Blog Archives

የጦላይ እስረኞች ይናገራሉ

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ሳምንት በአምስት የማቆያ ቦታዎች ለወራት ታስረው የነበሩ አስር ሺህ ገደማ ሰዎች መልቀቁን አሳውቋል፡፡ መንግስት ታሳሪዎቹ በቆይታቸው የተሃድሶ ስልጠና እንደተሰጣቸውና በጥሩ ሁኔታ እንደተያዙ ቢገልጽም ከእስር የወጡት ሰዎች ግን ድብደባ እና የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደደረሰባቸው ይናገራሉ፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢትዮጵያ አበረታች መድኃኒት የተጠቀሙን ታግዳለች

ኢትዮጵያ አበረታች መድኃኒት ተጠቃሚዎችን እድሜ ልክ ከውድድር እንደምታግድ አስታወቀች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ በአበረታች መድኃኒት ላይ ትዕግስት የለንም ብሏል። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በአሜሪካ ማሪዋናን እንደመድኃኒት

በዩናይትድ ስቴትስ 28 ክፍለ ግዛቶች ማሪዋናን ለህክምና መጠቀም የተፈቀደ ሲሆን ዋሽንግተንን ጨምሮ ስምንት ግዛቶች አጽድቀዉ እየተጠቀሙበት መሆኑን ከስፍራዉ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል። የህክምናና ጥንታዊ ስሙ ካናቢስ የሚባለዉ ማሪዋና በኢትዮጵያ እና መካከለኛዉ ምሥራቅ አካባቢ ሃሽሽ በመባል ይታወቃል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአሜሪካ እና የእስራኤል ውዝግብ 

«የእስራኤልን አቋም መደገፍ የአሜሪካንንም ሆነ የእሥራኤልን እሴቶች እንደመቃረን የሚቆጠር ነው » የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዞን ዘጠኞች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤት ለሰጠው ፍርድ መሠረት የሆኑ የሲዲ እና የሰነድ ማስረጃዎች አላገኘንም በሚል ብይኑን አስተላልፏል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አቶ በቀለ ገርባ ዳግም ከታሰሩ ዓመት አለፈ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ በቀለ ገርባ በድጋሚ ከታሰሩ አንድ ዓመት እና ጥቂት ቀናት ተቆጠሩ። የኦሮሞ ተቃውሞ በተቀሰቀሰ ማግሥት በሽብር ተጠርጥረው ከዓመት በላይ የታሰሩት አቶ በቀለ የፍርድ ሒደት አሁንም አልተጠናቀቀም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዶክተር መረራ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ዶክተር መረራ ከጠበቆቻቸዉም ሆነ ከራሳቸዉ የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸዉ ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም መርማሪዎች የጀመርነዉ ምርመራ አልተጠናቀቀም በማለታቸዉ ፍርድ ቤቱ ለመጪዉ ጥር 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የባህል ቅኝት በተሰናባቹ 2016

የዓመቱን የአዉሮጳ ማዕከል በማስተዋወቅ የጀመረዉ  የጎርጎርዮሱ 2016 ኢህአዴግ ሥልጣን የያዘበትን 25 ዓመት በተመለከተ በመንግሥታት ለዉጦች በተለይ በአማርኛ ቋንቋ ላይ ያሳደረዉን ተጽኖ  የቃኘንበት ፤ የሰማዕቱ ብፁዕ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ በቀደመ መካናቸው መመለስ ጎልተዉ ከወጡ ዝግጅቶች ነበሩ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በ2017 የጀርመን የአፍሪቃ ፖለቲካ ትኩረት 

2017 የጀርመን ምክር ቤት አባላት ምርጫ የሚካሄድበት በመሆኑ ፖለቲከኞች ከውጭ ይልቅ የሀገር ውስጥ ፖለቲካ ላይ ነው ትኩረታቸው ።የሀገር ውስጥ ፀጥታ የጡረታ እና የጤና ጉዳዮችን የመሳሰሉት የመነጋገሪያ አጀንዳዎች ይሆናሉ ። ሆኖም የ2017 የቡድን ሀያ ጉባኤ አስተናጋጅ ጀርመን በዓመቱ የአፍሪቃ መንግሥታትን የሚያሳትፍ ልዩ ጉባኤ ጠርታለች ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አቶ በቀለ ገርባ ዳግም ከታሰሩ አመት አለፈ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ በቀለ ገርባ በድጋሚ ከታሰሩ አንድ ዓመት እና ጥቂት ቀናት ተቆጠሩ። የኦሮሞ ተቃውሞ በተቀሰቀሰ ማግሥት በሽብር ተጠርጥረው ከዓመት በላይ የታሰሩት አቶ በቀለ የፍርድ ሒደት አሁንም አልተጠናቀቀም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዉጭ ዜጎችን ያስደነገጠዉ ሕግ በሳዉዲ

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ከሹፌርና ከቤት ሠራተኞች በስተቀር በግዛቱ የሚኖሩ የውጭ ሀገር   ዜጎችም ሆነ ሚስትና ልጆቻቸው ወርኃዊ ክፍያ እንዲከፍሉ ሊያደርግ ነው፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጀማሪ ኩባንያዎች የሚያግዘው የኬንያ ማዕከል

ናይሮቢ ኢንኩቤሽን ላብ ወይም ናይላብ የተሰኘው የኬንያው የሶፍትዌር ዝግጅት ማዕከል የተመሰረተው በጎርጎሮሳዊው 2010 ዓ.ም ነው። ማዕከሉ ከፍተኛ ማሕበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎችን ይደግፋል። የኬንያ የሶፍትዌር አዘጋጆች ለእለት ተለት ሕይወት ጠቀሜታ ያላቸው የፈጠራ ሥራዎቻቸውን በዚህ ማዕከል ያሻሽላሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብር ተቃርኖዎች

የኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት በታህሳስ 18 ውሎው የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብርን አጽድቋል፡፡ በስህተት ለእስር ለተዳረጉ ሰዎች የሚሰጥ ካሳ የህግ ማዕቀፍ እንደሚዘጋጅለት በመርሃ ግብሩ ተጠቅሷል፡፡ በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች በምርመራ ወቅት በቅርብ ሰው የመጎብኘት መብታቸው ገደብ ሊጣልበት እንደሚቻል የተቀመጠው ተተችቷል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሳይንሱ ዓለም አበይት ክስተቶች በ2016

አወዛጋቢ በሆነ በሆነ መልኩ ከሦስት ወላጆች በተገኘ ጽንስ በምድራችን የመጀመሪያው ልጅ መወለዱ ተሰምቷል። ህፃናት ሚጢጢ የራስ ቅል ይዘው እንዲወለዱ የሚያደርገው ከብራዚል የተነሳው ዚካ ተሐዋሲ የዓለም ስጋት ደቅኖ አልፏል። የጎርጎሪዮሱ 2016 ዓመት በርካታ ሳይንሳዊ ክስተቶች ታይተውበታል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አወዛጋቢዉ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትንበያ 

ኢትዮጵያ  የተባበሩት መንግስታት የንግድና የልማት ጉባኤ  ዝቅተኛ የገቢ መጠን አላቸዉ ብሎ ካስቀመጣቸዉ 48 የዓለም ሃገሮች አንዷ ናት።በተቋሙ የዘንድሮ የትንበያ ሪፓርት ከ2021 እስከ 2024 ድረስ ባሉት ዓመታት  16 ሀገሮች ከዝቅተኛ ወደ መካካለኛ ገቢ ይሸጋገራሉ ተብሎ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።  ኢትዮጵያ ግን  በዝርዝሩ ዉስጥ አልተካተተችም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ግቤ ሦስት ግንባታ እና ተቃዉሞው 

1, 870 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም ያለዉ የግልገል ግቤ ግድብ ባለፈዉ ቅዳሜ ተመርቋል። ይህ የኃይል ማመንጫ ግድብ በወንዙ የፍሰት መጠን እና በአካባቢዉ የሚኖሩ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖረዉ ሳርቫይቫል እንቴርናሽናል ሲገለፁ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ዘመቻዉን«መሰረተ ቢስ»  ይላሉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የእስራኤል የመንግሥታቱ ድርጅት ዉሳኔ ተቃዉሞ 

እስራኤል ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ውሳኔ በኋላ ከ12 ሃገራት ጋር ያላትን የሥራ ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቃለች። ግንኙነቱን ያቋረጠችው ምዕራብ ዮርዳኖስ እና ምሥራቅ ኢየሩሳሌም የአይሁድ ሰፈራን በማውገዝ የመንግሥታቱ ድርጅት ዐርብ እለት ያሳለፈውን ውሳኔ  በመቃወም ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አውሮፓ እና ጀርመን በ2016  

2016 በአውሮጳም ሆነ በጀርመን ሲቋጠር ሲፈታ የከረመው የስደተኞች ጉዳይ እና የሽብር ጥቃት ጥላ ያጠላበት ዓመት ነበር ። በ2016 ትኩረት ከሳቡት መካከል የብሪታንያ ህዝብ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመውጣት መወሰኑ አብዩን ቦታ ይይዛል ።በዓመቱ ማብቂያ ለህዝበ ውሳኔ የቀረበው የኢጣልያ ህገ መንግስት ይሻሻል አይሻሻል ጥያቄ ውጤትም እንዲሁ ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሶማሊያ ምክር ቤቶች ተመራጮች ቃለ መሃላ ፈጸሙ

መረጋጋት ርቋት የቆየችው ሶማሊያ ዛሬ ታኅሳስ 18/2009 ዓ.ም. ልታካሄደው የነበረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ መራዘሙ እና ወደ ጥር አጋማሽ ተገፍቷል፡፡ አጠቃላይ ምርጫው ማጭበርበሮች እና ማስፈራራቶች እየተደረጉበት ነው በሚል ክስ እየቀረበበት ይገኛል፡፡ ዛሬ የህግ መወሰኛ እና ተወካዮች ምክር ቤቶች ተመራጮች ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሐኪም ቤት መግባቱ ተገለጠ

በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ረፋዱ ላይ ዝዋይ ባቱ ሐኪም ቤት እንደገባ የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ለዶይቸ ቬለ ተናግሯል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የ2016 ቅኝት

የወባ በሽታን ማጥፋት እንደሚቻል በጎ ዜና፣ የHIV ተሐዋሲን ስርጭት ዳግም እንዳይስፋፋ ደግሞ ስጋት የተሰማዉ በጎርጎሪዮሳዊዉ 2016 ነዉ። የዓለም የሙቀት መጠን እንዳይጨምር ርምጃ ለመዉሰድ በፓሪስ የተስማማዉ ዓለም የአየር ንብረት ዉጥን አላምንም የሚሉ ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ 45ኛ ፕሬዝደንት የመሆናቸዉን ዜና ሲሰማ የተደናገጠዉም ኢንዲሁ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

2016 በስፖርቱ ዓለም

በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን አቆጣጠር 2016ዓ,ምን ጨርሰን 2017 ን ለመያዝ የቀሩን በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ናቸው። ይህ የምንሸኘው ዓመት በስፖርቱ ዘርፍ በርካታ አስደንጋጭ፣ አሳዛኝ፣ አስደሳች እና አስግራሚ ክስተቶች የታዩበት ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዲሱ የዚምባብዌ ሸርፍ የፈጠረው ስጋት

በዚምባብዌ በጣም ብዙ የተለያዩ ሸርፎች አሉ። በዋነኝነት ሰዎች የሚያገለገሉበት ዩኤስ ዶላር ሲሆን፣ ዩሮ፣ የደቡብ አፍሪቃ ራንድ እና የቻይና ዩዋንም ይጠቀሳሉ።  በሀገሪቱ በአሁኑ ጊዜ በጠቅላላ ዘጠኝ የተለያዩ ሸርፎች ይሰራባቸዋል። ያም ሆኖ የገንዘብ ሸርፍ እጥረት ይታያል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ለገና የፕላስቲክ ወይንስ የተፈጥሮ ጽድ

የአዉሮጳዉን የገና በዓል በመብራት እና ሌሎች ጌጣጌጦች ከተንቆጠቆጠዉ የገና ዛፍ ዉጭ ማሰብ አይቻልም። በአሁኑ ወቅት ደግሞ የገና በዓል ሲታሰብ በአብዛኛዉ በአሉ በሚከበርባቸዉ ሃገራት የገና ዛፍ ተፈላጊነቱ ጨምሯል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአሜሪካን የገንዘብ ድጋፍ እና አፍሪቃ

አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸዉን ሲልዙ ለአፍሪቃ የሚሰጠዉ ገንዘብ ሊቀንስ ስለሚችል ኢትዮጵያን ጨምሮ የአካባቢዉ ሃገራት ይጎዳሉ ተባለ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዓለም በ2016 ከሐምሌ እስከ ታኅሣሥ

ዓለም ታዋቂ ሰዎቿን ተነጥቃለች፤ ሽብር በርካቶችን ጭዳ አድርጓል፤ ኃያላን ተፋጠዋል፤ በእጅ አዙርም ተጠዛጥዘዋል፤ የሶሪያዋ አሌፖ ከ5 ዓመታት ውጊያ በኋላ በበሽር አል አሳድ እጅ ወድቃለች፤ በጎርጎሪዮሱ 2016 ዓመት 2ኛ አጋማሽ። የከሸፈው የቱርክ መፈንቅለ-መንግሥት ሙከራን ሰበብ ያደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሌላ ሰበብ በኢትዮጵያም ተደግሟል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጆርጅ ማይክል አረፈ

እንጊሊዛዊዉ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ጆርጅ ማይክል ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ። የ 53 ዓመቱ ብሪታንያዊ ሙዚቀኛ መኖርያ ቤቱ ዉስጥ መሞቱ ነዉ የተዘገበዉ። ምዕራባዉያኑ የገናን በዓልን በሚያከብሩበት ዕለት ታኅሳስ 25 ስለ እዉቁ ሙዚቀኛ  ጆርጅ ማይክል ይፋ በሆነዉ ጋዜጣዊ መግለጫ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዮአሂም ጋውክ የጀርመናውያን ቁጣ ወደ ጥላቻ እንዳይቀየር ጥሪ አቀረቡ

የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ዮአሂም ጋውክ ሽብር የቀሰቀሰው ቁጣ እና ንዴት ወደ ጥላቻ እና ኹከት እንዳይለወጥ ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝዳንቱ በዓመታዊ የገና ዋዜማ ንግግራቸው «በበርሊን የገና ገበያ የበርካቶች መሞት እና መቁሰል ጥልቅ ፍርሃት እና ረብሻ ፈጥሮብናል።» ሲሉ ተናግረዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዉይይት፤ የካቢኔ ሹም ሽርና የሕዝብ ጥያቄ

መንግሥት ለማሻሻል ወይም ለመለወጥ ቃል የገባቸዉ ሕግጋት፤አወቃቀሮች፤ ድርድር፤ የሥራ ፈጠራዎች ምንነት፤ጥቅም-ጉዳታቸዉ ወይም የገቢራዊነታቸዉ መዘግየት ብዙ ማነጋገሩ አይቀርም።ለዛሬ ለመነጋገሪያ ርዕስነት የመረጥነዉ ግን የተጀመረ ወይም የተጠናቀቀዉን የካቢኔ ሹም ሽሩን ነዉ።የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ መጥቀም-አለመጥቀሙን እንቃኛለን።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የገና በዓል መልክት

የገና ወይም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የጎሮጎሮሳዉያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተለዉ የክርስትና እምነት ተከታይ ዘንድ ዛሬ በመከበር ላይ ነዉ። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራት የሐይማኖት መሪዎችና ፖለቲከኞች ለየተከታዮቻቸዉ መንፈሳዊና ዓለማዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የምዕራባዉያኑ የገና አከባበር በአዲስ አበባ

የጎርጎረሳዉያኑን የቀን ቀመር የሚከተሉና የፈረንጆቹን የገና በዓል የሚያከብሩ ምዕመናን በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በመሰባሰብ ቀኑን አክበረዉ መዋላቸዉ ተሰምቶአል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዮዓኪም ጋውክ የጀርመናውያን ቁጣ ወደ ጥላቻ እንዳይቀየር ጥሪ አቀረቡ

የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ዮዓኪም ጋውክ ሽብር የቀሰቀሰው ቁጣ እና ንዴት ወደ ጥላቻ እና ኹከት እንዳይለወጥ ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝዳንቱ በዓመታዊ የገና ዋዜማ ንግግራቸው «በበርሊን የገና ገበያ የበርካቶች መሞት እና መቁሰል ጥልቅ ፍርሃት እና ረብሻ ፈጥሮብናል።» ሲሉ ተናግረዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትየገና በዓል መልክት

የገና ወይም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የጎሮጎሮሳዉያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተለዉ የክርስትና እምነት ተከታይ ዘንድ ዛሬ በመከበር ላይ ነዉ። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራት የሐይማኖት መሪዎችና ፖለቲከኞች ለየተከታዮቻቸዉ መንፈሳዊና ዓለማዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአፍሪቃ አበይት ጉዳዮች በ2016

ለየአገሮቻቸው መንበረ-ሥልጣን ከእኔ በላይ ላሳር ባዮቹ የአፍሪቃ መሪዎች ዛሬም ከተቃዋሚዎቻቸው እና ተቺዎቻቸው ጋር እሰጥ አገባ ላይ ናቸው። በውዝግቡ እስር እና ሞት እዚህም እዚያም ይሰማል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዲሱ የኢትዮጵያ የወጣቶች ስትራቴጂ ምን ይዟል?

ባለፈው ግንቦት የኢትዮጵያ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ያረቀቀዉ “የወጣቶች የልማትና የዕድገት ስትራቴጂ” በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ ተዘግቧል፡፡ የስትራቴጂው አንድ አካል ነው የተባለለት የ10 ቢሊዩን ብር ተንቀሳቃሽ ገንዘብ አተገባበር ደግሞ ከሳምንት በኋላ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለውይይት ሊቀርብ ቀጠሮ ተይዟል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የድረ-ገፅ አምደኛው ከእስር በኋላ

አቶ ስዩም እንደተናገሩት ወሊሶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩ ከ20 ቀናት በኋላ የወሊሶ ወረዳ ፍርድ ቤት የተያዙበት ጉዳይ ህዝብን በመንግሥት ላይ በማነሳሳት እንደማያስከስሳቸው ወሰኖላቸው ነበር ።ይሁን እና ከዛ በኋላ ኪሳቸው ውስጥ በተገኘ ጽሁፍ ምክንያት ወደ ጦላይ እንዲወሰዱ ተደረገ ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በጀርመን ጥቃት የጣለዉ ቱኒዝያዊ ተገደለ

የጀርመን ብሎም የአዉሮጳ የደኅንነት ሰራተኞች በሳምንቱ መጀመርያ ሰኞ ምሽት በርሊን ከተማ በሚገኝ በአንድ የገና ገበያ ላይ በከባድ ጭነት መኪና 12 ሰዎችን ደፍጥጦ የገደለዉና 50 ሰዎችን ለጉዳት የዳረገዉ የ 24 ዓመት ቱኒዝያዊ ሽብርተኛ ጣልያን ሚላን ከተማ ላይ ተገደለ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የረሃብ አደጋን በመስኖ እርሻ መቅረፍ 

ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ ሃገራት በመጭዎቹ ከ 60ዓመታት በላይ የሕዝባቸዉ ቁጥር በእጥፍ ስለሚያድግ ራሳቸዉን መመገብ አይችሉም መባሉ ተገለፀ። በሕዝብ ብዛት ቁጥር ላይ ጥናት የሚያካሂዱ ተቋማት እንደጠቆሙት ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር የአፍሪቃ ሃገራት ምግብን ገዝተዉ ሕዝባቸዉን መመገብ ግድ ይላቸዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የድረ ገፅ አምደኛው አቶ ስዩም

አቶ ስዩም እንደተናገሩት ወሊሶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩ ከ20 ቀናት በኋላ የወሊሶ ወረዳ ፍርድ ቤት የተያዙበት ጉዳይ ህዝብን በመንግሥት ላይ በማነሳሳት እንደማያስከስሳቸው ወሰኖላቸው ነበር ።ይሁን እና ከዛ በኋላ ኪሳቸው ውስጥ በተገኘ ጽሁፍ ምክንያት ወደ ጦላይ እንዲወሰዱ ተደረገ ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በልማት ስም የተፈናቀሉ አርሶአደሮች

አርሶ አደሮቹ ከመሬታቸዉ ሲነሱ የካሳ ክፍያ ገንዘብ ብቻ ተሰጥተዉ ቦታዉን እንዲለቁ ከማድረግ ዉጭ ምንም አይነት ድጋፍና ክትትል አይረግም ነበር ያሉት ሀላፊዉ፤የካሳ አሰጣጡም ቢሆን እጥረት የነበረበትና የአርሶ አደሮቹን ህይወት ለችግር የዳረገ እንደነበር ገልጸዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የሽብር ክስ ተቀየረ

ከታሰረ አንድ ዓመት ሊደፍን ጥቂት ቀናት የቀረው የቀድሞው የ“ነገረ ኢትዮጵያ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራው የተከሰሰበት የሽብር ወንጀል ተቀይሮ በመደበኛ የወንጀል ህግ ራሱን እንዲከላከል ብይን ተሰጠ፡፡ ብይኑን የሰጠው የጌታቸውን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ታህሳስ 13 በዋለው ችሎት ነው፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ትምህርትን በማዳረስ የኢንተርኔት ሚና 

ኢንተርኔትን በሚገድቡ እንደ ኢትዮጲያ ባሉ ሀገራት ደግሞ የሳተላይት ቴክኖሎጂ ትምህርትን ለማዳረስ አማራጭ መንገድ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የበርሊኑ ጥቃት፤ የገና በዓል፤ የኢትዮጵያዉያን አስተያየት

በሳምንቱ መጀመርያ በጀርመን መዲና በርሊን በተዘረጋዉ የጀርመናዊ ባህላዊ የገና ገባያ ላይ ጥቃት ከደረሰ ወዲህ ፤ በሃገሪቱ በየዓመቱ በሚጠበቀዉ የጀርመናዉያኑ የገና በዓል አከባበር ላይ የሃዘን ጥላ ያንዣበበበት ይመስላል። በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን የጀርመናዉያኑን ገና እንዴት ይሆን የሚያከብሩት? ኢትዮያዉያንን አስተያየት አሰባስናል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሶማሊያ ቀዉስና ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ  ለቆ መውጣት በሶማሊያ የመረጋጋት ተስፋ ላይ ጫና ያሳድራል እየተባለ ነው። የኢትዮጵያ ጦር ከለቀቃቸው ከተሞች መካከል የተወሰኑት በአል-ሸባብ እጅ ወድቀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ጦሩን ከሶማሊያ ለመውጣቱ ከሚሰነዘሩት ምክንያቶች መካከል የምዕራባውያኑን ዲፕሎማሲያዊ ጫና ማርገብ አንዱ ሳይሆን አይቀርም እየተባለ ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሥመ-ጥሩው ጠበቃ ተሾመ ገ/ማርያም አረፉ

ባለፈዉ አርብ ያረፉት የመጀመሪያዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ተሾመ ገ/ማርያም ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ተቀበሩ።በአፄ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓተ-መንግስት በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ያገለገሉት አቶ ተሾመ፤ የውጭ ተቋማትን በጥብቅና በመወከል ይታወቁ ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

  አቦሸማኔ ለአደጋ መጋለጡ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ብርቅዬ የዱር አራዊት እና ዉጤቶቻቸዉ ሕገወጥ ንግድ መበራከቱ ተገለፀ። ወደተለያዩ ሃገራት በተለይ ደግሞ ወደ አረብ ሃገራት በሚደረገዉ በዚህ  ሕገ ወጥ ንግድ ምክንያትም አብዛኞቹ ብርቅዬ የዱር አራዊት ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ መሄዱ እየተነገረ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የደቡብ ሱዳን ሠላም እና የግብፅ ዕቅድ

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታ አል-ሲሲ ባለፈው ሳምንት ወደ ዩጋንዳ ጎራ ብለው ከኡጋንዳው አቻቸው ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር በተለያዩ ጉዳዩች ላይ መክረዋል፡፡ በደቡብ ሱዳን እንዲሰፍር ለተቃደው የአካባቢው ሀገራት የጥበቃ ኃይል ግብጽ ጦር ብታዘምት እንደሚደግፉ ሙሴቪኒ አሳውቀዋል፡፡ ታዛቢዎች እንደሚሉት የግብፅ ዕቅድ በኢትዮጵያ ዘንድ ብዙም አይወደድም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ያንዱ ተሥፋ የሌላው ሥጋት-ጊቤ ሶስት

