እየተካሔዱበት ነው፤ የቅጽሩ መግቢያ ግራና ቀኝ፣ በኮንስትራክሽን ዕቃ ማከማቻነት በከፍተኛ ኹኔታ ተጣቧል፤ የዘጋው እንዲከፍት፣ ቤተ ክርስቲያን፣ በጽሑፍ ፈቃድ ለመጠየቅና ለመለመን ተገዳለች፤ በባሕረ ጥምቀቱ አካባቢ፣የራስዋን እንቅስቃሴ እንዳታደርግ ማዕቀብ የተጣለ ይመስላል፤ ይዞታን ማስከበር፣ሌሎቹን ለማስጠበቅና ጥምቀትንም በቅርስነት ለማስመዝገብ ያግዛል፤ የስፖርት ማዘውተሪያነቱን ያገናዘበ የመዋኛ፣ ጂምናዝየም፣ አዳራሽ ግንባታ ይታቀድ፤ *** ሊቀ ትጉሃን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ (የጠቅላይ ጽ/ቤት ዕቅድና ልማት መምሪያ ዋና ሓላፊ) … የጥምቀት በዓል ለዘመናት ሲከበርባቸው የኖሩ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የተቀደሱ ቦታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚጨምረው የሕዝበ ክርስቲያን ቁጥር ልክ እየሰፉና እየተዋቡ መሔድ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ፓትርያርኩ የበዓለ ጥምቀት ጉብኝታቸውን አቋርጠው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ፤ “በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት እንዲያከብሩ ኹኔታው ተመቻችቷል፤”

ፕሮቶኮሉ፣ ከሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ጋራ የፈጠሩት አለመግባባት በምክንያት ተጠቅሷል፤ የመስተንግዶ ወጪ ጫና በመነሻነት ቢጠቀስም፣ ጉዞው ከጅምሩ በአግባቡ የታቀደ አልነበረም፤ ከጥር 5 እስከ 14 ታቅዶ የተሰናከለው ጉዞ፥ የሰላም፣ የበረከትና የገጽታ ግንባታ ይዘት ነበረው፤ በግለሰቦች የሚወሰኑ የፓትርያርኩን ጉዳዮች በተቋማዊነት የማሻሻል አስፈላጊነትን አሳይቷል፤ የቅዱስነታቸውን የፕሮቶኮል ጉዳዮች፣ በሞያተኛ ሓላፊ መምራቱም ሊታሰብበት ይገባል፤     *** ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ፣ ራብዓይ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ በዓለ ጥምቀትን በጎንደር ከተማ ለማክበር ዐቅደው ካለፈው ቅዳሜ ማለዳ አንሥቶ ማካሔድ የጀመሩት ጉብኝት ተቋርጦ ትላንት ማምሻውን በድንገት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጉ ተገለጸ፡፡ ለጉብኝቱ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት፣ ቅዱስነታቸው ከ5 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ በመኾን ቅዳሜ፣ ጥር 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ማለዳ ጎንደር ደርሰው በጎንደር፣ ባሕር ዳር እና ደብረ ታቦር ከተሞች በካህናት፣ ሊቃውንት፣ ምእመናንና ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል ቢደረግላቸውም፣ የጉብኝታቸው ዋና ዕቅድ በኾነው የጎንደር ከተማ የበዓለ ጥምቀት አከባበር ላይ ሳይገኙ ትላንት ኀሙስ፣ ጥር 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ምሽት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቋሚ ሲኖዶስ: የኢየሩሳሌም ገዳማትን በሚያውኩ ‘መነኰሳት’ ላይ የተወሰደውን ርምጃ የሚያጣሩ ልኡካን ላከ

በሁከት ፈጣሪነት በተሰናበቱ አራት መነኰሳት ላይ የተወሰደውን ርምጃ ያጣራል፤ የተባረሩት መነኰሳት ውሳኔውን በመቃወም ለቅ/ፓትርያርኩ አቤቱታ አቅርበዋል፤ “በፖለቲከኞች ምክርና በሊቀ ጳጳሱ ወገንተኝነት የተላለፈ ውሳኔ ነው፤”/የተባረሩት/ “ከኮፕቶች ፈተና ለይተን በማናየው ዐመፀኝነት ገጽታችንን አበላሽተዋል፤”/ገዳሙ/ *** በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትን በአድማና ፀብ እያወኩ ሊቀ ጳጳሱንና አበው መነኰሳትን በመደብደብ ጉዳት ባደረሱ አራት መነኰሳት ላይ የተወሰደውን ከአገልግሎትና ከአባልነት የማሰናበት ርምጃ የሚመረምር የቋሚ ሲኖዶስ ልኡክ ዛሬ ማምሻውን ወደዚያው ያመራል፡፡ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ረዳት ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ዋና ሓላፊ መልአከ ብርሃናት አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎሬዎስ በአባልነት የሚገኙበት የቋሚ ሲኖዶሱ አጣሪ ልኡክ፣ የገዳሙን ውሳኔና አራቱ መነኰሳት ያቀረቡትን አቤቱታ በጋራ በመመርመር ለማኅበሩ አንድነትና ለገዳማቱ አገልግሎት መቃናት የሚበጅ ዘላቂ መፍትሔ ያስገኛሉ ተብሎ እንደሚታመን ተጠቁሟል፡፡ ባለፈው ታኅሣሥ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ቄሰ ገበዝ ለመምረጥ በተደረገው የገዳማቱ አጠቃላይ ስብሰባ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የአኵስም ጉብኝት መስተጓጎል: የመንግሥት አመቻች አካልና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በየበኩላቸው የሰጡት ምላሽ

“ተጠያቂው የትግራይ ክልል ሳይኾን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፤ከዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ጀምሮ ጉብኝቱን ለማመቻቸት ክልሉ ፈቃደኛና ዝግጁ ነው፤ አኵስሞችም ቅዱስነታቸው ከውጭ ከተመለሱ ጀምሮ ኮሚቴ አቋቁመውና ጥሪ አቅርበው ጉብኝታቸውን ሲጠባበቁ ነበር፤”/የጉብኝቱ አመቻች መንግሥታዊ አካላት/ “የጎንደሩን ጉብኝት ያመቻቹት የቅዱስነታቸው ቤተሰቦች ናቸው፤ በቤተሰቦቻቸው እጅ ነው ያሉት፤ የአየር ትኬት እገዛለሁ፤ አበል እከፍላለሁ፤ትራንስፖርት አመቻቻለሁ፤ የእኔ ድርሻ ይህ ነው፤ ለአኵስሙ ጉዞ ግን ሓላፊነት ወስዶ ደብዳቤ ጽፎ ያመጣልኝ ማንም የለም፤” /ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ/ “ፓትርያርክ እኮ ተቋምም ነው፤ ክፍተቱ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ለፓትርያርክ በሚገባ ደረጃ ካለመቀበል የሚመነጭ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የትኩረት ማነስ ነው፤ የሚሌኒየም አዳራሹ የድጋፍ አቀባበል ጊዜ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እንኳ፣ ወጪው ተጠንቶ ይቅረብልንና እንወስን፤ ሲሉ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ግን፣ ተገቢ በጀት ባለመመደብ ንፉግነቱን ከአቀባበላቸው ቀን ጀምሮ በግልጽ አሳይቷል፤ በተለያየ መልክ የቀጠለውም ይኸው የትኩረት ማነስ ነው፤” /አስተያየት ሰጭዎች/ “ቅዱስነታቸው ፕትርክና እንደተሾሙ አኵስም ሔደው በጸሎታችሁ አስቡኝ ብለው መባ ሰጥተዋል፤የአኵስም ጽዮን ካህናትም
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጥምቀትን በጎንደር ያከብራሉ

ከስደት መልስ ከአዲስ አበባ ውጭ የመጀመሪያ ጉብኝታቸው ነው፤ ጉብኝታቸውን ከአኵስም ለመጀመር የተያዘው ዕቅድ አልተሳካም፤ *** ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ከ26 ዓመታት ስደት ወደ ሀገር ከተመለሱ በኋላ ከአዲስ አበባ ውጭ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በጎንደር የሚጀምሩ ሲኾን፣ በዓለ ጥምቀትንም በዚያው ያከብራሉ፡፡ ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ፥ ከብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እና በጠቅላይ ጽ/ቤት የገዳማት አስተዳደር የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ጋራ በመኾን ወደ ጎንደር አቅንተዋል፡፡ እስከ ጥር 13 ቀን ድረስ በሚዘልቀው በዚሁ አባታዊ ጉብኝታቸው ጎንደርን ጨምሮ በባሕር ዳር እና በደብረ ታቦር ከተሞች እየተዘዋወሩ ቡራኬ የሚሰጡበት መርሐ ግብር እንደተያዘላቸው ታውቋል፡፡ ከአቀባበል መርሐ ግብር ጀምሮ የስብከተ ወንጌል እና የሰላም ተልእኮ ያለው ጉዞ እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡ የጉብኝት መርሐ ግብሩን ከአኵስም በመጀመር ለማካሔድ ታቅዶ ለሚመለከታቸው የክልሉ አካላት በጽሑፍ ጥያቄ በማቅረብ የተለያዩ ሙከራዎች ተደርጎ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ኾኖም፣ በፓትርያርክ ደረጃ የሚመጥንና የሚገባቸውን ዝግጅት አድርጎ ለመቀበልና ለማስተናገድ ምንም ዓይነት ምላሽ ባለመሰጠቱ፣
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ደቀ መዛሙርት በአስተዳደሩ ላይ ያቀረቡት ጥያቄና ቋሚ ሲኖዶሱ አጽድቆ ርምጃ የወሰደበት የአጣሪ ልኡካን ሪፖርት ሙሉ ቃል

የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳሱን ከፈራሚነት ከማግለል አንሥቶ በ9 የዩኒቨርሲቲው ሓላፊዎችና ሠራተኞች ላይ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ የተላለፈው ከቦታቸው የማንሣትና የማስተካከል ውሳኔ፣ ከዛሬ ጀምሮ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ወጪ እየኾነ እንዲደርሳቸው እየተደረገ ነው፤ ደቀ መዛሙርቱ፥ውሳኔው ተፈጻሚ እስኪኾንና በጊዜያዊነት ከተመደቡት ሓላፊዎች ጋራ በቀጣይ ኹኔታ ላይ ግልጽ ውይይት እስክናደርግ ድረስ ወደ ትምህርት አንመለስም፤ ብለዋል፤ ከአቋረጡ ወር አልፏቸዋል፤ በጸሎት ቤቱ እንዳይገለገሉ ታግደው በሜዳ ላይ እየጸለዩ ነው፤ ካናዳ ከሚገኙትና በቅርቡ ወደ አገር ቤት ከሚመለሱት ጊዜያዊ ዋና ዲን ቀሲስ ዶ/ር መብራህቱ ኪሮስ ጋራ እየመከሩ ነው፤ “ያለውን ችግር እንረዳለን፤ ግቢውን በጋራ እናስተካክላለን፤ አብረን እንሠራለን፤” ብለዋቸዋል፤ *** በገንዘብ ብክነትና ምዝበራ፣ በአካዳሚያዊ ነፃነት አፈናና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ በዕቅበተ እምነት ድክመትና የተቋሙን አጠቃላይ የመማር ማስተማር ተልእኮ የማዛባት አስተዳደራዊ ብልሽት ማጣራት በተካሔደባቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ 9 ሓላፊዎችና ሠራተኞች ላይ ቋሚ ሲኖዶስ፣ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ከፍተኛ የማጽዳትና የእርምት ውሳኔ አሳልፏል፤ በምትካቸው ኹለት ዲኖችን(ዋና ዲንና የአስተዳደር ምክትል ዲን) በጊዜያዊነት መድቧል፤ በሌሎቹም ቦታዎች ላይ በቂ የትምህርት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የአ/አበባ ሀ/ስብከት ምደባ: በመስፈርት እንጂ በቲፎዞ እንደማይኾን ቋሚ ሲኖዶስ ገለጸ፤ “አስነዋሪ ነው፤ በግለሰቦች ጥቆማና ፍላጎት የሚኾን አይደለም፤”/ብፁዓን አባቶች/

ማኅበረ ካህናት ነን ባዮች፣ “እነእገሌ ይኹኑልን” በማለት ለቋሚ ሲኖዶስ አባላት እና ለመንግሥት አካላት ወረቀት አሠራጭተዋል፤ “ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነን ለሥራ አስኪያጅነት አቅርበዋል፤ ለሰው ሀብት አስተዳደር፣ ለሒሳብ እና በጀት፣ ለካህናት አስተዳደርም ደልድለዋል፤” “ጫፍ ወጥተው ነው እየሔዱ ያሉት፤ ሊቀ ጳጳስ ሳይቀር መድበዋል፤ ቀልድ ነው፤ ተቀባይነት የለውም፤ መስፈርት አውጥተን ነው የምንሔድበት፤” /የቋሚ ሲኖዶስ አባላት/ የሥራ አስኪያጅ እና የሰው ሀብት አስተዳደር፣ የትምህርት ዝግጅትን ያህል ሀገረ ስብከቱን ከላይ እስከ ታች የማወቅ ከፍተኛ የሥራ ልምድንና ሥነ ምግባርን ይጠይቃል፤ “ታቹንም ላዩንም የሚያውቅ ያስፈልጋል፤ ችግሩ እኮ ከላይ ተወርውሮ እየመጣ ነው፤ አትከርምም፤ የምትይዘውን ይዘህ ሒድ፤ የሚል መካሪ ይገባበትና ነጣጥቆ ይሔዳል፤” /አስተያየት ሰጭዎች/         *** የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ አስኪያጅ እና የሰው ሀብት አስተዳደር ምደባ፣ ተገቢው መስፈርት ከወጣ በኋላ ቋሚ ሲኖዶስ ተነጋግሮበት የሚወስነው እንጂ፣ እንደ ቀደሙ በግለሰቦችና ቡድነኝነት ግፊቶችና ፍላጎት እንደማይኾን ብፁዓን አባቶች ተናገሩ፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ በዛሬው ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው ምደባዎቹን እንደሚያካሒድ ቢጠበቅም፣ እንደ አጀንዳ እንዳልቀረበና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የአ/አበባ ሀ/ስብከት ምደባ: በመስፈርት እንጂ በቲፎዞ እንደማይኾን ቋሚ ሲኖዶስ ገለጸ፤ “አስነዋሪ ነው፤ በግለሰቦች ጥቆማና ፍላጎት የሚኾን አይደለም፤”/ብፁዓን አባቶች/

ማኅበረ ካህናት ነን ባዮች፣ “እነእገሌ ይኹኑልን” በማለት ለቋሚ ሲኖዶስ አባላት እና ለመንግሥት አካላት ወረቀት አሠራጭተዋል፤ “ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነን ለሥራ አስኪያጅነት አቅርበዋል፤ ለሰው ሀብት አስተዳደር፣ ለሒሳብ እና በጀት፣ ለካህናት አስተዳደርም ደልድለዋል፤” “ጫፍ ወጥተው ነው እየሔዱ ያሉት፤ ሊቀ ጳጳስ ሳይቀር መድበዋል፤ ቀልድ ነው፤ ተቀባይነት የለውም፤ መስፈርት አውጥተን ነው የምንሔድበት፤” /የቋሚ ሲኖዶስ አባላት/ የሥራ አስኪያጅ እና የሰው ሀብት አስተዳደር፣ የትምህርት ዝግጅትን ያህል ሀገረ ስብከቱን ከላይ እስከ ታች የማወቅ ከፍተኛ የሥራ ልምድንና ሥነ ምግባርን ይጠይቃል፤ “ታቹንም ላዩንም የሚያውቅ ያስፈልጋል፤ ችግሩ እኮ ከላይ ተወርውሮ እየመጣ ነው፤ አትከርምም፤ የምትይዘውን ይዘህ ሒድ፤ የሚል መካሪ ይገባበትና ነጣጥቆ ይሔዳል፤” /አስተያየት ሰጭዎች/         *** የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ አስኪያጅ እና የሰው ሀብት አስተዳደር ምደባ፣ ተገቢው መስፈርት ከወጣ በኋላ ቋሚ ሲኖዶስ ተነጋግሮበት የሚወስነው እንጂ፣ እንደ ቀደሙ በግለሰቦችና ቡድነኝነት ግፊቶችና ፍላጎት እንደማይኾን ብፁዓን አባቶች ተናገሩ፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ በዛሬው ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው ምደባዎቹን እንደሚያካሒድ ቢጠበቅም፣ እንደ አጀንዳ እንዳልቀረበና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለአ/አበባ ሀ/ስብከት: ሥራ አስኪያጅ እና የሰው ኃይል አስተዳደር ሓላፊ ሊኾን የሚገባው ማን ነው? የሹመቱ ውትወታና ፍጥጫ

የትምህርት ዝግጅቱ የሥራ/የአገልግሎት ልምዱ ሓላፊነቱና ተግባሩ *** ለሥራ አስኪያጅነት፡- የሰዓሊተ ምሕረት ቅ/ማርያም ካቴድራል አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ክብሩ ገብረ ጻድቅ እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ መ/ር አባ ገብረ ሥላሴ በላይ ስማቸው በጒልሕ እየተነሣ ነው፤ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ሓላፊዎች በአንድ በኩል፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሓላፊዎች በሌላ በኩል በድጋፍና በተቃውሞ ውትወታ እና ፀረ ውትወታ ተፋጠዋል፤ *** ሰራቂነትንና መዝባሪነትን የዕለት ግብራቸው ባደረጉ አንቃዦች ዘይቤ፣ “ብር ላይ መቀመጥ ነው” የሚባልለት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምደባ/ሹመት፣ ቆይታው እንደ አነጋገሩ የተመቸ አይደለም፡፡ በሀገረ ስብከቱ መዋቅሮች አንዳችም የሠራተኝነት ታሪክ የሌላቸው ይቅሩና ከደርዘን በላይ ዓመታት ያስቆጠሩቱ ቢመደቡትም፣ ብዙም ሳይቆዩ የዘረፋ ቅሌታቸውን ተከናንበው፣ ችጋራቸውን አራግፈውና ለብዙ ብክነት ዳርገው በውርደት ከመወገድ በቀር የፈየዱለት ነገር አልነበረም፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዐቃዲው ደንብ መሠረት፣ ሀገረ ስብከቱ አገልግሎቱን የሚያከናውንበት ልዩ መተዳደር ደንብ የሌለው መኾኑ፤እንደሌሎች አህጉረ ስብከት ራሱን ችሎ በሊቀ ጳጳስ አለመመራቱና “ልዩ ሀገረ ስብከት” በሚል ፈሊጥ በቅርበት ሊከታተሉትና ሊቆጣጠሩት በማይችሉት ፓትርያርኩ በጎ ፈቃድ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በልደተ ክርስቶስ: በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ፍጹም ሰላም ተበሠረ፤ በሰውና በሰው መካከል ያለው ሰላም ግን እክል እያጋጠመው ነው፤ መወያየትና አንድነታችንን መጠበቅ ይገባናል-ቅ/ፓትርያርኩ

የሰላም ጸጋ፣ አምላካዊ ሀብት ቢኾንም፣ በአግባቡ ካልተያዘ በሰዎች ድርጊት ሊወሰድ እንደሚችል ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዳሉ፤ እኛም በተጨባጭ የምናየው ሐቅ ነው፤ የሀገራችን ሰላም ፈተና እያጋጠመው ያለው፣ በፖሊቲካ ኃይሎች ሽኩቻና አንዱ አንዱን ጥሎ ለማለፍ የሚደረገው ቅድድሞሽ ያስከተለው ችግር እንደኾነ አሌ የማይባል ሐቅ ነው፤ ሁሉም የፖሊቲካ ኀይሎች ሰፊ የውይይት መድረክ በመክፈት በሀገር አንድነትና በሰላም መጠበቅ፣ በዜጎች እኩልነትና ሰብአዊ መብት መከበር የጋራ አቋም በመያዝ ሰላምን ሊያረጋግጡ ይገባል፤ ሕዝቡ በአጠቃላይ በተለይም ወጣቱ ትውልድ፣ ተረጋግቶና ሰከን ብሎ በማሰብ ለሀገር አንድነት፣ ለሰላም መጠበቅና ለሰው ልጆች መብት መከበር በአንድነት እንዲተጋ በአጽንዖት እንመክራለን፤ መንግሥት ሁሉንም የፖለቲካ ኀይሎች በማሳተፍና በማወያየት፣ የሀገሪቱን ሰላምና አንድነትን እንዲያረጋግጥ፣ የዜጎችን ደኅንነትና ሰላም በመጠበቅ የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብር እናሳስባለን፤ *** መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ በሕመም ምክንያት በየጠበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ የሕግ ታራሚዎች ኾናችሁ በየማረሚያ ቤቱ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቋሚ ሲኖዶስ: የቅ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲን ሊቀ ጳጳስ ከፈራሚነት አገለለ፤ 5 ሓላፊዎችን አነሣ፤ ዋና ዲን እንዲሾም ወሰነ፤ የኑፋቄ ተጠርጣሪዎቹን ‘መምህርና ደቀ መዝሙር’ አገደ!

ዋናው ዲን በውድድር እስኪቀጠር፣ቀሲስ ዶ/ር መብራህቱ ኪሮስ በጊዜያዊነት ተመደቡ፤ አረጋዊውን የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስን ከፈራሚነት አገለለ፤ አካዳሚክ ዲኑ መ/ር ግርማ ባቱ፣ አስተዳደር ም/ል ዲኑ ሰሎሞን ኀይለ ማርያም፣ የቤተ መጻሕፍቱ ሓላፊ ብርሃኔ ገብረ ጻድቃን፣ ሬጅስትራሩ እና ጠቅላላ አገልግሎቱ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ወሰነ፤ በተነሡት ም/ል አስተዳደር ዲን ቦታ፣ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የልማትና ዕቅድ ዋና ክፍል ሓላፊው መ/ር ፍርድአወቅ ዓለማየሁ ተተክተዋል፤ በተለያዩ ድርጅቶች በፕሮጀክት ባለሞያነትና ዳይሬክተርነት ሠርተዋል፤ በቴዎሎጂ፣ በሳይኮሎጂና በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው፤ በንግድ አስተዳደር 2ኛ ዲግሪያቸውን በአ.አ.ዩ. እየተከታተሉ ነው፤ ከሊቀ ጳጳሱ ጸሐፊ ጋራ በመኾን የተማሪዎችን ዶርሚተሪ ለነጋዴ ያከራዩትና ሠራተኛውን ከመከታተል ይልቅ በሕንጻ ቁጥጥር የተጠመዱት ፐርሶኔሉ፣ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ይጻፍባቸዋል፤ ከቅጥራቸው ጀምሮ በኮሌጁ የሒሳብ ሥራ ላይ ከፍተኛ አለመተማመንና ክፍተት ፈጥረዋል የተባሉት የሒሳብ ባለሞያዋ እንዲነሡ ወስኗል፤               *** “ኢየሱስ ያማልዳል” ባዩ መምህር ጌታቸው ተረፈ፣ ከማስተማር ሥራው ታግዶ በሊቃውንት ጉባኤ ይመረመራል፤ በኑፋቄው ከዩኒቨርሲቲው ሲባረር ወደ መቐለ ቅዱስ ፍሬምናጦስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቋሚ ሲኖዶስ: ከልደት በዓል በኋላ የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅን ይመድባል

ሓላፊዎቹ ተመድበው አሠራሩ እስቲቃና ቅጥርና ዝውውር እንዳይፈጸም አገደ፤ ከ13 በላይ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎችን፣ ዝውውር አጸድቋል፤ ለደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት፣ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ተክለ ጊዮርጊስ ተመደቡ፤ *** ቋሚ ሲኖዶስ፣ ትላንት ከቦታቸው የተነሡትን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሦስት ሓላፊዎች የሚተኩ የፓትርያርኩ ረዳት ጳጳስ፣ ሥራ አስኪያጅ እና የሰው ኃይል አስተዳደር ሓላፊ፣ ከልደት በዓል በኋላ፣ በቀጣዩ ሳምንት ረቡዕ፣ ጥር 3 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚመድብ የተገለጸ ሲኾን፣ ሓላፊዎቹ ተመድበው መዋቅሩ፣ አደረጃጀቱና አሠራሩ እስቲቃና ድረስ ዋነኛ የጉቦ ምንጭ የኾነው የሠራተኛ ቅጥርና ዝውውር እንዳይፈጸም አግዷል፤ ምክትል ሥራ አስኪያጁ መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወልደ ሐና፣ ኹኔታውን በንቃት እየተከታተሉ እንዲቆዩ ታዘዋል፡፡ቋሚ ሲኖዶሱ ዛሬ ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሔደው ስብሰባው፣ ትላንት ከሓላፊነታቸው የተነሡት በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ጳጳሰ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ባላቸው የውጭ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ሓላፊነት ተወስነው እንዲሠሩ፣ መምህር ይቅርባይ እንዳለ እና መጋቤ ጥበባት ሲያምር ተክለ ማርያም ደግሞ ወደ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ተመልሰው እንዲመደቡ ወስኗል፡፡ በሌላ በኩል፣
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቋሚ ሲኖዶስ: በአ/አበባ የፓትርያርኩ ረዳት ጳጳስንና ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ 3 ሓላፊዎችን አነሣ፤ በሒሳብና በጀት ሓላፊውና በኮሌጁ ጉዳይ እየተነጋገረ ነው

  ብልሹ አሠራርንና ምዝበራ እንዲያስወግዱና ሀገረ ስብከቱን አረጋግተው እንዲመሩ የተሰጣቸውን ሓላፊነት መወጣት አልቻሉም ያላቸውን፦ ረዳቱ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ ሥራ አስኪያጁ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ እና የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ሓላፊው መጋቤ ጥበባት ሲያምር ተክለ ማርያም እንዲነሡ ወስኗል፡፡ *** ለመንበረ ፓትርያርኩ እና ለመንግሥት ለሳምንታት አቤቱታ ሲቀርብ ቆይቷል፤ ያለቋሚ ሲኖዶሱ ዕውቅና የተደረገው ሕገ ወጥ የአስተዳዳሪዎች ዝውውር ታግዷል፤ የብቃት እና የእምነት አቋም ጥያቄ የተነሣበት የግርማይ ሓዱሽ ምደባ እየታየ ነው፤ የታገደው ኤልያስ ተጫነ፣ ለ4ኛ ጊዜ እንዲመለስ ተወስኗል፤ መባሉ እያነጋገረ ነው፤ አዲስ አበባን፣ የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት ድንጋጌ ዋነኛ ችግር መኾኑ ታምኖበታል፤ ዛሬ ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 23/2011 ዓ.ም ሲያካሒድ የዋለውን ስብሰባ ነገም ይቀጥላል፤ አሁንም፤ ከሓላፊዎች “ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ” ምደባ ይልቅ፣ ለመዋቅር፣ አደረጃጀትና አሠራር ለውጡ ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል!!! ***
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የጽጌ ከበረን የገርጂ ጊዮርጊስ ዝርፊያ ያረጋገጠው ሪፖርት ሙሉ ቃል፤ መዝባሪ የሚሾምበት፣ ምዝበራን ያጋለጠ የሚንገላታበት የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት-አ/አበባ ውድቀት እና ውድቀት!!!

ከደረጃ ዝቅ ብሎ እንዲመደብና በሕግም እንዲጠየቅ ልኡኩ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ የውሳኔ ሐሳብ ቢያቀርብም፣ በዚያው በእልቅናው ወደ ደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ተዛውሯል፤ ዛሬ ቅዳሜ፣ ወደ ደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ለመግባት ቢቋምጥም፣ በፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ አቋም ከሚታወቁት ምእመናን ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚገጥመው ይጠበቃል፤ ማጣራቱ እንዲካሔድ ያዘዘው ቋሚ ሲኖዶስ ሳያውቅና ሳይወስን፣ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት አቅራቢነትና በፓትርያርኩ መመሪያ የተደረገ ሕገ ወጥ ዝውውር ነው፤ ቋሚ ሲኖዶስ፣ በቀጣዩ ሳምንት ስብሰባው፣ በጽጌ ከበረና ሌሎች 4 አለቆች ሕገ ወጥ ዝውውር መነሻ፣ የተጠያቂነት ሥርዐቱን አጠቃላይ ውድቀት በመፈተሽ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፤ *** ባለፈው ነሐሴ ቀርቦ ሳይወሰንበት የቆየው ሪፖርት፥ በአስተዳደር በደል፣ በገንዘብ ብክነት፣ በሥነ ምግባር ችግር፣ በመሬት ሽንሸና እና ወረራ፣ ጽጌ ከበረን በዋና ተጠያቂነት አስቀምጧል፤ የገርጂ ቅ/ጊዮርጊስ ሰበካ ጉባኤ፣ ካህናትና ምእመናን እንዲመረመር የጠየቁት የ7 ዓመት ሒሳብ፥ በጽጌ ከበረ፣ በዋና ጸሐፊውና በሒሳብ ሹሙ እምቢተኝነት እንደተቆለፈበት ነው፤ ጽጌ ከበረ፣ የእልቅና ደረጃው እንደተጠበቀ ያለተጠያቂነት ሲዛወር፣ ከመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ምዝበራውን ሲያጋልጡ የቆዩት የቁጥጥር
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ተጠያቂነትና ሞያዊነት ብርቅ በኾነበት የአ/አበባ ሀ/ስብከት: የገርጂ ጊዮርጊሱ ዘራፊ ጽጌ ከበረ ወደ ደ/አሚን ተ/ሃይማኖት በፓትርያርኩ መመሪያ ተዛወረ፤ የተሐድሶው ቃል አቀባይ ግርማይ ሓዲስ የሀ/ስብከቱ ሒሳብና በጀት ሓላፊ ኾነ

ወደ ቁሉቢ ከተጓዙት ፓትርያርኩ ውጭ ተሰብስበው የመከሩበት የቋሚ ሲኖዶስ አባላት ሊሞግቷቸው ወስነዋል፤ ******** ‘ሊቀ ማእምራን’ ጽጌ ከበረ • 104ሺሕ152 ካሬ ሜትር ይዞታውን በካሬ 7 ብር ከ3 እስከ 9 ዓመት እያከራየ መዝብሯል፤ ለመናፍቃን አሳልፎ ሰጥቷል፤ በርካታ እናቶችንና እኅቶችን ደፍሯል፤ • ወጣቶችና ምእመናን የእርሱንና የግብረ አበሮቹን ቢሮ በይደው ባሸጉበት ዕለት፣ “ሌባ፣ ሌባ” እያሉ ከደብሩ በፖሊስ አጀብ ያባረሩት መዝባሪ፣ ጠንቋይ እና ዘማዊ ነው፤ • በማጣራት በተረጋገጠው ዘራፊነቱና ነውረኛነቱ፣ በሕግ እንዲጠየቅና ከደረጃ ዝቅ ብሎ እንዲመደብ የቀረበው ልኡክ ሪፖርት፣ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ እየጠበቀ ነበር፤ • በዋና ጸሐፊውና ሌሎች 3 ሓላፊዎች ላይ መሰል የውሳኔ ሐሳብ ቢቀርብም ያለአንዳች ርምጃ ሲዛወሩ፣ ዘረፋውን ያጋለጡት ቁጥጥሩ፣ደረጃውን ባልጠበቀ ዝውውር እየተንገላቱ ነው፤ • ቀንደኛው የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎች ደላላ፣ መዓዛ ተክለ ወልድ፣ ከፍተኛ ገንዝብ መድቦ የቅዳሜውን የጽጌ ከበረ አቀባበል እያስተባበረ ነው፤ የሕዝብ ተቃውሞ ያሰጋል፤ • ከቋሚ ሲኖዶሱ ዕውቅና ውጭ ማክሰኞ፣ በፓትርያርኩ መመሪያ ከተዛወሩት ሌሎች አራት አለቆችም፣ ከደረጃ ዝቅ እንዲሉ የተወሰነባቸውና ጉዳያቸው በመታየት ላይ የሚገኙ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ: ወደ ዩኒቨርሲቲ ያደገበት ሒደት ግልጽነት እንደሚጎድለው አጣሪ ልኡኩ ጠቆመ፤ ለደቀ መዛሙርቱ ጥያቄ ባቀረበው መፍትሔ ላይ ቋሚ ሲኖዶስ ነገ ይወስናል

ያለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በፓትርያርኩ ደብዳቤ ብቻ ዩኒቨርሲቲ መባሉ፣ ሕግንና አሠራርን ይጥሳል፤ ከተጨባጩ የኮሌጁ ኹኔታ ጋራም አይጣጣምም፤ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የተቋቋመውና በቋሚ ሲኖዶስ ቃላዊ ይኹንታ የተሰጠው አጣሪ ኮሚቴ፣ በ12 የግንዛቤ ነጥቦችና በ14 የመፍትሔ ሐሳቦች የተቀነበበ ሪፖርቱን አቅርቧል፤ ለኮሌጁ የተጠሪነት ችግር የጠቆመው መፍትሔ የለም፤ አረጋዊውን የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ የሚያግዝ ባለሙሉ ሥልጣን ዋና ዲን ከመሾም ጀምሮ፣ በስግብግብነት መማር ማስተማሩን የበደሉ ጥቅመኛ የአስተዳደር ሓላፊዎች እንደሚወርዱና እንደሚቀጡ ይጠበቃል፤ ባለፉት አራት ዓመታት፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ለኮሌጁ ከሚመድበው ዓመታዊ በጀት ውስጥ፣ በእውን በሌሉ ከ76 ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ስም ሲወጣ የቆየው በጀት የት እንደሚገባ አልታወቀም፤     *** በየዓመቱ የሚመደበው በጀት እየጨመረ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ቢደርስም፣ የኮሌጁ የተማሪ ቅበላ መጠን ግን እየቀነሰ ከመምጣቱም ባሻገር፣“ለሽንኩርት መግዣ እንኳ አይኾንም፤” ተብሏል፤ የደቀ መዛሙርቱ መጸዳጃ ቤት ያለበቂ ምክንያት ተዘግቶ፣ ያለበቂ ጥናት እና ያለጨረታ ከካቴድራሉ አጥር ጋራ ተያይዞ ለተሠራው መጸዳጃ 790 ሺሕ ብር መውጣቱ የብኩንነቱ ማሳያ ኾኗል፤ ከኮሌጁ ቦርድም ኾነ አስተዳደር ጉባኤ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የኢየሩሳሌም ገዳማት አስተዳደር: አራት ዋልጌ የስም መነኰሳትን ከአገልግሎት አገደ፤ ከማኅበሩ ለየ

ውሳኔውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለእስራኤል የሃይማኖት ጉዳዮች ሚ/ር አስታውቋል፤ ለ15 ቀን በገዳሙ አካባቢ እንዳይደርሱ ተከለከሉ፤ የተጎዱት መነኰሳት በሕግ ይጠይቋቸዋል፤ በእስራኤል መንግሥት የታደሰውን የቅ/ሚካኤል ቤተ መቅደስ ተረከበ፤አገልግሎቱን ቀጥሏል፤ *** በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትን እያወኩ ሊቀ ጳጳሱንና ሌሎች አበው መነኰሳትን በመደብደብ ጉዳት ለማድረስ የሞከሩ አራት ዋልጌ የስም መነኰሳት ታገዱ፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ከቀትር በፊት፣ ሥርዐተ መቅደሱን ማስጠበቅን አስመልክቶ በተካሔደው ስብሰባ ላይ፣ ሊቀ ጳጳሱን ብፁዕ አቡነ እንባቆምንና ሌሎች አበው መነኰሳትን የደበደቡት ቄሰ ገበዙ አባ ወልደ ሩፋኤል ገብረ ጻድቃንና አባ ገብረ እግዚአብሔር ተስፋይ፣ ከአበሮቻቸው አባ ተስፋ ማርያም ይኅደጎ እና አባ ኀይለ ገብርኤል ጋራ፣ ከገዳሙ አገልግሎት እንዲታገዱ እና ከማኅበረ መነኰሳቱ እንዲለዩ በጉባኤ መወሰኑ ታውቋል፡፡ ክህነታቸው ያልተረጋገጠና በማኅበረ መነኰሳቱ የማይታወቁ ግለሰቦችን እያስገባ ሥርዓቱ እንዲጣስና መቅደሱ እንዲደፈር አድርጓል የተባለው ቄሰ ገበዙ አባ ወልደ ሩፋኤል ገብረ ጻድቃን፣ ሓላፊነቱን ካለመወጣቱም ባሻገር የኹለት ዓመት የግብዝና ጊዜውም በማለፉ በሌላ እንዲተካ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት፣ አባ ገብረ እግዚአብሔር
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በኢየሩሳሌም የገዳማቱ ሊቀ ጳጳስ እና አባቶች: በዋልጌ የስም መነኰሳት ተደበደቡ፤ “ለሕይወታችን ያሰጋሉ፤ መንግሥት ርምጃ ይውሰድ” ሲሉ ጠየቁ

ቄሰ ገበዙ አባ ወልደ ሩፋኤል ገብረ ጻድቃን፣ ክህነታቸው ያልተረጋገጠና በገዳሙ ማኅበር ያልታወቁ ግለሰቦችን ወደ መቅደሱ በማስገባት ሥርዓቱን አስደፍሯል፤ ለግብዝና የተመረጠበትን ጊዜ እንደጨረሰና ሓላፊነቱን በአግባብ ባለመወጣቱ ሌላ መመረጥ እንዳለበት የተናገሩትን ሊቀ ጳጳሱን ብፁዕ አቡነ እንባቆምን አንቆ ደብድቧል፤ ባለመታዘዝና በዐመፀኛነቱ የታወቀው አባ ተስፋ ማርያም ይኅደጎ፣ የብጥብጡ ቆስቋሽ ሲኾን፣ በ“ቦርደር” የገባው አባ ገብረ እግዚአብሔር ተስፋይ ደግሞ በአበርነት ተሳትፏል፤ አባ ተስፋ ማርያም ይኅደጎ ገዳሙን ከሦና 3 ዓመት ሞግቶ ለጥብቅና 80ሺሕ ብር ወጪ የዳረገ፤ ደብዳቤ ጽፎ ይቅርታ ጠይቆ የተመሰለ፤ በፓትርያርኩ ከምግብና የተሻረ፣ ተሽሎት ይኾናል ተብሎ ሲመረጥ ደግሞ የገዳሙ መነኮሳት የሻሩት ነው፤ “ሥርዐት አልበኞች ኹነው፣ ጠግበው፤ ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? ቢባሉ ወንበር አንሥተው ደበደቡ፤ ከእንግዲህ ከእነርሱ ጋራ አንቀድስም፤ አንቆርብም፤ ለሕይወታችንም አስጊዎች ናቸው፤ መንግሥት የሚያደርገውን ያድርግ፤” /ማኅበረ መነኰሳቱ/   *** በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስንና ሌሎች አበው መነኰሳትን በመደብደብ ጉዳት ለማድረስ የሞከሩ ኹለት ስመ መነኰሳትን የእስራኤል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተገለጸ፡፡ ትላንት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርኩ ከሞስኮ ጉዟቸው ፈጥነው ተመለሱ፤ በቀድሞው ርእሰ ብሔር ቀብር ላይ ይገኛሉ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሞስኮ በረራውን ዳግም መጀመሩን ምክንያት በማድረግ በአዘጋጀው መርሐ ግብር ወደ ሩስያ ያቀኑት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ለመልስ ጉዞ ከታቀደው ጊዜ ፈጥነው ዛሬ ማለዳ ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ ሲኾን፤ ከቀኑ 9፡00 ላይ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በብሔራዊ ክብር በሚፈጸመው የቀድሞው ርእሰ ብሔር የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ቀድሞ በተያዘው ፕሮግራም መሠረት፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ከሞስኮ የአየር መንገዱ ጉዞ የሚመለሱት ዛሬ ምሽት ላይ እንደነበርና በቀብሩ ላይ እንደማይገኙ መገለጹ፣ በቤተ ክህነቱም በቤተ መንግሥቱም አካላት ጥያቄ ማስነሣቱ ተጠቅሷል፡፡ ይኹንና በጉዞው የተያዘውን የአየር መንገዱን መርሐ ግብር በአንድ ቦታ አካትቶ ለማከናወንና ቅዱስ ፓትርያርኩም ለማነጋገር ያሰቧቸውን የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች በዚያው ለማግኘት በመቻላቸው፣ ቆይታቸው በአጭሩ ተጠናቅቆ ከታቀደው ጊዜ ፈጥነው ከልኡካን ቡድኑ ጋራ ዛሬ ማለዳ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱና በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የፓትርያርኩ በቀድሞው ርእሰ ብሔር የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ አለመገኘት ጥያቄ አስነሣ

ለቤተ ክርስቲያንም ላደረጉት አስተዋፅኦ አክብረው ሊሸኙ ይገባ እንደነበር ተገልጿል፤ ባለፈው እሑድ በቤታቸው ተገኝተው፣ሐዘናቸውን ገልጸው አጽናንተዋል፤ ተብሏል፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሞስኮ በረራ ዳግም መጀመር ወደ ሩስያ ተጉዘዋል፤ በኹለቱ አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት፣ብዙ ቱሪስቶችን ለማምጣት ታስቧል፤     *** ኹለተኛው የኢፌዴሪ ርእሰ ብሔር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ቀብር፣ ነገ ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. በብሔራዊ ክብር፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚፈጸም ሲኾን፤ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በሥነ ሥርዓቱ ላይ አለመገኘት ጥያቄ አስነሣ፡፡   ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ከ27 ዓመት በኋላ በትላንትናው ዕለት የሞስኮ በረራውን ዳግም የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዘጋጀውና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የአብያተ እምነት መሪዎች በታደሙበት መርሐ ግብር ወደ ሩስያ ተጉዘዋል፡፡ ለቀድሞው ርእሰ ብሔር ክብር እና ለአገራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሚመጥን ሽኝት ለማድረግ መንግሥት፣ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አቋቁሞ እየሠራ እንደሚገኝና የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው የሚፈጸምበት ታኅሣሥ 10 ቀንም ብሔራዊ የሐዘን ቀን ኾኖ እንዲውል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መታወጁን የጠቀሱ አስተያየት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለ3ኛ ጊዜ አላግባብ የተመደበው የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሒሳብና በጀት ሓላፊ መዝባሪው ኤልያስ ተጫነ ለ3ኛ ጊዜ ታገደ!

