Blog Archives

የአማራ ክልል ፀጥታና አስተዳደራዊ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሴ አሰሜ ከሕዝባዊ አመፁ ጋር በተያያዘ ከስልጣናቸው ተነሱ።

Filed under: political opinion
Posted in Ethiopian News

ሰመራ ዩንቨርስቲ አዲስ የተሰራው እስቶር በእሳት ነደደ

ሰመራ ዩንቨርስቲ አዲስ የተሰራው እስቶር በእሳት ነደደ። ከሬጂስትራል ጀርባ የሚገኘው አዲሱ እስቶር ምንም እንኳን ከተማሪወች ዶርምታሪ የራቀ ቢሆንም መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀው የእሳት አደጋ በክፍሉ የነበሩ እያንዳንዱ እቃ በእሳት ሙሉ በሙሉ ጋይተዋል። ኮምፒተሮችን፣ የመኪና ጎማወችን፣ሰሌዳውችን፣ የፅህፈት መሳሪያወችንና መሰል የዩንቨርስቲው ንብረቶችን የያዘ ነበር። ዕለተ ሐሙስ ከምሽቱ 2 ስዓት እስከ 5 ሰዓት የዘለቀው የእሳት አደጋ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ […]
Posted in Ethiopian News, News

ኮ/ል ደመቀ ከአርበኞች ግንቦት 7 ትእዛዝ በመቀበል አገርን በማወክ ክስ ተመሰረተባቸው

ኮ/ል ደመቀ ከአርበኞች ግንቦት 7 ትእዛዝ በመቀበል አገርን በማወክ ክስ ተመሰረተባቸው በአዲስ አበባ የሚገኘው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማክሰኞ በ18 ቀን 2009ዓም በዋለው ችሎት በኮሎኔል ደመቀና በአስራ ሶስት (13) የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ላይ አቃቤ ህጉ ያቀረበውን የክስ መዝገብ ተመልክቷል። ከአርበኞች ግንቦት 7 ቀጥታ ትእዛዝ በመቀበል ሃገሪቷን አውከዋል በማለት ወያኔ በአቃቢ […]
Posted in Ethiopian News, News

ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው – የሜቴክ ጉድ አይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጥጦ ከች ብሏል።

ጉደኛው ኢህአዴግ በስኳር ፋብሪካዎች ላይ ያለውን አቋም መሰረታዊ በሆነ መልኩ መቀየሩን የዛሬው የፋና ዜና ገልጿል። የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ መጓተት ያስከተለውን ምስቅልቅል ሜቴክም ሆነ ኢህአዴግ ሊደብቁት ከማይችሉበት ደረጃ ደርሷል። የስኳር ኮርፖሬሽኑ ቃል አቀባይ እንደሚሉት ከሆነ ለግንባታዎቹ መጓተት ምክንያቶቹ ሁለት ናቸው። 1ኛው የኮንትራት አስተዳደር ችግር ፣2ኛው ደግሞ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር። የነዚህን ፕሮጀክቶች ሂደት ከመጀመሪያው ጀምሮ ለተከታተልን ሰዎች […]
Posted in Ethiopian News

የኢትዮ ቴሌኮም የኔት ወርክ መቆጣጠሪያ ኮምፒውተር ሐክ ተደረገ::

በኢትዬጵያ ቴሌ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን መስሪያ ቤትና በብሄራዊ ደህንነቱ አይቲ ኢንጂነሮች ቁጥጥር ስር የሆነው የኔት ወርክ መቆጣጠሪያ ኮምፒውተር ሐክ ተደረገ:: ድንገተኛው የኮምፒውተር ሐክ እርምጃ የቴሌኮሚንኬሽኑን ሰርቨር ከአገልግሎት ውጭ በማድረጉ ምክንያት በአዲስ አበባና አካባቢው ላልተወሰነ መጠነኝ ሰሀት የሞባይል ግንኙነትና የኔት ወርክ አገልግሎት እንዲቋረጥ ሰበብ ሆኗል:: የሚፈለጉ የብሄራዊ መረጃው የመረጃ ዳታዋች የተጠለፉ ግንኙነቶችና የመግቢያ ሚስጥራዊ ኮዶች ላይ ያነጣጠረ […]
Posted in Ethiopian News, News

ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ለሁለተኛ ጊዜ ተጨማሪ የ28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተሰጦታል።

የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ለሁለተኛ ጊዜ በፖሊስ የተጠየቀን የተጨማሪ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ሃሙስ ፈቀደ። ምርመራውን እያካሄደ የሚገኘው ፖሊስ ዶ/ር መረራ በሽብር ወንጀል ድርጊት ስለመሳታፋቸው የተለያዩ ምርመራዎችን እያካሄደ መሆኑን ለችሎቱ ማስረዳቱን አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ዘግቧል። ቀደም ሲል ፖሊስ ዶር መረራን ያሰራቸው አስቸኳይ አዋጁን ተላልፈዋል በሚል የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ምርመራው የሽብር […]
Posted in Ethiopian News, News

የህወሀት አንድ ሽምበል ኮማንድ ፓስት ተደመሰሰ::

አዘናግቶና አድብቶ ከጀርባ በመምታት የነፃነት ሐይሎችን ለመደምሰስ ከአል-ቀዳሪፍ ወደ ሁመራ እና አካባቢው የተነቃነቀው 400 የሚጠጋ የህወሀት ቅጥረኛ ሰራዊት መሽገው ከነበሩ የነፃነት ሀይሎች ጋር የገጠመውን ድንገተኛ ውርጅብኝ ለመመከት ባደረገው ማፈግፈግ ከሌላኛው የህወሀት የጦር ቀጠና በመግባቱ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ከ 24 ተኛ ክ/ጦር የውስጥ አርበኞች የደርሰን መረጃ አመለከተ:: የህወሀት ወታደራዊ ኮማንደሮች ክስተቱ ሆን ተብሎ የተቀናበረ ነው በሚል […]
Posted in Ethiopian News, News

የአርበኛ ጎቤ ቤተሰቦች ለሕወሃት “አስታርቁኝ” ጎትጎታ የሰጡት ምላሽ፣

ሕወሃት “ከጀግናው አርበኛ ጎቤ ጋር አስታርቁኝ” በማለት የጎቤ ቤተሰቦችን በማሸገር ላይ መሆኑን የጎንደር ህብረት ሪፖርተር “ዞብል” ከጎንደር ዘግቧል። አርበኛ ጎቤ ሕወሃት የወልቃይት የአማራ ማንነት እና የነጻነት ጥያቄ ባነሱ ዜጎች ላይ በወሰደው ግድያ፣ እስራት እና ድብደባ ተማረው ሕወሃትን እስከወዲያኛው ለማስወገድ ቆርጠው በመነሳት ዱር ቤቴ ካሉት አርበኞች (የነጻነት ታጋዮች) መካከል አንዱ ናቸው። ሕወሃት በአርበኛ ጎቤ የሚመራውን እና […]
Posted in Ethiopian News, News

ስለ ነፃነታችን ከጎናችን የሚቆም ኃይል ሁሉ ወገናችን ነው ።

በትላንትናው እለት የግብፅ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የቀረበበትን ክስ በይፋ መልስ እንደሚሰጥ አስታወቀ የሚል ዜና በኢሳት ሰማሁ እናም የግብፅ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ላለው የዲፕሎማቲክ ግንኙነት የራሱን አካሄድ መከተል የራሱ ጉዳይ መሆኑን አምናለሁ ሆኖም ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ግን ከወያኔ ጋር የሚያብር ሁሉ የኢትዮጵያ ጠላት እንጂ ወዳጅ እንዳልሆነ እናምናለን ። ወያኔ ሲጀመር የኢትዮጵያ መንግሥት ሳይሆን ኢትዮጵያን […]
Posted in Ethiopian News

በጣና ግልገል በለስ ዘር ማጥፋት ፕሮጀክት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ አማራ ሊፈናቀሉ መሆኑ ተነገረ

በፋሽስት ህወሃት በውሃ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚ/ር የአማራን ህዝብ በስልታዊ መንገድ ለማጥፋት እና የትግራይ ተወላጆችን በስልታዊ መንገድ ለማስፈር ታቅዶ የተቀረጸው የጣና ግልገል በለስ ፕሮጀክት የትግራይ ተወላጆች የሚያስተባባብሩትና ከትግራይ በመጡ ሰራተኞች ሚከናወን ሲሆን ይህም ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የአማራን ህዝብ ከለም መሬቱ የሚያፈናቅል፣ለአስከፊ ችግር የሚጥል እና በምትኩ በሰራተኝነት ሽፋን የትግራይ ተወላጆችን በአካባቢው የሚያሰፍር ይሆናል።ለዚህ ፕሮጀክት ስኬታማነት የፋሽስት ህወሃት አሽከር […]
Posted in Ethiopian News, News

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እጅግ ታሞል ተባለ

በዝዋይ ባቱ ሆስፒታል የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁል ዛሬ ታህሳስ 18/09ዓ.ም ተመስገን ታሞ በአንፖላንስ ወደ ሆስፒታሉ እንደመጣ ነው፡፡ የእስር ቤቱ ወታደሮች ወደ ሆስፒታል ይዘውት ሲገቡ ቀደመው በአቅራቢያው የነበረውን ሰው ከቦታው ዙር እንዲሉ ስላደረጉ የተመስገንን የህምም ደረጅ ቀረብ ብሎ ማየት አልተቻለም፡፡ተመሰገን በእስትሬቸር እየገፉ ወደ ሆስፒታል ውስጥ አንደስገቡት ለማወቅ ችለናል፡፡አሁን ከቀኑ 8፡10 ሆናል እስካሁን ተመስገን በዝዋይ ባቱ ሆስፒታል ይገኛል:: […]
Posted in Ethiopian News, News

የወያኔ አስተዳደር በአለም እጅግ አደገኛ ከሚባሉት 19 አገሮች ተርታ ተመደበ

በለንደን የሚገኘው ሌጋተም ኢንስቲትዩት (Legatum Institute) በሚያደርገው አመታዊ የጥናትና የምርምር ፕሮግራሙ በአለማችን የሚገኙ እጅግ ሃብታምና ለኑሮ አመቺ አገሮችን እንዲሁም በተቃራኒው እጅግ አደገኛ የሆኑትንም ዝርዝር ይፋ ያደርጓል። ይህ ተቋም ዘጠኝ (9) ቁልፍ መስፈርቶችን በመጠቀም በ2016 እኤአ የአገራትን ብልጽግና እና ለኑሮ ተሰማሚነታቸውን በጥናትና ምርምር በተደገፈ ሁኔታ አቅርቧል። እነዚህ መስፈርቶች የሚያካትቱት የኢኮኖሚ ጥራትን፣ የንግድ አከባቢን፣ አስተዳደርን፣ ትምህርትን፣ ጤናን፣ […]
Posted in Ethiopian News, News

የሳምንቱ አበይት ዜናዎችና ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮችን የምንዳስስበት የሬዲዮ ዝግጅት ያዳምጡ

ኮሎኔል ደመቀን አናስወስድም ባሉ እስረኞች ላይ ወያኔ ኢሰባዊ ድርጊት የፈፅመ ነው ተባለ ጎንደር ከተማ  አንገረብ እስር ቤት አሁንም ውጥረቱ እንደተባባሰ ቀጥሏል የተባለ ሲሆን። ኮሎኔል ደመቀን አናስወስድም ባሉ እስረኞች ላይ እስከ እረፋዱ ድረስ የዘለቀ ተኩስ ተከፍቶባቸዋል። ስለደረሰ ጉዳት እስካሁን የታወቀ ነገርባይኖርም የተገደሉ እስረኞች ስለመኖራቸው ይነገራል ። ሰሜን ሸዋ መራህቤቴ አካባቢ መሳሪያቸውን ሊገፍ የሄደን የወያኔ ቅጥረኛ ድባቅ […]
Posted in Ethiopian News

አዲስ አበባ በ24 ሰአታት ውስጥ ሶስት የተለያዩ ቦታዎች የእሳት አደጋዎች ተከሰተ

ዲስ አበባ ከወትሮ ለየት ባለ ሁኔታ በሶስት (3) በተለያዩ ስፍራዎች 24ሰአት በልሞላ ሰአት ውስጥ አስተናግዳለች። የእሳት አደጋው በንብረት ላይ ከፍተኛ ጎዳት አድርሷል። ከመረጃዎች መረዳት እንደሚቻለው በአብዛኛው የንግድ ሱቆች በእሳት አደጋው ወድመዋል። የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለስልጣን የኮምንኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ እንደገለጹት አደጋው የተከሰተው በዋናው ፖስታ ቤት በአራዳና በጉለሊ ክፍለ ከተማ እንደሆነ […]
Posted in Ethiopian News, News

ጄግናው ኮረኔል ደመቀ በአንድ ክፍል በእግር ብረት መታሰሩ ታውቋል።

የእኛ ኩራት እንኳን እግረ ሙቅ ሌላም ነገር የአንተን ጽናት አያደክመውም። ትዝይልሀል? ሐምሌ አምስት በአራት አቅጣጫ ያፈነህን የወያኔ ሰራዊት እየተዟዟርክ አንዱ እንደ አራት ሰው ዙሪያህን በመመከት በጎንደር ከተማ ዘልአለማዊ የጄግና ተጋድሎ ያደረግከው? ነ ይህ መንግስት ሲያልፍ የአንተ የተጋድሎ ታሪክ በወርቅ ብእር ደምቆ ነገ ይጻፋል፣ እንደ አጼ ቴዎድርስ ትውልድ እየተቀባበለ ጄግንነትክን ይማርበታል። ጎንደር ከተማ የክፉ ቀን መጠጊያህ […]
Posted in Ethiopian News, News

ህወሃት በአማራ ክልል የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን ወደ ትግራይ በመውሰድ ልዩ ስልጠና እየሠጣቸው እንደሆነ ታወቀ።

በአማራ ክልል የተለያዩ የመንግሥት መሥሪያቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ በሃላፊነትና በአመራር ቦታዎች ተመድበው በመሥራት ላይ ለሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ትውልድ መንደራቸው ዋና ከተማ መቀሌ ውስጥ ልዩ ሥልጠና ተዘጋጅቶ በመሠጠት ላይ እንደሚገኝ ከውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ አጋለጠ። ከታህሳስ አንድ ቀን ጀምሮ ከሚሠሩባቸው የአማራ አስተዳደር ከተሞችና ዞኖች ወደ መቀሌ በመጓጓዝ ስልጠናውን እንዲወስዱ ለተደረጉ ለነዚህ ሠልጣኞች መንግሥት እንደሚገኙባቸው ቦታዎች […]
Posted in Ethiopian News, News

የአፈናውና ሰቆቃው መጠናከር ለነጻነታችን ከምናደርገው ትግል አይገታንም።

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሳምንታዊ ርዕሠ አንቀጽ ================================= የመንግሥትን በትረ ሥልጣን በጠመንጃ ሃይል ተቆጣጥረው ያሉት የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ላለፉት 25 አመታት በህዝባችን ላይ ተንሰራፍተው የዘረፉት የአገር ሃብት ፤ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ በየባንኩ ያከማቹት ጥሬ ገንዘብና በዘመድ አዝማዶቻቸው ሥም እዚህና እዚያ የዘረጉዋቸው የንግድ ድርጅቶች ብዛት እንዲሁም ያለዕውቀታቸውና ልምዳቸው ለሩብ አመታት ሲሿሿሙበት የኖሩት ሹመትና ማዕረግ አሁንም […]
Posted in Ethiopian News

ኮማንድ ፖስቱ እርምጃ ሊውስድባቸው የነበሩ ወገኖች የነጻነት ሀይሎችን መቀላቀላቸው ታወቀ::

በሳሞራ ይኑስ ክርን ውስጥ በኮማንድ ፓስቱ ቀኝ ግዛት ስር የወደቀው የሀገራችን ብሔራዊ ልእልና ወደ ለየለት ውንብድናና ነፍሰ ገዳይነት ከተሸጋገረ እንሆ ሰንበትበት ብሎአል በዚሕም የተነሳ በሰሜን ጎንደር፣ በደቡብ ጎንደር፣በባሕር ዳር፣ በሐረር በተለያዩ ስፍራዋች በወለጋ፣ በኦጋዴን፣ በያቤሎ በተለያዩ የሸዋ ወረዳዋች፣ በአዲስ አበባ እና በመሳሰሉት ክልሎች ላይ በሞት እንዲወገዱ ውስጣዊ ትእዛዝ የተላለፈባቸው 3014 ኢትዮጵያዊያን መካከል 2018 ይህሉ እራሳቸውን […]
Posted in Ethiopian News, News

የወያኔ አገዛዝ የስልጣን መሰረቱ እተናደ ነው ።

የአማራ ክልል ባለስልጣናት በወያኔ ኮማድ ፖስት ላይ ተቃውሞ አሰማ።በሰበብ አስባብ ሰዎችን በማሰር የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ ሲጠየቅ የኮማንድ ፖስት መልስ ከስልክ መረጃ ስለ ተገኘ ሊፈቱ አይችልም የሚል ስለሆነ የክልሉ አመራር እኛን እያታለላችሁ ሰውን ካሰራችሁ በኋላ ያሰራችሁትን ሰው እንድትፈቱ ስትጠየቁ መልሱ ይህ ከሆነ አብረን ልንሰራ አንችልም የሚል ተቃውሞ በቀበሌ አመራሩና ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንደገጠመው የተገኘው መረጃ አመልክቷል ። […]
Posted in Ethiopian News, News

የአምቦ ተማሪዎችን ተቃውሞ ተከትሎ በኦሮሚያ አዲስ ውጥረት ነግሷል።።

ህወሃት እስረኞችን “አሰልጥኜ” አስመረኩ አለ፤ እስረኞቹ “ በፍፁም፣ አይደገምም፣ የቀለም አብዮት፣ ህገ መንግስት እና የኢትዮጵያ ህዳሴ” የሚሉ ኮርሶች የወሰዱ ናቸው። ህወሃት አምስት ሺህ የሚጠጉ እስረኞችን “ተመራቂዎች” በሚል መፍታቱን ይፋ ባደረገበት ቀን በተመሳሳይ አምቦ ተማሪዎች ተቃውሞ ማሰማታቸው ተሰማ። በአምቦ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዶ\ር መረራ ጉዲና አቶ በቀለ ገርባና የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የተቃውሞ ትእይንት አደረጉ። በጊንጪ፣ […]
Posted in Ethiopian News, News

በኦጋዴን በተቀሰቀሰው ጦርነት የወያኔ 8 ወታደሮች መገደላቸው ተሰማ

የገዢው የህውሃት ወታደሮች በኦጋዴንም ጦርነት ተከፍቶባቸዋል። የኦጋዴን ነጻ አውጪ ዜና ኤጄንሲ እንደዘገበው በወያኔና በኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ሰራዊት መካከል ጠንከር ያለ ጦርነት ተካሂዷል። ግንባሩ ባለፈው ሃሙስ በኦጋዴን ቃብሪዳህር ወረዳ ዲሞዲሊ መንደር ውስጥ የህወሃት ኢህአዴግ ታጣቂዎች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ እንደተለመደው የጅምላ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና እስራት መፈጸማቸውን ተከትሎ ግንባሩ ከተጠቂዎቹ ጎን በመቆም አጸፋዊ ምላሽ መውሰዱን አስታውቋል። በሁለቱ […]
Posted in Ethiopian News, News

ኦሮምያ ክልል ጂማ ዞን የሊሙ ሰቃ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ብዙ ሰዎች እየታሠሩ መሆኑን ተናገሩ

ለእሥረኞቹ ስንቅና የጤና አገልግሎት እንደማይደርስ ሌሎችም የበረቱ ችግሮችን እየተጋፈጡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ቁጥሩ ከሃያ በላይ ሰው ታጉሮበታል ያሉትን የእሥር ሁኔታ ቪኦኤ ያነጋገራቸው ነዋሪ ከመቃብር ቤት ጋር አመሣስለውታል፡፡ ሰዎቹ የታሠሩት “በተራ ወንጀል አይደለም” ያለው የሊሙ ወረዳ ፖሊስ የተያዙትም በኮማንድ ፖስት እንደሆነ ገልጿል፡፡ የወረዳው ፖሊስ ኮማንደር ኢንስፔክተር ተሰማ እንግዳ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ሰዎቹ የታሠሩት መንግሥት ያወጣውን ሕግ በመተላለፍ፣ […]
Posted in Ethiopian News

በኮምማንድ ፓስቱ ቁጥጥር ስር የወደቀው የሰሜኑ እዝ ወደ ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር የላካቸው ወታደሮች አይመለሱም ተባለ

በኮምማንድ ፓስቱ ቁጥጥር ስር የወደቀው የሰሜኑ እዝ ወደ ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር የላካቸው በወታደራዊ ደህንነት እና በወታደራዊ ምህንድስና የተሰማሩ አባላቶች መገደላቸውንና መሰወራቸውን ለኮማንድ ፓስቱ በላከው ሪፖርት ለማወቅ ተችሎአል:: በሪፓርቱ መሰረት 1. ወታደር መሀንዲስ ትህትና በለው 2. ወታደራዊ የደህንነት አባል ቃሲም ይማም 3. ወታደር መሀንዲስ ዝናቡ ሕንጻ 4. ኮማንደር ማንያዝ ገብሬ 5. ወታደር ማሀንዲስ ቃቄ የደረሱበት […]
Posted in Ethiopian News, News

በጎጃም ጃዊ የአማራውን ተጋድሎ ለማፈን ሕወሓት 2 ታንኮችን ተጠቀመ | አንዱ ወድሟል እየተባለ ነው – ውጥረቱ አይሏል

ሰሞኑን 60 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መቃጠሉን ተከትሎ ውጥረቱ እየተባባሰ በመጣባት ጃዊ የአማራ ታጋዮች ከትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ጋር ትናንት እና እና ዛሬ ሲዋደቁ መዋላቸው ተሰማ:: የዘሐበሻ ምንጮች እንዳሉት የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት የአማራው ታጋዮችን ለማጥፋት 2 ታንኮችን የተጠቀመ ሲሆን አንደኛው ታንክ በአማራው ታጋዮች እንደወደመ እየተነገረ ነው:: የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት የጃዊ አርሶ አደሮችን መሬት ካለምንም […]
Posted in Ethiopian News, News

በአማራ ክልል እሁድ ዕለት ሦስት ወጣቶች መገደላቸው ቤተሰቦቻቸውና ነዋሪዎች ገለጹ

አቶ ዘውዱ ገብረማርያም እና አቶ ሙላው ከበደ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በመተማ አቶ ባህሩ ይታየው የተባለ ደግሞ በጎንደር ከተማ እሁድ ዕለት መገደላቸውን ነዋሪዎችና ቤትሰብ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል። የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ተገደሉ ስለተባሉት ወጣቶች ለጊዜው ከአካባቢው ርቀው ስለሚገኙ “መረጃ የለኝም” ብለዋል። በአማራ ክልል በመተማ ሁለት የወልቃይት ተወላጆች፣ በጎንደር ከተማ ደግሞ አንድ የማክሰኝት ከተማ ተወላጅ በድምሩ ሦስት […]
Posted in Ethiopian News, News

በጋምቤላ ክልል ሰፋፊ የእርሻ መሬት የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አልታወቀም ተባለ

በጋምቤላ ክልል በኢንቨስትመንት ስም ተመዝግበው ሰፋፊ የእርሻ መሬትን የወሰዱ 29 ድርጅቶች የገቡበት አለመታወቁን ከክልሉ መሬት አሰጣጥ ጋር ተፈጥሯል የተባለን ችግር እንዲያጠና የተቋቋመ ቡድን ይፋ አደረገ። ከአንድ አመት በላይ ጥናቱን ሲያካሄድ የቆየው ይኸው ቡድን በጋምቤላ ክልል ለኢንቨስትመንት ከተሰማሩ 623 ባለሃብቶች መካከል ለ381 ባለሃብቶች የተሰጠው ከ45ሺ ሄክታር በላይ መሬት ተደራርቦ እንደተሰጣቸው ተመልክቷል። የተደራረበ መሬት የተረከቡት እነዚሁ 381 […]
Posted in Ethiopian News, News

አቶ ዘለሌ ፀጋስላሴ አርበኞች ግንቦት ሰባትን ለቀቀ ተብሎ የተወራው የውሸት የነቤተ አብዋራ ወሬ ነው ተባለ

በ2002 ምርጫ ኢትዮጵያን ለቆ የተሰደደው፡ ግንቦት ሰባትን በሱዳን እያደራጀ እንደነበር በሃገር መክዳት ክስና ምስክር የቀረበበት፡ የቀድሞው ኢዴአፓ ሊቀመንበር፡ የስዊድን የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ግንቦት ሰባትን በይፋ መልቀቁ እየተነገረ ነው መባሉ ትልቅ ውሸት የወያኔና የወያኔ ባንዳዎች ወሬ ስለመሆኑ ተነግራል አቶ ዘለሌ ፀጋሥላሴ የስውዲን የግንቦት 7 ሰብሳቢ ከተወራው ድርጅቱን መሠናበት ጋ ምን ይላል ? ጥቅሙ ምን ይሆን ? […]
Posted in Ethiopian News, News

ጎንደር አንገረብ እስር ቤት አዲስ ደባ እየተፈፀመ ነው!

