Home › View all posts by Addis Admas
Blog Archives
“አገሪቱ አይታ በማታውቀው የዲሞክራሲ ለውጥ ውስጥ ገብታለች” ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መምራት ከጀመሩበት ሚያዚያ 2010 ዓ.ም ወዲህ ሃገሪቱ የዲሞክራሲ መሻሻሎችን እንዳሳየች ያስታወቀው ፍሪደም ሐውስ፤ አሁንም ዲሞክራሲውን እውነተኛ ለማድረግና ነፃ ህዝብ ለመፍጠር ሃገሪቱ ብዙ ሥራዎች ይቀራታል ብሏል፡፡ የዓለም ሃገራትን የዲሞክራሲ ይዞታ በየዓመቱ እየገመገመ ይፋ የሚያደርገው ፍሪደም ሃውስ፤ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በሃገሪቱ በተፈጠረ ህዝባዊ አመፅና የዲሞክራሲ ጥያቄ ምክንያት ስልጣንን ለብቻው ጠቅሎ ይዞ የነበረው ኃይል ተፈረካክሷል፣ አሁን ሃገሪቱን የሚመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር የለውጥ ኃይል ናቸው ብሏል፡፡ ለውጥን የሚያራምዱት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ነፃ የፖለቲካ ውይይት መስፋፋቱን፣ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸውን፣ ለመገናኛ ብዙኃን ነፃነት መሰጠቱን ያስታወሰው ሪፖርቱ፤ ነገር ግን አሁንም የሃገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መቶ በመቶ በአንድ የፖለቲካ ኃይል መያዙን አስታውቋል፡፡ የፓርላማ ውክልና በተመለከተ ኢትዮጵያ ከ12 በተያዘው የመለኪያ ነጥብ 1 ብቻ ማግኘቷንም አስታውቋል፡፡ ይህ የህዝብ ውክልና በቀጣይ እውነተኛ ሆኖ ሊረጋገጥ ይገባል ያለው ሪፖርቱ፤ ኢትዮጵያ ወደ ተጨባጭ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ተሸጋገረች
ፕ/ር መረራ ጉዲና በጐንደር ዩኒቨርሲቲ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል የሀገሪቱ ምሁራን ለሀገሪቱ የፌደራሊዝምና የፖለቲካ ችግር መፍትሔ ማምጣት እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡ የጐንደር ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ማናጅመንት ትምህርት ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው የፖለቲካ ውይይት መድረክ ላይ ፕ/ር መረራ ጉዲና፣ የጠ/ሚሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ዶ/ር አምባቸው መኮንንና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ ባለፈው ረቡዕ “የምሁራን ሚና እና አስተዋጽኦ በሀገሪቱ ፖለቲካ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ውይይት ላይ ፕ/ር መረራ ባቀረቡት ፅሑፍ “ምሁራን የታሪክ ፈተና አሁንም አለብን፤ ይሄን የታሪክ ፈተና የምንፈታበትን መንገድ እስካሁንም አላገኘነውም” ብለዋል፡፡ የታሪክ ፈተናን ለማለፍና የሀገሪቱን የፖለቲካ ‹ቡዳ› ለይቶ ለማውጣት ምሁራን ተግተው መስራት እንዳለባቸው፣ ሃላፊነትም በጫንቃቸው እንዳረፈ ጠቁመው፤ ለግጭትና መከፋፈል ምክንያት እየሆነ ያለውን የፌደራል ስርአት በተመለከተ ሠፊ ጥናቶችና ምርምሮች ሊሠሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ባለፉት 27 አመታት ጐንደርን ጐብኝተው እንደማያውቁና ወደ ጐንደር ከሄዱ ረጅም ዘመን እንዳስቆጠሩ የጠቆሙት ፕ/ር መረራ፤ እንዲህ ዝግ ያልሆኑና ሁሉን አቀፍ የምሁራን ውይይት በየአካባቢው ሊከፈቱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ምሁራን እንደከዚህ ቀደሙ ዳር ሆነው ከመመልከት በእውቀት
የእውቁ የህወሓት ታጋይና የትግርኛ ዘፋኝ ብርሃኑ ጋኖ እናት በችግር ጐዳና ላይ መውጣታቸው ተጠቆመ፡፡ ወይዘሮዋ 6 ልጆቻቸውን ለህወሓት ትግል ገብረው ጧሪ ቀባሪ በማጣት፣ በአሳዛኝ ሁኔታ በመቀሌ ጐዳና ላይ መውደቃቸውንና በቅርቡ ወደ ተንቤን መሄዳቸውን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁት አቶ አርአያ ተስፋማርያም ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ የህወሓት ታጋዮች በወኔ ወደ ትግል እንዲገቡ ሲቀሰቅሱና ሲያነሳሱ ከነበሩት ድምፃዊያን ታጋዮች መካከል አንዱ የሆነው ብርሃኑ ጋኖ፣ ለትግሉ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለ ቢሆንም ህወሓት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ እንደ ሸንኮራ ተመጥጠው ከተተፉትና ከተገፉት ታጋዮች አንዱ መሆኑን አቶ አርአያ አስታውሰዋል፡፡ ከስድስት አመት በፊት ከትግራይ ወደ ሱዳን የባህልና የኪነት ቡድን አሳፍሮ ይጓዝ በነበረ መኪና ላይ በደረሰ አደጋ ህይወታቸውን ካጡት ድምፃዊያን መካከል አንዱ ብርሃኑ ጋኖ ሲሆን፤ በተለይም እሱ ከሞተ በኋላ ወላጅ እናቱን የት ወደቅሽ ብሎ የሚጠይቃቸው ወዳጅ ዘመድ በማጣታቸው፣ በመቀሌ ጐዳና ላይ ለልመና ተዳርገው እንደነበር የቅርብ ምንጮቹን ጠቅሰው አቶ አርአያ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ የታጋዩና ድምፃዊው እናት በአሁን ሰዓት ከመቀሌ ጐዳና ወደ ተንቤን መሄዳቸውን የጠቆሙት
“የማንነት ጥያቄ ያነሱ ተማሪዎችና ሰራተኞች እየታሰሩ ነው” - የአካባቢው ተወላጆች በአገሪቱ ላይ የመጣው የለውጥ ሽታ በአካባቢያቸው እንዳልደረሰ በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን የሚገኙት የቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች አስታወቁ። የቁጫ ብሔረሰብ ላለፉት በርካታ ዓመታት የማንነት ጥያቄው እንዲመለስለት በሰለጠነና በሰከነ መንገድ ከወረዳ እስከ ክልል ብሎም እስከ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ ሲያሰማ መቆየቱን ያስታወሱት የብሄረሰቡ ተወካዮች፣ አሁን በመጣው ለውጥ ጥያቄያቸው እንደሚመለስ በማመን በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ለእስርና ለእንግልት እየተዳረጉ እንደሆነ አቶ ሀብታሙ ሃ/ጊዮርጊስና አቶ ተስፋዬ ፈለሃ የተባሉ የአካባቢው ተወላጆች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ ከአገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከተማሪዎችና ከተለያዩ ግለሰቦች የተውጣጡ ወደ 600 የሚጠጉ አባላት ወደ ሃዋሳ በመጓዝ፣ ለክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን የተናገሩት አቶ ሀብታሙ፤ የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት ኃላፊዎች ጉዳዩን በአግባቡ ካደመጡ በኋላ የቁጫን ብሔረሰብ ጨምሮ ለአራት ብሔረሰቦች እውቅና የመስጠቱ ጉዳይ በቅርብ እንደሚፈፀም ቃል መግባታቸውን አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ጥያቄ መመለስ የስልጣን ወንበራቸው እንዳይነቃነቅ ፍራቻ ያደረባቸው
ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን በማቋቋም ሲሰሩ የቆዩ ጋዜጠኞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ትናንት ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ጋዜጠኞቹ ትናንት ማለዳ 1 ሰዓት ላይ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሙያ አጋሮቻቸው፣ አክቲቪስቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና ፖለቲከኞች አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን አንጋፋው ጋዜጤኛና የጋዜጠኝነት መምህር ዶ/ር ማዕረጉ በዛብህ የእንኳን ደህና መጣችሁ ጉንጉን አበባ አበርክተውላቸዋል፡፡ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱት የኢሳት ጋዜጠኖችና ባልደረቦች መካከል በስብሰባ መሃል የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላይ ተቃውሞ ያቀረበው አበበ ገላው፣ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና፣ ገሊላ መኮንን፣ መሳይ መኮንን፣ መታሰቢያ ቀፀላ፣ ወንድማገኝ ጋሹ፣ እንግዱ ወልዴ፣ ደረጄ ሃ/ወልድ፣ አፈወርቅ አግደውና ሰርክ አዲስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ኢሳት በሃገር ውስጥ መሰረቱን ለማስፋትና ራሱን በጠንካራ መሰረት ላይ ለማቆም የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የዚህ ንቅናቄ አካል የሆነው “የኢሳት ቀን በዛሬው ዕለት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ 20ሺህ ያህል ታዳሚያን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ “ኢሳት ለሃገሬ” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው “የኢሳት
አውቶብሶቹን ያሳገዳቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው አንድ መቶ ያህል የአሊያንስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ንብረት የሆኑ የከተማ አውቶቡሶች ከስራ ታገዱ፡፡ አውቶቡሶቹ የታገዱት በባንክ የብድር አከፋፈል ስርዓት ላይ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነም ታውቋል፡፡ ባለፈው ረቡዕ ከሰዓት በኋላ የአሊያንስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢና አባላት በጌትፋም ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር አክሲዮን ማህበሩ በገባው ውል መሰረት ብድሩን በየወሩ ለመክፈል በአገሪቱ ላይ የተፈጠረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት፣ አውቶቡሶቹ የሚያስፈልጋቸውን የመለዋወጫ እቃ ከውጭ ለማስመጣት በነበረ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና ተያያዥ ችግሮች እንቅፋት በመሆናቸው በውል መሰረት መክፈል አለመቻላቸውንና በዚህም ምክንያት አበዳሪያቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቶዎቹ አውቶቡሶች ስምሪት ላይ እንዳይውል ከጥር 28 ጀምሮ እግድ ማውጣቱን ተናግረዋል፡፡ከ2500 በላይ ባለ አክሲዮኖች እና ከ600 በላይ ሰራተኞች ያሉት አሊያንስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር፤ በ2005 ዓ.ም 25 ያህል አውቶቡሶችን በመግዛት የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የገለፁት የቦርድ ሰብሳቢው ዶ/ር አዲል አብደላ፣ መንግሥት በ2008 ዓ.ም 500 ያህል የከተማ አውቶቡሶች በግል አንቀሳቃሾች ወደ አዲስ አበባ
በአማራ ክልል ጐንደር ደንበያ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃትና በፈጠሩት ግጭት በርካቶች መገደላቸውንና መኖሪያ ቤቶች መቀጠላቸውን ምንጮች ያስታወቁ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በጐንደር ከተማ አዘዞ አካባቢ ባለፈው ሐሙስ ምሽት በተፈጠረ የእሣት ቃጠሎ እንስሳትን ጨምሮ በርካታ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸው ታውቋል፡፡ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ እንዳለው ከረቡዕ ጥር 29 ቀን ጀምሮ በተለይ በደንቢያ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች “በአማራ እና በቅማንት ብሔረሰቦች” መካከል ግጭት መፈጠሩንና በዚህም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል፡፡ ግጭቱ በዋናነት የተፈጠረው በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ልዩነትን በመፍጠር አካባቢውን የግጭት ቀጠና ለማድረግ አቅደው በሚሠሩ ሃይሎች ነው ያለው የክልሉ መንግስት፣ ግጭት ፈጣሪ ታጣቂ ሃይሎቹ ከቀላል እስከ ከባድ መሣሪያ የታጠቁ መሆናቸውንም ገልጿል፡፡ ለዚሁ ግጭት ህገወጥ መሣሪያ ወደ አካባቢው ከመግባቱም በተጨማሪ የሚሠለጥኑ ሃይሎች እንዳሉ ያስታወቁ የክልሉ መንግስት፣ በግጭቱ የተሳተፉ ተጠርጣሪ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የእስር ትዕዛዝ ወጥቶ ፍለጋ እየተከናወነ መሆኑንም አክሎ ገልጿል፡፡ በምዕራብ ጐንደርና ማዕከላዊ ጐንደር ዞኖች እስካሁን በተፈጠሩ ግጭቶች ጥቃቶች ከ39 ሺህ በላይ