ሥራው በዋና ክፍሉ ምክትል ሓላፊ እየተከናወነ ይቆያል፤ “በሕገ ወጥ የአስተዳዳሪዎች ዝውውር ችግር ፈጥሯል፤” “የትላንትናውን ብልሹ አሠራር የሚያባብስ ነው፤”/የእገዳው ደብዳቤ/ ለ3ኛ ጊዜ መመደቡ፣“የአ/አበባ ሀ/ስብከት እንዘጭ እንቦጭ” ተብሎ ነበር፤     *** በአዲስ መልክ በተካሔደው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ክፍል ሓላፊዎች ምደባ፣ ለሦስተኛ ጊዜ አላግባብ ተመልሶ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍሉ ሓላፊ ኾኖ የተመደበው መዝባሪው ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ፣ በፓትርያርኩ ረዳት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ተፈርሞ ታገደ፡፡ ዛሬ ሰኞ፣ ታኅሣሥ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በረዳት ጳጳሱ ተፈርሞ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚገልጸው፣ ሊቀ ጠበብት ኤልያስ የታገደው፣ በቅርቡ በሕገ ወጥ አሠራር ለማድረግ ታስቦ በነበረው የ52 ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ዝውውር ጋራ በተያያዘ ነው፡፡ በሕገ ወጥ የድለላ ዝውውሩ ሳቢያ ችግር መፍጠሩንና ይህም የትላንትናውን ብልሹ አሠራር የሚያባብስ ኾኖ መገኘቱን የእገዳ ደብዳቤው አስረድቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ከግለሰቡ ጋራ ተግባብቶ ለመሥራት እንደሚያስቸግርና ከሓላፊነቱ ማገድ አስፈላጊ ኾኖ እንዳገኘው አስፍሯል፡፡ ከሓላፊነቱ የታገደው ሊቀ ጠበብት ኤልያስ፣ ወደመጣበት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሪፖርት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ: “ጽኑ ሕመም” ላይ ነው! ደቀ መዛሙርቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ድጋፍ ጠየቁ፤ ትምህርት ካቋረጡ ከሳምንት በላይ ተቆጥሯል

እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ በተደጋጋሚ የቀረቡ አስተዳደራዊና አካዳሚያዊ ጥያቄዎቻቸው ሰሚ አጥተዋል፤ እንደ ሌሎች ኮሌጆች ኹሉ፣ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተጠሪ ኾኖ በበላይነት እንዲከታተለው አመለከቱ፤ አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ በክብር እንዲነሡና አቅመ ቢስ አመራሮች በአፋጣኝ እንዲወገዱ ደቀ መዛሙርቱ ጠየቁ፤ ከነገ ጀምሮ፣ጥቅመኛ ሓላፊዎችንና ሠራተኞችን በማባረር ቢሮዎችን የማሸግ ርምጃ እንደሚወስዱ አስጠነቀቁ፤ ጭቁን መምህራንና ሠራተኞች እንዲሁም የማታ ደቀ መዛሙርት፣ ጥያቄዎቻቸውን እንደሚደግፉ አረጋገጡ፤ ንግዳዊነት የተንሰራፋበት ኮሌጁ፣ ተጠቃሎ ከመሸጡ በፊት ተቆርቋሪ ወገኖች ኹሉ እንዲደርሱለት ተማፀኑ፤ *** ለክፍያ ሲሉ ኮርሶችን በሚያግበሰብሱ ሓላፊዎች ሳቢያ፣ የትምህርት ጥራቱ “ሙሉ በሙሉ ሞቷል፤ ወድቋል፤” ከመምህራኑ ይልቅ ያለአግባብ የተሰገሰጉ ሠራተኞች፥በደመወዝ፣ በአበልና በበዓላት ቦነስ  በጀቱን ይቀራመታሉ፤ የተማሪዎች ማደሪያዎች ሳይቀሩ፣ለንግድ እና ለመኖርያ ተከራይተዋል፤ መጸዳጃ ቤቶቻቸው መጋዘን ኾነዋል፤ ነፃነት የታወጀበትና በቅርስነት መያዝ ያለበት የቀድሞ የሊቀ ጳጳሱ ቢሮ፣“ጾም የሚሻርበት ናይት ክለብ ኾኗል፤” “የተከራዮች ማንነትና ተመኑ ተለይቶ ይታወቅ፤ገቢው በውጭ ኦዲተር ተመርምሮ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ይተዳደር፤” “ለአንድ ትልቅ የትምህርት ተቋም ሕንፃ መገንባትና መነገድ የስኬት ጥግ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፤ በቤተ ክርስቲያንና በሕዝብ ሀብት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቤተ ክርስቲያን: አገር አቀፍ የሰላም እና ስብከተ ወንጌል ስምሪት ልታካሒድ ነው

ሥልጠናን፣ሕዝባዊ ውይይትንና ዕቅበተ እምነትን ያካተተ ስምሪት ነው፤ እስከ ታኅሣሥ መጨረሻ ድረስ፣52 አህጉረ ስብከትን ለማዳረስ ታቅዷል፤ በወቅቱ ፈተናዎች፥የካህናትና የወጣቶች መብትና ግዴታ ላይ ያተኩራል፤ በሰማዕትነትና በሚዲያ አጠቃቀም ረገድ ኦርቶዶክሳዊውን ወጣት ያነቃል፤ *** ከ9ሚ. ብር በላይ በጀት ተመድቧል፤250 ጠቅላላ ልኡካን ይሳማሩበታል፤ በእያንዳንዱ ስምሪት በሊቀ ጳጳስ የሚመሩ 5፣ 5 ልኡካን ይሳተፉበታል፤ ዓላማውን የሚያስፋፉ ንኡሳን ኮሚቴዎች በየአህጉረ ስብከቱ ይቋቁማሉ፤ ካህናትና ምእመናን ከአቀባበል ጀምሮ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል *** የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ ከነገ በስቲያ ኀሙስ፣ ታኅሣሥ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል የሚዘልቅ የአገራዊ ሰላም እና የስብከተ ወንጌል ስምሪት ሊያካሔድ ነው፡፡ በአገራችን አንዳንድ አካባቢዎች እየታየ ያለውና በቀላሉ የሚገታ የማይመስለው የሰላም ዕጦት ችግር ያሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ባለፈው ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሔደው የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባው ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት የተዘጋጀው ስምሪቱ፣ ቤተ ክርስቲያናችን በሰላም ዕጦት የሚገጥማትን ተግዳሮት የምትቋቋምበትና ለአገራዊ ዕርቅና ለሕዝብ አንድነት መጠበቅ ያላትን ታሪካዊና ብሔራዊ ሚና የምትወጣበት እንደኾነ ተገልጿል፡፡ ስምሪቱ፥ የሥልጠና፣
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በደቡብ ክልል የቤተ ክርስቲያንን መብት የሚጋፉ ባለሥልጣናት ተጽዕኖ እንዲቆም ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ አሳሰቡ፤“አማራጩ ራስን አጠናክሮ መገኘት ብቻ ነው”

ከባለሥልጣናቱ አንዳንዶቹ፣ የሃይማኖት ሰባክያን እና ሓላፊዎች ናቸው፤ በሆሳዕና እና በከምባታ፣ ሕጋዊ የባሕረ ጥምቀት ይዞታችንን እያወኩ ነው፤ “ጥቃትን የምንቋቋመው የመከላከል አቅምን በአንድነት በማጠናከር ብቻ ነው” በ1.5 ሚ. ብር ወጪ የአብነት ት/ቤት ለመሥራት ዝግጅት እየተደረገ ነው፤ *** በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በቤተ ክርስቲያናችን አገልጋይ ካህናት እና ምእመናን ላይ እየተሰነዘረ ያለውን ጥቃትና ጭፍጨፋ መቋቋም የምንችለው፣ የመከላከል አቅማችንን በአንድነት ስናጠናክር ብቻ እንደኾነ የሐድያና ስልጤ፣ ሀላባ ከምባታና ጠምባሮ አህጉረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ አሳሰቡ፡፡ በሶማሌ ክልል ከተሞች በሚገኙ አብያተ ክርስቲያን ላይ ከደረሰው ውድመት፣ በካህናት እና በምእመናን ላይ ከተፈጸመው ግድያና ጭፍጨፋ ተምረን በቀጣይ በሌሎች ቦታዎችም ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይደገም ከተፈለገ ያለው አማራጭ፣ “ራስን አጠናክሮ መገኘት ብቻ ነው፤” ብለዋል ብፁዕነታቸው፡፡ በደቡብ የሀገራችን ክፍል፣ አንዳንድ ባለሥልጣናት፥ ሕገ መንግሥቱን በመፃረር፣ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ በመጋፋትና ሥርዐተ እምነትን በነፃነት የመፈጸም መብትን በመጋፋት ተፅዕኖ እያደረሱብን እንደሚገኙ ብፁዕነታቸው ለዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡ ከእኒህም ባለሥልጣናት አንዳንዶቹ፣ የአብያተ እምነት ሰባክያንና ሓላፊዎች
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የግራኝ አሕመድ ጊዜ እንዳያገረሽ – ቤተ ክርስቲያናችን ዘመቻ ፊልጶስን ልታውጅ ይገባታል

(ዜና ቤተ ክርስቲያን፤ ርእሰ አንቀጽ፣ ጥቅምት እና ኅዳር ፳፻፲፩ ዓ.ም.) በአሁኑ ጊዜ ኹሉም የራሱን እምነት በሰላም ማራመድ ሲገባው በተቃራኒው ፀረ ኦርቶዶክስ ዘመቻ በኹለት ግንባር በመካሔድ ላይ ይገኛል – የፀረ ክርስትናው ቡድን ውድመት እና የሐሳውያን መናፍስት የቅሠጣ ዘመቻ፤ በሰባክያነ ወንጌል እጥረትና በአባቶች ቸልተኝነት፣ በደቡብ እና በምዕራብ ኢትዮጵያ አህጉረ ስብከት የሚገኙት አብያተ ክርስቲያን እየተዘጉ ናቸው፤ ምእመናንንም በነጣቂ ተኩላዎች እየተበሉ ናቸው፤ አገር ናትና፣ መደፈርና ውድመት ቢያጋጥማትም ችግሮች የበለጠ ተባብሰው የከፋ አደጋ እንዳያመጡ በትዕግሥት፣ በአርምሞና በጽሞና ማሳለፍ ከጀመረች እነኾ ወደ ግማሽ ምእት ዓመት አጋማሽ ተጠግቷታል፤ ሀገረ አምላክ ኢትዮጵያ፣ የእነ ሬንሐርድ ቦንኬ ሠራዊት መፈንጫ አገር ከመኾኗም ባሻገር ኹለተኛዋ ሊብያ እንዳትኾንና የግራኝ አሕመድ ጊዜ እንደገና እንዳያገረሽ፣ ቤተ ክርስቲያናችን ዘመቻ ፊልጶስን ልታውጅ ይገባታል፤ ከጦርነት ኹሉ የሃይማኖት ጦርነት ስለሚከፋ፣ የከፋ ችግር ከመፈጠሩ በፊት በሀገሪቱ ምሥራቃዊ እና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች እየተፈጸመ ያለው ኢክርስቲያናዊ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲገታ መንግሥትን ጠይቃለች፤ *** በአዲስ አበባ በአንድ ደብር ብቻ እስከ 10 ሰባክያነ ወንጌል ታጉረው
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

“የአንዳንድ አካባቢዎች የሰላም ዕጦት ለወደፊቱ ያሰጋል” ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ዐወጀ፤ ምልዓተ ጉባኤውን ባለ15 ነጥቦች መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ

ዐበይት ነጥቦች፡- በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታየውና በቀላሉ የሚገታ የማይመስለው የሰላም ዕጦት ወደፊት አስቸጋሪ ኹኔታዎች እንዳይከሠቱ ስለሚያሰጋ፣ የወንጌል ሥምሪት ተዘጋጅቶ ትምህርተ ወንጌል ተጠናክሮ እንዲሰጥ፤ ከዚህም ጋራ ከኅዳር 1 እስከ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በመላው አብያተ ክርስቲያን ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ መመሪያ አስተላልፏል፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልእኮ ለማስፋት ከላይ እስከ ታች የሚተገበር የኹለንተናዊ ለውጥ መሪ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የቀረበ ስለኾነ፣ ትግበራው በተከፈተው ጽ/ቤት ሥራውን እንዲቀጥል፤ በአንዳንድ ክልሎችና ዞኖች፣ የዜጎች ኅልፈተ ሕይወትና መፈናቀል፣ የአብያተ ክርስቲያን መቃጠልና የንብረት ውድመት መንግሥት አጽንዖት ሰጥቶ ሕጋዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ጠይቋል፤ የአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 37ኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ የጋራ መግለጫ ተፈጻሚ እንዲኾንና በሒደት የሚያጋጥም ችግር በቋሚ ሲኖዶስ እየታየ ለውጤት እንዲበቃ መመሪያ ሰጥቷል፤ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ አኀት አብያተ ክርስቲያናትን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግንኙነት የሚጠናከርበትን ኹኔታ የሚያመቻች የጋራ ጉባኤው ተስማምቷል፤ አስተዳደራዊ ችግር የገጠማቸው አህጉረ ስብከት፣ ተመርምረው ውጤታቸው ተፋጥኖ እንዲቀርብ አዝዟል፤ በውጭ አገር ቤተ ክርስቲያናችን፣ የየአገሮቹን ሕገ መንግሥት ባገናዘበ መልኩ ቃለ ዐዋዲ እንዲዘጋጅና ኹሉም አብያተ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በቅ/ሲኖዶስ አዲስ የአህጉረ ስብከት አደረጃጀት በውጭና በአገር ቤት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ስምና ምደባ ዝርዝር

ማስታወሻ፡- በቀደመው ዘገባ፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ በመካከለኛው ካናዳ ሀገረ ስብከትም እንደተመደቡ የተገለጸው፣ ብፁዕነታቸው በሀገር ውስጥ ብቻ ለመመደብ ለምልዓተ ጉባኤው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት በመለወጡ የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብቻ ኾነው ተመድበዋል፤ በተጨማሪም፣ በቦልቲሞር የመካነ ሰላም ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ – የፐልስንቫንያ ስቴት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ – በሮቸስተር የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ፤ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ – የሰሜን ካሊፎርኒያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሎሳንጀለስ የበላይ ጠባቂ፤ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ – የዩናይትድ ኪንግደም እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተሹመዋል፡፡
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ኮፕቲኮች በፈጠራ መረጃ በዴር ሡልጣን ባለቤትነት ላይ ከሚያካሒዱት ትንኮሳ እንዲታቀቡ ቅ/ሲኖዶስ አሳሰበ

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ መላው ኢትዮጵያውያን ትንኮሳውን ለመቃወምና ከግብጽ ያልተመለሱ ይዞታዎችን ለማስመለስ እንዲተባበሩ ጥሪ አቀረበ፤ የእስራኤል መንግሥት በቃሉ መሠረት፣ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ መቅደስ ላይ ጥገና በመጀመሩ አመሰገነ፤ ጥገናው ኹሉንም ይዞታዎች እንዲያካትት ጠየቀ፤ “ዴር ሡልጣን፣ የኢትዮጵያ የነበረና ምንጊዜም የኢትዮጵያ ኾኖ የሚቆይ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሳችን ነው፤” *** የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባላት፣ ጥንታውያንና ታሪካውያን ይዞታችን በኾኑት የዴር ሡልጣን ገዳማት ላይ ማስረጃ በሌለው የፈጠራ መረጃ የባለቤትነት ጥያቄ በማንሣት የሚያካሒዱትን አላስፈላጊ ሁከት እንዲያቆሙ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ አስተላለፈ፤ የእስራኤል መንግሥት ቃል በገባው መሠረት ከዴር ሡልጣን የቅዱስ ሚካኤል ቤተ መቅደስ የጀመረውን የእድሳት ሥራ አጠናክሮ በመቀጠል ኹሉንም የኢትዮጵያ የዴር ሡልጣን ይዞታዎች በአግባቡ እንዲጠግን ጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ ይዞታ በኾነው በዴር ሡልጣን ገዳም የቅዱስ ሚካኤል ቤተ መቅደስ እድሳት ላይ፣ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባላት ያሳዩትን ሕገ ወጥ ተቃውሞ አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ረቡዕ፣ ጥቅምት 21 ቀን በሰጠው መግለጫ፣ ግብጻውያኑ ከትንኮሳና ሁከት እንዲታቀቡ ጥሪ ያቀረበ ሲኾን፤ ቃል በገባው መሠረት፣
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ቅዱስ ሲኖዶስ: የፕሮቴስንታዊ ተሐድሶ መናፍቁን አእመረ አሸብርን አወገዘ!!

ሊቃውንት ጉባኤ ስለ ኑፋቄው ያቀረበውን 17 ገጽ ጽሑፍ መርምሮ አወገዘው፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበርም፣ የሚሠራበትን ቅጥርና ውክልና ማንሣት አለበት፤ “መዳን በኢየሱስ ብቻ ነው” በሚል ባሳተመው መጽሐፍ ኑፋቄውን ገልጿል፤    
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ሲኖዶስ: በአህጉረ ስብከት ድልደላ እና በብፁዓን አባቶች ምደባ ይወስናል፤ ምልዓተ ጉባኤውን ዛሬ ያጠናቅቃል፤ ከቀትር በኋላ መግለጫ ይሰጣል

ከጥቅምት 12 ቀን ጀምሮ ላለፉት 10 ቀናት፣ የመጀመሪያውን የምልዓተ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሒድ የቆየው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ጥቅምት 21 ቀን ከቀትር በኋላ 8:30 ላይ በሚሰጠው መግለጫ እንደሚያጠናቅቅ ለብዙኃን መገናኛ በላከው ጥሪ አስታውቋል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ከቀትር በፊት በሚኖረው ውሎ፣ ሰባት ብፁዓን አባቶች(ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ) እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በአስረጅነት በተገኙበት ሲሠራ የሰነበተው የአህጉረ ስብከት ድልደላ እና የብፁዓን አባቶ…ች ምደባ ቀርቦለት እንደሚወስን ተገልጿል፡፡ ኮሚቴው፣ በተለያየ አደረጃጀት የተሰጡትን ምክረ ሐሳቦች በመመርመር የድልደላና የምደባ ውሳኔ ሐሳቡን እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡ ከዝርዝሩ እንደሚታየው፣ በጠቅላላው ከ30 ያላነሱ ብፁዓን አባቶች በምደባው የተካተቱ ሲኾን፤ በሀገር ውስጥ የምዕራብ አርሲ/ሻሸመኔ/ ሀገረ ስብከትን ጨምሮ በውጭ በርካታ አዲስ የአህጉረ ስብከት አደረጃጀት ተደርጓል፡፡ በውጭ ከነበሩት ወደ ሀገር ውስጥ የተመደቡ/ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል፣ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ እና ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ/
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ሲኖዶስ: በአህጉረ ስብከት ድልደላ እና በብፁዓን አባቶች ምደባ ይወስናል፤ ምልዓተ ጉባኤውን ዛሬ ያጠናቅቃል፤ ከቀትር በኋላ መግለጫ ይሰጣል

ከጥቅምት 12 ቀን ጀምሮ ላለፉት 10 ቀናት፣ የመጀመሪያውን የምልዓተ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሒድ የቆየው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ጥቅምት 21 ቀን ከቀትር በኋላ 8:30 ላይ በሚሰጠው መግለጫ እንደሚያጠናቅቅ ለብዙኃን መገናኛ በላከው ጥሪ አስታውቋል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ከቀትር በፊት በሚኖረው ውሎ፣ ሰባት ብፁዓን አባቶች(ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ) እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በአስረጅነት በተገኙበት ሲሠራ የሰነበተው የአህጉረ ስብከት ድልደላ እና የብፁዓን አባቶ…ች ምደባ ቀርቦለት እንደሚወስን ተገልጿል፡፡ ኮሚቴው፣ በተለያየ አደረጃጀት የተሰጡትን ምክረ ሐሳቦች በመመርመር የድልደላና የምደባ ውሳኔ ሐሳቡን እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡ ከዝርዝሩ እንደሚታየው፣ በጠቅላላው ከ30 ያላነሱ ብፁዓን አባቶች በምደባው የተካተቱ ሲኾን፤ በሀገር ውስጥ የምዕራብ አርሲ/ሻሸመኔ/ ሀገረ ስብከትን ጨምሮ በውጭ በርካታ አዲስ የአህጉረ ስብከት አደረጃጀት ተደርጓል፡፡ በውጭ ከነበሩት ወደ ሀገር ውስጥ የተመደቡ/ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል፣ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ እና ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ/
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በሀገር ሰላምና በቤተ ክርስቲያን መብቶች መጠበቅ: ቅዱስ ሲኖዶስ ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከክልሎች ፕሬዝዳንቶች ጋራ ይመክራል

የቤተ ክርስቲያን ይዞታና መብት የአገርም እንደኾነ በማስገንዘብ እንዲከበር ያሳስባል፤ አባቶችና ሰባክያን የሚቀናጁበት፣ ዓለም አቀፍ የስብከተ ወንጌል ሥምሪት ይካሔዳል፤ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ተጠሪ የኾነ ዐቢይ አስተባባሪ ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ ይሠየማል፤ *** በሲኖዶሳዊ አንድነቱ፥የፀረ ተሐድሶ ጉባኤያት በመላ አህጉረ ስብከት እንዲቋቋሙ አሳሰበ፤ ለሲኖዶሳዊ እና አስተዳደራዊ አንድነት የደረሰበትን ስምምነት፣መርምሮ እንዲሰነድ አዘዘ፤ ከአኃት የኤርትራ ቤተ ክርስቲያን ግንኙነቱን ለማጠንከር፣ ከመንግሥት ጋራ ይሠራል፤ *** በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች እየተከሠተ በሚገኘው ግጭትና መፈናቀል በግንባር ቀደምነት እየተጠቁ ያሉትን ካህናትና ምእመናን እንዲሁም መብቶቿ እየተጣሱ እልቂትና ውድመት እየደረሰባት ያለውን ቤተ ክርስቲያን ለመታደግ ያለመ ምክክር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከክልሎች ርእሳነ ብሔራት ጋራ እንደሚካሔድ ተጠቆመ፡፡ ተጽዕኖውንና እልቂቱን ቤተ ክርስቲያን በሓላፊነት ስሜት ቻል ብታደርገውም፣ ከቀን ቀን እየተባባሰ በመሔዱ ልትታገሠው ከማትችልበት ደረጃ መድረሱን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ በምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸው ሲያመለክቱ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱም በአጀንዳው ተ.ቁ(7)፣ ሀገራዊ ሰላምና ዓለም አቀፍ የስብከተ ወንጌል ሥምሪት በሚል ርእስ ተነጋግሮበታል፡፡ ከመንግሥት የፍትሕና ጸጥታ አካላት ጋራ በቅንጅት በመሥራት ጥቃቱን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የኦሮሚያ አህጉረ ስብከት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የማቋቋም መነሻ ጥያቄዎች በመሪ ዕቅዱ ትግበራ ሊመለሱ እንደሚችሉ ተጠቆመ

“የመነሻ ኹኔታዎቹ ከመሪ ዕቅዱ የዳሰሳ ጥናቶች ጋራ ተመሳሳይ በመኾናቸው ችግሮቹ በትግበራው ሒደት ሊመለሱ ይችላሉ፤” /የምልዓተ ጉባኤው አባላት/ “በይደር ይጠና ከሚባል ይልቅ በመሪ ዕቅዱ ማሕቀፍ ውስጥ ሊታይ የሚችልበት ውሳኔ ቢተላለፍ ተመራጭ ይኾናል፤” /ከአስረጅዎች አንዱ/ *** ከወቅቱ የሐዋርያዊ ተልእኮ ችግሮችና ተግዳሮቶች አንጻር የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተደራሽና ውጤታማ ይኾን ዘንድ በክልል ደረጃ ሥራውን የሚያስተባብር ጽ/ቤት እንዲቋቋም የቀረበው ጥያቄ፣ በጸደቀው መሪ ዕቅድ ትግበራ ማሕቀፍ ሊመለስ እንደሚችል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተካሔደው ውይይት ተጠቆመ፡፡ ከክልል መዋቅር ጋራ አቻ የኾነ “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት” ማቋቋም እንደሚያስፈልግ የጠየቁትና “እነ አባ ገዳ ተሾመ ድረስ ያቀረቡት አቤቱታ” በሚል በተ.ቁ(21) በተያዘው አጀንዳ፣ የተዘጋጀው ጽሑፍ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለምልዓተ ጉባኤው በንባብ የተሰማ ሲኾን፣ ትላንት ደግሞ ስምንት አስረጅዎች(አባ ገዳ ተሾመ ድረስ፣ ዶ/ር ብርሃኑ አሰፋ፣ ጠበቃ ቀለም ወርቅ ሚደቅሳ፣ ጠበቃ ኃይለ ሚካኤል ታደሰ፣ ዶ/ር ጃራ ሰማ፣ ኢንጅነር ብርሃኑ በቸሬ፣ ዶ/ር ብርሃነ መስቀል ጠና) በአካል ቀርበው በቃል አብራርተዋል፡፡ በአፋን ኦሮሞ አገልግሎቱን የሚፈጽሙ ብቁ ሰባክያንና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በግብጻውያን የዴር ሡልጣን ሁከት ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ይሰጣል፤ የእስራኤልን መንግሥት ያመሰግናል

  የቅ/ሚካኤል ቤተ መቅደስ እድሳትን ለማደናቀፍ ቢሞክሩም አልተሳካም፤ እድሳቱን ከባለቤትነት መብት ጋራ አያይዘው የፈጠራ ታሪክ እየነዙ ነው፤ የዐረቡን ዓለም አስተባበረው በእስራኤል ላይ ጫና ለማሳደር እየሠሩ ነው፤ ቅ/ሲኖዶስ፣ለኮፕት ፖፕና ሲኖዶስ መግለጫ ዓለም አቀፍ ምላሽ ይሰጣል፤  *** በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የዴር ሡልጣን ገዳማችን፣ በአደጋ የተጎዳውን የቅዱስ ሚካኤል ቤተ መቅደስ እድሳት ለማደናቀፍ ሞክረው ያልተሳካላቸው የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ጳጳሳት፣ በፈጠራ ታሪክ የዐረቡን ዓለም በማስተባበር ጫና ለመፍጠር ለያዙት ዘመቻ ምላሽ ለመስጠትና በቃሉ መሠረት እድሳቱን ለጀመረው የእስራኤል መንግሥት ምስጋና ለማቅረብ ዓለም አቀፍ መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡   ጣሪያው በአደጋ ተሸንቁሮ ከዓመት በላይ አገልግሎት ያቆመውን የቅዱስ ሚካኤል ቤተ መቅደስ እንደሚያድስ የእስራኤል መንግሥት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ እና ለኢትዮጵያ መንግሥት በገባው ቃል መሠረት፣ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ጥቅምት 14 ቀን፣ የኢየሩሳሌም ማዘጋጃ ቤት የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ሠራተኞቹን ከሥራ መሣሪያዎቻቸው ጋራ ለማስገባት ሲሞክር፣ የኮፕት ዲያቆናት፣ ቀሳውስትና ምእመናን መግቢያውን በመዝጋት እንዳያልፉ ለመከላከል ሞክረዋል፡፡   የእስራኤል መንግሥት እድሳቱን እንዲያከናውን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል በአስቸኳይ አስተዳዳሪ እንዲመደብ ቅ/ሲኖዶስ አዘዘ

የካህናትና የምእመናን ተወካዮች ለምልዓተ ጉባኤው አስረዱ፤ የተባረሩት አስተዳዳሪ እና የጽ/ቤት ሓላፊዎች አይመለሱም፤ ከአዲሱ አለቃ ጋራ አዲስ የጽ/ቤት ሓላፊዎችም ይመደባሉ፤ ማጣራቱን በሓላፊነት ያስተባብራሉ፤አስተዳደሩን ያዋቅራሉ፤ *** ካለፈው ዓመት ታኅሣሥ ጀምሮ ጉዳዩ ሳይቋጭ በእንጥልጥል ለሚገኘው የደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል፣ አስተዳዳሪና የጽ/ቤት ሓላፊዎች በአስቸኳይ እንዲመደቡ ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ፡፡ ምልዓተ ጉባኤው፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ በካቴድራሉ ሒሳብ ላይ የተጀመረው ኦዲት እንደተጠናቀቀ በአስቸኳይ አስተዳዳሪ እንዲመደብና አስተዳደሩ እንዲዋቀር ያዘዘ ቢኾንም፤ ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቱ አባላት ዛሬ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ተመሥርቶ ምደባው እንዲቀድም ተለዋጭ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ዛሬ ሰኞ፣ ጥቅምት 19 ቀን ጠዋት በስድስት ተሽከርካሪዎች ወደ መንበረ ፓትርያርኩ የደረሱት የካቴድራሉ ካህናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ምእመናን 6 ተወካዮች ለምልዓተ ጉባኤው እንዳስረዱት፤ ባለፉት 11 ወራት መንፈሳዊ አገልግሎቱ ባይታጎልም፣ የተፈጠረውን የአስተዳደር ክፍተት ለግል አጀንዳቸው በመጠቀም ይዞታውን ለመቀራመት በሚሹና እልባት ባልተሰጣቸው ሌሎች ጉዳዮች ሳቢያ ችግሮቹ እየተወሳሰቡ በመኾኑ፣ የአስተዳዳሪና የጽ/ቤት ሓላፊዎች ምደባ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት የማጣራቱን ሒደት በባለቤትነት እንዲያስተባብሩና አስተዳደሩን እንዲያዋቅሩ ይደረግ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የአእላፋት ድምፅ ኅብረቱ: የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለውጥ አቋሙን ለቅዱስ ሲኖዶስ አስረዳ፤ “መክረን እናስታውቃችኋለን” /ቅዱስ ፓትርያርኩ/

ኹለንተናዊ ለውጥ ያመጣል የተባለ መሪ ዕቅድ እንዲተገበር ተወስኗል፤ ከፍተኛ ባለሞያዎችን በማስተባበር በትግበራ ሒደቱ ለመሳተፍ ዐቅዷል፤ የለውጡ ተስፋና ምልክት እስከ ግንቦት መታየት እንዲጀምር ጠይቋል፤ የምእመናን ተሳትፎ የሚያድግበት ሥርዓት እንዲዘረጋ አመልክቷል፤ *** (አዲስ አድማስ፤ ቅዳሜ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም.) ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመዋቅርና የአሠራር ችግሮች ኹነኛ መፍትሔ በመስጠት ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘውና በአምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ የሚመራው የአእላፋት ድምፅ የካህናትና ምእመናን ኅብረት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፊት ቀርቦ የአስተዳደር ለውጥ አቋሙን አስረዳ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱም በጥያቄዎቹ ላይ መክሮ ምላሽ እንደሚሰጥ ለኅብረቱ ተወካዮች አስታውቋል፡፡ የብዙ ሺሕ ካህናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ መንፈሳውያን ማኅበራት፣ የአገር ሽምግሌዎችና ታዋቂ ምእመናን ተወካዮች የኾኑና በአምባሳደር ካሳ ከበደ የሚመሩ 9 የኅብረቱ ልኡካን፣ ትላንት ዓርብ፣ ጥቅምት 16 ቀን ረፋድ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በመሪ ዕቅድ በመመራትና የምእመናንን ከፍተኛ ተሳትፎ በማረጋገጥ ማምጣት ስላለባት አስተዳደራዊ ለውጥ ያላቸውን አቋም በመካሔድ ላይ በሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ፊት ቀርበው ማስረዳታቸውን፣ ምክትል ሰብሳቢው አርክቴክት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅ/ሲኖዶስ: ለቅ/ላሊበላ አብያተ መቃድስ ጥገና 20 ሚሊዮን ብር እንዲመደብ ወሰነ

በፓትርያርኩ የሚመራ ዐቢይ ኮሚቴ ተቋቁሞ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ያሰባሰባል፤ የአኵስም ጽዮን ቤተ መዘክር ግንባታን ለማፋጠን 20 ሚ. ብር በጀት ፈቀደ፤ *** በአሳሳቢ አደጋ ላይ ለሚገኙት የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ መቃድስ ጥገና፣ የ20 ሚሊዮን ብር በጀት እንዲመደብ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የወሰነ ሲኾን፣ በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራና በዓለም አቀፍ ደረጃ በመንቀሳቀስ ድጋፍ የሚያሰባስብ ዐቢይ ኮሚቴ እንዲቋቋም አዘዘ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ትላንት ዓርብ ከቀትር በኋላ በነበረው ውሎ፣ በአጀንዳ ተ.ቁ(16) እና (17) ስለ አኵስም ጽዮን ማርያም ሙዝየም ርዳታ ጥያቄ እና የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያን ችግር በተመለከተ ከተወያየ በኋላ የበጀት ድጋፉን የፈቀደው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባውን በጀመረበት ባለፈው ሰኞ፣ የችግሩን አሳሳቢነትና አስቸኳይነት ለሚመለከታቸው አካላት ለማስረዳት፣ በቅዱስ ላሊበላ ደብር አስተዳዳሪና በከተማው ከንቲባ እየተመሩ ወደ አዲስ አበባ የመጡትን ልኡካን ተቀብሎ አቤቱታቸውን አዳምጧል፡፡ ለጥገናው የሚያስፈልጉ ነገሮች ተሟልተው ሳለ የሚያስፈልገውን ያህል ገንዘብ በአንድ ጊዜ ለማግኘት አስቸጋሪ መኾኑን ያስረዱት ልኡካኑ፣ በማእከል ደረጃ ዐቢይ ኮሚቴውን አቋቁሞ በስፋትና በቀጣይነት የመንቀሳቀስ ሐሳብ ማቅረባቸው ተገልጿል፡፡ የቅዱስ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ሲኖዶስ: ከ366 ሚሊዮን ብር በላይ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትን የ2011 ዓ.ም. በጀት አጸደቀ

ካለፈው በጀት ዓመት ጋራ ሲነጻጸር፣የ28 በመቶ ብልጫ በዕድገት አሳይቷል፤ የአህጉረ ስብከት የ35% ፈሰስ፣ የሕንፃዎች ኪራይ ጭማሪ አስተዋፅኦ አለው፤ ለጅግጅጋ አብያተ ክርስቲያን መልሶ ማቋቋሚያ 4 ሚሊዮን ብር በጀት መደበ፤ በየአህጉረ ስብከቱ ለካህናት ማሠልጠኛና ለአብነት ት/ቤቶች 10ሚ.ብር ይልካል፤ *** ለብዙኀን መገናኛ አገልግሎት ድርጅት (ኢኦተቤ ቴቪ)፣12 ሚሊዮን ብር ለቋል፤ ለመሪ ዕቅድ ትግበራ ጽ/ቤት ማቋቋሚያና ሥራ ማስፈጸሚያ 2.5ሚ.ብር ይዟል፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን አዳራሽ፣ በ25 ሚ. ብር ወጪ ለማስገንባት ተዘጋጅቷል፤ በአሮጌ ቄራና በባሻ ወልዴ ችሎት ለሚሠሩ 3 ሕንፃዎች 63 ሚ. ብር በጅቷል፤ *** የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በትላንት ኀሙስ፣ ጥቅምት 15 ቀን ውሎው፣ የቤተ ክርስቲያንን የሥራ አስፈጻሚነትና የአስተዳደር ተግባር የማከናወን ከፍተኛ ሥልጣን ያለውን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትን የ2011 ዓ.ም. በጀት መርምሮ አጸደቀ፡፡ በበጀትና ሒሳብ መመሪያ አማካይነት በበጀት ተደግፈው የቀረቡ ዝርዝር ተግባራትን የመረመረው ምልዓተ ጉባኤው፣ ለ2011 ዓ.ም. በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የቀረበውን የ366ሚ 250ሺሕ 448 ብር ከ05 ሳንቲም በጀት ረቂቅ ላይ በስፋት በመወያየት አጽድቋል፡፡ ከአምናው 286ሚ 468ሺሕ 911
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ሲኖዶስ: የመሪ ዕቅድ ትግበራ ጽ/ቤት እንዲቋቋም ያሳለፈው ውሳኔ እንዲፈጸም አዘዘ፤የባለሞያ ምእመናን ሰፊ ተሳትፎ ሊረጋገጥበት ይገባል

ለኹለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን ለውጥ፤ ለመዋቅር፣ አደረጃጀትና አሠራር ማሻሻያዎች የተደረጉ ጥናቶችን ኹሉ በመሠረታዊነት ይጠቀማል፤ በጥቅምት 2008 ዓ.ም. ተመድቦለት በነበረው 2.5 ሚሊዮን ብር መነሻ በጀት፣ ለተወሰነ ጊዜ በሚቀጠሩ ባለሞያዎች የሚደራጅ የፕሮጀክት ጽ/ቤት ነው፤ በሰነዶች ዝግጅት እና ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ በሚቋቋሙ የመተግበሪያ አካላት፣ የባለሞያ ምእመናን የትሩፋት ተሳትፎ በስፋት ሊረጋገጥ ይገባል፤ በየደረጃው በሚቋቋሙ የጽ/ቤቱ አካላት፣ የባለሞያ ምእመናንን ሚና ማስፋት፥ ተሳትፏቸውን በማሳደግ፣ ውጤታማነቱን በማጎልበትና በወጪ ቅነሳ በጎ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፤ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ፣ በትግበራው ሒደት የማያሠሩ(የማያስኬዱ) ኹኔታዎች ካጋጠሙት ለቀጣዩ ምልዓተ ጉባኤ ሪፖርት ያቀርባል፤ መሪ ዕቅዱ እና ሌሎች የለውጥ ጥናቶች፣ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከግንቦት 2005 እስከ ጥቅምት 2009 ዓ.ም. ባሳለፋቸው ውሳኔዎች፣ እያስጠና እንዲሠራባቸው አቅጣጫ የሰጠባቸው ሰነዶች ናቸው፤ የመሪ ዕቅዱ ትግበራ እና የጽ/ቤቱ መቋቋም፣ የአእላፋት ድምፅ ለአስተዳደራዊ ለውጥ የካህናትና ምእመናን ተናሥኦት ኅብረት ካነሣቸው ጥያቄዎች ቀዳሚው ነው፡ ***
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅ/ሲኖዶስ በአህጉረ ስብከት አቤቱታዎችና በሰዓሊተ ምሕረት ካቴድራል ጉዳይ ውሳኔዎችን አሳለፈ

ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፣ ከምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ለመነሣት ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሏል፤ ለሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ረዳት ጳጳስ ይመደብላቸዋል፤ በአዊ ዞን ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አባ ቶማስ ላይ የቀረበው አቤቱታ እንዲጣራ አዝዟል፤ የአ/አበባ ሀ/ስብከትን የመከፋፈል ጥያቄ፣በቅድሚያ የአሠራር ችግሮቹ እንዲፈተሹና በጥናቱ ውጤት ላይ በመመሥረት እንዲመለስ ተስማምቷል፤ የሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ኦዲት እንደተጠናቀቀ፣ አስተዳዳሪ እንዲመደብለትና አስተዳደሩ በአፋጣኝ እንዲዋቀር ወስኗል፤ *** ምልዓተ ጉባኤው፣ በዛሬ ረቡዕ፣ ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. የቀትር በፊት ውሎው፣ ከአምስት አህጉረ ስብከት በቀረቡ አቤቱታዎችና በሻሸመኔ የሀገረ ስብከት ጥያቄ ጉዳይ ውሳኔ ያሳለፈ ሲኾን፤ ከቀትር በኋላም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን የመከፋፈል አልያም እንደ አንድ ሀገረ ስብከት ራሱን ችሎ በሊቀ ጳጳስ ይመራ በሚሉ ጥያቄዎችና በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ወክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል ውዝግብ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ምዕራብ አርሲ(ሻሸመኔ)፤ በሀገረ ስብከት ራሱን እንዲችል ምእመናኑ በተደጋጋሚ ሲያቀርቡ የቆዩትን ጥያቄ ተቀብሎ፣ ከምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ተለይቶ ራሱን የቻለ ሀገረ ስብከት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በታጣቂዎች የተከበቡት የአሰቦት ገዳም መነኰሳት የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፤የወረዳው አስተዳዳሪ “ለቃችሁ ውጡ” በማለት እገዛ አላደረገም

ከጥቅምት 7 ጀምሮ በየምሽቱ ከታጣቂዎቹ ጋራ የተኩስ ልውውጥ በማድረግ ላይ ናቸው፤ ታጣቂዎቹ፣“የኦነግ ወታደሮች ነን”ቢሉም ተከፋይ ሁከተኞች ሊኾኑ እንደሚችሉ ተነግሯል፤ የወረዳው አስተዳደሪ፣ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው በዞኑ የተላለፈለትን ትእዛዝ አልፈጸመም፤ በሶማሌ ክልል ወሰን በኩል የመከላከያ ድጋፍ ቢጠየቅም ኦሮሚያ መፍቀድ አለበት፤ተብሏል፤ አንዱ በሌላው ሲያመካኝ፣ የግንቦት 1984 ዐይነቱ ወረራና እልቂት እንዳይደገም አስግቷል፤ በስብሰባ ላይ ያለው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣በአስቸኳይ የኦሮሚያን መንግሥት እገዛ ሊጠይቅ ይገባል፤ ፓትርያርኩ በመክፈቻቸው እንዳሉት፣ በተጽዕኖና በማፈናቀል ከማዳከም ስልቶች አንዱ ነው፤ ከፍትሕና ከጸጥታ አካላት ጋራ በመቀናጀት፣ ጥቃቱ ከወዲሁ ለማምከን መፍጠን ያስፈልጋል፤       ***
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 31 አጀንዳዎችን በማጽደቅ መወያየቱን ቀጥሏል

ከተደጋጋሚ ጥሪ በኋላ በምልዓተ ጉባኤው የተገኙትን ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስን በይቅርታ ተቀብሏል፤የሀገረ ስብከት ምደባ ይሰጣቸዋል፤ የአእላፋት ድምፅ የካህናትና የምእመናን ተናሥኦት ኅብረት ተወካዮች፣ በመሪ ዕቅድ ትግበራ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ለውጥ እንቅስቃሴያቸውን ቀርበው እንደሚያስረዱ ይጠበቃል፤   *** ከትላንት በስቲያ የተጀመረውና ሦስተኛ ቀኑን የያዘው፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ 31 አጀንዳዎችን በማጽደቅ ስብሰባውን ቀጥሏል፤ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን የመክፈቻ ንግግር ካደመጠ በኋላ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 37ኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ የአቋም መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ ላይ በመወያየት አጽድቋል፡፡ ከ27 ዓመታት በኋላ በተመለሰው ሲኖዶሳዊ አንድነት፣ የአህጉረ ስብከት ድልደላ እና የብፁዓን አባቶች ምደባ ማካሔድን በተመለከተ በአጀንዳ ተ.ቁ(3) በመያዝ፣ የድልደላና ምደባ ምክረ ሐሳቦችን ተቀብሏል፤ ጉዳዩን አደራጅተው ለምልዓተ ጉባኤው የሚያቀርቡ የብፁዓን አባቶች ኮሚቴም ሠይሟል፤ በድልደላው፣ ከሀገር ውስጥም ኾነ ከውጭ አህጉረ ስብከት በተደራራቢነት የተያዙት አህጉረ ስብከት ተነጣጥለው ምደባ እንደሚካሔድባቸው፤አዲስና ተጨማሪ የአህጉረ ስብከት አደረጃጀትም እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡ ከቀረቡትም ምክረ ሐሳቦች ውስጥ፤ ከሀገር ውስጥ በተደራራቢነት የተያዙ 8 አህጉረ ስብከት ራሳቸውን ችለው
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርኩ: “ከማኅበረ ቅዱሳን አልታረቅሁም፤ እስከምሞት እረግመዋለሁ” አሉ፤ ብፁዕ አባ ማርቆስም፣ “እኔም እስከሞት ከጎንዎት ነኝ” አሏቸው

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ እንዳልታረቁና እስከሞት ድረስ እንደሚረግሙት ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተናገሩ፡፡ ፓትርያርኩ ይህን የተናገሩት፣ ብፁዕ አባ ማርቆስ ከምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስነት እንዲነሡ የቀረበባቸውን አቤቱታ ለመመልከት በጀመረበት ወቅት ነው፡፡ ብፁዕ አባ ማርቆስ፣ ከምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እንዲነሡ ካህናቱና ምእመናኑ ስላቀረቡት አቤቱታ የተያዘው አጀንዳ ወደ ነገ እንዲተላለፍላቸው ቢጠይቁም ምልዓተ ጉባኤው ሳይቀበላቸው ጉዳዩን ማየት ይጀምራል፡፡ ሊቀ ጳጳሱም ወደ ውጭ ወጥተው ከአፍታ ቆይታ በኋላ እንደተመለሱ በድንገት፣ “ሰበር ዜና- ለቀቅሁላችኹ፤ እንደፈለጋችሁ አድርጉት” በማለታቸው አጀንዳው በአጭሩ የተቋጨ መስሎ ነበር፡፡ ኾኖም ስብሰባውን በርእሰ መንበርነት የሚመሩት ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳሱን ተከትለው በሰጡት ያልተጠበቀና ያልተገባ አስተያየት ምክንያት ጉዳዩ ወደ ኋላ ይመለሳል፡፡ ሊቀ ጳጳሱ፣ አንሡኝ ብለው ካመለከቱ በኋላ ፓትርያርኩ፥ “ማኅበረ ቅዱሳን እንዳስነሣቸው እወቁ፤ ሌላም ሰው ብንመድብ እንዲሁ ጫና ፈጥሮ እንደሚያስነሣችሁ እወቁ” በማለታቸው ኹኔታው አነጋግሯል፤ ራሳቸው ሊቀ ጳጳሱ፣ አንሡኝ እያሉና ጥያቄውም የብዙኀን ምእመናን ኾኖ ሳለ፣ ማኅበሩን ለይቶ መውቀስ አግባብ እንዳልኾነ ፓትርያርኩ በምልዓተ ጉባኤው ቢነገራቸውም፣
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ከምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ተነሡ!

ከቀትር በፊት አጀንዳው መታየት እንደ ጀመረ፣ “ሰበር ዜና: አንሡኝ፤ ለቀቅሁላችሁ፤ እንደፈለጋችሁ አድርጉት” ብለው ቢጠይቁም ፓትርያርኩ፣ አይነሡም፤ በማለታቸው አነጋግሮ ነበር፤ ካህናቱና የምእመናኑ አቤቱታ ቀርቦ ተሰምቷል፤ ለ13 ጊዜያት ያህል ወደ መንበረ ፓትርያርኩ በመመላለስ የተንገላቱበት ጉዳይ ምላሽ አግኝቷል፤ ፓትርያርኩ፣ መነሣታቸውን ቢቃወሙም፣ ሓላፊነት ይወስዳሉ ወይ? ተብለው ሲጠየቁ ፈቃደኛ አልኾኑም፤ የሀገረ ስብከቱን ምእመናን አንድነት ለመጠበቅ ትኩረት እንዲሰጥ ምልዓተ ጉባኤው አሳሰበ፡፡
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የመሪ ዕቅድ ትግበራ ጽ/ቤት ማቋቋም ወይስ በሌላ ጥናት ስም የቤተ ክርስቲያንን ችግር ማባባስ? በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባው የፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ መክፈቻ ንግግራቸው፣ የቤተ ክርስቲያናችንን አስተዳደራዊ ችግር መፍታት የምንችለው፣ በመሪ ዕቅድ በመምራትና መልካም አስተዳደርን በማበልጸግ እንደኾነ፤ ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ ሊኖር እንደማይችል አስገንዝበዋል፡፡ የመሪ ዕቅድን አስፈላጊነት በዚህ ደረጃ ማስገንዘባቸው መልካም ኾኖ ሳለ፣ ራሳቸው ባቋቋሙት ኹለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሰባት ከፍተኛ ባለሞያዎች ባሉበት ኮሚቴ የተዘጋጀ፣ ለምልዓተ ጉባኤው በተደጋጋሚ ቀርቦ የተገመገመና የጸደቀ፣ የትግበራ ጽ/ቤት ተቋቁሞለትና በጀት ተመድቦለት እንዲተገበር የወሰነበት መሪ ዕቅድ እያለ፣ “ሌላ ተጠንቶ ለቀጣዩ ስብሰባ እንዲቀርብ” ማለታቸው፣ ትግበራውን በጉጉት ለሚጠባበቁ ምእመናንና ካህናት ትልቅ ጥርጣሬን የሚፈጥር ነው፡፡ ቅዱስነታቸው በንግግራቸው፣ “አንገብጋቢና ወሳኝ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች” በሚል ለዘረዘሯቸው፥ ምእመናን ፍልሰት፣ የሰው ኃይል አጠቃቀምና የሀብት አያያዝ ችግር፣ የሐዋርያዊ ተልእኮ መዳከም እልባት የሚሰጥ መሪ ዕቅድ ነበረ፤ አለ!! በሌላ ጥናት ስም መፍትሔውን በማዘግየት የቤተ ክርስቲያንን ችግር ማባባስ፣ ለህልውናዋ መቀጠልና ለዕድገትዋ መስፋፋት የሚቆረቆሩ ምእመናንን ትዕግሥት የሚፈታተንና የሚያስቆጣ ነው፡፡ በመሪ ዕቅድ ትግበራ ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ለውጥ የምንነሣበት ጊዜ አሁንና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

“የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ ችግር ለመፍታት በመሪ ዕቅድ ከመመራት ውጪ አማራጭ ሊኖረን አይችልም፤”/የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የቅዱስ ሲኖዶስ መክፈቻ

“ሰፊና ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል መሪ ዕቅድ፣ ጊዜ ሳይወስድ በፍጥነት ተሠርቶ ለቀጣዩ ስብሰባ እንዲቀርብ ዛሬ መወሰን ይኖርብናል፤” – ሌላ ይዘጋጅ ከማለት ተዘጋጅቶ የጸደቀውና እንዲተገበር በተወሰነው ለምን አይሠራም??? “ቤተ ክርስቲያናችን የሚደርስባትን ጥቃት በልብዋ አምቃ ለማለፍ ብትሞክርም፣ ድፍረቱ ከቀን ቀን እየባሰ፣ ዕልቂቱም እየጨመረ በመሔዱ ልትታገሠው ከማትችልበት ደረጃ እየደረሰ ነው፤” “ምእመናንና ካህናት በነጻነት የማስተማር፣ የማምለክና የመኖር ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን በሚቃረን አኳኋን በሚደርስባቸው ተጽዕኖ ከቀዬአቸው እየተፈናቀሉ እንዲወጡና ሃይማኖቱ እንዲዳከም የሚደረጉ ደባዎች እየተበራከቱ ነው፤” “በቤተ ክርስቲያንና በአማንያን ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት አስቀድሞ ማምከን የሚቻልበት ጠንካራ የግንኙነት መረብና የቅድመ ትንበያ አሠራር መቀየስ የግድ ይላል፤” “በኢትዮጵያ እና በኤርትራ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖር የጋራ ኮሚሽን አቋቁመን መንቀሳቀስ ይኖርብናል፤” *      *     * መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ራብዓይ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና በክልል ትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨውና ደቡባዊ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የዘገየው የመሪ ዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ ጽ/ቤት ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ አጠቃላይ ጉባኤው ጠየቀ

37ኛ ዓመታዊ ስብሰባውን ባለ41 ነጥቦች የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ፡- የውይይት መድረኩ ቢዘገይም በጥሩ ኹኔታ ተካሒዷል፤ተጠናክሮ እንዲቀጥል አመለከተ፤ የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ(ስጋት ትንተና) መከላከል መምሪያ በጠ/ጽ/ቤቱ እንዲደራጅ፤ በላሊበላ አብያተ መቃድስ ጉዳይ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ ከመንግሥት ጋራ እንዲመክር አሳሰቧል፤ በሲኖዶሳዊ አንድነቱ የተመለሱት የውጭ አብያተ ክርስቲያን የ27 ዓመት ሪፖርት ቀርቧል፤ አስተዳደራዊ አንድነቱ፣ በሕግ የበላይነትና በአሠራር ማሻሻያ እንዲጠናከር አመልክቷል፤ ሕገ ቤተ ክርስቲያንና ቃለ ዐዋዲው ተጣጥመውና ወቅቱን አገናዝበው እንዲሻሻሉ መክሯል፤ በግፍ የተገደሉት የጅግጅጋ ኦርቶዶክሳውያን፣ ሐውልተ ስምዕ እንዲቆምላቸው ጠይቋል፤ ፀረ ሙስና አካል ራሱን ችሎ ሊቋቋም እንደሚገባ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፤ ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የአጠቃላይ ስብሰባው የውይይት መርሐ ግብር መራዘም ጉባኤተኛውን አሳዘነ፤ ከወዲሁ የመሰላቸት መንፈስ እየታየ ነው

መርሐ ግብሩ ወደ ጉባኤው መጠናቀቂያ ዕለት መራዘሙ ሲገለጽ አዳራሹን ለቀው የወጡ አሉ፤ ቀጣይ ህልውናችንን በሚወስኑ ጉዳዮች ውይይት እንደሚኖር በሊቃነ መናብርቱ ተጠቁሞ ነበር፤ አጠቃላይ ስብሰባ እንደመኾኑ፣ ከሪፖርት ባሻገር በዐቢይ አጀንዳ የምር መነጋገር ይጠበቅበታል፤ ገና ለገና፣“እነእገሌ ያደራጁት ቡድን አለ” በሚል ውይይትን መሸሽ ጉባኤተኛውን መናቅ ነው፤ “ያለውይይት እርባና የለውም፤በዝግ አዳራሽ ውስጥ ከፈሩት በዐደባባይ ይጋቱታል፤”/ልኡካኑ/     *** የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 37ኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ፣ ለቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ ለውጥና ለተጋረጠባት ወቅታዊ አደጋ ትኩረት ሰጥቶና በጥብቅ ተወያይቶ የጋራ አቋም እንደሚይዝና ለቅዱስ ሲኖዶስ የውሳኔ ሐሳብ እንደሚያቀርብ ቢጠበቅም፣ የውይይት መርሐ ግብሩ ወደ ጉባኤው መጠናቀቂያ ዕለት መራዘሙ ብዙዎቹን ተሳታፊ ልኡካን በእጅጉ አሳዛነ፡፡ዓመታዊ ስብሰባው፣ ትላንት ሰኞ፣ ጥቅምት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ሲከፈት፣ የአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ርእሰ መንበር በኾኑት በቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ምክትል ሰብሳቢ በኾኑት በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ እና በፕሮግራም አስተዋዋቂው፣ ውይይት እንደሚኖርና መወያየት የሚያስፈልግባቸውን አንገብጋቢ ጉዳዮች በንግግሮቻቸው በመጠቆማቸው፣ ተሳታፊ ልኡካኑ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የ37ኛው አጠቃላይ ጉባኤን ምክክርና ግምገማ የሚሹ ወቅታዊ ጉዳዮች – ከቅዱሳን ፓትርያርኮች የጉባኤ መክፈቻ ቃለ በረከት