ጎንደር አንገረብ እስር ቤት ከኮሎኔል ደመቀ ጋር የነበሩ እስረኞች በሁለት መኪኖች ተጭነዉ በዛሬው ሌሊት ወደ ኮምቦልቻ ተወሰዱ። ኮሎኔል ደመቀን በሃይል ለመውሰድ የሚመጡትን የትግራይ አፋኝ ቡድኖች በመከላከል የአንገረብ እስረኞች ከፍተኛውን ሚና መጫወታቸው ይታወቃል። ለዚህም የህይወት መስዋእትነት የከፈሉ ጀግኖች ብዙ ናቸው። ስለሆነም ወያኔ እንደ አዲስ የነደፈው እቅድ እስረኞችን ወደሌላ ቦታ በመውሰድ የሚገጥማቸውን ከባድ ተቃውሞ ማመንመንና ብሎም አፈና […]
Posted in Ethiopian News, News

ጎንደር ዛሬም ከወያኔ አፋኝ ሰራዊት ጋር ፍጥጫ ላይ ነች፥

አንገረብ እስር ቤት የሚገኘውን ኮሎኔል ደመቀን ወያኔዎች እንወስዳለን፥ የጎንደር ሕዝብ ዓናስወስድም በማለት አንገረብ ዙሪያ በሰነበተው ግርግር፥ ትላንት ሌሊት አንገረብ እስር ቤት በከባድ መሳሪያ ተከባ የጎንደር ገበሬዎች በውጭ ሆነው የተኩስ ሽፋን እየሰጡ፥ በእስር ቤቱ የሚገኙት ታራሚዎች በውስጥ እየተፋለሙ ከፍተኛ ግብግብ እንደነበረ መረጃዎች ያመለክታሉ፥ በእስረኞቹ ላይ አስለቃሽ ጋዝ ስለጣሉባቸው ብዙ ሰው እንደተጎዳ የሞቱም እንዳሉ ተገምቷል፥ ኮሎኔል ደመቀም […]
Posted in Ethiopian News, News

ሕወሓት በወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ላይ አስከ ሞት የሚያስቀጣ ክስ መሰረተባቸው።

የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በሚባል ሽፋን በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መሪነት በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች፣ ታኅሳስ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሠረተባቸው የሰሜን ጎንደር ከተማ ነዋሪዎች አቶ መብራህቱ ጌታሁን፣ ጌታቸው አደመ፣ አታላይ ዛፌና […]
Posted in Ethiopian News, News

ኮ/ል ደመቀ ዘዉዱን ከጎንደር አንገረብ ማረሚያ ቤት በአጋዚ ልዩ ኮማንዶ አስገድዶ በጨለማ ለመዉሰድ ግብግብ ላይ ነው።

ወያኔ በአሁኑ ስዓት [እሁድ ታህሳስ 9 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከቀኑ 12፡00] ኮ/ል ደመቀ ዘዉዱን ከጎንደር አንገረብ ማረሚያ ቤት በአጋዚ ልዩ ኮማንዶ አስገድዶ በጨለማ ለመዉሰድ ግብግብ ላይ ነው። ታራሚዉ «ኡኡ!» በማለት አንደኛዉን በር ሰብሮ ወጥቷል፤ ኮሎኔሉንም ከበዉ ይዘዋል። ይህን ስራ ለመስራት ከቀናት በፊት ኮ/ሉን ከዋናዉ ታራሚ ለይተዉ ለብቻዉ አንድ ክፍል እንዲቀመጥ ትዕዛዝ ሰጥተዉ ነበር፤ ሆኖም እሱም ታራሚዉም […]
Posted in Ethiopian News, News

በትግራይ ምድር በሚገኙ ዩኒቨርሲቲወች በአማራና ኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየተፈፀመባቸው ነው!

በአዲ ግራት ዩኒበርስቲ ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ መብራት የለም፤ ይህንን የጨለማ አጋጣሚ ተገን በማድረግ በእራት ሰአት ጊዜ የትግራይ ተማሪወች በተጠናና በተደራጀ ሁኔታ ወደ አማራና ኦሮሚያ ልጆች መመገቢያ ሳህንና ወንበር በተደጋጋሚ እየወረወሩብን እና እየደበደቡን ይገኛሉ፤ በዚህ ያልተመለሱት የህወኃት ተከታዮች ከፕሬዘዳንት እስከ ተማሪ ህብረት ያሉት የትግራይ ተወላጆች የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ በአማራ ተማሪወች ላይ እስከ መባረር የደረሱ፣ ፒሲ የተቀሙ፣ […]
Posted in Ethiopian News, News, Politics

የነጻነት ችቦው ከዳር እስከዳር ተቀጣጥሏል።

ጀግና አርበኛ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተንስ! የህዝቡን የኣምቢተኝነት ትግል ከወያኔ ኣረመኔያዊ ጥቃት ተከላከል!! ራስህን ኣደራጅ! ታጠቅ! ወያኔዎችና ነፍሰ ገዳዩን ኣጋዚን ኣድብተህና ኣድፍጠህ በሁሉም ቦታ ምታቸው! የሕዝብ ትግል በመላው ኢትዮጵያ ከተቀጣጠለ ወያኔ ዘረኛ ፋሽስት በኣጋዚ ነፍሰ ገዳዮቻችው ሁሉንም ሊያፍኑ ሁሉንም የኢትዮጵያ ኣካባቢዎች ሊቆጣጠሩ ከቶውኑ አይችሉም። በየቦታቸው ያንተ ጥቃት ሲመታቸው፣ የህዝብ ብትር ሲያደማቸው በይቦታው ሲመቱ ፣ የአጋዚ ነፍሰ […]
Posted in Ethiopian News, Politics

የጎንደር የ12ቱ ክፈለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ወስጥ 8ቱ ሲታገዱ 4ቱ ታስረዋል።

ወያኔ የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፍቶበታል። በጎንደር ከተማ ትናንት ሌሊት የነበረውን ከባድ ተኩስ ምክንያት አድርጎ ወያኔ ወጣቶችን እያፈሰ እያሰረ ነው። በሰላም ሰርተው የሚኖሩ ወጣቶችን ማሳደዱ ሁላቹህም ጫካ ግቡ ብሎ ማወጅ ነው ብለውታል የጎንደር ወጣቶች። አንድ አካባቢ ተደራጅተው የኮብል ስቶን ስራ ላይ ቆይተው ሲመለሱ 6 ወጣቶች እንደታፈኑና ወደ እስር እንደተጋዙ የአይን እማኞች ገልፀዋል። በጎንደር በተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት የቅስቀሳ […]
Posted in Ethiopian News, News

ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያለው ትብብር እንዲቀጥል የፕ/ር መራራ ሁኔታ ማብራርያ ተጠየቀ!!

በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት ምካከል ያለው መልካም ትብብር እንዲቀጥል የፕ/ር መራራ ጉዲና ሁኔታና ስለ ተከሰሱበት ጉዳይ ግልፅ ማብራርያ እንዲሰጣቸው የህብረቱ ም/ቤት ፕሬዘዳንት ለኢትዮጵያው ፕሬዘዳንት በፃፉት ደብዳቤ አሳወቁ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት ፕሬዘዳንት የሆኑት ሚስተር ማርቲን ሹልስ ለኢትዮጵያው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በጻፉት ደብዳቤ ዶ/ር መራራ ጉዲና ባለፈው ወር ብራስልስ እንደነበሩና በቆዩበትም ጥቂት ቀናት ከህብረቱ የፓርላማ አባላት ጋር […]
Posted in Ethiopian News, News

ወያኔ በጎንደር የወረዳና የቀበሌ አመራሮችን ማሰር ጀመረ

በጎንደር ያለው አለመረጋጋት አሁንም እንዳየለ ሲሆን በ አማራ ታጋዮች እና በትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮችና ተላላኪዎቹ መካከል የሚደረገው የሞት ሽረት ውጊያም እንደቀጠለ ነው። በጎንደር ህዝብ ላይ እምነት ያጣው የትግራዩ መንግስት በዚህ ሳምንት ታቦት ይዘን አንወጣም ሃይማኖታችንን ለፖለቲካ መጠቀሚያ አናረክስም ያሉ የሃይማኖት አባቶችን አፍሶ ማሰሩን ዘሐበሻ የዘገበች ሲሆን ዛሬ የተሰማው መረጃ እንደሚጠቁመው ደግሞ ሕወሓት በጎንደር ያሉ የወረዳና […]
Posted in Ethiopian News, News

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ እጁን በሚያስገባ በሩስያም ሆነ በማንኛውም የውጭ አገር መንግሥት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስጠነቀቁ።

“የምርጫ ሂደታችንን ክብር የሚነካ አንዳች ነገር ሲፈጸም፣ እርምጃ መውሰዳችን የግድ መሆኑ፣ የሚያጠያይቅ አይመስለኝም” ብለዋል የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ። “በእርግጥም እናደርገዋለን” በማለት ሃሳባቸውን አጠናክረዋል፣ ሚስተር ኦባማ ዛሬ ጧት ኤንፒአር ለተባለው ራዲዮ በሰጡት ቃል። አንዳንዶቹ እርምጃዎቻችን ግልፅና ሕዝብ የሚያውቃቸው ወይም የሚሰማቸው፣ ሌሎቹ ደግሞ በተቃራኒ የሚወሰዱ እንደሚሆኑ ነው ፕሬዚዳንቱ ያስገነዘቡት። የሩስያ የኢንተርኔት ሰርጎ ገቦች፣ በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንታዊ […]
Posted in Ethiopian News

ኢትዮጵያና ኬንያ ላሙ ወደብን በጋራ ለማልማት ያቀዱት የ22 ቢልዮን ዶላር ፕሮጄክት የገንዘብ እጥረት ገጠመው

ኢትዮጵያና ኬንያ ከአራት አመት በፊት የኬንያ – ላሙ ወደብን በጋራ ለማልማት ያቀዱት የ22 ቢልዮን ዶላር ፕሮጄክት የገንዘብ እጥረት አጋጠመው። የኬንያ ባለስልጣናት በአፍርካ ግዙፍ እንደሆነ ብዙ የተነገረለት ይኸው ፕሮጄክት እስካሁን ድረስ በተጠበቀው መጠን ተግባራዊ አለመደረጉ ስጋት እያሳደረ መምጣቱን በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ዘስታር የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ አርብ እልት ዘግቧል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና የኬንያው የቀድሞ ፕሬዚደንት […]
Posted in Ethiopian News, News

ጋምቤላ ልጆቿ በጥይት የተጨፈጨፉበት ምክንያት ይፋ ሆነ!

የካሩቱሪ መሬት ለትግራይ “ባለሃብቶች” ሊሰጥ ነው ዜናውን “መገጣጠም” ሲሉ በቁጭት ይገልጹታል። የትግራይ “ባለሃብቶች” በጋምቤላ መበደላቸውን ለውጭ አገርና ለአገር ውስጥ መገናኛዎች ያስታወቁበት ዕለትና የአኙዋክ ምስኪኖች በምድራቸው በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን ተሳሳመ። ደም እንደጎርፈ በፈሰሰበት፣ ንጹሃን እንደ እንስሳ የተቀሉብት ቀን ተዘንግቶ በሙታን ዱካ ተተክተው “ተበደልን” ያሉ የብሶት ዜና ተሰማበት – ታህሳስ 4፤ 2009 (ዲሴምበር 13 ቀን 2016)። ታህሳስ […]
Posted in Ethiopian News

በጎንደር ከተማ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

ማምሻዉን በጎንደር ከተማ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። ወጣቶችን ለማሰር የተንቀሳቀሱ የአገዛዙ ታጣቂዎች መንገድ ላይ በከፋኝ ታጣቂዎች በደረሰባቸው ጥቃት ሶስት ወዲያዉኑ እንደተገድሉና በርካቶች ቆስለው ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ ነው እየሰማን ያለነው። በአገዛዙ ታጣቂዎች ላይ የተወሰደዉን እርምጃ ተከትሎ አገዛዙ እጅግ በጣም በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችን ወደ ከተማዋ አስገብቷል። አንዳንድ ወገኖች እንዲህ አይነት ዜናዎችን ስንለጥፍ “እየፈጠራችሁ፣ እየዋሻችሁ” ነው […]
Posted in Ethiopian News, News

በጅማ ዩኒቨርስቲ፤ የአማራ ተማሪዎች የኮማንድ ፖስቱ ሰለባ እየሆኑ ነዉ

አሁን በቅርቡ የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተዉ፤ በጅማ ዩኒቭርሲቴ በክፍል ተጠሪነትና በተማሪዎች መማክርት የሚያገለግሉ ተማሪዎች በኮማንድ ፖስቱ ታስረዋል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች የግቢዉ ተማሪዎች የኢሬቻን በአል መቢከበርበት ወቅት ከኦሮሞዎች ጋር አብራችሁ ተማሪዉን ለአመጽ ቀስቅሳችሁአል የሚል ሲሆን ተማሪዎቹ ግን በአመጹ ምንም እንደሌሉበት የሚገልጹ ምንጮች ብዙ ናቸዉ፡፡ የህ የሚያመለክተዉ የአማራ ተማሪዎች በየዩኒቭርስቲዉ ኢላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነዉ፡፡ ስለሆነም ተማሪዎች ባለዉ መንገድ ሁሉ […]
Posted in Ethiopian News, News

በልደታ ክ/ከተማ የመሰረት ጉድጓድ በመቆፈር ባሉ 14 ሰራተኞች ላይ የህይወትና የአካል ጉዳት ደረሰ።

በዘርይሁን ሹመቴ በኢትዮጵያ በግንባታ መስክ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሰራተኞች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ጉዳት እየጨመረ መሆኑን ታወቀ። በገዢው ፓርቲ አጽንኦት የሚሰጠው መሬትን ለባለሃብት በልማት ስም የመቸብቸብ ሂደት እንጂ በልማቱ ወይም በግንባታዎች ላይ ተቀጥረው ቤተሰባቸውን ስለሚያስተዳድሩት ሰራተኞች ደህንነት አለመሆኑ በየአመቱ ቁጥሩ እየጨመረ የሚገኘው የአካልና የነፍስ መጥፋት ጉልህ ማሳያ ነው። በቅርቡ ከአማራ ክልል በግንባታ መስክ ላይ በቀን ረዳትነት […]
Posted in Ethiopian News, News

ጎንደር ከተማ በተኩስ ስትናወጥ አደረች!

በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሌሊቱ 7 ሰዓት እስከ ንጋቱ 1 ሰዓት ድረስ ደፈጫ ወደሚባለው አካባቢ ተኩሱ አይሎ አድሯል። ዛሬ አርብ ታሀሳስ 7 ቀን የኮረኔል ደመቀ የወያኔ የይስሙላ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ቀን ነው። ተኩሱ ከዚሁ ጋር ይያያዝ ወይም ሌላ ሁኔታ እያጣራን ነው። የጎንደር ህዝብ የተለመደውን ጥበቃውንና አጋርነቱን በማሳየት ጀግናውን ተግተን መከታተልና መጠበቅ እንዳለበት ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት ወገኖች የአደራ […]
Posted in Ethiopian News, News

የወያኔ ብዓዴን ጦር ሰሜን ጎንደር አበሳውን እያየ ነው፥

የወያኔ አገዛዝ ጎንደር ላይ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ እንቢተኝነት ለማፈን አቅሙን የሚፈታተኑ ብዙ ተግዳሮቶች እንደገጠሙት እየተሰማ ነው፥ ጦር ጭኖም ሆነ በሽምግልና መልክ መርቶ የወረደ የወያኔ ብዓዴን ጦር ሰሜን ጎንደር አበሳውን እያየ ነው፥ ጎንደር ሆስፒታል በቁስለኛ ሞልቷል፥ ከዓምባጊወርጊስ እስከ አዘዞ የሚታየው የወታደር ቀብር በጥይት ሳይሆን በወረርሽኝ በሽታ ያለቀ ይመስላል አሉ። የወያኔ ስርዓት ዓንታዘዝም የሚሉ የውስጥ ሃይሎች እንደተነሱበትና በሕዝቡ […]
Posted in Ethiopian News, News

ሕግን ማክበር ያስከብራል pr መስፍን ወልደ ማርያም

“በየትም አገር፣ ሠለጠነም አልሠለጠነ፣ ሰው ሲያጠፋ በፖሊስ ተይዞ ፍርድ ቤት ይቀርባል፤ ፍርድ ቤቱ ክሱንና መከላከያውን ሰምቶና መርምሮ ፍርዱን ይሰጣል፤ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ መኖር ወደአለበት ማረፊያ ቤት ይወሰዳል፤ የወህኒ ቤት አዛዡ እስረኛውን ሲረከብ አግባብ ያላቸውን ሰነዶች በሙሉ አብሮ ይረከባል፤ ‹‹የሕግ እስረኛውን›› ለተወሰነበት ጊዜ በሕግ እየተንከባከበ ይጠብቀዋል፤ ያበላዋል፤ ያጠጣዋል፤ ለጤንነቱ የሚያስፍልገውን ሁሉ አቅሙ በፈቀደ መጠን ያደርግለታል፤ ከወዳጆቹና […]
Posted in Ethiopian News

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ሊሰጡት የነበረ መግለጫ ተሠረዘ፡፡

ትናንት፣ ረቡዕ ታኅሣስ 5/2007 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የገባው በዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ታም ማሊኖውስኪ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቡድን ዛሬ ረፋድ ላይ መግለጫ ሊሰጡ በዕቅድ ተይዞ እንደነበር ታውቋል፡፡ ፕሮግራሙ ለምን እንደተሠረዘ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለፅ አለመፈለጉን ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ሚስተር ማሊኖውስኪና የቡድናቸው አባላት […]
Posted in Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት የስለላ ተግባርን ለማከናወን የሚረዳ ቴክኖሎጂን እየተጠቀመ እንደሚገኝ ተገለጸ

የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕ ፓኬት ኢንስፔክሽን (Deep Packet Inspection) የተሰኘና የኢንተርኔት የስለላ ተግባርን ለማከናወን የሚረዳ ቴክኖሎጂን እየተጠቀመ እንደሚገኝ ተገለጸ። ቴክኖሎጂው በህጋዊ መንገድ የደህንነት ተያያዥ ስራዎችን ለማከናወን በተለያዩ አለም አቀፍ ኩባንያዎች በመቅረብ ላይ ቢሆንም፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገራት አገልግሎቱን እየገዙ ለኢንተርኔት የስለላና ቁጥጥር ስር በማዋል መሆናቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ይፋ አድርጓል። ቴክኖሎጂውን ለስለላ ተግባር እየተጠቀመ […]
Posted in Ethiopian News, News

የህወሀት ኮማንድ ፓስት የሰሜኑ አየር ሀይል ማዘዣ ና አብራሪዎች ላይ ያነጣጠረ ድንገተኛ አፈና ሊያካሄድ እንደሆነ ታማኝ የመረጃ ምንጮች አሳዉቀዋል።