የኢሳት ጋዜጠኞች ወደ ሃገራቸው ይገባሉ በምርጫ 97 የአውሮፓ ታዛቢ ልኡክ መሪ የነበሩት እና ጎሜዝ፤ የፊታችን አርብ ለ3 ቀናት ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሲሆን ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር እንደሚወያዩና በሚሌኒየም አዳራሽ ለህዝብ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ የአውሮፓ ፓርላማ አባሏ አና ጎሜዝ፤ በሃገሪቱ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ተቋማት፣ ጋዜጠኞችና ታዋቂ ግለሰቦችም ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ይወያያሉ ተብሏል፡፡ የ97 ምርጫ ቀውስን ተከትሎ “ኢትዮጵያ ነፃ እስክትወጣ እታገላለሁ፤ከነፃነት በኋላ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በአዲስ አበባ ጎዳና እንሸራሸራለሁ” ማለታቸው የሚነገርላቸው ጎሜዝ፤ “አሁን ያንን ቃሌን የምፈፅምበት ጊዜው ደርሷል” በማለት ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት እንደተዘጋጁ የአቀባበሉን ስነ ስርአት ያሰናዳው ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ አና ጎሜዝ ለሶስት ቀን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ መንግስት አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያደርግላቸው ማረጋገጡን የጠቆሙ የአቀባበል ኮሚቴው፤ ከህዝብ ጋር በሰፊው የሚገናኙበት መድረክም ቅዳሜ የካቲት 9 በሚሌኒየም አዳራሽ በሚከበረው የኢሳት ቀን ላይ ይሆናል ብለዋል፡፡ ከዚሁ የኢሳት ቀን ጋር በተያያዘም የጣቢያው ጋዜጠኞች ከረጅም አመታት በኋላ አርብ የካቲት 8 ቀን ወደ አገር ቤት
“የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍና የልማት ማህበር” የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለሃገር አንድነት ለከፈለው መስዋዕትነት ተገቢው እውቅናና ክብር እንዲሰጥ ለማድረግ ጥረት እያደረግኩ ነው አለ፡፡ ማህበሩ ጥቅምት 25 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተመሰረተ በኋላ ሶስት ያህል ጉባኤዎችን በማካሄድ የአባላት ቁጥሩን ከማበራከት ጎን ለጎን፣ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን የማደራጀትና በኢኮኖሚም የመደገፍ ተግባር ለማከናወን መርሃ ግብር ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የሃገር ባለውለታ የሆኑና በህይወት ያሉም ሆነ የሌሉ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን የህይወት ታሪክና የሙያ አስተዋፅኦ በጥናትና ምርምር ታግዞ በፅሁፍ፣ በድምፅና በምስል ሰንዶ ታሪካቸውን ለትውልድ ለማስተላለፍ ማህበሩ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ ማህበሩ ሰራዊቱ ለአገር አንድነት የከፈለውን ከፍተኛ መስዋዕትነት በክብር እንዲዘከርና የነበረው መልካም ስምና በጎ ምግባር ጎልቶ እንዲወጣ፣ ተከታታይ ታሪክን የመዘከር ተግባር አከናውናለሁ ብሏል፡፡ ሰራዊቱንና ቤተሰቦቻቸውን ከመደገፍ ባሻገር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ በሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ላይም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማህበሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
‹‹ከዚህ በፊት በማናውቀው ሰነድ ላይ እንድንወያይ ተደርገናል” - የፖለቲካ ድርጅቶች በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት እና በተናጠል የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች የሚገዛ የአሠራር የቃል ኪዳን ሰነድ በምርጫ ቦርድ በኩል ለፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት የቀረበ ቢሆንም ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም በማናውቀው ሰነድ ላይ ነው እንድንወያይ የተደረገው ብለዋል፤ ውይይቱም ያለ ስምምነት በይደር ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ የአገርን ብሔራዊ ደህንነት፣ የዜጐችን ነፃነትና መሠረታዊ መብት ባከበረ መልኩ እንዲንቀሳቀሱ ለማስቻል ሰነዱ መዘጋጀቱ በምርጫ ቦርድ በኩል ተገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ የፖለቲካ ድርጅቶች በእለቱ ለውይይት የተጠሩት ለተጀመረው ሃገራዊ ድርድር እና ውይይት እንደነበር ነገር ግን ከዚህ ቀደም በማያውቁት “የቃል ኪዳን” ሰነድ ላይ እንዲወያዩ መደረጋቸውን በውይይቱ የተሳተፉ ፖለቲከኞች ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ በዚህም በውይይቱ ወቅት በርካታ አለመግባባቶች መፈጠራቸውንና ውይይቱ በስርአቱ ባለመመራቱ በይደር የካቲት 15 ቀን መተላለፉን ከተሣታፊዎቹ አንዱ የሆኑት የመኢአድ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ አመልክተዋል፡፡ ሰነዱ ከየት መጣ? የፓርቲዎች ስነስርአት አዋጅ በ2002 የወጣውን የሚሽር ነው? አገልግሎቱ ምንድን ነው? ቀድሞስ እንዲህ ያለ
በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት በሃገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፖለቲካ ልሂቃን፣ የሲቪክ ተቋማትና ፖለቲከኞች መካከል የተጀመረው “ብሔራዊ ውይይት” (National Dialogue) የሃገሪቱን የፖለቲካ ስርአትና የዲሞክራሲ ይዞታ ያሻሽላል የሚል ተስፋ መሰነቃቸውን ፖለቲከኞች እና ምሁራን ገለፁ፡፡ የተጀመረው ብሔራዊ ውይይት ለረጅም አመታት እንዲፈጠር ሲጠየቅ የነበረ መሆኑን የገለፁት በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ፖለቲከኞች እና ምሁራን እንዲህ ያለው ውይይት በሃገሪቱ ከጉልበት ይልቅ ሃሳብ የገዥነቱን ቦታ እንዲያገኝ እንዲሁም የሃሳብ ገበያ በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ እንዲንሸራሸር በማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ ይህ “የብሔራዊ ውይይት” መድረክ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት መጀመሩና ቁርጠኝነታቸውን ለማሳየት የውይይቱ አካል መሆናቸው በሃገሪቱ በተጀመረው የሃሳብ ገበያን የማስፋትና ዲሞክራሲን የማጎልበት ሂደት በእጅጉ ተስፋ እንዲሰንቁ እንዳደረጋቸውም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የተወከሉ፣ ከሲቪክ ተቋማት የተውጣጡ እንዲሁም በተለያየ መድረክ ሃሳባቸውን ሲገልፁ የቆዩ የፖለቲካ ልሂቃንን ጨምሮ 8 መቶ ያህል ተሳታፊዎች ተገኝተው እንደነበር የሚገልፁት የመድረኩ አመቻችና አስተናባሪ የሆኑት አቶ የሸዋስ አሰፋ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ የሃገሪቱ መሪ እና ሌሎች ፖለቲከኞች ስለሃገራቸው የዲሞክራሲ