“ከቤተ ክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ አስተዳደር ጀምሮ ከየአህጉረ ስብከቱ የሚቀርበውን ሪፖርት በማድመጥና እያንዳንዱን ተግባር በመገምገም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተጨባጭ ኹኔታ የሚታወቅበት ጉባኤ ነው፡፡” …ዓመታዊ ጉባኤያችን፣ የጉባኤውን ሪፖርት አንብበንና ሰምተን የምንለያይበት ብቻ ሳይኾን፣ የጋራ ዕቅድ የምናቅድበትና የምንወያይበት ስብሰባ መኾን ይኖርበታል፡፡ ስለኾነም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ አስተዳደር ጀምሮ ከየአህጉረ ስብከቱ የሚቀርበውን ሪፖርት በማድመጥ፣ አንዱ ከሌላው ልምድ የሚቀስምበት፤ እያንዳንዱ ተግባር የሚገመገምበት፤ በጉባኤው የተገኙ ልምዶች ተቀምረው ተቋማዊ ቅርጽ ይዘው የቤተ ክርስቲያኒቱ ተጨባጭ ኹኔታ የሚታወቅበት ጉባኤ በመኾኑ፣ ጉባኤውን በሠመረ፣ በሰከነና በተረጋጋ መንፈስ በማካሔድ፣ ለአሁኑ ትውልድ የሚመጥን ዕቅድ በማዘጋጀት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅጣጫ የሚያዝበት ታሪካዊ ጉባኤ መኾን ይችል ዘንድ ሁላችሁም የጉባኤው ተሳታፊዎች የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ አባታዊ መልእክቴን ሳስተላልፍ፣ ልዑል እግዚአብሔር በረድኤቱ እንዲጠብቀን በመጸለይ ነው፡፡ በድጋሜ ከ27 ዓመት የስደት ዘመን በኋላ በእግዚአብሔር ቸርነት እንኳንም በዐይነ ሥጋ ለመገናኘት አበቃን፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ጉባኤያችንና ሀገራችን ኢትዮጵያን ይባርክ፤ ይቀድስ፤ አሜን፡፡ አባ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ *** “ቤተ ክርስቲያን ስለተጋረጠባት አደጋ የምንመክርበት ጉባኤ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በሰፊ መሪ ዕቅድ የታገዘ አስተዳደራዊ ለውጥ ለቤተ ክርስቲያን ቀጣይ ህልውና ወሳኝ እንደኾነ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ፤“ወቅቱ የለውጥ ነው፤ባለው የድንግዝግዝ አሠራር ከቀጠልን አደጋው የከፋ ነው”/ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ/

የመንበረ ፓትርያርክ ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 37ኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ተጀመረ፤ ከ61 የሀገር ውስጥ እና የውጭ አህጉረ ስብከት የተውጣጡ ከአንድ ሺሕ በላይ ልኡካን ተሳታፊዎች ናቸው፤ የቅዱስ ሲኖዶስ መዋሐድና የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ አንድነት በተፈጸመበት ማግሥት የሚካሔድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ነው፤ የአስተዳደር ለውጥን ሊያረጋግጥና ሊያግዝ የሚችል፣ የሀገራችንን ወቅታዊ ኹኔታ ያገናዘበ ውይይት ይጠበቃል፤ ለዚህ ታላቅ ጉባኤ ሐሳቦች ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘመኑን የዋጀ ውሳኔና በተግባር ሊዳሰስ የሚችል የሥራ መመሪያ ከቅዱስ ሲኖዶስ ይጠበቃል፤ በሰፊ መሪ ዕቅድ በታገዘ የአሠራር ፖሊሲዎችና ደንቦች ትግበራ የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ለውጥ በወሳኝ መልኩ ማምጣት ይቻላል፤ ለውጡን ማምጣት ሳንችል ቀርተን ባለው የድንግዝግዝ አሠራር ከቀጠልን አደጋው ለቤተ ክርስቲያናችን የከፋ ሊኾን እንደሚችል መዘንጋት ያለብን አይኾንም፡፡     ***   …የዘንድሮውን 37ኛ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ልዩ የሚያደርገው፣ ከ27 ዓመታት በኋላ በውጭ አገራት የነበሩት ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገራቸው ተመልሰው፣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት እና የቅዱስ ሲኖዶስ መዋሐድ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በቅዱስ ፓትርያርኩ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ያለው አለመግባባት በውይይት ተፈታ

ቅዱስነታቸው፣ ከሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ጋራም ተወያዩ፤ ውይይቱን ያመቻቸው ለአባቶች ዕርቀ ሰላም የተንቀሳቀሰው ኮሚቴ ነው፤ ሒደቱ የሚጠናቀቅበት የራት ምሽት፣ በመንበረ ፓትርያርኩ ይካሔዳል፤ ለለውጥ ያላደለው የአ/አበባ ሀ/ስብከትስ፣መሰል ጥረት እየጠበቀ ይኾን? ††† በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር አገልግሎቱን በሚፈጽመው በማኅበረ ቅዱሳንና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መካከል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት በውይይት መፈታቱ ተገለጸ፡፡ ለሲኖዶሳዊው የአባቶች ዕርቀ ሰላም የተንቀሳቀሰው ኹለተኛው ዙር የሰላምና አንድነት ዓለም አቀፍ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ አባላት፣ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩንና የማኅበሩን የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት በተናጠል ያነጋገሩ ሲኾን፤ ትላንት ኀሙስ፣ ጳጉሜን 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት፣ የማግባባት ሒደቱ የሚቋጭበት የጋራ የራት መርሐ ግብር በቅዱስነታቸው ጽ/ቤት እንደሚከናወን ታውቋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ 6ኛው ፓትርያርክ ኾነው ከመሠየማቸው በፊት በሊቀ ጳጳስነት በመሯቸው የሰሜን አሜሪካ እና የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም አህጉረ ስብከት እንዲሁም ከተሾሙም በኋላ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የሰሜን ሸዋ ሀ/ስብከት አስተዳደራዊ ችግሮቹን እየፈታ ነው፤ ለሶማሌ ተጎጅዎች 100ሺሕ ብር ረዳ፤ ተጨማሪ ለማሰባሰብ ኮሚቴ አቋቋመ

አባቴ፤ ልጄ የሚባባሉት ሁለቱ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት አባቶች፤ አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም(ግራ)፤ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ሊቀ ጳጳስ(ቀኝ) የቤተሰባዊ ትስስርና የዘመድ አዝማድ መሳሳብ ችግርን የማስተካከል ርምጃ ወሰደ፤ ሞያዊ ግምገማና ሥልጠና በማካሔድ፣ ሁሉንም ወረዳዎች ያማከለ ምደባ አደረገ፤ አንጋፋና በዕድሜ ለጡረታ የደረሱ 32 የጽ/ቤት እና የወረዳ ሠራተኞችን አሰናበተ፤ በችሎታ፣ በሥራ ልምድና በሥነ ምግባር ላይ በተመሠረተ ምደባና ዝውውር ተካ፤ ሀ/ስብከቱን በዕቅድ የመምራቱ ሥራ፣የጽ/ቤቱን ተግባርና በጀት በማዘጋጀት ጀመረ፤ ስብከተ ወንጌልንና ዕቅበተ እምነትን በሥልጠናዎች በማጠናከር ቅሬቶችን ያጸዳል፤ ††† የአረጋዊው ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሕይወት ታሪክ ዝግጅት እንዲቀጥል አዝዟል፤ “ለዝግጅቱ ሕጋዊ ውክልና ሰጥተውኛል፤”ባዩ ግለሰብ ከጽ/ቤቱጋ እየተወዛገበ ነው፤ ከ250 እስከ 450ሺ ብር እንዲከፈለው ቢጠይቅም ለማስገምገም ፈቃደኛ አይደለም፤ ውሉና ክፍያው ክብራቸውን ጠብቆና ሕግን ተከትሎ እንዲፈጸም ጽ/ቤቱ አሳስቧል፤ የአረጋዊውን አባትና የብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን ወዳጅነት ለማናጋት እየሠራ ነው፤ “ዝቅ የተደረጉ መዝባሪዎችንና የመናፍቃን ተላላኪዎችን ቢያሰለፍም አይሳካለትም፤” ††† በአድሏዊ አመራርና አሠራር ሳቢያ በሚቀርቡ አቤቱታዎች ሲታመስ የቆየው የሰሜን ሸዋ ሀ/ስብከት፣ በተጠናቀቀው በጀት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

መከላከያ ሚኒስቴር: በሶማሌ ክልል ተጎጂዎችን ማረጋጋትና መልሶ ማቋቋም የቤተ ክርስቲያንን ጥረት እንደሚያግዝ አስታወቀ

ጠቅ/ሚኒስትሩም፣ አስተማሪ የሕግ ተጠያቂነት እንደሚረጋገጥ አስታወቁ፤ መከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ፣ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ ተወያዩ፤ የርዳታ አቅርቦቱን፥ በትራንስፖርትና በሰው ኃይል እንዲሁም በእጀባ ያግዛል፤ ለምእመኑ የኑሮና የመንቀሳቀስ መብት ትኩረት እንዲሰጥ ፓትርያርኩ ጠየቁ፤ ††† “በማረጋጋቱ ቤተ ክርስቲያንም ትልቁን ሚና እንድትወጣ እንሻለን፤”/ሚኒስትሩ/ “ያልደረስንባቸው ቦታዎች ስላሉ አሁንም ከለላ እንፈልጋለን፤”/ሥራ አስኪያጁ/ በተገደሉትና በተጎዱት የካሳ ጥያቄ የሚቀርብበት ኹኔታ ስለመኖሩ ተጠቆመ፤ የዐቢይ ኮሚቴ፣ቀጣይ ዙር የጊዜያዊ ርዳታ አቅርቦት ነገ ወደ ክልሉ ያመራል፤ ††† በኢትዮ ሶማሌ ክልል በተፈጸመ አረመኔያዊ ግድያ፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ የተጎዱባትን ካህናትና ምእመናን ለመርዳትና መልሶ ለማቋቋም እንዲሁም መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማስቀጠል ቤተ ክርስቲያን ለምታደርገው ጥረት፣ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የበኩሉን ድጋፍና እገዛ እንደሚሰጥ፣ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ አስታወቁ፤ ሕዝቡን በማረጋጋትና ሰላም በማስፈን በኩልም፣ ቤተ ክርስቲያን ቀዳሚ ሚናዋን እንድትወጣ ጠየቁ፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩና ባልደረቦቻቸው፣ ዛሬ ዓርብ፣ ነሐሴ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ረፋድ፣ በመንበረ ፓትርያርኩ ተገኝተው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ የተወያዩ ሲኾን፤ ቤተ ክርስቲያን የምታጓጉዘውን ጊዜያዊ ርዳታ፣ ተጎጅዎችን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የድሬዳዋ ሀ/ስብከትና አጥቢያዎች: ለሶማሌ ተጎጂ ቤተሰቦችና አብያተ ክርስቲያን መንግሥት እንዲክስና አስተማማኝ ጥበቃ እንዲያደርግ ጠየቁ፤ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ረዱ

263ሺሕ ብር በጥሬ ገንዘብ፣ ከ300ሺሕ ብር በላይ የምግብና ቁሳቁስ ርዳታ አደረጉ፤ ሀገረ ስብከቱ እና 11 አጥቢያዎች፤ የሰንበት ት/ቤቶች እና ማኅበረ ቅዱሳን ተሳተፉ፤ ልግስናና ርኅራኄን ለምታስተምር፣ምላሹ ግድያና ማቃጠል መኾኑ በእጅጉ አሳዝኖናል፤ በሌሎች ክልሎች ፍትሕ ያጣው የግፍ ድርጊት በሶማሌም መደገሙ የበደል በደል ነው፤ ††† ለካህኑና ምእመኑ፣የዜግነት መብትና የሕይወት ዋስትና መንግሥት ጥበቃ ያድርግ፤ በጭካኔ ግድያ ለሞቱ ወገኖች ቤተሰቦች፥ መንግሥት የሕይወት ካሳ ሊከፍል ይገባል፤ ለተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያንም ካሳ ተከፍሎ በአስቸኳይ ዳግም እንዲታነፁ ይደረግ፤ የሕይወትና የንብረት ጥፋት አስፈጻሚዎችና ፈጻሚዎች ተለይተው ለፍርድ ይቅረቡ! ††† በሌሎች ክልሎች ተገቢ ፍትሕ ያልተሰጠበት የንጹሐን ካህናትና ምእመናን ግድያና የቤተ ክርስቲያን መቃጠል በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልም መደገሙ፣የበደል በደል እንደኾነ የገለጹ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ያሉ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን፣ መንግሥት፥ አስፈጻሚና ፈጻሚ ወንጀለኞችን ለይቶ ለፍርድ እንዲያቀርብ፤ ለካህናትና ምእመናን የሕይወት ዋስትናና የመንቀሳቀስ የዜግነት መብትም አስተማማኝ ከለላና ጥበቃ እንዲያደርግ በአጽንዖት ጠየቁ፡፡ ለተጎጅዎች በመድረስ ቀዳሚ የኾነው ሀገረ ስብከቱ፣ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ለአስተዳደር ጉባኤው በሰጡትና ለአጥቢያ አብያተ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለኢትዮ ሶማሌ ተጎጅዎች ተከታታይ የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎች ይደረጋሉ፤ የበረከት መታሰቢያ ካርዶች በስርጭት ላይ ናቸው

ከመጀመሪያው እንቅስቃሴ፣ ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ በተስፋ ሰነድ ተገኘ፤ ከ50 እስከ 500 ብር ያሉ 80ሺ የመታሰቢያ ካርዶች በስርጭት ላይ ናቸው፤ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፣ የካርዶቹን ሥርጭትና ሽያጭ ያስተባብራሉ፤ በሙሉ ለሽያጭ ሲውሉ፣ 11ሚ. ብር ያህል ገቢ እንደሚያስገኙ ተጠቆመ፤ የአልባሳት ርዳታውን፣በየአጥቢያው የማሰባሰቡ ሒደት ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ በአካልም ተገኝቶ ተጎጅዎችን ማበርታት እንደሚያስፈልግ ሊቀ ጳጳሱ አሳሰቡ፤ “ክልሉም፣የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያን በበጀቱ የማሠራት ሓላፊነት አለበት፤” /መ/ር ብርሃኑ አድማስ/ ††† በኢትዮጵያ ሶማሌ ሀገረ ስብከት በተፈጸመው አሠቃቂ ግድያና ውድመት የተጎዱ ካህናትን፣ ምእመናንንና አብያተ ክርስቲያንን በዘላቂነት ለማቋቋም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በተሠየመው ዐቢይ ኮሚቴ ሥር የሚንቀሳቀሰው የቅስቀሳና ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ፣ ከመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብሩ ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ በተስፋ ሰነድ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ ኮሚቴው፣ ትላንት እሑድ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሔደው የገቢ ማስገኛ መርሐ ግብር፣ ከ250 ያላነሱ ለጋሾች የተገኙ ሲኾን፣ በተሠራጨው የተስፋ ሰነድ(promissory note) ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ ለመለገስ ቃል
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

መንግሥት የሀገርን አንድነትና የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ጠየቀ

ከመጠን ያለፈ ትዕግሥት፣ የሀገሪቷን አንድነትና የዜጎቿን ደኅንነት በከባዱ እየሸረሸረ ነው፤ በዜጎችና በቤተ ክርስቲያን ላይ፥አሠቃቂ፣ አሳፋሪና ዘግናኝ የጭካኔ ድርጊት እየተፈጸመ ነው፤ በሶማሌ፣ በባሌ፣ በሻሸመኔና በጣና በለስ የተፈጸመው ድርጊት፥ከኢአማኒ እንኳ አይጠበቅም፤ በማንም ላይ እጇን ባልጫነችው ቤተ ክርስቲያን ላይ የኾነባት፣ የእናት ጡት ነካሽ ያሰኛል፤ 9 አብያተ ክርስቲያን ተቃጠሉ፤ 5 ካህናት ተገደሉ፤ የምእመኑ ቁጥር በውል አልታወቀም፤ ኢሰብአዊ በኾነ አሠቃቂ የጭካኔ ድርጊት፣ በጽኑ የተደበደቡ 7 ካህናት ሕክምና ላይ ናቸው፤ ††† ለርዳታውና ለመልሶ ማቋቋሙ፣ኢትዮጵያዊ ኹሉ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ይረባረብ፤ ስላለፈው እንከን ስናቀነቅን የወደፊቱ ዕድል እንዳያመልጠን በፍቅር እና በይቅርታ እንለፍ፤ የሃይማኖት መሪዎች፣ሽማግሌዎች፣ምሁራንና አርቲስቶች ያለመታከት ሌት ተቀን ይሥሩ፤ ወጣቶች፥ በስሜት ተገፋፍቶ በወገን ላይ መጨከንን፣ ከዛሬ ጀምሮ እርም ብላችሁ አቁሙ፤ መንግሥት፥ የዜጎችን የመኖር ዋስትና፣ የሃይማኖትን ልዕልና በማስጠበቅ ጸጥታ ያስከብር፤ ገደብ የለሽ ነፃነትና መብት ብቻ ሳይኾን፣የሕግ የበላይነትን ማስፈንና ሥርዐትን ማስጠበቅ! ††† ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ወቅታዊ ኹኔታ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የአ/አበባ ሀ/ስብከት እንዘጭ እንቦጭ! በመዝባሪነቱ የተነሣው ኤልያስ ተጫነ ለ3ኛ ጊዜ በሒሳብና በጀት ሓላፊነት ተመደበ፤ ለውጥ ፈላጊዎች ሁሉ ሊቃወሙት ይገባል

ባለፈው ሰኞ ከተመደቡት 14 የዋና ክፍል ሓላፊዎች አንዱ ነው፤ የሒሳብና በጀት አሠራሩ፣ የሀ/ስብከቱ ለውጥ ዋነኛ ማሳያ ነበር፤ ለውጡን የማያሳካ፣ ግልጽነትና አርኣያነት የጎደለው ምደባ ነው፤ ከጉድና ጉደኞች እንዳይወጣና እንዳይለወጥ የተረገመ መስሏል፤ ††† አጥቢያዎችን፣ የ112 ሚሊዮን ብር የፈሰስ ባለዕዳ ያደረገ ነው፤ ደመወዝ ለማጸደቅ የወር ጭማሪውን በጉቦኝነት ሲበላ ኖሯል፤ የዘመናዊ ቤቶችና ፎቅ፣የባንክ አክስዮንና ግሮሰሪ ባለቤት ነው፤ ለውጥ ፈላጊ ካህናትና ምእመናን ሁሉ፣ሊቃወሙት ይገባል! ††† ቤተ ክርስቲያናችን በአስተዳደር ስለሚያስፈልጋት የለውጥ አመራር፣ በየስብሰባው እየወተወቱና መግለጫ እያወጡ በተግባር ግን አፈጻጸሙን ማደናቀፍ፤ በቀኖናም በሕግም ሊጠየቁና ሊቀጡ ስለሚገባቸው ግለሰቦች ሕጸጽና ጥሰት በዐደባባይ እየበየኑ በስውር ግን፣ በጎጠኝነትና በጉቦኝነት መሾምና መሸለም ቤተ ክህነታችን የተዘፈቀበት ነባር ተቃርኖ(አያዎ) ነው፡፡ ለችግሩ በዋና ማሳያነት ለሚጠቀሰው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ የዋና ክፍል ሓላፊዎችን ለመመደብ፣ ሰሞኑን በመንበረ ፓትርያርኩ የታየው መራኰትና መደራደር ይህንኑ መስተፃርር የሚያስረገግጥ ነው፡፡ በጅግጅጋና አካባቢው የነውጠኞች አሠቃቂ ግድያና ውድመት፣ ቤተ ክርስቲያን ሐዘኗን ገልጻ ባወገዘችበት ባለፈው ሳምንት ሰኞ የተካሔደው የቋሚ ሲኖዶሱ ስበሰባ፥በአስተዳደር በደል፣ የአሠራር ጥሰትና ሌብነት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በመንበረ ፓትርያርኩ ማረፊያቸው ጠየቁ፤ የዕርቀ ሰላሙ ብሥራት በክልል ከተሞች እንዲቀጥል አደራ አሉ

ቅዱስነታቸው፣ ከአሜሪካ የመልስ ጉዞ ወቅት፥“ትጠይቀኛለኽ ወይ? ሥራ ይበዛብሃል፤ ማን ይጠይቀኛል አኹን? እንዴት ትጠይቀኛለህ?” ሲሉ ጠ/ሚኒስትሩን ጠይቀዋቸው ነበር፤ ቅዱስነታቸው፥ ከመናገር አብዝተው ሲታቀቡ ቢስተዋልም ይነጋገራሉ፤ ከቅርብ ልዩ አገልጋይ(ረዳት) ጀምሮ በግል ሐኪምና ነርስ ክትትል ይደረግላቸዋል፤ እንደሚጠይቋቸው ቃል የገቡላቸው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ በመንበረ ፓትርያርኩ ማረፊያቸው ተገኝተው አይተዋቸዋል፤ ቤተ ክርስቲያን፥ ለአገር የመጸለይና የማስታረቅ ሓላፊነቷን እንድትወጣ፤ በሰላም፣ በልማትና በማኅበራዊ ጉዳይ መንግሥትንና ሕዝብን እንድታግዝ አደራ አሉ፤ ††† ዶ/ር ዐቢይ፥ የኢትዮ ሶማሌ ክልልን ጸጥታ ጉዳይ ሲከታተሉ መሰንበታቸውን ጠቅሰው፣ በመግደል ጸጸት እንጅ ማሸነፍ እንደሌለ ተናግረዋል፤ የተገንጣዮችን ሐሳብና አሠቃቂ ድርጊት ሲቃወሙም፣ “ኢትዮጵያ በዋዛ ፈዛዛ አትበተንም፤ ሰው ኾኖ የማይሞት የለም፤ ባልተገባ ጊዜ መግደል ደግሞ ውድቀት ነው፤” ብለዋል፤ አብረዋቸው ቅዱስነታቸውን የጠየቁት የክልል ትግራይ ም/ል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ ሲኖዶሳዊ ዕርቀ ሰላሙ፣ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና መተባበር አብነታዊ እንደኾነ ገልጸዋል፤ በጥየቃቸው ደስታቸውን የገለጹት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ትኩረቱ፥ ለቤተ ክርስቲያን ታሪካዊነት፣ ሥራና ዕድገት ቀጣይነት ጥሩ ዕድል እንደኾነ ጠቅሰው አመስግነዋል፤ ††† ጠቅላይ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዐቢይ ኮሚቴ: ለሶማሌ ሀ/ስብከት ተጎጅዎች የመጀመሪያ አስቸኳይ ርዳታ ነገ ያደርሳል፤ ምእመናኑን ያጽናናል፤ ጉዳቱን ያጠናል

ዐቢይ ኮሚቴው፣ በሦስት ንኡሳን ኮሚቴዎች ተዋቅሯል፤ የዘላቂ ድጋፍ የገንዘብ ርዳታ የሚሰበሰብበት አካውንት በንግድ ባንክ ከፍቷል፤ አህጉረ ስብከት፣ ግለሰቦች፣ መንግሥታዊ የኾኑና ያልኾኑ አካላት እንዲተባበሩ ጠየቀ፤ ††† የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000254922898 አራት ኪሎ ቅርንጫፍ ††† በኢትዮጵያ ሶማሌ ሀገረ ስብከት፣ በጅግጅጋና የአካባቢው ዞኖች፣ በተፈጸመው አሠቃቂ ግድያና የንብረት ውድመት ጉዳት ለደረሰባቸው ካህናት፣ ምእመናንና አብያተ ክርስቲያን፣ ድጋፍ የሚያደርግና ርዳታ የሚያሰባብስብ ዐቢይ ኮሚቴ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ የተቋቋመ ሲኾን፣ የመጀመሪያውን አስቸኳይ ርዳታ፣ ነገ ቅዳሜ ረፋድ እንደሚያደርስ ተገለጸ፡፡ በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ የሚመራውና አምስት አባላት ያሉት የዐቢይ ኮሚቴው አካል፣ ነገ ቅዳሜ፣ ነሐሴ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጅግጅጋ በመብረር፣ የተሰባሰቡ ደረቅ ምግቦችንና የታሸገ ውኃ በረኀብና ጽም ቀናትን ላስቆጠሩ ካህናትና ምእመናን እንደሚያደርስ ታውቋል፡፡ የምድቡ ዋና ተልእኮ፣ በጅግጅጋና የአካባቢው ዞኖች በተፈጸመው ግድያና የንብረት ውድመት የደረሰውን ጉዳት መጠን አጣርቶና ለይቶ ሪፖርት ማቅረብ ሲኾን፤ ሕዝበ ክርስቲያኑንም የማጽናናት ሓላፊነት እንደተሰጠው በምደባ ደብዳቤው ተገልጿል፡፡ የሀገረ ስብከቱ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ጠቅላይ ቤተ ክህነት: ለተጎዱት የሶማሌ ሀ/ስብከት ምእመናንና አብያተ ክርስቲያን፣ የርዳታና መልሶ ማቋቋም አስተባባሪ ኮሚቴ ሠየመ

ነገ ዓርብ በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሥራ ይጀምራል፤ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ይመራል፤ የገንዘብ አሰባሰቡ በማእከል በሚከፈት ሒሳብ ሊኾን ይገባል፤ “ጥቃትን አስቀድሞ ማስቀረት፣ በጉዳትም ፈጥኖ መድረስ፤” ††† በኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት፣ ባለፈው ሳምንት በተፈጸመው የጭካኔና የዐመፅ ድርጊት ለተጐዱት ካህናትና ምእመናን እንዲሁም ለተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት፣ የርዳታና መልሶ ማቋቋም አስተባባሪ ኮሚቴ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተሠየመ፡፡ አስተባባሪ ኮሚቴውን፣ የኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በሰብሳቢነት ይመሩታል፡፡ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ፣ ከማኅበረ ቅዱሳንና ከምእመናን የተውጣጡ 12 አባላትን በዐቢይ ኮሚቴነት የያዘ ሲኾን፣ ከ5 እስከ 7 ንኡሳን ኮሚቴዎች እንደሚኖሩት ተጠቅሷል፡፡ የአስተባባሪ ኮሚቴውን መቋቋም ለማሳወቅና የርዳታ ማሰባሰቡን ሒደት ለማስጀመር፣ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ፣ ነገ ዓርብ፣ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡ በጅግጅጋና ጥፋቱ በተፈጸመባቸው የደጋሃቡር፣ ቀብሪደኃርና ዋርዴር ከተሞች፣ ቤት ንብረታቸውን አጥተው በቤተ ክርስቲያን፣ በካምፖችና በሌሎችም መሸሸጊያዎች ለተጠለሉ ካህናትና ምእመናን ፈጥነው መድረስ ያለባቸውን የምግብ፣ የአልባሳትና የቤት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለሰንበት ት/ቤቶች አገልግሎት በቂ ትኩረትና በጀት እንዲሰጥ ተጠየቀ፤ 7ኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ ባለ13 ነጥቦች መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ

  ከ35 አህጉረ ስብከት የተወከሉ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ አባላት፣ ከግንቦት 17 ቀን ጀምሮ ላለፉት ሦስት ቀናት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ሲያካሒዱ የቆዩት፣ 7ኛው ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ማምሻውን፣ ባለ13 ነጥቦች የጋራ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡ ዐበይት ነጥቦች፡- ወጣቱን ከግብረ ሰዶማዊነት ወረርሺኝ ለመታደግ ቤተ ክርስቲያን ድምፅዋን ታሰማ፤ እንደሕግ ያጸደቁት ሀገራት ወጣቱን ሰለባ ለማድረግ የተለያየ ስልት እየተገበሩ ነው፤ ከነጣቂ ጠብቆ ተተኪ ለማድረግ የሚሠራበት ዘመን እንደኾነ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል፤ “የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሓላፊነትም፣ወጣቱን ከሃይማኖት ዘራፊ መጠበቅ ነው፤” የኢኦተቤ ቴቪ ከሌሎች ሚዲያዎች በተሻለ ወጣቱን ያቀፈና ሳቢ እንዲኾን ተጠየቀ፤ ሰንበት ት/ቤቶችን ያማከለ መደበኛ መርሐ ግብር ይኑረው፤የአየር ሰዓትም ይሰጠው፤ ††† ከ1ኛ‐12ኛ ክፍል የተዘጋጀው ሥርዐተ ትምህርት በአበው ምክር እንዲጸድቅ ተጠየቀ፤ ለአተገባበሩ የሚረዱ መምህራን ሥልጠና መርሐ ግብርም እንደሚቀረጽ ይጠበቃል፤ የቀጣዩ 5ዓመት መሪ ዕቅድ ዝግጅት፥ተጨባጭ ኹኔታዎችን እንዲያገናዝብ ይሠራል፤ የሰንበት ት/ቤቶች የፋይናንስ ፖሊሲና አያያዝ መመሪያው ጸድቆ በኹሉም ይተግበር፤ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትን የማዋቀሩ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በአሳሳቢው የሥነ ምግባር ጉዳይ: ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ለትውልዱ ሓላፊነት አለባቸው፤7ኛው ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች ጉባኤ እየተካሔደ ነው

ግብረ ገብ የለሽ ዓለማዊነትና የማንነት ነጠቃ ባህል፣ከተደቀኑባቸው ፈተናዎች ቀደምቱ ናቸው የሰብአዊ መብቶች እና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ኾነው፣ዓለማችንን በነውረ ኃጢአት እየዘፈቋት ነው በገንዘብ፣በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ የታገዙ ናቸውና የቤተ ክርስቲያንን የተደራጀ ምላሽ ይሻሉ በ“ክርስቲያናዊ ሉላዊነት” ዓለምን ኹሉ ደቀ መዝሙር የማድረግ አቅሙን ልናዳብር ይገባል፤ ††† ኦርቶዶክሳውያን የሰንበት ት/ቤት አባላት፣ “በዓለም እንደሐዋርያት ተብተነው ይገኛሉ፤” ቤተ ክርስቲያን፥በዓለም ያላትን ተሰሚነት የሚያረጋግጡ“ሚሊዮን ድምፆች” ሊኾኑ ቢችሉም… ትውልዱን በሠናይ ምግባር ምሳሌነት የማነፅና የማዳን ክርስቲያናዊ ሓላፊነት ቢኖራቸውም… የማደራጃ መምሪያው ዝግጅት፥ፈተናውን በአሸናፊነት ለመወጣት የሚያበቃ አይደለም ተብሏል  ††† የሰንበት ት/ቤቶችንና አባሎቻቸውን ብዛት በቁጥርና ጥራት የማሳደግ የመሪ ዕቅዱ ቀዳሚ ግብ ስኬት በቅጡ አልተገመገመም፤ የዋና ሓላፊውም ሪፖርት ዘልማዳዊ እንጅ የጠቆመው ነገር የለም፤ ከ35 ሚሊዮን በላይ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች እንዳሉ የጠቀሰበት መነሻም እያነጋገረ ነው፤ በጥቅምት ወር 2009 ዓ.ም. ላይ የቆመውን የማደራጃ መምሪያውን ድረ ገጽ፣ “ከኻያ ምርጥ ድረ ገጾች አንዱ” ማለቱም ለትዝብት ዳርጎታል፤ የቀጣይ 5 ዓመት መሪ ዕቅድ ቢቀረጽም፥ የመማሪያ አዳራሾችና የመምህራን ሥልጠና ዝግጅቱ በቂ አይደለም፤ ለመምሪያው የሚፈቀድለት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቤተ ክርስቲያንን ነጻነትና ተደማጭነት ለመመለስ ያለመ የማኅበረ ካህናት አንድነት ተመሠረተ

በሰ/አሜሪካ ቢጀምርም፣በመላው ዓለም ኦርቶዶክሳውያን ካህናትን ለማቀፍ ይንቀሳቀሳል ቤተ ክርስቲያን በሚገባት ክብርና ልዕልና እንዳትገኝ የካህናት ግድየለሽነት አባብሶታል በጎሠኝነትና ምንደኝነት፥በከፋ ኹኔታ ተከፋፍለናል፤መተማመን ጎድሎናል፤ተራርቀናል ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ ጎድቷታል፤ መከራዋን አብዝቶታል፤ በአንድነት ልንፈታው ይገባል፤ አባላቱ፣ ከግለኝነት እና ጎሠኝነት የጸዱ ሊኾኑ ይገባል፤ የአስተዳደር ልዩነቱ አይገድበውም፤ ††† አንድነት ሲኖረን እግዚአብሔር ይሰማናል፤ምእመኑን ወደ አንድነት ማምጣቱም አይከብድም ቅ/ሲኖዶሱ ሚናውን በነጻነት እንዲወጣ፤ ፓትርያርኩ ሓላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲተገብሩ… የቤተ ክህነት ሓላፊዎች ለሁለት ጌቶች ሳይገዙ የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ብቻ እንዲፈጽሙ… መንግሥት ተገዶም ቢኾን ያደምጠናል፤ተቋማት ያከብሩናል፤ሉዓላዊነትና ነጻነት ይመለሳል፤ “እንችላለን” በሚል እምነት የሌሎችንም ችግር የሚቀርፍ ሙሉ አቅም ለመፍጠር እንነሣ! ††† የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ከየትኛውም አካል የሚደርስባትን ትንኮሳና ጥቃት በመመከትና በመከላከል ዘርፈ ብዙ ፈተናዎቿን በጋራ የመፍታት ዓላማን ያነገበ የካህናት አንድነት ማኅበር በሰሜን አሜሪካ ተመሠረተ፡፡ የማኅበረ ካህናቱ አንድነት የተመሠረተው፣ ከአሜሪካ እና ከካናዳ አህጉረ ዓለም የተሰበሰቡ ሊቃውንት፣ ካህናትና ዲያቆናት፣ “ቤተ ክርስቲያናችንን እንታደግ“ በሚል መሪ ቃል ለሦስት ቀናት በሲያትል ከተማ ባደረጉት ጉባዔ ነው፡፡ ከመላ የአሜሪካ ግዛትና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ: የምዕራብ ጎጃም – ፍኖተ ሰላም ሊቀ ጳጳስ ኾነው የተመደቡት የኒውዮርክ ሀ/ስብከታቸውን እንደያዙ ነው

ወደ አሜሪካ/ኒውዮርክ የመግቢያ ቪዛ እስኪያገኙ ደርበው ይመራሉ፤ የቪዛ ማመልከቻቸው በፍጥነት እንዲፈጸም ሀ/ስብከቱ እየሠራ ነው፤ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከታቸውን እንደያዙ ናቸው፤ አልተዛወሩም! ††† “የተደራጀ መንበረ ጵጵስና/ማረፊያ የለውም” መባሉ አግባብ አይደለም፤ መንበረ ጵጵስናውና ጽ/ቤቱ፣በቅዱስ ሲኖዶስና በአባቶች የተወደሰ ነው፤ በምዕራቡ ክፍለ ዓለም የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ምልክት ነው፤ ††† ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ሊቀ ጳጳስ፣ የምዕራብ ጎጃም – ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመደባቸው ሲኾን፤ ላለፉት ዐሥር ዓመታት የመሩት የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከታቸው ጽ/ቤት በበኩሉ፣ “ተዛወሩ” በሚል የተሠራጨው ዜና ሐሰት እንደኾነ አስታውቋል፡፡   ምልዓተ ጉባኤው፣ ሚያዝያ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሔደው የቀትር በፊት ስብሰባው፣ ለሰባት ብፁዓን አባቶች ዝውውርና ምደባ ባደረገበት ውሳኔው፥ የሰሜን ምሥራቅ ደቡብ ምሥራቅ እና መካከለኛው አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፣ የምዕራብ ጎጃም – ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲያስተዳድሩ መድቧቸዋል፡፡   ምደባው ለብፁዕነታቸው የተሰጠው፣ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ – ኒውዮርክ የመግቢያ ቪዛቸው ሒደት ፍጻሜ እስኪያገኝ ድረስ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ጠቅ/ሚኒስትሩ የሰላምና አንድነት ኮሚቴውን የዕርቀ ሰላም ጥረት አበረታቱ – የቤተ ክርስቲያን ሰላም የሀገርም ሰላም ነው

በልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም የሚመሩ የኮሚቴው ሽማግሌዎች፣ የሰዓሊተ ምሕረት ምእመናንን አጽናኑ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሲኖዶሳዊ አንድነት ለመመለስ እየተደረገ ለሚገኘው የአባቶች ዕርቀ ሰላም ጥረት መንግሥት ያላሰለሰ ድጋፍ እንደሚያደርግ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ለዚሁ ዓላማ በአዲስ መልክ ተቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘውን ሁለተኛው ዙር የሰላምና አንድነት ዓለም አቀፍ ኮሚቴ አበረታቱ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም የሚመራውን የሰላምና አንድነት ኮሚቴ ስድስት አባላት፣ ዛሬ ከቀትር በፊት በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ አንድነትና ሰላም ወደ ነበረበት መመለስ የሀገርም ሰላም እንደኾነ የገለጹ ሲኾን፤ ኮሚቴው በአባቶች መካከል ዕርቅንና ሰላምን ለመፍጠር በጀመረው ጥረት እንዲገፋበት አበረታታዋል፡፡ ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚሁ ውይይት፣ የኮሚቴው አባላት የእስከ ዛሬውን የዕርቀ ሰላም ጥረት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራራት መንግሥት ከጎናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡ በሀገርም ይኹን በሃይማኖት ደረጃ ዕርቅና አንድነት ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት መንግሥታቸው ከመደገፍ ወደኋላ እንደማይል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠውልናል፤ ያሉት የኮሚቴው አባላት፣ “በግላቸውም ቢኾን ጥረቱን እንደሚያግዙ በመግለጽ አበረታተውናል፤ በጣም ደስ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የተክሌ አቋቋም ሊቁ መምህር እንደሥራቸው ከተሰወሩ እነኾ 24 ዓመት ኾነ፤ ዳግማዊ አለቃ ተክሌን መልሱልን

አሁን ያሉን መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ መምህር እንደሥራቸው በታሰሩበት ቦታ በቅርቡ አንድ ልኡክ ጉብኝት አድርጎ ነበር፡፡ መምህር እንደ ሥራቸው፣ መመንኮሳቸውንና አዘውትረው የሚጸልዩትም በአንድ እግራቸው ቆመው መኾኑን አመልክተዋል፡፡ አሁን ዕድሜያቸው ወደ 74 ዓመት የተጠጋውን እኒህን አረጋዊ የተክሌ ምትክ እባካችሁ ፍቱልን፡፡ ~~~~~~ /ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት/ “አራቱ ኃያላን” የተባለውን መጽሐፍ በ2006 ዓ.ም. ጎንደር ላይ ስንመርቅ፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ መሪጌታ እንደሥራቸው ስለሚባሉ የተክሌ አቋቋም ሊቅ አንሥተው፣ “የተክሌ አቋቋም ከጊዜ በኋላ ቢጠፋ ወይም እኔ አንድ ነገር ብኾን ብለው 9 ካሴት የሚኾን ዜማ በካሴት ቀርፀው አስቀምጠዋል፤” ሲሉ ተናገሩ፡፡ ሌሎች ሊቃውንትም፣ “እንደሥራቸው መቋሚያ ይዞ ሲዘም እንኳን ሰዎች ንቦች ይመሰጣሉ፤” ሲሉ ስለ እርሳቸው መሰከሩ፡፡ ከዚያ በኋላ፣ እንደሥራቸው ማን ናቸው? የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ ይመላለስ ጀመር፡፡ በተለያየ አጋጣሚ የደብረ ታቦርና የተክሌ አቋቋም ሊቃውንትን ባገኘሁ ቁጥር፣ እኒህን ሊቅ በተመለከተ እጠይቃቸው ነበር፡፡ ሁሉም የሚመሰክሩልኝ፣ “ከአለቃ ተክሌ በኋላ የመምህር እንደሥራቸውን ያህል አቋቋምን የሚያውቀው የለም፤” በማለት ነው፡፡ ዛሬ በቦታው የሚገኙት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሩስያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ያደርጋሉ

የ2ቱን አብያተ ክርስቲያን ግንኙነት ዳግም ለማጠናከር በሰፊው እየተሠራ እንዳለ ገልጸዋል በማኅበራዊ፣ በሰላምና በልማት ተግባራት በጋራ መሥራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል ምዕራባውያኑን ባዶ ያስቀረውን ፈተና በጋራ የመቋቋም፣የኦርቶዶክሳውያን ትብብር አካል ነው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎትን የሚገነባ ተልእኮ እንደኾነ የገለጸው ቅ/ሲኖዶስ ደግፎታል ከጉብኝቱ መልስ፣ በአ/አበባ ሀ/ስብከት ላይ የቀረቡ አቤቱታዎችን የማጣራቱ ሥራ ይጠበቃል፤ ††† የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የሞስኮና መላው ሩስያ ፓትርያርክ ክሪል ባደረጉላቸው ግብዣ መሠረት፣ ከነገ ማክሰኞ፣ ግንቦት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የአምስት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ፡፡ ከቅዱስነታቸው ጋራ፤ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እና የውጭ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ሓላፊ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ ዛሬ ማምሻውን አብረዋቸው የተጓዙ ሲኾን፤ በሞስኮ መንበረ ፕትርክና ከሚኖራቸው የውይይት መርሐ ግብር በተጨማሪ የትምህርትና የምርት ተቋማትን፣ ገዳማትንና ቤተ መዘክሮችን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርጉ ታውቋል፡፡ የቅዱስነታቸው ጉብኝት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንንና የሩስያ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በሲኖዶሳዊው ዕርቀ ሰላም ጉዳይ ጠቅ/ሚኒስትሩ ፓትርያርኩን አነጋገሩ፤ “ልዩነታችሁን ሥበሩና ለእኛ አርኣያ ኹኑን” – ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

በግላቸውም ኾነ በመንግሥት ደረጃ፣ለዕርቀ ሰላሙ ሥምረት ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታወቁ አንዲትና ታላቅነቷ የተጠበቀ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የማየት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ “ለአንድነት ታሪካዊ ሚና ያላት ተቋም፣ራሷ መከፋፈሏ ለብሔራዊ ተግባቦቱ ተግዳሮት ነው፤” “ልዩነቱ ምንም ቢኾን የማይፈታ አይደለም፤ችግር ፈቺዎቹ ከተቸገሩ ትልቁ ችግር እርሱ ነው፤” “በጥረታችሁ ግፉበት፤ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ነን፤ልዩነቱን ሥበሩና ለኛም አርኣያ ኹኑን፤” “የልኡካን አባቶችን ስጋት የሚያስወግድና የሰላም ኮሚቴውን የሚያበረታታ ነው፤”/ታዛቢዎች/ ††† በውጭ ሀገር በስደት በሚኖሩት አባቶች ከተቋቋመው ሲኖዶስ ጋራ ለተጀመረው የዕርቀ ሰላም ጥረት መሳካት፣ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ኹሉ እንደሚሰጥ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ትላንት ቅዳሜ፣ ግንቦት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ረፋድ፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሯቸው ሲኾን፤ ቅዱስነታቸውና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ አንድነት ለማስጠበቅ በጀመሩት የዕርቀ ሰላም ጥረት እንዲገፉበት አሳስበዋል፤ለሥምረቱም መንግሥታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ ለሀገራችን ኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ከፍተኛ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ዶ/ር ዘሪሁን ሙላቱ: የኦርቶዶክሳውያን ይኹንታና ውክልና የተሰጣቸው ምእመናን፣ ሊቃውንትና ምሁራን የሚሳተፉበት ሕዝባዊ ሲኖዶስ እንዲቋቋም ጠየቁ

“አባቶቼ ጳጳሳት፣ ሲኖዶሳዊ ጉባኤውን ፍትሕ የማትሰጡበት ከኾነና ከማኅበረ ምእመናን ጋራ መገናኘታችሁ እየተቋረጠ ከሔደ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያንና ስለ ሀገር አንድነት ሲባል ሕዝባዊ ሲኖዶስ ሊቋቋም ይገባል!” – ዶ/ር ዘሪሁን ሙላቱ ˜˜˜˜˜˜˜ ዐበይት ነጥቦች፡- ቅዱስ ሲኖዶስ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚመራው ሳይኾን የግለሰቦች ፍላጎትና ጥቅም የሚዘውረው ከኾነ እግዚአብሔር ስለማይደሰትበት፣ ልዕልናው እና ቅድስናው አጠያያቂ ይኾናል፤ ይህን አሠራር እግዚአብሔር ስለማይደሰትበት፣ ቡራኬውን ወደ እርግማን ይቀይረዋል፤እናስተምር ቢሉ አእምሮውን ጥበቡን ይነሳቸዋል፤ ጩኸታቸውንም የማይሰማቸው ይኾናሉ፤ ምእመኑን በትውልዱና በጎሣው ምክንያት እየለዩ ጭፍን ጥላቻ የሚያንጸባርቁና ከሕግ አግባብ ውጭ የኾኑ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ማየት ብርቃችን አይደለም፤ ገንዘብና ዘመድ የሌላቸው ሊቃውንትና ካህናት፣ ፍትሕን ፍለጋ የሚንገላቱት የተለየ በደል ፈጽመው ሳይኾን፣ ከጎሣና ጥቅም የጸዳ አባትና ሲኖዶሳዊ አካል ስላጡ ብቻ ነው፤ “እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናል”የሚለውን የሐዋርያትን የጉባኤ ቃል ለይምሰል እየጠቀሱ በዋጋ የሚያስተምሩ አባቶችን መመልከታችን የትንቢቱ ፍጻሜ ላይ መድረሳችንን ያረጋግጣል፤ “የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ለሠራተኛ ቅጥር 100ሺሕ ብር ጉቦ መቀበሉ ታወቀ” ሲባል፣ ያሰናብቱታል ወይም አግደው ጉዳዩን ያጣሩታል ብለን ገምተን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርኩ: በአ/አበባ ሀ/ስብከት ላይ የቀረቡ አቤቱታዎችን የሚያጣራ አካል ያቋቁማሉ፤ “አጥፊውንና ተባባሪዎቹን ጠርጌ አስወጣለሁ!”

በ6 አለቆች አሸማጋይነት ችግሩን ለመፍታት የተደረገውን ሙከራ ፓትርያርኩ ውድቅ አደረጉ ሸምጋዮቹ፣ “አጣሪ ሳይልኩ እኛ እንፍታው፤” ቢሉም “ሳይጣራ የሚኾን ነገር የለም” አሏቸው ጎይትኦምን ከከሣሾቹ ማስታረቁን ፓትርያርኩ ባይቃወሙም፣ “ለማንም ሽፋን አልሰጥም፤” አሉ በሰዓሊተ ምሕረት ምእመናን ላይ የአማሳኞችን ግንባር የመፍጠር ግብ ያለውም ሽምግልና ነበር የፓትርያርኩ አቋም የሐቅ ከኾነ፣“አቤት ባዮችንና ፍትሕ ፈላጊዎችን ኹሉ የሚያስተባብር ነው” በቅ/ሲኖዶሱ እንዲታይ ጠይቀው የተከለከሉ አባቶች፣“ለመንግሥት እናቀርባለን፤” ብለው ነበር፤ ††† በአሸማጋይነት የቀረቡት፦ የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል፣ የሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል፣ የብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ፣ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም፣ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት አለቆች፤የቀድሞው የሀገረ ስብከቱ የሰው ኃይል አስተዳደር ሓላፊ የነበሩና አሁን ተዘዋዋሪ ሰባኪ እንዲሁም የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ሲኾኑ፤ ትላንት ኃሙስ ሠርክ ላይ ወደ ፓትርያርኩ ከመግባታቸው በፊት እስከ ቀትር ድረስ ከሥራ አስኪያጁ ጎይትኦም ያይኑ ጋራ በሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ አዳራሽ ሲመክሩ መቆየታቸው ታውቋል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ላይና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – አባ ሠረቀ ብርሃን ከፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊነት ተነሡ!