የህወሀት ኮማንድ ፓስት የሰሜኑ አየር ሀይል ማዘዣ ና አብራሪዎች ላይ ያነጣጠረ ድንገተኛ አፈና ሊያካሄድ እንደሆነ ታማኝ የመረጃ ምንጮች አሳዉቀዋል። መረጃዋች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በሰሜን ጎንደር አካባቢ እየተካሄደ በሚገኘው ጀግና የአማራ ገበሬዋችና የ አርበኞች ግንቦት 7 ሐይሎች በተሰባጠረ መልኩ የከፈቱትን የህወሃት በቃን ዘመቻን ለመመከት እንዲሁም ለማጥቃት በተለይም ለእግረኛ የወይን ቅጥረኛ ወታደሮች ቅኝት እና ሽፋን ለመስጠትና ብሎም ጭራሹን […]
Posted in Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን መብት ከማቀብና ኢንተርኔትን ከመገደብ እንዲቆጠብ አምነስቲ አሳስቧል

የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን መብት ከማቀብና ኢንተርኔትን ከመገደብ እንዲቆጠብ አምነስቲ አሳስቧል የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ “ሪፖርቱ የመንግስትን ምላሽ ያላካተተ የአንድ ወገን ሪፖርት ነው” ብሎታል። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ “የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት ነፃነትን በማፈን ሰብዓዊ መብትን ገድቧል” ሲል በዛሬው ዕለት ዝርዝር ሪፖርት አውጥቷል። “የኢትዮጵያ መንግሥት ሆን ብሎ በተቀነባበረና ሕገወጥ በሆነ […]
Posted in Ethiopian News

የጎንደር ሕዝብ ትግል ከሱዳን ጠረፍ ከቋራ እስከ ታላቁ ራስ ዳሸን ተራራ ጥግ ጃናሞራ ተዛምቷል።

እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የመጣው የጎንደር ሕዝብ ትግል ከሱዳን ጠረፍ ከቋራ እስከ ታላቁ ራስ ዳሸን ተራራ ጥግ ጃናሞራ ተዛምቷል። በአርማጭሆ፣ በቆላማው ወገራ፣ በወልቃይት ጠገዴ፣ በመተማ ቋራ በገበሬወች ላይ ሲካሄድ የነበረው ውጊያ ሰሞኑን ወደ ስሜን በኩል ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልጋቸው አዳዲስ ሶስት ግንባሮች ላይ ጦርነት ተከፍቶ ፍልሚያ አለ። የተገፋው ገበሬ እራሱን ለመከላከል እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ እያደረገ ነው።… ግራ […]
Posted in Ethiopian News, News

በደባርቅ ወረዳ የቦዛ ድምብልግሳ ቀበሌ ተወላጅ የሆነዉ የልዩ ሀይል ኢንስፔክተር በዛብህ ተገደለ።

በደባርቅ ወረዳ የቦዛ ድምብልግሳ ቀበሌ ተወላጅ የሆነዉ የልዩ ሀይል ኢንስፔክተር በዛብህ ተገደለ። ከወያኔ ጋር በሚሊሽያነት የሚያገለግሉ የአካባቢው የአማራ ተወላጆች ስርአቱን እየጣሉ እየወጡ ነው። ለተቀሩትም ህዝቡ ጥሪና ማስጠንቀቂያ እያስተላለፈላቸው ነው። ወያኔ የአማራውን ህዝብ እርስ በርስ እንዲገዳደል የዶለተውን ሴራ ተገንዝበው ለወያኔ ያደሩ ሆዳሞች ከህዝባቸው ጎን እንዲቆሙ ግፊቱ አይሎባቸዋል። ለወያኔ አልታዘዝ የሚሉት ብዛታቸው እየጨመረ በመሆኑ ወያኔ ተደናግጣ ታማኝ […]
Posted in Ethiopian News, News

ደቡብ አፍሪካ ለብሄራዊ ደህንነቱ መረጃዋች በመላክ የሚታወቀው ለአለማየሁ ገ/ህይወት የሰፃፈ

ይድረስ ለአለማየሁ ገ/ህይወት .. አድራሻ ደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ተንቀሳቃሽ ስልክ… 0027843737201 አለማየሁ በአሁኑ ወቅት ከሀገር ተሰደህ ደቡብ አፍሪካ እየኖርክ ባለህበት ሁኔታ የምትደግፈዉን የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን በግፈኝነት ለማስቀጠል በብርቱ እየሰራህ እንደሆነ በተደጋጋሚ አንተ በኢንባሲ በኩል ለብሄራዊ ደህንነቱ በምትልከው መረጃዋች ለማወቅ ችለናል። አለማየሁ በተለይም ካለፉት 4 አመታት አንስቶ በርሶ የተሳሳተ መረጃ ምክንያት በዘር እና በሀይማኖት ሆን […]
Posted in Ethiopian News, News

በጎንደር ብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ በኮማንድ ፖስቱ ታስረው መፈታታቸው ተነገረ

የሰሜ ጎንደር ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ በጎንደር ኮማንድ ፖስት ትናንት ታህሳስ 4, 2009 ዓ.ም ከ9፡00 ሰዓት ታስረው የቆዩ ሆን ሕዝብ ቁጣውን ሲያሰማ ወዲያውኑ እንደተለቀቁ ሆኖም ግን ከርሳቸው ጋር አብረው ታስረው የነበሩት ሊቀ አዕላፍ ቀለመወርቅ አሻግሬ በኮማንድ ፖስቱ እንደታሰሩ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ:: አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ዞን ሀገር ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ […]
Posted in Ethiopian News, News

በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎችን ለማጥቃት አዲስ እንቅስቃሴ ተጀመረ

ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ በዞኑ የተለያዩ ግንባሮች በተደረጉ ውጊያዎች ከፍተኛ ሽንፈት የደረሰበት የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ፣ ዛሬ ረዕቡ ማለዳ ጀምሮ በርካታ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎችን ወደ ወልቃይት አሰማርቷል። አዲሱ እንቅስቃሴ የጸረ ሽምቅ አዛዥ ኮማንደር ዋኘው አዘዘ መታሰራቸውን ተከትሎ የታቀደ ሲሆን፣ ቀደም ብለው የተደረጉት ተመሳሳይ ዘመቻዎች ሳይሳኩ ቀርተው ነበር። ለውጤት መጥፋቱ ተጠያቄ የተደረጉት ኮማንደር ዋኘው ሲሆኑ፣ […]
Posted in Ethiopian News, News

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈው የአጭርና የመካከለኛ ሞገድ

* የስርጭት ቀን እና ሰአት ** * ማክሰኞ ጠዋት ከ12፡00-12፡30 ምሽት ከ12፡30-1፡00 * ሀሙስ ጠዋት ከ12፡00-12፡30 ምሽት ከ12፡00-12፡30 * አርብ ጠዋት ከ12፡00-12፡30 ምሽት ከ12፡00-12፡30 * እሁድ ጠዋት ከ12፡30-1፡00 ምሽት ከ12፡00-12፡30 ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈው የሥርጭት ሞገድ 👉 መካከለኛ ሞገድ (Medium Wave) በ358 ሜትር ባንድ በ837 ኪሎኸርዝ 👉አጭር ሞገድ (Short Wave) በ31 ሜትር ባንድ በ9700 ኪሎኸርዝ በ41 […]
Posted in Ethiopian News, News

በታንዛንያ የሰባት ኢትዮጵያውያን አስከሬን ከወንዝ ውስጥ ተገኘ።

በታንዛንያ የሰባት ኢትዮጵያውያን አስከሬን ከወንዝ ውስጥ ተገኘ። በታንዛንያ የሰባት ኢትዮጵያውያን አስከሬን ከወንዝ ውስጥ ተገኘ። ዘ ሲቲዝን የተሰኘው የታንዛንያ ድረገጽ አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅሶ እንደጻፈው በሩቩ ወንዝ ውስጥ መገኘቱን ሲጠቁም አስከሬኖቹ እድሜያቸው ከ 25 እስከ 35 አመት የሚሆናችው ወጣቶች መሆናችው ተግልጿል በጣም የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ደሞ እነዚህ ወገኖቻችን የሚረከባቸው አተው እዛው በታንዛኒያ እንዲቀበሩ መደረጉ ነው ለህዝብ […]
Posted in Ethiopian News, News

በጎንደር የሚደረገው ፍልሚያ አድማሱን እያሰፋ ነው!

በመተማ ቋራና በስሜን በኩል አዳዲስ የጦርነት ግንባሮች ተቀስቅሰዋል። ዝርዝር ጉዳዩን እያጣራን ነው። ወያኔ በጎንደር ህዝብ ላይ ይፋ ጦርነት ከፍቷል። ጥረው ግረው በሚኖሩ ሰላማዊ ገበሬወች ላይ በከባድ መሳሪያ የተደገፈ ጦርነት መክፈቱ አይደለም ኢትዮጵያውያንን ቀርቶ የአለምን ህዝብ ሊያሳስብና ሊያስቆጣ ይገባ ነበር። ለጉዳዩ የተቀናጀ የሚዲያና የዲፕሎማሲ ሽፋን በማሰጠት ለህዝባችን አጋርነትን ማሳየት ይገባናል። በሰላማዊ ሰልፍ ላይ በዱላ ለተደበደቡና ለታሰሩ […]
Posted in Ethiopian News

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ሦስተኛ ሆናለች

ዋና መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ(CPJ) ዓመታዊ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞችን ቁጥር ቀምሮ ይፋ በሚያደርግበት ዓመታዊ ሪፖርቱ በዚህ ወር በሚጠናቀቀው የአውሮፓውያን 2016 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ 259 ጋዜጠኞች ታስረው እንደሚገኙ አስታውቋል። በዚህ ሪፖርቱ ከአፍሪካ ግብጽ 25 ጋዜጠኞችን በማሰር 1ኛ፣ ኤርትራ 17 ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛና ኢትዮጵያ 16 ጋዜጠኞችን በማሰር ሦስተኛ ሀገር ተብላለች። የሲ.ፒ. ጄ የምስራቅ […]
Posted in Ethiopian News, News

በአማራ ክልል ከሚታየው የነጻነት ትግል መጠናከር ጋር በተያያዘ ፣ ህዝባዊ ትግሉን ይደግፋሉ ወይም ስርዓቱን ውስጥ ሆነው ይቃወማሉ የተባሉ የተለያዩ የብአዴን አባላት እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው።

ኢሳት ዜና :- የሰሜን ጎንደር ዞን የጸረ ሽምቅ ዋና አዛዥ ኮማንደር ዋኘው አዘዘ፣ በነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ታማኝ ወታደሮች መካከል የሚደረገውን ውጊያ ተከትሎ ፣ በገዢው ፓርቲ በኩል ለደረሰው ሽንፈት ተጠያቂ ናቸው በሚል ከታሰሩ በሁዋላ ፣ በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ አመራሮች እየተገመገሙ ሲሆን፣ አመራሮች ለሁለት ተከፍለዋል። አንደኛው ወገን የኮማንደሩን መታሰር አጥበቆ እየተቃወመ ሲሆን፣ የህወሃት ድጋፍ አላቸው […]
Posted in Ethiopian News, News

አሜሪካ አንድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መወሰኗን ሰኞ ይፋ አደረገች።

በኢትዮጵያ ባለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ስጋቷን ስትገልጽ የቆየችው አሜሪካ አንድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መወሰኗን ሰኞ ይፋ አደረገች። የዴሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ የሚመራ የልዑካን ቡድን ከረቡዕ ጀመሮ በአዲስ አበባ የአራት ቀን ጉብኝት እንደሚያደርግ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። በኢትዮጵያ የአራት ቀን ቆይታ የሚኖራቸው ቶም […]
Posted in Ethiopian News, News

ኦህዴድ እየታመሰ ነው ። ዶ/ር ታደሰ ብሩ

በጥልቅ በመታደስ” አመራሩን ከህወሓት በላይ ህወሓት እያደረገ ያለው ኦህዴድ በግምገማና ዳግም ግምገማ እየታመሰ ነው። የአሁኑ ከቀድሞው ለየት የሚያደርገው “አርበኞች ግንቦት 7 ኦህዴድ ውስጥ ገብቶብናል፤ ሴሎቹንም ዘርግቶብናል” የሚለው ስሞታ አይሉት መርዶ መብዛቱ ነው። በዚህም ሰበብ በርካታ የዞንና የወረዳ አመራሮች እየለቀቁ ነው፤ ጥቂት የማይባሉ ከአገር ለቀው ወጥተዋል፤ የታሰሩም አሉ። ባለፈው ሳምንት በረከት ስምኦን የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችን አፍሪካ […]
Posted in Ethiopian News

የብሪታኒያ መንግስት ለዜጎቹ የጉዞ ማስጠንቀቂያ የሚቀጥል መሆኑን አስታወቀ

ለሃገሪቱ ዜጎች ማሳሰቢያን ያሰራጨው የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጸገዴ፣ በምዕራብና ታች አርማጭሆ የሰሜን ጎንደር ስፍራዎች አስፈላጊ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች እንዳይደረጉ በመግለጫው አመልክቷል። ከብሪታኒያ መንግስት በተጨማሪ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ በድጋሚ ማሳሰቡ ይታወሳል። ለሁለተኛ ጊዜ ማሳሰቢያውን ያሰራጨው የአሜሪካ መንግስት ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ የደህንነት ስጋት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት […]
Posted in Ethiopian News, News

ቋራ ወረዳ ዛሬ በከፍተኛ ጦርነት ሲካሄድባት ማደሩ ተነገረ

በስሜን ጎንደር ቋራ ወረዳ ሱዳን ደንበር አካባቢ የታጠቁ ገበሬዎች ከመንግሰት ታጣቂዎች ጋር በዛሬው እለት ከፍተኛ ጦርነት ውሉዋል ገበሬዎችም ድል እየቀናቸው ነው ። በርካታ የወያኔ ጦር ሙትና ቁስለኛ ሆነዎል ከወገን ጦር 2 ገበሬዎች ብቻ ቆስለዋል እስከ 10:21 ውጊያው እንደቀጠለ ነበር ። የቋራ እናቶች በሚደነቅ የጄግንነት ወኔ በውጊያ መካከል ተገኝተው “ትሽሽ እና ቤትህ እየፈረሰ አንት የሴት ልጂ […]
Posted in Ethiopian News, News

የወያኔ መንግስት የአየር ኃይል ደኅንነት ኃላፊን ለመግደል ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ ወታደሮችና ግለሰቦችላይ ክስ መሰረትኩ አለ

የአገር መከላከያ ሠራዊትን በመክዳት የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅን በመተላለፍ፣ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ሥር ውለዋል የተባሉ ወታደሮችና ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ ተከሳሾቹ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል መሆናቸውን የሚገልጸው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ፣ ወደ ኤርትራ በመሄድ የድርጅቶቹን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሥልጠና መውሰዳቸውን ያስረዳል፡፡ አድራሻቸው ኤርትራ መሆኑ የተገለጸው ተከሳሾች አወል አባጊዲና ሰይድ መሐመድ […]
Posted in Ethiopian News, News

በሱዳን በሰላም ማስከበር ተግባር ተሰማርተው የቆዩት ኮ/ል ሃጎስ ምስግና መገደላቸውን ምንጮች አስታወቁ።

በሱዳን በሰላም ማስከበር ተግባር ተሰማርተው የቆዩት ኮ/ል ሃጎስ ምስግና መገደላቸውን ምንጮች አስታወቁ። በትግራይ ኢሮብ ወረዳ የተወለዱት የቀድሞ የህወሃት ታጋይና የመከላከያ መኮንን ኮ/ል ሃጎስ ሆን ተብሎ ከኌላ በተተኮሰባቸው ጥይት ጭንቅላታቸውን ተመተው መሞታቸው ሲታወቅ፣ ለግድያ ያበቃቸው በጥቂት ከፍተኛ ጄኔራሎች የሚፈፀመውን ሙስና በተለይ በሰላም አስከባሪነት በሚሰማራው ወታደር የሚደርስበት ብዝበዛን በመቃወማቸው እንደሆነ ምንጮች አመልክተዋል። በ1996 ዓ.ም መለስ በመሩት ስብሰባ […]
Posted in Ethiopian News, News

በጎጃምና በጎንደር ከ20ሺ በላይ ወጣቶች መታሰራቸው ተገለጸ፤

የወያኔ ፍርሀት መሸሻና መደበቂያ የሆነውን አስቸኳዋይ ጊዜ አዋጅ የቂም መወጣጫ ያደረጉት የብአዴን የወረዳ ባለሥልጣናት አስካሁን በቻግኒ ከፍጠኛ ቁጥር ያለው ወጣት በቀበሌ ጽ/ቤቶች ታጉሮ እንደሚገኝ መረጃዎች አመለከቱ፡፡ ይህ ከፍተኛ ዘግናኝ ድርጊት የፊድራሉ መንግሥት ሪፖርት ካደረገው ውጭ ሆነው ቁጥር ባለሥልጣናቱ በቀበሌ ሊቀ መናብርቶቻቸው አማካኝነት የአማራን የለውጥ ኃይል ሞራላዊ ጉዳት እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማጥፋት በማለም እየተንቀሳቀሱሰ ሲሆን በዞን […]
Posted in Ethiopian News

ህውሀት ገዳማትን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ በቃጠሎ ሊያወድማቸው ነው!!!

በሰ/ጎንደር ለ 2 ሳምንታት በተከታታይ በነፃነት አይሎች  ድባቅ የተመታው የህውሀት ሰራዊት የጨበጣው ውጊያ እንደማያዋጣው ሲረዳ ትናንት እና ዛሬ አካባቢውን በከባድ መሳሪያ ከርቀት ሲደበድብ መዋሉ ተነግራል ። ከነፃነት አይሎች  ምንም ጉዳት ባይደርስም ቀርና፣ አምባ፣ ኪዳነምረት ገዳም በድብደባው ምክንያት እሳት እየተነሳ ስለሆነ ህውሀት በዚህ እኩይ ተግባሩ ከቀጠለ ገዳሙ ሙሉ ለሙሉ እንደሚወድም የመረጃ ምንጫችን ከቦታው አረጋግጧል። ገዳሙ ረዥም እድሜ […]
Posted in Ethiopian News

ከትላንት አመሻሽ ጀምሮ በጃዊ የነፃነት ሐይሎች ከሕውሃት ወታደሮች ጋር እየተዋጉ ነው ተባለ

ከትላንት አመሻሽ ጀምሮ በጃዊ የነፃነት ሐይሎች ከሕውሃት ወታደሮች ጋር እየተዋጉ ነው ። በዚህ ጦርነት የወያኔ መንግስት ከታንክ ጀምሮ ሌሎች ከባድ መሳርያዎችን ያሰለፈ ሲሆን ቁጥራቸው በጣም የበዛም የኣግአዚ ወታደሮችም አዝምቷል ! ሕውሃት እስካሁን ድረስ ወደ ጃዊ አካባቢ ካዘመታቸው ወታደሮች የተመለሰ የለም የተባለ ሲሆን ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተነገራል! በተያያዘም ዜና በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ጦርነቱ እንደተፏፏመ ሲሆን […]
Posted in Ethiopian News, News

በጎንደር አዘዞ የሚገኘው የ24ኛ ክ/ጦር ሆስፒታል በቁስለኛ የወያኔ ወታደሮች መጨናነቁ ተነገረ።

በጎንደር አዘዞ የሚገኘው የ24ኛ ክ/ጦር ሆስፒታል በቁስለኛ የወያኔ ወታደሮች ተጨናንቋል ተባለ ካለፋት 2 ሳምንታት በፊት ጀምሮ ሞልቶ የሚገኘው ይህው ሆስፒታል በተጨማሪም በያዝነው ሳምንት በሁለት ኦራል የገባው ቁስለኛ ከሰሜን ጎንደር የጦር ግምባሮች የተሰበሰበ እና በእየ አካባቢው ካሉ ጤና ጣቢያወች አገልግሎት ባለማግኘቱ እየተሰቃየ ይገኛል ተብላል። በአርበኞች ግንቦት 7 ና በአማራ ገበሬ አርበኞች አይቀጡ ቅጣትን እየቀመሰ ሙትና ቁስለኛ […]
Posted in Ethiopian News

ዶ/ር መረራን ጠበቆቻቸው አሁንም አላገኟቸውም ተባለ

ኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬም ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ ተገልጿል። ጤንነታቸውም የተሟላ አለመሆኑንና የሚገባላቸውን ምግብ አንዳንድ ጊዜም እንደማይመገቡ ተሰምቷል። ጠበቆቻቸው እርሳቸውን ለማናገር የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ። http://amharic.voanews.com/a/3630242.html Filed under: NEWS
Posted in Ethiopian News, News

በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ጦርነት ዛሬ ቀጥሎ ውላል

በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ጦርነት ዛሬ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ታጋዮች የያዙትን ምሽግ ሰብሮ መግባት ያልቻለው የአገዛዙ ጦር፣ ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠር እየሞከረ ነው። ከጦር ግንባሩ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በአካባቢው በብዛት የሰፈሩት ወታደሮች ሞርታርና ዲሽቃ እየተኮሱ አካባቢውን ሲደበድቡ ውለዋል። የግንባሩን ቃል አቀባይ በቀጥታ ለማግኘት ባንችልም፣ ከአካባቢው ምንጮች […]
Posted in Ethiopian News, News

በኢንስፔከተር ምስጋናዉ የተመራዉ የወያኔ ልዩ ሀይል 1 ጋንታ ሙሉ የገባበት አልታወቀም።

አርብ ህዳር 30 2009 ይህ የተፈፀመው ቀበሌ 18 አካባቢ መሆኑ ታውቋል። ገዳዩ ወዲያውኑ ተሰውሯል። የወታደራዊ አመራሮች ድርጊቱን ለመሸፋፈንና ለመደበቅ ሲጣጣሩ ተስተውሏል። የወያኔ ሃይል ጎንደር ላይ ባለው ጦርነት እየተሸበረ ይገኛል። በየ ቀኑ ጥለው የሚሸሹና በርሃ የሚገቡት ቁጥራቸው እየተበራከተ ነው። የሟቹን ሻለቃ ማንነትና ያማሟቱን ሁኔታ እያጣራን ነው። የጎንደር ልዩ ሀይል ምክትል አዛዥ ኢንስፔከተር ልደቱ ትላንት በካባድ ሁኔታ […]
Posted in Ethiopian News, News