- ህጉ የቢራ ፋብሪካዎችንና የሚዲያ ተቋማትን በእጅጉ የሚጐዳ ነው ተብሏል - ውሣኔው ለአገሩና ለዜጐቹ የሚቆረቆር መንግስት መምጣቱን አመላካች ነው - አስተያየት ሰጪዎች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ወጣቶችና የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የንግድና ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴዎች፤ ከፍተኛ ክርክርና ውይይት አድርገውበት፣ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡትን የውሣኔ ሃሳብ መነሻ በማድረግ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአልኮል መጠጦችን በሬዲዮና በቴሌቪዥን ማስተዋወቅ ሙሉ በሙሉ የሚከለክለውን ህግ አፀደቀ፡፡ ህጉ ከሶስት ወራት በኋላ ተፈፃሚ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡ ከትናንት በስቲያ በምክር ቤቱ ያፀደቀውና ከ3 ወራት በኋላ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል የተባለው ህግ፤ ማንኛውም የአልኮል መጠጦችን በሬዲዮና በቴሌቪዥን ማስተዋወቅና የአልኮል መጠጦችን ከሎተሪ እጣ ወይንም ከሽልማት ጋር ማያያዝ እንዲሁም የአልኮል መጠጦች ማስታወቂያ በቢል ቦርድ ማስተዋወቅን ጭምር የሚከለክል ነው፡፡በኢትዮጵያ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ከሳምንታት በፊት በምክር ቤቱ የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የንግድና ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተወያይተውበት፣ የውሳኔ ሃሳባቸውን ለምክር ቤቱ እንዲያቀርቡ በሚል ተመርቶ ነበር፡፡ በዚሁ መሰረትም፤ ሁለቱ ቋሚ
በቤት ኪራይ እጦት ችግር ላይ ወድቀን ነበር - ማዕከሉ ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በቤት ኪራይ ችግር ላይ ለነበረው “ነህምያ የኦቲዝም ማዕከል” የ600 ሺህ ብርና የ50 ብርድልብሶች ድጋፍ አደረገ፡፡ የኩባንያው ኃላፊዎች ትላንት ረፋድ ላይ በተለምዶ ጎተራ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አቅራቢያ በሚገኘው የኦቲዝም ማዕከሉ በመገኘት ነው ድጋፉን ያደረጉት፡፡የኬኬ ኩባንያ የቦርድ ዳይሬክተርና አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ቦጋለና ባልደረቦቻቸው ድጋፉን ካደረጉ በኋላ ማዕከሉን የጎበኙ ሲሆን ማዕከሉ ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር ብዙ ድጋፍ እንዳላገኘ ገልፀው፣ ያደረግነው ድጋፍ ጥቂት ቢሆንም ሌሎችም ባለሀብቶችና መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንዲደግፋቸው ለማነሳሳት ነው ሲሉ አቶ ቴዎድሮስ ገልፀዋል፡፡ የማዕከሉ ዳይሬክተር ወ/ሮ ራሄል በበኩላቸው፤ በቤት ኪራይ ክፍያ ችግር በጭንቀት ላይ በነበርንበት ወቅት ስለደረሱልን እናመሰግናለን ብለዋል፡፡ ማዕከሉ የተመሰረተው የመስራቿ የወ/ሮ ራሄል ነህምያ የተባለ ሁለተኛ ልጃቸው የኦቲዝም ተጠቂ በመሆኑ እርሱን የሚያስተምሩበት ት/ቤት አጥተው መቸገራቸውን ተከትሎ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ማዕከሉ 60 ልጆችን እየረዳ መሆኑንና ለመመዝገብ የሚጠባበቁ ልጆች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ መንግስትና ባለሀብቶች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው የጠየቁት መስራቿ፤ በቀጣይ በአዲስ
- እራስን ነፃነት ነፍጐ በአንድ ቦታ ተወስኖ መቆየት ያው እስር ቤት ነው - በህገወጦች ላይ የምንወስደው እርምጃ የትዕግሥታችንን ያህል መራራ ነው - በአገራችን ያለው የጦር መሳሪያ ብዛት ከህዝብ ቁጥር ይበልጣል - የዛሬ 30 ዓመት የነበረ አስተሳሰብ የከሰረ አስተሳሰብ ነው፤ አያስፈልገንም በኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ፈፅሞና ወንጀል መፈፀሙ ታውቆ ያልታሰረ አንድም ሰው አለመኖሩንና ልዩነቱ የቦታ ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦችን እየያዙ ለፍርድ የማቅረቡ ጉዳይ ቀጣይነት ያለው ነው ብለዋል፡፡ የሰብአዊ መብት ጥስትና የተደራጀ ዘረፋ በመፈፅም የተጠረጠሩ ግለሰቦችን መንግስት ከተደበቁበት መያዝ ያልቻለበት ምክንያት ምንድነው በሚል ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ፈፅሞ ያልታሰረ አንድም ሰው አለመኖሩንና ልዩነቱ መንግስት እየቀለበውና እየጠበቀው መታሰሩ ላይ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ “ራስን ነፃነት ነፍጐ በአንድ ቦታ ተወስኖ መቀመጥ
በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት በዓለም ባንክ ውስጥ ለከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ እንዳይወዳደሩ የተደረጉት ኢትዮጵያዊው ምሁር ዶ/ር ዮናስ ብሩ በተቋሙ ውስጥ የሚፈፀመውን ዘረኝነት በመቃወም ከ2 ሳምንት በላይ በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ እና ድምፁን እንዲያሰማ በደብዳቤ ተጠይቋል፡፡ ላለፉት 7 ዓመታት በዓለም ባንክ ውስጥ የአለማቀፍ ንፅፅሮሽ መርሃ ግብርን በምክትል ስራ አስኪያጅነት የመሩት ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ዮናስ፤ ተቋሙ ላወጣው የመወዳደሪያ መስፈርት ብቁ መሆናቸውን ጠቅሰው ራሳቸውን ለቦታው በእጩነት ቢያቀርቡም አፍሪካዊ በመሆናቸው ብቻ ተቀባይነት ማጣታቸው ተጠቁሟል፡፡ ከዓለም ባንክ አመራሮች “አውሮፓውያን አንተን የመሳሰሉ ጥቁር አፍሪካውያንን በከፍተኛ የስልጣን ቦታ ተቀምጠው ማየት አይፈልጉም” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ዶ/ር ዮናስ ይናገራሉ፡፡ ጉዳዩን ወደ አሜሪካ ፍ/ቤት ለመውሰድ አስበው እንደነበር የሚገልፁት ዶ/ር ዮናስ፤ የዓለም ባንክ ያለመከሰስ መብት እንዳለው በመረዳታቸው ተቋውሟቸውን በተለያየ መንገድ ለመግለፅ መወሰናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የመጀመሪያ አማራጭ ያደረጉት ደግሞ የረሃብ አድማ ማድረግ ነው፡፡ ላለፉት ሁለት ሳምንታትም በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙት ዶ/ር ዮናስ፤ ይህን ተቋውሟቸውንም ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እያሳወቁ