የአቅም ማነስ፣ አለመታዘዝና ችኩልነት በምክንያትነት ተጠቅሷል በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ላይ ያሳዩት ጣልቃ ገብነት ብዙዎችን አስቆጥቷል ለበጀት ዓመቱ ያቀረቡት የ13 ሚ. ብር ዕቅድ ጥያቄ አሥነስቶ ነበር በጎንደር እና በጎጃም ተቃውሞ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን ወንጅለው ነበር *                   *                    * ባለፈው ዓመት ሐምሌ፣ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት፣ በልዩ ጸሐፊነት ተመድበው የነበሩት ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ ከሓላፊነታቸው ተወገዱ፡፡ ዛሬ፣ ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ ከፓትርያርኩ በተጻፈ ደብዳቤ፣ ሓላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣትና ሥራን ተረጋግቶ ባለመሥራት የተመዘኑት አባ ሠረቀ ብርሃን፤ በእጃቸው የሚገኘውን ንብረት፣ ለልዩ ጽ/ቤቱ ሠራተኛ ለሊቄ አሰፋ ሥዩም አስረክበው ቢሮውን እንዲለቁ መታዘዛቸው ታውቋል፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃን፣ በተመደቡ በወራት ጊዜ ውስጥ ከሓላፊነታቸው የተነሡበት ምክንያት፣ በጽ/ቤቱ ሥራዎችና የአሠራር ግንኙነቶች የታየባቸው የአቅም ማነስ፣ አለመታዘዝና የታወቀው ችኩልነታቸው እንደኾነ ተገልጧል፡፡ የጽ/ቤቱን ሓላፊነት ከቀድሞው ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ከተረከቡበት ካለፈው ዓመት ሐምሌ 12 ጀምሮ፣ ከሦስት ወራት በላይ ቢቆጠሩም፣ በተለይም የፓትርያርኩን ቃለ ምዕዳንና ቃለ በረከት የማሰናዳት ሥራው፣ በቀድሞው ልዩ ጸሐፊና በኮሚቴ እየተዘጋጁ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቤተ ክርስቲያናችንን ቴሌቭዥን መደበኛ ሥርጭት ለማስጀመር ኹኔታዎች እየተመቻቹ ነው

27 የመርሐ ግብር ዓይነቶችና ይዘታቸው በዝርዝር ተለይተዋል በሦስት ዘርፎች፣ የሰው ኃይል ቅጥር ሒደቱ እየተጠናቀቀ ነው ቅድሚያው፣“ለቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ሠራተኞች ነው” ሞያውን ከነገረ ቤተ ክርስቲያን ያቀናጁትን በበቂ አላፈራንም *               *               * ከፍተኛ ግዥዎችን አከናዋኝ ኮሚቴው፣ ሥራ ጀምሯል ኦርቶዶክሳውያን ዕቃ አቅራቢዎች እንዲሳተፉ ይፈለጋል በርካታ ስቱዲዮዎችና ክፍሎች ያሉት ቋሚ ቢሮ ተጠይቋል አህጉረ ስብከት የፊልም ክምችቶችን እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል *               *               * በሙከራ ሥርጭት ላይ የሚገኘው፣ የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሳተላይት ቴሌቭዥን(EOTC TV) የሚጠቀምበት ሎጎ፣ የቤተ ክርስቲያናችን ዓርማ ነው፡፡ በሙከራ ላይ የሚገኘውን፣ የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሳተላይት ቴሌቭዥን (EOTC TV)፣ መደበኛ ሥርጭት ለማስጀመር የሚያስችሉ ኹኔታዎች እየተመቻቹ መኾኑን የአገልግሎት ድርጅቱ ገለጸ፡፡ ድርጅቱ፣ ለመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 35ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ባቀረበው የ2008 ዓ.ም. ክንውን ሪፖርቱ እንደገለጸው፤ ላለፉት አራት ወራት በሙከራ የቆየው የቴሌቭዥኑ ሥርጭት መደበኛ በኾነ መልኩ መቀጠል የሚችልበት ኹኔታ እየተመቻቸ ሲኾን፣ “በዐዲሱ በጀት ዓመት የመደበኛ ፕሮግራም ሥርጭቱ ይጀመራል፤” ብሏል፡፡ ባለፈው ዓመት ሰኔ፣
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የአ/አበባ ሀ/ስብከትን ሒሳብ በፊርማቸው ያንቀሳቅሳሉ፤ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የከፍተኛ ሓላፊዎች ሽግሽግ ተደረገ

በሀገረ ስብከቱ፥ ሥልጣን፣ የሀብት ማፍርያና የመጠቃቀሚያ መሣርያ ኾኖ የመቀጠሉ እውነታ! የጠቅ/ ጽ/ቤቱ የሓላፊዎች ሽግሽግ፣ “ሥራና ሠራተኛን በማገናኘት የተሻለ ውጤት ይኖረዋል” *                    *                    * የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት(ከላይ)፤ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት(ከታች) የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የኾነውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የባንክ ሒሳብ፣ ብፁዕ አቡነ ገሪማ በፊርማቸው እንዲያንቀሳቅሱ፣ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መመደባቸው ተገለጸ፡፡ ብፁዕነታቸው፣ የልዩ ጽ/ቤቱ የውጭ ግንኙነት የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ሲኾኑ፣ በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ የነበሩትን ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልን በመተካት ሒሳቡን በፊርማቸው እንዲያንቀሳቅሱ ትላንት፣ ጥቅምት 18 ቀን ከፓትርያርኩ በተጻፈ ደብዳቤ መመደባቸው ታውቋል፡፡ ባለፈው ዓመት የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ፣ በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት እንዲኾኑ የተመደቡት የካፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ “የሥራ ጊዜዎ ስላለቀ” በሚል ከፓትርያርኩ በተጻፈ ደብዳቤ፣ የምደባቸው ጊዜ ማብቃቱ እንደተገለጸላቸው ተጠቅሷል፡፡ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ባለፈው ዓመት ግንቦት፣ በፓትርያርኩ ተመርጠው በምልዓተ ጉባኤው ሲመደቡ፣ እስከ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ሲኖዶስ: መንግሥት እና ተቃዋሚዎች የሀገር ችግሮችን በጋራ ውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ

መላው ካህናትና አገልጋዮች፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ ለአገሩ ሰላምና አንድነት ተባብሮ እንዲቆም በየጉባኤያቱ እንዲያስተምሩ መመሪያ አስተላለፈ  ከ201 ሚሊዮን ብር በላይ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የ2009 ዓ.ም. የበጀት ዕቅድ በሙሉ ድምፅ አጸደቀ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አባላት ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከጥቅምት 12 ጀምሮ ላለፉት አምስት ቀናት ሲያካሒድ የቆየውን ስብሰባ በማጠናቀቅ፣ ዛሬ፣ ጥቅምት 16 ከቀትር በኋላ ባለ12 ነጥቦች መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ቋንቋዎች ተናጋሪ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለአያሌ ዘመናት የኖሩባትና አኹንም የሚኖሩባት በአርኣያነት ልትጠቀስ የሚገባት ብቸኛ አገር መኾኗን ያስገነዘበው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በአኹኑ ጊዜ ግን፣ የሰዎች ሕይወት እየጠፋ መኾኑን፣ የአገር ሀብትና ንብረት እየወደመ መታየቱን፣ ከነበሩበትና ከኖሩበት ቦታ የሕዝቦች ፍልሰት ማስከተሉን፣ በዚኽም ሳቢያ በሰላማዊው ኅብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት እየሰፈነ መምጣቱን አብራርቷል፡፡ በመኾኑም ጥያቄዎች፣ ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ፣ በሰከነና በተረጋጋ ኹኔታ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርቡ፤ መንግሥትም፣ ለሚያስተዳድራቸው ዜጎች እንደ ቤት ሓላፊና እንደ መሪ መጠን፣ ጥያቄዎቹን በአግባቡ በመፈተሽና በማጥናት ለአገርና ለወገን የሚጠቅም ምላሽ እንዲሰጥባቸው፣ ለሕዝቡ የገባውንም ቃል በተግባር አውሎ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ሲኖዶስ: ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘጎሬን በሰማዕትነት ሠየመ

ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘጎሬ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከመጀመሪያዎቹ አምስት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት አንዱ ለነበሩትና በፋሽስታዊው የኢጣልያ መንግሥት፣ በግፍ ሰማዕትነት ለተገደሉት፣ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘጎሬ የሰማዕትነት ሥያሜ ሰጠ፡፡ ብፁዕነታቸው፣ በ1928ቱ የፋሽስት ኢጣልያ የአምስት ዓመት የወረራ ዘመን፣ ለተዋሕዶ ሃይማኖታቸው እንዲኹም ለሀራቸው ልዕልና እና ነፃነት ከፍተኛ ተጋድሎ መፈጸማቸውን ቅዱስ ሲኖዶሱ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡ ከኢትዮጵያውያን ሐርበኞች ጎን በመኾን ጠንክረው እንዲዋጉ ሲያስተምሩ በነበረበት ወቅት፣ በ1929 ዓ.ም. በፋሽስታዊው መንግሥት በጎሬ ከተማ በግፍ ሰማዕትነት እንደተገደሉ ምልዓተ ጉባኤው ገልጾ፣ ሰማዕት ተብለው እንዲጠሩ መወሰኑን፣ ዛሬ፣ ረቡዕ ጥቅምት 16 ቀን ከቀትር በኋላ ባወጣው ሲኖዶሳዊ መግለጫው አስታውቋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል፣ መንበረ ጵጵስናቸው በነበረበትና በሰማዕትነት ባለፉበት በኢሉ አባ ቦራ ሀገረ ስብከት ጎሬ ከተማ የቆመላቸው ሐውልተ ስምዕ፣ ባለፈው ዓመት መጋቢት አጋማሽ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተመረቀ ሲኾን፤ የቤተ መዘክር ግንባታ ዕብነ መሠረት መቀመጡም ይታወሳል፡፡
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገራችን የሰላም ጉዳይ ይነጋገራል፤ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት አልተካተተም

በወቅታዊው የሰላም ኹኔታ፣ የቤተ ክርስቲያንን ተሳትፎ የሚያሳድግ መግለጫ ያወጣል ግጭቶችና ሑከቶች፣ ያደረሱት የሰላም መደፍረስ እና የኅሊና ስብራት ቀላል አይደለም ሕዝቡ፥ የስምምነት፣ የአንድነት፣ የሰላምና የፍቅር ሕዝብ እንዲኾን በበቂ አልሠራንም *** ጳጳሳት፣ ሊቃውንት፣ ካህናትና ሰባክያን፥ አስተማሪ እና ሠርተን የምናሳይ መኾን አለብን ቤተ ክርስቲያን፥ በማዕከላዊነት እና በገለልተኛነት የሰላም መልእክቷን ለኹሉም ታደርሳለች ልማትን በማስፋፋትና ለወጣቱ የሥራ ዕድል በመፍጠርም እናትነቷን በተጨባጭ ታሳያለች *** ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የ2009 ዓ.ም. የመጀመሪያ የምልዓተ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን፣ ርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን ጠዋት፣ በብዙኃን መገናኛ ፊት ባሰሙት የጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳን ጀምሯል፡፡ የሰላም መጠናከርና መጠበቅ፣ የስብከተ ወንጌል መጠናከርና የልማት ሥራ መስፋፋት፤ ምልዓተ ጉባኤው ሰፊና ጥልቅ ውይይት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያን፣ ለሕዝብና ለሀገር የሚጠቅሙ ውሳኔዎች የሚያሳልፍባቸው የትኩረት አጀንዳዎች እንደኾኑ ነው፣ ፓትርያርኩ በመክፈቻ ቃለ ምዕዳናቸው የጠቆሙት፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በየጊዜው በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች የሚወያይባቸውን ጉዳዮች የማዘጋጀት ሓላፊነት ያለበት ቋሚ ሲኖዶስም፣ በመነሻነት ካቀረባቸው አምስት ነጥቦች መካከል፣ “በአገሪቱ ወቅታዊ የሰላም
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሕዝቦች እናት ነች፤ የሀገርን አንድነት በልዩ ትኩረት ማስተማር ይኖርብናል/የፓትርያርኩ የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ መክፈቻ ንግግር/

Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቅዱስ ሲኖዶስ መክፈቻ ጸሎት ተካሔደ፤ ለሰላም ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠይቋል

ቤተ ክርስቲያን፣ መምህር ወመገሥጽ ዘኢያደሉ ለገጽ በመኾን ከክርስቶስ በተቀበለችው አደራና ሓላፊነት፥ መንጋውን የመጠበቅ፣ የማጽናናትና የማስታረቅ ሥራ ልትሠራ ይገባል/ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ከፍተኛ መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ ሕግ አውጭና ወሳኝ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖስ፣ የ2009 ዓ.ም. የመጀመሪያ መደበኛ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባውን ነገ ይጀምራል፡፡ በፍትሕ መንፈሳዊ በአንቀጽ 5 ቁጥር 164 በታዘዘው መሠረት፣ ነገ ቅዳሜ፣ ጥቅምት 12 ቀን ለሚጀመረው የምልዓተ ጉባኤው ስብሰባ፣ ዛሬ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል፡፡ በመክፈቻ ጸሎቱ የዕለቱን ወንጌል(ማቴ. ምዕ. 22 ቁ. 35) በንባብ በማሰማት ትምህርት የሰጡት፣ የሶማሌና የአርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ ከአበው ሐዋርያት ሲያያዝ በመጣው ትውፊት መሠረት፣ የቤተ ክርስቲያንን ዐበይት ጉዳዮች በአጀንዳነት ቀርጾ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተናግረዋል፡፡ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ፣ በፍጹም ነፍስና በፍጹም ሐሳብ በመውደድ፣ ጾምና ጸሎትን ገንዘቡ ያደረገ የወሰነው ውሳኔ ነቀፌታ እንደማይኖረውም ብፁዕነቸው በአጽንዖት አስረድተዋል፡፡ ከመክፈቻ ጸሎቱ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

35ኛው አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ ተጠናቀቀ፤ በተለያዩ አካባቢዎች ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ኹሉ ሐዘኑን ገለጠ፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ተመኘ

ባለፈው ሰኞ የተጀመረው፣ 35ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ ባለኻያ ነጥቦች የጋራ አቋም መግለጫ በማውጣትና ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የውሳኔ ሐሳብ በማቅረብ፣ ትላንት፣ ኃሙስ ቀትር ላይ ተጠናቋል፡፡ አጠቃላይ ጉባኤው፣ በኦሮሞ ሕዝብ ባህል በየዓመቱ በቢሾፍቱ በሚከበረው የኢሬቻ ሥነ ሥርዓት ላይና በሌሎቹም አካባቢዎች በተፈጠረ “ሁከትና ግርግር” ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ኹሉ፣ ቋሚ ሲኖዶስ የሰባት ቀን ጸሎተ ምሕላ ዐውጆ ሥርዓተ ጸሎቱ መፈጸሙን አስታውሶ፤ የተሰማውን ሐዘን ገልጧል፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡ በዓመታዊ ስብሰባው መዝጊያ፣ “ሰላሜን እተውላችኋለኹ” ባለው የወንጌል ቃል መነሻ፣ ቃለ በረከት የሰጡት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም ባለቤት መኾኗን ገልጸው፣ የጉባኤው ልኡካን ስለ ሰላም እንዲሰብኩና እንዲያስተምሩ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም፣ “ችግር ነበር፤ አኹን ግን ጥሩ ኾኗል፤ ረግቧል፤” ያሉት ፓትርያርኩ፣ “የሚጥመው ይጥመዋል፤ የማይቀበለው የራሱ ጉዳይ ነው፤ በሪሞት ኾነው የሚያተራምሱትን ሐሳባቸውን መደገፍ የለብንም፤” ብለዋል፡፡ ከፓትርያርኩ ቀደም ብለው የማጠቃለያ የሥራ መመሪያ የሰጡት የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ÷ ቤተ ክርስቲያን ማንም እንዲጠፋ ምኞቷ አለመኾኑን ተናግረዋል፡፡ ይኹንና፣
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በ2008 ዓ.ም. ከ50 ሺሕ በላይ አማንያን ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ

18 ሺሕ 578ቱ፣ ከማኅበረ ቅዱሳን መርሐ ግብር ጋር በመቀናጀት የተጠመቁ ናቸው ጥሙቃኑን ለማጠናከርና በቅድመ ጥምቀት ለሚማሩቱ፣ ኹለንተናዊ ድጋፍ ተጠይቋል ያሉንን ምእመናን፣ ካህናትና አብያተ ክርስቲያን ቁጥር መዝግቦ የማወቅ ሒደቱ ቀጥሏል *               *              * የሐዲሳን አማንያን ጥምቀተ ክርስትና ሲካሔድ(ፎቶ: የማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ገጽ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፥ የካህናት፣ የምእመናን፣ የገዳማት፣ የአድባራትና የገጠር አብያተ ክርስቲያን ብዛትና ያሉበትን ኹኔታ ለማወቅ ምዝገባ(ቆጠራ) እያካሔደች ነው፡፡ “በጎቼንና ጠቦቶቼን ጠብቅ፤ ግልገሎቼን አሰማራ”/ዮሐ.21፥ 15-18/ የሚለውን የጌታችንን ቃል ልንፈጽም የምንችለው ስናውቃቸው ነው፡፡ መጠናቸውንና ያሉበትን ኹኔታ መዝግቦና አጥንቶ ማወቅ፣ መንፈሳዊ አገልግሎታችንን ዐቅደንና በሕዝብ ላይ መሥርተን እንድንሠራ ያደርገናል፤ የት ቦታ ምን ዓይነት አገልግሎት፣ የትኛው የልማት ወይም የማኅበራዊ ተቋም መሠራት እንዳለበት የሚወሰነው መዝግቦ በማወቅ እንደኾነ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ያስረዳሉ፡፡ አህጉረ ስብከት፣ ይህን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ለማስፈጸም፡- ከፍተኛ በጀት በመመደብና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶችን፣ ምእመናንንና ካህናትን በማስተባበር ጥረት እያደረጉ እንደኾነ በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ጉባኤ 35ኛው
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

አህጉረ ስብከት: በፀረ – ተሐድሶ ኑፋቄ ተጋድሎ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን አስታወቁ

አብዛኞቹ አህጉረ ስብከት፣ የፀረ – ተሐድሶ ቋሚ ጉባኤያትን በጥምረት አደራጅተዋል ለተሐድሶአውያኑ“የእምነት መግለጫ”  የጽሑፍ ምላሽ ዝግጅት ተጠናቋል/ሊቃውንት ጉባኤ/ “ወዳጅም ጠላትም ይስማ! ሀ/ስብከታችን ለተሐድሶ መናፍቃን ቦታ የለውም!” /ምዕ. ወለጋ/ “በሀገረ ስብከታችን÷ ተሐድሶ የሚባል ስም አጠራሩ ከምድረ ገጽ ጠፍቷል!” /ጅማ/ *               *               * ፴፭ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባውን በማካሔድ ላይ የቤተ ክርስቲያን ቀዋሚና የማይነጥፉ ሀብቶቿ ምእመናን ናቸው፡፡ ምእመናን ሀብቶቿ ያሉበትን በውል ማወቅ፣ ዐውቃም ወደ ለመለመ የወንጌል ማዕድ በማሰባሰብ በቃለ እግዚአብሔር መጠበቅና በሥነ ምግባር መከባከብ፤ ለንስሐና ለሥጋ ወደሙ ማብቃትና የመንግሥተ እግዚአብሔር ወራሾች እንዲኾኑ ማድረግ ቀዳሚ ትኩረቷ ነው፡፡ ማኅበረ ካህናት ወምእመናንን አቅፎ የተደራጀው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፥ ይህንኑ ክህነታዊ ግዴታውን ለመወጣት ያስችለው ዘንድ፣ በስብከተ ወንጌልና በማኅበራዊ ልማት መስፋፋት፤ በሰንበት ት/ቤቶችና በአብነት ት/ቤቶች መጠናከር ውጤታማ ለውጦችን እያስመዘገበ እንዳለ፣ በ35ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየቀረቡ ያሉ የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች ያመለክታሉ፡፡ ምእመናን፣ ለሃይማኖታቸው ቀናዒ እንዲኾኑና በምግባር እንዲጸኑ የተጠናከረ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

35ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጀመረ፤ ጸሎተ ምሕላ ከማወጅ ጋር ትልቅ የሰላም አጀንዳ ቀርጾ መወያየት ይጠበቅበታል!

የሰላም ዕጦት ቤተ ክርስቲያኒቱን እየለበለባት ነውና ከዳር ቆማ የምታይበት ሰዓት አይደለም መንግሥት ሲናገር በመናገር፣ ዝም ሲልም ዝም በማለት የሚታለፍ ጉዳይ መኾን የለበትም የችግሩን መንሥኤ አጥንታ መፍትሔ በማመንጨት፣ በያገባኛል ስሜት ልትንቀሳቀስ ያሻል መሪዎችዋ፥ በአንድ ልብ ሊወያዩ፣ ያለአድልዎ ኹሉንም ሊያስተምሩና ሲገሥጹ ያስፈልጋል ምሕላ ከማወጅ ባሻገር፣ በግጭቱ የተጎዱ ወገኖችን በመደገፍ አለኝታነቷን ማሳየት ይገባታል *                 *               * በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መተዳደርያ ደንብ ቃለ ዓዋዲ ድንጋጌ መሠረት፣ በየዓመቱ ጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ የሚካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ ዛሬ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠዋት፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጀምሯል፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመምሪያዎች፣ ድርጅቶችና አገልግሎቶች ዋና ሓላፊዎች ጀምሮ ከ49 የሀገር ውስጥና የውጭ አህጉረ ስብከት የተውጣጡ ከአራት መቶ ያላነሱ፡- የሰበካ ጉባኤያት፣ የካህናት፣ የስብከተ ወንጌል፣ የሰንበት ት/ቤቶችና የምእመናን ተወካዮች የሚሳተፉበት ነው – አጠቃላይ ዓመታዊ ጉባኤው፡፡ የጉባኤው ርእሰ መንበር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በመክፈቻ ቃለ በረከታቸው፣ “ሰበካ ጉባኤ፣
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች አቡነ አብርሃምን አነጋገሩ፤ “ሃይማኖታዊ ግዴታዬን ነው የተወጣኹት”/ብፁዕነታቸው/

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ፣ መንግሥት ምን ማድረግ እንደሚገባ፣ አባታዊ ምክር ሰጥተዋል “መናገር ያለብኝን ነው የተናገርኩት፤ ሃይማኖታዊ ግዴታዬን ነው የተወጣኹት” ብለዋል *               *               * ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ሰው አላት ያሰኘና እውነትን መሠረት ያደረገ ወቅታዊ መልእክት ነው፤ ኹሉም ብፁዓን አባቶች፣ እንዲኽ፣ የኅሊናቸውን እውነት የሚናገሩበት ቀን ሩቅ አይኾንም!! /አስተያየት የሰጡ ምእመናን/ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፤ የባሕር ዳር፣ የምዕ/ጎጃም፣ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ (አዲስ አድማስ፤ መታሰቢያ ካሳዬ፤ ቅዳሜ፣ መስከረም ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.) በባሕር ዳር ከተማ መስቀል ዐደባባይ በተካሔደው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙትና የሰሞኑ አገራዊ የመወያያ አጀንዳ የኾኑት፣ የባሕር ዳር፣ የምዕ/ጎጃም፣ የአዊ እና የመተከል ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን፣ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ከትላንት በስቲያ አነጋገሯቸው፡፡ ከውስጥ ዐዋቂ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሠረት፤ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ከኾኑት የመንግሥት ባለሥልጣናት መካከል፡- የፌዴራል እና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃንና በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ህላዌ ዮሴፍ ናቸው፣ ሊቀ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

አቡነ አብርሃም: ሕዝቡና ሠራዊቱ እንዲተዛዘኑ መከሩ፤ መንግሥትንና ሚዲያውን አሳሰቡ፤“በመሣርያ ሰላም አይገኝም፤ አይተነዋል፤ እያየነውም ነው፤ ሊኾንም አይችልም!”

የመሣርያ ምላጭ ከመሳብ ይልቅ፣ የፍቅር መሳቢያን ተጠቀሙ፤ የፍቅር ማሰርያን ተጠቀሙ  ጉልበታችን ሊያስመካን አይገባም፡፡ ሊያስመካን የሚችል ቢኖር መስቀሉ ብቻ ሊኾን ግድ ነው  ሰላም፣ የሰዎችን ድምፅ ሰምቶ፣ መልስ በመስጠትና ችግርን በማስወገድ ነው የሚመሠረተው  በኃይል ሰላምን አምጥተው በሰላም የኖሩ፣ በየትም ዓለም የሉም፤ የቀን ቆጠራ ካልኾነ በቀር! *                *             * ምንጊዜም ችግር የመሪው መንግሥት እንጂ የተመሪው ሕዝብ አይደለም፤ በቤተ ክህነትም!  መንግሥት፣ እንደ ወላጅም እንደ መሪም፣ ችግሮችን በመፍታት መፍትሔ መስጠት አለበት  በግድያ እና ሕዝቡን በማላቀስ፣ ነገ ሌላ የታሪክ ጠባሳ በስሙ እንዳያኖር ሊጠነቀቅ ይገባዋል!  የጩኸቱን ድምፅ ሰምቶ ለጩኸቱ ካልመለሰ፣ ሕዝቡ ጩኸቴን አላቆምም ቢል የተለመደ ነው *                *             * ሚዲያዎች፣ ያሻችኹን እየቀጠላችኹ ከሕዝቡ አጋጫችኹን፤ ምን አባት አለን? አሰኛችኹ  የቤተ ክርስቲያን፣ ድምፅዋ ይሰማ! ለማንም አትወግንም፣ የምንናገረውን በትክክል አድርሱ!  ቤተ ክርስቲያንን የሚናፍቃት የውሸት ዕርቅና የምፀት ሰላም ሳይኾን የመስቀሉ ሰላም ነው  እርስበሳችን በፈጠርነው መከራና ችግር መሣቂያና መሣለቂያ ከመኾን እግዚአብሔር አድነን!! *                *             * “ኹለችኁም ወደዚኽ መስቀል ተመልከቱ፤ በመሣርያ ሰላም አይገኝም፤
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የመስቀሉ ሰዎች፣ በመሸነፍ ውስጥ ማሸነፍ እንዳለ ይናገሩ! በመሸነፍ አሸናፊነት ለኢትዮጵያችን እንበጃት!

የ፳፻፱ ዓ.ም. መስቀል – ደመራ በዓል፣ በአዲስ አበባ መስቀል ዐደባባይ መስቀልን ስናከብር፡- ማኅተመ ፍቅር፣ ትእምርተ ሰላም፣ ትእምርተ መዊዕ መኾኑን እናስባለን የሰው ልጆችን በፍቅር ዐይን መመልከት፣ በማኅተመ መስቀሉ የምናስረግጠው ዐቢይ ጉዳይ ነው የጎሰኝነት አዋራን፣ ከደመራው በሚነሣው የዕጣን ጢስ ጥዑም መዓዛ ሳንተካ ማለፍ አይገባንም በአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች መሀል ጠብ የሚዘራው ርኩስ መንፈስ በመስቀሉ ሊወገዝ ይገባዋል *                       *                      * በመንፈሰ ኤልያስ የሚሔዱና በመጥምቁ ዮሐንስ ጥብዓት የሚናገሩ ሰባክያነ ሐዲስ ያስፈልጋሉ ስብከተ መስቀሉ የዐደባባይ ነውና፣ ጸዋርያነ መስቀል ነቀፋ ካለበት አሰላለፍ ሊታረሙ ይገባል የመስቀሉ ሰዎች ራሳቸው ቀድመው ይቅር መባባል አለባቸው፤ ሳይታረቁ ማስታረቅ አይቻልም የሕዝብን ጥያቄ በመቀበል እና ጥያቄንም ለሀገር ጥቅም በማስገዛት፣ ለኢትዮጵያችን እንበጃት! *                       *                      * የመስቀሉ ሰዎች፣ በመሸነፍ ውስጥ ማሸነፍ እንዳለ ይናገሩ! በመሸነፍ አሸናፊ ኾነን ለኢትዮጵያችን እንበጃት! /ዲያቆን ዓባይነህ ካሴ/ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችኹ! የዘንድሮ በዓለ መስቀል በዐደባባይም ይኹን በቤት ሲከበር በአእምሮ የሚጉላላ (የሚወጣ እና የሚወርድ) አንድ ብርቱ ጉዳይ በጀርባው ታዝሎ ይታያል፡፡ እርሱም ወቅታዊው ነገረ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የአእላፍ ቅዱሳን ሀገር ኢትዮጵያ: የሀገር ሽማግሌ ዐጣችን?

(ቁም ነገር መጽሔት፤ 15ኛ ዓመት ቅጽ 15 ቄጥር 264፤ መስከረም 2008 ዓ.ም.) /ተክለ ኪዳን አምባዬ/   መነሻ አንድ በቅርቡ ለአራተኛ ጊዜ የበጎ ሰው ሽልማት መካሔዱ ይታወሳል፡፡ ከሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ቀደም ብሎ ስለዝግጅቱ በተጠራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ ለፕሮግራሙ አዘጋጆች ከጋዜጠኞች የቀረበ አንድ ጥያቄ ነበር፡፡ የበጎ ሰው ሽልማት ከሚሸልምባቸው ዘርፎች መካከል፣ ‹‹የዓመቱ የሰላም ሰው›› የሚል ነበር፤ ነገር ግን ዘንድሮ የለም፤ ለምንድን ነው? የሚል ነበር፡፡ ከፕሮግራሙ አዘጋጆች አንዱ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ‹‹ለዘንድሮ ብቻ ሳይኾን ላለፉት ተከታታይ ዓመታት የዓመቱን የሰላም ሰው ለመሸለም ዝርዝራችን ውስጥ ነበር፤ ነገር ግን የሰላም ሰው ብለን የምንሸልመው መስፈርቱን የሚያሟላ ሰው ባለማግኘታችን ልንሸልም አልቻልንም፡፡›› ከአገራችን 90 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ውስጥ ለተከታታይ ዓመታት አንድም የሰላም ሰው መፍጠር አለመቻላችን፣ ማኅበረሰባችን ሕመም ላይ መኾኑን አመላካች ነው፡፡ መነሻ ኹለት ባለፈው ሳምንት እሑድ በተከበረው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ማግሥት፣ አንጋፋው ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም፣ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ‹‹የወቅቱን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ወቅታዊው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገራዊ ሚና

የማቀራረብ፣ የማስማማት እና የማስታረቅ አገራዊ ሚና ያላት፣ አገናኝ ተቋም ናት ከመንፈሳዊ ተልእኮዋ እና ከታላቅ ማኅበራዊ ተቋምነቷ የመነጨ፣ ታሪካዊ ሚናዋ ነው ተቃራኒዎችን ማቀራረብ፣ ታማኝነትንና የመንፈስ ልዕልናን የሚጠይቅ ሓላፊነት ነው በመተማመን፣ የተጐዱ የሚካሱበትና ያጠፉ የሚታረሙበት ከበቀል የጸዳ ፍትሕ ይሰፍናል ግጭቶች በውይይትና በዕርቅ እንዲፈቱ ያደረገችበትን ሚናዋን፣ ዛሬም ልትገፋበት ይገባል *               *               * አገራችን ኢትዮጵያ ጽኑ ሕመም ይዟታል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች፣ ለዓመታት የታመቁ ቅሬታዎችና ምሬቶች ገንፍለው እየወጡ ለግጭቶች ምክንያት እየኾኑ ነው፡፡ በሕዝብ ሲቀርቡ የቆዩ ጥያቄዎች፣ ወቅታዊና ተገቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው ያለማቋረጥ እየተከሠቱ ባሉ ግጭቶች፣ በርካታ ዜጎች እየተገደሉ፣ አካላቸው እየጎደለ፣ ለእስራትና እንግልት እየተዳረጉ ነው፤ የአገር ንብረትም እየወደመ ነው፡፡ በማኅበራዊ ግንኙነት፣ ላለፉት 25 ዓመታት፣ ከኢትዮጵያነት ይልቅ እንዲጎላና እንዲጠናከር ተደርጎ የተቀነቀነው ጎሳዊ ማንነትም፣ ግጭቶቹን እንዳያስፋፋና አጠቃላይ ህልውናችንን የሚያሳጣ አደጋ እንዳያመጣ ስጋቱ አይሏል፡፡ ገዥው ግንባር ኢሕአዴግ፣ ያለፉትን 15 ዓመታት ‹‹የሕዳሴ ጉዞ›› እና የወቅቱን ልዩ ልዩ የፖሊቲካ ዝንባሌዎች በጥልቀት ገምግሜበታለኹ ባለው፣ የነሐሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ድርጅታዊ መግለጫው፣ ‹‹በአኹኑ ወቅት በአንዳንድ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሕዝብን የሚያዳምጥ መንግሥት፤ መንግሥትን የሚያዳምጥ ሕዝብ

ማዳመጥ ማለት፥ ይኹነኝ ብሎ መስማት፤ ሰምቶ ማስተዋል፤ አስተውሎም መመለስ ነው የሕዝብ የመናገር ነጻነት ዋጋ የሚያገኘው፣ በመንግሥት የመደመጥ መብት ሲኖረው ነው የሚያዳምጠው ሲያጣ፣ ራሱን ማዳመጥ ይጀምርና በኋላ የሚኾነውን ለመገመት ያስቸግራል ጠያቂውን የሕዝብ ወገን የችግሩ መነሻ ማድረግ፣ ሕዝብን ያለመስማት ዋና መገለጫው ነው ሕዝብ፣ አክብሮ ይሰማኛል ብሎ የሚያምነውን መንግሥት ያዳምጣል፤ መደማመጥ የጋራ ነው፤ *               *               * የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅኔ ሕዝብ ነውና፣ ሕዝቡን ለማዳመጥ ባለቅኔ መንግሥት ያስፈልገዋል እወደድ ባዮች፣ ለመንግሥት የሚያስፈልገውን ትተው እርሱ የሚፈልገውን ብቻ ይነግሩታል ከሕዝብ መክሮ ከሚፈልገው ይልቅ የተጠየቀውን የመለሰ መንግሥት፣ ሕዝብን የሚሰማ ነው መንግሥት ማዳመጡን በምላሹ ይገልጣል፤ ምላሹ ለማዳመጥ በሰጠው ማስተዋል ይወሰናል ሕዝብ ባለመደመጡ ተስፋ ሲቆርጥ፡- አይቀበለውም፤ ልብ አይለውም፤ ምላሽ አይሰጠውም፡፡ *               *               * (አዲስ አድማስ፤ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ ቅዳሜ፣ ነሐሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም.) ‹ደንበኛ ንጉሥ ነው› እያልን ‹ሕዝብ ንጉሥ ነው› የሚለውን እንዴት መቀበል ያቅተናል? ‹ደንበኛ አይሳሳትም› እያልን ‹ሕዝብ አይሳሳትም› የሚለውን እንዴት ማመን ይሳነናል? ሀገር ሰላም እንድትኾን፤ ሰላም ኾናም በብልጽግና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ከእመቤታችን የእናትነት ፍቅር ሊለዩን የሚሞክሩትን፥ በእግዚአብሔር ቃል፣ በኦርቶዶክሳዊና በኢትዮጵያዊ መንፈስ ልንቋቋማቸው ይገባል – ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ

ነገረ ፍልሰታዋን፣ ቃለ እግዚአብሔርን በማስታወስና ለቃሉ ተገዥ በመሆን እንፈጽማለን ትውልድ ኹሉ፣ የጌታ እናትነቷን አምኖ ብፅዕት ነሽ እያለ እንዲያመሰግናት በቃሉ ታዟል ወላዲተ አምላክ ሳንላት፣ ጌታችንን አምላክ ወሰብእ ብለን ማመንና መዳን አንችልም እነኋት እናትህ በሚለው ቃል፣ እመቤታችን በእያንዳንዱ አማኝ ቤት በመንፈስ ትኖራለች በቤቱ፣ “እምዬ እናቴ፣ ብፅዕት ነሽ” እያለ በሥዕሏ የማይጸልይ እና የማይማፀን የለም ከፍቅርዋ የሚለዩንን በቃሉ፣ በኦርቶዶክሳዊ እና በኢትዮጵያዊ መንፈስ እንቋቋማቸው! ስለ እርስዋ ፍቅር ለድሆች የምንዘክርበት ተግባር ዛሬም ሳይቀዘቅዝ ሊቀጥል ይገባል፡፡ *               *               * በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡ በሀገር ውስጥም ሆነ በተለያዩ ክፍላተ ዓለም የምትገኙ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ወምእመናት፤ እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት የቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!! ‹‹ቃለ እግዚአብሔር ንጹሕ ወያሐዩ ለዓለም = የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ነው፤ ለዘላለሙም ያድናል›› (መዝ.18፥9)፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ስለ ቃለ እግዚአብሔር አስመልክቶ በዘመረው መዝሙር ሲናገር፣ ‹‹የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ነው›› ይላል፤ በርግጥም የእግዚአብሔር ቃል የተለያዩ ፍጡራን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

አባ ሠረቀ ብርሃን የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊነት፤ ንቡረ እድ ኤልያስ የማሳተሚያ ድርጅት ሥራ አስኪያጅነት ተመደቡ፤ እነአባ ሠረቀ በልዩ ጽቤቱ ተገን ለጵጵስና እየቀሰቀሱ ነው

ለ2ኛ ጊዜ በተመሳሳይ ወቅት ተዛውረዋል፤“ከድጡ ወደ ማጡ” ተብሏል አባ ሠረቀ በሓላፊነታቸው ተገን ለጵጵስና እንዲታጩ እየተሯሯጡ ነው በሹመኞች እና በአማሳኞች ድጋፍ አስመራጩን ለማስገደድ እየሠሩ ነው የኮሚቴውን አባላት አማስነዋል ያሏቸውን ተጠቋሚዎች ሽፋን አድርገዋል “በራሴ ፍላጎት የሚሰጥ ጵጵስና ካለ ለሕይወቴ ካንሰር ነው፤” ብለው ነበር “የቤተ ክህነቱ ነገር ተቃራኒ ነው፤ ሹመት ለማይገባው ሹመት ይሰጣል፡፡” /ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ሳሉ፣ የአባ ሠረቀ ብርሃንን የመምሪያ ሓላፊነት ምደባ በመቃወም ከተናገሩት/ *                *               * በአዳማዊ የውርስ ኃጢአት በእመቤታችን ንጽሕና ላይ ከተሰነዘረው ኑፋቄ ጋር ተባብረዋል በፓትርያርኩ አቅራቢነት ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ታይቶ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል “አቋሜ ከኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ አይለይም” ቢሉም ቃላቸውን በጽሑፍ አላረጋገጡም በቅዱስ ሲኖዶስ vs. በፓትርያርኩ፣ የበላይነትና ቅድምና(supremacy)መደናገር አለባቸው በሎሳንጀለሱ የታቦትና የንዋየ ቅድሳት ስርቆታቸውም፣ ፓትርያርኩ በእማኝነት ተጠቅሰዋል “ሥልጣን፣ ገንዝብና ክብር በልጦባቸው የሰረቁ እና የዋሹ” በሚል ምንኵስናቸው ተነቅፏል! *               *               * እንደተገመተውና አስቀድሞ እንደተጠቆመው፥ አወዛጋቢው፣ ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ኤጲስ ቆጶስነት የሚሾመው ከቆሞሳት መካከል በትምህርቱ በትሩፋቱ ልቆ የተገኘ አባት ነው – ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በምሥጢረ ክህነት እንዳስተማሩት

ሐዋርያት ከጌታ በተሰጣቸው ሥልጣነ ክህነት ያስሩና ይፈቱ ነበር፡፡ የማሰርና የመፍታት ማለትም አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት የመለየት፣ በይቅርታ ወደ ቤተ ክርስቲያን የመመለስ፤ ምሥጢራትን የመፈጸም ተልእኮ እስከ ኅልፈተ ዓለም የሚቆይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ክህነት ከምኩራቡ ዘርዐ ክህነት የተለየ ነው፡፡ የምኩራቡ ክህነት፣ ሌዊንና አሮንን መሠረት አድርጎ ነው፡፡ በእነርሱ የዘር ሐረግ ብቻ የሚተላለፍ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ክህነት ግን ክርስቶስን መሠረት አድርጎ ነው፤ የዘር እና የጐሳ ልዩነት አይደረግበትም፡፡ በቤተ ክርስቲያን የዲቁና ማዕርግ የሚሰጠው ከጋብቻ በፊት ነው፡፡ ዲቁናውን እንደተቀበለ ለመመንኰስ ቢፈልግ ገዳም ገብቶ፣ በረድእነት አገልግሎ ይመነኵሳል፡፡ ከመነኰሰ በኋላ የቅስና ማዕርግ ይቀበላል፡፡ ለቁምስናና ለኤጲስ ቆጶስነትም መንገዱ ይህ ነው፡፡ ኤጲስ ቆጶሱ በማይገኝበት ቦታ እንደ ኤጲስ ቆጶስ ኾኖ የሚያገለግል ቆሞስ፣ በቤተ ክርስቲያናችን ይሾማል፡፡ የቁምስና ሹመት የሚሰጠው በኤጲስ ቆጶስ ነው፡፡ ቆሞስ የሚኾኑት በድንግልና የመነኮሱ፣ የቅስና ማዕርግ ያላቸው ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት፣ ኤጲስ ቆጶስነት የሚሾመው፣ ከቆሞሳት መካከል በትምህርቱ በትሩፋቱ ልቆ የተገኘ አባት ነው፤ የሚመረጠውም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በቁልቢ ቅ/ገብርኤል በወር እስከ 250ሺሕ ብር ይመዘበራል፤ ምእመናን፣ አለቃውና አጋሮቻቸው በሕግ እንዲጠየቁ ለፓትርያርኩ አቤት ብለዋል

ከበዓላት ውጭ በወር ከ300ሺሕ ብር በላይ ቢገኝም፣ ለገዳሙ የሚገባው ከ100ሺሕ አይበልጥም፤ ለ24 ዓመት የቆዩት አለቃ፣ ከ20ሚ. ብር በላይ የባንክ ተቀማጭና የአክስዮኖች ባለድርሻ ናቸው፤ ከሒሳብ ሹሟ ጋር ምንኵስናቸውን እያዋረዱ፣ ለጵጵስና አለመጠቆማቸው በእጅጉ አሳዝኗቸዋል፤ ገቢውን በአራጣ ጭምር የሚያበድሩ የጽ/ቤቱ ሓላፊዎች፣ ከፍተኛ ሕገ ወጥ ሀብት አድልበዋል፤ እስከ25 ዓመት ያገለገሉ ካህናትና መዘምራን የማያገኙት፣ ከዕጥፍ በላይ ደመወዝ ይከፈላቸዋል፤ የካህናት ማሠልጠኛውና የተጀመሩ ቤተ ጉባኤያት፣ በትኩረትና በቁጥጥር ማነስ ተዘግተዋል፤ ስብከተ ወንጌልና ማኅበራዊ ልማት ባለመኖሩ፣ የምእመናን ቁጥር እያጠጠና እየተቀሠጡ ነው፤ *           *           * የካህናትና ምእመናን ኮሚቴ፣ ገቢውን በመቆጣጠርና ግልጽነትን በማስፈን ሚና ነበረው፤ የገዳሙ ሕግ ተሻሽሏል በሚል አባላቱ በመሰናበታቸው፣ ለምዝበራና ብክነት ተጋልጧል፤ መንበረ ፓትርያርኩ አቤቱታቸውን ችላ ብሎ ገቢ በመሰብሰብ ብቻ መወሰኑን ተችተዋል፤ ኮሚቴው እንዲመለስና ቆጠራውም የባንክ ሠራተኞች በተገኙበት እንዲካሔድ ጠይቀዋል፤ አሠራሩ ተስተካክሎ ምዝበራው ካልቆመ፣ ሓላፊዎቹን ለሕግ እንደሚያቀርቡ አሳስበዋል፤ *           *           * ገዳሙን፣ የምሥራቅ ኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል የማድረግ ጅምር ነበር፤ በታኅሣሥና በሐምሌ በዓላት፣ በስእለትና በምጽዋት ከ40 ሚ. ብር በላይ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – የኤጲስ ቆጶሳት የመጨረሻዎቹ 31 ዕጩዎችና ተወዳዳሪዎች ታወቁ

የሐዋሳ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ አባ ሀ/ማርያም ገ/መስቀል ተካተዋል የጋምቤላው አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ ያለተወዳዳሪ በብቸኝነት ቀርበዋል ራሳቸውን ከጥቆማ አግልለው የነበሩት አባ ሚካኤል ገ/ማርያም ተይዘዋል የቅ/ላሊበላው አለቃ አባ ወ/ትንሣኤ አባተ እስከ2ኛው ዙር ተወዳዳሪ ነበሩ *               *              * ቅዱስ ሲኖዶስ በየአህጉረ ስብከቱ ክፍት በኾኑ መንበረ ጵጵስናዎች፣ ብቁ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም ባለው ዕቅድ መሠረት፣ ለምልአተ ጉባኤው ቀርበው ከታመነባቸው በኋላ በምርጫ የሚወዳደሩ የኤጲስ ቆጶሳት ዕጩዎች ታወቁ፡፡ የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ፥ ተጠቋሚ መነኰሳትንና ቆሞሳትን፤ በአየካባቢው በመለየት የመመርመር፣ የማጥናትና የማጣራት ሥራውን በማጠናቀቅ ዛሬ፣ ረቡዕ፣ ሐምሌ 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀትር በፊት፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ቀርበው በዕጩነታቸው ከታመነባቸው በኋላ በምርጫ የሚወዳደሩ 31 የኤጲስ ቆጶሳት ዕጩዎችን ለይቷል፡፡ ኮሚቴው፣ የመጨረሻዎቹን 31 ተጠቋሚዎች መለየት ብቻ ሳይኾን፣ ሢመቱ ለሚካሔድባቸው 16 አህጉረ ስብከት የሚወዳደሩትን ዕጩዎች እያጣመረ ማቅረቡም ታውቋል፡፡ ከዕጩዎቹ መካከል፣ የጋምቤላና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ፣ ያለተወዳዳሪ ለብቻቸው በመቅረባቸው፣ 32 መኾን የሚገባውን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ምንኵስናን “አደንዛዥ ዕፅ” የሚሉት የሆሳዕናው አባ ብንያም መንቾሮ ጵጵስና ይሻሉ፤ “ልጅ ሳልወልድ አልሞትም” እያሉ የሚዝቱ ቧልተኛና ሆድ አምላኩ ናቸው!

የተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኞችን፣ ለጉባኤ በመጋበዝና በማወደስ ግንባር ቀደም ናቸው ለቅዳሴ የተሠየሙትን ልብሰ ተክህኖ በማስወለቅ ለሥርዓቱ ንቀታቸውን አሳይተዋል በገና እና በሰኔ አጽዋማት ሉካንዳ ያዘወትራሉ፤ በሑዳዴም በጠዋት ገበታ ይሠየማሉ ውዳሴ ማርያም፣ ገድላት፣ ስግደት፣ ጾም፣ ፍትሐት፣ ንስሐ አያስፈልጉም፤ ብለዋል በጸሎተ ቅዳሴ ላይ ሳሉ በሞባይላቸው ፖርኖግራፊ ያያሉ፤ በፌስቡክ ቻት ያደርጋሉ ምንኵስናን “አደንዛዥ ዕፅ” በማለት እንደሕይወት ጥሪ ሳይኾን እንደሸክም ይቆጠራሉ “ለማግባት ባይሳካልኝም፣ ልጅ መውለዴ ግን የማይቀር ጉዳይ ነው፤” እያሉ ይዝታሉ *               *               * ከሰዎች ጋር ዓምባጓሮ በፈጠሩ ቁጥር፣ ቆባቸውንና ልብሳቸውን በማሳየት፣ “ይህ አደንዛዥ ዕፅ (ምንኵስና) ይዞኝ እንጂ እያንዳንዳችኹን በጫማ ጥፊ ነበር የምዘረጋችኹ፤” በማለት በዐደባባይ የሚናገሩና ምንኵስናን እንደ ጸጋ ሳይኾን እንደ ሸክም የሚቆጥሩ ናቸው፤ “ክርስቲያን መኾን ማለት በ40/80 ቀን ክርስትና መነሣት ወይም ነጭ ለብሶ ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣት አይደለም፤ ጌታን ተቀበል ሲሉህ አትከራከር፤ አትጨቃጨቅ፤ ወዳጄ፣ እጅህን አንሣና ጌታን ተቀበል፤” ሲል የተናገረውን በጋሻውን በመደገፍና በማሞካሸት፣ “እንዲኽ ዓይነት ደፋር መምህር በማጣታችን እስከ ዛሬ ተጎድተናል፡፡ ከዚኽ በኋላ ወደ ኋላ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የጋምቤላው አባ ተክለ ሃይማኖት ጵጵስና ከተሾሙ: “ምሥጢረ ክህነት ተራ ይኾናል፤ ቤተ መቅደስ ይረክሳል፤ የተሐድሶ መናፍቃን ይፈነጫሉ” ሲሉ አገልጋዮች አስጠነቀቁ

መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ  ኤጲስ ቆጶስነት ቢሾሙ ምን ሊፈጠር ይችላል? በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡ ይድረስ፡- ለኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ፤ የጋምቤላ ክልል፣ ሊቀ ጳጳስ ሳይኖረው መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይኹን እንጂ፣ የጋምቤላና ደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የኾኑት፣ መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት በኤጲስ ቆጶስነት ሊመረጡ መኾኑን ጭምጭምታ ስንሰማ፣ በጣም አዘንን፤ ምክንያቱ ምንድን ነው ከተባለ ከዚኽ በታች አቅርበነዋል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት በቀኖናቸው፡- ትምህርት ያለው ኤጲስ ቆጶስነት ይሾማል፤ ሥራውን ውሎ አድሮ ይማረዋል፤ በትምህርት መናፍቃንን ተከራክሮ ይረታልና ሥራ ያለው ይሾም፤ በትሩፋቱ በጸሎቱ ሰውን ያጸድቃልና፤ እንዳሉ እናውቃለን፡፡ በአንፃሩ፣ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት፣ ኹሉም የሌላቸው መኾኑን እናውቃለን፡፡ እኛ የጋምቤላ አገልጋዮች ይህን ጽሑፍ ስንጽፍ፣ ዓላማችን፣ ቤተ ክርስቲያንን በሥርዓት የሚያስተዳድር፤ ለቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ክብር የሚሰጥ አባት ቤተ ክርስቲያን እንድታገኝ ከመፈለግ አንፃር እንጂ፣ በእርሳቸው ቅናት፣ ምቀኝነት ወይ ጠብ ኖሮን አይደለም፡፡ የጻፍነው ኹሉ ትክክል መኾኑን በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መጥቻሁ ከምእመናንና ከቀሳውስት መረዳት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለኤጲስ ቆጶሳት ምርጫው: ከወሎና ከሰሜን ሸዋ አህጉረ ስብከት ለመጨረሻው ዙር ማጣርያ ያለፉ ዐሥር ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት

በቀሪዎቹ 68 ተጠቋሚዎቹ ላይ፣ ማጣራቱ ይቀጥላል እስከፊታችን ዓርብ 32ቱ ዕጩዎች ይታወቃሉ ተብሏል በቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ፣ ከወሎ እና ከሰሜን ሸዋ አህጉረ ስብከት ለመጨረሻው ዙር ማጣራት የሚያካሒድባቸውን፥ ዐሥር ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት ለየ፡፡ በዚኽም መሠረት፣ እስካለፈው ሰኞ ድረስ፤ ከወሎ 15፣ ከሰሜን ሸዋ 13 የነበሩት ተጠቋሚዎች፣ ከእያንዳንዳቸው እንደ ቅደም ተከተላቸው፣ በዐሥር እና በስምንት ቀንሰው፣ ለመጨረሻ ዙር ማጣራት የሚካሔድባቸው አምስት፣ አምስት ተጠቋሚዎች መለየታቸው ታውቋል፡፡ ይህም ከ118 ጠቅላላ ተጠቋሚዎች ወደ 86 ቀንሶ የነበረውን ቆሞሳትና መነኰሳት ቁጥር፣ እስከ ዛሬ፣ ሐምሌ 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ባለው አኃዝ ወደ 68 እንዲወርድ አድርጎታል፡፡ ኮሚቴው፣ እስከ መጪው ሳምንት ዓርብ፣ ቀሪ ተጠቋሚዎችን የማጥናት፣ የመመርመርና የማጣራት ሥራውን በማጠናቀቅ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምርጫ የሚቀርቡትን 32ቱን የኤጲስ ቆጶሳት ዕጩዎች እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል፡፡ ሹመቱ፣ ክፍት በኾኑና መንበረ ጵጵስና ላላቸው 16 አህጉረ ስብከት የሚደረግ ሲኾን፤ ለየመንበረ ጵጵስናው ኹለት፣ ኹለት ዕጩዎች በምርጫ ይወዳደራሉ፡፡ *                *                * ከወሎ አህጉረ ስብከት ለመጨረሻው ዙር ማጣራት ያለፉ አምስቱ ተጠቋሚዎች፡-
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ጵጵስናው ያልተሳካላቸው አባ ገብረ ሕይወት ገ/ሚካኤል: “በዶላር ተሽጧል” አሉ፤ በዘማነታቸው ከድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል እልቅና ተባረሩ!