የአውሮፓ ሃገራት ዜጎቻቸው ወደ ሰሜን ጎንደር እንዳይጓዙ አዲስ ማሳሰቢያን አወጡ

በሰሜን ጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስትና በግንቦት ሰባት ሃይሎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የአውሮፓ ሃገራት ዜጎቻቸው ወደ ስፍራው እንዳይጓዙ አዲስ ማሳሰቢያን አወጡ። ተደጋጋሚ የጉዞ ማሳሰቢያን ሲያወጡ የነበሩት የጀርመንና የቤልጅየም መንግስታት በኢትዮጵያ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ መሻሻልን ቢያሳይም በአማራ ክልል ስር በሚገኙ ሶስት ዞኖች የጸጥታ ስጋት መኖሩን ይፋ አድርገዋል። ለዜጎቻቸው አዲስ የጉዞ ማሳሰቢያን ያሰራጩት ሁለቱ የአውሮፓ ሃገራት በጸገዴ፣ […]
Posted in Ethiopian News, News

የቀድሞውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና ጠቅላይ ሚኒስትር ተስፋዬ ዲንቃ አረፉ።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ተስፋዬ ዲንቃ የተወለዱት አምቦ ሲሆን ሊባኖስ በሚገኘው አሜሪካን ስኩል ኦፍ ቤይሩት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የተቀበሉ ሲሆን ኒዮርክ በሚገኘው ሲራከስ ዩኒ…ቨርስቲ በኢንጂነሪንግ ማስተርሳቸውን ሠርተዋል። አምባሳደር ተስፋዬ በተለያዩ ዘርፎች ሚኒስትር ሆነው ሃገራቸውን አገልግለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የፋይናንስ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ለረዥም ግዜ ሃገራችንን አገልግለዋል። በተለይም በርካቶች የሚያስታውሷቸው ኢትዮጵያን […]
Posted in Ethiopian News, News

ሰብር መረጃ . . የኮማንድ ፖስቱ አመራሮች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነዉ።

የህወሃት ብሔራዊ መረጃና የወታደራዊ ደህንነቱ በትናንትናዉ እለት ድንገተኛ ስብሰባ አካሄደዋል ወታደራዊ ደህንነቱ ጥቃት ደርሶብኛል ይላል 3 የኮማንድ ፖስቱ አመራሮችን በጎንደርና በሐረር ያስገደለዉ በጌታቸዉ አሰፋ የሚመራዉ ብሔራዊ ደህንነቱ ነዉ በሚል ከፍተኛ ዉጥረት ነግሷል። የጌታቸዉ አሰፋን ብሔራዊ መረጃ ከስራ ዉጭ በማድረግ አጠቃላይ ሐገራዊ ደህንነቱን የተቆጣጠረዉ የሳሞራዉ ወታደራዊ ክንፍ መንግስታዊ ወንጀል ተፈጽሟል በማለት ዉስጣዊ ክስ አቅርቦ ንትርኩ ያለስምምነት […]
Posted in Ethiopian News, News

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አድማ ላይ መሆናቸው ተነገረ

በዛሬ ቀን ወያኔ የብሄረሰቦች ባሕል ብሎ ያመጣውን ማወናበጃ በጎንደር ዬኒብርሲቲ አልተከበረም። ምክኒያቱም ወልዲያ ላይ የታሰሩ ተማሪዎች አሉ። ከጥቂት ቀናት በፊት በግፍ የታሰሩ ከ120 በላይ የጎንደር የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብር ሸለቆ ውስጥ ታስረው እየተሰቃዩ ስለሆነ ተማሪው አድማ ላይ ነው። በተጨማሪም በሃገራችን ገበሬ ላይ የተከፈተው የግፍ ጦርነት በህዝባችን ላይ ወያኔ የዘር ፍጅት እየፈፀመ ነው የሚል እልህና ቁጭት በተማሪው […]
Posted in Ethiopian News, News

በአዋሽ አርባ በርሃ የታሰሩ ዜጎች በምግብና ውሃ እጦት እየተሰቃዩ ነው

ከአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በኮማንድ ፖስቱ ኃይሎች እየታደኑ ለእስራት ከተዳረጉ ቁጥር የለሽ የስርዓቱ ገፈት ቀማሾች መካከል ከ5000 የማያንሱት በአዋሽ አርባ በረሃ በሚገኝ ወህኒ ቤት ውስጥ ታጉረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከአዲስ አበባ በቅርቡ በአዋሽ አርባ እንደሚገኙ የተነገረላቸውን የቤተሰቦቻቸውን አባላት ለመጠየቅ ያመሩ እናቶች፣አባቶች፣የትዳር አጋሮችና ህጻናት በወህኒ ቤቱ ጠባቂዎች ‹‹ሁለተኛ ድርሽ እንዳይሉ››ማስጠንቀቂያ ተነግሯቸው የናፈቋቸውን ወገኖቻቸውን የሚገኙበትን ሁኔታ ለማየት ጭምር […]
Posted in Ethiopian News

አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔን ሰራዊት በሁመራ አዲስ አለም ዳንሻ አብደራፊ ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ እንደሆነ ተናገሩ።

የአርበኞች ግንቦት 7 የፖለቲካ ጉዳዮች ዋና ሃላፊና የግንባሩ ቃለ አቀባይ የሆኑት አቶ መንግስቱ ወልደስላሴ በወያኔ አገዛዝ ጋር ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ እንደሆነ ተናገሩ። እንደ ቃለ አቀባዩ ገለጻ የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በጥልቀት ሰርገው ገብተዋል። የፓለቲካ ጉዳዮች ዋና ሃላፊውም በማከልም እነዚህ ሰርገው የገቡት ወታደሮች ከወያኔ ጦር ጋር የሚያደርጉትን ውጊያ አጠናክረው እንደቀጠሉ ይናገራሉ። አቶ መንግስቱ […]
Posted in Ethiopian News, News

የጎንደር አካባቢ የመንግስት ሰራተኞች ብሶት ውስጥ ናቸው!

ይኸውም ደባርቅ ፣ ጃናሞራ ፣ ወገራ ፣ ዳባት አዲአርቃይ ላይ ከሃያ አንድ ጀምሮ ይከፈል የነበረ የወር ደሞዝ እስካሁን አልተከፈለም። በተጨማሪም ወያኔ በራሱ ሹመኞች እምነት አጥቷል። በተለያዩ የጎንደር ወረዳወች ላይ በወያኔ ካቢኔ አመራር ላይ እስር እየተፈፀመባቸው ነው። የተቀሩትም እየሸሹ ነው። በአርማጭሆ የታሰሩትን ዝርዝር ትናትና ጠቅሸ ነበር። ዳባት ከተማ የፀረ ሽምቅና ፀጥታ ጉዳይ ሃላፊ የነበረው ቀንደኛ የወያኔ […]
Posted in Ethiopian News, News

ሀገራችንን ወደ ማያባራ እልቂት የሚመራት ጎሰኝነትና የጎሳ ፖለቲካ ነው

ጎሠኝነት በክልል፧በአውራጃ፧ በወረዳ፧በቀበሌ፧በመንደጨር ጠቦ ጠቦ ወደቤተሰብ ይሄዳል!! ትዳር ያለያያል፧ ልጆች ያለአሳዳጊ ይቀራሉ ። የዜጎች በሠላም በፍቅር አይኖሩም። የጎሳ መሪዎች በመፎካከር በሚቀሠቅሱት ጦርነት ንፁሀን ዜጎች ወደማያባራ የጦርነት እልቂት ይገባሉ። በዚህ ወቅት የአገር እድገት ብልፅግና አይታሠብም። በሚቀሠቀሠው ጦርነት የውጭ ሀይሎች መሣርያዎቻቸውን ይቸበችባሉ። የአገሪቱን ጥሬ ሀብት ይዘርፋሉ። በሩዋንዳ፧በሶማልያ …..ወዘተ እንደታየው መሆኑ ነው። የጎሳ ፓለቲከኞችና ደንታ የሌላቸው መሪዎቻቸው በገንዘብ […]
Posted in Ethiopian News

ከቆላማው ወገራ የጦር ግንባር ልዩ ሪፖርት! – ምክትል ሳጅን ዋጋየ ጫቅሉ በጦርነቱ መገደሉ ተነገረ

እኛ በቆላማው ወገራ ጥረን ግረን የምንኖር ገበሬወች ላይ በግፈኛው ወያኔ በህልውናችን ላይ የተቃጣብንን ጥቃት እውነትንና ፈጣሪን ይዘን ተከላክለን እያጠቃን እንገኛለን። ሁለተኛ ሳምንቱን ያስቆጠረው ጦርነት አሁንም ለአምስተኛ ዙር 11 መኪና ሞልተው በላኩት መደበኛ ወታደርና ባንዳ ጉጀሌ ጋር በቆራጥነት እየተጋፈጥን ነው።   ይህ ጦርነት የተነሳው እራሳችንን ስንጠብቅበት የኖረውን መሳሪያ ካልገፈፍን ብሎም አስረን ካላዋረድናቹህ ሲሉን ነው። በጎንደር ሕዝብ […]
Posted in Ethiopian News

የፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እስር ዲፕሎማሲያዊ ጫና መፍጠር ጀመረ

ባለፈው ረቡእ ህዳር 21 2009 ዓም በደኅንነት ኃይሎች ከመኖሪያ ቤታቸው  በቁጥጥር ስር ውለው በእስር ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር መረራ መታሰር በኢትዮጲያ መንግስት ላይ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጫና መፍጠር መጀመሩ እየተዘገበ ነው፡፡ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን በብራስልስ እንዲገኙ የጋበዙት እና የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑት ወ/ሮ አና ጎሜዝ በቅርቡ አዲስ አበባን ጎብኝተው ለነበረው ጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርከል በፃፉት ደብዳቤ ቻንስለረዋ […]
Posted in Ethiopian News, News

ከህወሃት ደህንነት አፈትልኮ የወጣ

የነፍስ አድን ጥሪ ለብአዴን አባላት እና ግብረ አበሮቹ ! ህወሐት በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጃ ፡ ሎሌው ብአዴንን እንደ ትልቅ መሳሪያ በመጠቀም፡ ህዝባዊ ትግሉን በሀይል ለመቀልበስ ስትቀሳቀስ ቆይታለች፡፡ ነገር ግን አናብስት የአማራ ጀግኖች በህወሐት የተቃጣበትን ጥቃት መመከት መቻሉ እጂጉን እንዳስደነገጠውና ለዚ ትግል ውስጥ ውስጡን ፡ የብአዴን አባላት እንዳሉበት ፡ ተደርጎ የብአዴን አባላትን ለመምታት እስከ ግድያ […]
Posted in Ethiopian News, News

ስቴት ዲፓርትሜንት ከዚህ በፊት የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ዛሬ በአዲስ ማስጠንቀቂያ ተካው።

ወያኔ ያወጣው የ 6 ወር አስቸኳይ አዋጅ ዜጎችን ካለፍርድ ቤት ትእዛዝ የማሰር መብትና ሌሎችንም እርምጃ የመውሰድ መብት ያጎናፀፈው መሆኑን በማስገንዘብና ህገ ወጥ ድርጊቶች ብሎ የሰየማቸውን ለምሳሌ ከሁለት በላይ ሁኖ አንድ ላይ ቆሞ መነጋገር፤የተለያዩ የመገናኛ መንገዶችን መጠቀም፤በስብሰባ መሳተፍ፤ ከተለያዩ የውጭ አገር መንግሥታትና ድርጅቶች ጋር መገናኘት(መነጋገር) የሰዓት እላፊ ገደብን ማለፍ እና ሌሎችንም ያልተጠቀሱ ተግባሮችን ምክንያት በማድረግ የአሜሪካ […]
Posted in Ethiopian News, News

ኮለኔል ገ/ኪዳን ገ/ማሪያም መረጃ ዉስጥ አፈትልኮ የወጣ ፍንጭ

ሰበር መረጃ ። ከመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ስምሪት የበላይ ሐላፊ ኮለኔል ገ/ኪዳን ገ/ማሪያም መረጃ ዉስጥ አፈትልኮ የወጣ ፍንጭ እንደጠቆመዉ የህወሃት መከላከያ በሰሜን ጎንደር የኮማንድ ፖስቱ ተግባር ተገቷል በመሆኑም በጄኔራል ሲራጅ ፈርጌሳ ትእዛዝ ከምስራቅ እዝና ከመካከለኛዉ እንዲሁም በትግራይ ከሚገኙ ክፍለ ጦሮች የተዉጣጣ ሰራዊት ወደ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር እንዲሰማራ ታዟል በተያያዘ መረጃ የአማራ ገበሬዎችን ለማጥቃት ከጀርባ […]
Posted in Ethiopian News, News

የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ለ48ኛ ሕዳር 27፣ 2009 ለመጨረሻ የይግባኝ ብይን ይቀርባሉ፡፡

አምስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች፣ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ (ከእስር ቤት)፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ አቤል ዋበላና ናትናኤል ፈለቀ ነገ ማክሰኞ ሕዳር 27፣ 2009 ለመጨረሻ የይግባኝ ብይን ይቀርባሉ፡፡ ሰባት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችና ሶስት ጋዜጠኞች ከታሰሩበት ሚያዚያ 17፣ 2006 ጀምሮ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት እየቀረቡ ቆይተው አምስት ተከሳሾች ከሳሽ የፌደራል ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን ክስ አንስቻለሁ በማለቱ ሐምሌ 01፣ 2007 […]
Posted in Ethiopian News

ደባርቅ፣ ዳባት፣ አምባጊዮርጊስና ጎንደር በወያኔ ሙትና ቁስለኛ ተጥለቅልቀዋል።

v ሁለተኛ ሳምንቱን በያዘው የቆላማው ሰፊ የወገራ ምድር ላይ የሚደረገው ጦርነት አሁንም በጀግና ህዝባችን ድባቅ ተመቷል። በ11 መኪና ወደቆላው ድንበር የተራገፈው አጋዚ በባንዳ እየተመራ ወደቆላው ቢዘልቅም አይቀጡ ቅጣት ተመቶ የተረፈው የቻለውን ያህል ሙትና ቁስለኛ ይዞ ወደመጣበት እግሬ አውጭኝ ብሎ ተመልሷል። ዛሬ የዳባት ከተማ በአጋዚ ተጥለቅልቃለች። የዳባት ሃኪም ቤት በቁስለኛ ወታደር ተጨናንቋል። አምባ ጊዮርጊስ ላይ ብዙ […]
Posted in Ethiopian News, News

የአፍሪካ ቀንድ የሳኡዲ ወታደራዊ ማእከል ሊቋቋምባት ነዉ

ሳኡዲ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አሰብን ለወታደራዊ መስፋፋትና መደራጀት ፍጆታቸዉ ሊያዉሉ መሆኑ መረጃዎች ይፋ ከሆኑ አንድ አመት በሗላ ሳኡዲ አረቢያ ጅቡቲ ዉስጥ ሌላ ወታደራዊ ማእከል ልታቋቁም ከስምምነት ላይ መደረሱ ታወቀ። የጅቡቲ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳኡዲ አረቢያ በጅቡቲ ዉስጥ ወታደራዊ ማእከል (Military Base) ማቋቋሟን አገራቸዉ በጽጋ እንደምትቀበለዉ አሳዉቀዋል ሲል አል አረቢያ ዘግቧል። የሳኡዲ ወታደራዊ አመራሮችን ወሳኝ […]
Posted in Ethiopian News, News

በዐማራ ገበሬዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቸልታ እያየው ነው፤

በወገራ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ቤተሰቦች ቤታቸውና ንብረታቸው በመንግሥት ወታደሮች ተጥሏል፤ በዐማራ ገበሬዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቸልታ እያየው ነው፤ የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በዐማራው ሕዝብ ላይ እያደረሰው ያለው በደል ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ሒዷል፤ በዐማራ ሕዝብ ላይ ይፋ የእልቂት አዋጅ ታውጇል፡፡ ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል እየተጋደሉ ያሉ ዐማሮች በሕይወታቸውና በንብረታቸው ላይ ይህ ነው የማይባል […]
Posted in Ethiopian News

የበረከት ስምኦን “የምስክርት ቃል”

ባለፈው ሮብ በረከት ስምዖን ከፍተኛ የኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎችን አፍሪካ አዳራሽ ውስጥ ሰብስቦ በአገራችን የሰፈነውን አምባገነን አገዛዝን ውስጥ ውስጡን አየተቃወሙ ያሉትን የኢሕአዴግ አባላትን ሲወርፍ ….. “እኛን ያሰቃየን ከሕዝቡ ይልቅ በውስጣችን ያለው የውስጥ አርበኛ ነው” ዓይነት ዓረፍተ ነገር ተናገረ። እኔ ይህችን ዓረፍተነገር ብቻ ወሰድኩ እንጂ በረከት ለሰዓታት በምሬት እንደተናገረ ስብሰባው ውስጥ የነበራችሁ የምታውቁት ነው። ከላይ ቀንጭቤ ከወሰድኳት […]
Posted in Ethiopian News

አቶ የሺዋስ አሰፋ በአቶ ይድነቃቸው ከበደ በተፈረመ ደብዳቤ፤ ምክር ቤቱ ሳያፀድቀው ለምርጫ ቦርድ አስገብ

የአቶ የሺዋስ አሰፋ እና የተወሠኑ የአፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው ግለሠቦች “ጠቅላላ ጉባኤ” በመስከረም 28/2009 ዓ.ም ተካሄደ ከተባለ በኃላ ፤ አቶ የሺዋስ አሰፋ ስራ አስፈፃሚዎቼ ናቸው ያላቸውን ኮሚቴዎች ስም ዝርዝር፤ በአቶ ይድነቃቸው ከበደ በተፈረመ ደብዳቤ፤ ምክር ቤቱ ሳያፀድቀው ለምርጫ ቦርድ አስገብቷል። ከገቡት የስም ዝርዝሮች ውስጥ ከታች ቅጂው ተያይዞ ባለው ለምርጫ ቦርድ በተላከው ደብዳቤ፥ በተራ ቁጥር 1. ላይ […]
Posted in Ethiopian News

የበርካታ ወረዳ አድማ በታኝ ፖሊሶች በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የበርካታ ወረዳ አድማ በታኝ ፖሊሶች በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል ከእነዚህም የመተማ፣ የምዕራብ አርማጭሆ እና የወገራ ወረዳ አድማ በታኞች ሲሆኑ በትናንትናው እለት አንድ ታዋቂ ወታደራዊ መኮንን ከመያዛቸው በፊት ከፋኝ የነጻነት ኃይልን መቀላቀላቸው ታውቋል። ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ አስፈላጊ አልሆነም። ድሉ፣ የእኛ ነው ድሉ! ልያ ፋንታ፣ Filed under: NEWS
Posted in Ethiopian News, News

ተጨማሪ የአጋዚ ሃይል በጎንደር በኩል ወደ ዳባት እየገባ ነው! ይህን መልእክት በቶሎ አስተላልፉ።

ሰኞ ህዳር 26 ቀን 2009 ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘው የቆላማው ወገራ ከባድ ጦርነት አሁንም በጀግናው ህዝባዊ የበላይነት ድል እንደቀጠለ ነው። ይህ ከባድ ህዝባዊ ቁጣ ያስደነገጠው ወያኔ በሶስት ዙር የላከው ሃይል ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። አብዛኛው ሞቷል የተረፈውም ጥሎ ፈርጥጧል። እጃቸውን የሰጡትም ወያኔን መልሰው እየወጉ ነው። ለወያኔ የባንዳ ስራ የሚሰሩ ቅጥረኞችም አይቀጡ ቅጣት እየተቀበሉ ነው። በአንድ ግንባር ብቻ […]
Posted in Ethiopian News, News

በወልቃይት ፣ በጠገዴም በሁመራ ካፍቲያ፣ በወገራ ፣ በታች አርማጭሆ፣ በመራብ አርማጭሆ ሕዝቡ ከሕወሃት ታጣቂዎች ጋር ከፍተኛ ጦርነት እያደረገ ነው።

ጦርነት አገርን አወዳሚ ነው።ወደ ጦርነት እንዳይኬድ ፣ በአገራችን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር፣ የሰላማዊ ፓርቲዎች ለማጠናከር በመሞከር ብዙዎቻችን ማድረግ የምንችለውን አድርገናል። ሆኖም ሕወሃቶች የሰላማዊ ታግዮችን እያፈኑ ነው። የሕወሃት ግትር ፖለቲካ ቀስ በቀስ ወደ ከፋ ደረጃ እያደረሰን ነው።፡ ሕወሃት ነገሮችን አድበስብሶ ፣ ምንም ችግር እንዳልተፈጠረ ሊነግረን ይሞክራሉ። ግን በሽታንን ከደበቅን በሽታን መጨረሻ ይገድለናል። አገራችን በአሁኑ ወቅት ታማለች። […]
Posted in Ethiopian News

ወደ አንቃሽ የተንቀሳቀሰው ጦር ሙሉ በሙሉ ወድሞ ውጊያው በድል ተጠናቋል፤

ከትናንት ጀምሮ ሰሜን ጎንደር ወገራ የሔደው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡ ዛሬ ኅዳር 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ከሰዐት በኋላ እንቃሽ ላይ ሌላ አዲስ ጥቃት መከፈቱን ገልጸን ነበር፡፡ እኩለ ሌሊት ላይ ውጊያው በገበሬዎች ተጋድሎ ድል አድራጊነት የተደመደመ ሲሆን እስካሁን አንድም ሰው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ ፈለቀ አለበል የተባለ የአካባቢው ተወላጅና የመንግሥት ታጣቂ፣ […]
Posted in Ethiopian News, News

ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር በመሆን ኢትዬጵያዊነትን ይዞ ወደፊት

ይህ ትግል የህዝብ ትግል እንደመሆኑ መጠን ማንኛውም ግለሰብ የማንንም ፍላጎትና ይሉኝታ ሳያስፈልገው አቅሙ በሚችለው መንገድ መታገልና ወያኔ የተባለን ዘረኛ ሰው በላ ስርዓት በማስወገድ የዜግነት ድርሻችንን እንወጣ :: በአሁኑ ሰዓት ያለውን ስርዓት ለማስወገድ የጎንዮሽ ንትርኩን ትተን የጋራ የሆነውን ጠላታችን ማስወገድ ግድ ይላል 25 አመት የተሰራን ስራ እንዲሁ በቀላሉ ያለ ስራ ወያኔ ወያኔ እያሉ እንደ ዳዊት ከመድገም […]
Posted in Ethiopian News, News