የአካባቢ ተቆርቋሪዎች የቱርካና ኃይቅ ሥጋት ነው ሲሉ የሚተቹት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በአንፃሩ የአገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ለማሟላት ከፍ ያለ ጠቀሜታ አለው ብሎ ተስፋ የጣለበት የጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ ከተመረቀ ቀናት ተቆጠሩ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሰማያዊ ፓርቲ ዉዝግብ

ሰማያዊ ፓርቲ በዉስጣዊ ቀዉስ እየታመሰ ነዉ። ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሕጋዊዉ የፓርቲዉ ሊቀመንበር እኔ ነኝ ሲሉ፤ በአቶ የሺዋስ አሰፋ የሚመራዉ ቡድን ደግሞ የምርጫ ቦርድ ተወካይ ባለበት ጠቅላላ ጉባኤ አካሂደን ሽረናቸዋል ይላል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የበርሊን የገና ገበያ ጥቃት፣ ምርመራ እና አስተያየት

በጀርመን መዲና፣ በርሊን  ማዕከል ትናንት ማታ በአንድ የገና ገበያ በተጣለ ጥቃት ቢያንስ 12 ሰዎች ተገድለው ወደ 50 የሚጠጉ መቁሰላቸውን የጀርመን የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አስታወቁ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአውሮጳ ህብረት እና የአፍሪቃ ስደተኞች

የአውሮጳ ህብረት ስደተኞች ወደ ክፍለ ዓለሙ እንዳይመጡ ለመከላከል እና በአውሮጳ ተገን ያላገኙትንም ለመመለስ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል ። በዚህ ረገድ ህብረቱ ከአፍሪቃ መንግሥታት ጋር የተፈራረማቸው ስምምነቶች ተጠቃሽ ናቸው ። የስምምነቶቹ ዓላማ ግን በይበልጥ  የአውሮጳ ኩባንያዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ነው የሚል ትችት ይቀርባል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሰዉ ሠራሽ የአየር ንብረት ለዉጥ ተጽዕኖ

በሰዎች እንቅስቃሴ አማካኝነት መፈጠሩ የሚነገረዉ የምድራችን የአየር ንብረት ለዉጥ በተለይ ባለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2015 ዓ,ም በዓለም ላይ ከተከሰቱ ፅንፍ የወጡ የአየር ጠባይ መገለጫዎች በአብዛኞቹ ላይ ተፅዕኖዉ ማሳረፉን አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የበርሊኑ የገና ገበያ ጥቃት

ትናንት ምሽት ጀርመን ርዕሰ ከተማ በርሊን የሚገኝ አንድ የገና ገበያን ጥሶ በገባ ከባድ የጭነት መኪና የደረሰው ጥቃት ጀርመናውያን በእጅጉ አስደንግጧል ። የጀርመን መሪዎች እና ፖለቲከኞች በስፍራው የደረሰው የሽብር ጥቃት ሳይሆን አይቀርም እያሉ ነው ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በርሊን ጥቃት

አደጋዉን ያደረሰዉ ወይም ያደረሱት ወገኖች ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ይኑራቸዉ አይኑራቸዉ በዉል አይታወቅም። ፖሊስ ቢያንስ አንድ ተጠርጣሪ መያዙን አስታዉቋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በቱርክ የሩስያ አምባሳደር አንካራ ዉስጥ ተገደሉ

ቱርክ አንካራ ከተማ ዉስጥ በሩስያ አምባሳደር ላይ በተጣለ ጥቃት ተገደሉ። የ 62 ዓመቱ አምባሳደር አንድሪ ካርሎቭ በቱርክዋ ርዕሰ መዲና አንካራ ዉስጥ አንድ የፎቶ አዉደ ርዕይ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ ሳሉ ነዉ ከአንድ ግለሰብ በተቃጣ የሩምታ ተኩስ የተገደሉት።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሩስያ አምባሳደር ተገደሉ

ቱርክ አንካራ ከተማ ዉስጥ በሩስያ አምባሳደር ላይ በተጣለ ጥቃት ተገደሉ። የ 62 ዓመቱ አምባሳደር አንድሪ ካርሎቭ በቱርክዋ ርዕሰ መዲና አንካራ ዉስጥ አንድ የስዕል አዉደ ርዕይ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ ሳሉ ነዉ ከአንድ ግለሰብ በተቃጣ የሩምታ ተኩስ ነዉ የተገደሉት።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዓለም በ2016 ከጥር እስከ ሰኔ

የአፍቃኒስታን የአስራ-ስድት ዓመት፤ የኢራቅ የ13 ዓመት፤የሊቢያና የሶሪያ የአምስት ዓመት፤የየመን፤ የዩክሬን-ሩሲያ፤የሩሲያ-ምዕራባዉያን የሁለት ዓመት የጦርነት፤የእልቂት፤ዉዝግብ ታሪክ  እንደደመቀ-ዘንድሮ አምና ሊሆን የአስር ቀን ዕድሜ ቀረዉ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስፖርት፤ ታኅሣሥ 10 ቀን፣ 2009 ዓ.ም.

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቸልሲ 11ኛ ተከታታይ ጨዋታውን በማሸነፍ ታሪክ ሠርቷል። ከተፎካካሪዎቹ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነትም አስፍቷል። አርሰናል ትናንት ነጥቡንም ደረጃውንም ለማንቸስተር ሲቲ አስረክቦ ዛሬ ተስተካካይ ጨዋታውን ከሚያከናውነው ከሊቨርፑል ስር ለመሆን ተገዷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሕጻናት ረሃብ አደጋ በናይጀርያ

በሰሜናዊ ናይጄርያ የሚገኙ ሕጻናት በአስቸኳይ ርዳታ ካላገኙ በሚቀጥለዉ ዓመት ለአስከፊ ረሃብ ይጋለጣሉ ሲል የተባበሩት መንግስታት  ህፃናት መርጃ ድርጅት አስጠነቀቀ። እንደ ድርጅቱ መግለጫ በሚቀጥለዉ ዓመት ወደ 80 ሺህ የሚሆኑ ሕጻናት ቦኮ ሃራም አካባቢዉ ላይ በደቀነዉ ቀዉስ በችጋር ይሞታሉ ሲል አስታዉቋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአስቸኳይ ጊዜ ታሳሪዎች ጉዳይ በኢትዮጵያ 

መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ ከ11,000 በላይ ሰዎች ማሰሩን አስታዉቋል። ከነዚህ እስረኞች መካከል በህግ ይጠየቃሉ የተባሉት ብቻ ሲቀሩ፤  ሌሎቹ «የተሃድሶ ስልጠና» የተሰጣቸዉ እንደሚለቀቁ የኮማንድ ፖስቱ ፅሕፈት ቤት ሐላፊ  አቶ ሲራጅ ፌጌሳ ባለፈዉ ቅዳሜ  በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቀዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዲስ የፍልሰት ፖሊሲ ለአፍሪቃ

በባህር በኩል እያደረጉ ወደ አውሮጳ ለመግባት ከሚሞክሩ ስደተኞች መካከል ብዙዎቹ አፍሪቃውያን ናቸው። ይሁንና፣ በገሀድ እንደሚታየዉ፤ ከአፍሪቃውያን ስደተኞች መካከል ብዙዎቹ አሁንም በዚያው በአፍሪቃ ከአገራቸው እና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ናቸው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የቀድሞ የኦሮሚያ ባለስልጣን ክስ እንዲቆም ተደረገ

በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ አመጽ ምክንያት ከስልጣናቸው የተነሱት እና በስተኋላም በሙስና ወንጀል የታሰሩት አቶ ዘላለም ጀማነህ የክስ ሂደታቸው ለጊዜው እንዲቆም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዝዟል፡፡ የክልሉ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ግን በመስሪያ ቤቱ አቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያቀረበው ይግባኝ ውሳኔ ካገኘ በኋላ ክሱ ይቀጥላል ብሏል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በሩስያ የተሰራዉ ጀበና እና አዲስ ካፌ

አዲስ አበባ ከተማ ፍቅር የተያዘችዉ ሩስያዊቷ ወጣት ማርያ ከኢትዮጵያ ወደ ሃገርዋ ይዛ የተመለሰቻቸዉን የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና እቃዎችን በጥቅሉ ስትገልፀዉ „ትንሽ ኢትዮጵያን ይዤ ነዉ ወደ ሃገሬ የተመለስኩት“ ስትል ነዉ። እሷ ጋ ቡናን ሊጠጣ የሚመጣዉ ሰዉ በመብዛቱም ተለቅ ያለ ጀበናዉን ለምን አላሰራም ስትል አሰበች፤ ሞከረች፤ ተሳካላትም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የገዢዉ ፓርቲ ከተቃዋሚዎች ጋር የመነጋገር ዝግጁነት

ኢትዮጵያ ዉስጥ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ባየለበት ሰሞን  መንግስት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እንደሚነጋገር ሲገልጽ ተሰምቷል። በዚህ ወቅትም በተለይ የምርጫ ሕግና ሥርዓቱን ዳግም ለመፈተሽ ብሎም ለማስተካከልም መዘጋጀቱንም ገልጾ ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ተመረቀ

እሁድ ታኅሣሥ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. የምረቃ ስነ-ሥርዓት የተከናወነለት የግልገል ጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ በከፊል ሥራ መጀመሩ ተገለጠ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ተመረቀ

እሁድ ታኅሣሥ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. የምረቃ ስነ-ሥርዓት የተከናወነለት የግልገል ጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ በከፊል ሥራ መጀመሩ ተገለጠ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኮት ዲ ቯር ምክር ቤታዊ ምርጫ

ኮት ዲቯር በነገው ዕለት ምክር ቤታዊ ምርጫ ታካሂዳለች። እጎአ በ2011 ዓም ከተካሄደው ምክር ምርጫ ርቆ የነበረው ትልቁ የተቃዋሚው የኮት ዲቯር ሕዝባዊ ግንባር ፣ በምህፃሩ «ኤፍ ፔ ኢ» የተባለው በነገው ምርጫ ይሳተፋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይዞታ

ላለፉት 10 ቀናት ደብዛው ጠፍቶ የሰነበተው እና በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዳገኙት ቤተሰቦቹ አስታወቁ፡፡ ቤተሰቦቹ “ተመስገን ዝዋይ የለንም ተብለናል” ሲሉ አቤቱቻቸውን ለተለያዩ አካላት ሲያቀርቡ ሰንብተዋል፡፡ ዛሬ ለጥቂት ደቂቃዎች ተመስገንን መመልከት እንደቻሉና ጤንነቱ መቃወሱን ተናግረዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

   የዩናይትድ ስቴትስ ፀረ-ሽብር ዘመቻ

ዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ፀረ-ሽብር ዘመቻ ካወጀችበት ከ1993 ጀምሮ የአሜሪካ ጦር በገባበት ሐገር በሙሉ በሽብር፤ ጦርነት እና ሁከት እየተተራመሱ ነዉ። አንድ የሶማሊያ ምሁር እንደሚሉት ደግሞ የአሜሪካ ሶማሊያ ላይ የከፈተችዉ ጦርነት ለሐገሪቱ ሕዝብ ያተረፈዉ ሞት እና ስደት ነዉ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የEBC ኃላፊዎች ሹመት

እስከ ትናንት ድረስ የአማራ መስተዳድር የመገናኛ ብዙሐን ሐላፊ  የነበሩት አቶ ሥዩም መኮንን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነዉ ሲሾሙ፤ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነዋል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኮምፒውተርን በቋንቋው የሚያናግሩ ልጃገረዶች

የአሜሪካን ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለቤት ጂል ባይደን ለሁለት ነገር ስሱ ናቸው- ለሴቶች ጉዳይ እና ለትምህርት፡፡ በትምህርት የዶክትሬት ማዕረግ ያላቸው ባይደን ዋይት ሃውስ ገብተው እንኳ የእንግሊዘኛ መምህርነታቸውን አልተውም፡፡ ባለፈው ሐምሌ ወር ወደ ምስራቅ አፍሪካ ለመጓዝ ሲሰናዱም የሴቶችን የትምህርት ዕድል ጉዳይ አንግበው ነበር፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች

በመደበኛ መልኩ ይፋ ያልሆኑ ሆኖም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናልም፥ አያገባንም የሚሉ የተለያዩ ትንንሽ ድርጅቶች እዚህም እዚያም እንደ አሸን እየፈሉ ነው። ከሰሞኑ አንድ ሌላ ተቋቁሟል። «ሸነግ» ይሰኛል በምሕጻሩ። ይኸኛው በእርግጥ ሌሎቹን ትንንሽ ድርጅቶች ለመወረፍ ብሎም ለመሳለቅ የተፈጠረ ምናባዊ ድርጅት ነው። የሸገር ነፃ አውጪ ግንባር «ሸነግ»።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሰብዓዊ መብት እና አዲሱ የአሜሪካን ህግ