የሰበካ ጉባኤ አባሏን፣ በምሽት እየደወሉ በብልግና ጥያቄዎች ሲያስጨንቁ ቆይተዋል፤ ምንኵስናቸው እንደማይከለክላቸውና ሲሾሙ እንደሚወስዷቸው በመግለጽ አባብለዋል፤ “ሲያስጨንቁኝና ዕንቅልፍ ሲነሱኝ ስለቆዩ ላጋልጣቸው ወሰንኩ”/ተበዳዩዋ ምእመንት/ የክህነት አገልግሎታቸው፣ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተመርምሮ እንዲወሰን ተጠይቋል፤ በሕዝቡ ጥያቄና በሊቀ ጳጳሱ መመሪያ፣ የወር ደመወዝ ተሰጥቶአቸው ተሰናብተዋል! ቀድሞም ከአኵስም ጽዮን ንቡረ እድነት የተነሡት፣ ቀኖናዊ ባልኾነ ድርጊታቸው ነው፡፡ *                *               * ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በየአህጉረ ስብከቱ ክፍት በኾኑ መንበረ ጵጵስናዎች ብቁ ኤጲስ ቆጶሳትን መርጦ ለመሾም ባለው ዕቅድ መሠረት፣ ከድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ከተጠቆሙት አባቶች አንዱ የነበሩትና በመጀመሪው ዙር ማጣሪያ የወደቁት የሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል አስተዳዳሪ፣ ንቡረ እድ አባ ገብረ ሕይወት ገብረ ሚካኤል፣ “ጵጵስናው በገንዘብ ተሽጧል” ማለታቸው ካህናትንና ምእመናን ያስቆጣ ሲኾን፤ እየፈጸሙት ባለው የዝሙት ነውርና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ የኾነ ድርጊት ከሓላፊነታቸው እንዲወገዱ ሲቀርብ በሰነበተው ጥያቄ መሠረት፣ ዛሬ፣ ሐምሌ 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል በተላለፈ መመሪያ እንዲሰናበቱ መደረጉ ተገለጸ፡፡ የካቴድራሉ 16 መምህራን፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት፤
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለጵጵስና የተጠቆሙት በጥንቆላ አታላዩ: አባ ተክለ ማርያም አምኜ(ነቅንቅ) ማን ናቸው? በምስክርነት ሊቀርቡ የሚችሉ ካህናትና ምእመናን አቤቱታ

ለአስመራጭ ኮሚቴው መቅረቡ የተገለጸው የተቃውሞ አቤቱታ፤ አባ ተክለ ማርያም አምኜ፣ በትውልድ ሀገራቸው አካባቢ ሥርዓተ ጋብቻ ፈጽመው እንደኖሩ፣ ሚዜዎቻቸውን በእማኝነት በመጥቀስ ያጋልጣል፡፡ ይህ በኾነበት ለኤጲስ ቆጶስነት መጠቆማቸው፣ “በሥርዓተ ድንግልና መንኩሶ ቤተ ክርስቲያንን በክህነት ያገለገለ” የሚለውን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገ ቤተ ክርስቲያን በቀጥታ የሚቃረን ነው፡፡ የአዊ ሕዝብ ደግፎኛል፤ በሚል አሰባሰብኩ ያሉትን የምእመናን ፊርማ አቅርበዋል በጥንቆላ ማታለል፤ ዝሙትን በጀብድ መናገር፤ ዘረፋና ማጭበርበር ልማዳቸው ነው “ከሓላፊነት አውጥታችሁ፣ ከእይታ ዘወር ያለ ሥራ ሰጥታችሁ አሳርፉን”/አቤቱታው/ *               *               * በቤተ ክርስቲያናችን የክህነት አሰጣጥ፥ ዕጩ ካህናት ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁ ያስፈልጋል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚያውቁ፤ ከዚኽም ጋር ሙሉ አካልና የመንፈስ ጤንነት ያላቸው ካህናት እንዲሾሙ ታዟል፡፡ ዲያቆናት ሚስት ካገቡ በኋላ ወይም መንኵሰው የቅስና ማዕርግ ይቀበላሉ፡፡ ኤጲስ ቆጶስ ለመኾን መብት ያላቸው ግን፡- በድንግልና የመነኰሱ፣ የቅስናና የቁምስና ማዕርግ ያላቸው ናቸው፡፡ ማዕርገ ዲቁና ከተቀበሉ በኋላ ሚስት ለማግባት ይቻላል፡፡ የቅስና ማዕርግ ከተቀበሉ በኋላ ግን ለማግባት አይቻልም፡፡ ኤጲስ ቆጶስ በማይገኝበት ቦታ፣ እንደ ኤጲስ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ብዛት 16 ነው፤ በየአካባቢው የተለዩትን ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት ወቅታዊ የስም ዝርዝር ይመልከቱ

መረጃዎችና አቤቱታዎች በዋና ጸሐፊው በኩል ለአስመራጭ ኮሚቴው ይቀርባሉ ማስረጃዎቹ እና አቤቱታዎቹ ባለቤታቸው የታወቁ እና የተረጋገጡ ሊኾኑ ይገባል ትኩረትና ተጨማሪ ማስረጃ የሚያስፈልጋቸውን ተጠቋሚዎች ለመለየት አግዘዋል የምንኵስና፣ የክህነት፣ የትምህርትና የውጤታማነት ማስረጃዎች በጥብቅ ይፈተሻሉ *                 *                * የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ በዕጩነታቸው ካመነባቸው በኋላ፣ በቅርቡ ተመርጠው እንደሚሾሙ የሚጠበቁት ኤጲስ ቆጶሳት ብዛት፣ 16 እንደኾነ ተገለጸ፡፡ በየአህጉረ ስብከቱ ክፍት በኾኑ መንበረ ጵጵስናዎች፣ ብቁ ኤጲስ ቆጶሳትን መርጦ ለመሾም ቅዱስ ሲኖዶስ በያዘው ዕቅድ መሠረት፣ በቅርቡ 16 ኤጲስ ቆጶሳት እንደሚሾሙና፤ ለዚኽም 32 ዕጩዎች በተወዳዳሪነት እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡ ባለፈው ዓርብ፣ ሐምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ በተካሔደው የቋሚ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ፣ በርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው፣ የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ የሥራ ክንውን ውይይት ከተደረገበት በኋላ መመሪያዎች መሰጠታቸው ተጠቅሷል፡፡ ከ118 ያላነሱ ቆሞሳትንና መነኰሳትን ስም ዝርዝር፣ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በጥቆማ የተቀበለው ኮሚቴው፤ ተጠቋሚዎቹን በየአካባቢው ከለየ በኋላ የማጣራት ሥራውን በማከናወን ላይ እንዳለ ተመልክቷል፡፡ ኮሚቴው፣ ቆሞሳቱንና መነኰሳቱን በየአካባቢው ከለየ በኋላ በቀጠለው የማጣራት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ካህናትና ሕዝቡ በተሳተፉበት ምርጫ ጵጵስና መሾም ታላቅ ዕድል ነው፤ ከነቀፌታ የጸዱትን ለማግኘት ብዙ ማጣራት ያሻል/ብፁዕ አቡነ ሙሴ/

ለኤጲስ ቆጶስነት ከሚያበቁ መስፈርቶች ቀዳሚው፣ የቅድስና ሕይወት ነው የቅድስና እና የድንግልና ሕይወቱ፤ በሕዝብ የተመሰከረለት መኾን አለበት የሕዝብ አስተያየትና የካህናቱ ግምገማ ከሌለ፣ አባቶችን ማግለል ይከተላል ከምርጫ በኋላ ሳይሾሙ ማቆየት፣ ችግር ያለባቸውን ለመቃወም ያስችላል ሢመቱ፥ በወገን ብዛት፣ በገንዘብ ኃይል አይደለም፤ መኾንም የለበትም ከእኛ የተሻሉ፤ከነቀፌታ የጸዱ አባቶችን ለማግኘት ብዙ ማጣራት ያሻል *               *               * ብፁዕ አቡነ ሙሴ፣ አኹን ለደረሱበት ከፍተኛ ሓላፊነት፣ በ1989 ዓ.ም. ከሌሎች ጋር ተወዳድረው ከተመረጡ በኋላ፤ በ1991 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ በኤጲስ ቆጶስነት ማዕርግ ተሾሙ፡፡ እንደተሾሙ፣ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ ለተወሰነ ጊዜ ከሠሩ በኋላ፤ በምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት ለኹለት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ብፁዕነታቸው፣ ምሥራቅ ትግራይ(ዓዲ ግራት) ከገቡ በኋላ፣ በአካባቢው በተደጋጋሚ ይከሠት የነበረው ድርቅ ተወግዶ በምትኩ ዝናም በመዝነሙና አዝመራው ተሳክቶ ጥጋብ በመኾኑ የዓዲ ግራት ሕዝብ፣ “የበረከት አባት” የሚል የቅጽል ስም ሰጥቷቸዋል፡፡ ከምሥራቅ ትግራይ ወደ ሀገረ እንግሊዝ እንደተዛወሩም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን አስፋፍተዋል፡፡ ዳግም ወደ አገራቸው ተመልሰው፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የኤጲስ ቆጶሳት ዕጩዎችን የማሳወቂያው ጊዜ በ15 ቀናት ተራዘመ፤ ከ118 ባላነሱ ተጠቋሚዎች ላይ ግምገማና ምዘና እየተካሔደ ነው

ካህናት እና ምእመናን መረጃዎችንና አቤቱታዎችን ወደ አስመራጭ ኮሚቴው እያጎረፉ ነው የዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት እና የሚሾሙባቸው አህጉረ ስብከት ቁጥር እንደሚጨምር ተጠቁሟል የኑፋቄው ሕዋስና የአማሳኙ ቡድን፥ ምልምሉን ለማሾምና ‘ስጋቱን’ ለማስወገድ እየሠራ ነው ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ሢመቱ፣ ከዘመን መለወጫ በፊት እንዲከናወን ፍላጎት አላቸው ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ እንጂ ሕዝብን የሚያሳዝን እንዳይኾን ማሳሰቢያዎች እየተሰጡ ነው *               *                * በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ፣ ተጠቋሚ መኰሳትንና ቆሞሳትን ገምግሞና መዝኖ ተወዳዳሪ ዕጩዎችን በመለየት የሚያሳውቅበት ጊዜ በ15 ቀናት መራዘሙ ተገለጸ፡፡ ኮሚቴው፣ ተጠቋሚዎቹን በመመርመር፣ በማጥናትና በማጣራት ውጤቱን እስከ ትላንት፣ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዲያቀርብ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ በርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤው ወስኖ የነበረ ቢኾንም፤ የተጠቋሚዎቹ ብዛትና ሒደቱ የሚጠይቀው ከፍ ያለ ጥንቃቄ የቀነ ገደቡን መራዘም አስፈላጊ አድርጎታል፡፡ ቀደም ሲል ለሹመት የሚያስፈልጉት ሐዲሳን ኤጲስ ቆጶሳት ከ14 – 16 እንደሚኾኑ ቢገለጽም፤ በሞተ ዕረፍት በተለዩትና በእርግና በሚገኙት አባቶች ምክንያት ክፍት ከኾኑት መንበረ ጵጵስናዎች ብዛት አንፃር፣ በኮሚቴው የሚቀርቡ ዕጩዎችና የሚሾሙባቸው አህጉረ ስብከት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለጵጵስና በተጠቆሙት የቨርጂኒያው አባ ፊልጶስ ከበደ ላይ የምእመናን አቤቱታ ቀረበ፤ ፀረ ቅዱሳን፣ ሞያ ቢስ፣ ሐኬተኛና አድመኛ ናቸው

በቅስናቸው በቂ ሞያ የሌላቸው፣ ካህናትንና ምእመናንን የሚከፋፍሉ አድመኛ ናቸው በሂዩስተን ሕፃናትን በግብረ ሰዶማዊነት በማበላሸት (child molestation) ይታወቃሉ በፖሊቲካ ጥገኝነት የሚኖሩት ቤተ ክርስቲያንን በማሳጣትና ሲጠሩም ፈርጥጠው ነው ክብረ ክህነትንና የተቀደሱ ምስጢራትን የሚያቃልሉ፣ ሐኬተኛና እምነት አልባ ናቸው ለተወገዱት ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በርካታ ገንዘብ እንደሰጡ ተናግረዋል የዘመናት ምኞታቸው ጵጵስና ነው፤ በሻንጣ ልብስ በመደለል እንደሚያገኙት ያስባሉ *          *          * ኤጲስ ቆጶስ በሕዝብ ተመርጦ ለሕዝብ የሚሾም የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፡፡ በሹመቱ “ገብር ኅሩይ ዘእግዚአብሔር = የእግዚአብሔር ምርጥ አገልጋይ” ሊባል የሚችለው፡- ስለ ደግነቱና ትሩፋቱ፤ ስለ ንጽሕናውና ከነውር የራቀ ስለመኾኑ፣ ሊቀ ጳጳሱ በሚመራው ጉባኤ በካህናትና በምእመናን ምስክርነት ሲረጋገጥለት ነው፡፡ ደግነቱ ያልታወቀ፣ ስለ ሠናይ ተግባራቱ መልካም ምስክርነት የሌለው ቆሞስ እና መነኵሴ ነኝ ባይ ኹሉ፥ በሲሞናዊነት፣ በአድርባይ ፖሊቲከኞችና በጎጠኞች መንገድ ካልኾነ በቀር ኤጲስ ቆጶስነት ሊሾም አይችልም፤ አይገባም፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናችን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያናችንና የምርጫ ማስፈጸሚያ ደንቡ፥ ሹመቱ ስለሚገባቸው ቆሞሳትና መነኰሳት ያስቀመጧቸው መመዘዎች፤ የተቆጠሩና የሚለኩ ናቸው፡፡ ኤጲስ ቆጶስ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ከልዩ ጽ/ቤቱ ተወገዱ!

ምንም ዓይነት ምደባ አልተሰጣቸውም ምደባቸውን በውጭ ኾነው ይጠባበቃሉ “ቦታ የለኝም”/ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ/ ቀጣዩ ልዩ ጸሐፊ ከዋና ሥራ አስኪያጁ ጋር በመመካከር ይመደባል፤ ተብሏል *               *               * በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የልዩ ጸሐፊነት ሥልጣናቸው ተገን፣ የሙስና ሰንሰለት ዘርግተው ሕገ ወጥ ሀብት በማካበትና በክፉ ምክራቸው ለበርካታ የውስጥ አለመግባባት መንሥኤ የነበሩት የመዝባሪዎች አለቃ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ከሓላፊነታቸው ተወገዱ!! ልዩ ጸሐፊው፣ በእጃቸው የሚገኘውን ንብረት፣ ዛሬ፣ ሰኞ፣ ሰኔ 27 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ቀሲስ፣ አባ ኪዳነ ማርያም ደስታ አስረክበው፣ ልዩ ጽ/ቤቱን እንዲለቁ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከቅዱስነታቸው በተላለፈ ትእዛዝ መሠረት ነው፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከልዩ ጽ/ቤት ሓላፊነታቸው የተወገዱት፡፡ ንቡረ እድ ኤልያስ፣ ከሓላፊነታቸው ከተወገዱ በኋላ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከሚገኙት ድርጅቶች አልያም መምሪያዎች በአንዱ፣ በዋና ሓላፊነት ሊመደቡ እንደሚችሉ ቀደም ብሎ ቢዘገብም፣ ምንም ዓይነት ምደባ እንዳልተሰጣቸውና በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቦታ ተገኝቶላቸው እስኪመደቡ ድረስ እንዲጠባበቁ በፓትርያርኩ ከተጻፈላቸው የማሰናበቻ ደብዳቤ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የኮሌጆቻችን ምሩቃን: እንኳን ደስ አላችኹ፤ በጎች ምእመናንን በአደራ የተቀበላችኹበት ቀን ነው፤ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ምስክር መኾን ይጠበቅባችኋል

በቀጣዩ ዓመት የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ወደ ሙሉ ዩኒቨርስቲ ይሸጋገራል የሥርዓተ ትምህርቱና የዩኒቨርስቲ ኮሌጆች አወቃቀር ጥናቱ እየተከናወነ ነው አጋዥ የዕውቀት ዘርፎች የሚበለጽጉበት ማዕከል ይኾናል /አቡነ ጢሞቴዎስ/ የማይነጥፉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ምንጭ ይኾናል /አቡነ ዲዮስቆሮስ/ የዕውቀት ችሎታን ከፍ ለማድረግ እንጂ ለይስሙላ አልተደረገም/ፓትርያርኩ/ *               *               * ያለፉት ኹለት ሳምንታት፣ ለቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳውያን ኮሌጆች፣ የደቀ መዛሙርት ምረቃ ሳምንታት ነበሩ፡፡ ከሦስቱም ኮሌጆች፥ በተለያዩ የቀን መደበኛ፣ የማታ ተከታታይና የርቀት መርሐ ግብሮች የተመረቁት ደቀ መዛሙርት አጠቃላይ ብዛት 604 ነው፡፡ ከእኒኽም፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፡- 287፤ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፡- 237፤ የአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ቅዱስ ፍሬምናጦስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፡- 80 ደቀ መዛሙርትን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ አስመርቀዋል፡፡ ምሩቃን ደቀ መዛሙርትንና ዕጩ መምህራንን በሙሉ፤ እንኳን ደስ ያላችኹ፤ እያልን፣ መልካም የአገልግሎት ጊዜ እንመኝላቸዋለን፡፡ በምረቃው መርሐ ግብራት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የኹለቱ ኮሌጆቹ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለጵጵስና የተጠቆሙት አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ: ከኦክላንድ ደብረ ኢየሱስ በዝሙት ቅሌት የተባረሩ፤ “የኢትዮጵያ ሕዝብ በጌታ ሳያምን በውኃ ይጋፋል” ያሉ መናፍቅ ናቸው!

በተማሪነቱ፣ የመናፍቅነት ጠባይ እና ዝንባሌ በማሳየት፣ በደቀ መዛሙርት ማስረጃ ቀርቦበታል ከምእመናን ያለደረሰኝ የሰበሰበውን 10ሺሕ ዶላር፣ ለምን እንዳዋለው ሳይታወቅ ተጠቅሞበታል በ3ሺሕ500 ዶላር ለተዋዋለበት ሥራ 500 ዶላር በመክፈል እምነት አጉድሏል፤ አደራ በልቷል መናፍቅነቱ፣ ጥቅመኛነቱ እና ሴሰኛነቱ፤ በሔደባቸው ስቴቶች ኹሉ መጠጊያ ሲያሳጣው ኖሯል *               *               * “ሴትን ለግላዊ ሥጋዊ ጥቅም ብቻ መገልገል” በሚሰኝ “sadistic” ፍትወቱና ግብሩ ይታወቃል ጋለሞታዎችን አሳዳጅ ነው፤ባለትዳር ሴቶችንም በማማገጥ ለቤተሰብ መፍረስ መንሥኤ ኾኗል የቤቱ፣ የሆቴልና የሞቴል ቅንዝረኛነቱ ሳይበቃ በቤተ ክርስቲያን ቢሮና ማረፊያም አይታቀብም የኦክላንድ ምእመናን፣ ለሴት ሕፃናትና አዳጊዎቻቸው የሚሰጉት ጉምዡና ሴሰኛ ኾኖ ቆይቷል *               *               * የዝሙት ቅሌቱ በምስክሮች፣ በፎቶና በቪዲዮ ማስረጃዎች ተረጋግጦ ከቤተ ክርስቲያን ተባሯል በፓትርያርኩ ወዳጅ አግባቢነት ወደ ሀገር ተመልሶ የጠቅ/ጽ/ቤት የውጭ ጉዳይ ሓላፊ ኾኗል የውጭ ግንኙነት ጉዳዮችን፣ የእናት ቤተ ክርስቲያንን አንድነት በሚጎዳ መልኩ እየመራ ይገኛል ቅ/ሲኖዶስ ከሓላፊነቱ እንዲነሣ ቢወስንም፤ ለማዕርገ ጵጵስና ተጠቁሞ ወደ ግቡ እየተዳረሰ ነው *               *               * የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ክፍት በኾኑ የአህጉረ ስብከት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

“የእግዚአብሔር ምርጥ” ኤጲስ ቆጶስ ማን ነው? በፍቅረ ንዋይ ያበዱትንና የውድቀት ታሪክ የሞላባቸውን ጎጠኞችና ሲሞናውያን እናጋልጥ!

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት አባቶች ያኖሩትን ትምህርት በመጣስ፣ አንድ ሰው፣ አምኛለኹ፤ በቅቻለኹ ብሎ ቢቀርብ እንኳ ቤተ ክርስቲያን መሾም የለባትም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ማዕርግ በታማኝነት ሊያገለግሏት የሚችሉትን አገልጋዮች በጥንቃቄ መምረጥ አለባት፡፡ የአበውን ትውፊት በመጣስ፣ የዕድሜን የአገልግሎትን ኹኔታ ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገቡ ቢሾሙ፤ በዲያቢሎስ ሽንገላ በትዕቢት እየተነፉ፣ እነርሱም ሳይገለገሉ ቤተ ክርስቲያንንም ሳያገለግሉ የጥፋት መሣርያ ይኾናሉ፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥሯን መሠረቷን የሚያውቁ፤ በገድል የተቀጠቀጡና በትሩፋት ያጌጡ፤ በአጠቃላይ በቅድስና ሕይወት ጸንተው የኖሩ አባቶችን ከገዳም ጭምር እየፈለገች መሾም ይጠበቅባታል፡፡ በቅድስናቸው የተመሰከረላቸውን አባቶች መሾም፣ በእውነት ምእመናንን በጸሎታቸው የቅድስና ሕይወታቸው ተካፋይ ያደርጋቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በአግባቡ ያላገለገሉ፤ በገዳማዊ ሕይወት ያልተፈተኑ ሰዎች፤ በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድ የወደቁ፤ በፍቅረ ንዋይ ያበዱ፤ የውድቀት ታሪክ ያላቸው ሰዎች ያለምንም መስፈርት ሳይመረመሩ ቢሾሙ፣ ቤተ ክርስቲያንን ሊመሯት አይችሉም፤ እንሥራ ቢሉም ይጎዷታል፡፡ ስለዚኽ በአገልግሎት ያልተፈተኑ በውጭ ባሉ ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር የሌላቸውን ሰዎች መሾም አደጋው
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የአ/አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት በተሐድሶ ኑፋቄ አደጋ ውስጥ! ‘አባ’ አፈ ወርቅ ዮሐንስ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተመደበ፤15 አለቆችና ጸሐፊዎችም ተዛውረዋል

ከሆሮ ጉድሩና ወሊሶ በምግባር ብልሽትና በእምነት ሕፀፅ ቢባረርም፤ በቀድሞው የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅነት ተመድቦ በምዝበራ የቆየውና፤ ከውጭ ጉዳዩ ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ ጋር ባለው የዓላማና የጥቅም ግንኙነት፤ ከፓትርያርኩ በተሰጠ ቀጥተኛ አመራርና በሥራ አስኪያጁ ጎይትኦም ያይኑ በተፈረመ ደብዳቤ፣ በዛሬው ዕለት፣ በሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት የተመደበው፣ መናፍቁ እና ዋልጌው መልአከ ገነት ’አባ’ አፈ ወርቅ ዮሐንስ በምደባው፥ የውጭ ጉዳዩ ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ፣ ፓትርያርኩን በመማለድ ሚና ተጫውቷል በአሜሪካ ያሉት፣ ረዳት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ስለማወቃቸው አጠያያቂ ኾኗል ከወሊሶ በብልሹነቱ ሲባረር፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ በሥ/አስኪያጅነት ተመድቦ ቆይቷል በክፍለ ከተማው፣ በአጥቢያዎች የቦታ ኪራይ ሙስና፣ በእምነት ሕፀፅና በዘለፋው ይታወቃል ከጎይትኦም ቀጥሎ፣ በከፍተኛ ሓላፊነት የተቀመጠ የተሐድሶ መናፍቅ መኾኑ ነው!!! *               *             * ዝውውሩ፥ ጎይትኦም ያይኑ፣ ከአስተዳደሩ ይልቅ ከንቡረ እድ ኤልያስጋ የመከረበት ነው ሀገረ ስብከቱ፣ “ተሸጠናል” በሚሉት እና ዝውውሩን በሚደግፉት መካከል እየታመሰ ነው እነንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ በሥራ አስኪያጁ አማካይነት በመቶ ሺሕዎች
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የቆሞሳትና መነኰሳት ጥቆማ እየተካሔደ ነው፤ የካህናትና የምእመናን መረጃና አስተያየት በእጅጉ ይፈለጋል

(መመዘኛውንና የተጠቆሙትን ቆሞሳትና መነኰሳት የስም ዝርዝር ይመልከቱ) የሚሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት ብዛት ከ14 ‐ 16 ሲኾኑ፤ 28 ዕጩዎች ብቻ ለውድድር ይቀርባሉ ተጠቋሚዎች፣ የሚሾሙበትን ሀ/ስብከት ቋንቋ ማወቅ ከመሠረታዊ መመዘኛዎች አንዱ ኾኗል አስመራጭ ኮሚቴው በቀጣዩ ሳምንት የተጠቋሚዎችን ማንነት ማጣራት ይጀምራል፤ ተብሏል  *               *               * ከተጠቋሚዎቹ፣ ንጹሐንና ብቁዎች ያሉትን ያኽል ኑፋቄ፣ ነቀፌታና ነውር የሞላባቸውም አሉ አስመራጭ ኮሚቴውን በአማላጅ፣ በእጅ መንሻና በውዳሴ ከንቱ የሚያጨናንቁ እንዳሉ ታውቋል ካህናትና ምእመናን፣ ስለብቃታቸው፣ ከነውርና ነቀፌታ ስለመራቃቸው ሊመሰክሩላቸው ይገባል  *               *               * ማስገንዘቢያ፡‐ ከዚኽ በታች የሰፈረው የተጠቋሚ መነኰሳትና ቆሞሳት የስም ዝርዝር፣ በተለያዩ መንገዶች የተሰበሰበና ከእነርሱም የሚበዙት ለአስመራጭ ኮሚቴው ስለመድረሱ የተገለጹትን ብቻ የሚያካትት ነው፤ በመኾኑም ዝርዝራቸውን የማሳወቁ ኹኔታ ቀጣይነት ይኖረዋል፤ የስም ዝርዝሩ፣ ለጡመራ መድረኩ በተላከበት ቅደም ተከተል የቀረበ ሲኾን፤ የተጠቋሚዎችን አስማተ ማዕርጋት ያልያዘና በተወሰነ መልኩም የአባት ስም ያልተጠቀሰበት ነው፤ ሹመት የሚያስፈልጋቸው አህጉረ ስብከት፡- ሰሜን ምዕራብ ትግራይ/ሽሬ/፣ ምሥራቅ ትግራይ/ዓዲ ግራት/፣ ማዕከላዊ ዞን ትግራይ/አኵስም/፣ደቡብ ጎንደር/ደብረ ታቦር/፣ ዋግ ኽምራ/ሰቆጣ/፣ ደቡብ ወሎ በአማራ ክልል ኦሮሚያ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ፓትርያርኩ: ምእመናን፣ የቴሌቭዥን አገልግሎቱን እንዲደግፉና እንደ ዓይን ብሌን እንዲጠብቁት ጥሪ አቀረቡ

የምእመናን ሀብትና ንብረት የኾነ የቤተ ክርስቲያኗ ልዕልና መገለጫ ነው ሃይማኖታዊ ሰብእና ያለው ጤናማ ማኅብረሰብ ለመገንባት የታሰበበት ነው በተለይ ወጣቱ፣ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን በንቃት ሊከታተልበት ይገባል ደማቁን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሲማር ኢትዮጵያንም እዚያው ያገኛታል *               *               * የሙከራ ስርጭቱ መጀመር በመንበረ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት በይፋ በተበሠረበት ወቅት(ፎቶ: አ/አበባ ሀ/ስብከት) ቤተ ክርስቲያናችን ለሚዲያ አገልግሎት ትኩረት መስጠቷ፥ ዐዋቂውም ኾነ ወጣቱ ትውልድ፥ ስለሃይማኖቱ እና ስለታሪኩ፣ ስለሀገሩና ስለማንነቱ፣ ስለባህሉና ስለትውፊቱ ማወቅ የሚገባውን ዐውቆ የባለቤትነትና የታሪክ ጠባቂነት ሓላፊነትን እንዲሸከም ለማድረግ ነው፤ ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፤ ገናናዋ ቤተ ክርስቲያናችን ድምፅዋን በመላው ዓለም ለሚገኙ ልጆችዋ የምታሰማበትን የብዙኃን መገናኛ፣ ምእመናን ኹሉ እንዲደግፉና እንደ ዓይናቸውም ብሌን እንዲጠብቁት ጥሪ አቀረቡ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ “ለረጅም ጊዜ በጉጉት ስትጠባበቁት የነበረውን የታላቋ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ድምፅ፤ እግዚአብሔር ለፍጡራን በሰጠው አእምሮ በተሠራ በዚህ የብዙኃን መገናኛ ለመስማት በመብቃታችኹ እንኳን ደስ አላችኹ!!” በማለት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቭዥን አገልግሎት (EOTC tv.) የሙከራ ስርጭቱን በይፋ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የጋምቤላ ፕሬዝዳንት: የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ጵጵስና እንዲሾሙላቸው ፓትርያርኩን ጠየቁ፤ ሌላ አባት ቢመደብ ክልሉ እንደማይቀበል አስጠነቀቁ

ክልላዊ መንግሥቱ፡- “የጋምቤላ እና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ጳጳስ” ኾነው በአባትነት እንዲቀመጡ ጠይቋል በ2ሺሕ ካ.ሜ. መሬት መንበረ ጵጵስና እያስገነባ ሲኾን፤ የቤት መኪናም አዘጋጅቻለኹ፤ ብሏል “ሕገ መንግሥቱ እንደሚያዝ የሕዝብ ድምፅ ይከበርልን” ሲል ክልላዊ አቋም እንደኾነ ገልጧል ለ7ኛ ጊዜ መጠየቁን አስታውሶ፣ “ሌላ ጳጳስ ቢመደብ ከባሮ ቆላ ከኤርፖርት አናሳልፍም” ብሏል *** ርእሰ መስተዳደሩ ጋትሉዋክ ቱት ኮት፡- “ከአባ ተክለ ሃይማኖት ውጪ ጳጳስ፣ አባት አንፈልግም፤ ሲኖዶስ በጫና ቢመድብብን የግንኙነት መስመራችን ይበጠሳል፤ ቢመጣም ከባሮ ቆላ ከኤርፖርት አናሳልፍም፤ አንቀበልም፡፡” *** ጵጵስና፣ ክህነታዊ ማዕርግ በመኾኑ ቀኖናዊና መንፈሳዊ ሹመት እንጂ እንደ ሕዝባውያን በ“ድምፃችን ይከበር” ዓይነት ውትወታ(lobby) ብቻ የሚወሰን አይደለም፤ የሥራ አስኪያጁ የአገልግሎት ፍሬዎችና የድጋፍ መሠረቶች፣ በአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መሪነት ተረጋግጦ፤ ጥቆማውም፣ በደንቡ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል፡፡ በዛቻና በማስፈራሪያ መልክ የቀረበው የርእሰ መስተዳደሩ ጥያቄ ኢ-ሕገ መንግሥታዊና ኢ-ቀኖናዊ በመኾኑ ያለማመንታት መታረም ይኖርበታል፤ ይህንንም በማድረግ ቤተ ክርስቲያናችንንም ራሳቸውንም የማስከበሩ ቅድሚያ፣ ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጀመር ይገባዋል፤ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ “ይደልዎ፤ ይደልዎ” ተብሎ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቤተ ክርስቲያናችን የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት የሙከራ ስርጭት መጀመር በፓትርያርኩ ቡራኬ ይፋ ይደረጋል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቴሌቭዥን አገልግሎት(EOTC tv) የሙከራ ስርጭት መጀመር፣ ዛሬ፣ ሰኔ 16 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቡራኬ ይፋ ይደረጋል፡፡ ቅዱስነታቸው፣ የሙከራ ስርጭቱን መጀመር አስመልክቶ፣ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የመምሪያ ሓላፊዎችና የብዙኃን መገናኛ ስርጭት ድርጅቱ የቦርድ አባላት በተገኙበት በጽ/ቤታቸው ለብዙኃን መገናኛ መግለጫ እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱን ሎጎ/መለዮ/ በመጠቀም የሙከራ ስርጭቱን(logo display) የጀመረው አገልግሎቱ፣ በቀጣይ ልዩ ተልእኮውን የሚገልጽ የራሱ ሎጎ ይኖረዋል፤ ለዚኽም ግልጽ የውድድር ማስታወቂያ እንደሚያወጣ ተጠቁሟል፡፡ አጠቃላይ የሰው ኃይሉን(በይዘት ዝግጅት እና በኤዲቶሪያል ኮሚቴዎች) ለማዋቀርም፤ ባወጣው ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ መሠረት በሠራተኞች ቅጥር ሒደት ላይ ይገኛል፡፡ ቢሮውን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አድርጎ፣ ለስርጭት የሚኾኑትን ማናቸውንም ፕሮግራሞች በሀገር ውስጥ የሚያዘጋጀው አገልግሎቱ፤ በውሉ መሠረት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ጋር በተደረገ ስምምነትና ገዳሙ ካለበት ከኢየሩሳሌም በሚገኝ የሳተላይት ድርጅቱ ቢሮ አማካይነት ስርጭቱን ያከናውናል፡፡ ለምሥራቅና ሰሜን አፍሪቃ እንዲኹም ለመካከለኛው ምሥራቅና ደቡብ አውሮጳ በናይል ሳት፤ ለሰሜን አሜሪካ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሳይመረምር በፖለቲካና በጎጠኝነት የሚሾም፥ በክፉ ሥራ ይሳተፋል፤ በእግዚአብሔርም ይጠየቃል፤ በሀገረ አሜሪካ የሚስተዋለው እውነታ

“ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ” የሚለው የጵጵስናቸው ተቀዳሚ አደራ ተዘንግቷቸው፥ ነውር ነቀፋ፣ ኑፋቄና ክሕደት አለበት፤ እያሉ ምእመናን እየጮኹ፣ ለጩኸቱ ተገቢውን ምላሽ እንደ መስጠት በምን ታመጣላችኹ ዓይነት አካሔድ፥ ዲቁና፣ ቅስናና ኤጲስ ቆጶስነት እስከ መሾም ደርሰው ኀዘናችንን አብሰውታል። ጎጠኝነቱ፣ ከፖለቲካው አልፎ በቤተ ክርስቲያናችን ጭምር ዙፋኑን ዘርግቶ፣ የቤተ ክርስቲያኒቷ አስተምህሮ ምን ይላል፤ ሳይኾን “የእኛ ወገንና ዘር” የምንላቸው ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ ጳጳሳት ምንም ይናገሩ፤ ምንም ያጥፉ፤ በጎጠኝነቱ አተላ ሰክረን በጭፍን እንድንደግፋቸው እያደረገን ነው። ጎበዝ፥ ወዴት እየሔድን ይኾን? በምድረ አሜሪካ “ስደተኛ ሲኖዶስ” ተብለው የሚጠሩት፣ ነገ ከነገ ወዲያ አንድነቱን ሊያመጣ የሚችል ኹኔታ ቢከሠትስ፤ በዚኽ ምርትና ግርዱ በተቀላቀለበት ሒደታቸው እንዴት ነው ተፈላጊው አንድነት ሊመጣ የሚችለው? የሰሞኑ አሠራራቸው ልዩነቱን አጥብቆ ለማስፋት የተደረገ ሤራስ አይኾንም? በያለንበት ኾነን አደብ ግዙ እንበላቸው። *                *               * ቀሲስ ስንታየሁ አባተ /ደቡብ አውስትራልያ/ እግዚአብሔር እንደ ሰው አይቸኩልም። ዝምታውም ነገሮችን ፈቅዶና ወድዶ የመቀበሉ ምልክት አይደለም። ወደ አሜሪካ ያሉት “አባቶች”፣ በቤተ ክርስቲያናችንና በሕዝባችን ላይ እየፈጸሙት ያሉትን ግፍ የቤተ ክርስቲያን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርኩ: የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና፣ ማንነት፣ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ የሚቀርቡትን የሰንበት ት/ቤቶች ጥያቄዎች መመለስ ግዴታ ነው፤ አሉ

ሀገር አቀፉ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ባለ15 ነጥቦች መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ ሀገር አቀፍ የፀረ ተሐድሶ ቋሚ ጉባኤ፣ በአህጉረ ስብከት ቋሚ ጉባኤያት ተወካዮች ይቋቋማል የተሐድሶ መናፍቃን የጥፋት ማስረጃዎች፣ ለቅዱስነታቸው እና ለቅዱስ ሲኖዶሱ ይቀርባሉ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስና የካናዳ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ ከ፭ኛው ሀገር አቀፍ ዓመታዊ ስብሰባ ተሳታፊዎች ጋር በየዓመቱ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሳምንት የሚካሔደው፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ፣ ከሰኔ 10 እስከ 12 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ አዳራሽ ሲያካሒድ የቆየውን ፭ኛውን ዓመታዊ ስብሰባውን፣ ባለ15 ነጥቦች የጋራ አቋም መግለጫ በማውጣት ዛሬ ማምሻውን አጠናቀቀ፡፡ ከ25 አህጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤያትና የሰንበት ት/ቤቶች ዋና ክፍሎች የተውጣጡ ልኡካን የተሳተፉበት ጉባኤው፣ በጋራ መግለጫው፡- የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትን፣ ፀረ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ ለማስቆም፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ አካላት አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስዱ፤ መጠነ ሰፊ ጥፋታቸውን የሚያሳዩና በሀገር አቀፉ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መረጃ ክፍል የተሰበሰቡ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሀገር አቀፉ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፥ የፀረ ተሐድሶ ኑፋቄ ቋሚ ጉባኤ ያቋቁማል፤ በዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት ጥቆማው በንቃት ይሳተፋል

በ፭ኛው ሀገር አቀፍ ዓመታዊ ስብሰባ፣ የዛሬ፣ እሑድ በዓለ ጰራቅሊጦስ ረፋድ ውሎ ካለፈው ዓርብ፣ ሰኔ 10 ቀን ጀምሮ በመካሔድ ላይ የሚገኘው፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፭ኛው ዓመታዊ ስብሰባ፣ ሀገር አቀፍ የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ቋሚ ጉባኤ እንደሚያቋቁም ተጠቆመ፡፡ ከየአህጉረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ የክንውን ሪፖርቶች የቀረቡለት ዓመታዊ ስብሰባው፤ ከፀረ ሙስናና ሥነ ምግባር ኮሚሽን በመጡ ባለሞያ እንዲኹም፤ በሉላዊነትና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አደጋዎች ዙሪያ በተሰጡ ገለጻዎች ላይ በስፋት ሲወያይ የቆየ ሲኾን፤ በአኹኑ ሰዓትም በመምሪያው መሪ ዕቅድና በቀጣዩ በጀት ዓመት ቁልፍ የትግበራ ጉዳዮች በመወያየት ላይ እንዳለ ተጠቅሷል፡፡ የጉባኤውን የትላንት አብዛኛውን ውሎ የያዘውና ለዛሬም ያደረው አጀንዳ፤ ለቤተ ክርስቲያን የህልውና ስጋት የኾነውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ የማጋለጥና የመከላከል ጉዳይ ነው፡፡ በዚኽ ረገድ የማደራጃ መምሪያው እንቅስቃሴ፣ በግለሰቦች ጥረት የተወሰነና የሚጠበቅበትን ያኽል እንዳልሠራ የተቸው ጉባኤው፣ “መምሪያው ወቅቱ የሚጠይቀውን አገልግሎት መስጠት አልቻለም፤” ብሏል፡፡ በመርሕ ደረጃ ከተወሰኑ ገለጻዎችና “የመዝሙርና የሥርዐተ ትምህርት ወጥነት” እየተባለ በየዓመቱ፣ በተደጋጋሚ ከሚቀርቡ የወረቀት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

፭ኛው ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ተጀመረ፤ የመ/ር ዕንቊ ባሕርይ ተከሥተ የ፳ ዓመት “ለውጥ የለሽ” አመራር ገደብ እንዲበጅለት ተጠይቋል

፭ኛው ሀገር አቀፉ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ በጸሎት በተጀመረበት ወቅት(ፎቶ: የሰንበት ት/ቤቴ ማስታወሻዎችና ሰንበት ት/ቤቴ) በየዓመቱ፣ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሳምንት የሚካሔደው፣ ሀገር አቀፉ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ፣ አምስተኛውን ዓመታዊ መደበኛ ስብስባውን፣ ዛሬ፣ ዓርብ፣ ሰኔ 10 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የመምሪያ ሓላፊዎች በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ጀምሯል፡፡ ዓመታዊ ጉባኤው፤ ከስትራተጅያዊ ዕቅዱ አኳያ የበጀት ዘመኑን የቁልፍ ጉዳዮች ዕቅድ ክንውኖች፣ ከማደራጃ መምሪያውና ከየአህጉረ ስብከቱ በሚቀርቡ ሪፖርቶች ከማዳመጥና ከመገምገም ባሻገር፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዓበይት ወቅታዊ ጉዳዮች በኾኑት፡- የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ሤራ፤ የፀረ ሙስና እና የመልካም አስተዳደር አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይመክራል፤ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ የመዝሙርና የትምህርት አገልግሎት እንዲኹም የመረጃ ግንኙነት ወጥነት መሠረት የሚጣልበትም ነው፤ ተብሏል፡፡ የጠቅላይ ጽ/ቤቱን ሓላፊዎችና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጨምሮ ከ350 ያላነሱ የ45 አህጉረ ስብከት አቀፍ አንድነት ጉባኤያት ልኡካን የሚሳተፉበት ይኸው ዓመታዊ ስብሰባ፤ እስከ መጪው እሑድ፣ በዓለ ጰራቅሊጦስ ይቆያል፡፡ በመንበረ ፓትርያርክ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ስለድንግል ማርያም ፍቅር የተመተረውን የእናት ወሰን የለሽ ፈቃዱን እጅ ዐየኹት፤ የሰማዕትነት ቋጠሮ ነው፤ ንሥኡ ፍሬ ሃይማኖት!