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊትና ልዩ ኃይል ጦር ጋር ዋልድባ ላይ ባደረገው ከባድ ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ትናንት ከቀትር በኋላ ዋልድባ ላይ በሰነዘረው ድንገተኛ እና ከባድ ጥቃት የህወሓት መራሹን የመከላከያ ሰራዊትና ልዩ ኃይል ጦር ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ አመሻሽ 12 ሰዓት ድረስ ለሁለት ተከታታይ ሰዓታት በጥይት ቆልቶታል፡፡ በመሆኑም ከህወሓት ጦር በኩል በትንሹ 29 ወታደሮች ሲሞቱ ከ40 በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡ Filed under: NEWS
Posted in Ethiopian News, News

ዛሬ ጠዋት መሳለሚያ አካባቢ በደረሰ አስከፊ የመኪና አደጋ 24 ሰው ሲገድል 34 ሰዎች ለከባድ ጉዳት ዳርጋል ።

ዛሬ ጠዋት 2 ሰአት ላይ መሳለሚያ አካባቢ በደረሰ አስከፊ የመኪና አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሳል ። ኮንቴነር የጫነው ከባድ መኪና ፍሬን አሊዝ ብሎት 24 ሰው እና 5 አህያ ወዲያው ሲገድል 34 ሰዎች ለከባድ ጉዳት ዳርጋል ። በስምንት መኪናዎችም ላይ ከባድ ጉዳት አድርሳል ። በሂወት ተርፈው ለከባድ ጉዳት የተዳረጉት ሰዎችም ለህክምና ወደ ጥቁር አንበሳ […]
Posted in Ethiopian News, News

የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተር ፕሬዝዳንት ትራምፕን አስጠነቀቁ

አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገና የነጩን ቤተ መንግሥት በር ሳይረግጡ ከአሜሪካው ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት (CIA) ዋና ዳይሬክተር ጆን በርናን ምክር አዘል ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በተለይም ትራምፕ አሜሪካ ከኢራን ጋር የጀመረችውን የኑክሊየር ጉዳይ ድርድር ለማቋረጥ ማሰቡ ‹‹ትልቅ ቅዠትና የቂልነት ጥግ ነው›› ያሉት የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተሩ እንደዚህ አይነቱ ውሳኔ አሜሪካን ዋጋ የሚያስከፍልና ኢራንና መሰሎቿን ኑክሊየርን ለጥፋት […]
Posted in Ethiopian News, News

በፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ቦንብ ተገኝቷል በሚል ሰበብ በርካታ ፖሊሶች ታሰሩ

ኢሳት ዜና :- ከሶስት ቀናት በፊት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው በፌደራል ፖሊስ ዋናው ጽ/ቤት ወንጀል ምርመራ ክፍል ውስጥ ቦንብ ተገኝቷል በሚል ሰበብ በርካታ የኦሮሞና አማራ ተወላጅ ፖሊሶች ታሰረዋል። ምንጮች እንደገለጹት ቦንቡ ሆን ተብሎ ፖሊሶችን ለማጥመድ ተብሎ በህወሃት የፌደራል ፖሊስ አባላትና የደህንነት ሰዎች የተቀነባባረ ነው። በወንጀል ምርምራ ክፍል ውስጥ የጦር መሳሪያ እንደማይገባ የሚገልጹት ምንጮች፣ ድርጊቱ አገዛዙን ይቃወማሉ […]
Posted in Ethiopian News, News

ጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ወያኔ ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ታሪኩንና አቅዋሙን ይዞ በትግሬነት ተሸፋፍኖ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መቆም አይችልም፤ የትግራይ ሕዝብም ከወያኔ ጋር ቆሞና የወያኔ ምሽግ ሆኖ ወያኔ በዙሪያው ያጠረለትን የጠላትነት አጥር አልፎ ኑሮውን ለማሻሻል አይችልም፤ እንዲያውም የጦርነት ሜዳ ይሆናል፤ የወያኔ መሪዎች ዛሬም የሚያስቡት ወያኔን በሥልጣን ላይ ለማቆየት የትግራይ ሕዝብ ገና ወደፊት የሚከፍለውን መስዋእትነት ነው፤ ሥዩም መስፍን የሚከተለውን ይላል፡ ከ60 ሺ በላይ […]
Posted in Ethiopian News, News

ሰበር ዜና። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በአውሮፓ ህብረት ስብሰባ ከተሳተፉ በኋላ ዛሬ ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ ለእስር ተዳረጉ።

ላለፉት 25 አመታት በስላማዊ መንገድ ወያኔን እየታገሉ ካሉ ግንባር ቀደም ተጠቃሹ የዩኒቨርስቲ መምህሩ ዶክተር መራራ ጉዲና ከ አውሮፓ ህብረት በ ኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት እና አመፅ ዙሪያ መንግሥት እየወሰደ ባለው እርምጃ ጉዳይ ለይ ማብራሪያ እንዲሰጧቻው ተጠርተው በ ህብረቱ ጉባኤ ተገኝተው ገለፃ ማድረጋቻው የሚታወስ ሲሆን ። እንዲሁም አውሮፓ ህብረት ለስብሰባ ጠርቷቸው የመጡትና ከተለያዩ ኢትዮጵያዊያ ጋር ህዝባዊ […]
Posted in Ethiopian News, News

ሰሜን ጎንደር ግንባር…አዲስ የአጋዚ ሃይል ዳባት ገብቷል! ጥንቃቄ! ALERT our people and SHARE IT!

ስድስት ቀን በዘለቀው ጦርነት ወያኔ በቆላማው ወገራ በታጠቀው ገበሬ የደረሰበትን አይቀጡ ቅጣት ለመመከት ተጨማሪ ሃይል ወደቆላው ለመላክ ዳባት ላይ አዲስ የአጋዚ ሃይል አስፍሯል። ይህ ትናንት የገባው አጋዚ በስተሰሜን በደባርቅ በኩል እንደመጣ ታውቋል። ከትግራይ የመጣ ነው ተብሎ ይታመናል። በጎጃም መስመርም አዲስ ሃይል ወደዚህ አቅጣጫ እየተላከ ለመሆኑ መረጃወች አሁንም እየደረሱ ነው። ስለሆነም ለወገን ዘመድ ነቅቶ በር እንዲጠብቅ […]
Posted in Ethiopian News, News

ወያኔ ወደ ሱዳን በመግባት የነጻነት ሃይሎችን ከጀርባ ለመምታት ማቀዱ ምንጮች ገለጹ።

የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ለሳምንታት የዘለቀው ጦርነት ዛሬ በደቡብ ጎንደርና በበለሳ መሃከል ዳዊጭ በሚባል አካባቢ ቀጥሎ ውሎአል። በሁለቱም ወገኖች ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ አልደረሰንም። ይሁን እንጅ ጦርነቱ ከፍተኛ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል። በሌላ በኩል አገዛዙ ሰራዊቱን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እያንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ትናንት ሰኞ ወታደሮችን የጫኑ ኦራል መኪናዎች ቁንዝላ ከተማ መግባታቸውንና […]
Posted in Ethiopian News, News

የአማራና የኦሮሞ ስደተኞች ተለይተው ያለፍቃዳቸው ለወያኔ መንግስት በአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አማካኝነት ከጅቡቲ ተላልፈው ተሰጡ።

ስሙን መግለጽ ያልፈለገና ሁኔታውን ሲከታተል የነበረ በጅቡቲ የሚገኝ የአይን እማኝ ወደ 150 የሚደርሱ ስደተኞች ያለፍላጎታቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል በማለት ተናግሯል። እነዚህ ስደተኞች ከየመን በመርከብ ተጭነው በአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አማካኝነት ወደ ጅቡቲ ቢገቡም የወያኔ መንግስት የጅቡቲ መንግስትና የአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በመደዋወል በተለይ የአማራና የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ያለፍቃዳቸው ወደ ኢትዮጵያ ቅዳሜ 17 ህዳር 2009ዓም በአውሮፕላን […]
Posted in Ethiopian News, News

የብሪታኒያ ሌበር ፓርቲ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ለሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጥሪ አቀረበ

የብሪታኒያው አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለሃገሪቱ ዜጎች መብት መከበር የገቡትን ቃል በማክበር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የሚፈቱበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹ የሃገሪቱ ሌበር ፓርቲ ጥሪውን አቀረበ። በአቶ አንዳርጋቸው ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ መግለጫን ያወጣው ፓርቲው፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉ ለማድረግ የፊርማ ድጋፍ የማሰባባሰቢያ ዘመቻ እንደሚያካሄዱም ይፋ አድርጓል። ላለፉት ሶስት ወራት የብሪታኒያ ባለስልጣናት አቶ […]
Posted in Ethiopian News

በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው የአማራ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ወጣቶች እያባበለ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው የአማራ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ወጣቶች እያባበለ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ በክልሉ ካለው ውጥረት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የወደቀው የክልሉ አስተዳደር፣ በተለይም ታጣቂው አርሶ አደር ከመንግስት ጋር ይፋ ጦርነት መጀመሩ በእጅጉ ረብሾታል ተብሏል፡፡ እንደ መረጃዎች ገለጻ ከሆነ፣ ክልሉን የሚያስተዳድረው የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ካቢኔ፣ ልቡ ለለውጥ የሸፈተውን ነዋሪ በገንዘብ ጭምር የመደለል ስራ እየሰራ እንደሚገኝ […]
Posted in Ethiopian News, News

ስዊድን በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ የዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ገለጸች

ስዊድን በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጋዋ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ስጋት እንዳሳደረባት ገለጸች። የስዊድን ዜግነት ያላቸውና የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ላይ ለመስራት ከጥቂት አመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የነበሩት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከሶስት አመት በፊት ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል። በፌዴራል አቃቤ ህግ የተመሰረተባቸውን ክስ ሲከታተል የነበረው ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የህክምና […]
Posted in Ethiopian News, News

አርበኞች ግንቦት ሰባት በጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች ውጊያ እየተካሄደ ነው

መንግሥት በምዕራብ ትግራይ ዞን በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ‘የጥፋት ሃይሎች’ ሲል የገለፀቸው ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብሎአል፡፡ ለዚህ ዘጋባ መነሻችን ኢሳት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን በባለፈው ሣምንት ያቀረበው ዜና ነው፡፡ ኢሳት በዘገባው በአርበኞች ግንባር ግንቦት ሰባት ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ የሆኑትን ሻለቃ መሣፍንት ጥጋቡ ሠሜን ጎንደር ውስጥ በተካሄደ ውጊያ እጃቸውን ላለመስጠት ሕይወታቸውን አጥፍተዋል ብሏል፡፡ ለተጨማሪ […]
Posted in Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በስዊድን የተሳካ ስብሰባ ማካሄዱን ገለጸ- ኢሳት ዜና

በቅርቡ በ4 የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ትናንት እሁድ በስቶክሆልም ከተማ የተሳካ ስብሰባ ማድረጉን ገልጿል። የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር መሪ አቶ ሌንጮ ለታ እንዲሁም የአፋር ህዝብ ፓርቲ መሪ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን፣ ስብሰባው በስቶክሆልም /ስዊድን የንቅናቄው አስተባባሪ አቶ ዘለሌ ጸጋ ስላሴ ንግግር ተከፍቷል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ […]
Posted in Ethiopian News, News

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ኢትዮጵያንና ኢትዮጲያዊነትን ለማዳን ብሎም የተጨቆነውን ህዝባችንን በጫንቃው ላይ የተጫነበትን የባርነት ቀንበር አሽቀንጥሮ በመጣል ህዝብ ቀና ብሎ እንዲሄድና የዴሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆን መራራና እልህ አስጨራሽ የትጥቅ ትግል እያካሄደ የሚገኘው ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይልና መከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት እርምጃ የወያኔን ሹማምንቶች አንገት ያስደፋ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡን አርበኛ […]
Posted in Ethiopian News, News

ሰበር መረጀ..ህወሃት ካድሬዋቹን በመሀበራዊ መገናኛዋች

የህወሃት ልሳን የሆነዉ እዲስ እራይ ህትመት ወያኔ በመሃበራዊ መግናኛ አዉታር ዙሪያ መበለጡን ባመሳከረ መልኩ በመስከረም እና ጥቅምት ወራት ላይ ባወጣዉ እትሙ ላይ ዘግቦአል። አዲስ ልሳን አያይዞ የመሀበራዊ መገናኛ የበላይነቱን ለመቆናጠጥ ከፌደራል እስከ ቀበሎ በተነደፈ ኢምስትቱይት መዋቅር ወደ ተግባር የተገባ እንደሆነ ገልጾ እንደ ልማት ሰራዊት ዲስኩር ሚዲያ ሰራዊት በሚል ስያሜ በፓለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ብሄር ተኮር ስምሪቶች መልካም […]
Posted in Ethiopian News

ሕወሃት እና ብአዴን በማሕበራዊ ድረገጾች

ህወሃት በሰሜን ኢትዮጵያ ከአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ጋር እየተዋጋ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ አመነ። በርካታ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮችን ማረኩ፣ በርካታ ገደልኩ፣ የጦር መሳሪያም ማረኩ ብሏል። ሕወሃት እና ብአዴን በማሕበራዊ ድረገጾች ላይ ባሰማሯቸው ካድሬዎቻቸው አማካይነት “አርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የለውም፣ ሻብያ አርበኞች ግንቦት 7 ወደ ኢትዮጵያ እንዲዘልቅ አይፈቅድም፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚዋጉት አርሶአደሮች ብቻ ናቸው አርበኞች ግንቦት […]
Posted in Ethiopian News

በኮንሶ ሰዎች አሁንም በጅምላ እንደሚታሰሩ፣ እንደሚደበደቡና ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነ ተገለጸ

ኮንሶ ሰዎች አሁንም በጅምላ እንደሚታሰሩ፣የኮንሶን ሕዝብ ወክለው ጥያቄ ያቀርቡ የነበሩ የኮሚቴ አባላት የተወሰኑት መታሰራቸውን አብዛኞቹ ደግሞ መኖሪያ መንደራቸውን ትተው መሰደዳቸውን እኛም በስደት ጫካ ገብተን ነው የምናነጋግራችሁ ሲሉ ሁለት የኮንሶ ነዋሪዎች ነን ያሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ። ያነጋገርናቸው ሁለት ሰዎች ቤተሰቦቻቸው እንደታሰሩባቸው፣ በኮንሶ የተነሳውን በዞን የመደራቸት ጥያቄ ያነሱ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው ጫካ መግባታቸውንና እየተፈጠሩ ባሉት ሁኔታዎች ግራ […]
Posted in Ethiopian News, News

በዳባት ወረዳ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ታጋዮች ከህወሃት ወታደሮች ጋር ከፍተኛ ውጊያ ማካሄዳቸው ተገለጸ

በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ልዩ ስሙ መንደርጌ ተብሎ በሚጠራ ቦታ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ታጋዮች ከህወህት ወታደሮች ጋር ከፍተኛ ወጊያ በትናንትናው ዕለት እንዳካሄዱ የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ህወሀት በውጊያው ያሰለፋቸው ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ አጋዥ ሀይል ለማስገባት እንቅስቃሴ ላይ ማደርጉ ታውቋል። ህወሃት በጭላ ማርያም እና በበንከር ልደታ በኩል ተጨማሪ ወታሮችን ለማስገባት የሞከረ ሲሆን […]
Posted in Ethiopian News, News

ቱርክ በ መቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ልታደርግ ትችላለች ተባለ

ቱርክ ለአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመደራደር የተገባላት ቃል ተግባራዊ አለመደረጉን ተከትሎ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ልታደርግ እንደምትችል አሳስባለች። ባለፈው አመት የሶሪያ ስደተኞች ቱርክን በመጠቀም ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ሲገቡ የነበረ ሲሆን፣ ህብረቱ ቱርክ ሰደተኞቹን በሃገሩ እንድታቆይ የጥቅማ-ጥቅም ቃል ገብቶ እንደነበር ይታወሳል። ቱርክ የሃገሯ ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ አውሮፓ እንዲገቡና ሃገሪቱ የአውሮፓ ህብረት አባል […]
Posted in Ethiopian News

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት አቶ ጌታቸው በከፍተኛ ህክምና ታይላንድ ባንኮክ ይገኛሉ።

በቅርቡ ጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ባወቀሩት ካቢኔ ውስጥ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት አቶ ጌታቸው አምባዬ ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ በስራ ገበታቸው ላይ አለመሆናቸው ታወቀ። የቅርብ ምንጮች እንደገለጹት ባለስልጣኑ በታይላንድ ባንኮክ በከፍተኛ ህክምና ላይ ይገኛሉ። ሹመቱ የተሰጣቸው በውጭ ሃገር በህክምና ላይ መሆናቸው እየታወቀ መሆኑን መረዳት ተችሏል። በቅርቡ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓም በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ በነበሩት […]
Posted in Ethiopian News, News

ሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ሳንጃ እና በጠገዴ ወረዳ ግጨው እንዲሁም አደት ልዩ ስሙ ሀመረ በተባለ ቦታ በጥዋት የተጀመረው ውጊያ ቀጥላል

በዛሬው እለት በሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ሳንጃ እና በጠገዴ ወረዳ ግጨው እንዲሁም አደት ልዩ ስሙ ሀመረ በተባለ ቦታ በጥዋት የተጀመረው ውጊያ አሁንም ድረስ የቀጠለ ሲሆን በተለይም በአደት ሀመረ ላይ በተደረገው ውጊያ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የህውሀት / ኢህአዴግ የመከላከያ ሰራዊት የተገደሉ ሲሆን ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ወታደሮች በውጊያው ቆስለዋል ሌሎች ዎታሮችም በተከፈተባቸው ውጊያ በመደናገጥ ወደ ገደል […]
Posted in Ethiopian News, News

አርበኞች ግንቦት 7 አሁንም ከፋሽስት ዎያኔ ጋር ትንቅንቁን እደቀጠለ ነው

አርበኞች ግንቦት 7 አሁንም ከፋሽስት ዎያኔ ጋር ትንቅንቁን እደቀጠለ ነው ፣ ዎያኔ ታንኮችን በብዛት አስገብታ እየተዋጋች ነው ሻለቃ መሳፍት ( ገብርየ) በነበረበት ግንባር በብዛት ታኮች እና ከባድ መሳሪያዎች የተሰለፉ ሲሆን ከፋሽስት ዎያኔ ሰራዊት በብዛት ተማርከዋል ተሰውተዋል ከአርበኞችም እንደዚሁ መስዋት የሆኑ አሉ ፣ መቸም መስዋት ሳይሆን ድል የለም ታዲያ አርበኞች ግንቦት 7 ወደፊት እየተወረወሩ ቦታ እየያዙ […]
Posted in Ethiopian News, News

በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ እንደቀጠለ ነው ፥ ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ ኢሳት በሰበር ዜናው ለተያያዘው ምስል ይቅርታ ጠየቀ

ከአርበኞች ግንቦት 7 የጦር አዛዦች አንዱ በሆነው በሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት የለውጥ ደጋፊዎች ሃዘንና ቁጭታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። በሌላም በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ አሁንም መቀጠሉን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ ኢሳት በሰበር ዜናው ለተያያዘው ምስል ዝግጅት ክፍሉ የሟቹ ቤተሰቦቹንና ተመልካቾቹን ይቅርታ ጠየቀ። የቀድሞ የደርግ መንግስት ለመጣል በተደረገው ትግል በብዓዴን/ኢህአዴግ ትግል […]
Posted in Ethiopian News, News

በአርማጭሆ የተቀሰቀሰው ጦርነት ቀጥሏል፤ የተጠለፉ የመብራት ኃይል ሠራተኞች እስካሁን አልተመለሱም

በአርማጭሆ የዐማራ ታጋዮች ከሕወሓት ወታደሮች ጋር ሲያደርጉት የዋሉት ጦርነት እስካሁን እንደቀጠለ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ዛሬ ኅዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠዋት የዐማራ ታጋዮች ከሕወሓት ወታደሮች ጋር በታች አርማጭሆና በጠገዴ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ጦርነት በከፋኝ የተደራጁ የዐማራ ታጋዮች ድል እንደቀናቸው ተናግረዋል፡፡ ከታጋዮች ጋር የነበረው ግንኙነት ከሰዐት በኋላ በአካባቢው የመገናኛ ኔትወርክ በመቋረጡ ምክንያት የተሟላ ባይሆንም ውጊያው ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት […]
Posted in Ethiopian News, News

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ከDCESON ሬዲዮ ይከታተሉ

የብሪታንያ መንግስት የሀገሩ ዜጎች ወደ አማራ ክልል እንዳይሔዱ አስጠነቀቀ በአርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል የደቡብ ወሎዋ አርጎባ ልዩ ወረዳ በወያኔ ሀይሎችና በነዋሪው መካከል ከፍተኛ ውጊያ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተነገረ፡፡   የወያኔ አገዛዝ ልትሸፍቱ ትችላላሁ በሚል ስጋት ዐማሮችን በገፍ እየሰረ ነው ተባለ፤ ።  አርበኞች ግንቦት 7 ከህወሀት አይሎች ጋር ያደረገ ያለው ውጊያ መቀጠሉ ተነገረ   የድንገተኛ […]
Posted in Ethiopian News

በአርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ረቡዕ ዕለት አንድ የጭነት መኪና በተወሰደበት ዕርምጃ መቃጠሉንም የአይን ዕማኞች ገልጸዋል። በተበታተነ መልኩ ሲካሄዱ የነበሩ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በአንድ ዕዝ በተቀናጀ መንገድ እንዲካሄዱ ስምምነት ላይ መደረሱንም በበረሃ የሚገኙት ታጣቂዎች ከኢሳት ጋር ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ ገልጸዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በተለይም […]
Posted in Ethiopian News