ህጉ በሙስና እና በሰብዓዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ተጠያቂ በሆኑ ላይ የአሜሪካን የይለፍ ፈቃድ ቪዛ እገዳ እና የተለያዩ ማዕቀቦችን በቀላሉ መጣል ያስችላል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢንተርኔት አፈና በኢትዮጵያ 

የኢትዮጵያ መንግሥት «ሆን ብሎ እና ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ » ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችና የመረጃ አቅራቢ ድረ ገጾችን እየዘጋ ሰብዓዊ መብትን ከመደፍለቅ እንዲቆጠብ ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የመዉሊድ ባህላዊ አከባበር

በየዓመቱ በሚከበረዉ በነብዩ መሐመድ የልደት ቀን  የኃይማኖት ተቋማት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በአስተምሮቱ ሰላምን መረዳዳትን፣ ፍቅርና መከባበርን እንደሚያነሳ የነገሩንን እንግዶች ይዘን የመዉሊድን ባህላዊን የአከባበር ሁኔታ እንቃኛለን።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

  አሌፖ፤ ድልና ዉዝግብ

ፍርስራሽ፤ ፍርክስካሽ፤ አዋራ፤ አሸዋ የተሞሉባቸዉ ከረጢቶች ክምር፤ የደረቀ ደም የተጣበቀበት ግርግዳ፤ የመኪና፤ የቁሳቁስ ጭርምትምት፤ የቀለሕ ቁልል፤ የጨርቃጨርቅ ብጥቅጣቂ፤---ይሕ ነዉ የዚያች ጥንታዊ፤ ታሪካዊ፤ ሥልታዊ፤ ከተማ የዛሬ ገፅታ። ሐላብ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የድሬዳዋ የኢንዱስትሪ መንደር

በከተማዋ ለመጀመሪያው ዙር የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ የሚውል የ150 ሄክታር መሬት ርክክብ ተካሂደል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአሜሪካን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ ጉብኝት 

ስለ ማሊኖቭስኪ የኢትዮጵያ ጉብኝት የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ቃል አቀባይ ማርዮን ዎልስ ለዶቼቬለ በኢሜል በሰጡት መልስ ሀገራቸው ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት በኢትዮጵያ እንዲከበር ተጽዕኖ ታደርጋለች ብለዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያውያን የደም ልገሳ እገዳ መነሳት

ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ቤተ እስራኤሎች እርምጃዉ ቢዘገይም አዎንታዊና በሀገሪቱ የሕግ የበላይነት መኖሩን አመላካች ነዉ ብለዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያውን የተባለ ሰባት አስክሬን ተገኘ

በታንዛንያ ዳሬ ሰላም ከተማ አቅራቢያ የኢትዮጵያውን እንደሆነ የተጠረጠረ ሰባት አስክሬን ከወንዝ ተጥሎ ተገኝቷል፡፡ የሀገሬው ፖሊሶች በአስክሬኖቹ ላይ ምርመራ እያደረጉ ሲሆን በአቅራቢያው ባለ ጫካ 81 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መያዛቸው ሟቾቹ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ አይቀርም የሚለውን ጥርጣሬ አጠናክሮታል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዓለም ባንክ ጥቆማ እና የብር የምንዛሪ ተመን

በኢትዮጵያ የገቢ እና የወጪ ንግድ መካከል የሚታየውን ጉድለት ለማስተካከል አገሪቱ የብር የምንዛሪ ተመንን እንድታስተካክል የዓለም ባንክ ጥቆማ አቅርቧል። ኢትዮጵያውያን የኤኮኖሚ ባለሙያዎች ግን ከሚገባው በላይ ይመነዘራል የሚባለውን የብር የምንዛሪ ተመን ማስተካከል ውስብስብ ችግሮች ያሉበትን የወጪ ንግድ አይታደግም ባዮች ናቸዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሳካሮቭ ተሸላሚዎቹ ናድያ እና ላምያ 

የዘንድሮው የአውሮጳ ኅብረት ፓርላማ የሰብዓዊ መብቶች ሽልማት ለሁለት የዚድ የተባለው ሃይማኖት ተከታዮች ትናንት ተበርክቷል። ሳካሮቭ የተሰኘው ይኽው ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ሽልማት የተሰጣቸው ሁለቱ ወጣቶች ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን ለወራት አፍኖ የወሲብ ባርያ አድርጓቸው ነበር ፣
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዓመታዊው  የወባ በሽታ ዘገባ

የዓለም ጤና ድርጅት፣ «WHO» ሰሞኑን ያወጣው ወባን የተመለከተው ዓመታዊ ዘገባ ተስፋ የሚሰጥ ነው። ይሁንና፣ በፀረ ወባ በሽታ ትግል አኳያ ገና ብዙ መሰራት ያለበት ነገር እንዳለ «WHO» አስጠንቅቋል።  ወባ አሁንም፣ በተለይ ፣ ከሰሀራ በስተደቡብ ባሉ ሃገራት ውስጥ አሳሳቢ የጤና ችግር እንደሆነ ይገኛል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስደተኞች የማዳኑ ተልዕኮ መዘዝ

ከአፍሪቃ ወደ አዉሮጳ ለመሰደድ ሲሉ በባህር ዉስጥ ለመስጠም አደጋ የሚጋለጡትን ለማዳን የተሰማራዉ ተልዕኮ አሉታዊ የጎንዮሽ ዉጤት እንዳስከተለ ተገለጸ። በሊቢያ የተመድ ልዩ ልዑክ ማርቲን ኮብለር እንደሚሉት የአዉሮጳ ኅብረት የባህር ላይ ተልዕኮ ከሚንቀሳቀስበት ርቀት ዉጭ ባለዉ አካባቢ ሕገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎች የተለመደ ተግባራቸዉን ቀጥለዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአውሮጳ ኅብረት እና የአፍሪቃ ግንኙነት

በአውሮጳ ኅህብረት እና በአፍሪቃ መካከል ባለው ግንኙነት ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ባሉዋቸው ጉዳዮች ላይ የኅብረቱ አባል ሃገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ሰሞኑን በሰፊው ተወያይተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢንተርኔት መሹለኪያና መደበቂያዎች

በኢንተርኔት የሚንሸራሸሩ መረጃዎች እገዳ አለያም መሰናክል ሲገጥማቸው ዜጎች ከሌላው ዓለም ጋር ግንኙነታቸው በአያሌው ይስተጓጎላል። ለዚህ ግን መላ አልጠፋም። የተከለከሉ ወይንም በኢንተርኔት በኾነ ምክንያት ከእይታ የተሰወሩ መረጃዎችን እና ድረ-ገጾችን እንዴት መከታተል እና ማሰስ ይቻላል? ራስንስ ከክትትል እና ስለላ በምን መልኩ ማዳን ይቻላል?
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ለሽብርተኛዉ ሰለባዎች የሳሃሮቭ ሽልማት

እራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ በሚጠራዉ አሸባሪ ቡድን ታፍነዉ የነበሩ ሁለት የያዚድ ሃይማኖት ተከታዮች የአዉሮጳ ኅብረት የሚያበረክተዉን የዘንድሮዉን የሳሃሮቭ ሽልማት አገኙ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የ«CPJ» ዓመታዊ ዘገባ

ድርጅቱ ትናንት ባወጣዉ ዓመታዊ ዘገባዉ እንዳስታወቀዉ በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ከዓለም አንደኛ ቱርክ፤ ሁለተኛ ቻይና ሆነዋል።ከሁለቱ ሐገራት ጋር ሲወዳደር ብዙ ጋዜጠኞችና መገናኛ ዘዴዎች የሌሉባቸዉ የምስራቅ አፍሪቃ ሐገራት ከ3 እስከ አምስት ያለዉን ሥፍራ ይዘዋል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የብሔረሰቦች ቀን በሪያድ

ካለፈዉ ሐሙስ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ በተከበረዉ በዓል ላይ ሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን፤ጥሪ የተደረገላቸዉ የተለያዩ ሐገራት ዲፕሎማቶች እና የሳዑዲ አረቢያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ተወካይ ተገኝተዋል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የCPJ ዓመታዊ ዘገባ

ድርጅቱ ትናንት ባወጣዉ ዓመታዊ ዘገባዉ እንዳስታወቀዉ በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ከዓለም አንደኛ ቱርክ፤ ሁለተኛ ቻይና ሆነዋል።ከሁለቱ ሐገራት ጋር ሲወዳደር ብዙ ጋዜጠኞችና መገናኛ ዘዴዎች የሌሉባቸዉ የምስራቅ አፍሪቃ ሐገራት ከ3 እስከ አምስት ያለዉን ሥፍራ ይዘዋል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አውሮጳ እና ህገ ወጥ የሰው አሻጋሪዎች

የአውሮጳ መንግሥታት ህገ ወጥ የሚሉትን ስደት ለመግታት የሚወስዷቸውን እርምጃዎች አጠናክረው ቀጥለዋል ። ይሁን እና በሜዲቴራንያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩት ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይደለም ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የግልጽ ጽዳትና ጥንቃቄ

በሰዉነታችን የተለያዩ ክፍሎች ለጤንነት የሚያስፈልጉና የተፈጥሮ ሚዛኑን የሚያስጠብቁ ባክቴሪያዎች ወይም ተሐዋሲያን እንዳሉ ያዉቃሉ? የእነዚህ አስፈላጊ ተሐዋሲን  መኖር በሚገባቸዉ ስፍራ አለመኖር ወይም ቁጥራቸዉ ማነስ ደግሞ የጤና ቀዉስን ማስከተሉንስ?
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢጋድ በኢትዮጵያ

የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት /ኢጋድ/  አባል ሃገራት መሪዎች ባለፈዉ ቅዳሜ አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተዉ አሁን በሶማሊያና በደቡብ ሱዳን ያለዉ የፖለቲካ ቀዉስ ላይ መወያየታቸዉን የደርጅቱ ኮሙኒኬሼን ኃላፊ ማሀመድ አህሜድ ለዶቼ ቬሌ የላኩት መግለጫ ያመለክታል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአሸባብ የቦንብ ጥቃት በሶማሊያ

የሶማሊያ አክራሪ የእስልምና ቡድን አልሸባብ ከምን ጊዜዉም በበለጠ ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ። ዓለም አቀፉ የጸጥታ ጥናት ተቋም እንደገለጸዉ ቡድኑ በአሁኑ ጊዜ ለሶማሊያም ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃ ብሎም የዓለም  ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት ምንጭ እየሆነ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጠበቆች ዶ/ር መረራን ማግኘት አልቻልንም አሉ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም የወጣውን መመሪያ ጥሰዋል በሚል የታሰሩት ዶ/ር መረራ ጉዲናን ለማነጋገር ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራ አለመሳካቱን ጠበቆቻቸው አስታወቁ፡፡ የጤንነታቸው ሁኔታም አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስም (ኦፌኮ) አመራሮች ዶ/ር መረራን ለመጎብኘት እንዳልተፈቀደላቸው ተናግረዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስፖርት፤ ታኅሣሥ 03 ቀን፣ 2009 ዓ.ም.

እንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ  የደረጃ ሠንጠረዥ መሪው ቸልሲ እና ተከታዩ አርሰናል በሳምንቱ ማሳረጊያ ላይ ባደረጉት ጨዋታ አሸንፈው ተጨማሪ ነጥብ ሰብስበዋል። ሊቨርፑል ነጥብ መጣሉን ቀጥሏል።  በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ላይፕትሲሽ ማሸነፍ ቢችልም በደረጃ ሰንጠረዡ መሪነቱን ለባየር ሙሽይንሽን አስረክቧል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሁለት ሐገራት ምርጫ

የጋምቢያ አሸናፊዎች ተሸናፊዎችን ሲያስፈራሩ፤ ጋናዎች ተሸናፊዎችን ያመስግኑ ነበር።ጋናዎች ከተሸናፊዎች ጋር ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ እንደሚመክሩ ሲያስታዉቁ፤ የጋምቢያ ምርጫ ዉጤት የወለፊንድ ባረቀ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በኢትዮጵያ የተፈናቀሉ ሰዎች ጉዳይ

ዓለም አቀፉ በሀገር ዉስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች ተከታታይ ማዕከል በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተዉ የተፈጥሮ አደጋና ግጭቶች መንስኤ 450,000 ሰዎች ከቀያቸዉ መፈናቀላቸዉን ባለፈዉ ሳምንት ባወጣዉ ዘገባ አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት የተጠቀሰዉን ቁጥር አለመቀበሉን መገናኛ ብዙሃን ጠቅሰዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወዴትነት ዉዝግብ 

በሚያቀርባቸዉ ጽሑፎቹና ሃሳቦች ጥፋተኛ ተብሎ የሦስት ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ፤ ቤተሰቦቹ የተለያየ ፍርድ ቤት ቢፈልጉትም የለም እየተባሉ መመለስ ከጀመሩ ስድስተኛ ቀን እንደሞላቸዉ ለዶይቼ ቬለ ገለጹ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአብራሪ የለሽ ጦ/አይሮፕላን ማረፊያ ሰፈር በኒጀር

ዩኤስ አሜሪካ በኒጀር የአብራሪ የለሽ(የድሮን) ጦር አይሮፕላን ማረፊያ ሰፈር በመገንባት ላይ ትገኛለች። ከአጋዴዝ ከተማ በስተደቡብ አሜሪካ ለጀመረችው ፀረ ሽብር ትግሏ ማራመጃ እየገነባችው ያለው ይኸው የድሮን ማረፊያ ሰፈር 500 በ500 ሜትር ስፋት እንዳለው ይገመታል። የአጋዴዝ ከተማ ነዋሪዎች በዚሁ ያሜሪካውያን ፕሮጀከት አልተደሰቱም።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢመደበኛው የውጭ ምንዛሪ ገበያ

በኢትዮጵያ «ሬሚተንስ» በያመቱ ከአራት ቢልዮን ዶላር በላይ እንደሚደርስ የዓለም ባንክ ዘገባ ያሳያል። ከዚሁ መካከል ግን ከ95% የሚበልጠው መደበኛ ባልሆነው መንገድ እንደሚላክ በየጊዜው የሚወጡ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ውጤት አስታውቀዋል። ስለዚሁ እጅ በእጅ በሚካሄደው ሕጋዊ ባልሆነው የውጭ ምንዛሪ ገበያ ውይይት አካሂደናል። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

«ያባትዋ ልጅ»

የመጀመሪያ መፅሀፏን «ባርቾ» ብላዋለች ።ሁለተኛዉን «በቅርብ ቀን» ብላናለች። ከዚህም ሌላ በተለይ በማሕባራዊ መገናኛ ዘዴ ተሳትፎዋ በይበልጥ በፌስቡክ ጽሑፎቿ ትታወቃለች።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የመውሊድ በዓል በአንዋር መስጂድ

1491ኛው የነቢዩ መሐመድ ልደት (መውሊድ) በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስጂድ ተከበረ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በጋና የተቃዋሚው ፓርቲ ዕጩ አኩፎ አዶ ማሸነፍ

በጋና የዋነኛው የተቃዋሚው፣ አዲሱ የአርበኞች ፓርቲ» በምህጻሩ የ« ኤን ፒ ፒ« ዕጩ ናና አኩፎ አዶ ባለፈው ረቡዕ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድል ተቀዳጁ። የሀገሪቱ አስመራጭ ቦርድ እንዳስታወቀው፣ የ72 ዓመቱ አኩፎ አዶ 53.85% በሆነ ድምጽ የገዢውን የብሄራዊ ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪና የጋናን ፕሬዚደንት ጆን ድራማኒ ማህማን አሸንፈዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዓይን ገላጭ ዐውደ-ርዕይ

ብይ ተጫዋቾች፣ አርበኞች፣ ቀሳውስት፣ ጸሎተኞች፣ ጫማ አሳማሪ፣ አልቢኖ - እኒህን በሀሳብም፣ በድርጊትም፣ በይዘትም ከጫፍ ጫፍ የተራራቁ ነገሮች “ምን አንድ ቦታ ኮለኮላቸው?” ለሚል መልሱ “አዲስ ፎቶ ፌስት” ነው፡፡ አዲስ አበባን፣ ፎቶግራፍንና ፌስቲቫልን ያጣመረው ይህ ስያሜ በየሁለት ዓመቱ ብቅ ለሚል ዓውደ ርዕይ መለያነት የዋለ ነው፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጋምቢያ ስደተኞች በጀርመን

ጋምቢያን  ከ 21 ዓመታት በላይ የመሩት ፕሬዚዳንትነት ያህያ ጃሜ በተቃዋሚዉ መሪ መሸነፋቸዉን ተከትሎ በሃገሪቱ የሚታየዉ ደስታ እንደቀጠለ ነዉ። በሌላ በኩል በምዕራብ አዉሮጳ የሚኖሩ የጋምብያ ተገን ጠያቂዎች ፕሬዚዳንት የያህያ ጃሜ ከስልጣን መዉረድ ቢያስደስታቸዉም፣ 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአቶ ተስፋዬ ዲንቃ ዜና እረፍት

ኢትዮጵያን ከሚኒስትር ዴታ እና ሚኒስትርነት አንስተዉ፣ ከ1981 እስከ 83 ሚያዝያ ወር በዉጭ ጉዳይ ሚኒስርነትና ከ19 83 ሚያዝያ እስከ ግንቦት 1983 ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት አቶ ተስፋዮ ዲንቃ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ተሰማ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአዉቶብስ «ኤሌክትሮኒክ ትኬት ሽያጭ» በኢትዮጵያ 

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን  ከነገ ጀምሮ ለአገር አቋራጭ አዉቶብሶች በቴክኖሎጅ የተደገፈ አዲስ የቲኬት ሽያጭ አገልግሎት እንደሚጀምር ለመረዳት ተችለዋል። ቀደም ሲል ትኬት ለማግኘት በቅድምያ የአዉቶቡስ መናሃርያ ሄዶ መግዛት ወይም አዛዉ እተሳፈሩበት አዉቶብስ ዉስጥ መቁረጥ እንደነበረ ይታወቃል። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ደቡብ ሱዳን እና የተመድ አጣሪ ቡድን

ውጊያ በቀጠለባት በደቡብ ሱዳን የሰብዓዊ መብት ይዞታ እጅግ እያሽቆለቆለ መሄዱን የተመድ አስታወቀ ። በተለይ በሀገሪቱ ዘር ለይቶ የሚፈጸም ወሲባዊ ጥቃት መባባሱን በደቡብ ሱዳን የድርጅቱ የሰብአዊ መብቶች አጣሪ ቡድን ባለፈው ሳምንት ገልጿል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች በዓለሙ የቅርስ መዝገብ

አስራ አንደኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ተቋም (UNESCO) የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች «ኢንታንጀብል ካልቸራል ሄሪቴጅ» ጉባዔ ከኅዳር 19 እስከ 23፣ አዲስ አበባ ውስጥ ተካሂዶአል። የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋም ኢትዮጵያ ላይ ይህን ጉባዔ ሲያዘጋጅ ለመጀመርያ ጊዜ ሲሆን እጅግ አመርቄ እንደነበርም ተነግሮለታል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ምርጫ እና አንደምታው

የአፍሪካ ህብረትን በሊቀመንበርነት እየመሩ የሚገኙት ደቡብ አፍሪካዊቷ ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ለመሪነት ቦታው በድጋሚ እንደማይወዳደሩ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ተተኪያቸውን ለመምረጥ እንቅስቃሴ ከተጀመረ መንፈቅ አለፈው፡፡ የህብረቱ ኮሚሽን ዕጩዎች የሚከራከሩበት መድረክ ለነገ አርብ ህዳር 30 አዘጋጅቷል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የዓለም ባንክ ዘገባ እና ትችቱ

ኢትዮጵያ ወጪዋ ከገቢዋ ጋር ባለመመጣጠኑ በምጣኔ ሃብቷ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረዉ የዓለም ባንክ ትናንት አስታወቀ። በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ የተከሰተዉ ድርቅ ችግር ቢፈጥርም የሀገሪቱ የኤኮኖሚ እድገት በመጠኑም ቢሆን መረጋጋት ማሳየቱንም ድርጅቱ ባወጣዉ ዘገባ አመልክቷል።  
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዳዲስ መመርያዎች ለግንባታ

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ትልልቅ የግንባታ ስራዎች «በተቀመጠላቸው ጊዜ እና በጀት እንዲጠናቀቁ» እንዲሁም የግንባታ አማካሪዎች ስራቸዉን በትክክል ካልተወጡ ፍቃዳቸዉ እስከ ሶስት ዓመት እንደሚወሰድባቸዉ የሚያዝ መመሪያ ማዘጋጀቱ እየተዘገበ ይገኛል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

    የICC እና አፍሪቃ ግንኙነት

የአፍሪቃዉያንን ያክል አባላት የሌሉት ፍርድ ቤት እስካሁን ከአፍሪቃዉያን ዉጪ የከሰሰ፤ ያሳሰረ ወይም ያስፈረደበት የለም።ይሕ በርካታ የአፍሪቃ መንግሥታትን ቅር አስኝቷል።እንደ ደቡብ አፍሪቃ፤ ቡሩንዲ እና ጋምቢያን የመሳሰሉ ሐገራት ከአባልነት ሲወጡ፤ ሌሎች እንሱን ለመከተል እያንገራገሩ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ልውጠ ኅያዋን የጥጥ ዘር ግብይት

ኢትዮጵያ በዘረ-መል ምኅንድስና የተዘጋጀ የጥጥ ዘር ግብይትን ለመፍቀድ እየተዘጋጀች ነው። የአካባቢ ተቆርቋሪዎች እና የሸማቾች መብት ተሟጋቾች ግን አገሪቱ አሁንም ልውጠ ኅያዋን የጥጥ ዘር ለመጠቀም ዝግጁ አይደለችም ሲሉ ይሞግታሉ። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

 የአዉሮጳ ሕብረት የልማት ዕቅድ

ሕብረቱ ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ዉስጥ ይፋ ያደረገዉ ሰነድ የተባበሩት መንግሥታት የነደፈዉ ዘላቂ  የልማት ግቦች ዕቅድ አዉሮጳና በመላዉ ዓለም ገቢር የሚሆንበት ሥልት ያካተተም ነዉ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ድርቅ በደቡብ ኦሞ ዞን

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የተከሰወዉ የዝናብ እጥረት እና ድርቅ ከብቶችን እየገደለና እየጎዳ መሆኑን የአካባቢዉ ኗሪዎች አመለከቱ። አንድ የአካባቢዉ ነዋሪ በተለይም በና ፀማይ ወረዳ በርከት ባሉ ቀበሌዎች ሕዝቡ ከዚህ ቀደም ከሚከሰተዉ የከፋ መሆኑን የሚናገርለት ይህ ድርቅ ብዙ ከብቶችን እየገደለ መኖሆኑን ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአሜሪካ ንግድ ምክር ቤት በኢትዮጵያ

AMCHAM በሚል ምሕፃሩ የሚጠራዉ  ፅሕፈት ቤት አሜሪካዉያን ነጋዴዎችና ባለሐብቶች ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸዉ ጋር ያላቸዉን የሥራ ግንኙነት ለማጠናከር ይረዳል ተብሏል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

 የባሕል ሳምንት በድሬዳዋ

ድሬዳዋ ላይ ትናንት ተጀምሮ እስከ ነገ የሚቀጥለዉ ዉይይት፤ ትርዒት መቻቻልና አብሮ መኖርን ያጠናክራል ተብሏል።ወደ ምሥራቅ የተጓዘዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር እንደነገርን አዘጋጆቹ የድሬዳዋ የባሕል እና ቱርዚም ቢሮ እና የኢትዮጵያ የባሕል ማዕከል ናቸዉ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኦሮሞ ስደተኞች ጉዳይ በካይሮ

በኦሮሚያ ክልል የተከሰተውን ተቃዉሞ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ለደህንነታቸዉ በመስጋት አካባቢያቸዉን ጥለው ወደ ጎረቤት ኬንያ፣ ሱዳንና ግብፅ ተሰደዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ የጉንዳን ሠራዊት የዓለም ሥጋት

በአካላዊ አወቃቀሩ እና ፈጣን ሥርጭቱ ልዩ የሆነ የጉንዳን ሠራዊት ከኢትዮጵያ ተነስቶ ለዓለም ስጋት ሊሆን ይችላል የሚል ዘገባ ሰሞኑ በወጣ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ ተገልጧል። የጉንዳር ሠራዊቱ ከባሕር ዳር አንስቶ እስከ ደብረታቦር ድረስ በአፈር ቅጠሉ ይርመሰመሳል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሜርክል ለፓርቲያቸዉ መሪነት በድጋሚ ተመረጡ