የአዲስ አበባ አስተዳደር ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ዛሬ በካፒታል ሆቴል፣ በሽብር ምክንያት ታስረው ከተፈቱ ከ2 00 በላይ ዜጎች ጋር የውይይትና የእራት ፕሮግራም ማዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡ የፕሮግራሙ አስተባባሪ ከሆኑት አንዱ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ስለ ፕሮግራሙ ለአዲስ አድማስ በሰጡት መረጃ፤ በሽብር ክስ ተፈርዶባቸው ታስረው የተፈቱ በከተማዋ የሚገኙ 2 መቶ ያህል ሰዎችና የህግ ጥብቅና ሲቆሙላቸው የነበሩ የህግ ባለሙያዎች በመርሃ ግብሩ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ መርሃ ግብሩንም ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ከአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረ/ፕ ነብዩ ባዬ ጋር በመሆን ይመሩታል ተብሏል፡፡ በሽብር ምክንያት ታስረው የተፈቱ ዜጎች በእስር ወቅት ለደረሰባቸው እንግልትና ጉዳት እውቅና ይሠጣል፤ በቀጣይም ከስነ ልቦናና ማህበራዊ ተግዳሮት የሚላቀቁበት መንገድ በመድረኩ ይመከርበታል ተብሏል፡፡ በእለቱም በሽብር ምክንያት ተከሰው የነበሩ ዜጎች መልሰው የሚቋቋሙበትንና የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ እንዲሁም መብትና ጥቅማቸውን በዘላቂነት የሚያስጠብቅላቸው ማህበር ይቋቋማል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ዳንኤል አስረድተዋል፡፡
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት በእጩነት መቅረባቸው ታወቀ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት በእጩነት ያቀረቡት ዶ/ር ግሩም ዘለቀ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው የእጩነት ጥያቄውን መቀበሉን አረጋግጧል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ለሃገራቸው እና ለጎረቤት ሃገራት ሰላም መስፈን ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸውን፣ በኢትዮጵያ ከስጋት ይልቅ ተስፋ እንዲያብብ ማስቻላቸው በእጩነት ማመልከቻው ተጠቅሷል፡፡ ለሁለት አስርት ዓመታት በጦርነት ውስጥ በነበሩት ኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር እንዲሁም የአካባቢው ሃገራት መንግስትን ለመሳም እንዲሰሩ አነሳስተዋል የሚለው ለእጩነት ካስቀረባቸው ዋነኛው መሆኑን አመልካቹ ገልፀዋል፡፡ ላለፉት 40 ዓመታት በጥርጣሬ ይተያዩ በነበሩት ሶማሊያና ኢትዮጵያ መካልም መተማመን ፈጥረዋል ተብሏል፡፡ በትጥቅ ጭምር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እንደ ኦነግ፣ ኦብነግ አርበኞች ግንቦት 7 እና ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ወደ ሃገራቸው ገብተው፣ በሃገራቸው ፖለቲካዊ ጉዳይ ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ እድሉን ማመቻቸታቸው፣ የፖለቲካ እስረኞችን እንዲሁም ጋዜጠኞችን ከእስር መፍታታቸው ተጠቅሷል፡፡
በደቡብ ክልል በተፈጠረ በግጭትና የታጠቁ ሃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት በዚህ ሣምንት ብቻ የ14 ሰዎች ህይወት መቀጠፉ ታውቋል፡፡ በደቡብ ክልል ቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ሐሙስ በተቀሰቀሰ ግጭት የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ የኦነግ ታጣቂዎች በአማሮ ወረዳ በፈፀሙት ጥቃት ደግሞ የአራት ሰዎች ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በቴፒ ከተማ የተፈጠረው ግጭት ከዚህ ቀደም ተቀስቅሶ የ13 ሰዎች ህይወት ከቀጠፈው ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ጋር የተገናኘ መሆኑ ታውቋል፡፡ በእለቱ ከአቅራቢያው የማሻ ከተማ ወደ ቴፒ በሁለት አውቶብሶች የተጫኑ ግለሰቦች መግባታቸውን ተከትሎ ግጭቱ መቀስቀሱን ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ ግጭቱ በተደጋጋሚ እያጋጠመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ግጭት ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ በከተማዋና አካባቢው የሚገኙ 60 ያህል ቤቶች መቃጠላቸውንና በርካቶች ከቤት መፈናቀላቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ከአራት ወር በፊት በከተማዋ በተቀሰቀሰ ተመሳሳይ ግጭት 13 ሰዎች ተገድለው ከ6 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በሌላ በኩል፤ ማክሰኞ ጥር 22 ቀን 2011 ዓ.ም በዚያው በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት አራት ሰዎች