የብሪታንያ መንግስት የሀገሩ ዜጎች ወደ አማራ ክልል እንዳይሔዱ አስጠነቀቀ

በአማራ ክልል በመንግስት ወታደሮች እና በታጣቂ ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ መቀጠሉ ታውቋል፡፡ ራሳቸውን ያደራጁ የህዝብ ወገኖች በመንግስት በተለይም በህወሓቱ አጋዚ ወታደሮች ላይ እያደረሱ ያሉት ጥቃት መንግስትን ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል ተብሏል፡፡ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚደረገው ውጊያም የፌደራሉን ጨምሮ የክልሉን መንግስት ስጋት ላይ እደጣላቸው የመረጃ ምንጮች አመላክተዋል፡፡ እንደ መረጃዎች ገለጻ ከሆነ፣ በአርማጭሆ ውስጥ ሳንጃ በተባለ ወረዳ ከፍተኛ […]
Posted in Ethiopian News

በኢትዮጵያ መንግስት የታገቱትን ፓይለቶች ለማስፈታት የአሜሪካና የብርታኒያ ባለስልጣናት ጥረት እያደረጉ ነው።

የአሜሪካና የብሪታኒያ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ የተደረጉና በአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች እንዲለቀቁ ውይይት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ሃሙስ አስታወቁ። የተለያዩ ሃገራት ዜግነት ያላቸው እነዚሁ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ፓይለቶች አፍሪካን በሚሸፍን  የአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩ አዘጋጆች ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የውድድሩ አዘጋጆች ረቡዕ አንድ ብሪታኒያዊ ፓይለት ከሱዳን ወደ ጋምቤላ ክልል በመጓዝ ላይ እንዳለ ደብዛው መጥፋቱን አስታውቆ እንደነበር  […]
Posted in Ethiopian News, News

የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የሚፈታው በትግራይ ክልል ባለስልጣናት ውሳኔ መሆኑ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ

ለአማራ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀስ ምክንያት የሆነው የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የሚፈታው በትግራይ ክልል ባለስልጣናት ውሳኔ መሆኑ ተነገረ፡፡ ይህን ያሉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሲሆኑ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልል ያለው የወሰን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ለትግራይ ባለስልጣናት ተላልፎ መሰጠቱን ከርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ‹‹ከወልቃይት ጋር የተያያዘው ጉዳይ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ተከትሎ የትግራይ ክልል […]
Posted in Ethiopian News, News

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔ ጦር ላይ በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን በመቀጠል ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ነበልባል የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ህዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም ለሊት ጎንደር ዳንሻ ከተማ ልዩ ስሙ አዲስ አለም በተባለ ቦታ ሰፍሮ ከሚገኝ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው ድንገተኛ ማጥቃት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ አጥቅቶ ተሰውሯል፡፡ በወሰደው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃም 15 የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮችን በመግደል ቁጥራቸው ያልታወቀ ደግሞ ማቁሰሉን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራው […]
Posted in Ethiopian News, News

ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ለትግራዩ መንግስት ጦር እጄን አልሰጥም በማለት ራሱን ሰዋ

በሰሜን ጎንደር ከአማራ ታጋዮች በተጨማሪ ውጊያ እያደረገ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 በአርማጭሆ አብደራፊ ባደረገው ውጊያ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ (ገብርዬ) በሕወሓት ወታደሮች በተከበበት ወቅት እጄን አልሰጥም በማለት ራሱን በያዘው ጠመንጃ ማጥፋቱ ተሰማ:: ምንጮች እንዳሉት በሰሜን ጎንደር በተለያዩ ግንባሮች የአማራ ገበሬዎች እና የአርበኞች ግንቦት 7 የሕወሓትን መንግስት እየተዋጉት ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ኮማንደር የነበረው ሻለቃ መሳፍንት በአብራፊ […]
Posted in Ethiopian News, News

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ”ለጊዜው የመሸግንበትን ቦታ ወያኔ/ኢሕአዴግ በሄሊኮፕተር ቢደበድብም ሰራዊታችን መክቷቸዋል”

ህዳር 10/2009 ዓ.ም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተላለፈ ጥሪ በሃገራችን ኢትዮጵያ የወያኔ ኢሃዴግ ዘረኛን መንግስት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅሎ ለመጣል እንደ መስቀል ችቦ በአራቱም መአዘናት ተቀጣጥሎ የሚገኘው የነጻነት ትግል ቀና ብሎ መጓዝን አሃዱ በማለት ጀምሯል። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ባሳለፍነው ሳምንት ወስጥ በአደባይ፣በሃከር፣ ቀፍታና ሁመራ አካባቢ ከህዝብ ጠላትና ዘረኛ ስረዓት አራማጅ ከሆነው የወያኔ ኢሃዴግ ሰራዊት […]
Posted in Ethiopian News, News

ዛሬ ማለዳ ላይ ልዩ ስሙ ሸጐሌ አንበሣ ጋራዥ በተባለው አካባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ 51516 የሆነ አሸዋ የጫነ ሲኖ ትራክ መኪና ቤት ውስጥ ጥሶ በመግባት የሁለት ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል ተባለ

ዛሬ ማለዳ ላይ ልዩ ስሙ ሸጐሌ አንበሣ ጋራዥ በተባለው አካባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ 51516 የሆነ አሸዋ የጫነ ሲኖ ትራክ መኪና ቤት ውስጥ ጥሶ በመግባት የሁለት ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል ተባለ… ይህንን ያለው የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ነው፡፡ የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ እንደነገሩን ከሆነ ህይወታቸውን ያጡት በ30 እና በ32 የእድሜ […]
Posted in Ethiopian News, News

በመሰላ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ15 ዓመት ልጅ 11 ዓመት እስር ተፈረደበት ተባለ

በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የመሰላ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኦሮሚያ ክልል ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በታሰሩ 13 ተከሳሾች ላይ አመፅ በማነሳሳትና ንብረት በማውደም ጥፋተኛ ናቸው ሲል የ11 ዓመት እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ፈርዷል። ከፍርደኞቹ መካከል የ15 ዓመት ልጅና እና የስድስተኛ ክፍል ተማሪ እንደሚገኝበት ነዋሪዎቹ ይገልፃሉ። የፍርድ ሂደቱን የተከታተሉ ቤተሰቦች ፍርደኞቹ ተማሪዎችና ገበሬዎች ሲሆኑ የታሰሩትና […]
Posted in Ethiopian News, News

ጥብቅ መረጃ ልበደቡብ አፍሪካ እና አካባቢዉ ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊ።

ይህ ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ግለሰብ ይበልጣል ካሳዬ ይባላል በተለየ መልኩ ከህወሃት የደህንነት ቢሮ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በማድረግ ብዙዎችን ለአደጋ አጋልጧል ከህወሃት ጋር ባለዉ ከፍተኛ ትስስር ምክንያት ያለ በቂ የትምህርት ማስረጃ የኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ እንዲያጠና በሚል ሽፋን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ወጣት ተማሪዎች ሲያሳፍንና ሲያስገድል የነበረ ከመሆኑ ባሻገር ለስለላ ስራ ወደ ሳዉዲ አረቢያ ተልኮ በዚይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን […]
Posted in Ethiopian News, News

ሀገራችን ከገባችበት ችግር ለማዉጣት ብቸኛዉ አማራጭ የትጥቅ ትግልን ማፋፋም ነዉ ::

ታጋይ ጌትነት አናጋዉ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አመራር ሀገራችን ከገባችበት አዘቅት ዉስጥ ለማዉጣት ህዝቡ እና በሀገርዉስጥም ሆነ በዉጭ ሀገር የሚኖሩ በሰላማዊ መንገድ ስርአቱን እንቀይራለን ብለዉ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዋች ሰፊ እንቅስቃሴ ድፍን 24 አመት ሲይደርጉ ቆይተዋል ነገር ግን ይህ ትግል ገዥዉ ቡድን ካለዉ ባህሪ አንፃር እራሱን ወያኔን ሲያጠናክር እና እንደ እስስት መልኩን እየቀየረ የብዝበዛ እና […]
Posted in Ethiopian News

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡ በትላንትናው ምሽት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ማካሔዳቸውን መረጃዎች የጠቆሙ ሲሆን፣ ተቃውሞ የተካሔደውም በዩኒቨርሲቲው አዋሮ ካምፓስ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም የተነሳ ዛሬም ድረስ በጊቢው መረጋጋት እንደሌለ የጠቀሱት ምንጮች፣ በዩኒቨርሲቲው ጊቢ እና ከግቢው ውጭ የአጋዚ ወታደሮች ታጥቀው መሰማራታቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ለተቀሰቀሰው የተማሪዎች ተቃውሞ ዋነኛ […]
Posted in Ethiopian News

አርበኞች ግንቦት ሰባት ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ ስልጠና መስጠት ጀመረ ።

ሰሜን ጎንደር የነጻነት ተጋድሎው ተጠናክሮ መቀጠሉ እየተሰማ ነው፥ ወያኔ ጉድ ፈላብሽ፥ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት የሰሜን በሮችን እየሰበረ፥ ከአማራ የማንነት ጥያቄ ታጋዮችና ከአገር ውስጥ አርበኞች ጋር እየተቀላቀለ ነው። የአማራ የማንነት ጥያቄን አንግቦ፥ ለመብቱና ለነጻነቱ ለመታገል ዱር ቤቴ ያለው የጎንደር ጀግና፥ የአርበኞች ግንቦት 7 የነጻነት ኃይሎችን እጆቹን ዘርግቶ መቀበሉንና በአንድነት ተሰልፎ ወያኔን እንደሚመታ በደስታ እያወጀ ነው፥ […]
Posted in Ethiopian News, News

ጅማ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ተቃውሞ ስትናጥ አደረች

የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ የጅማ ዩኒቨርስቲ ኪቶ ፉርዲሳ ግቢ ትናንት ማታ ከአምስት ሰዓት እስከ ሠባት ሰዓት ሰልፍ ያደረጉት ተማሪዎች አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ ወዲህ የፀጥታ ኃይሎች ሌሊት ሌሊት እየገቡ ተማሪዎች ይወስዳሉ፡፡ “እስካሁን የወሰዱዋቸውን የት እንዳደረሱዋቸው አናውቅም” ብለዋል፡፡ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉት ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲው ዋናው ግቢ ዶክተር ፍቃዱ አሰፋ የሚባሉ መምህር […]
Posted in Ethiopian News, News

በመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ በኩል አማራ ክልል መድሃኒት እንዳያገኝ እየተደረገ ነው ተባለ።

ለአማራ ክልል የመድሃኒት አቅርቦት የሚያካሂዱ 3 ቅርንጫፎች አሉ።ደሴ  ባህር ዳርና ጎንደር ይገኛሉ። እነዚህ ቅርንጫፎች መድሃኒት የሚላክላቸው ከኢትዮጵያ መድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ሲሆን በሰበብ አስባቡ ለአማራ ክልል የሚላከው መድሃኒት ይዘገያል ወይም የተመደበው ተቀንሶ ነው። አገልግሎቱ የሚዘገየው  የስርጭት ትራንስፖርት ጫራታ የተሰጠው ለትግሬ በመሆኑ እንዲሁም የተቋሙ የስርጭት ዳይሬክተርም ትግሬ በመሆኑ ነው።ሌላው ምክንያት #ከኤጀንሲው ውስጥ የትግራይ ተወላጆች የዚህ ወንጀል ተባባሪ […]
Posted in Ethiopian News, News

ሰበር ዜና:-በጄኔራል ሲራጅ ፈርጌሳ የሽፋን ስእል በጄኔራል ሳሞራ የኑስ የበላይነት ቁጥጥር ስር የወደቀዉ የወታደራዊ ደህንነት የመከላከያ ሰራዊቱ ላይ አደገኛ እርምጃ በመዉሰድ አተኩሯል።

በመሆኑም ያለ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ኮማንድ ፖስቱ በስዉር እንዲያጠቃ ትእዛዝ ተላልፎለት የኮማንድ ፖስቱ ደህንነትን ተገን ያደረገዉ ዉሳኔ በ8 የመከላከያ አባላቱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በማዘዙ ትናንት በ11/03/2009 በመላዉ ሐገሪቱ የተነሳዉን ህዝባዊ እንቢተኝነት ይደግፋል ያደራጃል የተባለዉ የመካከለኛዉ እዝ ባልደረባ የም/መቶ አለቃ አለበል ትእዛዙ የዉሳኔዉ ሰለባ ሲሆን በተጨማሪ ከሰሜን እዝ ወታደራዊ መምሪያ ክፍል ወታደር ቅጣው ቢያድግልኝ ላይ […]
Posted in Ethiopian News, News

የህወሃት ወታደራዊ ደህንነት በሁለት የመከላከያ አባላቱ ላይ እርምጃ ወሰደ

የህወሃት ወታደራዊ ደህንነት በሁለት የመከላከያ አባላቱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በወሰነዉ መሰረት ትናንት በ11/ህዳር/2009 የም/መቶ አለቃ አለበል ትእዛዙ ከመካከለኛው እዝ እና ከወታደራዊ መምሪያ ሰሜን እዝ ውታደር ቅጣው ቢያድግልኝ ላይ እርምጃ ወሰደ! በመረጃ አጠባበቅና ፍልሰት ላይ ከ አርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት እንደላቸው አረጋግጫለው ያለው የ ኮማንድ ፓስቱ ደህንነት ክፍል የመከላከያ አባላቱ ላይ ድንገተኛ በሚመስል መልኩ በ […]
Posted in Ethiopian News, News

አቶ ሬድዋን ሁሴን “አህያውን ፈርቶ..

አቶ ሬድዋን ሁሴን ሚኒስትር ተደርገው እንደተሾሙ ቅድሚያ ያመሩት ወደኦሎምፒክ ኮሚቴ አካባቢ ነበር። ምክንያቱ አንድ ቀድሞ የደረሳቸው ጥቆማ ስለነበር፤ ከትጥቅ አምራች ኩባንያዎች (አዲዳስ ወይም ናይክ..) ትጥቅ የሚመጣውና ለሁሉም ስፖርት ፌዴሬሽኖች የሚከፋፈለው በኦሎምፒክ ኮሚቴ በኩል ነው። ለምሳሌ ናይክ ከሆነ ከአምራቹ ጋር ከኦሎምፒክ ኮሚቴው የተወከሉ ሰዎች ሄደው ካምፓኒውን ያናግራሉ። ሯጮች፣ ኳስ ተጨዋቾችና ሌሎች የብ/ቡድን ስፖርተኞች በየፌዴሬሽናቸው በኩል ትጥቁን […]
Posted in Ethiopian News

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት ህዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም በቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይነብሪ በተባለው ቦታ ከመቀሌ የተላከ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይል ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ድል ተጐናፅፏል። ይህ ከመቀሌ የተንቀሳቀሰው የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል ዋና ተልዕኮ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊትን እንቅስቃሴ ለመግታት ታስቦ ሲሆን […]
Posted in Ethiopian News, News

ብአዴን በሐረር ቤተ መንግሥት የጠራው ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፤

ብአዴን 36ኛ ዓመቱን ለማክበር በዓለማያ ዩንቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎችንና በሐረር ከተማ ይደግፉኛል ያላቸውን ነዋሪዎች ሰብስቦ ለማነጋገር ኅዳር 9 እና 10 ቀን 2009 ዓም ሙከራ አድርጎ ነበር። ከዓለማያ ዩንቨርሲቲ ዋና እና ሐረር ግቢዎች ተማሪዎችን ወደ ቤተ መንግሥት አዳራሽ የሚወስዱ ዐሥር አውቶቢሶችን ዩንቨርሲቲው መድቦ ነበር። የዐማራ ተማሪዎች “እናንተ እነማን ናችሁ የምትሰበስቡን? ለዐማራ ሕዝብ ሳትቆሙ የ36 ዓመት ጎልማሳ ነን […]
Posted in Ethiopian News, News

በሰሜን ጎንደር በአምስት ግምባር ከፍተኛ ጦርነት ተጀምሯል፡

በሰሜን ጎንደር በአምስት ግምባር ከፍተኛ ጦርነት ተጀምሯል፡፡ ወያኔም ጨንቋታል፡፡ ታጋዮችም በርካታ አካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል፡፡ በቅርብ ቀን ውስጥ ማለትም በ15 ወይ 20 ቀን ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ይታያል እናም መላው የሀገሪቱ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ ወያኔን ለማስወገድ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ የወያኔ ወታደር መድረሻ አጥቷል፡፡ ድሉ የህዝብ ነው በአለም ታሪክ አንድ መንግስት ህዝብ ጋር ጦርነት ከፍቶ ያሸነፈ የለም እናም […]
Posted in Ethiopian News, News

13 የሃይማኖት አባቶች አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ

በዋልድባ ገዳም እና በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ሲያገለግሉ የነበሩ 13ቱ አባቶች ወደ በረሃ ለመውረድ የወሰኑት አገዛዙ በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እያዩ ዝም ለማለት ህሊናቸውና ሃይማኖታቸው ስላልፈቀደ መሆኑን ተናግረዋል። ይሄ ጉዳይ የእነ ዶ/ር ብርሃኑ ጉዳይ ብቻ አይደለም ያሉት የሃይማኖት አባቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሎ እንዲታገል ጥሪ አስተላልፈዋል፣ ካህናቱ በአማራ ክልል ሕወሃት እየወሰደ ባለው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ […]
Posted in Ethiopian News, News

በደቡብ ኢትዮጵያ ግድያውና እስራቱ ቀጥሎአል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በደቡብ ኢትዮጵያ በፓርቲ መሪዎች፣ በፓርቲ አባላት እና በህዝብ ላይ ወታደራዊ የኃይል እርምጃን ጨምሮ ከፍተኛ የሰብዐዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ህዳር 5 /2009 ዓ.ም የኦሞ ህዝቦች ዲሞክርሲዊ ኅብረት/ ኦህዲኅ/ ምክትል ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ተጠሪ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን ፣ የዞኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል […]
Posted in Ethiopian News, News

የአርበኞች ግንቦት 7 ክ/ጦር ዛሬ ቁልፍ ቁልፍ የተባሉ ሁለት መደበኛ የዉጊያ መስመሮችን ሰብሮ በመዝለቅ ወደ ፊት እየገሰገሰ ነው

ወሃት ወያኔ በመላዉ ሐገራችን ኢትዮጵያ ላይ የደነገገዉ የአስቸክዋይ ግዜ አዋጅ በሰሜን ጎንደር ፈጽሞ ሊሰራ አለመቻሉን ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎች እያመላከቱ ይገኛሉ ዛሬ ለሶስተኛ እለት ቀጥሎ የዋለዉ የሰሜን ጎንደሩ ዉጊያ የህወሃታዊያንን ጉልበት በእጅጉ አዳክሞታል። በቃብትያ ሁመራና አጎራባች ቀበሌዎች የህወሃት ኮማንድ ፖስት በመደምሰሱ ተጨማሪ ሐይል ሲያሰባብስብ የነበረዉ የትግራይ ነጻ አዉጩዉ ቡድን ሰርከሌት በተባለዉ ስፍራ ወታደራዊ ማዘዣና ቁልፍ የአደባይ […]
Posted in Ethiopian News, News

በአማራ ክልል ሁለተኛ ዙር አፈሳ ሊጀመር መሆኑ መረጃዎች አጋለጡ

ዛሬ ህዳር 9/2009 ዓም በአማራ ክልል ሁለተኛ ዙር አፈሳ ሊጀመር መሆኑ መረጃዎች አጋለጡ በደብረታቦር የህወሓት የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ማስታወሻ /አጀንዳው /በህዝብ ልጆች ተሰርቆ ሲታይ እንዲያዙ የተፈለጉ ሰዎች በጀንዳ ውስጥ የበርካታ ሠዎች ስም ዝርዝር ተገኝቷል ስማቸው በአጀንዳው ላይ እንዲያዙ ዝርዝራቸው የተፃፈ ሠዎች ለጊዜው አምልጠዋል በተጨማሪም በማክሰኝትና አካባቢው የ25 ሠዎች ዝርዝር እንዲያዙ ማደኛ መውጣቱን በአገዛዙ ውስጥ የሚገኙ […]
Posted in Ethiopian News, News

አርበኞች ግንቦት 7 ከህወሀት አይሎች ጋር ያደረገ ያለው ውጊያ ለ3ጊዜ መቀጠሉ ተነገረ

አይቀሬው ጦርነት በይፋ ከተጀመረ ዛሬ 3ኛ ቀኑን ይዛል ጀግናው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት ከጀግኖች የአማራ ታጋይ ገበሬዎችና ከተደራጁ የነፃነት ሀይሎች ጋር በመሆን የወያኔ ሰራዊት ላይ ጠንካራና ብርቱ ክንዱን በማሳረፍ ግስጋሴውን እያፋጠነ ነው ። ~ ዛሬም እየተካሄደ ባለው ጦርነት ጀግኖቻችን የወያኔን ጦር እየሰባበሩና እያርበደበዱ ዶግ አመድ በማድረግ ወደ ጎንደር እየተቃረቡ እንደሆነ ለማወቅ ተችላል ። ~ እናም […]
Posted in Ethiopian News, News

ኤሊያስ ገብሩ፣ ዳንኤል ሽበሺ እና አናኒያ ሶሪ መታሰራቸው እየተወራ ነው፡፡

መጀመርያ እንደምንም ብለው ማኖ ያስነኩሻል,,,, ብሩክ የተባለው የፋና ቲቪ አዘጋጅ አናንያን ከሌሎች ሆድ አደሮች ጋር አድርጎ አወያየው። አናንያ ነቅሶ ችግራቸውን አፈር አስበላቸው። ያኔ ማኖ ማስነኪያ ቄራ ቤታቸውን አፀዳድተው አናነያን ጠበቁት። እንደተመኙትም በአዋጁ አመካኝተው ከተቱት። ኤልያስንም በተከራየው ቤት በኩል ምልክት ሰጡት። አገር ጥሎላቸው እንዲወጣ ነበር አልሆነም ስለዚህ ኮማንድ ፖስት የተባለ አሸባሪ ድርጅታቸውን ላኩበት። ያሳዝናል። በዲፕሎማቲክ አካባቢም […]
Posted in Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሁሉንም ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሲፒጄ ጥሪ አቀረበ

የአለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) ኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆዎርናሊስትስ የኢትዮጵያ መንግስት ለእስር የዳረጋቸውን ሁሉም ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ሃሙስ ጥሪውን አቀረበ። በሃገሪቱ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ወከባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ድርጅቱት ለመንግስት ባቀረበው የጸሁፍ መልዕክት አመልክቷል። ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ አንድ ጋዜጠኛን ጨምሮ ሁለት ጦማሪያን ለእስር መዳረጋቸውን ያወሳው ሲፒጄ ሌላ […]
Posted in Ethiopian News, News

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከሕወሃት ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ውጊያ ሲያደርጉ ውለው ከርሰሌት በምትባል ቦታ የሚገኘውን የአደባይ ተራራን ተቆጣጥረዋል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከሕወሃት ሰራዊት ጋር ከፍተኛ ውጊያ ሲያደርጉ ውለው ከርሰሌት በምትባል ቦታ የሚገኘውን የአደባይ ተራራን ተቆጣጥረዋል። በአሁኑ ወቅት በአርበኞች ግንቦት 7 ሃይሎች እና በሕወሃት ሰራዊት መካከል በቃፍታ ሁመራ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ኢሳት በስፍራው የሚገኙ እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል። “የአርበኞች ግንቦት7 የሰሜን ጎንደር አስተባባሪዎች ንቅናቄው ለአንድ ሳምንት በተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት ሲፈጽም መቆየቱን እንዲሁም […]
Posted in Ethiopian News, News

የድንገተኛ አዋጁን ተከትሎ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እየታሰሩ ይገኛሉ።

በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ተስፋፍቶ የነበረውንና በዋና ከተማዋ በአዲስ አበባ ባሉ አቅራቢያ ከተሞች ተከስቶ የነበረውን ህዝባዊ አመፅ ለማብረድ መንግስት መስከረም 29፣2009 ዓ.ም ያወጣውን የድንገተኛ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት በፖሊስ ከያሉበት እየታደኑ እስር ቤት መግባታቸውን የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህን ተከትሎ በቅርቡ የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ ሆና የተመረጠችው ወጣት ብሌን መስፍን፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር […]
Posted in Ethiopian News, News

አዋጆች በደቡብ ኦሞ በትክክል እንደማይተገበሩ የኦሕዴኅ መሪ ተናገሩ

“በሀገሪቱ የሚወጡ አዋጆች ከማዕከል ርቆ በሚገኘው ወገናችን በትክክል አይተገበርም” ሲሉ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት ሊቀ መንበር ተናግረዋል። አዲስ አበባ — እስከ ትላንት፣ ማክሰኞ፣ ኅዳር 6/2016 ዓ.ም. ድረስ ምክትላቸውን ጨምሮ አራት የፓርቲው አመራር አባላት ጂንካ ከተማ ውስጥ መታሠራቸውን የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ግርማ በቀለ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡ ፀረ-ሽብር አዋጁ በወጣበት ወቅት የፓርቲያቸው የአመራር አባላት ለሁለት ሣምንታት ታስረው […]
Posted in Ethiopian News, News

የባሕርዳር ከተማ የፓርላማ ተወካይን ወ/ሮ አዲሴን ማን ገደላቸው?