ሜርክል ከሁለት ዓመት በፊት በተደረገዉ ተመሳሳይ ምርጫ ለሊቀመንበርነት የተመረጡት በ96,7 ከመቶ በሆነ ድምፅ ነበር።ሜርክል በመጪዉ የጎርጎሪያዉያን 2017 በሚደረገዉ ምርጫ ለመራሔ መንግሥትነት እንደሚወዳደሩ ይፋ አድርገዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢጣልያ የፖለቲካ ቀውስ

የኢጣልያው ጠቅላይ ሚኒስትር ማቴዮ ሬንሲ ባልተጠበቀው የህዝበ ውሳኔ ውጤት ሰበብ ከሥልጣን ለመውረድ ወስነዋል ። ውጤቱ የሀገሪቱን ጽንፈኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስፈንጥዟል ። ህዝቡ የሰጠው መልስ በአውሮጳ ህብረት በኢጣልያ እና ሀገሪቱ አባል በሆነችበት በዩሮ ቀጣና ሊያስድር የሚችለው ተጽእኖ ማነጋገሩ ቀጥሏል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የካቢኔ ሹመት በትግራይ ክልል

የትግራይ ክልል ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክርቤት ትላንትና ባካሄደዉ አስቸኳይ ጉባኤ አዳዲስ የካብኔ አባላትን ለተለያዩ የመንግስት የሃላፊነት ደረጃ ሾሟል። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሶማልያ እና የስዊድን ትብብር

የስዊድን የርዳታ ሚኒስትር ኢዛቤላ ሎቪን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ያለችዉን ሶማልያ ጎብኝተዉ ተመልሰዋል። ሎቪን ወደ ሶማልያ ያቀኑት ሃገራቸዉ ለሶማሊያ የምታደርገዉ ርዳታና የልማት ትብብርን ለማጤን ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በተበጠበጠው ቀጠና የተረጋጋ ምርጫ የምታካሒደው ጋና

ጋናውያን ነገ አዲስ ፕሬዝዳንት እና የምክር ቤት አባላትን ሊመርጡ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ያቀናሉ። ፕሬዝዳንት ማሕማ እና ተፎካካሪያቸው የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪ ናና አኩፎ አዶን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች እስከ ዕለተ-ሰኞ ድረስ ድምፅ ሰጪዎችን ለማሳመን በብርቱ ሲፎካከሩ ሰንብተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዶክተሮች ለኢትዮጵያ

ጀርመን ዉስጥ ከተመሠረተ ብዙም ጊዜ ያልሆነዉ አንድ ማኅበር በኢትዮጵያ አንድ ሃኪም ቤት የተሻለ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እንዲችል እገዛዎችን ለማድረግ መንቀሳቀስ ጀምሯል። ጀርመናዉያን የህክምና ባለሙያዎችን ያካተተዉ የዚህ ማኅበር እንቅስቃሴም በሀገሪቱ የሕፃናት እና እናቶችን ሞት ለመቀነስ የበኩሉን አስተዋፅኦ የማድረግ ዓላማ ሰንቋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሁለተኛ ምርመራ

በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በሁለተኛ ዙር መመርመር መጀመሩን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጣልያን ሕዝበ ዉሳኔና ጠቅላይ ሚኒስትሩ

የኢጣልያ መንግሥት የሃገሪቱ ሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ተሃድሶ እንዲደረግ ባቀረበዉ ሕዝበ ዉሳኔ ሕዝብ ማሻሻያ አለመፈለጉን ገለፀ። የሕዝበ ዉሳኔዉን ዉጤት ተከትሎ የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማትዮ ሬንዚ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ስልጣን እንደሚለቁ በይፋ አስታዉቀዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስፖርት፤ ኅዳር 26 ቀን፣ 2009 ዓ.ም.

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ባለፈው ሳምንት በአርሰናል 3 ለ1 የተቀጣው ቦርሞትስ የማታ ማታ ሊቨርፑልን ጉድ አድርጓል።  በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ዘንድሮ ከታችኛው ዲቪዚዮን ያደገ ቡድን የደረጃ ሰንጠረዡን በመሪነት ተቆናጧል። አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዲስ መጪው ፋሲል ከነማ መሸነፉ ብዙዎችን አስደምሟል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከስልጣን ያነሳዉ የጣልያን ሕዝበ ዉሳኔ 

የኢጣልያ መንግሥት የሃገሪቱ ሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ተሃድሶ እንዲደረግ ባቀረበዉ ሕዝበ ዉሳኔ ሕዝብ ማሻሻያ አለመፈለጉን ገለፀ። የሕዝበ ዉሳኔዉን ዉጤት ተከትሎ የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማትዮ ሬንዚ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ስልጣን እንደሚለቁ በይፋ አስታዉቀዋ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሶሪያ ጦርነት፤ የዓለም ቸልተኝነት

የሶሪያ ተፋላሚ ሐይላትን እንዲሸመግሉ ዓለም አቀፉ ድርጅት የወከላቸዉ ሰወስተኛዉ ዲፕሎማት ስቴፋን ደ ሚስቱራም ሥለሽምግልናዉ ዉጤት የሚዘግቡት ባይኖራቸዉ፤ የሚናገሩት አላጡም።የሟቾች ቁጥር።ደ ሚስቱራ ባለፈዉ ሚያዚያ እንዳሉት 400 ሺሕ ሶሪያዊ ተገድሏል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢንቴርኔት አገልግሎት እንደገና መጀመሩ   

የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ካወጀ ከሁለት ወር በፊት ጀምሮ በእጅ ስልክ፣ የቀጥታ የኢንቴርኔት አገልግሎት ወይም «mobile data» ን ዘግቶ እንደነበረ ዘገባዎች ያመለክታሉ። መንግስት ይህን አገልግሎት ባለፈዉ ዓርብ መልሶ ከፍቶታል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ጋምቢያ፦ወደፊት ወይስ ወደ ኋላ?

ለ22 አመታት ጋምቢያን እንደ ብረት ቀጥቅጠው የገዙት ያሕያ ጃሜህ በስተመጨረሻ ሽንፈታቸውን ተቀበሉ። የምርጫው ውጤት ጋምቢያውያንን አዲስ ተስፋ ቢሰጣቸውም ያለፈውን ጊዜ በቀላሉ የሚዘነጉት አይመስልም። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰብዓዊ መብት ይዞታ 

ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች፣ አዋጁ የህዝብ እንቅስቃሴን እና የመገናኛ ዘዴዎች ነፃነቶችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ግንኙነቶችን ገድቧል ሲሉ ይተቻሉ። ከአዋጁ በፊት እንደነበረው ጋዜጠኞች እና የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች እና አባላት መታሰራቸው ቀጥሏል ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጋምቢያ ፕሬዚዳንት ሽንፈታቸውን ተቀበሉ

ጋምቢያን ለ22 ዓመታት የመሩት ያሕያ ጃሜሕ የምርጫ ሽንፈታቸውን ተቀበሉ። ትናንት ምሽት በአገሪቱ ብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ያሕያ ጃሜሕ ለአሸናፊው አዳማ ባሮው የእንኳን ደስ አለዎ መልክት አስተላልፈው ሥልጣናቸውን በሰላም እንደሚያስረክቡም ቃል ገብተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ያገረሸው ግጭት

በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ባለፈው ሳምንት በታየው ግጭት  85 ሰዎች ተገድለዋል። ከመዲናይቱ ባንጊ በስተሰሜን ምሥራቅ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የኦት ኮቶ ግዛት ዋና ከተማ፣ ብሪያ በታጣቂዎቹ ቡድኖች መካከል በተካሄደው ግጭት 11,000 ተፈናቅለዋል። የተመድ ዋና ጸሀፊ ፓን ኪ ሙን ግጭቱን በማውገዝ ባፋጣኝ እንያበቃ አሳስበዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢሬቻዉ አደጋ እንዲጣራ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ ቢሾፍቱ ከተማ ሊከበር በነበረዉ የኢሬቻ በዓል ላይ መንግሥት በወሰደዉ ርምጃ ሕይወታቸዉ የጠፋዉ ቁጥርና የአደጋዉ ምክንያት ተጣርቶ ምላሽ አልተሰጠም ሲል የጀርመኑ ገዜልሻፍት ፉዩር በድሮህተ ፎልከር የተሰኘዉ ለተጨቆኑ ሕዝቦች የቆመዉ ድርጅት ትናንት ባወጣዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ቅርጫት ኳስ፡ ስፖርት እና የህይወት ዘይቤ

ጀምበር ማዘቅዘቅ ስትጀምር የጋምቤላ ከተማ ወጣቶች አንድ ልማድ አላቸው፡፡ ከተማዋን አፍኗት የሚውለው ወበቅ ቀዝቀዝ ማለት ሲጀምር ጋምቤላን ሰንጥቆ ወደሚያልፈው የባሮ ወንዝ ዳርቻ ይተምማሉ፡፡ በወንዙ ዳርቻ ያለውን ነፋሻማዋን አየር እየተመገቡ ሻይ ቡና ለማለት ብዙዎች ቦታውን ያዘወትሩታል፡፡ ወደ ወንዙ ወርዶ ገላን መለቃለቅም ያለ ነው፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሮዝበርግ እራሱን ከመኪና ስፖርት አገለለ

ጀርመናዊዉ የመኪና እሽቅድምድም ተወዳዳሪ ማይክ ሮዝበርግ እራሱን ከመኪና ስፖርት አገለለ።በሜርሴዲስ መኪና የሚወዳደረዉ ሮዝበርግ ፉርሙላ-አንድ የተሰኘዉ የመኪና ዉድድር የዓመቱ አሸናፊ የሆነዉ ባለፈዉ ዕሁድ ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የእነ ሐብታሙ አያሌው የፍርድ ቤት ውሎ 

የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት በሽብር ተከሰው ይግባኝ የተጠየቀባቸው የቀድሞው የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ፍትህ ፓርቲ አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና የአረና ትግራይ አባል አቶ አብርሃ ደስታ እንዲከላከሉ ዛሬ ብይን ሰጠ። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ ሐብታሙ አያሌው የክስ መዝገብ ከተካተቱ አምስት ተከሳሾች መካከል ሶስቱን በነፃ አሰናብቷል። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

«ኤ ኤን ሲ» እና አወዛጋቢው የዙማ ሥልጣን 

የደቡብ አፍሪቃ ገዢ ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት በእንግሊዘኛው ምህፃር «ANC» ሰሞኑን ባደረገዉ ግምገማ በተለያዩ ችግሮች የተተበተቡት ፕሬዚዳንት ጄኮብ ዙማ ከሥልጣናቸዉ ይዉረዱ የሚለዉን ሀሳብ አለመቀበሉን ገለፀ ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

HIV ዳግም እንዳያገረሽ ስጋት መኖሩ

ባለፉት አምስት ዓመታት ስለHIV ይሰጡ የነበሩ ትምህርቶች መቀዛቀዛቸዉ በሀገሪቱ HIV እንደ አዲስ እንዳያገረሽ ስጋት እንዳለባቸዉ የጤና ባለሙያዎች አሳሰቡ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኪውባና ትዝታችን

በኪዩባ የኖሩ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች አባታችን የሚልዋቸዉ የዘጠና ዓመቱ ፊደል ካስትሮ ከዚህ ዓለም በመሞታቸዉ አዝነዋል። ኩዩባ ለኛ ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን ለመላ አፍሪቃ ብሎም ለመላ ጭቁን ሕዝብ አባት ነዉ ሲሉ ነዉ፤ ለፊደልና ለኪዩባ ፍቅራቸዉን የሚገልጹት። በጨቅላ እድሜያቸዉ ከቤተሰቦቻቸዉ ተነጥለዉ ወደ ኪዩባ የሄዱት እነዚህ ተማሪዎች፤
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በሙከራ ላይ የሚገኘዉ የ«HIV» መከላከያ ክትባት

ደቡብ አፍሪቃ በዓለማችን በ«HIV» የተያዙ በርካታ ሰዎች የሚኖሩባት ሃገር ናት። በጥናት በተገኘ መረጃ መሠረት አሁንም በቀን ከ 1.000  ሰዎች በላይ በቫይረሱ ይያዛሉ። በአሁኑ ወቅት የፀረ HIV ተሐዋሲ መድኃኒት የሚጠቀሙ ሰዎች በመበራከታቸዉ የበሽታዉ ገዳይነት የቀነሰ ይመስላል። 
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አቶ ካሕሳይ በርሀ ተቀበሩ