እናታችን፣ በቀዶ ሕክምና የማይመለሰውን የግራ እጃቸውን ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው እና ስለ ድንግል ማርያም ስም ላይመለስላቸው ዐጡት፤ የድንግል ማርያምን ልዩ ፍቅር ከሚሰብከው ማንነት እንማር፡፡ ይህ አረንጓዴ ሰማዕትነት አይደለም፤ ነጭ ሰማዕትነትም አይደለም፤ ይህ ቀይ የደም ሰማዕትነት ነው፤ ለምን ኾነ ሳይኾን፣ በኾነው ነገር ኹሉ ስለሚሰጠን ትምህርት፣ ጽናት እና ዋጋ ልንጨነቅ ይገባል፡፡ (ዶ/ር አክሊሉ ደበላ) ዶ/ር አክሊሉ ደበላ ዛሬ፣ ሰኔ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ጠዋት፣ በጅማ ዞን የም ወረዳ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ገደማ በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመው አሠቃቂ መጨፍጨፍ አሳዛኝ ነው፡፡ ተራኪዋ በደራረቁ የእንባ ዘለላዎች ውስጥ ፍጹም ሰላምተኛነትን ታሳያለች፡፡ አደጋው የደረሰባቸው እናት በሚሰማቸው ከፍተኛ የሕመም ስሜት ውስጥም ኾነው ጉዳታቸውን አቅልለው ለማየት የሚያደርጉት ጥረት ያስታውቃል፡፡ የግራ እጃቸው፣ ከትልቁ የእጅ ጣት በስተቀር፣ አራቱ ጣቶች ከመነሻ መገጣጠሚያቸው አንሥቶ ተቆርጠዋል፡፡ ተቆርጦ የተነሣው የግራ እጅ ክፍል ለብቻው በሌላ መያዣ ተቀምጧል፡፡ ይህን የተቆረጠ እጅ ስመለከት፣ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ትዝ አለኝ፡፡ የተነጨው ጽሕሙና የተነቀለው ጥርሱ!! “ንሥኡ፤ ይህ የክርስትና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት: የጅማ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል የአክራሪዎች ተጠቂዋንና ቤተ ሰዎቻቸውን አጽናኑ

ሦስት ጉዳተኞች በወሊሶ ሆስፒታል በሕክምና ላይ ናቸው ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ዛሬ ማለዳ በአክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸውአንዷ የኾኑትንና በጥቁር አንበሳ ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙትን ምእመንት ጎበኙ፤ ቤተ ሰዎቻቸውንም አጽናኑ፡፡ ቅዱስነታቸው፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ከምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ከስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ጋር በመኾን ነው፣ ዛሬ ማምሻውን በሆስፒታሉ የተገኙት፡፡ ለጉዳተኞች ጸሎተ ማርያም ከደረሰ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትያርኩ ባሰሙት ቃል፤ “ለሃይማኖታችኹ የከፈላችኹት ዋጋ ነው፤ ይህ መከራ አባቶቻችን የተቀበሉት ነው፤ አዲስ አይደለም፤ አባቶች ብለን የምንጠራቸው እንዲኽ ባለው ግፍ በእምነታቸው ጸንተው ስላለፉ ነው፤” በማለት ቤተ ሰዎቻቸውንም አጽናንተዋል፡፡ ጥቃቱ ዛሬ ማለዳ ከተፈጸመ በኋላ፣ ረፋድ 4፡30 ገደማ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሆስፒታሉ የደረሱት ምእመኗ፣ በ40ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገመቱ ሲኾን፤ ከአንድ እጃቸው አውራ ጣታቸው ሲቀር የተቀሩት አራት ጣቶች ከመዳፋቸው በጥቃቱ መቆረጡን፤ ከከንፈሮቻቸው መገጣጠሚያና ከአፍንጫቸውም
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – በጅማ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል አክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት አደረሱ

2 ኦርቶዶክሳውያን እና 5 ሙስሊሞች መጎዳታቸው እየተገለጸ ነው ከ4ቱ የጥቃቱ አድራሾች አንዱ ተይዟል፤ 3ቱ አምልጠዋል፤ ተብሏል ሀ/ስብከቱ ከወረዳው የአስተዳደርና የጸጥታ አካላት ጋር እየሠራ ነው (UPDATES) በጅማ ሀገረ ስብከት የም ልዩ ወረዳ ቁንቢ ቀበሌ፣ በቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች፣ ዛሬ፣ ሰኔ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ማለዳ በአክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተሰማ፤ በነዋሪ ሙስሊሞችም ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ምእመናኑ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው፣ በቤተ ክርስቲያኑ የኪዳን ጸሎት አድርሰው በሚመለሱበት ወቅት ነው፤ ተብሏል፡፡ በጥቁር አልባሳት ፊታቸውን የሸፈኑ አራት የጥቃቱ አድራሽ አክራሪዎች፣ ወደ አካባቢው በመኪና እንደ ደረሱ ጥቃታቸውን የጀመሩት፣ በቀጥታ በአካባቢው ወደሚገኝ አንድ መስጊድ በመግባት እንደኾነ ተገልጧል፡፡ “ግንባር፣ አንገት፣ እጅ እየመቱ ያገኙትን በስለት ጨፈጨፉ፤” ያለው የስፍራው ምንጭ፣ በጭፍጨፋው አምስት ሙስሊሞች(አክራሪዎቹ እንደ ከሐዲ/ካፊር የሚቆጥሯቸው ነዋሪዎች) ክፉኛ መቁሰላቸውን ተናግሯል፡፡ ከመስጊዱ እንደወጡ ወደ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አቅጣጫ በማምራት፣ የኪዳን ጸሎት አድርሰው በመመለስ ላይ በነበሩ ምእመናን ላይም በቀጠሉት ጥቃት፤ ኹለት ምእመናንን ክፉኛ አቁስለዋል፤ ከቆሰሉት የአንዷ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ: “በጐች በበጐች ላይ እንዳይሰማሩ”:-ካህናቱንና ምእመናኑን ማሳተፍ፤ ከኹሉም በላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲመርጥ መጸለይ ይገባል/ዜና ቤተ ክርስቲያን/

በአባቶች እግር አባቶችን የመተካት አስፈላጊነት፡- ብዙ ጠንካሮች አባቶቻችን በተከታታይ አንቀላፍተዋል፤ በሕመምና በዕርግና ከቤት የዋሉም አሉ እግዚአብሔር አልባነት፣ አምልኮ ባዕድ፣ የመንጋ ቅሠጣና የአህጉረ ስብከት ብዛት ጉዳዮች ናቸው ለቤተ ክርስቲያን ያሰቡ መስለው ጥቅሟን ለመቦጥቦጥ የተነሡ ውስጠ ተኩላዎች ተበራክተዋል ቤተ ክርስቲያን፥ “ከወዳጅ ጠላቴ ጠብቀኝ” ብላ ጸሎት የምታቀርብበት ጊዜ ላይ ደርሳለች፤ በአባቶች እግር አባቶችን መተካት ግዴታ ቢኾንም፡- ከነጣቂ ተኩላዎች የሚያድኑ፣ የሕዝብ መብራትና ቸር እረኛ የኾኑት ሊለዩና ሊመረጡ ይገባል በጐች በበጐች ላይ የሚሰማሩበትና ጠባቂዎች ተጠባቂዎች እንዳይኾኑ ካለፈው ተሞክሮ ይወሰድ ለቤተሰብ የማያዳሉ፣ ለዓለም የማይገዙና ቅድስናቸውን ያረጋገጡ በውስጥም በውጭም ይታሠሡ ትክክለኛ የኤጲስቆጶሳት ምርጫና ሹመት ቤተ ክርስቲያንን ከወቅቱ አደጋ የመታደግ ጥያቄ ነው ካህናቱንና ሕዝበ ክርስቲያኑን የምርጫው ተሳታፊ ማድረግ፡- በሰውና በእግዚአብሔር ፊት አቅርቦ መምረጥ የቅዱስ ሲኖዶስ ሓላፊነትና ተጠያቂነት ነው የዕጩዎች ዕውቀት፣ አገልግሎትና ቅድስና ሳይጋነንና ሳይንኳሰስ ያለአድልዎ ለመመርመር፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ የሚወረወረውን ትችት ካህናቱም፣ ምእመናኑም እንዲጋሩት ያስችላል ከካህናቱ እና ከሕዝቡ ምስክርነት ጋር መንፈስ ቅዱስ እንዲመርጥ ኹሉም ሊጸልይ ይገባል፡፡ *           *         
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቅ/ላሊበላ ቤተ ሩፋኤል እና ቤተ ገብርኤል አብያተ መቃድስ: በ15 ሚ. ብር ወጪ ተጠገኑ

በከፍተኛ ባለሞያዎችና በላቀ ቴክኖሎጂ ጥገና የተደረገላቸው ቤተ ሩፋኤልና ቤተ ገብርኤል ዩኔስኮ፣ የዓለም ቅርስ ፈንድና የአሜሪካ መንግሥት በገንዘብና በሞያ ደግፈዋል ቤተ ክርስቲያን፥ ከጸሎት እና ጥብቅ ክትትል ጋር በባለቤትነት ተሳትፋለች ለይምርሐነ ክርስቶስ ጥገና የ150 ሺሕ ዶላር የጥናት ስምምነት ተፈርሟል ደብሩ በአ/አበባ ሕንፃ ለማስገንባትና አስጎብኚ ቢሮ ለመክፈት ዐቅዷል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፶፮፤ ቅዳሜ ሰኔ ፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) በዩኔስኮ የዓለም አስደናቂ ቅርሶች የተመዘገቡትና የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አካል የኾኑት የቤተ ሩፋኤል እና ቤተ ገብርኤል አብያተ መቃድስ፤ በረጅም ጊዜ አገልግሎት እና በተፈጥሮ በደረሰባቸው የመሠንጠቅና የማፍሰስ ጉዳት የተነሣ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ የነበሩ ሲኾን፤ በ15 ሚሊዮን ብር ወጪ በከፍተኛ ቴክኖሎጂ የታገዘ ውጤታማ ጥገና እንደተደረገላቸው ተገለጸ፡፡ ከዩኔስኮ፣ ከዓለም ቅርስ ፈንድ(World Monument Fund) እና ከአሜሪካ መንግሥት(American Ambassador’s Fund) በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ የተካሔደውን የጥገና ፕሮጀክት በሓላፊነት ያሠራው በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የቅርስ ጥበቃ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ እስከ ሰኔ 30 የዕጩዎችን ዝርዝር ያቀርባል፤ የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት፣ ላለፉት 16 ቀናት ሲያካሒደው የቆየውን የ2008 ዓ.ም. የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ ስብሰባውን ዛሬ አጠናቋል፡፡ ግንቦት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. የተጀመረው ጉባኤው፣ ዛሬ፣ ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ረፋድ ላይ የተጠናቀቀው፣ ባለ17 ነጥቦች መግለጫ በማውጣት ነው፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ መግለጫውን በንባብ ያሰሙት ርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ምልአተ ጉባኤው ጠቀሜታ ባላቸው አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታውቀዋል፡፡ ከውሳኔዎቹ ዓበይት ነጥቦች መካከል፣ የአዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በምልአተ ጉባኤው የታመነበት ሲኾን፤ በዕቅዱ መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በአስረጅነት የሚገኙበትና ሰባት አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ እንዲቋቋም መደረጉ ተገልጧል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው፣ ዕጩ መነኰሳቱን፥ መርምሮ፣ አጥንቶና አጣርቶ ውጤቱን እስከ ሰኔ 30 ቀን እንዲያቀርብ ተወስኗል፡፡ በዕጩነት የሚቀርቡት ቆሞሳትና መነኰሳትም፡- ፈተናውንና መሰናክሉን ኹሉ አልፈው ዕውቅና ያገኙትን፤ በብሔር አቀፍና በዓለም አቀፍ ትምህርት የበሰሉትን፤ የወቅቱንም ችግር ይፈታሉ ተብለው እምነት የተጣለባቸውንና የሚጣልባቸው መኾን እንደሚገባቸውም በመግለጫው ተዘርዝሯል፡፡ በየሦስት ዓመቱ በሚደረገው
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ: የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ሠየመ፤ ዕጩዎች በሠሩባቸው ቦታዎች ካህናትንና የሰንበት ት/ቤቶችን ያነጋግራል

በሃይማኖት አቋም፣ በሥነ ምግባር፣ በሥራ አመራር እና አፈጻጸም ይገመገማሉ ካህናትና ምእመናን ከሢመቱ በፊት “ይገባዋል” ሲሉ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል በተሐድሶ ኑፋቄ ቅጥረኝነትና በሲሞናዊነት ለመሸመት ካሰፈሰፉት እንጠብቀው *               *               *    የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤውን እያጠናቀቀ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በዛሬው፣ ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የቀትር በፊት ውሎው፣ ተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት አስፈላጊ መኾናቸውን በማመን አስመራጭ ኮሚቴ ሠየመ፤ ለሹመቱ በሚጠቆሙና በሚመረጡ መነኰሳትና ቆሞሳት ጉዳይም መመሪያ ሰጠ፡፡ በመመሪያው መሠረት ጥቆማው፥ የማኅበረ ካህናትን፣ የሰንበት ት/ቤቶችንና የማኅበረ ምእመናንን ተሳትፎ ባረጋገጠ ግልጽነት እንዲፈጸም ያሳሰበው ምልዓተ ጉባኤው፤ ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ሳዊሮስ በአስረጅነት የሚገኙበት፣ ሰባት አባላት ያሉበት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙ ታውቋል፡፡ በዚኽም መሠረት በአስመራጭነት የተሠየሙት ብፁዓን አባቶች፡- ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በአስረጅነት ናቸው፡፡ የኮሚቴው አባላት፣ ተጠቋሚ ዕጩዎች
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅ/ሲኖዶስ: ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፥አቡነ ሉቃስ፣ አቡነ እስጢፋኖስ፣ አቡነ ሙሴ፣ አቡነ ዳንኤልና አቡነ ኄኖክ ተጨማሪ ምደባዎች ሰጠ

ጁባ፣ ካርቱም፣ ግብጽ፣ እንግሊዝና አውስትራልያ ይገኙበታል በእጥረቱ መነሻነት በጊዜያዊነት የተደረጉ ምደባዎች ናቸው በምልዓተ ጉባኤው ተጨማሪ ምደባዎች የተሰጧቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት(ከግራ ወደ ቀኝ)፡- ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ አቡነ ሙሴ፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤልና ብፁዕ አቡነ ኄኖክ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ በዛሬው፣ ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የቀትር በፊት ውሎው፣ ለአምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የተጨማሪ አህጉረ ስብከት ምደባዎችን ሰጥቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው፣ “በውጭ ያሉ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት በሌሉባቸው ተደርበው እንዲሠሩ” በሚል በተ.ቁ(18) በያዘው አጀንዳ መሠረት፣ የሰጣቸው ተጨማሪ ምደባዎች፣ ባለው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እጥረት ሳቢያ በጊዜአዊነትና በፈቃደኛነት ላይ ተመሥርቶ የተደረገ መኾኑ ተገልጧል፡፡ በዚኽም መሠረት፡- በክልል ትግራይ የምዕራብ ሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፡- የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት የበላይ ሓላፊ፤ የሰሜን ሱዳን(ካርቱም) እና ግብጽ አህጉረ ስብከትን ደርበው ይመራሉ፤ የጅማ፣ ኢሉ አባ ቦራ እና ጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፡- የደቡብ ሱዳን(ጁባ) ሀገረ ስብከት ደርበው ይመራሉ፤
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የባንኮ ዲሮማው ባለ9 ፎቅ የገበያ ማዕከል: በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተመረቀ፤ “ትንሣኤ ሕንፃ” ተብሏል፤ ብር 17 ሚልዮን ዓመታዊ ገቢ ያስገኛል

  የመንበረ ፓትርያርኩ የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ከ122 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያሠራውና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ “ትንሣኤ ሕንፃ” ተብሎ የተሠየመው የባንኮ ዲሮማ ግቢው ሕንፃ(ፎቶ: አ/አ ሀ/ስብከት) ከ42 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅ/ጽ/ቤቱ ያስገነባው ሕንፃ፣ ዐዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነው ባሉን ክፍትና በመልሶ ማልማት በሚሰጡን ትክ ቦታዎች ለመገንባት አጋዥ ተሞክሮ ተገኝቷል የገቢው 70 በመቶ ለአገልግሎት ሲውል፣ 30 በመቶ ለቀጣይ ልማት በዝግ ሒሳብ ይቀመጣል ባቢሎናዊ መንፈስ፣ ወኔ ገዳይ አሉባልታ፣ የወንዝ ቆጠራና የጥሎ ማለፍ አባዜ መሰናክል ነበሩ በየ3 ዓመቱ የሚሾሙ ብፁዓን አባቶች፣ ቢያንስ አንድ ሕንፃ ቢሠሩ የሚል ሐሳብ ተጠቁሟል፡፡ *          *          * የሕንፃው ገቢ ሌሎች ሕንፃዎችን እንደሚወልድና ቀጣይ ልማት እንደምናካሒድ ተስፋ አለኝ፡፡ /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/ ሞራላዊ ጥንካሬ ባይኖር፣ ሕንፃው ቆሞ መተረቻ በኾን ነበር፤ በብዙ ወጀብ ውስጥ ተጠናቋል፡፡ /ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ / አባቶች ያወረሱንን ቤቶች እያስተዳደርን ነው፤ አኹን በራሳችን በጀት ገንብተናል፤ እንቀጥላለን!! /ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፤ የልማትና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅ/ሲኖዶስ: በፀረ ተሐድሶ ኑፋቄ አጀንዳ መወያየት ጀመረ፤ ሕዋሱ ምልምሎቹን በኤጲስ ቆጶስነት ለማሾም እየሠራ እንዳለ ተጠቁሟል

የተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ጥቆማና ምርጫ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግበት ተጠይቋል ብፁዓን አባቶች፣ በአደረጃጀትና በእንቅስቃሴ የአህጉረ ስብከታቸውን ተሞክሮ አቀረቡ የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቋሚ ጉባኤ የወራት አፈጻጸም በጥቅሉ ተገምግሟል በልዩ ጽ/ቤቱና በአባ ቃለ ጽድቅ ያለው የኑፋቄው ስጋት ዛሬም ትኩረት ተሰጥቶታል የፀረ ተሐድሶ ጉባኤውን ከአጥቢያ እስከ አህጉረ ስብከት ማዋቀሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ኑፋቄውን በሚያጋልጡና በሚያመክኑ ተጨማሪ ስልቶች ላይ ምክክሩ ነገም ይቀጥላል *                     *                     * የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ(ፎቶ: አ/አ ሀ/ስብከት) የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ የመጠበቅና የማስጠበቅ፤ አገልግሎቷም የተሟላ እንዲኾን የማድረግ ዓላማዎች ያሉት ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለትምህርተ ሃይማኖታችንና ለመዋቅራዊ አንድነታችን የህልውና ስጋት የኾነውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ለማጋለጥና ለማምከን ስለሚደረገው የመከላከል እንቅስቃሴ መወያየት ጀመረ፡፡ ምልዓተ ጉባኤው፣ በዛሬ፣ ግንቦት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. የቀትር በኋላ ውሎው፣ “ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አንፃር የመናፍቃን እንቅስቃሴ ጉዳይ” በሚል በተ.ቁ(15) በያዘው አጀንዳ መነጋገር እንደጀመረ ተገልጿል፡፡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ከኑፋቄው ተጽዕኖና ተጨባጭ አደጋዎቹ በትይዩ፣ በማስረጃ ለማጋለጥ እና በትምህርት ለመከላከል ያደረጓቸውን እንቅስቃሴዎችና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የጠቅ/ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተመረጡ፤ ፓትርያርኩ በከባዱ ተገሥጸዋል

ለዋና ጸሐፊነት የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የደቡብ ምዕ. ሸዋ ወሊሶ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ(በግራ)፤ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የደቡብ እና ምሥራቃዊ ትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ(በቀኝ) ፓትርያርኩ፣ የአስመራጭ ኮሚቴውን ዕጩዎች ካልተቀበሉ ነባሮቹን ብፁዕ ዋና ጸሐፊ እና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ለድጋሚ የሦስት ዓመታት የሥራ ዘመን እንደሚያስቀጥላቸው አሳስቧቸው ነበር፤ “እነርሱንስ ከምታስቀጥሉ እኔን አንሡኝ፤” ያሉት ፓትርያርኩ፣ ማሳሰቢያውን ተከትሎ በምልዓተ ጉባኤው በተሠየመው አስመራጭ ኮሚቴ የቀረቡትን ዕጩዎች በመቀበላቸው፣ በምስጢራዊ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓቱ መሠረት፣ የብፁዕ ዋና ጸሐፊው እና የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ምርጫ ተከናውኗል፤ ለቀጣይ ሦስት የአገልግሎት ዓመታት፣ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ድምፅ ከሰጡት 38 የምልዓተ ጉባኤው አባላት የ22ቱን በማግኘት፤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ድምፅ ከሰጡት 38 የምልዓተ ጉባኤው አባላት የ26ቱን በማግኘት በቅዱስ ሲኖዶሱ ተመርጠዋል፤ በምልዓተ ጉባኤው በአብላጫ ድምፅ የተመረጡት፣ አዲሱ ብፁዕ ዋና ጸሐፊ እና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ በብፁዕ ወቅዱስ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርኩ: የምልዓተ ጉባኤው አስመራጭ ኮሚቴ ለዋና ሥራ አስኪያጅነትና ለዋና ጸሐፊነት ያቀረባቸውን ዕጩዎች አልቀበልም በማለታቸው ሒደቱ ተስተጓጎለ

ሕግ አፍራሽነት፣ የአማሳኞችና የጨለማ ቡድን አስፈጻሚነትና ቂመኝነት መርሓቸው ኾኗል ከአመራራቸው ጋር በተያያዙ ወሳኝ አጀንዳዎች በተቿቸው አባቶች ላይ ቂማቸውን አሳይተዋል ከቀረቡት ዕጩዎች፣ አቡነ ዲዮስቆሮስንና አቡነ ሳዊሮስን “ይውጡልኝ” ሲሉ ሒደቱን አውከዋል ምልዓተ ጉባኤው መርጦ ለሚሠይማቸው የሹመት ደብዳቤ መስጠት እንጂ መቃወም አይችሉም ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፣ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴን የበላይ ጠባቂነት ተመድበዋል *                *                * በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን እንደተደነገገው፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው የሚመረጡት ብፁዓን አባቶች የአገልግሎት ዘመን ለሦስት ዓመታት ነው – በአንቀጽ 24/4 እና አንቀጽ 43/3 እንደተደነገገው፡፡ በየሦስት ዓመቱ ለሚካሔደው ምርጫ፣ በምልዓተ ጉባኤው የሚሠየም አስመራጭ ኮሚቴ፣ የሥራ አመራር ልምድንና ችሎታን መሠረት አድርጎ ሦስት ተወዳዳሪዎች በጉባኤው እንዲጠቆሙ ካደረገ በኋላ፣ ምርጫው በምስጢር ድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት ተከናውኖ ከፍተኛ ድምፅ ያገኘው ብፁዕ አባት በዋና ጸሐፊነት እና በዋና ሥራ አስኪያጅነት ይሠየማል፡፡ ይህም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፈርመው በሚሰጧቸው የሹመት ደብዳቤ ይገለጻል፡፡ በዋና ጸሐፊነት እና በዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመረጡት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ለቤተ ክርስቲያናችን የ24 ሰዓት ቴሌቭዥን አገልግሎት የቅጥር ማስታወቂያ ወጣ፤ የቤተ ክርስቲያን አባልነት አንዱ መስፈርት ነው

በተለያዩ የሥራ መደቦች 15 ባለሞያዎች እና 6 ድጋፍ ሰጪዎች ይፈለጋሉ ከአብነት ጉባኤ ቤትና የማስተርስ ዲግሪ እስከ 2ኛ ደረጃ ዝግጅት ይጠይቃል ለአዘጋጆችና ዘጋቢዎች የግእዝና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በቂ ዕውቀት ያሻል ማመልከቻውን የማቅረቢያ ጊዜ እስከ ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ነው ኦርቶዶክሳውያን ጋዜጠኞች፣ ጸሐፊዎችና የቴክኖሎጂ ሞያተኞች አመልክቱ! *                *                * በቀናት ጊዜ ውስጥ የሙከራ ስርጭት የሚጀምረውን፣ የቤተ ክርስቲያናችንን የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት የሚመራው፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የብዙኃን መገናኛ አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ቢሮ የክፍት ሥራ ቦታ ማስታወቂያ አወጣ፡፡ የሥራ ቦታውን፣ በአዲስ አበባ የመንበረ ፓትርያርኩ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ያደረገው ቢሮው ባወጣው ማስታወቂያ፤ በተለያዩ ሞያዎችና የሥራ ዘርፎች 21 ሠራተኞችን እንደሚቀጥር ተጠቅሷል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባልነት ማስረጃን ጨምሮ መሥፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች፣ እስከ ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ለቢሮው ማመልከት የሚጠበቅባቸው ሲኾን፤ የቅጥሩ ኹኔታ፣ ለውጭ ተወዳዳሪዎች በኮንትራት፣ ለውስጥ ተወዳዳሪዎች ደግሞ በዝውውር መኾኑ ተገልጧል፡፡ በተጠቀሱት የሞያ እና የሥራ ዘርፎች የሚካሔደው ቅጥር÷ ለቦታው የሚመጥኑ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጰስ ኾነው ተመደቡ

እስከ መጪው ዓመት ጥቅምት በዚኹ ሓላፊነታቸው ይቆያሉ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፤በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳትና የካፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ የካፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተመደቡ፡፡ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ዛሬ፣ ግንቦት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ብፁዕነታቸውን የመደበው፣ በሥራ ላይ በሚገኘው ሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት፣ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጥቆማ በመቀበል ነው፡፡ አዲስ አበባ በ2005 ዓ.ም. ለአራት አህጉረ ስብከት ተከፍሎ በነበረበት ወቅት፣ ብፁዕነታቸው የደቡብ እና ምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው የሠሩ ሲኾን፤ አኹን በያዙት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስነት ምደባ፣ እስከ መጪው ጥቅምት፣ 2009 ዓ.ም. ድረስ እንደሚቆዩ ተገልጧል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው፣ አዲስ አበባን የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የሚያደርገው የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ድንጋጌ ተጠንቶ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅ/ሲኖዶስ የእንደራሴ ምደባ ደንብ አርቃቂ ኮሚቴ ሠየመ፤ ልዩ ጸሐፊው እና የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሓላፊው በአጭር ጊዜ እንዲነሡ አሳሰበ

ኮሚቴው፣ የሕገ ቤተ ክርስቲያኑን የአ/አበባ ሀ/ስብከት ድንጋጌዎችንም ያጠናል ከቀትር በኋላ ለአ/አበባ ሀ/ስብከት፣ የረዳት ሊቀ ጳጳስ ምርጫና ምደባ ያካሒዳል “[ልዩ ጸሐፊውን ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃን] በቅርብ ቀን አነሣዋለኹ፤” “በውጭ ጉዳይ መምሪያ ዋና ሓላፊው አባ ቃለ ጽድቅ ማስረጃ እፈልጋለኹ፡፡” /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ/ *               *                * የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፥ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ሓላፊነትና መንፈሳዊ አመራር በሚጠበቀው ብቃትና ደረጃ እንዲያከናውኑ የሚያግዛቸውን እንደራሴ ለመመደብ የሚያሰችለውን ደንብ የሚያረቅ ኮሚቴ ሠየመ፡፡ የምደባ ደንቡ፥ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን መሠረት በማድረግ፣ የእንደራሴውን አመራረጥና ማሟላት የሚጠበቅበትን መመዘኛ፤ ተግባርና ሓላፊነቱን፤ እንዲኹም ተጠሪነቱንና የአገልግሎት ዘመኑን ያካተተ እንደሚኾን ተጠቁሟል፡፡ ሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ሰባት አባላት ያሉት ይኸው ኮሚቴ፣ የምደባ ደንብ ረቂቁን ለመጪው ጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ እንዲያቀርብም የተወሰነ ሲኾን፤ የምልዓተ ጉባኤው አባላትም፡- ብፁዕ አቡነ ገብርኤል(የሐዋሳ እና ነገሌ ቦረና አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) ብፁዕ አቡነ አብርሃም(የባሕር ዳር፣ ምዕ.ጎጃም፣ መተከልና አዊ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ) ብፁዕ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በፓትርያርኩ እንደራሴ አስፈላጊነት ከስምምነት ተደረሰ፤ “ወቅቱን የጠበቀ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፣ “ቅ/ሲኖዶሱ ተስማምቶ ካልወጣ ለሕዝብም ለሀገርም ጥሩ አይኾንም” ብለዋል

በምልዓተ ጉባኤው ውሎ በተደረሰው መግባባት፤ የእንደራሴው መመዘኛ፣ ፓትርያርኩን የማገዝ ተግባሩና ሓላፊነት ደንቡ በቀጣዩ ጉባኤ ይታያል፤ በልዩ ጽ/ቤቱ፣ ለሥራ ዕንቅፋት የኾኑ ሰዎች ተነሥተው፣ እንዲስተካከልና እንዲረጋጋ ይደረጋል፤ የገዘፈ ችግር ያለበት የአ/አበባ ሀ/ስብከት፣ በረዳት ሊቀ ጳጳስ እየተመራ ሕጉ የሚሻሻል ይኾናል፤ ፓትርያርኩ፣ ስለወቅታዊ ኹኔታዎች ያላቸው አረዳድ ውስንነት ምደባውን አስፈላጊ አድርጎታል፤ ተግባር የሚሻው የልዩ ጸሐፊውና የጨለማ አማካሪዎች ግፍና አውዳሚነት አጽንዖት አግኝቷል፡፡ ሚኒስትሩ ስለአጀንዳዎቹና በውሏቸው እንደታዘቡት፡- ከጥቅማጥቅም ጋር ሳይገናኙና ራስን ማዕከል ሳያደርጉ ጤናማ ውይይት ሊካሔድባቸው ይገባል፤ ጠንካራ ቅ/ሲኖዶስ፤ ጠንካራ አደረጃጀትና ፖሊሲ፤ አስፈጻሚና ፈጻሚ የሰው ኃይል ያስፈልጋል፤ እናንተ ናችሁ እኛን መደገፍ ያለባችሁ፤ ቤቱ ተኣማኒነቱና ተጽዕኖ ፈጣሪነቱን ማጣት የለበትም፤ በጨለማ የሚያማክሩት እነማን ናቸው? በእምነት፣ በምግባርና በዕውቀትስ ለቤቱ ይመጥናሉ? አለመተማመን ይታያል፤ ይህ ፍጹም ክፍተት አምጥቷል፤ በጋራ መሥራት ይጠበቅባችኋል፡፡ የሚኒስትሩ እንደታዛቢ መጠራት፡- ከቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ከሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች አንፃር መነጋገርያ ኾኗል፤ የፓትርያርኩ ግትርነት ዋናው መንሥኤ ቢኾንም፣ ምልዓተ ጉባኤው በጥሪው መስማማቱ አስቆጥቷል፤ ጥሪው፥ “ኃይል አለኝ” ሲሉ የዛቱት ፓትርያርኩ፥
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – የእንደራሴ ምደባ አጀንዳ የመንግሥት ታዛቢ ባለበት እንዲታይ ተወሰነ፤ ፓትርያርኩ በተቃውሟቸው እንደቀጠሉ ናቸው

ዛሬ ከቀትር በኋላ አልያም ነገ ታዛቢ ባለበት ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ተደርሷል በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ ለተከታታይ ሦስተኛ ቀን ውይይቱን የቀጠለው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ በፓትርያርኩ ተቃውሞ ምክንያት ከስምምነት ለመድረስ ባለመቻሉ፣ የመንግሥት ታዛቢ ባለበት ለመነጋገር ወሰነ፡፡ ፓትርያርኩ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን የመጨረሻ አቋም እንዲያሳውቁ፣ ምልዓተ ጉባኤው በትላንቱ የቀትር በኋላ ውሎው፣ እስከ ዛሬ ጠዋት የማሰላሰያ ጊዜ ሰጥቷቸው የነበረ ቢኾንም፣ ምደባውን፥ ከቤተ ክርስቲያን ህልውና አንፃር ከማሰብ ይልቅ  ከሥልጣን ተጋሪነትና ከጥቅም ጋር ብቻ በማገናኘት በተቃውሟቸው መቀጠላቸው የታዛቢውን መገኘት አስፈላጊ አድርጎታል፤ ተብሏል፡፡ ስብሰባውን በጸሎት ዘግቶ ምልዓተ ጉባኤውን ማሰናበት አልያም፣ ሌላ ሰብሳቢ ሠይሞ በእንደራሴ ምደባው ላይ በአብላጫ ድምፅ በመወሰን ወደ ሌሎች አጀንዳዎች መቀጠል፣ ጉባኤው ለተከታታይ ሦስተኛ ቀን በአንድ አጀንዳ ተወስኖ ለገባበት እግዳት በአማራጭነት የተያዙ እንደነበሩ ተጠቅሷል፡፡ በስብሰባው ላይ ይገኛሉ የተባሉት የመንግሥት ታዛቢ፣ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ሲኾኑ፣ በፓትርያርኩ በኩል ጥሪው እንዲደርሳቸው መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው፣ ታዛቢው እንደተገኙ፣ ዛሬውኑ ከቀትር
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ: ፓትርያርኩ እስከ ነገ አቋማቸውን የሚያሳውቁበት የማሰላሰያ ጊዜ ተሰጣቸው

ከንግግራቸው በተፃራሪ በአማሳኞችና በተሐድሶ መናፍቃን ተጽዕኖ ውስጥ ወድቀዋል የተጽዕኖው አስጊነት ምደባውን አስፈላጊ እንዳደረገው በምልዓተ ጉባኤው ታምኖበታል ፓትርያርኩ፣ “ሌላ አለቃ ልታስቀምጡብኝ ነው ወይ?” በሚለው ተቃውሟቸው ውለዋል በተቃውሞ ከጸኑ፣ ጉባኤው በአብላጫ ድምፅ ወስኖበት ሌላ ሰብሳቢ በመምረጥ ይቀጥላል *           *           * ቅ/ሲኖዶስ፣ የመጨረሻው መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ ሕግ አውጭ እና ወሳኝ አካል ነው ሕጎችን ያወጣል፤ ያሻሽላል፤ ይሽራል፤ የአስተዳደር መዋቅርን ደረጃና ተጠሪነት ይወስናል በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ የሚያሳልፈው ውሳኔም፣ የሕገ ቤተ ክርስቲያኒቱ አካል ይኾናል ፓትርያርኩን በአመራር ለማገዝ ለሚሾመው እንደራሴ ምደባ፣ ዝርዝር ደንብ ይወጣል *           *           * ፓትርያርክ የሚባሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ የቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን አባት ናቸው የፓትርያርክነት/ርእሰ ሊቃነ ጳጳስነት ሥልጣናቸው የአመራር እንጂ የክህነት ደረጃ አይደለም ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው ያለአድልዎ የማስተዳደር እና የመምራት ሓላፊነት አለባቸው ቤተ ክርስቲያንን ማስነቀፋቸውና ታማኝነት ማጣታቸው ከተረጋገጠ ከሥልጣናቸው ይወርዳሉ *           *           * በዛሬ፣ ግንቦት ፳፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከምደባው ጋር በተያያዘ ከምልዓተ ጉባኤው ውይይት የሚጠቀሱ፡- ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፡- “በሕጉ እንደራሴ ይመደብ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የደ/አፍሪቃ ፍ/ቤት: አባ ጥዑመ ልሳነ አዳነን ከካቴድራሉ አገደ፤ የልዩ ጽ/ቤቱ ትእዛዝ ለአደጋ አጋልጦታል፤ ምእመናኑ ቅ/ሲኖዶስን ተማፀኑ

በማናቸውም የካቴድራሉ አገልግሎት እና አስተዳደራዊ ተግባራት ሚና አይኖራቸውም የመጋቤ ብርሃናት አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ ምደባ፣ በእነንቡረ እድ ኤልያስ ተሰናክሏል ያለሕጉ በታገደው ሰበካ ጉባኤ ምትክ፣ ያለደንቡ ምርጫ እንዲካሔድ ልዩ ጽ/ቤቱ አዝዟል የፍ/ቤቱን ትእዛዝ የሚጥስና በሀገሪቱ ሕግ የካቴድራሉን ህልውና ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው ቅ/ሲኖዶስ፥ ለአንድነት የሚበጅና ሀ/ስብከቱን በሰላም የሚመራ ውሳኔ እንዲሰጥ ተጠይቋል *                *                * በደቡብ አፍሪቃ የጆሐንስበርግ ከፍተኛ ፍ/ቤት፣ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅና የጆሐንስበርግ ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ካቴድራል አስተዳዳሪን መጋቤ ሃይማኖት አባ ጥዑመ ልሳነ አዳነ ትኩንና ሰባት ግለሰቦችን፣ ከካቴድራሉ ጋር በተገናኙ ማናቸውም ጉዳዮች እንዲታገዱ ወሰነ፡፡ ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና ከደብሩ አስተዳዳሪ የሰነድ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ፣ በአንደኛ አመልካች የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ እና በኹለተኛ አመልካች በካቴድራሉ የሰንበት ት/ቤት እንዲኹም በመልስ ሰጪዎች በመጋቤ ሃይማኖት አባ ጥዑመ ልሳንና ሰባት ግለሰቦች መካከል የነበረውን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው ከፍተኛ ፍ/ቤቱ፣ ከትላንት በስቲያ፣ ግንቦት 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ባሳለፈው ውሳኔ፤ ተከሣሾችን በማገድ አራት ትእዛዞችን ሰጥቷል፡፡ በከፍተኛ ፍ/ቤቱ የመዝገብ ቁጥር 18204/16
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የፍጹም ተኃራሚው ሣልሳዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐውልት: በቅዱስ ፓትርያርኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ይመረቃል

“እጅግ ፈታኝ በኾነ ወቅት ቤተ ክርስቲያኗን በመምራት ሓላፊነታቸውን በአግባቡ የተወጡ የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ፓትርያርክ ናቸው::”/ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/ “ተወልጄ ያደግኹበት ቦታ ይህ ነው ብለው ከመናገር ይልቅ በፍጹም ኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ ያምኑ ነበር፡፡ አበ ብዙኃንነትን አጉልተው በማሳየት ኹሉን እኩል በመመልከት ብቃታቸው ብዙዎችን ሲያስገርሙ የኖሩ አባት ናቸው፡፡”/ዜና ሕይወታቸው/ “ሐውልቱን ለማስጠገን ስጀምር የቅዱስነታቸውን ታሪክና ሐዋርያዊ አገልግሎት አንብቤአለኹ፤ በእውነት ትልቅ አባት ነበሩ፤ ልቤ ተነክቷል፤ ይህን በመሥራቴም ከፍተኛ ደስታ ተሰማኝ፡፡” /በጎ አድራጊው በኵረ ምእመናን ቁምላቸው ገብረ ሥላሴ/ *          *          *   በበጎ አድራጊው በኵረ ምእመናን ቁምላቸው ገብረ ሥላሴ ድጋፍ ዕድሳት የተደረገለት የፍጹም ተኃራሚው ሣልሳዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የመታሰቢያ ሐውልት በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚገኘውና ሙሉ ጥገና እና ዕድሳት የተደረገለት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሦስተኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የመታሰቢያ ሐውልት ነገ፣ እሑድ፣ ግንቦት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ዳግም ምረቃ እንደሚደረግለት ተገለጸ፡፡ ከጠዋቱ 3፡00፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፤
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የእንደራሴ ምደባ በፈጠረው መካረር ስብሰባው በድንገት ተቋረጠ፤ ፓትርያርኩ “ኃይል አለኝ” ሲሉ ዛቱ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱ አዝነውበትና ጸልይውበትይወስኑበታል

“ኃይል አለኝ፤ ነገር ግን መጠቀም አልፈልግም” በሚል በሊቃነ ጳጳሳቱ ላይ ዝተዋል ምደባው፥ ቤተ ክርስቲያንን የመታደግና አደራን የመጠበቅ ጉዳይ እንደኾነ ተገልጧል፤ የልዩ ጽ/ቤትና የአ/አበባ ሀ/ስብከት አጀንዳዎች እንዲሰረዙ በያዙት ተቃውሞ ቀጥለዋል፤ “አንሡኝ!”ላሉበት አቋማቸው፣ “ቤተ ክርስቲያንን ለመታደግ እናደርገዋለን!” ተብለዋል፤ በጎጥና በጎሳ ለማሸማቀቅ የሞከሩ የምልዓተ ጉባኤው አባላት በከፍተኛ ደረጃ ተገሥጸዋል፤ *               *               * የ3 ዓመት ዘመነ ፕትርክና አፈጻጸማቸው በምልዓተ ጉባኤው ተገምግሟል፤ የፀረ ሙስና አቋማቸው ንግግር በማሣመር የተወሰነና ተግባር የራቀው ነው፤ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመጣስ አማሳኞችን ተባብረዋል፤ ከለላም ሰጥተዋል፤ የመናፍቃን ቅጥረኞችና አማሳኞች፣ በአባቶች ላይ ለመዝመት እየመከሩ ነው፤ *               *              * ብር 800ሺሕ የወጣበት በዓለ ሢመት፣ ብክነትና መንበረ ፓትርያርኩን ያዋረደ ነው፤ ለቤትና ለጂምናዝየም ዕቃዎች ማሟያ፣ 2 ሚ. ብር ከአ/አ ሀ/ስብከት ወጪ ተደርጓል፤ በደቡብ አፍሪቃ፣ የልዩ ጽ/ቤታቸው ጣልቃ ገብነት ችግሩን አባብሶ ለውርደት ዳርጎናል፤ በዱባይ የተሐድሶ መናፍቃን ያሉበት ደረጃ፣ በጉዳዩ ላይ ለዘብተኝነታቸውን አሳይቷል፤ *              *               *   “ኃይል አለኝ፤ ነገር ግን መጠቀም አልፈልግም” በሚል በሊቃነ ጳጳሳቱ ላይ ዝተዋል፤ የአማሳኞች
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅ/ሲኖዶስ: የፓትርያርኩን አመራር ውጤታማ በሚያደርጉ አሠራሮች ላይ መምከር ጀመረ

የመንበረ ፓትርያርኩ እንደራሴ ምደባና የጽ/ቤቱ አደረጃጀት ትኩረት ተሰጥቶታል ቅዱስ ፓትርያርኩ፥ “ሊያሠራኝ ስለማይችል አልቀበለውም” በሚል እየተቃወሙ ነው የቃለ ዓዋዲው ማሻሻያ ረቂቅ ለብዙኃን ውይይት እስከ አጥቢያ እንደሚወርድ ተጠቆመ *                *                * ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ በ፫ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን አመራር ውጤታማ ያደርጋሉ ባላቸው አሠራሮች ላይ መምከር ጀመረ፡፡ ከዚኹ ጋር በተገናኘ፣ ምልዓተ ጉባኤው የሠየመውና በብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ሊቀ መንበርነት የሚመራው ስምንት አባላት ያሉት የአጀንዳ አዘጋጅ ኮሚቴ፣ ሦስት ዐበይት ጉዳዮችን የለየ ሲኾን፤ ለምልዓተ ጉባኤው ቀርበው ከጸደቁት 24 የመነጋገርያ ነጥቦች ውስጥ እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡ እኒኽም፣ በተ.ቁ(4) የእንደራሴ ምርጫ፤ በተ.ቁ(7) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስ የሊቀ ጳጳስ ምደባ፤ በተ.ቁ(10) የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጭ ግንኙነት መምሪያ አደረጃጀት እና በሊቃነ ጳጳሳት መመራት እንደኾኑ ተጠቅሷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው፣ በትላንት፣ ግንቦት 18 ቀን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ሲኖዶስ: በቤተ ክርስቲያን መተዳደርያ ደንብ/ቃለ ዓዋዲ/ ማሻሻያ ረቂቅ እየተወያየ ነው

የቤተ ክርስቲያንን ኵላዊነት እንዲያገናዝብ እና ከሀገሪቱ ሕጎች እንዲጣጣም ይጠበቃል በመንግሥት እና በሚመለከታቸው አካላት ተቀባይነት እና ዕውቅና እንዲያገኝ ይደረጋል ከሥራ ቋንቋ አማርኛ ሌላ በተለያዩ የሀገርና የውጭ ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተጠቁሟል ቃለ ዓዋዲ፣ የአስተዳደርን ጨምሮ ልዩ ልዩ ደንቦች የሚጠሩበት አጠቃላይ ስያሜ ነው በ2004 ዓ.ም. የተወሰነው የማሻሻሉ ሥራ ከአራት ዓመታት በላይ ሲጓተት ቆይቷል *           *           * በማኅበረ ካህናት እና በማኅበረ ምእመናን አንድነት ተደራጅታ፣ በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የምትመራው ቤተ ክርስቲያናችን፣ የምትተዳደርበት የቃለ ዓዋዲ ማሻሻያ ረቂቅ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡ ቃለ ዓዋዲው፣ በ1991 ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ ከተሻሻለ በኋላ ላለፉት 17 ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ ሲኾን፤ የቤተ ክርስቲያንን የአስተዳደር ሥራ ከወቅቱ አንፃር በብቃት ለመምራት ውስንነት እንዳለበት፤ በፍርድ ቤቶችና በመንግሥት አካላት ዘንድም የዕውቅና እና የተቀባይነት ተግዳሮት እንደገጠመው በተለያዩ ሪፖርቶች ተገልጧል፡፡ የቃለ ዓዋዲው ማሻሻያ፥ የኵላዊት እና የአንዲት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የደረሰበትን ዕድገት ያገናዘበ እንዲኹም ከሀገሪቱ ሕጎችና ደንቦች ጋር የተጣጣመና ተቀባይነት ያለው ኾኖ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ: ለፓትርያርኩ እንደራሴ ለመምረጥ እና ጽ/ቤታቸው በአደረጃጀት ተጠናክሮ በሊቀ ጳጳስ እንዲመራ ለመወሰን ይነጋገራል

ከአጀንዳው ጋር በተያያዘ በወጡ መረጃዎች፡- እንደራሴው፣ ፓትርያርኩ ሓላፊነታቸውንና አመራራቸውን በብቃት እንዲያከናውኑ ያግዛል፤ የልዩ ጽ/ቤታቸውና የውጭ ግንኙነት ሠራተኞች ወደሌላ ተዛውረው በሊቃነ ጳጳሳት ይመራሉ፤ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ እና ዋና ሓላፊው አባ ቃለ ጽድቅ ከቦታቸው ይወገዳሉ!! ልዩ ሀገረ ስብከታቸው አዲስ አበባ፣ በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ራሱን ችሎ ሊቀ ጳጳስ ይመደብበታል፤ ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ለውድድር ቀርበው፣ በጉባኤው የሚመረጠው ብፁዕ አባት ይመደብበታል፤ በ፫ኛ ዓመት በዓለ ሢመት አከባበር፣ መንበረ ፓትርያርኩን የማይመጥኑ ግድፈቶች ይገመገማሉ የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ይሠየማል፤ ዕጩ ተሿሚዎች በግልጽ እንዲታወቁ ተጠይቋል ምልዓተ ጉባኤው የተጠቆሙትንና ሌሎች 24 አጀንዳዎችን በማጽደቅ መወያየት ጀምሯል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሕዝቡ፥ ቤተ ክርስቲያን ለችግሩ ደራሽና አለሁላችኹ ባይ ኾና ማየት ይፈልጋል፤ እሰየው የሚያሰኝ አሠራር ማረጋገጥ አለብን – ፓትርያርኩ

ሕዝበ ክርስቲያኑ፡- ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እና ለሃይማኖት መጠበቂያ ብሎ በእምነት የሚለግሰው ገንዘብ እና ንብረት ከምዝበራ ተጠብቆ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል፤ መልካም አስተዳደር ሰፍኖ፤ አድልዎ፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ፣ መለያየት፣ በአጠቃላይ ከሃይማኖቱ መርሕ ጋር የማይጣጣም ኋላ ቀር አሠራር እና አሰተሳሰብ ተወግዶ፣ የተስተካከለ ሥርዐትን ማየት፤ ስለ ሃይማኖት ክብር እና ህልውና ከልብ የሚቆረቆሩ፣ መልካም ሥነ ምግባርና የተስተካከለ ሰብእና ያላቸው፣ በኑሯቸው ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንደ ሞዴል የሚጠቀሱ ውሉደ ክህነትና ሠራተኞች እንዲመሩት፤ ቤተ ክርስቲያን÷ በኹሉም መስክ ጠንካራ አቅም ገንብታ፣ እንዲኹም ለሕዝበ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ችግር ደራሽ እና አለሁላችኹ ባይ ኾና ማየት ይፈልጋል፡፡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፡- የሕዝበ ክርስቲያኑን ጥያቄ በጽሞና አዳምጠው እና ተቀብለው፣ በቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ፤ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ድንጋጌ እና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማዕከልነት የማስተናገድ ክርስቶሳዊ ግዴታ አለብን፤ ከሕግ የወጣ አሠራር ሲኖርም፣ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በወቅቱ ማረም ያስፈልጋል፡፡ /ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር/ *               *               * በሃይማኖት እና በሃይማኖተኝነት ላይ ከባድ ተጽዕኖ በመፍጠር
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በርክበ ካህናት ቅ/ሲኖዶስ መክፈቻ ጸሎት: በጎጥና በሙስና መሾም ተወገዘ፤ ሕግ እንዲከበርና ፍትሕ እንዲሰፍን ተጠየቀ፤ “ፖሊቲካ ይውጣ፤ እውነት ይገለጥ”/ብፁዕ አቡነ እንድርያስ/

ምልዓተ ጉባኤው ከሚነጋገርባቸው አጀንዳዎች መካከል፡- የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የጠቅ/ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምርጫ እና ምደባ በአ/አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ምርጫ እና ምደባ ካህናት እና ምእመናን በጥቆማ ያልተሳተፉበት የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እና ሢመት ጉዳይ ሙስናንና ኑፋቄን ጨምሮ ኹለተናዊ ችግሮች የተጠኑበት የዐቢይ ኮሚቴ ሪፖርት ተጠቅሰዋል ጉበኞች እንዲወጡ፤ በዝባዦች እንዲጋለጡ፤ ምርጫ እና ምደባ በሞያ እንዲኾን ተጠይቋል  *               *               * የአራቱ ጉባኤያት ተጠያቂ፤ መምህር ወመገሥጽ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፤ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በዓለ ትንሣኤ በዋለ በአራተኛው ሱባኤ/፳፭ኛ ቀን/፣ የሚያካሒደው የምልዓተ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ የመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዓት፣ ዛሬ፣ ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.፣ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በዚኹ ሥነ ሥርዓት፤ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢው ብፁዕ አቡነ እንድርያስ የመርሐ ግብሩን ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ ብፁዕነታቸው÷ የቤተ ክርስቲያንን ዐበይት ወቅታዊ ችግሮችና ተግዳሮቶች የዳሠሡበትና ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ከነገ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በምዕራብ አርሲ፣ በባሌ፣ በአርሲ እና በደቡብ ክልል ዞኖች የሚተዳደሩ 13 ወረዳዎች በሀገረ ስብከት ራስን የመቻል ጥያቄ አቀረቡ