ትናንት ከቢሯቸው እንደተገደሉ መረጃዎች ቢወጡም እስካሁን ይህንን ሊያረጋግጥ ወይም ሊያጣጥል የሚችል ማስረጃ አልተገኘም። ክብርት ወ/ሮ አዲሴ ዘለቀ በ1961 ዓ.ም በደብረማርቆስ ከተማ በተወለዱ ሲሆን ከ1ኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ ዘመን ከተማ ተከታትለዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ትምህርት ያገኙ ሲሆን 2ኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በዚሁ ዩኒቨርሲቲ በኤክስኪዩኒቭ ቢዝነስ ማኔጅመንት በ2008 ዓ.ም ማግኘት ችለዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ […]
Posted in Ethiopian News, News

ሰበር ዜና፡ አማራዎች አላማጣ ከተማ ላይ ንግድ መነገድ አትችሉም ተባሉ !!!

ወያኔ ትግሬ የወሎ አማሮችን አላማጣ ከተማ ላይ መነገድ አትችሉም እያለ እያስጠነቀቀና እያስፈራራ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ እንደሚታወቀው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አላማጣ የአማራ ግዛት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በወያኔ ትግሬ ትዛዝ መሬቱ እስከ ህዝቦቹ ያለ ምንም የህግ አግባብ ወደ ትግራይ እንዲጠቃለል ተደርጓል፡፡ በጊዜው ይህንን ተቃወሙ በሺዎች የሚቆጠሩ የወሎ አማሮች እንዲገደሉ፤ እንዲታሰሩና ደብዛቸው እንዲጠፋ ተደርጓል፡፡ አሁን […]
Posted in Ethiopian News, News

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ቀንና ሌሊት በሰንሰለት እንደሚታሰር ታውቋል

ፌስቡክ ላይ በጻፋቸው ጹሁፎች ምክንያት የሽብር ክስ ቀርቦበት ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ የሚገኘውና በእስር ቂሊንጦ ያለው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በሚገኝበት እስር ቤት ውስጥ ከአርብ ህዳር 2/2009 ዓ.ም ጀምሮ ቀንና ሌሊት በሰንሰለት ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለዚህ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የዳረገው ህዳር 2/2009 ዓ.ም የፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበራቸው እነ […]
Posted in Ethiopian News, News

በጎንደር የነጻነት ትግሉ ፍም እየጣለ ነው

በትናንትናው እለት የነጻነት ትግል ተሳታፊ ናችሁ የተባሉ እስረኞችን ወቅን ከተባለች ስፍራ ወደ ዳባት ከተማ ይዘው በመጓዝ ላይ በነበሩ ፖሊሶች ላይ ሳይታሰብ ድንገት በተከፈተ ተኩስ ሁለት ፖሊሶች ሲገደሉ ሁለት እሰረኞችም በተመሳሳይ ሁኔታ ሰማዕታት ሆነዋል። ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ከፖሊስምሆነ ከእስረኞቹም የቆሰሉ መሆኑ ታውቋል። የሟቾቹ አስከሬን በዳባት ፖሊስ ጣቢያ በአሁኑ ስአት የሚገኝ ሲሆን ። ዳባት ከተማ ከፍተኛ አለመረጋጋት […]
Posted in Ethiopian News, News

አንድ የካናዳ ፓርላማ አባል በኢትዮጵያ ላይ ግፊት እንዲደርግ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ እንደሚጀመሩ አስታወቁ

የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊትን አጠናክሮ እንዲቀጥል አንድ ታዋቂ የሃገሪቱ የፓርላማ አባል ፊርማ የማሰባሰብ ዘመቻ በቅርቡ እንደሚጀምሩ ለኢሳት ገለጹ። አሌክስ ነታል የተባሉት እኚሁ የፓርላማ አባል ከተለያዩ አካላት ዘንድ የሚሰባሰበው የድጋፍ ፊርማ ለካናዳ መንግስት ቀርቦ የሃገሪቱ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ እንደሚያግዝ ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። የፓርማላ አባሉ […]
Posted in Ethiopian News, News

አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሃያ ሁለት የኦፌኮ አባላት ጉዳይ በዝግ ችሎት እንዲታይ ተጠየቀ

አቶ በቀለ ገርባን ጭምሮ በሽብር ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው ሃያ ሁለት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትና ደጋፊዎች ጉዳይ በዝግ ችሎት እንዲታይ ፍርድቤቱ ጥየቀ። አዲስ አበባ — የተከሳሽ ጠበቆች “ጥያቄው ኢሕገ መንግሥታዊ ነው” ሲሉ ተቃወሙ። ባለፈው ሣምንት ሳይቀርቡ የቀትሩት አምስቱ ተከሳሾች ዛሬ ቀርበዋል። መለስካቸው አመሃ ዝርዝር አለው። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ። http://av.voanews.com/clips/VAM/2016/11/15/dad52243-edf6-4979-8fc3-ae90e64c8d8f.mp3 Filed under: NEWS
Posted in Ethiopian News, News

የብአዴን አባሏ የፓርላማ ተመራጭ አዲሴ ዘለቀ ማክሰኞ ምሽት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተገለው ተገኙ።

የብአዴን አባሏ የፓርላማ ተመራጭ አዲሴ ዘለቀ ማክሰኞ ምሽት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተገለው ተገኙ። ሕወሓት የብአዴን ወሳኝ የሚባሉ ሰዎችን በተቀናበረ መልኩ በግደሉን ቀጥሎበታል ዛሬ ማምሻውን የፓርላማ አባል እና የብአዴን ሰው የነበረችውን ወ/ሮ አድሴ ዘለቀ ከቢሯቸው ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል ። ካሁን በፊት ታጋይ ሙሉዓለም በቢሮው ውስጥ ሞቶ ሲገኝ ማን ገደለው ለምን ተገደለ እና እንዴት ተገደለ ብሎ […]
Posted in Ethiopian News, News

በሰሜን ጎንደር በመንግስት ወታደሮችና ራሳቸውን ባደራጁ ሃይሎች መካከል ያለው ፍጥጫ እንደቀጠለ ነው።

ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ እንቃሽ አካባቢ ራሳቸውን ያደራጁ የነጻነት ሃይሎች ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር ለሳምንት የዘለቀው ፍጥጫ ዛሬም ቀጥሎአል። የቡድኑ አስተባባሪ ለኢሳት እንደገለጸው፣ ቀደም ብሎ ተደርጎ በነበረው የተኩስ ልውጥ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ምንም እንኳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች አካባቢውን ከበው በመጠባበቅ ላይ ቢሆንም፣ ጫካ የገቡት ሃይሎች አሁንም በጥሩ የጥንካሬ […]
Posted in Ethiopian News, News

ካናዳ በኢትዮጵያ ስር ነቀል የፖለቲካ ተሃድሶ እንዲደረግ ጠየቀች

ካናዳ በኢትዮጵያ ስር ነቀል የፖለቲካ ተሃድሶ እንዲደረግ የጠየቀች ሲሆን መንግስት የሚወስደው እርምጃ እጅግ ኣስጨንቆኛል በማለት ተናግራለች። ስላማዊና ኣስቸኳይ ውይይት እንዲደረግ የጠየቀችው ካናዳ በቅርቡ በኣማራና በኦሮሚያ ክልል ቤመንግስት የተፈጸሙ ግድያዎችና ኣፈናዎች ኣሳሳቢና ሊጣሩ የሚገቡ ናቸው ስትል ኣስታውቃለች። ካናዳ ለኢትዮጵያ እርዳታ ከሚሰጡ ኣገሮች እንዲሁም በፖለቲካ የተገፉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከሚያስጠጉ ኣገሮች አንዷ ናት። Filed under: NEWS
Posted in Ethiopian News, News

ሠበር ዜና በጎንደር ከፋኝ ያሉ ገበሬዎች ታሪክ እየሰሩ ነው

የጎንደር ገበሬዎች ከፋኝ ብለው በህወሓት አገዛዝ መሸፈታቸውን በጀግንነት እያስመሰከሩ ነው ለዛሬ አጥቢያ ህዳር 5/2009 ዓም ሌሊት ታች አርማጭሆ አሸሬ ዝቅ ብለን የምናገኛትን ማክሰኞ ገበያን ጀግኖቹ በሌሊት በመውረር የህወሓትን ወታደር በማባረር ተቆጣጥረዋት አድረዋል የህወሓት ወታደር የጀግኖቹ ትንፋሽ አቃጥሎት እግሬ አውጭ ብሎ ከተማዋን ለጀግኖቹ ለቆ ወጥቷል ጀግኖቹ ገበሬዎች ዛሬ ጠዋት የማክሰኞ ገበያን ህዝብ ሰብስበው በትግሉ ዙሪያና በተለይ […]
Posted in Ethiopian News, News

በደቡብ ኢትዮጵያ በስሎቫኪያና ቼክ ሪፐብሊክ ቱሪስቶች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ

በደቡብ ክልል ሚዛን ከተማ አካባቢ በጉብኝት ላይ የነበሩ 10 የስሎቫኪያና የቼክ ሪፐብሊክ ቱሪስቶች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ዝርፊያ ተፈጽሞባቸው ሹፌራቸው መገልደሉ ተገለጸ። የቼክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቀናት በፊት በክልሉ ጉብኝት በማድረግ ላይ የነበሩት ቱሪስቶች በታጠቁ ሃይሎች ገንዘብን ጨምሮ የባንክ መገልገያ ካርዶችና ሌሎች ንብረቶቻቸው እንደተወሰደባቸው ሰኞ ይፋ አድርጓል። የቼክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ የሆኑት ኢሬና ቫሌንቶባ፣ ዝርፊያ […]
Posted in Ethiopian News, News

የነጻነት ተጋድሎው በሰሜን ጎንደር ተጠናክሮ ቀጥሏል፥

አሻፈረኝ ብለው ከወያኔ ሰራዊት ጋር ለመፋለም ጫካ የከተቱ ታጣቂዎች፥ ታች አርማጭሆ ሳንጃ የወያኔ የጦር ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሰው የወያኔ ወታደሮችን መግደላቸው ተሰምቷል:: ታጣቂዎች ቅዳሜ ሌሊት ሳንጃ የሚገኘው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ወታደራዊ ካምፕ ላይ አደጋ ጥለው የጦሩን አዛዥ ጨምሮ 4 ወታደሮችን ገድለዋል፥ በተወሰደው እርምጃ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን መማረካቸውም ታውቋል። ሳንጃ ላይ ሌሊሉትን የዘለቀ ከፍተኛ ውጊያ […]
Posted in Ethiopian News, News

የውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ወርቅነህ ገበየሁን ትግሬነት ያጋለጠው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ተጨማሪ መረጃዎችን ሰጠ

.ወርቅነህን የማውቀው ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳለን ነው። ያኔ የዘር ነገር ብዙ አሳሳቢ አልነበረም ነገር ግን በሁዋላ ስናውቅ ከትግራይ ቤተሰብ ሻሸመኔ ተወልዶ አድጎ ነው። ኦሮሚኛ አቀላጥፎ ስለሚናገር ሕወሓት የሚያደርገው ሲያጣ ነው ለኦህዴድ ባለስልጣንነት የሾመው አሁን ደግሞ እሱኑ የኦሮሞ የውጭ ጉዳይ ተሾመ ይሉናል። ወርቅነህ ትግሬ እንጂ ኦሮሞ አይደለም ይሄን ዶ/ር መራራም ያውቃሉ። አስተምረውታል ከፈለጉ ቀደም ብለው ማጋለጥ ይችሉ […]
Posted in Ethiopian News

ሳንጃ የሚገኘው የወያኔ ወታደራዊ ካንፕ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት

ዛሬ 03/2009 ለ04/2009 ዓም ሌሊት 6 :40 ላይ ሳንጃ የሚገኘው የወያኔ ወታደራዊ ካንፕ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት ጀግኖቹ የአማራ ገበሬዎች የነጻነት ተዋጊዎች ወታደራዊ ካንፑን በሌሊት በመውረር ቁጥራቸው ያልታወቀ የወያኔ ወታደሮችን መግደላቸው ታውቋል እንዲሁም በርካታ የጦር መሣሪያ እና ወታደሮችን ይዘው መሠወራቸው ተረጋግጧል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ሣንጃ ጦር ካንፕ አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል በአከባቢው ሰው ማለፍ እንደማይቻል ምንጮች […]
Posted in Ethiopian News, News

-አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ሰሜን ጎንደር እንቃሽ

ሰሜን ጎንደር እንቃሽ ላይ አምስተኛ ቀኑን በዘለቀው ጦርነት የተበሳጨው ወያኔ ያለ የሌለ ሃይሉን በመላክ ከበባ በማድረግ ላይ ስለሆነ በጀግንነት እየተዋጋ ያለው የገበሬ ጦር አፋጣኝ ትብብር ከቅርብም ከሩቅም ላለ ወገን አቅርቧል። 1) በተለይም በጃኖራ፣ በአጅሬ፣ በቆላ ወገራ ያለው ወገን በፍጥነት እንዲደርስ። 2) በኪንፋዝ በለሳ ያለው ወገን አቆራርጦ እንዲደርስ። 3) በቆላ መረባና በመሬና ያለው ወገን ደግሞ በበርሃው […]
Posted in Ethiopian News, News

የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባላት ተሰብስበው በሙስና ወንጀል ታስረው የነበሩትን የፓርቲው አባላት ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል

የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባላት ተሰብስበው በሙስና ወንጀል ታስረው የነበሩትን የፓርቲው አባላት ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል በዚህ መሰረት በሙስና ወንጀል የተፈረዱና የተጠረጠሩ እስረኞች (የህወሓት አባላት) በሙሉ ከእስር መለቀቃቸው ተረጋግጧል። ምክንያት፡ ሁሉም የህወሐት አባላት በሙስና መጨማለቃቸው በመረጋገጡና “ማን ታስሮ ማን ይቀራል?!” የሚል ውዝግብ በመነሳቱ ነው። እናም ሁሉም የህወሓት አመራር ከሚታሰር የታሰረ ሁሉ ይፈታ ተብሏል። ለህወሓት ሰዎች ሙስና ህጋዊ […]
Posted in Ethiopian News, News

ጦማሪ በፈቃዱ ኃይሉ መሪ አከባቢ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ተዘዋወረ

በትላንትናው ዕለት በጠቅላይ እዙ ትፈለጋለህ ተብሎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ጦማሪ በፈቃዱ ኃይሉ ሲምሲ አከባቢ ወደሚኘው በየካ/ክ/ከ/ የማኅ/አቀፍ የመሪ እና አከባቢው የማኀ/አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ጣቢያ መዘዋወሩ ታዉቋል። ለጠቅላይ እዙ ቃሉን እንደሰጠና ፍርድ ቤትም የማይቀርብ መሆኑም ተረጋግጧል። የቀረበበት ውንጀላም ለአሜሪካን ድምፅ አማርኛ መርሐግብር በሰጠኸው ቃለ መጠይቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎችን መብት እንደሚያፍን በመግለፅ አጥላልተሃል የሚል ነው። […]
Posted in Ethiopian News, News

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ፋግታ ለኮማ እንደውሃ ቀበሌ በሚገኘው የዝረሂ ተራራ ላይ የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ተከሰተ፡፡

እስካሁን ድረስም 400 ሜትር አካባቢ የሚረዝመው የተራራው ክፍል በጭስ በመሸፈን ላይ ነው፡፡ የእሳተገምራ ፍንዳታ (volcanic eruption) በብዛት በሞቃታማ አካባቢዎች ይፈጠራል ፡፡አሁን የተነሳበት ቦታ ግን ውሃማ እና ከፍተኛ ከሆነ ቦታ ላይ ነው፡፡በዚህ ሁኔታ እንዴት እንደተከሰተ ለማወቅ የባህር ዳር ዩኒቨርሲተ በነገው ዕለት ከጃፓናውያን የከስርሰምድር ባለሙያዎች ጋር ጥናት ለማድረግ ወደ ቦታው ያመራሉ፡፡ በክስተቱ የሰው ህይወት ባይጠፋም፣ በአዕፍትና በእፅዋት […]
Posted in Ethiopian News, News

እነ አቶ በቀለ ገርባ ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው ለፍርድ ቤት ተናገሩ

መቅረብ ከነበረባቸው 22 ሰዎች አምስቱ አልቀረቡም – “አራቱ የተለያየ እስር ቤት ስለሆኑ አላቀረብኳቸውም አንዱ ግን የት እንዳለ አላውቅም” ፖሊስ ከቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ በኋላ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት በዐቃቤ ሕግ በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትና ደጋፊዎች መካከል አምስቱ ዛሬ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ። ተጠርጣሪዎቹ […]
Posted in Ethiopian News, News

ሰሜን ጎንደር አምባጊዮርጊስ አካባቢ ልዩ ስሙ እንቃሽ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ለሶስተኛ ቀን ከባድ ውግያ የተካሄደ ነው ተባለ

ሰሜን ጎንደር አምባጊዮርጊስ አካባቢ ልዩ ስሙ እንቃሽ ተብሎ የሚጠራ የጀግና መፍለቂያ ላይ በገበሬው ሰራዊትና በአጋዚ መካከል የሚካሄደው በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ ከባድ ውጊያ ለሶስተኛ ቀን ቀጥሏል። በአጋዚ በኩል ከ80 በላይ እንደሞተና ብዙ እንደተማረከ ከቦታው አረጋግጠናል።ዲሽቃ፣ ብሬን፣ መትረጌስና ስናይፐር መሳሪያወች ተማርከዋል። ከገበሬው በኩልም እስካሁን ወደ 6 ጀግኖች ተሰውተዋል። ወያኔ የተማረኩትን ወታደሮችና የቡድን መሳሪያወች መልሱልኝ በማለት የሃይማኖት […]
Posted in Ethiopian News, News

የሳሞራና የጌታቸው ግብግብ እና እንድምታው

በአሁኑ ሰዓት የህወሓት አገዛዝ የገባበት ቀውስ እየተወሳሰበ ነው። አሁን እውነተኛ የመንግሥት ስልጣን ያለው በሳሞራ የኑስ እጅ ውስጥ ቢሆንም እንኳን ተቀናቃኙ ጌታቸው አሰፋ ሽንፈቱን ሙሉ በሙሉ አልተቀበለም። የሳሞራ የኑስ ቀኝ እጅ የሆነው በገብሬ አድሀና (ዲላ) የሚመራው ወታደራዊ መረጃ የጌታቸው አሰፋን “የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን” ሊውጥ አፉን ከፍቷል። ጌታቸው የኃይለማርያምን ካቢኔ ከቀውስ የመውጫ ቀዳዳ ሊያደርገው እየጣረ ነው። […]
Posted in Ethiopian News, News

የኢትዮጵያ ፖሊቲከኞች ከአሜሪካ ፖሊቲከኞች ምን ይማራሉ?