ከሕዝባዊ ወያኔ ትግራዊ ማለትም ሕወሃት መሥራቾች ከነበሩት አንዱ የአቶ ሕኽሳይ በርሀ የቀብር ሥርዓት በዛሬ ዕለት ትግራይ ሰለኽላኻ ዉስጥ ተፈጸመ። አቶ ካሕሳይ ኅዳር 11 ቀን እዚህ ጀርመን ሀገር በሙንስተር የዩኒቨርሲቲ ክሊኒክ ለአንድ ወር ያህል በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ተሰምቷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

 የገዳ ሥርዓት መመዝገብ

ገዳ ዓለም አቀፍ ጥበቃ የሚደረግለት የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ለኢትዮጵያ ድል፤ ለባሕሉ ባለቤቶች እርካታ ነዉ።ለአባገዳ ጃሎ ማዶ ደግሞ አስደሳች ነዉ።መረቁም አባገዳዉ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

 የኦፌኮ መሪ መረራ ጉዲና ታሰሩ

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ በርካታ አባላቱ እና አራት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱ ከዚሕ በፊት ታስረዉበታል።ዶክተር መረራ አምስተኛዉ መሆናቸዉ ነዉ።አቶ ገብሩ ገብረማርያም  «ትግሉ ይቀጥላል» ባይ ናቸዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ወደ የመን የቀጠለዉ ስደት

በጦርነት ወደምታመሰዉ የመን የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አመለከተ። ከቀጠለዉ ግጭት እና የከፋ የሰብዓዊ ሁኔታ በተቃራኒ ካለፈዉ ጥር እስከያዝነዉ ኅዳር ወር ድረስ ከአንድ መቶ ሺህ የሚበልጡ ከአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ የፈለሱ ተሰዳጆች የመን መግባታቸዉን ድርጅቱ ትናንት ይፋ ባደረገዉ መግለጫ ጠቅሷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ከሳውዲ የኢትዮጵያውያን በግዳጅ መባረር መቀጠሉ

ሕገ ወጥ ናችሁ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ ዐረቢያ በገፍ ከተባረሩ ሶስት ዓመት ሞላቸው፡፡ በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በገፍ የተባረሩት ህዳር፣ 2006 ዓም ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አዲስ አበባ እና የሜትር ታክሲዎቿ

የአዲስ አበባን የታክሲ አገልግሎት ለማዘመን አዳዲስ የአገልግሎት አቅራቢዎች ወደ ገበያው ብቅ ብለዋል። መንገደኞች ከአሽከርካሪዎች ጋር የሚያደርጉት ድርድር ቀርቶ በተጓዙት ርቀት የሚያስከፍሉት ኩባንያዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ለመሆኑ አዲስ አበባ ለአገልግሎቱ ምን ያክል ዝግጁ ነ?
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኮማንድ ፖስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አነጋገረ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም የተቋቋመው የኮማንድ ፖስት ሴክሬተሪያት ጽህፈት ቤት የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ዛሬ ሰብስቦ አነጋግሯል፡፡ በስብሰባው ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሾች ቢሰጡም ከውይይት እና ዘላቂ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ “አዋጁን ተቀበሉ“ የሚል መንፈስ ነበረው በሚል ተችተውታል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኤርባስ ኩባንያ ተሸላሚው ኢትዮጵያዊ መሀንዲስ

ለሽልማት አዲስ አይደሉም። በተሰማሩበት የምህንድስና ዘርፍ በተደጋጋሚ ተሸላሚ ኾነዋል። ኢትዮጵያዊው መሀንዲስ ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄ። የዕውቁ የጃዝ ሙዚቃ ጠበብት፣ የኢትዮ ጃዝ አባት፦ ሙላቱ አስታጥቄ ታናሽ ወንድም። ዘንድሮ ሲሸለሙ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ቀደም ሲል የዓመቱ ጥቁር መሐንዲስ በሚል በሚኖሩበት ዩናይትድ ስቴትስ ለሽልማት በቅተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሶማሊያ ምርጫ ውጥንቅጥ

ለረቡዕ ህዳር 21 ቀን ተቆርጦለት የነበረው ሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ  ምርጫ በድጋሚ ተራዝሟል፡፡ ምርጫው ቀጥተኛ ያልሆነ ስርዓትን የሚከተል እንደመሆኑ ፕሬዝዳንቱ መመረጥ የነበረባቸው በተወካዮች ምክር ቤት አባላት ነበር፡፡ የምክር ቤት አባላቱ ምርጫ ባለመጠናቀቁ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ከተያዘለት ቀን እንዲገፋ ምክንያት ሆኗል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአውሮጳ ህብረት እና የቱርክ ውዝግብ  

የአውሮጳ ህብረት እና የቱርክ ውዝግብ ተባብሶ ቀጥሏል ። የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ ባለፈው ሳምንት የቱርክ የህብረቱ አባልነት ድርድር እንዲቆም ድምጽ ከሰጠ በኋላ ቱርክ ያስጠጋቻቸውን ስደተኞችን እለቅባችኋለሁ ስትል የህብረቱን አባል ሀገራት እያስፈራራች ነው ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የ«ኤች አይ ቪ» ስጋትነት ቀጥሏል

«ኤች አይ ቪ» ዛሬም የአዉሮጳ መሠረታዊ የጤና ሥጋት መሆኑን በዛሬዉ ዕለት የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። የአዉሮጳ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዛሬ እንዳስታወቀዉ ከሰባት አንዱ አዉሮጳዊ በተሐዋሲዉ መያዙን አለማወቁ በጣም አሳሳቢ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የታሳሪዎች ሰብዓዊ መብትና የቤተሰቦቻቸዉ ጭንቀት

በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተፈፃሚነት የሚመረምረዉ አጣሪ ቦርድ ካለፈዉ ሰምንት ጀምሮ የታሳሪዎችን የሰብዓዊ መብት ይዞታ ለመመርመር በኦሮሚያና በአማራ ክልል ያሉ እስርቤቶችንና ወታደራዊ ካምፖችን ኢየጎበኘ መሆኑ ተነግሯል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ተጠርጣሪዉ ሰዉ አሸጋጋሪ ፍርድ ቤት ቀረበ

ኢጣሊያን ጨምሮ የአዉሮጳ መንግስታት በሰዉ አሸጋጋሪዎች ላይ ጠንከራ ርምጃ እንደሚወስዱ በተደጋጋሚ ቢዝቱም ኢጣሊያ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር እያሻቀበ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ካስትሮ፤ ለና በኢትዮጵያ ዘንድ

«እኛ የጠላነዉ፤ ላጭር ጊዜም ቢሆን መሸነፋችንን በመገመት ነዉ።» «መሸነፋችንን።» ይሕቺ ቃል   ጦርነቱ የኢትዮጵያ-የሶማሊያ ብቻ ሳይሆን የኩባና የሶማሊያ፤የደቡብ የመንና የሶማሊያ መሆኑንም አረጋገጠች።ይሕቺ ቃል ጦርነቱ የሶቭየት ሕብረትና የዩናይትድ ስቴትስ፤ የሶሻሊስቱና የካፒታሊስቱ ዓለም ጦርነት፤ የቀዝቃዛዉ ጦርነት አካል መሆኑን አረጋገጠች።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአስቸኳይ ጊዜው እና የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እስራት

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ወር የአስቸኳይ ጊዜ ካወጀ ወዲህ 11, 607 ሰዎች መታሰራቸዉን ፣ ከነዚህም መካከል ከ80% በላዩ መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አጣሪ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዶክተር ፍቅሩ ማሩ በቂሊንጦ ቃጠሎ መከሰሳቸው

 በአዲስ አበባ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ ባለፈው  ነሃሴ 28 ቀን 2008 ለደረሰው የእሳት ቃጠሎ ተጠያቂ ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ 38 ታራሚዎች ላይ ባለፈው ሳምንት ክስ ተመስርቷል። በአደጋው የ23 ሰዎች ሕይወት ነበር ያለፈው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ መንግሥት ደጋፊዎች ሰልፍ በብራስልስ

በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ቤልጅየም መዲና፣ ብራስልስ በሚገኘው የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን እና በአውሮጳ ምክር ቤት ፊት ለፊት ዛሬ ሰልፍ አካሄዱ። እነዚሁ ከተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት ወደ ብራስልስ የተጓዙት ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ ሰላም እና አንድነት፣ እንዲሁም፣  የሀገሪቱ  መንግሥት ለጀመረው የልማት ሂደት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስፖርት፤ ኅዳር 19 ቀን፣ 2009 ዓ.ም.

ኢትዮጵያ የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ጽ/ቤትን ከግብጽ መዲና ካይሮ ለማስመጣት የማግባባት ሥራ ላይ ናት በሚል የተሰራጨው ዜና ሐሰት መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ፌዴሬሽን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለዶይቸቬለ ዛሬ ተናግረዋል።  በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የእግር ኳስ ጨዋታ አርሰናል በሰፋ ልዩነት ትናንት አሸንፏል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የለንደን ሕዝባዊ ስብሰባ

የአርበኞች ግንቦት 7 የድጋፍ አባላት ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በለንደን ሕዝባዊ ስብሰባ አካሄዱ። በዚሁ ስብሰባ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣን ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ እና አቶ ብዙነህ ጽጌ ለስብሰባው ተሳታፊ ንግግር አሰምተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ዉይይት፤ ገላጋይ ያጣዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃዉሞን ተከትሎ የተደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ የተከሰተዉን የፖለቲካ ቀዉስና አመፅ ለማስወገድ ረድቶ ይሆን? መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የነበረዉን ቀዉስ ለማረጋጋት ረድቷል ሲል ይገልጻል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ፊደል ካስትሮ በ90 ዓመታቸው አረፉ

የቀድሞው የኩባ ፕሬዝዳንት እና አብዮታዊው ፊደል ካስትሮ በ90 ዓመታቸው ኩባ መዲና ሐቫና ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት ለደቡብ አፍሪቃዊቷ

ለብዙዎች መከታ ሆነው ቆይተዋል። በርካቶች ያገራቸው ሰዎች ከልብ ያፈቅሯቸዋል።  ለሕገ-መንግሥቱ ጠበቃ ሆነው በመሟገት ሙስናን አጥብቀው ታግለዋል፤ ደቡብ አፍሪቃዊቷ ዳኛ ቱሊሲሊ ማዶንሲላ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሠርግ ድግስ ከማስዋብ ወደ ተቋም ባለቤትነት

አስር ሚሊዩን ሰዎች፡፡ ሰላሳ አምስት ሺህ ዝግጅቶች፡፡ 160 ሀገሮች፡፡ እነዚህ ከዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሳምንት ክንውኖች ጀርባ ያሉ እውነታዎች ነው፡፡ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ከሚከበረው ሳምንት ውስጥ አጓጊው የዓመቱ ወጣት የሥራ ፈጣሪዎች ውድድር እና አሸናፊውን የማሳወቅ ሥነ-ስርዓት ነው፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በጋምቤላ ቤት ለቤት የጦር መሳሪያ አሰሳ እየተደረገ ነው

በጋምቤላ ከተማ የጦር መሳሪያን ለመያዝ በሚል የቤት ለቤት ፍተሻ ረቡዕ  ህዳር 14 መደረጉን እና በሌሎችም የጋምቤላ ወረዳዎች አሰሳው እንደሚቀጥል ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ ገለጹ፡፡ ፍተሻውን እያደረጉ የሚገኙት የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የክልሉ ልዩ ኃይላት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሰብዓዊ መብት አያያዝ በኢትዮጵያ

የአፍሪቃ ኅብረት አካል የሆነዉ የአፍሪቃ የሰብዓዊና የሕዝቦች መብት ኮሚሽን ከትላንትና ወድያ ባወጣዉ የዉሳኔ መግለጫ በአሁኑ ግዜ በኢትዮጵያ ዉስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀምን ተከትሎ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ እየከፋ መሄዱ በጣም እንዳሳሰበዉ ገልፀዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

 የምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ፀጥታ

ተሰብሳቢዎቹ ሰላምን በማስፈኑ ረገድ የአስሩን ሃገራት ትብብር ለማጠናከር የሚረዳ የጋራ መመሪያ እንዲረቀቅ ተስማምተዋል
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና የዩኒቨርስቲዎች አለመረጋጋት