በጅግጅጋ ያለው አለመረጋጋት በነዋሪዎች ላይ ስጋት ፈጥሯል በተቃውሞና ግጭት ውስጥ የሰነበተችው የድሬደዋ ከተማ ከማክሰኞ ጀምሮ ወደ መረጋጋት እየተመለሰች ሲሆን በጅግጅጋ በየጊዜው የሚያጋጥመው ግጭት በነዋሪዎች ላይ ስጋት መፍጠሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ በድሬደዋ ከተማ ከጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞና ግጭት ለማብረድ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከመከላከያ ሰራዊትና ከድሬደዋ ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ጥረት ሲያደርግ መሰንበቱን ለአዲስ አድማስ የገለፁት ምንጮች፤ በሳምንቱ መጀመሪያም በግጭቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 10 ያህል የፀጥታ አባላትና የከተማዋ አመራሮችን ጨምሮ ከ300 በላይ ወጣቶች መታሰራቸውን ጠቁመዋል፡፡ “የታሰሩ ሰዎች ይፈቱ” በሚል ካለፈው ረቡዕ ለ3 ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ተጠርቶ እንደነበር የገለፁት ነዋሪዎች፤ አካባቢውን የተቆጣጠረው የምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት የሚመራው ኮማንድ ፖስት አድማው እንዳይካሄድ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተከትሎ በከተማዋ ለአድማ በታቀዱት ቀናት ከጥቂት የንግድ መደብሮች በቀር መደበኛ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዋናነት አስተዳደር ስርአቱ ይቀየር የሚለው የተቃውሞ አጀንዳ ሲሆን አሁን በክልሉ ሁሉም መዋቅር በሚባል ደረጃ ስልጣንና የአመራር ቦታዎች የተያዙት
በ1987 የኢፌዴሪ ህገመንግስት ሲረቀቅ ወሳኝ ሚና የነበራቸው የመጀመሪያው የኢህአዴግ ዘመን መንግስት አፈጉባኤ ዳዊት ዮሐንስ የቀብር ስነሥርዓት ዛሬ ይፈፀማል፡፡ ሃገራቸውን በአፈ ጉባኤነትና አምባሳደርነት ያገለገሉት ዳዊት ዮሐንስ፤ የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ሐምሌ 17 ቀን 1983 ዓ.ም ሲመሠረት በህግ ቋሚ ኮሚቴና በህገ መንግስት አርቃቂ ኮሚሽን ፀሐፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከ1987 እስከ 1998 ድረስም በሁለት ዙር የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ በመሆን ለአስር አመታት በም/ቤቱ ቆይተዋል፡፡ አምባሳደር ዳዊት ዮሐንስ የቀድሞ ብአዴን የማዕከላዊ ኮሚቴና አስፈፃሚ አባል በመሆንም ሀገሪቱን በከፍተኛ የስልጣን እርከን ከመሩ ባለስልጣናት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ የተወለዱት አምባሳደር ዳዊት ዮሐንስ፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን እንዲሁም ሁለተኛ ድግሪያቸውን ከአምስተርዳም ዩኒቨርስቲ በህግ አግኝተዋል፡፡ በ63 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት አምባሳደር ዳዊት ዮሐንስ፤ ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት የነበሩ በህክምና ሲረዱ በቆዩበት አሜሪካን ሀገር ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት ሻምበል ለገሠ አስፋው የቀብር ስነሥርዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ በ76 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት
በምግብ ማምረት፣ ማቀናባበርና ማሸግ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ አካላት በጋራ የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽን በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው፡፡ ከግንቦት 1 ቀን 2011 ዓ.ም እስከ ግንቦት 3 ቀን 2011 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ኤግዚቢሽን፤ በግብርና ዘርፍ፣ በምግብና መጠጥ ማቀነባበርና የተቀነባበሩ ምርቶችን ማሸግ ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ይሳተፉበታል፡፡ በጀርመኑ ታዋቂ የንግድ ትርኢት አዘጋጅ ፌርትሬድና በፕራና ኢቨንትስ የጋራ ትብብር በሚዘጋጀው በዚህ 3ኛው የኢትዮጵያ የግብርና ምግብና መጠጥ ቴክኖሎጂ እና ተያያዥ የሆኑት የፕላስቲክ ህትመትና ፓኬጂንግ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ ጀርመን ኔዘርላንድ፣ ቱርክ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይና ጣሊያን ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለኢትዮጵያ ገበያ ፍላጐት የተዘጋጁ ቴክኖሎጂዎችና መፍትሔዎች ይገኙበታል የተባለውን ይህንኑ ኤግዚቢሽን አስመልክቶ አዘጋጆቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ከምስራቅና ከመካከለኛው አፍሪካ ግንባር ቀደም የምግብ ገበያ አላት፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት ያወጣውን መረጃ ዋቢ አድርገው አዘጋጆች እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2017 ዓ.ም በአገር ውስጥ ያላት የምግብ ገበያ 4‚088 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን ከውጪ የምታስገባው የምግብ ምርት ደግሞ 1‚889 ቢሊዮን ዶላር አስገኝቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
- “የአቶ በረከት መታሰር የለውጥ ኃይሉ የህግ ማስከበር ሂደቱን ወደፊት እየገፋበት መሆኑን አመላካች ነው” - ፕ/ር መረራ ጉዲና - “የእነ አቶ በረከት መታሰር ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ነው - አቶ ጌታቸው ረዳ - አሁን ብዙዎች ጥሩ አየር መተንፈስ ይችላሉ” - አና ጐሜዝ የህዝብ ሃብት በማባከን ተጠርጥረው የታሰሩት የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ትናንት ፍ/ቤት ቀርበው የ14 ቀን ተጨማሪ ቀጠሮ የተሰጠባቸው ሲሆን ተጠርጣሪዎች ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ጉዳያችን በፌደራል ፍ/ቤት ይታይልን የሚል ጥያቄ በፍ/ቤቱ ውድቅ ተደርጓል። በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም ያለ ሀብትና ንብረት ታግዷል፡፡ ሁለቱም ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው ቤተሰቦቻቸው በቅርበት በሚገኙበት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እንዲታይላቸው እንዲሁም የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ጉዳያቸውን በውጪ ሆነው እንዲከታተሉ የጠየቁ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ሁለቱንም ጥያቄዎች ውድቅ በማድረግ ጉዳዩን ለየካቲት 1 ቀን2011 ዓ.ም ቀጥሮታል፡፡ አቃቤ ህግ ተመዘበረ ከተባለው ሃብት አንፃር ጉዳዩ ዋስትና የማያሰጥ ነው የሚል መከላከያ ያቀረበ ሲሆን ምስክሮች በአማራ ክልል ስለሚገኙና ወንጀሉም የተፈፀመው በአማራ ክልል በመሆኑ ጉዳዩ