መስፍን ወልደ ማርያም ኅዳር/2009 የአሜሪካንን ምርጫ ስከታተል ሃምሳ ዓመታት አልፈውኛል፤ ነገር ግን ተወዳዳሪ ፖሊቲከኞቹንም፣ ሕዝቡንም፣ ጋዜጠኞችንም በሚያሳፍር (የሚያፍር ከተገኘ!) ሁኔታ በጭቅጭቅና በስድብ የታጀበ ውድድር ስመለከት ይህ የመጀመሪያዬ ነው፤ እኛ ወደነሱ እንሄዳለን ስንል እነሱ ወደኛ እየመጡ ይመስላል፡፡ በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ፖሊቲከኞቻችን ሁሉ ፖሊቲከኛ መሆን የሚቸገሩበትን ምክንያት በአሜሪካኑ የምርጫ ውድድር ላይ በገሀድ ያየነው ይመስለኛል፤ ኦባማና ትረምፕ በሃያ አራት […]
Posted in Ethiopian News, News

ምስ/ጎጃም ወጥቶ መመለስ አዳጋች ሆኗል።

ህወሀት በልጁ ብአዴን አማካኝነት የተሳለውን የበቀል ካራ በጎጃሞች አንገት ላይ ማሳረፉን ተያይዞታል።ምስ/ጎጃም ሰላም አይደለም በተለይ ሞጣ ቀራኒዮና ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ግንደወይን ከተማ አፈናውና አፈሳው ከምንጊዜውም በላይ ጨምሯል።ይህ ግፍና በደል የሚፈፀመው ደግሞ በህወሀት እጅ በተሰሩት የብአዴን ሰወች ጠቋሚና ተባባሪነት በመሆኑ ህመሙን ያበረታዋል። ከቀናት በፊት በሞጣ ከተማ ፕሪፓራትሪ ት/ቤት አንድ መምህሪ በመንግስታዊ የሺብር ቡድኑ ታፍኖ በመታሰሩ […]
Posted in Ethiopian News, News

በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አንድ ዓመት ሞላው

በኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና አመጽ አንድ ዓመት ሞላው። በኢትዮጵያ ትልቁን ቁጥር ለሚይዘው የኦሮሞ ማኅበረሰብ የተቃውሞ መነሻ የሆኑት የፖለቲካ ነፃነት እና ፍትሃዊ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄዎች ዛሬስ ተመልሰው ይኾን? የአሜሪካ ድምጿ ማርታ ቫንዶርፍ ከብራስልስ ባጠናቀረችው ዘገባዋ ታነሳዋለች። በሌላ በኩል የኦሎምፒክ የማራቶን የብር ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ለሊሳ ፈይሳ፣ የግንቦት ሰባቱ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና […]
Posted in Ethiopian News, News

በወገራ ወታደሮች ገበሬዎችን ለማጥቃት ምሽግ እየቆፈሩ እንደሆነ ታወቀ፤

በገበሬዎች የተማረከውን የጦር መሣሪያ ለማስመለስ በሃይማኖት አባቶች ሙከራ አድርጎ ያልተሳካለት የወያኔ ጦር ምሽግ እየቆፈረ እንደሆነ የጎበዝ አለቆች አስታወቁ። የጎበዝ አለቆቹ እንደሚሉት ዛሬ ሰላም ይወዳርዳል በማለት 15 የማረክናቸውን ወታደሮች ለቀንላቸው ነበር። ሆኖም ወያኔዎች የማረካችሁትን መሣሪያም መልሱልን አሉን። ወታደሮቹን መልቀቅ አልነበረብንም፤ የሃይማኖት አባቶች ሲያስቸግሩን ሰላም ይውረድ ብለን ነበር የሸኘናቸው። ግን ዘግይተን መሳሳታችን አወቅን። ሊገሉን ስለመጡ መሞት ነበረባቸው። […]
Posted in Ethiopian News, News

በምዕራብ ዐማራ ሞጣ ከተማ ዛሬ 7 መምህራን ታስረዋል እንዲሁም ከተማዋ በወታደር ተሞልታለች

ጀነራል አበበ የተባሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ በአማራ ክልል አስፋጻሚ ከሆኑት አንዱ ትናት የመሰናዶ መምህራንን ሰብስበው እኔ የተላኩት ሙሉ መምህራንን እንዳስር ነው አዋጁን ስለጣሳቹህ ካሉ ቡሃላ ዛሬ ሌሊት 10 ሰዐት 7 መምህራን ከቤታቸው በማስገደድ ወስደው አስራዋቸዋል 6 የከፍተኛ መሰናዶ መምህራን ሲሆኑ አንዱ መምህር መኳንት ከሞጣ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መሆኑ ታውቋል። ወታደር በየትምህርት ቤቶችና በከተማዋ ዋና […]
Posted in Ethiopian News, News

ከትናንት ጀምሮ በተደረገ ውጊያ በወገራ 50 ወታደሮች ሲማረኩ ቁጥራቸው የበዛ ደግሞ መገደላቸው ተነገረ፤

በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ የእንቃሽ ቀበሌ የዐማራ ገበሬዎችን ትጥቅ ለመንጠቅ የተንቀሳቀሰው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ በምርኮና በሞት ተደምስሷል፡፡ ከቦታው በስልክ ያነጋገርናቸው የጎበዝ አለቆች ‹‹ሆን ብለው አዝመራችን በምንሸክፍበት በዚህ ወቅት መሣሪያ ለመግፈፍ መጡብን፤ እኛም ገጥመን ፈጀናቸው›› ብለዋል፡፡ ከትናንት ጥቅምት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ከሰዐት በኋላ ጀምሮ ሌሊቱን ባደረው ጦርነት 50 የሚሆኑ ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ተማርከዋል፡፡ […]
Posted in Ethiopian News, News

ትጥቅ ለማስፈታት ወደ አማራ ክልል ሰሜን ጎንደር የተንቀሳቀሰው የመንግስት ሃይል ከህዝብና ራሳቸውን የነጻነት ሃይሎች ከሚሉ ታጣቂዎች ከፍተኛ ጥቃት ተሰነዘረበት

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ ትጥቅ ለማስፈታት ወደ አማራ ክልል በተለይም ሰሜን ጎንደር የተንቀሳቀሰው የመንግስት ሃይል ከህዝብና ራሳቸውን የነጻነት ሃይሎች ከሚሉ ታጣቂዎች ከፍተኛ አጸፋ እንደተሰነዘረባቸው መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልጹ። በወገራ ወረዳ እንቃሽ አካባቢ በተካሄደው ጦርነት 30 ታጣቂዎችና ወታደሮች ከነመሳሪያቸው መማረካቸውን የነጻነት ሃይሎች ተናግረዋል። ተጨማሪ 3 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ወደ አካባቢው ተጉዘዋል። በተለይም አንቃሽ በተባለ ቦታ ላይ ሽፍቶችን […]
Posted in Ethiopian News, News

የባህርዳር ፖሊስ ከእስረኛ ቤተሰቦች ጋር ተፋጣል

የታሰሩ የደባርቅ ወጣቶችን ከፓሊስ ጣብያ አውጥተው የት እንደሚወስዷቸው አልታዎቀም፡፡ እናቶች በአሁኑ ሠዓት እያለቀሱ ይገኛሉ ህዝብ ፓሊስ ጣብያ ሞልቶ ይገኛል።አሁን የመኪናው ሹፌር አጋዚዎች ጫን ብለው ከወሰዱት በሁዋላ ወጣቶች መሆናቸውን ሲያውቅ አልጭንም በማለት ከህዝብ ጋር መሆኑን አሳይቷል ጭቅጭቅ እንደቀጠለ ነው። ልጆቻችንን አናስወስድም ያለውን ህዝብ ለመበተን ጥይት መተኮሳቸው ታውቋል። በእስር ላይ ያሉት ወጣቶች ግን ህዝቡን ሲያስተባብሩ ተስተውሏል። እባካችሁ […]
Posted in Ethiopian News, News

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሁኔታ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ የብሪታኒያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጠየቁ

የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት የሃገሪቱ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበትን ሁኔታ ተከታትሎ ለህዝብ በአስቸኳይ ይፋ እንዲያደርግ በድጋሚ ጥሪን አቀረቡ። የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች በብሪታኒያ ባለስልጣናት በኩል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደማይገኙ መረጃን ቢሰጡም የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ማረጋገጫ አለማግኘቱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ከነሃሴ ወር ጀምሮ አቶ […]
Posted in Ethiopian News

በሰሜን ጎንደር በወገራ ወረዳ በገበሬዎች ላይ ጦርነት ተከፍቷል፤

በሰ/ጎንደር በወገራ ወረዳ እንቃሽ ቀበሌ የገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የሄደው የአጋዚ ወታደር በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጦርነት ከፍቷል። እስካሁን ድረስ 5 ያክል ወታደሮች በገበሬው ጦር መሞታቸውን እና 15 ክላሽንኮቭ መሳሪያ መማረካቸውን የጎበዝ አለቆች ከቦታው አስታውቀዋል። የጎበዝ አለቆቹ ሌላው የአማራ ሕዝብ እንዲደርስላቸውም ጥሪ አስተላልፈዋል። በወገራ ወረዳ የተቀሰቀሰው ጦርነት በቶሎ የሚበርድ አይመስልም ሲሉም አስተያየታቸውን ገልጸዋል። የበለሳና የአርማጭሆ አማሮች ወደ […]
Posted in Ethiopian News, News

የአውሮፓ ሕብረት የፖለቲካ መሪዎችንና ታዋቂ ሰዎችን ማነጋገር ጀመረ

ዛሬ የአውሮፓ ሕብረት በብራስልስ ባደረገው ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያውያኖችን ጋብዞ አነጋገረ። ከተጋባዦቹ መካከል ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ፕ/ር መረራ ጉዲና እና አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ይገኙበታል። በስብሰባው ላይ አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ንግግር ማድረጉን ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ ጠቁሟል። ሁለቱም ፕሮፌሠሮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ንግግር ማድረጋቸውንም ለመረዳት ችለናል። የአውሮፓ ሕብረት […]
Posted in Ethiopian News, News

ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ተማሪዎች ዶርም በእሳት ጋየ ::

ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ተማሪዎች ዶርም በእሳት ጋየ ::ዩንቨርስቲው አግዶት የነበረውን welcome ceremony ትናንትና ጀምሮ ቢፈቀድም ፤ ትናንትን የትግርኛ ሙዚቃ well come ጋር በመጋበዙ አዳራሹ በጨኸት እየተናወጠ ተማሪዎች አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል። ይሔ ከሆነ ከ1 ቀን በኋላ በአሁኗ ሠአት የአዲስ ተማሪዎች ዶርም በእሳት እየጋየ ነው። እሳቱ በጣም ከባድ ነው። ከአሁኑ ጋር ይህ block ሲቃጠል 3 ኛው ነው። […]
Posted in Ethiopian News, News

ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፅህፈት ቤቶቻቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ለመቀየር እያሰላሰሉ ነው።

ሕወሓት ለስልጣኑ ሲል ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ የማውደም ሥራ እየሰራ ነው።በዐማራ ክልል ከገጠር እስከ ከተማ ፍፁም ፋሽሽታዊ በሆነ መልኩ በሕዝቡ ላይ ግድያ እና እስር እየተፈፀመ ነው።ይህ በእንዲህ እያለ የኢንተርኔት አገልግሎት በመቆራረጡ እና በአብዛኛው ጊዜ ዝግ በመሆኑ የአፍሪካ ኅብረት፣ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቢሮዎቻቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ለመቀየር እያሰላሰሉ ነው። በኢንተርኔት ምክንያት ሥራ መስራት […]
Posted in Ethiopian News, News

“በውጭ ሀገር ሠላማዊ ሠልፍ የተሳተፉ ሠዎች ቤተሠቦች እየታሠሩ ነው” – ሒውማን ራይትስ ወች

  በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል በአውስትራሊያ በሰኔ ወር ሠላማዊ ሠልፍ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊ በዕድሜ የገፉ ወላጅ እናት እንደሚገኙበትም ታውቋል። የዚህ ግለሰብ ሶስት ወንድሞችም የደረሱበት መጥፋቱን የመብት ድርጅቱ ዘግቧል። የ25 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ሹክሪ ሻሃፌ ጉሌድ ተወልደው ያደጉት በሶማሊያ ክልል ሲሆን በአውስትራሊያ ለአለፉት ስድሥት ዓመታት ኖረዋል፤ በአለፈው ሰኔ ወር ሜልበርን አውስትራሊያ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሐሙድ ኡማር […]
Posted in Ethiopian News, News

“የአፋር ሕዝብ የኦሮሞዎችን እና የአማሮችን ትግል ይቀላቀላል ፣በቅርቡም የምናየው ይሆናል ” ~ ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራ

የአፋር ህዝብ እየደረሰበት ያለው መከራ ከምንጊዜውም በላይ እየከፋ በመምጣቱ የኦሮሞዎችንና የአማራዎችን እንዲሁም የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ትግል የሚቀላቀልበት ምዕራፍ ላይ መድረሱን ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ገልጹ። የአፋር ህዝብ ሱልጣን በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት የቀድሞ ዲፕሎማትና የክልሉ ፕሬዚደንት ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ፣ በቅርብ ወራት ውስጥ የአፋርን ህዝብ የለውጥ እንቅስቃሴ እናያለን ሲሉ ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል። ሱልጣን ሃንፍሬ አሊምራህ በዋሽንግተን ዲሲ […]
Posted in Ethiopian News, News

የወያኔ ተላላኪው ደህዴን በወላይታ የሚኖሩ አማራዎች ለማፈናቀል እንቅሥቃሤ ጀምረዋል ተባለ፡፡

ወያኔ ካፈራቸው አሻንጉሊቶች አንዱ ደህዴን እና ሥጋ ለበስ አሻንጉሊቱ አባላቶቹ ይገኙበታል፡፡ በደቡብ ውስጥ ከትግሬ የዘር ግንድ (የንጉስ ጦና የዘር ግንድ አልን የሚሉት) ጋር ግንኙነት አለን ብለው የሚያስቡ ወላይታ ውስጥ ካሉት ንዑሳን ወላይቶች በተደጋጋሚ የሚነገር ተረታቸው ነው፡፡ እነዚህ ንዑሳ ወላይቶች ከወያኔ በተነገራቸው ልብ ወለድ ከጎረቤቶቻቸው ማለትም ከሲዳሞ፣ ጎፋ እንዲሁም ከኦሮሚያ (ሻሼመኔ) ከሚገኙ ማህበረስብ ጋር ደሮና ጥሬ […]
Posted in Ethiopian News, News

ህዝቡን ግን በእውነት አዋጁ ገድቦታልን?

ወያኔ ይህን አፋኝ አዋጅ ባወጀ ማግስት በተልቱላ ሚዲያው አዋጁ መታወጁ የህብረተሰቡን ሰላም መልሷል ብሎ ተናግሯል። ግን የህዝቡ ዝምታ አዋጁ ስለገደበው ይሆን? አይደለም። 1. እጅን አጣምሮ መውጣት በአደባባይ ግደለኝ መጥቸልሃለሁ እንደማለት ስለሆነ ይህን የትግል ስልት በሌሎች ስልቶች ለመተካት ሲባል ነው። 2. የትጥቅ መሳሪያዎችን በእጅ ለማስገባት ዝንታው የተሻለ ስለነበር ነው። 3. በጎንደር ሁመራ ሰሊጥ ተሰብስቦ እስኪያልቅ ድረስ […]
Posted in Ethiopian News

የሞጣ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪወች በዛሬው እለት ከፍተኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ ናቸው።

የሞጣ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪወች በዛሬው እለት ከፍተኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ ናቸው። እንቅስቃሴው የተጀመረው ፀረ አማራው መንግስት በሞጣ ፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት የሂሳብ መምህር የሆኑትን አቶ ሰለሞን አራጌን አፍኖ በመውሰዱ ነው። በአሁኑ ሰዓት የወያኔ ኮማንድ ፓስት ንፁሃን የአማራ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ እርምጃ እየወሰ ነው። የጉዳቱ መጠን ሲደርሰን እናሳውቃለን ። በተያያዘ ዜና በዳባት ወረዳ በጃንበለው ቀበሌ አደለይ […]
Posted in Ethiopian News, News

የብአዴንን የጥልቅ ተሃድሶ ህወሃት ውድቅ አደረገባቸው።

ለ3ኛ ጊዜ የተገማገመው ብአዴን ህወሃትን ስላላስደሰተው እንደገና ይገማገሙ በማለት ባለ11 ነጥብ የመገማገሚያ መስፈርት ተልኮላቸዋል። ደመቀ መኮንን ብአዴን በጥልቀት ታድሰናል በማለት በቴሌቪዥን ወጥቶ ሊ/መንበሩ እና ምክትሉ በከባድ ማስጠንቀቂያ፣አንድ ሰው ደግሞ ከማዕከላዊ ኮሚቴ በማሰናበት እና ሌሎች ላይ ቀላል ቅጣት ማስተላለፉን ተናግሮ ነበር። ይህንን ሪፖርት የተመለከተው የበላይ ጠባቂያቸው ህወሃት ግን የብአዴንን ግምገማ አላመንኩበትምበማለቱ ከአርብ ዕለት ጀምረው እንደገና ለግምገማ […]
Posted in Ethiopian News, News

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ውይይት እንዲጀመር የኢትዮጵያ መንግስትን ጠየቁ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሳዛና ዙማ በኢትዮጵያ የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ አስቸኳይ የፖለቲካ ውይይት ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ ጥሪ አስተላለፉ፡፡በአገሪቱ የመጨረሻ መፍትሄ ለማግኘት መነጋገር በጣም ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ ወይሮዋ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባር ላይ ሲያውል የዜጎች መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበራቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ ተቃውሞውን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ዕቀባ መደረጉን የተቃወሙት ዙማ […]
Posted in Ethiopian News, News

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ አስመርቋል ፡፡

የኢትዮጲያን ህዝብ ከጭቆናና የስቃይ ህይወት ለማላቀቅ እና አምባገነኑን የህወሓት አገዛዝ ገርስሶ ለመጣል የትጥቅ ትግል እያደረገ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ለወራት ያክል በወታደራዊ ፣ ፖለቲካዊና ሌሎች ተጓዳኝ ትምህርቶች ዙሪያ ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን ምልምል አርበኛ ታጋዮች እሁድ ጥቅምት 27 ቀን 2009 ዓ.ም. በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል ፡፡ በዚህም የምረቃ ስነ-ስርዓት በዓል ላይ የድርጅቱ […]
Posted in Ethiopian News

የአየለ ጫሚሶ ቢሮውን አከራይቶ እየበላ ነው “ተባለ

የአየለ ጫሚሶ ቢሮ አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ትገኛለች ።በፋይዚት ተከፋፍላ ኮምፒውተር ተደርድሮባት ሁልጊዜም በሯ ወለል ተደርጎ ይከፈታል ። በሯ ላይ የተለጠፈውን “ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ “የሚል ታፔላ ተመልክተው ወደ ውስጥ ሲያማትሩ ወጣገባ የሚሉ ሰዎችን ይመለከቱና “እንዴ ይሄ ፓርቲ ዘንድሮም ሰው ይከተለዋል “ሊሉ ይችላሉ ።ነገሩ ግን ሌላ ነው ። የፓርቲው ቢሮ በፋይዚት መከፋፈሉን ነግሬዎት […]
Posted in Ethiopian News, News

ኢትዬጵያውያን በእስራኤል አደባባይ የድረሱልን ጥሪ አሰምተዋል።

በእስራኤል ምድር ውስጥ ከ135,500 በላይ ኢትዬጵያውያን ጂውሾች ይኖራሉ አብዛኞቹም የጎንደር ጀግኖች ናቸው። እኒህ ኢትዬጵያውያን በምቾት ነው የሚኖሩት ወደ ሰላማዊ ሰልፍ የሚገፋፋቸው ነገር ቢኖር በኢትዬጵያ ውስጥ የሚኖሩ በነፃነት እጦት የታፈኑ በጥይት የተገደሉ ወገኖቻቸው ደም ነው። እኒህ የአርበኛ ልጆች ኢትዬጵያውያን በእስራኤል አደባባይ የድረሱልን ጥሪ አሰምተዋል። የእራኤል የሚመለከተው የመንግስት አካል እንዲህ ብሏል። ከዚህ በሃላ ኡትዬጵያ ውስጥ ምንም አይነት […]
Posted in Ethiopian News, News

“ደባርቅ ሰሜን ጎንደር የጅምላ እስር እየተካሄደ ነው!

የደባርቅ መውጫ መግቢያ በወታደር ታጥሯል ለጊዜው የሶስት ወጣቶች ስም ዝርዝር ደርሶኛል 1. አግንቸ ማውሻ 2. ሐብታሙ መኮነን 3. መልስ ጌታቸውFiled under: NEWS
Posted in Ethiopian News, News

በአዉሮፓ የስደተኛዉ ቁጥር ላይ ዕቀባ ማድረጉን አስከትሎ ወደ አገራቸዉ ለሚመለሱት ስደተኞች አስፈላጊዉን እርዳታ እንደሚያደርጉ የአዉሮፓ ሕብረት ገለፀ።

በምሕፃረ ቃል IOM በመባል ሚታወቀው የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት እንደገለፀዉ ባለፉት ሁለት ወራት ዉስጥ ሕጋዊነት የሌላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ከየመን፤ ከዛምቢያ፤ ከሳዉዝ አፍሪካ፤ ከታንዛኒያ፤ እና ከሳዉዲ አረቢያ በግዳጅ መመለሳቸዉን ገልፆአል። በአሁኑ ጊዜ ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ የተባሉት እነዚሁ በአዉሮፓ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸዉ ኢትዮጵያዉያኖች ምን ያህል እንደሆኑ አልታወቀም። ኢትዮጵያዉያኖቹ ህይወታቸዉን አደጋ ላይ ጥለዉ እና በጣም አስቸጋሪ ጉዞ ተጉዘዉ […]
Posted in Ethiopian News, News

“ኮማንድ ፖስቱ ገና አልተደራጀም ተብያለሁ። እስከዛሬም ማንም ያነጋገረኝ አካል የለም”

ዳግማዊ ተሰማ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሃላፊና የምክር ቤት አባል የነበረው ዳግማዊ ተሰማን እኔ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አናንያ ሶሪ፣ ሃብታሙ ምናለና ፍቃዱ በቀለ ካዛንቺስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጠይቀነው ነበር። ዳግምም “ከታሰርኩ ዛሬ ሳምንቴ ነው። እስከዛሬ ማንም ያነጋገረኝ አካል የለም። ስም፣ አድራሻዬንና የትምህርት ደረጃዬን ብቻ ነው የተጠየኩት። ኮማንድ ፖስቱ ገና አልተደራጀም […]
Posted in Ethiopian News, News