በኢትዮጵያ መንግስት የታወጀዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ተፈጻሚ መሆን ከጀመረ በኋላ የመብት ጥሰቶች መባባሱን ስንዘግብ ቆይተናል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁና የዩኒቨርስቲዎች አለመረጋጋት

በኢትዮጵያ መንግስት የታወጀዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ተፈጻሚ መሆን ከጀመረ በኋላ የመብት ጥሰቶች መባባሱን ስንዘግብ ቆይተናል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሠዓሊዋና ሥራዎችዋ

ሠዓሊዋ በጀርመን ስትኖር ወደ 20 ዓመታትን ያስቆጠረች ብትሆንም፤ የሥነ-ጥበብ ተሰጥኦዋ ድንገት ብቅ ያለዉ የዛሬ አራት ዓመት ነዉ። ሠዓሊ ሃይማኖት መሰለ እናትም ወጣትም ናት ግን የሥዕል ተሰጦኦን ያገኘችዉ፤ ከመሸ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ለሩዋንዳ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ይቅርታ

ሩዋንዳ የምትገኘዉ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በጎርጎሪዮሳዊዉ 1994ዓ,ም በሀገሪቱ በተካሄደዉ የዘር ማጥፋት ድርጊት ለነበራት ሚና ይቅርታ ጠየቀች። ቤተ ክርስቲያኒቱ በወቅቱ በድርጊቱ የተሳተፉት ተግባር የሚፀፅት መሆኑን ገልጻለች።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአማራ ክልል የካቢኔ ሽግሽግና የቀረበበት ትችት

የአማራ ክልል መንግስት ትናንት ባካሄደው ሹም ሽር አስራ ሁለት የካቢኔ አባላትን ከቦታቸው በማንሳት በአዲስ ተሿሚዎች ተክቷል፡፡ የክልሉ መንግስት አዳዲሶቹ ተሿሚዎች “በህዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚችሉ ናቸው” ቢልም አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ግን “ጥገናዊ ለውጥ እንኳ ለመባል የማይመጥን” ሲሉ የክልሉን እርምጃ ተችተዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

በሳዑዲ  የደሞዝ ቅነሳ ተጽዕኖ

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በጠቅላላው የመንግሥት ሠራተኞች ላይ የወሰነዉ የደሞዝ ቅነሳ በሀገሪቱ የንግድ መቀዛቀዝ ፤ በአብዛኛው የውጭ ሀገር ቅጥር ሠራተኞች ላይ ደግሞ ሥራን የማጣት ስጋት አሳድሯል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአስቸኳይ ግዜ አዋጂና የዩኑቬርስትዎች አለመረጋጋት

በኢትዮጵያ መንግስት የታወጀዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ተፈጻሚ መሆን ከጀመረ በኋላ የመብት ጥሰቶች መባባሱን ስንዘግብ ቆይተናል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች ሰባተኛ መጠለያ ጣቢያ ተከፈተ

በደቡብ ሱዳን ያለውን የእርስ በእርስ ጦርነት የሸሹ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች በየቀኑ ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን ተከትሎ በጋምቤላ አዲስ መጠለያ ጣቢያ ተከፍቷል። የአዲሱ ጣቢያ መከፈት በኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች የተከፈቱትን ጣቢያዎች ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ያደርገዋል፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የባለ ድርሻዎች ስንብት በኢትዮጵያ ባንኮች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም. በፃፈው መመሪያ የኢትዮጵያ ዜግነት የሌላቸው ግለሰቦች በባንኮች እና የመድን ሽፋን ሰጪ ኩባንያዎች ውስጥ ያላቸውን የባለቤትነት ድርሻ እንዲመልሱ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢትዮጵያና የኬንያ ታላቁ አዉራ ጎዳና 

ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያገናኘዉና 500 ኪሎሜትር ርዝመት ያለዉ አዉራ ጎዳና ግንባታ ተጠናቆ ሥራ ለመጀመር የምርቃት ሥነ-ስርዓቱን እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ተዘግቦአል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

   የደቡብ አፍሪቃ የሥራ አጥ ቁጥር ማሻቀብ

ደቡብ አፍሪቃ በየዓመቱ ለ300 ሺሕ ዜጎችዋ አዳዲስ የሥራ ዕድል ካልፈጠረች ሥራ አጥነት የሐገሪቱን የምጣኔ ሐብት ዕድገት ሊያናጋዉ ይችላል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኢንተርኔት መዘጋት ያስከተለዉ ችግር

የኢትዮጵያ መንግሥት የስድስት ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ ወዲህ በተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት አገልግሎትን ወይም የሞባይል ዳታን ዘግቷል፤ በርካታ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችንም አግዷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ውቅያኖስ በድንኳ ፕላኔት፥ፕሉቶ

ምድር ከፀሐይ ከምትርቀው 40 ጊዜ እጥፍ ትርቃለች፤ ድንኳ ፕላኔት ፕሉቶ። ይኽች ከፕላኔቶች ወዲያ በርቀት የምትገኘው ድንክ ፕላኔት፥ ለዘመናት እንቆቅልሽ ሆና ቆይታለች። ከእነ አምስት ጨረቆቿ ከሥርዓተ-ፀሐይ ሽክርክሪት ጠርዝ ላይ ተንሳፋ ምሥጢር ሆና ዘመን ፈጅታለች። ካለፉት ስድስት ወራት አንስቶ ግን ፕሉቶ በየጊዜው አስደናቂነቷ እየጎላ ነው።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የግዕዝ ትምህርት በቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ

ካናዳ የሚገጘዉ የቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጠ። በዩንቨርሲቲዉ በታሪክ ትምህርት ዘርፍ ዶክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ማይክል ግሬቨርስ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በቅርብና መካከለኛዉ የምስራቅ ስልጣኔ ትምህርት ክፍል ስር በጎርጎሮሳዊዉ ዘመን ቀምር ከጥር 2017 ጀምሮ  ቋንቋዉን ማስተማር ይጀምራል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሪየክ ማቻር በኢትዮጵያ እንዳይተላለፉ ታገዱ

የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ ሪየክ ማቻር ኢትዮጵያን አቋርጠው ወደ ሌላ ቦታ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ በክልከላ ምክንያት ተደናቀፈ፡፡ የአማጽያኑ ቃል አቃባይ ማቻር በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለአጭር ጊዜ ታስረው እንደነበር ለዜና ወኪሎች ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንትን መታሰር አስተባብላለች፡፡
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአንጌላ ሜርክል በእጩነት የመቅረብ ውሳኔ

የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሚቀጥለው አውሮጳዊ ዓመት 2017 ዓም በሀገራቸው ለሚካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ ፓርቲያቸውን የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረት፣ በምህፃሩ «ሴ ዴ ኡ»ን ወክለው ለ4ኛ ጊዜ መወዳደር እንደሚፈልጉ ባለፈው እሁድ በይፋ ማሳወቃቸው ይታወሳል።  
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

«ኦቻ»፤ ኢትዮጵያን የመታዉ ድርቅ መዘዝ ቀጥሎአል

በኢትዮጵያ የተከሰተዉ ድርቅ 10,2 ሚልዮን ሰዎችን ጎድቶ እንደበር የሚታወስ ነው። ይኸው ቁጥር በወቅቱ ቢቀንስም፣ የ9,7 ሚልዮን ሰዎች ህይወት አሁንም አደጋ ዉስጥ መሆኑን የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ መስሪያ ቤት፣ በምህፃሩ «ኦቻ» ትንንት ባወጣዉ ዘገባ አመልክተዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ስፖርት፤ ኅዳር 12 ቀን፣ 2009 ዓ.ም.

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቸልሲ የአንደኛነት ደረጃውን ቅዳሜ ዕለት ነጥብ ከጣለው ሊቨርፑል ተረክቧል። ልዩነታቸው ግን የአንድ ነጥብ ነው። የኢትዮጵያ ፕሬሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተከናውነዋል። ኃያሉ ባየር ሙይንሽን በቦሩስያ ዶርትሙንድ ድል ተነስቷል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የኦባማ ስንብት፤ የዓለም መሪዎች መልዕክት

የፖለቲካ ተንታኞች  እንደሚሉት ደግሞ ኦባማ በርሊን ላይ ለሰበሰቧቸዉ ለጀርመን፤ ለብሪታንያ፤ለፈረንሳይ፤ ለስጳኝና ለኢጣሊያ መሪዎች ከነገሩት ይልቅ ካስተናጋኛቸዉ ከጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት ጋር በዝግ ያደረጉት ምክክር ከፍ ያለ ሥፍራ የሚሰጠዉ ነዉ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

አጣሪ ቦርድ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ፍተሻ መጀመሩ 

በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደስአለኝ የሚመራዉ የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት 11ሽ በላይ ሰዎችን በተላያዩ እስር ቤቶችና ወታደረዊ ካምፖች ማሰሩ በቅርብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የመራሒተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል ውሳኔ

በጀርመን ፖለቲከኞች ዘንድ ለወራት የዘለቀው ግምት አሁን ትናንት መቋጫ ተበጅቶለታል። የ62 አመቷ የጀርመን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለውድድር ይቀርባሉ
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሜርክል ለ4ኛ የስልጣን ዘመን መወዳደር ይሻሉ

የጀርመኗ መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለአራተኛ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ ተናገሩ። አንጌላ ሜርክል ለወግ አጥባቂው ክርስቲያ ዴሞክራቶች ፓርቲ አባላት በሚቀጥለው ዓመት በሚካሔደው ምርጫ ለመወዳደር እንደሚፈልጉም ገልፀዋል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ኢትዮጵያ፤ ተቃዉሞዉ እና አስተምሕሮቱ

በርግጥ ሕዝብ ተረጋግቶ የዕለት ከዕለት ሥራዉን የሚያከናዉንበት ሠላም ሰፍኗል? ዓመት የደፈነዉ ተቃዉሞ፤ የመንግሥት እርምጃዎች፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎችስ ምን ዉጤት አመጡ።ጥቅም፤ ጉዳት አስተምሕሮቱንስ?
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

16ኛው ታላቁ ሩጫ

42 000 ሰዎች የተሳተፉበት 16ኛው ታላቁ ሩጫ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሔደ። የኢትዮጵያ መንግሥት ገቢራዊ ካደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተሳተፈበት የአደባባይ ውድድር በሰላም መጠናቀቁን የዶይቼ ቬለ ወኪል ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር ከአዲስ አበባ ዘግቧል።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

ሞሮኮ በ2.3 ቢሊዮን ዶላር በድሬዳዋ ፋብሪካ ልትገነባ ነው

ሞሮኮ የማዳበሪያ ማምረቻ ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ በ2,3 ቢሊዮን ዶላር ለመገንባት ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ተፈራረመች።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የባራክ ኦባማ የበርሊን ጉብኝት

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በርሊን ጀርመን ውስጥ ከአውሮጳ ሃገራት አምስት መሪዎች ጋር ዛሬ ተነጋግረዋል። ኦባማን የሚተኩት ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጉዳይ ዋነኛ መነጋገሪያ ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የለጋሽ ሀገራት ርዳታ ለማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ

የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ጊዚያዊ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የርዳታ ድርጅቶች ከብዙ ጊዜ ወዲህ ጥሪ ሲያሰሙ ቆይተዋል። ጥሪውን ተከትሎም የአውሮጳ ህብረት ከሁለት ቀናት በፊት ባለፈው ሀሙስ በብራስልስ ከ80 የሚበልጡ ሀገራት፣ የዓለም ባንክና የተመድን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጭምር የተሳተፉበት የለጋሽ ሀገራት ጉባዔ  አስተናግዶ ነበር።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የአንድነት ፓርቲ የቀድሞው አመራር መታሰራቸው ተገለጠ

የቀድሞው የኢትዮጵያ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) አመራር አባላት እንደታሰሩ ተዘገበ።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News

የሞሮኮ የአፍሪቃ ኅብረት አባልነት ጥያቄና የድንበር ችግር

ሞሮኮ በከፊል ከግዛትዋ ከጠቀለለላቻት ከሣህራ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር የገባቸው ድኅረ ቅኝ ግዛት ንትርክ አልተቋጨም። የአፍሪቃ ኅብረት አባል ለመሆን ጥያቄ አቅርባለች።
Posted in Amharic, Amharic News, Ethiopian News, News