የአሜሪካው ታዋቂ መጽሄት ፎሪን ፖሊሲ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ከአለማችን የአመቱ 100 ምርጥ አለማቀፍ አሳቢዎች አንዱ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡መጽሄቱ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው የ2019 የፈረንጆች አመት 100 ምርጥ አለማቀፍ አሳቢዎች ዝርዝር ውስጥ ባሰፈረው ጽሁፍ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አንድ አመት ባልሞላው የስልጣን ዘመናቸው፣ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ሰላም በመፍጠር ታሪክ ሰርተዋል፤ በሁለቱ አገራት መካከል ሰላም መስፈኑ የተለያዩ ቤተሰቦችን ከማገናኘት ባለፈ በአገራቱ መካከል ለረጅም ጊዜያት ተቋርጦ የነበረውን የንግድ ግንኙነት እንዲቀጥል በር ከፍቷል ብሏል፡፡ መከላከያና ደህንነት በሚለው መስክ በምርጥ አለማቀፍ አሳቢነት ያካተታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን በመፍታት ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ እንደሚገኙም ጠቁሟል፡፡ፎሪን ፖሊሲ መጽሄት ለአስረኛ ጊዜ ባወጣው አመታዊው የ100 ምርጥ አለማቀፍ አሳቢዎች ዝርዝር ውስጥ በፖለቲካ፣ በደህንነት፣ በቴክኖሎጂ፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ ሳይንስ፣ ጤናና ሌሎች መስኮች ተጽዕኖ የፈጠሩ አለማቀፍ አሳቢዎችን በ10 የተለያዩ ዘርፎች ነው ግለሰቦችን ያካተተው፡፡በዘንድሮው የመጽሄቱ ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት መካከልም የአይኤምኤፍ ዳይሬክተር ክርሲያን ላጋርድ፣ የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ መርኬል፣ የቀድሞው
የኦነግና የመንግሥት (ኦዴፓ) እርቅ የበለጠ ሊጠናከር እንደሚገባው የተገለፀ ሲሆን በአባገዳዎች የሚመራው 71 አባላት ያሉት የአፈፃፀም ኮሚቴ ከትናንት በስቲያ ስራውን በይፋ ጀምሯል፡፡ ሁለቱ አካላት እርቅ የፈፀሙበት የሽምግልናና የአባገዳዎች የእርቅ ስነ ስርአት ሂደት በሃገሪቱ ያሉ ሌሎች መሰል ችግሮችን ለመፍታት ሊውል እንደሚገባው የገለፁት የፖለቲካ ልሂቃን፤ በዚህ ረገድ የሃገር ሽማግሌዎች የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡ አባገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች ያከናወኑት የእርቅ ስርአት በቀላሉ ውጤታማ ሆኗል ያሉት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ የሽምግልና ባህላችን ተገቢውን ቦታ እየያዘ መምጣቱ በእጅጉ ተስፋ ሰጪ ነው ይላሉ፡፡ የሽምግልና ስርአታችን ባልና ሚስት ብቻ ከማስታረቅ አልፎ ሁለት ጦር የተማዘዙ አካላትን ማስታረቁ የኦሮሞ ህዝብ ጥንት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የአባ ገዳና የሃደ ሲንቄ የእርቅ ስርአቶች ተመልሰው መምጣታቸውን ያመላክታል ብለዋል፡፡ እርቁ በቀጣይም በሌሎች የተጋጩ ወገኖች ዘንድም ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ተናግረዋል - ዶ/ር ነጋሶ፡፡ አባ ገዳዎች፤ የኦነግ እና የኦዴፓ የአስመራ ውይይትን በመሃል ተገኝተው ቢከታተሉና ቢታዘቡ ኖሮ አሁን ለእርቅ የተቀመጡበት ግጭት አይፈጠርም ነበር ያሉት ፖለቲከኛው፤ ሌሎች የኦሮሞ የፖለቲካ
ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በግማሽ አመት ብቻ 52 ሰራተኞች ስራቸውን ለቀዋል ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የጠረፍ ንግድ አሰራርን ለማሻሻል የሚያስችል ሰነድ መዘጋጀቱና በኢትዮ - ኤርትራ ድንበር ላይ የድንበር ንግድ ስምምነት ድርድር ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ከትናንት በስቲያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የ2011 ዓ.ም የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ እንደተናገሩት፤ በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ላይ እየተካሄደ ያለውን የንግድ ሁኔታ በማጥናትና ይህንኑ ሁኔታ የሚገልጽ ሪፖርት በማዘጋጀት፣ ለድንበር ንግድ ስምምነት ድርድሩ ግብአት እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል፡፡ ከኤርትራ ጋር ስለሚደረገው የድንበር ንግድ፤ ረቂቅ ስምምነት ተዘጋጅቶ በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ በሚመሩት ኮሚቴዎች ቀርቦ፣ የመጨረሻ ቅርፁን በማስያዝ ለኤርትራ ወገን እንዲላክ መግባባት ላይ መደረሱንም ወ/ሮ ፈትለወርቅ ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮው ዓመት የተገኘው የውጪ ንግድ ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ135.82 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱንና በበጀት ዓመቱ 6 ወራት 1.21 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ የተፈጥሮ ሙጫና እጣን፣ ቆዳና
በቅርቡ በደቡብ ክልል የወረዳ እና የዞን አደረጃጀት ለውጥ ሲደረግ ራሱን የቻለ ዞን እንዲሆን የተወሰነው የኮንሶ ወረዳ አከላለልና አስተዳደር ሁኔታ ቅሬታ የፈጠረ ሲሆን የኮንሶ የህዝብ ተወካዮች አቤቱታቸውን አዲስ አበባ ለሚገኘው የሰላም ሚኒስቴር አቅርበዋል፡፡ ህዝቡ በአሁኑ ወቅት በዋናነት በምንፈልጋቸው በምናምናቸው ሰዎች እንመራ እንዲሁም በ1 ወረዳ የሚኖር የኮንሶ ህዝብ ወደ ሌላ ዞን እንዲከለል መደረጉ አግባብ አይደለም የሚል ጥያቄ ይዞ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱን የኮንሶ ህዝብ ኮሚቴ አባል አቶ ገመቹ ገንሳ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ ህዝቡ ይሄን ጥያቄ ወደ ፌደራል ይዞ ከመምጣቱ በፊት በተደጋጋሚ ለደቡብ ክልል ብሔራዊ መንግስት ማቅረቡን ነገር ግን ምላሽ የሚሰጥ አካል መታጣቱን የጠቆሙት አቶ ገመቹ ከወራት በፊት በኮንሶ ላራት ከተማ 2መቶ ሺ ያል ሰው አደባባይ ወጥቶ ጥያቄውን ማቅረቡን አስታውቀዋል፡፡ በወቅቱም የክልሉ አመራሮች አደባባይ የወጣውን ህዝብ ለማረጋጋት በሚመስል ሁኔታ ጥያቄያችሁ ሁሉ ምላሽ ያገኛል የምትፈልጓቸውን አመራሮች በፅሁፍ በኮሚቴ በኩል አሳውቁን እንዲሁም ያሏችሁን ተጨማሪ ጥያቄዎች በተመሳሳይ አቅርቡ ብለው ህዝቡን ተሰናብተው ወደ መጡበት መመለሳቸውን ያስታወሱት አቶ