ሻሸመኔን ዋና ከተማው ያደረገው የምዕራብ አርሲ ዞን ከተቋቋመ 11 ዓመታት ተቆጥረዋል የዞኑ ምእመናን፣ በአዳማ ሀገረ ስብከት ሥር መጠቃለላቸው እንግልት እያደረሰባቸው ነው ከሰኔ 2007 ዓ.ም. አንሥቶ እስከ መንበረ ፓትርያርኩ ጥያቄአቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል የመልካም አስተዳደር ችግሩ፣ በአንድነት የነበሩትን የሻሸመኔን 6 አጥቢያዎች ሰላም ነስቷል ውዝግቡ ሠርግና ምላሽ የኾነላቸው አማሳኞችና የተሐድሶ መናፍቃን ጥምረት ፈጥረውበታል ዛሬ፣ ግንቦት 16 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም በተካሔደው፣ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት፤ በምዕራብ አርሲ ዞን የሻሸመኔ ምእመናን፣ በሀገረ ስብከት ራስን የመቻል ጥያቄ አቅርበዋል፤ ሊቀ ጳጳስ እንዲመደብላቸውም ጠይቀዋል፡፡ በአራት መኪኖች ተጭነው የመጡ ከ150 በላይ ምእመናን፣ በመክፈቻ ጸሎቱ ፍጻሜ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከእንባ እና ከፍተኛ ተማኅፅኖ ጋር በንባብ ባሰሙት አስተዳደራዊ ጥያቄ፤ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማግኘት እና መንፈሳዊ ግዴታቸውን ለመፈጸም ወደ አራት የተለያዩ አህጉረ ስብከት ለመሔድ በመገደዳቸው፣ ለእንግልት እየተዳረጉ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ ምእመናኑ በጽሑፍ ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አሰራጭተዋል፡፡በአኹኑ ወቅት፣ 
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሐውልተ ስምዕ በፓትርያርኩ ተመረቀ፤ በሙርሌ ታጣቂዎች ተወስደው የተመለሱ ሕፃናትን ባርከዋል

የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ሙዝየም ዕብነ መሠረት፣ በፓትርያርኩ ተቀምጧል የክልሉን የፖሊስ ኮሚሽነር ጨምሮ ለ87 ምእመናን ጥምቀተ ክርስትና ተፈጽሞላቸዋል በሙርሌ ታጣቂዎች ወላጆቻቸውን ያጡትን ቤተ ክርስቲያን ታሳድጋለች፤ታስተምራለች /ፓትርያርኩ እና የጋምቤላ ሀገረ ስብከት/ በጎሬ ከተማ የተመረቀው የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሐውልተ ስምዕ የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል የምስክርነት ሐውልት፣ ትላንት ግንቦት 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት፣ ማኅበረ ካህናት እና ማኅበረ ምእመናን በተገኙበት ሰማዕትነትን በተቀበሉበት በጎሬ ከተማ ተመርቋል፡፡ የብፁዕነታቸው ዐፅም ከነበረበት ሐውልታቸው ወደቆመበት ስፍራ በክብር ያረፈ ሲኾን፤ በስማቸው የሚገነባ ቤተ መዘክር ዕብነ መሠረትም በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተቀምጧል፡፡ ግፈኛው የኢጣልያ ፋሽስት፣ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ፣ ሕዝቡን ሰብስበው ለጠላት እንዳይገዛ በማስተባበር፣ የቤተ ክርስቲያኑን ክብር እንዲጠብቅ በማደፋፈር ላይ ሳሉ ኅዳር 17 ቀን 1929 ዓ.ም. በፋሽስቱ እጅ የወደቁት ብፁዕነታቸው፥ ሕዝቡን እንዲያባብሉ፤ ኢጣልያም የኢትዮጵያ ገዥ እንደኾነች እንዲናገሩ፤ ፋሽስቱ በትልቅ ሹመት እና ሽልማት አግባብቷቸው ነበር፡፡ ብፁዕነታቸው ግን፡- “እኛ ጌታችን እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ሌላ ገዥ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በሓላፊነታቸው እንደማይቀጥሉ በፓትርያርኩ ተነገራቸው፤ የአያሌ አባቶች እንባና እርግማን አለባቸው

ቤተ ክርስቲያንን “የተደረተች”፤ፓትርያርኩን“ብቃት የሌላቸው”፤ ጳጳሳቱን“ማይሞች እና ደደቦች” እያሉ መዝለፍ አዘውትረዋል፤ ራሳቸውን የመንግሥት ታማኝ አድርገው ስም እየጠሩና “እገሌ ደወለልኝ” እያሉ በፓትርያርኩም ላይ ጫና ሲፈጥሩ ቆይተዋል፤ “ጥላ ወጊ አለኝ፤ በጥላ ወጊ እሸበልለዋለኹ!” የሚለው ከንቱ የጥንቆላ፣ የመተት እና የመርዝ ማስፈራሪያቸውም አይዘነጋም! ምደባቸው፥ ከሹመት ቦታዎች ውጭ እንዲኾን በተደጋጋሚ ቢጠቆምም፤ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የድርጅት ሓላፊነት እየተፈለገላቸው ነው በበኬ ከተማ ባለ6 ፎቅ ሕንፃ እያስገነቡ ነው፤ የተለያዩ ይዞታዎች ባለቤት በኾኑበት በየረር ሰፈራ ባለ5 ፎቅ ሊገነቡ ይንቀሳቀሳሉ *          *          * የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ በልዩ ጽ/ቤቱ ሓላፊነታቸው እንደማይቀጥሉ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እንደተነገራቸው ተሰማ፡፡ ፓትርያርኩ ውሳኔአቸውን ያሳወቋቸው፣ ለኢየሩሳሌም ጉብኝት ከመነሣታቸው አራት ቀናት በፊት እንደነበር የተናገሩት ምንጮቹ፤ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ከልዩ ጸሐፊነታቸው መነሣታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ሳይደርሳቸው እንዳልቀረ ጠቁመዋል፡፡ በሓላፊነት በተቀመጡባቸው ቦታዎች ኹሉ፥ በምዝበራ ሰንሰለታቸው የሙስና ገበያውን እያጧጧፉ ሕገ ወጥ ሀብት በማካበት፤ የጎጥ እና የመንደር ቡድን እያቋቋሙ በመከፋፈል፤ የቀድሞውንም ይኹን የወቅቱን ፓትርያርክ ክፉ እየመከሩ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ እና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የዴር ሡልጣን ጉዳይ ከዋነኛ ተግባራችን አንዱና በየደረስንበት የምናስረዳው አጀንዳ ነው – በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ

“ግብፃውያን እንዳያድሱ ርስትነቱ የእነርሱ አይደለም፡፡ እኛም ከተከለከልን ማደስ ያለበት፣ መንግሥት ነው፡፡ ችግሩ የእስራኤልንም መንግሥት የሚያስነቅፍ ነው፡፡”/ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/ “በኤምባሲው ዓመታዊ ዕቅድ ውስጥ፣ ከዋነኛ ተግባራት አንዱ ኾኖ ተቀምጦ፣ ዋና መሥሪያ ቤቱም ክትትል የሚያደርግበት ነው፡፡” /በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ህላዌ ዮሴፍ/ “ምንም ቢኾን መነጋገር የማይፈታው ነገር የለምና እንነጋገርበታለን፤ ጉዳዩን እንፈታዋለን፡፡”/የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ሩቨን ሩቭሊን/ *               *               * “ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በተጓዝን ቁጥር የንግሥት ሳባን ፈለግ መከተላችንን እናስባለን፤” ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በኢትዮጵያ እና በእስራኤል መካከል ያለው ዝምድና፣ በዓለም ሃይማኖታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ታሪክ እጅግ ጥንታዊው መኾኑን ለእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ነግረዋቸዋል፤ ይላል የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረ ገጽ ዘገባ፡፡ ይኹንና ከሦስት ሺሕ ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የዴር ሡልጣን ገዳማችን አለመታደሱ አግባብ አለመኾኑን የገለጹት ፓትርያርኩ፤ በእግዳት ውስጥ እስካለ ድረስ ሓላፊነቱ የመንግሥት መኾኑን ለፕሬዝዳንቱ አስረድተዋቸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱም በምላሻቸው፣ “መነጋገር የማይፈታው ነገር የለምና እንነጋገርበታለን፤ ጉዳዩን እንፈታዋለን፤” እንዳሏቸው ኢቢሲ፣ በትላንት፣ ግንቦት 10 ቀን ምሽት ዜናው ገልጿል፡፡ የፓትርያርኩ ሐዋርያዊ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቤተ ክርስቲያናችን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ከቀናት በኋላ የሙከራ ስርጭት ይጀምራል

መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ አገልግሎቱን በዋና ዳይሬክተርነት ይመራሉ በፓትርያርኩ የኢየሩሳሌም ጉብኝት ከኮሚዩኒኬሽን ኩባንያው ጋር ውል ተፈጽሟል ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ለሥርጭቱ የ30,050 ዶላር ወርኃዊ ክፍያ ለኩባንያው ይፈጽማል ፓትርያርኩ የኹለት ሳምንት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ከቀትር በኋላ ይመለሳሉ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተወሰነው መሠረት፤ ቤተ ክርስቲያናችን፣ በሀገር ውስጥ እና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ምእመናን ድምፅዋን የምታሰማበት እና መረጃ የምትሰጥበት የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ከኹለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የሙከራ ስርጭቱን እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡ የስርጭት አገልግሎቱን ለመስጠት ለወድድር ከቀረቡት ሦስት ኩባንያዎች መካከል በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የብዙኃን መገናኛ ድርጅት ቦርድ ከተመረጠውና በእስራኤል ከሚገኘው የኮሚዩኒኬሽን ኩባንያ ጋር የሥርጭት ስምምነት ውሉ ፓትርያርኩ ኢየሩሳሌምን እየጎበኙ በነበሩበት በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ መፈጸሙም ታውቋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ለአገልግሎቱ 12 ሚሊዮን ብር የአንድ ዓመት በጀት ያጸደቀ ሲኾን፤ በዚኽ ሳምንት በተፈረመው የስምምነት ውል መሠረት ቤተ ክርስቲያናችን፣ 30,050 ዶላር(ከ660ሺሕ ብር በላይ) በየወሩ ለኩባንያው እንደምትከፍል ተጠቁሟል፡፡ የብዙኃን መገናኛ ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ በቦርዱ የተመደቡት እና ስምምነቱን ከኩባንያው ጋር የተፈራረሙት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በቡሌ ሆራ ገርባ ከተማ የምእመናን ደኅንነትና የእምነት ነፃነት አስጊ ኾኗል፤ በፋሲካ እርድና የሉካንዳ ንግድ በተፈጠረ ሁከት ለድብደባና ለእስር ተዳርገዋል

በአንዳንድ ባለሥልጣናት ግፊትና በተደራጀ ኃይል የጥላቻ ቅስቀሳ ይካሔድባቸዋል ጭምብል አጥልቆ፣ ገጀራ እና ጦር ይዞ ካህናትንና ምእመናንን እየመረጠ ያጠቃል የመኖርያ እና የንግድ ቤቶቻቸውን እየለየ በድንጋይ ይደበድባል፤ ዝርፊያ ይፈጽማል በጾም ሉካንዳዎችን በግድ ያስከፍታል፤ የሚዘጉቱም በፋሲካው እንዳይሠሩ ይከለክላል *                *                 * ጥንታዊውን የገርባ ደብረ ሰላም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ለመጉዳት ተሞክሯል ደወል በማሰማት ደብራቸውን የተከላከሉ ምእመናን በሁከተኛነት ተወንጅለው ታስረዋል ምእመኑ፥ ተጎጅም ተከሣሽም መደረጉን የሀገር ሽማግሌዎች በስብሰባ ላይ ተቃውመዋል *               *                * ለምእመናኑ የደኅንነት ስጋትና ለዞኑ ጥያቄ ወረዳው የሚሰጠው ምላሽ ርስበሱ ይጋጫል ለወረዳው አነስተኛ ጸጥታ “ኃይል እየመጣ ነው” ሲል ለዞኑ ጥያቄ ግን“ሰላም ነው” ይላል የማረጋጋት ዓላማ ያላቸው ሕዝባዊ ስብሰባዎችና ምክክሮች እንደቀጠሉ ናቸው፤ ተብሏል *                *                * “የሃይማኖት ግጭትም አይደለም፤ የብሔረሰብ ግጭትም አይደለም፤ ችግሩ የተወሰኑ ሰዎች ስሜት እና አጀንዳ ነው፤ ሕዝቡ አብሮ የኖረ ነው፤ ነገም አብሮ የሚኖር ነው፤ ግለሰብ ጠብ አጫሪዎች እና በሕዝቡ ወይም በሃይማኖት ተቋማት ሽፋን በመጠቀም የብጥብጥ ሙከራ የሚያደርጉ በየመሥሪያ ቤቱም ኾነ በየሃይማኖት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ: የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጁን ተማሪ አባረረ፤“ቤተ ክርስቲያን በማታውቃቸው እንቅስቃሴዎች መገኘቱ ተረጋግጧል”/ኮሌጁ/

“ፍኖተ ሕይወት ተስፋ ተሐድሶ” የተሰኘየፕሮቴስታንታዊ ድርጅት እንቅስቃሴ ተሳታፊ ነበር በድርጅቱ ምልምሎች ምረቃ፥ መቋሚያ በማደልና ከበሮ በመምታት ቀሣጢነቱን አረጋግጧል የቀን እና የማታ መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት በተከታታይ ማጣራቱ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል የተወሰደው ርምጃ ለኮሌጁ ማኅበረሰብ ይፋ አለመደረጉ አስተዳደሩን ለትችት እየዳረገው ነው መ/ር ሰሎሞን ኃ/ማርያም በጎይትኦም ያይኔ ቦታ በአስተዳደር ምክትል ዲንነት ተመድበዋል *                *                * የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ በቤተ ክርስቲያን በማይታወቁ እና ኮሌጁ በማይቀበላቸው የኑፋቄ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አግኝቸዋለኹ፤ ያለውን አንድ ተማሪ ማሰናበቱ ተገለጸ፡፡ አስቻለው ዮሴፍ ኤዳኦ የተባለው ይኸው ግለሰብ፣ በኮሌጁ የማታው ዲፕሎማ መርሐ ግብር የሦስተኛ ዓመት ተማሪ የነበረ ሲኾን፤ አስተዳደሩ ባገኘው ጠንካራ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ተከታታይ ማጣራት ሲደረግበት መቆየቱ ተጠቅሷል፡፡ በቁጥር 924/05/04/08 በቀን 06/08/2008 ዓ.ም. በበላይ ሓላፊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ፥ ተማሪ አስቻለው ዮሴፍ፣ በተደረገበት ክትትልና ማጣራት ቤተ ክርስቲያን በማታውቃቸው እና ኮሌጃችን በማይቀበላቸው የሃይማኖት እንቅስቃሴዎች ውስጥ መገኘቱ እንደተረጋገጠ ገልጿል፤ በኮሌጁ ሕግና ደንብ መሠረትም፤ ከማታው መርሐ ግብር መሰናበቱን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ: ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለፓትርያርኩ የጻፈውን ጽሑፍ በማተሙ በጠቅ/ቤተ ክህነቱ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ተከሠሠ

ከስም ማጥፋት ወንጀል በተጨማሪ የ100 ሺሕ ብር የፍትሐ ብሔር ክሥ አቤቱታም ቀርቧል ግንቦት 17 እና 26 ቀን በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት ይቀርባል የሕግ አገልግሎት መምሪያው የጉዳዩ አያያዝ እና የክሡ አቀራረብ ጥያቄ አሥነስቷል *                *                * ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለማረጋገጥ እንደተቻለው፤ የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል፥ ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ዋና ሓላፊ አማካይነት የክሥ ጽሕፈቱ ደርሶታል፡፡ በክሥ ጽሕፈቱ እንደተገለጸው፥ ከሣሹ፣ የሕግ አገልግሎት መምሪያው ዋና ሓላፊ እና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ወኪል አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት ሲኾኑ፤ ተከሣሹ ደግሞ፤ የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ፍሬው አበበ ናቸው፡፡ የክሡ ምክንያት፣ ጋዜጣው በ11ኛ ዓመት ቁጥር 551 ረቡዕ መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. እትሙ፣ “ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት” በሚል ርእስ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተጻፈውን ጽሑፍ እንዲታተም በመፍቀዱ እና በማተሙ እንደኾነ ተጠቅሷል፡፡ በ2000 ዓ.ም. በወጣው የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት ዐዋጅ ቁጥር
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቀድሞው የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ: የሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ዓምባገነናዊና አማሳኝ አመራር በቀድሞው ዋና ሓላፊ ሲፈተሽ

“ሀገረ ስብከቱ ልምድ ባለው ረዳት ሊቀ ጳጳስ የቅርብ ክትትል እና የትምህርት ዝግጅትን፣ ሞያዊ ብቃትን፣ ልምድንና መንፈሳዊነትን መሠረት አድርጎ በሚገባ በተዋቀረ የአስተዳደር ጉባኤ እስካልተመራ ድረስ፥ የሥራ ብልሽቱ እና ተበዳይ አልቃሹ እየበዛ እንደሚሔድ እርግጠኛ ነኝ፡፡”  /መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድ ይፍራው፤ የቀድሞው የሀ/ስብከቱ የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ሓላፊ/ *          *          * የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት በኾነው በአዲስ አበባ፣ በመጋቢት ወር የተደረገውን የሥራ አስኪያጅ እና የዋና ክፍሎች ሓላፊዎች ለውጥ ተከትሎ ጥያቄዎች እየተነሡ ነው፡፡ የመጀመሪያው፥ ሓላፊዎቹ በፓትርያርኩ ቀጥተኛ ውሳኔና ከልዩ ጽ/ቤታቸው በወጡ ደብዳቤዎች የተነሡበትና የተመደቡበት መንገድ፣ ቀደም ሲል ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ የተሠራውን ስሕተት የሚደግምና የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ተጠሪ የሆነለትን የጠቅላይ ጽ/ቤቱን ሥልጣን የሚጋፋ መኾኑ ነው፡፡ ኹለተኛው፥ የአህጉረ ስብከት ማዕከል በኾነው አዲስ አበባ ምደባው፣ ብቃትንና ልምድን መሠረት ያደረገ ኹሉን አካታች መኾን ሲገባው ቀድሞም የነበረውንና ቤተሰባዊ እስከመኾን የደረሰውን የአንድ ወገን ብዙኅነት ያስቀጠለ ነው፤ የሚለው ትችት ነው፡፡ ሦስተኛውና ዋነኛው ጥያቄ፥ ርምጃው የሀገረ ስብከቱን የመዋቅር፣ የአደረጃጀት እና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ከቦሌ መድኃኔዓለም ለየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እና ለኤልያስ ተጫነ በ“ስጦታ” የተበረከተላቸው 104 ሺሕ ብር እያነጋገረ ነው፤ “ሲያንስባቸው ነው”/ዋና ጸሐፊው/

“ስጦታው”፥ የካቴድራሉ መደበኛ የደመወዝ ጭማሬ መፈጸሙን ተከትሎ የተደረገ ነው ካህናቱ እና ሠራተኞቹ አለውድ በግድ ለመዋጮ ፈርመዋል፤ ካልፈረሙትም ተቆርጧል ዋና ጸሐፊው ተስፋ ማርያም ነጋሽ እና ሒሳብ ሹሙ ግርማይ ሐዲስ አስፈጽመውታል “ለምስጋና ነው” የሚሉት ዋና ጸሐፊው“መኪናም ቢሸለሙ ሲያንስባቸው ነው” ይላሉ  *** ሰበካ ጉባኤው የሥራ እና የሒሳብ ሪፖርት ሳያቀርብ እንዲወርድ ግፊት እየተደረገ ነው “ፓትርያርኩ አዘውናል” በሚል ግፊት የሚያደርጉት፥ አለቃው እና ዋና ጸሐፊው ናቸው ከቃለ ዐዋዲው ውጭ በኾነ የምርጫ ቅድመ ዝግጅት ሰበካ ጉባኤውን ለማቋቋም ይሠራሉ በሙስናው አቀባባዮች ላይ አብነታዊ የኾነ ሕጋዊና አስተዳደራዊ ርምጃ ሊወሰድ ይገባል *** (አዲስ አድማስ፤ ማሕሌት ኪዳነ ወልድ፤ ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለምና መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ ካቴድራል የደመወዝ ጭማሬ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስለተደረገላችኹ የአንድ ወር የደመወዝ ጭማሬአችሁን ለስጦታ አዋጡ ተብለን በግዳጅ ሰጠን፤ ሲሉ አንዳንድ የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለምና መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ ካቴድራል ካህናትና ሠራተኞች አስታወቁ፡፡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የካቴድራሉ ካህናት ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፤
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ነገ ምሽት ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዛሉ

ጉብኝቱ÷ በእግዳት ውስጥ ላለው የዴር ሡልጣን ገዳማችን ዓለም አቀፍ ትኩረት እና ድጋፍ ለማሰባሰብ፤ ጉዳዩንም ወደፊት ለመግፋት ያግዛል፤ ተብሏል ይዞታ ካላቸው ጥንታውያን ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት እና ሌሎች አብያተ እምነት መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል የቀድሞውን ፓትርያርክ ሲወቅሱ የቆዩት የሀገረ ስብከቱ – ሊቀ ጳጳስ – ነበር የአኹኑ ፓትርያርክ፣ በአሳዛኝ ኹናቴ ላይ ላለው ይዞታችን መጠበቅ የሚጠቀስ ርምጃ እንዳላሳዩ ይወቀሳሉ የግብጽ እና የኢትዮጵያ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ሲኖዶሳዊ ውይይት ችግሩን እንደሚፈታው የገለጹት ፓትርያርኩ፤ “ጉዳዩ በእስራኤል መንግሥት ስለተያዘ ተስፋ አለኝ፤” ይላሉ *          *          * ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ከነገ ሚያዝያ 26 ቀን ጀምሮ በእስራኤል የአንድ ሳምንት ሐዋርያዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ጉብኝታቸው፣ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት የታሪክና የቅድስና መካናት ጉዳይና ከዚኹ በተገናኘ ይዞታ ካላቸው አኃት አብያተ ክርስቲያናትና ሌሎች አብያተ እምነቶች ጋር ባለው ግንኙነትና የይዞታ አጠቃቀም ችግሮች ላይ እንደሚያተኩር ተገልጧል፡፡ ከጥንታውያኑ የአርመን እና የሶርያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ፤ የግሪክ እና የሩስያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካቶሊክ እና ሩማንያ የመሳሰሉት
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ትንሣኤ የአሸናፊነትና የድል አድራጊነት በዓል ነው! ከሴኩላሪዝምና ግሎባላይዜሽን ከባድ ጫናዎች ሃይማኖታችንንና ዕሴቶቹን መጠበቅና ማጽናት ይገባል(ፓትርያርኩ)

የዘመናችን ትልቁ የሃይማኖት ተግዳሮት፡- ቴረሪዝም፣ ሴኩላሪዝምና ግሎባላይዜሽን፥ በማንነትና በሃይማኖት ላይ ከባድ ጫና እየፈጠሩ ነው ሃይማኖትንና የማንነት ዕሴቶችን አጽንቶ በመያዝ ካልተመከቱ በቀር ፈተናው ቀላል አይኾንም ምእመኑ ለሃይማኖቱ እንዲጋደልና ማንነቱን እንዲጠብቅ ቤተ ክርስቲያን አጥብቃ ትመክራለች +++ የሞት እና የመቃብር ምንጩ ሕገ ተፈጥሮ ሳይኾን ግብረ ኃጢአት ነው፤ የበደል ውጤት ነው አለመታዘዝ እና የተሳሳተ ምርጫ ኃጢአትን ወልዶ የሞት እና የመቃብር ቅጣትን አስፈርዷል ዲያብሎስ በኃጢአት ጦር ሰውን ሲገድል፤ መቃብር ሙታንን ሲማግድ ፭ሺ፭፻ ዓመታት አለፉ +++ ኃያል ድል አድራጊ ዘር የተሸነፈውን ሊታደግ ከሴት እንደሚወለድ ተስፋ ድኅነት ተሰጥቷል በኃጢአት፣ በዲያብሎስ፣ በሞት እና በመቃብር ላይ ሙሉ ሥልጣኑን በትንሣኤው አረጋግጧል በትንሣኤው የተሸነፉት ሞትና መቃብር፣ በዳግም ምጽአቱ ህልውናቸውን አጥተው ያከትማሉ +++ የአሸናፊነትና የድል አድራጊነት በዓል – ትንሣኤ፡- በእግዚአብሔር አርኣያ እና ምሳሌ የተፈጠረው ሰው በመጨረሻ በአምላኩ ቸርነት አሸናፊ እንደኾነ ያስገነዝበናል፤ ዲያብሎስን፣ ኃጢአትን፣ ሞትንና መቃብርን የሚያሸንፉ መስተጋድላንና መዋዕያን ቅዱሳንን በብዛት አስገኝቷል፤ ክርስቶስ ተነሣ ብለን የምሥራች በመናገር ብቻ ሳይኾን ተስፋ ትንሣኤያችንን በማስተጋባት ልናከብረው
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በዓለ ስቅለት እና በዓለ እግዝእትነ ሲገጣጠሙ ይሰገዳል ወይስ አይሰገድም? “በበዓለ ስቅለት እንዳይሰገድ የሚከለክል በዓል የለም፤ ሊኖርም አይችልም”

/መምህር ብርሃኑ አድማስ/ ነገሩን ከመሠረታዊው የቤተ ክርስቲያን ትውፊት እና አስተምህሮ አንጻር ማየት አለብን በቤተ ክርስቲያናችን የበዓላት አከባበር ቀኖና እና ትውፊት መሠረት በዓላት ይበላለጣሉ እጅግ የተለየ ክብር ካላቸው አራቱ የጌታችን ዐበይት በዓላት÷ በዓለ ስቅለት አንዱ ነው በስቅለት ቀርቶ በሰሙነ ሕማማት በየትኛውም ዕለት እንዳይሰገድ የሚከለክል በዓል የለም በዓለ ስቅለት፡- በፍትሐ ነገሥቱ የበዓላት ክብር ቅደም ተከተል መሠረት፣ ከጌታችን ዐበይት በዓላት ቀጥላ የምትከበረውን ቀዳሚት ሰንበትን ከሻረ የማይሽረው ሌላ ምንም በዓል ሊኖር አይችልም፤ ልደት፣ ጥምቀት እና ትንሣኤ ሐዘንን ይሽራሉ፤ ስቅለትም ማንኛውንም ደስታ ይሽራል፤ በሐዘን፣ በጾም፣ በስግደት የሚከበር ስለኾነ የሌላን በዓል ጠባይ በፍጹም አይወርስም፤ እነዚኽ በዓላት ከሌሎቹ ጋር ሊነጻጸሩ እንደማይችሉ በደንብ ከገባን፣ የስቅለት ዕለት በተደረበ በዓል ምክንያት ይሰገዳል አይሰገድም የሚለው ክርክር ሊፈጠር አይችልም፤ ጠብ እና ክርክር ከማስነሣት፣ ተስማምቶና ተከባብሮ አንዱን ማድረጉ የተሻለ በመኾኑ ራስን ከክርክር መቆጠቡ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፤ በዓሉም የሚሻው ዐቢይ ነገር ነውና፡፡  *                *               * መምህር ብርሃኑ አድማስ ምንም እንኳ ይህ ጥያቄ በብዙ ሰዎች
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቋሚ ሲኖዶስ: ለደቡብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስን በሥራ አስኪያጅነት ሾመ፤ አባ ጥዑመ ልሳን አዳነ ወደ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ተጠርተዋል

መጋቤ ብርሃናት ቆሞስ አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ ቋሚ ሲኖዶስ፥ በዛሬ ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው፣ በአስተዳደራዊ ውዝግብ ሲታመስ በቆየው የደቡብ አፍሪቃ አህጉረ ስብከት እና የጆሐንስበርግ ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ደብር ጉዳይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በውሳኔው መሠረት፣ ላለፉት ዓመታት አህጉረ ስብከቱን በሥራ አስኪያጅነት ደብሩንም በአስተዳዳሪነት ሲመሩ ከሰበካ ጉባኤው ጋር በፈጠሩት ውዝግብ፣ ለምእመናኑ አንድነትና ከሀገሪቱ ሕግም አንፃር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ህልውና ከፍተኛ ስጋት ጋርጠዋል የተባሉት አባ ጥዑመ ልሳን አዳነ ከሓላፊነታቸው ተነሥተው ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ እንዲመለሱ ተጠርተዋል፡፡ በምትካቸው፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የጎፋ ጥበበ እድ ካህናት ማሠልጠኛ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ፣ መጋቤ ብርሃናት ቆሞስ አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ የተመደቡ ሲኾን አህጉረ ስብከቱን በሥራ አስኪያጅነት ከመምራት ባሻገር የጆሐንስበርግ ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ደብርንም በእልቅና ያስተዳድራሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን የአብነት ትምህርት በሰፊው የደከሙትን መጋቤ ብርሃናት አባ ተክለ ያሬድን “ብጥር መሪጌታ ናቸው” ይላሉ፤ የሊቅነትና ክህነታዊ ሞያቸውን በቅርበት የሚያውቁላቸው፡፡ የመዝገብ ቅዳሴ፤ የዝማሬ መዋስዕት፣ የአቋቋም እና የሐዲስ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ከግንቦት 17 – 22 ቀን በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ዕውቅና አገኘ

የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ዕውቅና የአዲስ አበባ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት፣የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ዕውቅናውን የሰጠው፥ ዛሬ፣ ሚያዝያ 11 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ ከጠዋቱ 3፡00 ላይ እንደኾነ የማሳወቂያ ቅጹ ያመለክታል፡፡ “የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ማሳወቅ” በሚል ዓላማ ባገኘው ዕውቅና ከግንቦት 17 – 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሸት 4፡00 ድረስ ለሚካሔደውና ከ100 ሺሕ በላይ ተመልካች እንደሚጎበኘው ለሚጠበቀው የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ መንግሥት የፖሊስ ጥበቃ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ የማኅበሩ አመራር እና የዝግጅቱ ዐቢይ ኮሚቴ፣ ቀደም ሲል ከመጋቢት 15 እስከ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በዚያው በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ታቅዶ የነበረው የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ መርሐ ግብር ባልተለመደ ሕግና አሠራር እክል ከገጠመው ደቂቃ ጀምሮ፥ የአዲስ አበባ አስተዳደርንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ ሓላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በትዕግሥት ሲያካሒድ ሰንብቷል፡፡ ውይይቶቹ በተካሔዱባቸው አጋጣሚዎች ኹሉ፣ መርሐ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

መናፍቁ ከፍ ያለው ቱፋ: በአሰበ ተፈሪ ያልተፈቀደ ኅቡእ ጉባኤ በማካሔድ በቁጥጥር ሥር ዋለ፤ ወደ ኮሌጁ የመመለስ ጥያቄው በፍ/ቤቱ ለ2ኛ ጊዜ ውድቅ ተደርጓል

ከፍ ያለው፥ ከ22 ኅቡእ ተሰብሳቢዎች ጋር በፖሊስ የተያዘው በመኖርያ ቤት ውስጥ ነው 5ቱ ግለሰቦች በፖሊስ ጣቢያው ተይዘው ሲገኙ፤ 17ቱ ጉዳያቸውን በውጭ ይከታተላሉ ከፍ ያለውን ጨምሮ በመኖርያ ቤቱ ባለቤትና በ5ቱ ግለሰቦች ላይ ምርመራው ቀጥሏል ፕሮቴስታንቱ የተስፋ ክሊኒክ ባለቤት ለከፍ ያለው ቱፋ ጠበቃ ለማቆም ይሯሯጣል የከፍ ያለው ቱፋን የሖቴል መስተንግዶ የሸፈነው ይኸው ፕሮቴስታንታዊ ግለሰብ ነው *               *               * ከጅምሩ ሲከታተለው የቆየው የምዕ/ሐረርጌ ሀ/ስብከት፣ ከፖሊስ ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ፣ በሀገረ ስብከቱ ጥያቄ አስፈላጊ ማስረጃዎችን ልኳል በቤት ለቤት ጉባኤያት ኑፋቄን በኅቡእ መዝራት፤ ከኮሌጁ የተባረረበት አንዱ ምክንያት ነው የኮሌጁን ውሳኔ ለማሳገድ ላቀረበው ክሥ፤ የኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ችሎት ነገ ውሳኔ ይሰጣል እየተማረ ጉዳዩን ለመከታተል በቃል ያቀረበውን ጥያቄ ችሎቱ ለ2ኛ ጊዜ ውድቅ አድርጎታል የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ፥ የከፍ ያለውን ቱፋን መናፍቅነት በሚያረጋግጡ ተጨባጭ ማስረጃዎች ላይ ተመሥርቶ የበላይ ሓላፊውን ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልን ጨምሮ የአስተዳደር ጉባኤ አባላቱ፣ መምህራኑና የተማሪዎች መማክርቱ በያዙት የጋራ አቋም
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በቦሌ መድኃኔዓለም: ምዝበራ እና ለአገልግሎቱ የተሰጠው ትኩረት ካህናትን እያማረረ ምእመናንን እያሸሸ ነው፤ ለሕዳሴ ግድብ ቦንድ የተዋጣው 400ሺሕ ብር የገባበት አልታወቀም

በካቴድራሉ አስተዳደር፡- የደመወዝ ጭማሪ ለማጸደቅ 104ሺሕ ብር ለየማነ ዘመንፈስ ቅዱስና ለኤልያስ ተጫነ ተሰጥቷል ኹለት ሕንፃዎች÷ ያለሰበካ ጉባኤው ዕውቅናና ያለጨረታ ከአካባቢው ዋጋ በታች ተከራይተዋል የስፍራው ዋጋ በካሬ ከ400 – 500 ብር ቢኾንም ሕንፃዎቹ ከ54 – 120 ብር ነው የተከራዩት የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራ ሰነዶች መኖራቸው አጠራጥሯል፤ ባንክ ለመግባቱም ማረጋገጫ የለም በካቴድራሉ አገልግሎት፡- የቀድሞውን መጋዘን ማረፊያ አድርገው የሚኖሩት ካህናት ለተለያዩ የጤና እክሎች ተዳርገዋል ለቅዳሴው፣ ለማሕሌቱና ለስብከተ ወንጌሉ ትኩረት በማነሱ አገልግሎት ለመፈጸም ተቸግረዋል አካባቢውን ያገናዘበ ልማት ቢታቀድም፣ ካቴድራሉ ጥራቱን የጠበቀ መጸዳጃ ቤት እንኳ የለውም የካቴድራሉን ደረጃ የጠበቀ፣ ሳቢና ማራኪ አገልግሎት ባለመኖሩ ምእመናን ከአጥቢያው ይሸሻሉ ዐሥር ዓመት ያስቆጠረው የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ፡- ከፍተኛ ሞያ እና ልምድ ያላቸው ምእመናን ቢገኙበትም አስተዳደሩ ሊያሠራቸው አልቻለም በዕቅዱና በበጀቱ ለመሥራት አለመቻሉን በመጥቀስ፣ ጽ/ቤቱን “አሰናብቱን” እስከማለት ደርሷል በርካታ አቤቱታዎችንና ማስረጃዎችን ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ቢያቀርብም መፍትሔ አልተገኘም ከካቴድራሉ አቅምና ጥያቄ ውጭ፥ የሀ/ስብከቱን የዘፈቀደ የሰው ኃይል ምደባ ለመቀበል ተገዷል  የካቴድራሉ አስተዳዳሪ፡- ካህናቱንና ምእመናኑን በዐደባባይ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና -አማሳኙ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ተወገደ! የተሐድሶ ኑፋቄ ተላላኪው ጎይቶኦም ያዩኒ ተተካ፤ 3 ተጨማሪ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎችም ተነሥተዋል

በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ምትክ፥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ዛሬ ከቀትር በኋላ በፓትርያርኩ ደብዳቤ የተመደቡትና ለልዩ ጸሓፊው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአስተዳደር ምክትል ዲን መ/ር ጎይቶኦም ያዩኒ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሓላፊው ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ፤ የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ክፍል ሓላፊው ሊቀ ሥዩማን ወልደ ሰንበት አለነ፤ የዕቅድና ልማት ዋና ክፍል ሓላፊው ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዝዘዋል፤ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ወጪ ኾኖ ማምሻውን ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የደረሰው የሹም ሽር ምደባና ዝውውር፣ “የሠራችኹት ተመርምሮና ተገምግሞ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጣችኹ ድረስ” የሚልና በጊዜያዊነት የተደረገ ስለመኾኑ ተጠቁሟል፤ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በሕገ ወጥ መልኩ ከሥራ አስኪያጅነቱ ጋር ደርቦ በያዘውና ቀድሞ ሲሠራበት በነበረው የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር ዋና ጸሐፊነቱ ይቀጥላል፤ “የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጣችኹ” በሚል ከተነሡት ሓላፊዎች ኹለቱ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ተመድበዋል፤ ሊቀ ጠበብት ኤልያስ፥ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የገዳማት መምሪያ ጸሐፊነት፤ ሊቀ ሥዩማን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርኩ: በአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅና በልዩ ጸሐፊያቸው ጉዳይ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገባቸው ነው፤ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከሓላፊነቱ ሳይወገድ እንዳልቀረ ተጠቁሟል

በሙስና፣ በመልካም አስተዳደርና በፍትሕ ዕጦት በሚታመሰው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፡- የቅ/ሥላሴ ኮሌጅ አስተዳደር ም/ዲን፣ ጎይቶኦም ያዩኑ፣ ለአ/አበባ ሥራ አስኪያጅነት ታስቧል በዓዲ ግራት እና በቅ/ጳውሎስ ኮሌጅ ሬጅስትራርነቱ ለተሐድሶ ኑፋቄ በመሥራት ይታወቃል የጠቅ/ቤተ ክህነቱ ትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ሓላፊ አባ ሰረቀም ከታሳቢዎቹ ይገኙበታል ም/ል ሥራ አስኪያጁ አእመረ፥“ምንም መሻሻል ስለማይታይ” በሚል በታኅሣሥ በፈቃዱ ለቋል ርቱዐ ሃይማኖትና ኹሉን አቀፍ የኾኑ፤ ተፈላጊው ዕውቀት እና ብቃት ያላቸው ጠፍተው ነውን? ፓትርያርኩ፥ በቅዱስ ሲኖዶስ በተተቹበትና በሕገ ቤተ ክርስቲያንም ጥያቄ በተነሣበት የልዩ ጽ/ቤታቸው ሚና እና አሠራር፡- የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሴ ሐረገ ወይን በልዩ ጸሐፊነት ታስበዋል ልዩ ጽ/ቤቱ፣ የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ዓለም አቀፋዊነት በጠበቀ ፕሮቶኮል ያልተደራጀ ነው መዋቅሩ፥ እንደ ሕጉ ሚናውን ጠብቆ የፓትርያርኩን ተግባራት ብቻ ማከናወን ይጠበቅበታል ንቡረ እድ ኤልያስ ከአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመቆራኘት ጭምር ሲመዘብሩበት ቆይተዋል ከየማነ ጋር፣ በጥቅምናፓትርያርኩ ላይ በሚያሳርፉት ተጽዕኖ ሚዛን ሲወዛገቡና ሲፎካከሩ ነበር
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ ኮሌጅ: መናፍቃንንና ምንደኞቻቸውን ማጥራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፤ የተባረረው ከፍ ያለው ቱፋ ከፍተኛ ውሳኔ እንዲተላለፍበት ተጠይቋል

የኮሌጁ አስተዳደር ጉባኤ ከማታ መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት ጋር ተወያይቷል የበላይ ሓላፊው ሊቀ ጳጳስ: በሃይማኖት ድርድርም ኾነ መሸማቀቅ የለም፤ ብለዋል ዘካርያስ ሐዲስ: ለተጠርጣሪዎች በሽምግልና ተልከዋል፤ መባሉን አስተባብለዋል መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን፣ የቤተ ክርስቲያናችን ነባር አስተምህሮ በዘመናዊ አቀራረብ የሚሰጥባቸው የወንጌላውያንና ዘመናውያን ምሁራን መፍለቂያ ምንጮች ናቸው፡፡ የአብነት ትምህርቱን ከዘመናዊው ጋር አዋሕደው በመሠልጠን ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ አገልግሎት የሚሰጡ ሊቃውንትንም እያፈሩ ቆይተዋል፡፡ የነበረውና ወደፊትም የሚኖረው የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮና ትውፊት ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ፤ የክርስቶስን ወንጌል ያልሰሙ እንዲሰሙ፣ የሰሙ በእምነታቸው ጸንተው የሃይማኖት ፍሬ እንዲያፈሩ፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ ወገኑን የሚወድ፣ ለሀገርና ለወገን ዕድገት የሚያስብ ለዚኽም የሚጥር ትውልድ የማፍራት ርእያቸውና ተልእኳቸው በስኬት ይቀጥል ዘንድ ግና አስተዳደራዊና አካዳሚያዊ ሥራዎቻቸው እንዲኹም የፋይናንስ አቅሞቻቸው ሊጎለብቱ ይገባል፡፡ ከዚኽ አኳያ፣ የኮሌጆቹን አስተዳደር ሞያዊነት ማጠናከር፤ የመምህራኑን ሃይማኖት ማረጋገጥና የማስተማር ክህሎታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ እንዲኹም የሥርዐተ ትምህርቱ አቀራረጽና የመማርያ መጻሕፍቱ ዝግጅት ተፈትሾ እንዲሠራባቸው ማድረግ፥ የትምህርቱን ጥራት በመጠበቅ በሃይማኖታቸው የጸኑ፣ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ያላቸው፣ በነገረ መለኰት በቂ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – የሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ ኮሌጅ: በኑፋቄ ተግባር ያገኘውን ደቀ መዝሙር አባረረ፤ የሦስት ተጨማሪ ደቀ መዛሙርት ጉዳይ እየታየ ነው

ውሳኔውን፥ በሽምግልና፣ በዛቻና በማስፈራራት ለመቀልበስ እየተሯሯጠ ነው የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፥ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣ ሥርዐትና ትውፊት ውጭ ኑፋቄን ሲያስፋፋና ሲተገብር በተጨባጭ አግኝቸዋለኹ፤ ያለውን አንድ ደቀ መዝሙር ከኮሌጁ ማሰናበቱ ተገለጸ፡፡ ከፍ ያለው ቱፋ የተባለው ግለሰብ፣ በቀን ተመላላሽ የሦስተኛ ዓመት ሰሚነሪ ደቀ መዝሙር ሲኾን፤ በኮሌጁ ውስጥ በኅቡእ ኑፋቄን ሲያስፋፋና በቅጥረኛነትም ከኮሌጁ ወደ መናፍቃን ጎራ አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን እየመለመለ ሲቀሥጥና ሲያስኮበልል መቆየቱ ተጠቅሷል፡፡ በኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሚመራ፥ የአስተዳደር፣ የመምህራንና የደቀ መዛሙርት መማክርት ጉባኤ÷ መጋቢት 16 ቀን ባካሔደው ስብሰባ፣ የመናፍቃን ቅጥረኛ ኾኖ በሚንቀሳቀሰው ደቀ መዝሙር ላይ ሲሰበሰቡ የቆዩ የድምፅ እና የመተማመኛ ማስረጃዎችን ከመረመረና ደቀ መዝሙሩንም አቅርቦ ከጠየቀ በኋላ ከኮሌጁ ጨርሶ እንዲሰናበት ልዩነት በሌለው ድምፅ መወሰኑ ታውቋል- “ከመጋቢት 19 ቀን ጀምሮ በኮሌጁ እስከ መጨረሻው እንዳይማሩ ተሰናብተዋል” ይላል፤ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከአስተዳደር ምክትል ዲኑ ቢሮ የወጣው ደብዳቤ፡፡ ተሰናባቹ ከፍ ያለው ቱፋ፣ የደቀ መዝሙርነት መታወቂያውን ለኮሌጁ ሬጅስትራር ክፍል
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርኩ: የማነ ዘመንፈስ ቅዱስን “ቀንደኛ ሌባ” አሉት፤ አማሳኝ አጋሮቹ “አእምሯቸውን እናስተካክላለን” በሚል ምዝበራውን ለማስተባበል ደጅ እየጠኑለት ነው

በሕመምተኛ ልጁ ሕክምና ስም በርካታ አጥቢያዎች በ፻ሺሕዎች እያወጡ በሰጡበት ኹኔታ፥ “እኔ ሳላውቅ ስሜን ለማስጠፋት የተሠራ ነው” በሚል ምዝበራውን ለማስተባበል እየጣረ ነው ግማሽ ሚሊዮን ብር እንዲሰጠው የተወሰነበት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት አስተዳደር ኮሚቴ ውሳኔ ቃለ ጉባኤ፣ በአስተዳደራዊ ውሳኔ ተሽሮ ውሳኔውን በሚያስተባብል ሌላ ቃለ ጉባኤው እንዲቀየር ሓላፊዎቹን አስገድዶ ነበር “ድጋፉን የሰጠነው ተዋቅሮ በተላከ ኮሚቴ በተጠየቅነው መሠረት ነው፤” ያሉት ዐሥር የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ አባላት ትእዛዙን ባለመቀበላቸው በየማነ ከሥራና ከደመወዝ ታግደው ነበር የእገዳ ርምጃውንና አጠቃላይ ኹኔታውን ከገዳሙ ሓላፊዎች ያዳመጡት ፓትርያርኩ፥ “እርሱ ቀንደኛ ሌባ ነው፤ እናንተም ሌቦች ናችኹ” ሲሉ ገሥጸው ጉዳዩ በአስቸኳይ እንዲጣራ አዘዋል በሥራ አስኪያጅነት ሥልጣኑ አጥቢያዎችን በማስፈራራት ከብር 3 ሚሊዮን በላይ የሰበሰቡለት አማሳኝ አጋሮቹ፥ “እርሱ አያውቅም፤ ከግል ገንዘባችን ነው የረዳነው” በሚል ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳንና ምዝበራውን ለማስተባበል ልዩ ጽ/ቤታቸውን ደጅ እየጠኑለት ነው “እገሌንና የእገሌን ልጅ አሳክመናል፤ ከኪሳችን እንጂ ከሙዳየ ምጽዋት አልነካንም፤” የሚሉት አማሳኞቹ፥ “የቅዱስነታቸውን አእምሮ እንቀይራለን” በሚል ጉዳዩን ለማዳፈን ይንቀሳቀሳሉ *               *               * (አዲስ አድማስ፤
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ማኅበረ ቅዱሳን: ዐውደ ርእዩ የታገደው በመንግሥት አካላት መመሪያ መኾኑን ገለጸ፤ ፓትርያርኩ እንዳሉበት “በኦፊሴል የምናውቀው ነገር የለም”ብሏል

ተለዋጭ ጊዜና ቦታው፥ የመመሪያውን መነሻና አግባብነት በማጣራት እንደሚወሰን ተገልጧል ብዙ የተደከመበት እና አያሌ ለውጥ የሚያመጣ ዝግጅት ሲታገድ ስሜቱና ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ያለአሠራሩ ለመሰረዝ የተገደዱት የማዕከሉ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ትብብር፣ “ቀና ነበር” ብሏል በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዳይካሔድ በመከልከሉ ታላቅና ተገቢ ዓላማው አይከሽፍም፤ በፍጹም! አስፈላጊው ጥረት ከተደረገ በኋላ ተወስኖ መታየት ይኖርበታል ብሎ የማኅበሩ አመራር ያምናል ማኅበሩ፥ ዓላማውን ለምእመኑ ለማድረስ የሚያስበው በተገቢ፣ ትክክለኛና ሰላማዊ መንገድ ነው *                     *                    * የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ፤ አቶ ተስፋዬ ቢኾነኝ ማኅበረ ቅዱሳን፣ ከመጋቢት ፲፭ እስከ ፳፩ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.፣ “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን: አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል መሪ ቃል በኤግዚቢሽን ማዕከል ለማካሔድ ዐቅዶ ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀበት ዐውደ ርእይ ለጉብኝት ክፍት የሚኾንበት የመጨረሻ ሰዓት ሲዳረስ በእንግዳ አሠራር ተደናቅፏል፡፡ “ቤተ ክርስቲያንን በሰፊው የሚያስተዋውቅና ከምእመኑ የሚጠበቀውን ድርሻ በአግባቡ የሚያሳይ ዐውደ ርእይ አዘጋጅተን በምናቀርብበት ሰዓት መከልከላችን ከፍተኛ ስሜት የሚፈጥር ነው፤” ብለዋል የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ ተስፋዬ ቢኾነኝ – ትላንት ማምሻውን በማኅበሩ የዋናው
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ዐውደ ርእዩ በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዳይካሔድ የተከለከለው በመንግሥት ትእዛዝ ነው፤ “ላልተሟሉት ቅድመ ኹኔቻዎች” ማዕከሉ ሓላፊነቱን ወስዷል

ፈቃዱን ለመስጠት ይመለከተዋል የተባለው የአዲስ አበባ አስተዳደር፣ “ለዐውደ ርእይ ፈቃድ የመስጠት አሠራር የለኝም፤ በእንግዳ ሕግ ፈቃድ ለመስጠት አልችልም፤” ብሏል፡፡  “ዝግጅቱን ለማካሔድ የሚያስፈልጉ ቅድመ ኹኔታዎችን በተሟላ መልኩ ኤግዚቢሽን ማዕከሉ ለአዘጋጆች ባለመግለጹና እንዲያሟሉ ባለማስቻሉ ዝግጅቱ በተያዘለት ፕሮግራም ሊካሔድ አልቻለም፡፡”/ማዕከሉ/ በተፈጠረው ክፍተት ላይ ከማኅበሩ ጋር ተከታታይና ሰላማዊ ውይይት ማድረጉን የገለጸው ማዕከሉ፥ “ለማኅበረ ቅዱሳን፣ ለተሳታፊዎችና ለተመልካቾች ከፍተኛ ይቅርታ ይጠይቃል፤” በማለት የይቅርታ መልእክቱን በተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች እያስተላለፈ ነው፡፡ የማኅበሩ ጽ/ቤት፣ የዐውደ ርእዩን ተለዋጭ ቦታ እና ጊዜ ገና አልወሰነም፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫው፣ በዋናው ማእከል ጽ/ቤት በዋና ጸሐፊው እየተሰጠ ነው፡፡  
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የማኅበረ ቅዱሳን ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ ቅድመ ዝግጅት ሒደት እውነታዎችና ቀጣይ ወቅታዊ ጥረቶች

በታቀደው መርሐ ግብር የማካሔድ ጥረቱ ዛሬም ተጠናክሮ ይውላል ዛሬ ከቀኑ 10፡00 በዋናው ማእከል ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል የዝግጅቱ ቀጣይነት፣ ጊዜና ቦታ የሚታወቀው በሚሰጠው መግለጫ ነው ጳጉሜን 5 ቀን 2007 ዓ.ም. – የማኅበሩ የሥራ አመራር ጉባኤ ጽ/ቤት፣ ማኅበሩ በአራት ዓመት ስትራተጅያዊ ዕቅዱ ያካተተውን የዐውደ ርእይ ልዩ ዝግጅት ለሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማሳሰቡን በመጥቀስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እንዲጻፍለት ጠየቀ፤ ጳጉሜ 5 ቀን 2007 ዓ.ም. – የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ የዝግጅቱን መካሔድ ፈቅዶ፥ “ከዚኽ በፊት እንደተለመደው ኹሉ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግ” በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም በመጠየቅ ለኤግዚቢሽን ማዕከል እና የገበያ ልማት ድርጅት የድጋፍ ደብዳቤ ጻፈ፤ መስከረም 03 ቀን 2008 ዓ.ም. – የማኅበሩ ጽ/ቤት በዋና ጸሐፊው፣ የኤግዚቢሽን ማዕከሉ ደግሞ በዋና ሥራ አስኪያጁ አማካይነት በስድስት አንቀጾች የተዘረዘረ የአገልግሎት ውል በመፈራረም የጠቅላላ ዋጋውን 35 በመቶ ብር 200 ሺሕ ቅድመ ክፍያ ፈጸመ፤ ጥቅምት ወር 2008 ዓ.ም.፡- የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ ዝግጅት ዐቢይ ኮሚቴ፣ በማኅበሩ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ መክፈቻ ጊዜ ባልተለመደ ሕገ ወጥ አሠራር እክል ገጠመው፤ መርሐ ግብሩን በዕቅዱ ለማስቀጠል ጥረቱ ቀጥሏል

ኤግዚቢሽን ማዕከሉ፣ ማኅበሩ ከአዲስ አበባ አስተዳደር የፈቃድ ደብዳቤ እንዲያጽፍ ጠይቋል በማዕከሉ ኤግዚቢሽን የሚያዘጋጁ አካላት፥ ፈቃድ የሚያቀርቡት ዕውቅና ካገኙበት ተቋም ነው ማኅበሩ ከማዕከሉ ጋር የፈጸመው ውል በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ደብዳቤ የተደገፈ ነው ያለሰዓቱ የተጠየቀው ፈቃድ፥ በማዕከሉ አሠራር ያልተለመደና በአ/አ አስተዳደርም የሕግ ማህቀፍ የሌለው ነው የማኅበሩ አመራር፣ ዐውደ ርእዩን በታቀደለት መርሐ ግብር ለማስቀጠል ጥረቱን ቀጥሏል፡፡ *          *          * ማኅበሩ ባለፈው ዓመት ጳጉሜን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተጻፈለት የድጋፍ ደብዳቤ፤ ማኅበሩ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ በተጻፈለት የትብብር ደብዳቤ መሠረት በመስከረም ወር መጀመሪያ ከኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ጋር የፈጸመው ውል፤
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሤራና አቀንቃኞቹ የተጋለጡበት የድል ጉባኤ ‐ በዲላ

በዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና ዳማ ቅዱስ ጊዮርጊስ አድባራት ሰበካ ጉባኤና በማኅበረ ቅዱሳን የዲላ ወረዳ ማዕከል በመተባበር የተዘጋጀው መንፈሳዊ ጉባኤ ከመጋቢት 2 እስከ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ለአራት ተከታታይ ቀናት ተካሒዷል፡፡ ጉባኤው የተደረገው፥ የሲዳማ፣ ጌዴኦ፣ አማሮና ቡርጂ ዞኖች ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሰበካ ጉባኤውና በወረዳ ማዕከሉ በጋራ ለቀረበለት ጥያቄ፣ የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በቁጥር 9130/6/1/2008 በተጻፈ ደብዳቤ ፈቃድ በመስጠቱ ነው፡፡ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን በማጋለጥ ሤራው በቂ ግንዛቤ ተይዞበት፤ ምእመኑና አገልጋዩ ከኑፋቄው ተጽዕኖዎች ተጠብቆ ሥርዐተ አምልኮውንና አገልግሎቱን በቀናች እምነትና ሥርዓት እንዲፈጽም ማብቃት፤ ከጉባኤው ዐበይት ዓላማዎች አንዱ ነበር፡፡ በአራቱ ቀናት በጉባኤው ያገለገሉት ሰባክያነ ወንጌል፣ መምህራኑ፥ ዲ/ን ኢንጅነር ስንታየሁ ጅሶ፣ ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ እና ዲ/ን ታደሰ ወርቁ ሲኾኑ ዘማርያኑም፥ በኵረ ዘማርያን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ፣ ዘማሪት መሠረት ማሞ እና ዘማሪት ወርቅነሽ ተፈራ ናቸው፡፡ በጉባኤው ከዲላና አካባቢው የመጡ ከዐሥራ አምስት ሺሕ በላይ ምእመናን የተገኙ ሲኾን፥ ከወትሮ በተለየ ማኅበረ ካህናቱ ማስታዎሻ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ባልታወቁ ታጣቂዎች የዘረፋ ስጋት ውስጥ ወድቋል

በአመክሮ ላይ ካሉ ጥቁር ራሶች ጋር ውዝግብ በመፍጠር ደብድበዋቸዋል የደሴቶቹና የአካባቢው ኅብረተሰብ ኹኔታውን በንቃት እየተከታተሉ ናቸው የ740 ዓመት ገዳሙ፣ የበርካታ ጥንታውያን ብራናዎችና ቅርሶች ማዕከል ነው በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት በጣና ሐይቅ ውስጥ ከሚገኙ የደሴት ገዳማት አንዱ የኾነው ጥንታዊው የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም፣ ካለፈው ሳምንት ኀሙስ ጀምሮ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች የዘረፋ ስጋት ተደቅኖበት እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ ምንጮች እንደገለጹት፣ ባለፈው ኃሙስ ምሽት ግለሰቦቹ በሦስት ጀልባዎች ከፎገራ አቅጣጫ በመምጣት ወደ ገዳሙ የደሴት ክልል ተጠግተው ያደሩ ሲኾን፤ ትላንት፣ መጋቢት 12 ቀን ምሽት 2 ሰዓት ላይ ደግሞ ጀልባዎቹ በቁጥር ጨምረውና ግለሰቦቹም በትጥቅ ተደግፈው መምጣታቸው ስጋቱን ከፍ አድርጎታል፡፡ ኀሙስ ምሽት የመጡት ጀልባዎች ዓርብ ጠዋት ስፍራውን ለቀው ቢሔዱም ትላንት ምሽት ከተመሳሳይ አቅጣጫ በስምንት ጀልባዎች ተጓጉዘው የመጡት የታጠቁ ግለሰቦች በገዳሙ አቅራቢያ ማደራቸው በምንጮቹ ተጠቅሷል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ዛሬ ጠዋት ድረስም፣ ከስምንቱ ጀልባዎች አምስቱ ከነታጣቂዎቹ በስፍራው እንዳሉ ተገልጧል፡፡ አመጣጣቸው ዓሣ ለማስገር እንደኾነ በመግለጽ ኃሙስ ሌሊቱን ከገዳሙ አበምኔትና ከማኅበረ መነኰሳቱ ጋር ፍጥጫ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ: በሕመምተኛ ልጁ ሕክምና ስም የሚያካሒደው የገንዘብ ምዝበራ ተጋለጠ፤ ከየአጥቢያው ከብር 3 ሚሊዮን ያላነሰ መሰብሰቡ ተጠቁሟል

ከእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ብቻ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንዲሰጠው ተወስኗል ክፍያውን አልፈጽምም ያሉት የገዳሙ ሒሳብ ሹም ከሥራ እና ከደመወዝ ታግደዋል የሒሳብ ሹሟን ተቃውሞ ተከትሎ የመዘበረውን ክዶ በግለሰቦች ለማላከክ እየሠራ ነው አማሳኞቹ ኃይሌ፣ ዘካርያስ፣ ነአኵቶና 16 የአጥቢያ ሓላፊዎች በኮሚቴነት ያሰባስባሉ (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፵፰፤ መጋቢት ፲ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ “ለታማሚ ልጃቸው ማሳከሚያ” በሚል እጅግ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ እንዳሉ የጠቆሙት ምንጮቻችን፤ ከእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ብቻ፣ ግማሽ ሚሊዮን ብር ወጪ ኾኖ እንዲሰጥ በአስተዳደር ኮሚቴው መወሰኑን የተቃወሙት የገዳሙ ሒሳብ ሹም ከሥራ እና ከደመወዝ መታገዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ሥራ አስኪያጁ፣ ሕመምተኛ ልጃቸውን በውጭ ሀገር ለማሳከም ይችሉ ዘንድ፣ ከሀገረ ስብከቱ የገዳማትና የአድባራት ሓላፊዎች ተውጣጥተው በየክፍላተ ከተማው በተዋቀሩ ኮሚቴዎች ቢያንስ ከሦስት ሚሊዮን ብር ያላነሰ መሰብሰቡን የጠቀሱት ምንጮች፤ የገንዘብ ርዳታውን አገልጋዮች በየግላቸው በበጎ ፈቃድ እንዲያበረክቱ ከመጠየቅ ይልቅ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅ/ሲኖዶስ: በመላው ገዳማት፣ አድባራትና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ዐወጀ፤“ባሳለፍናቸው ሳምንታት ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችን በመሪር ሐዘንና በጸሎት እናስባቸዋለን”

የካቲት ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ ኅሡ ሰላማ ለብሔር እስመ በሰላመ ዚአሃ ይከውን ሰላምክሙ፤ (የአገርን ሰላም እሹ ፈልጉ የአገራችኹ ሰላም የእናንተ ሰላም ነውና)  የተወደዳችኹ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤ የሀገርና የወገን ፍቅር ያለው ሕዝብ፥ ሰላም ከእግዚአብሔር መኾኑን ያውቃል፤ ሰላም ለሰው ልጆች ከማናቸውም መሠረታውያን ፍላጎቶች በላይ ተቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ተቻችለውና ተረዳድተው የሚኖሩባት የዓለም ምሳሌ ናት፡፡ ይህን ዓለምን የሚያስደንቅ ገጽታችንን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዲከተለው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ የተወደዳችኹ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያት፤ ኢትዮጵያ አህጉረ ሰላም(የሰላም አገሮች) ከሚባሉት ከዓለም አገሮች አንዷ ስትኾን በአኹኑ ጊዜ በአንዳንድ ክልሎችና ከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ኹሉንም የሚያሳሳብ ኾኖ አግኝተነዋል፡፡ ከዚኽም ጋር ባለፍናቸው ሳምንታት በተከሠተው ያልተጠበቀ ችግር፡- በአንዳንድ አካባቢ የሰው ሕይወት ሲጠፋ፤ ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ፤ የንግድ ተቋማት፣ የሕዝብና የመንግሥት ንብረት ሲወድም፤ የሕዝባችን የዕለት ከዕለት ኑሮ ሲናጋ ኹሉም ኅብረተሰብ የችግሩ ተጠቂ ኾኗል፤ የዚኽ ዓይነቱ ድርጊት በዚኽ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ብፁዕ አቡነ ያሬድ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተመደቡ

ብፁዕ አቡነ ያሬድ፤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊና የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ባለፈው ሳምንት ሰኞ በሞተ ዕረፍት በተለዩት የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ምትክ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ደርበው እንዲሠሩ መደባቸው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ብፁዕነታቸውን የመደባቸው፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ የጀመረውን ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በመፈራረምና በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ በማውጣት ባጠቃለለበት ውሎው ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ያሬድ በአኹኑ ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊና የሶማል/ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በሀገረ ስብከቱ በሰሞኑ ግጭት የቃጠሎ ጉዳት ስለደረሰባቸው አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ የተወያየው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱና ከሀገረ ስብከቱ በተውጣጣ ልኡክ ተጨማሪ ማጣራት እንዲካሔድና አስፈላጊው የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ እንዲደረግ በመወሰን ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ የብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሥርዐተ ቀብር በአሰላ ደብር ቅዱስ ደብረ መዓዛ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ባለፈው ኃሙስ በተከናወነበት ወቅት፤ የልዩ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ቅዱስ ሲኖዶስ: ፓትርያርኩ ሕግ አክብረውና መዋቅር ጠብቀው እንዲሠሩ አስጠነቀቃቸው፤ በሰላም ጉዳዮች ዛሬ መግለጫ ያወጣል

በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያስተላለፏቸው መመሪያዎችና የጠሯቸው ስብሰባዎች ሕገ ወጥ ተብለዋል ቋሚ ሲኖዶስ፥ የስምዐ ጽድቅን የፀረ ተሐድሶ ጽሑፍ ጨምሮ የተደረጉ መጻጻፎችን ይመረምራል የፓትርያርኩ ጉዞዎች፥ ስፖንሰር ተገኘ በሚል ሳይኾን በቋሚ ሲኖዶሱ ማስወሰን ይኖርባቸዋል ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ መዋቅር ጠብቀው በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑና ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ በቅዱስ ሲኖዶስ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ ከቀትር በኋላ ባካሔደው ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ጽሑፎች ላይ ቀርበዋል ለተባሉ አቤቱታዎች የነበራቸውን አያያዝ፣ የወሰዷቸውን አቋሞችና የሰጧቸውን ምላሾች ገምግሟል፡፡ ፓትርያርኩ አቤቱታዎቹን ለመመልከት በሚል በራሳቸው የጠሯቸው የኮሌጆችና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ መምሪያዎች ሓላፊዎች ስብሰባዎች፤ ማእከላዊ አሠራርን ያልጠበቁና አድሏዊ እንደነበሩ ጉባኤው ተችቷል፡፡ ከዚኽም ጋር በተያያዘ ፓትርያርኩ፣ ከልዩ ጽ/ቤታቸው በተጻፉ ደብዳቤዎች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያስተላለፏቸው የክሥና የቅስቀሳ መመሪያዎች የቅዱስ ሲኖዶስን የምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መንፈስ የሚፃረሩና ሕገ ወጥ መኾናቸውን ያረጋገጠ ሲኾን በስብሰባዎቹ ወጥተዋል የተባሉ የአቋም መግለጫዎችም ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ተገልጧል፡፡ ፓትርያርኩ ዛሬ ለተጀመረው ዐቢይ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ቅዱስ ሲኖዶስ ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ ተቀመጠ፤ ማዕከላዊነትን ስላልጠበቁ አሠራሮችና ወቅታዊ ጉዳዮች ይወያያል

ድንገተኛ ልዩ ስብሰባው የተጠራው በቋሚ ሲኖዶሱ ነው በፓትርያርኩና በማኅበረ ቅዱሳን ውዝግብ ላይ ይወያያል በዐቢይ ጾም የጸሎተ ምሕላ ጉዳይም ውሳኔ ያሳልፋል ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ዛሬ የካቲት ፳፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ጀምሮ ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ መቀመጡ ተገለጸ፡፡ ድንገተኛ ልዩ ስብሰባውን የሚያካሒዱት፣ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሞተ ዕረፍትና ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሢመት በመዲናይቱ አዲስ አበባ የተሰበሰቡ ከ25 ያላነሱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ናቸው፡፡ ስብሰባው እንደሚካሔድ የታወቀው፣ ፓትርያርኩ በመጪው ሰኞ የሚጀመረውን ዐቢይ ጾም በማስመልከት ዛሬ ረፋድ ላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ በተገኙበት በቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው እንዳበቁ ሲኾን አስቀድሞ መረጃው እንዳልነበራቸው ተገልጧል፡፡ ፓትርያርኩ መግለጫውን በንባብ ካሰሙ በኋላ ከአዳራሹ ለመውጣት ተነሥተው እንደቆሙ፤ በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጥያቄ ተመልሰው እንዲመቀጡ መደረጉን የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ፓትርያርኩ ተመልሰው እንደተቀመጡ፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቡነ ማቴዎስ፣ ማእከላዊ አሠራርን ባለመጠበቅ እየተከሠቱ ስለሚገኙና እልባት ለመስጠት ስላዳገቱ ችግሮች በስፋት አስረድተዋል፡፡ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በበላይነት የሚመራው
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – መፍቀሬ ኢትዮጵያ ወገባሬ ሠናይ: የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐረፉ

ሥርዓተ ቀብራቸው ከነገ በስቲያ በአሰላ ደብር ቅዱስ ደብረ መዓዛ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ይፈጸማል በታኅሣሥ 1966 ዓ.ም. በንጉሠ ነገሥቱ ትእዛዝ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቻንስለር ኾነው ተሹመው ነበር ከአምስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ዕረፍት በኋላ ለስድስት ወራት በዐቃቤ መንበርነት አገልግለዋል *               *               * “በሔዱበት ኹሉ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖታቸውን ይጠብቃሉ፡፡ የሚኖሩት ግን ተዋርደው ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት እያሳፈረን ነው፡፡ በእውነት አባትህን ጠይቅ ይነግርሃል፤ ነው፡፡ አፍሪካውያን በሙሉ በቅኝ ግዛት ሲገዙ ኢትዮጵያውያን ለቅኝ ገዥዎች እጃቸውን ያልሰጡት በምን ምክንያት ነው ብለው የዛሬ ክርስቲያኖች በሙሉ ማጥናት አለባቸው፡፡” /ብፁዕ አቡነ ናትናኤል/ *               *               * ነገ ቤተ ክርስቲያን ይከፍታልብሎ ያሳደገኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፤ የአቅሜን ያኽል ተምሬአለኹ፤ ቤተ ክርስቲያን አሳድጋኛለች፤ ባለውለታዬ ነች፤ ውለታዋን አኹንም አልከፈልኩም፤ እስከሞት ቢኾን ውለታዋን ተሸክሜ ወደ መቃብር ከመግባት በስተቀር ውለታዋን አልከፈልኩም፤ ይኼን የምናገረው ከልቤ ነው፤ ኹሉም ውለታ አለበት፤ የቤተ ክርስቲያኑን ውለታ መመለስ አለበት(ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፤ ፲፱፻፳፫ – ፳፻፰ ዓ.ም) “ነቢዩ ኤርሚያስ፥ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን አይለቅም፤ ይላል፤ ይህ ሊጠና ይገባል፡፡ እንባችንን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትርያርኩ መምሪያ ምላሽ ሰጠ፤ የስምዐ ጽድቅ ጽሑፍ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ የማሳወቅ ግዴታችን አካል ነው፤ ደብዳቤውም መድረክ ስለተነፈገንና ፍትሕ ስለተጓደለብን ነው

የጋዜጣው ጽሑፎች፣ «መንፈሳዊ ኮሌጆቹ በአጠቃላይ የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው» አይሉም በጋዜጣው አጻጻፍ አንዳንድ የቃላት አጠቃቀሞች ላይ ቅሬታ ካለ ለመወያየት ዝግጁዎች ነን ጉዳዮቹን እንድናስረዳና የተፈጠረውንም ችግር ለመረዳት የውይይት መድረክ ይዘጋጅልን በተለያየ መንገድ እንደጠየቅነው፣ በአካል የመወያያ ዕድል ማጣታችን በእጅጉ ያሳዝነናል  ለሚታረም ነገር እርምት መውሰድና ስናጠፋም ይቅርታ መጠየቅ የአገልግሎታችን መርሕ ነው *           *          * ሰዎች እንደመኾናችንና ልንሳሳት ስለምንችል፣ በማንኛውም ደረጃ ተወያይተን የሚታረም ነገር ካለ አስፈላጊውን እርምት መውሰድ እና በትክክል ጥፋት እንዳጠፋንም ስንረዳ ይቅርታ መጠየቅ አንዱና ዋነኛው የአገልግሎታችን መርሕ ነው፡፡ በሀገራችን የተከሠቱትን ማኅበራዊ ችግሮች ለመፍታት ኹሉም አካል በየዘርፉ በሚረባረብበት በዚኽ ወቅት፣ ትልቅ ሓላፊነት ያለባት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባትና ልጆች እንዲህ ዓይነት ደብዳቤዎችን በመጻጻፍ መጠመዳችን በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡ ሕግ አውጥቶ፣ ሥርዓት ሠርቶ የሰጠን የቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በማኅበሩ አገልግሎቶች ላይ አኹንም እየተፈጠሩ ያሉት ዕንቅፋቶች እንዲታዩልንና አስፈላጊው እርምት እንዲደረግልን በታላቅ ትሕትናና አክብሮት እንጠይቃለን፡፡ (የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከዚኽ በታች ይመልከቱ)  
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአ/አበባ ሀ/ስብከት አስተዳደር: የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ስለምን ውኃ በላው?

የመሬትና የገቢ ማስገኛ ተቋማት ኪራይ ውሳኔው አልተተገበረም፤ የጥናቱም ሒደት ታጉሏል የቤተ ክርስቲያንን መብትና ጥቅም የማያስከብሩ ውሎች በወጥነት መስተካከል ነበረባቸው በጥናቱ የታዩ ጥፋቶች እንዲቀጥሉና አድባራቱ ተገቢ ጥቅማቸውን እንዲያጡ አድርጓቸዋል በፍጻሜው፥ ቤተ ክርስቲያን የመሬትና የሕንፃ ኪራይ ፖሊሲ እንዲኖራት አስተዋፅኦ ነበረው *          *          * የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ውሳኔውን ወደ አጥቢያዎቹ ባለማስተላለፉ ለውጤታማነቱ ተግዳሮት ኾኗል፡፡ ይህም ለቀጣዩ ጥናት ዕንቅፋት በመኾኑ ሒደቱ እንዲስተጓጎል አድርጎታል፡፡ የሕግ አውጭና የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ የኾነውን የበላይ አካል ውሳኔ አለማክበርና አለማስከበር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ያለን ንቀት ከሚያመለክት በቀር ሌላ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም፡፡ ብዙ የተደከመበት እና የውጤት ጭላንጭል የታየበት ጥናት በከንቱ እንዳይቀር፣ የሚመለከተው አካል በትኩረት ሊከታተለው ይገባል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የመሪነት ሚናውን በማስከበር ለቤተ ክርስቲያን ይበጃል ብሎ የወሰነው ውሳኔ ተግባራዊ እንዲኾን ሓላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል፡፡ /የአጥኚ ኮሚቴው ጸሐፊ ለዜና ቤተ ክርስቲያን ከጻፉት/ *          *          * ዜና ቤተ ክርስቲያን በዚኽ ወር እትሙ በርእሰ አንቀጽ ደረጃ እንደነገረን፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፥ ሙስናን አዳክመናል፤ መልካም አስተዳደርን አስፍነናል በሚል
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እየተደረገ ያለው ድራማዊ መሸላለም፥ “ወይኖ አረሰው ወይኖ ጎረሰው” ዓይነት ነገር ነው/ዜና ቤተ ክርስቲያን/

የማነ ዘመንፈስ ቅዱስና መሰሎቹ በወርቅ ሐብላት እና ብራስሌት ‘ሽልማቶች’ም ይበዘብዛሉ ፐርሰንት አስከፍያለሁ ብሎ በ5 ወራት ብቻ የእጅ ሰዓት፣ የወርቅ ሐብላትና ብራስሌት ሰብስቧል ከየአጥቢያው በኃይልና በግድ ፻ሺሕዎች ለሽልማት እየተሰበሰበ እርስበርሳቸው ይሞጋገሱበታል ከንፋስ ስልክ ላፍቶ አጥቢያዎች ብቻ ከብር 300ሺሕ በላይ ተሰብስቦ ወርቃወርቅ ተሸላልመዋል “ራስን ለማጋነኛና ቦታ ለማግኛ የሚካሔዱ መደለያዎች ናቸው፤ ችግሩ በመሸላለም አይፈታም” /ታዛቢ የክፍላተ ከተማ ሓላፊዎችና ሠራተኞች/ *           *          * ከምስክር ወረቀት ባለፈ ወርቃወርቅ እና ቁሳቁስ መሸላለሙ ወደ ሙስና ሊመራ ይችላል በድርቅ ለተጐዱት ርዳታ በማሰባሰብ ላይ እያለን በየምክንያቱ መሸላለም ከትዝብት ይጥላል ገባእተ ነግሁ ብዙ ሠርተው ቤተ ክርስቲያንን ለገባኡተ ሠርኩ ያስረከቧት ያለመሸላለም ነው “የሚገባችኹን ሠርታችኹ የሚገባንን እንጂ ከሚገባን በላይ አልሠራንም በሉ” ተብለን ታዘናል /ዜና ቤተ ክርስቲያን፤ ጥር እና የካቲት ፳፻፰ ዓ.ም./ *           *          * … ዜና ቤተ ክርስቲያን ለሀገረ ስብከቱ የሚያሳስበው ዐቢይ ጉዳይ ቢኖር፣ ሀገረ ስብከቱ መኪናዎችን ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የድካማቸውን ዋጋ በማሰብ በጉዳይ አስፈጻሚነት የመደባቸውን የራሱን ሠራተኞች እንደ ውጭ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርኩ:ደንባዊ ህልውናውን የካዱት ማኅበረ ቅዱሳን፣ በስምዐ ጽድቅ ላወጣው የፀረ ተሐድሶ ኑፋቄ ጽሑፍና በደብዳቤ ለሰጣቸው ምላሽ በአምስት ቀናት ውስጥ ይቅርታ እንዲጠይቅ መመሪያ ሰጡ

ማኅበሩ መመሪያውን በግልጽ ተቀብሎ በደብዳቤ ይቅርታ ካልጠየቀና ይህንኑም በኹሉም ሚዲያዎቹ ካልገለጸ፥ “የማስተካከያ ሥራ ለመሥራት የምንገደድ መኾኑን በጥብቅ እናስታውቃለን፤” ብለዋል “የማስተካከያ ሥራ” ያሉት፥ የማኅበሩን የኅትመት ሚዲያዎች ማገድ፤ በኮሌጆቹ የስም ማጥፋት ወንጀል ክሥ እንዲመሠረትበት ማድረግና ሌሎችንም አስተዳደራዊ ጫናዎችንና ማነቆዎችን እንደሚጨምር ተጠቁሟል በመመሪያዎቻቸው፣ “ማኅበረ ቅዱሳን የተባለ ማኅበር” እያሉ በመጥራት፤ የመተዳደርያ ደንብ እንዳይኖረው አድርገው በአየር ላይ እንዳስቀሩት በመግለጽ ደንባዊ ህልውናውን ክደዋል፤ በቅዱስ ሲኖዶስ በሙሉ ድምፅ በጸደቀው መተዳደርያ ደንቡ መሠረት ክፍሎችን አዋቅሮ የሚፈጽመው አገልግሎት፣ የብዝበዛና ቤተ ክርስቲያን የማታውቀው እንደኾነ ገልጸዋል *                *               * መመሪያው፥ ፓትርያርኩ፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ እና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲኹም በቋሚ ሲኖዶሱ፣ ማዕርገ ክብራቸውንና ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲሠሩ የተሰጣቸውን ምክር እና አስተያየት ባለመቀበል ያለመዋቅር በተጽዕኖ በጠሩት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ስብሰባ ተጠቅመው ያስተላለፉት ነው፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በቃለ ዐዋዲው ድንጋጌዎች፣ ፓትርያርኩ የሚሰበስቧቸውና በርእሰ መንበርነት የሚመሯቸው ስብሰባዎች፥ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ቋሚ ሲኖዶስና የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከአማሳኙ አለቃ ተማክሮ ያሳሰራቸው የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ምእመናን በዋስ ተፈቱ፤ሌሎች ሰባት ምእመናንንም ለማሳሰር ዶልተው ነበር

ለኹለት ቀናት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በእስር ቆይተው ዛሬ ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት ቀርበው ማምሻውን በአራት ሺሕ እና በኹለት ሺሕ ብር ዋስትና የተፈቱት፥ በአማሳኙ አለቃ አላግባብ የታገደው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር፣ የክፍለ ከተማው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትና የደብሩ ሰንበት ት/ቤት አመራሮችና አባላት በቀጥታ ወደ አጥቢያቸው በማምራት በጸሎትና በመዝሙር ምስጋና አቅርበዋል፤ አቀባበል ያደረጉላቸውም ምእመናን፥ “ጀግኖቻችን ናችሁ፤ አርኣያ ኹናችሁናል፤ ከምንጊዜውም በበለጠ ተባብረን ቤተ ክርስቲያናችንን ከሙሰኞች እናጸዳለን፤” ሲሉ አጋርነታቸውንና ለቀጣዩ ተጋድሎም ዝግጁነታቸውን አረጋግጠውላቸዋል፡፡ “ሕገ መንግሥቱን ተላልፈው ሕገ ወጥ ደብዳቤ አሠራጭተዋል” ያለው ፖሊስ “ሌሎች የምንይዛቸው አሉ” በሚል የ20 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸው ነበር፤ “አያሰጥም”/ፍርድ ቤቱ/ በማስፈራሪያዎች ያልተበገሩ በርካታ ምእመናን፣ በክፍለ ከተማው እና በችሎት ተገኝተው ድጋፋቸውን አሳይተዋል፤ “አርኣያ ኾናችኁናል፤ ደብራችንን ከሙሰኞች እናጸዳለን!” የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፥ የቀሩት አስተባባሪዎች ካልታሰሩ ወደ ደብሩ መመለስ አልችልም፤ ያሉት አለቃ የጠቆሟቸውን ሰባት የሰንበት ት/ቤቱን አመራሮችና አባላት ዛሬ ለማሳሰር ባለፈው እሑድ ቃል ገብቶላቸው ነበር፤
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጥያቄ:የደ/ሲና እግዚአብሔር አብ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበርን ጨምሮ ከ14 በላይ የሰንበት ት/ቤቱ አባላትና ምእመናን ታሰሩ፤“ሀገረ ስብከቱና ፖሊስ ለአማሳኙ አለቃ በማድላት በደል እየፈጸሙብን ነው”/ምእመናኑ/

የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ: ሕገ ቤተ ክርስቲያን ተጥሶ በአወዛጋቢ ኹኔታ በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅነት ከተሾመ ከነገ በስቲያ አንድ ዓመት ይኾነዋል፡፡ አብሮት የተሾመው ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ “…ነገሮች ይስተካከላሉ ብዬ ብጠብቅም ምንም ዓይነት መሻሻል ስለማይታይ” በሚል ለፓትርያርኩ የዝውውር ጥያቄ አቅርቧል፤ ከመልካም አስተዳደር መርሖዎች ጋር በመሠረቱ ሳይታረቅና “ምንም ዓይነት መሻሻል ሳይታይበት” ዓመት ላስቆጠረው ባዶ የማጭበርበርያ ዲስኩሩና አሠራሩ የቅርብ ምስክር ነው፡፡ ጠያቂ የሌለው የአማሳኞች ከለላ በመኾን ምእመናንን እያሸማቀቀና እያስለቀሰ ይገኛል በብልሹ አስተዳደርና ሙስና የተባረሩትን አለቃ ንጹሕ ናቸው ብሎ እንዲመለሱ ጽፏል የደብሩ ሒሳብ እንዳይመረመር በመከልከል ለአለቃው ምዝበራና ሙስና ሽፋን ሰጥቷል በምእመናኑ ከተባረሩም በኋላ በደብሩ ገንዘብ ለብቻቸው እያዘዙበትና እያባከኑት ነው *                   *                   * ግልጽነት በጎደለው ማጣራት ምእመናኑን ጥፋተኛ በማድረግ በሕግ እንዲጠየቁ ወስኗል የክ/ከተማው ፖሊስ፥ የሕገ ወጥ ትእዛዝ አስፈጻሚ በመኾን ምእመናኑን እያስጨነቀ ይገኛል ምእመናኑ፣ በሳምንት ለኹለተኛ ጊዜ በእስር ቢንገላቱም የደብራቸውን ጥበቃ አጠናክረዋል ለሚፈጠረው የሰላም መደፍረስና ሰብአዊ ጉዳት ተጠያቂው አለቃውና ሀ/ስብከቱ ይኾናሉ *                   *                   * የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ: ሕገ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የአብያተ ክርስቲያን፣ የካህናትና የምእመናን ምዝገባ ሊካሔድ ነው፤ የመላው አገልጋዮችና ምእመናን ንቁ ትብብርና ተሳትፎ ወሳኝ ነው

የአሠልጣኞች ሥልጠና በሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ተሰጥቷል ለማረሚያ ቤቶች፣ ለገዳማትና ለአብነት ት/ቤቶች ትኩረት ይሰጣል የውጭ አህጉረ ስብከት ምዝገባ በመገናኛ ቴክኖሎጂው ይመቻቻል ውጤቱና ትንተናው በበጀት ዓመቱ መጨረሻ እንደሚታወቅ ይጠበቃል ቤተ ክርስቲያን፣ አገልጋዮቿንና ምእመናኗን የመመዝገብ መብት አላት *               *               * (ሰንደቅ፤ 11ኛ ዓመት ቁጥር 545፤ ረቡዕ፣ የካቲት 9 ቀን 2008 ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፥ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተግባራቷን ተኣማኒነትና ተቀባይነት ባላቸው መረጃዎች ላይ ተመሥርታ በዕቅድ በመምራት ሐዋርያዊ ተልእኮዋን ለመወጣት የሚያስችላትን የአብያተ ክርስቲያናት፣ የአገልጋዮች እና የምእመናን ምዝገባ በቀጣዮቹ ኹለት ወራት ውስጥ እንደምታካሒድ አስታወቀች፡፡ ምዝገባው፥ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የአኃዛዊ መረጃ (ስታትስቲክስ) ክፍል አስተባባሪነት፣ ከመጪው መጋቢት መባቻ እስከ ሚያዝያ ወር መጨረሻ 2008 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሔድ ታውቋል፤ የምዝገባውን ሒደት በትክክል ለማከናወን ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚሠራባቸው ልዩ ልዩ ቅጾች ተዘጋጅተው የተሠራጩ ሲሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችም መሠራታቸውን የመምሪያው ሓላፊዎች ገልጸዋል፡፡ ምዝገባው ያስፈለገበት ዋና ምክንያት፥ ስለ ቤተ ክርስቲያን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ቋሚ ሲኖዶስ: የተሐድሶ ኑፋቄ በኮሌጆች የሚገኝበትን ኹኔታ የሚያጠና ኮሚቴ ሠየመ፤ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያኑ የእምነት መግለጫ ምላሽ እንዲሰጥ አዘዘ

በመንበረ ፓትርያርኩ ይፋዊ መግለጫ ይሰጥበታል አሳታሚው እና ማተሚያ ቤቱ በሕግ ይጠየቃሉ ቋሚ ሲኖዶስ፥ በዛሬ፣ የካቲት 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው፣ ለቤተ ክርስቲያናችን የህልውና ስጋት የኾነውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ከመከላከልና ከማጋለጥ አኳያ  ወሳኝ የኾኑኹለት ዐበይት ውሳኔዎችን አሳልፏል፤ ትእዛዞችንም ሰጥቷል፡፡ የተሐድሶ መናፍቃን፣ መንፈሳውያን ኮሌጆችን የእንቅስቃሴአቸው ዕንብርትና ማእከል(ስትራተጅያዊ ቦታ) በማድረግ የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ በአጭር ጊዜ ወደ ፕሮቴስታንታዊ አቅጣጫና መንገድ ለመለወጥ በኅቡእ ስለሚያካሒዱት ዘመቻ የተወያየው ቋሚ ሲኖዶሱ፣ ኹኔታውን በጥልቀት አጥንተው ለመጪው ግንቦት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሚያቀርቡ የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ሠይሟል፡፡ በጥቅምቱ ምልዓተ ጉባኤ የተቋቋመውን የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቋሚ ኮሚቴ በሚመሩት በብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሰብሳቢነት በኮሌጆቹ ላይ ምርመራውንና ፍተሻውን የሚያካሒዱት የኮሚቴው አባላት ብዛት ስድስት ሲኾኑ እነርሱም፡- 1) መጋቤ ሐዲስ ኃይለ እግዚእ አሰፋ 2) ሊቀ ጠበብት ሐረገ ወይን አገዘ 3) መሪጌታ ሳሙኤል አየሁ 4) ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ 5) ዶክተር በለጠ ብርሃኑ 6) ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ናቸው፡፡ በሌላ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የመምሪያ እና የኮሌጅ ሓላፊዎችን አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ

የማኅበሩ ሚዲያዎች ታግደው ክሥ እንዲመሠረትበት አቋም ለማስያዝ እየተቀሰቀሰ ነው ልዩ ጸሐፊአቸው ንቡረ እድ ኤልያስ እና አባ ሰረቀ ብርሃን ግንባር ቀደም ቀስቃሾች ናቸው ቋሚ ሲኖዶስ እና ብፁዓን አባቶች፣ ፓትርያርኩን ሲመክሩ እና ሲያስጠነቅቁ ሰንብተዋል ፓትርያርኩ፥“ምን ሲኖዶስ አለና” በሚል የጠሩት ስብሰባ፣ ሕጋዊም መዋቅራዊም አይደለም ፓትርያርኩ እና ልዩ ጸሐፊአቸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ፓትርያርክ አባ ማትያስ፥ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያዎችን ዋና እና ምክትል ሓላፊዎችን እንዲኹም የሦስቱን መንፈሳውያን ኮሌጆች የአስተዳደር ሓላፊዎችን፣ ዛሬ፣ የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ መጥራታቸው ተሰማ፡፡ በመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ላይ የተጠራው አስቸኳይ ስብሰባው÷ ማኅበሩ በኮሌጆች ውስጥ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ስለሚገኝበት አሳሳቢ ኹኔታ በሚዲያዎቹ ማስነበቡን ተከትሎ፣ ፓትርያርኩ በክሥ እና በቅስቀሳ መልክ ያሳለፉትን መመሪያ የማጠናከር ዓላማ እንዳለው ተገልጧል፡፡ መመሪያው፣ የተሐድሶዎችን ክሥ የሚያስተጋባና የእውነት ጠብታ እንደሌለው በመተቸት ማኅበሩ ባለፈው ሳምንት በሰጠው የጽሑፍ ምላሽ ክፉኛ ተበሳጭተዋል የተባሉት ፓትርያርኩ፣ በተለይም ከማኅበሩ አገልግሎት ጋር የሚገናኙ የሥራ ዘርፎችን በሚመሩ ሓላፊዎች በኩል ተጽዕኗቸውን ለማጠናክር
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ማኅበረ ቅዱሳንን የወለደው፥“እኔ ለቤተ ክርስቲያኔ ምን ማድረግ እችላለኹ” የሚለው ሐሳብ ነው፤ይጥፋ የሚሉት የጥቅም ጋብቻ የፈጸሙ አማሳኞችና የተሐድሶ መናፍቃን ናቸው/ሰብሳቢው/

ቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ በማኅበሩ የመጀመሪያው ደንብ ፥ የማኅበሩ ወሰን በሚለው፣ ‹‹ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ አይገባም›› የሚል ነበረበት፤ ነገር ግን በ1994 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ተመልክቶ፣ የማኅበሩ በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ አለመግባት ትክክል ነው፤ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ አንገባም ማለት ግን፣ እኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ አካል ናችሁ ብለን እያጸደቀን ስንፈልጋችሁ እምቢ ልትሉን ነው ወይ? ስለዚህ ይህ “ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጣልቃ አይገባም” የሚለው ንኡስ አንቀጽ መውጣት አለበት አሉን፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ ነው መተዳደሪያ ደንቡን፣ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይበጃል ባሉት መንገድ አሻሽለው ኹሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፈርመውበት ያጸደቁት፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተቋቋመ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ቀኖና የመከተል ግዴታ አለበት፡፡ የቤተ ክርስቲያን የበላይ ውሳኔ ሰጭ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ፥ አይ ይበቃል፤ የማኅበሩ አገልግሎት አያስፈልገኝም ካለ ሊዘጋው ይችላል፡፡ አገልግሎት የምንሰጠው ቤተ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ማኅበረ ቅዱሳን: የኦርቶዶክሳዊነትን ዓለም አቀፋዊነትና በቤተ ክርስቲያን የምእመናንን ድርሻ የሚያስገነዝብ ዐውደ ርእይ ያዘጋጃል

ከመቶ ሺሕ በላይ ተመልካቾች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል ኦርቶዶክሳዊ ክውን ጥበባት ልዩ ገጽታዎቹ ይኾናሉ ተብሏል ለአጠቃላይ ዝግጅቱ ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይደረጋል የዐውደ ርእዩ መሪ ቃልና መለዮ ዛሬ በማዕከሉ ጽ/ቤት ይፋ ይኾናል   *               *               * (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፴፰፤ ቅዳሜ፤ ጥር ፳፰ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን፥ የቤተ ክርስቲያንን ዓለም አቀፋዊነት፣ ነባራዊ ኹኔታ እና ተግዳሮቶች ተረድተው የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የሚያስገነዝብ ልዩ ዐውደ ርእይ በመጪው መጋቢት ወር አጋማሽ እንደሚያካሒድ ማኅበረ ቅዱሳን አስታወቀ፡፡ ማኅበሩ፣ ከመጋቢት 15 – 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚያካሒደው ዐውደ ርእይ፣ ለአምስተኛ ጊዜ የሚያዘጋጀው ሲኾን፣ “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን: አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ!!” የሚል መርሕ እንዳለው የዝግጅቱ ዐቢይ ኮሚቴ ገልጧል፡፡ በዘንድሮው ዐውደ ርእይ፥ ቤተ ክርስቲያን በአደረጃጀቷ የካህናትና የምእመናን ኅብረት መኾኗን በማስገንዘብ ምእመናን ድርሻቸውን ዐውቀው ሓላፊነታቸውን የሚወጡበትን መንገድ የሚያሳዩ፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የአንድ አካባቢ ወይም ጎሳ ብቻ ሳትኾን በባሕርይዋ ዓለም አቀፋዊት(ኵላዊት) እና
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ ያሰጋው ማኅበረ ቅዱሳን: የፓትርያርኩ የክሥ መመሪያ የእውነት ጠብታ የሌለበት እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለው ገለጸ

ቅዱስ ሲኖዶስ እርምትና አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ተማፅኗል ከኑፋቄ፣ ከአስተዳደር በደል እና ከዝርፊያ የተነሣ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ አስግቶታል በማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ የፓትርያርኩ አካሔድ “እንግዳ እና አስገራሚ ነው” ብሏል በአካልና በግለሰቦች በኩል እንዲኹም በደብዳቤ 6 ጊዜ ለውይይት ቢጠየቁም ፈቃደኛ አልኾኑም በፓትርያርኩ ስም የሚጻፉ ደብዳቤዎች ክብርና ተኣማኒነት ያላቸው ይኾኑ ዘንድ አመልክቷል አግባብነት ያለው ወቅታዊ እርምትና መተማመኛ ያለው አሠራር ተግባራዊ እንዲኾን ጠይቋል *                        *                        * (ሰንደቅ፤ ረቡዕ፤ ጥር ፳፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)(የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ከዜናው በታች ይመልከቱ) የማኅበረ ቅዱሳን የዋናው ማእከል ጽ/ቤት የማኅበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፣ በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ በስውር የሚካሔደውና ለቤተ ክርስቲያንን የህልውና ስጋት የኾነው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ አሳሳቢ ደረጃ ስለ መድረሱ በተከታታይ መዘገቡን ተከትሎ፣ ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የማያቋርጥ ትግል እንዲካሔድ ለኮሌጆቹ ያስተላለፉት የክሥና የቅስቀሳ መመሪያ፣ አንዳችም የእውነት ጠብታ በሌለው መረጃ ላይ የተመረኮዘና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆቹን ክሥ የሚያስተጋባ እንደኾነና እጅግ ከባድ አደጋ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርኩ፡የማኅበረ ቅዱሳንን ደንባዊ ህልውና የሚክድ የክሥ መመሪያ ለኮሌጆች አስተላለፉ፤ ተቃውሟቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ በማሳሰብ ቀሰቀሱበት

“ቅዱስ ሲኖዶሱን በመጋፋት ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ ነው”   /ፓትርያርኩ/ “የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ በመፈጸምና ለአባቶች በመታዘዝ ታሪክ እየሠራ ነው” /የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ/ *               *               * (ሰንደቅ፤ ረቡዕ፤ ጥር 18 ቀን 2008 ዓ.ም.)(ደብዳቤውን ከዜናው በታች ይመልከቱ) ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ለሚገኙት ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና ለሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ መቐለ ለሚገኘው ለቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በአድራሻ በጻፉት ደብዳቤ፤ ማኅበረ ቅዱሳን፣ “የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን በመጋፋት እና ቤተ ክርስቲያንን በማተራመስ ቀኖና የለሽ ሥርዓት ሲከተል ይስተዋላል፤ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ ነው፤” ሲሉ ከሠሡ፤ የማኅበሩን የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ዘገባ ሰበብ በማድረግ በኮሌጆቹ አንዳንድ አካላት በማኅበሩ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም መመሪያ አስተላለፉ፡፡ ፓትርያርኩ በዚኹ የጽሑፍ መመሪያቸው፣ ማኅበሩ ከኦርቶዶክስ ቀኖና ውጭ በመዋቅር ያልታቀፉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው እና የተበታተኑ ማኅበራት እንዲፈጠሩ እና ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ውጭ በየመንደሩ እና በየአዳራሹ እንዲሰበሰቡ በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ ያልኾነ ባህልን
Tagged with:
Posted in Ethiopian News

በደብረ ብርሃን በሊቀ ጳጳሱ መኖርያ ቤት ቦምብ ፈነዳ፤ “በሊቀ ጳጳሱ እና በአስተዳደራቸው ላይ ጫና የመፍጠር ዓላማ ያለው ነው”/የሀገረ ስብከቱ ምንጮች/

ፖሊስ አምስት ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያካሔደ ነው ከደረጃቸው ዝቅ የተደረጉት የሀገረ ስብከቱ ሓላፊ ይገኙበታል አማሳኞች፣ ጠንቋይ አስጠንቋዮችና መናፍቃን ፈተና ኾነዋል (ሰንደቅ፤ ረቡዕ፤ ጥር ፲፩ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፤ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የደብረ ብርሃን መኖርያ ቤታቸው፣ ታኅሣሥ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ምሽት ቦምብ መፈንዳቱ ተገለጸ፡፡ በመንበረ ጵጵስናው የሊቀ ጳጳሱ መኖርያ በሚገኘው ዕቃ ቤት አጠገብ የፈነዳው ቦምቡ፣ በብፁዕ አቡነ ኤፍሬምም ኾነ በሌላ ሰው ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም፡፡ ከፍተኛ ድምፅ የተሰማበት የፍንዳታው ስፍራ ጉድጓድ ፈጥሮ የሚታይ ሲኾን የዕቃ ቤቱ መስኮቶች ረግፈዋል፤ በመንበረ ጵጵስናው አጠገብ በሚገኘው የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የሊቀ ጳጳሱ ቢሮ መስተዋቶችም ተሰነጣጥቀዋል፡፡ የከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት፣ አምስት የሀገረ ስብከቱን ሓላፊዎች እና ሠራተኞች ታኅሣሥ 27 እና ጥር 3 ቀን በቁጥጥር አውሎ ምርመራ እያካሔደ መኾኑ ተጠቅሷል፡፡ የሰው ኃይል አስተዳደር ክፍል ሓላፊው ቀሲስ አስቻለው ፍቅረ፣ የሕግ ክፍሉ
Tagged with:
Posted in Ethiopian News