በድሬደዋ የተቀላቀለውን ግጭት ተከትሎ 84 ተጠርጣሪዎች ታስረዋል ከሰሞኑ በምስራቅ ኢትዮጵያ የጅግጅጋ እና ድሬደዋ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ የሶማሌ ክልል መንግስት 6 ከፍተኛ አመራሮን ከስልጣን ያባረረ ሲሆን የድሬደዋ አስተዳደር ደግሞ 84 የወንጀል ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ታውቋል፡፡ በሶማሌ ክልል/ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ኡመር ላይ የማጥላላት ዘመቻ በመክፈት የመፈንቅለ ስልጣን ሙከራ አድርገዋል በተባሉ ስድስት የክልሉ መንግስት የካቢኔ አባላት ናቸው ከትናንት በስቲያ ሐሙስ የተባረሩት፡፡ በዚህም መሰረት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩት አቶ ጉሌድ አዋለ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት አማካሪ አቶ አብዲ ሃኪ፣ የክልሉ ልዩ ፖሊስ ኢንተርፕራይዝ ምክትል ኃላፊ አቶ ሃሰን አሊ፣ የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ኃላፊ አቶ አብዲ ሀኪም አሊ፣ የክልሉ የከተማ ስፋ ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲ ኢሌ አብዱላሂ እና የክልሉ የውሃ ልማት አማካሪ አቶ አብዲ ሙሃመድ ኡስማን ከካቢኔው መሰናበታቸውን የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡ እነዚህ አመራሮች በዋናነት በእስር ላይ የሚገኙትን የቀድሞውን የክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሃመድን አላማ ለማስፈፀምና በሰብአዊ መብት ጥሰትና በአስተዳደር ብልሹነት
“ለዓለም ህብረተሰብ መተማመንን የሚፈጥር ማብራሪያ ሰጥተዋል” ባለፈው ሰኞ ጥር 13 የአውሮፓ ጉብኝታቸውን ከጣሊያን - ሮም የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ በሮም ከጣሊያኑ አቻቸው ጋር ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን ከአዲስ አበባ ምፅዋ የሚዘረጋውን የባቡር መስመር ጨምሮ ጣሊያንና ኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቀጣይ ግንኙነቶች ላይም መክረዋል፡፡ በጣሊያን ከሚገኙ ባለሀብቶችና የታላላቅ ኩባንያ ባለቤቶችና ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ጋር በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡ የጣሊያን ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁ የካቶሊክ ጳጳስ መቀመጫ የሆነችውን ቫቲካንን የጎበኙ ሲሆን ከፓፕ ፍራንሲስ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፤ የአቢሲኒያ ቤተክርስቲያንንም ጎብኝተዋል፡፡ ረቡዕ በተጀመረው የዳቮስ የዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ ንግግር ካደረጉ የዓለም መሪዎች አንዱ የነበሩት ጠ/ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና አካባቢያዊ ዲፕሎማሲ ላይ ያደረገቻቸውን ማሻሻያዎችና ለውጦች በስፋት አብራርተዋል፡፡ በኢትዮጵያ መደመር በተሰኘ ፍልስፍና እየተመሩ ሁሉን አካታች የሆነ የፖለቲካ ንጣፍ ለመዘርጋት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ያወሱት ጠ/ሚኒስትሩ፤ በኢኮኖሚው ረገድም ቴሌ እና አየር መንገድን ጨምሮ በመንግስት በብቸኝነት ተይዘው የነበሩ ኩባንያዎችን በሙሉ እና በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር መንግስታቸው በቁርጠንነት እየሰራ መሆኑን
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ተቋም በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ዜጐችን በተመለከተ ያካሄደውን ጥናት ይፋ ያደረገ ሲሆን ከተፈናቃዮች መካከል 51 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው ብሏል፡፡ ተቋሙ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ማለትም ከጥር 2010 እስከ ታህሳስ 2011 ዓ.ም የተፈናቀሉ ዜጎችን አስመልክቶ በአሃዝ አስደግፎ የተለያዩ ትንታኔዎች አቅርቧል፡፡ 1.773.482 ያህል ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ መፈናቀላቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ 498‚417 የሚሆኑት በአየር ፀባይ ለውጥ ምክንያት እንዲሁም 61‚037 ያህሉ ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች መፈናቀላቸውን አመልክቷል፡፡ በተፈናቃዮች ቁጥር ኦሮሚያ ክልል ቀዳሚ ሲሆን፤ ሶማሌና ትግራይ ተከታዩን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡ አለማቀፉ የስደተኞች ተቋም ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ይፋ ባደረገው በዚህ ሪፖርቱ፤ ከአጠቃላይ ተፈናቃዮች 51 በመቶ ሴቶች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም ቁጥራቸው ላቅ ያለው እናቶችና ህፃናት ናቸው ብሏል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በግጭት ምክንያት 986‚458 ሰዎች ተፈናቅለው፣ በ447 የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ሲገኙ፣ 103‚440 ያህሉ በአየር ፀባይ ለውጥ የተፈናቀሉና በ44 የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ናቸው ብሏል - ሪፖርቱ። በሌሎች ምክንያቶች የተፈናቀሉት ደግሞ በ24 ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን ቁጥራቸውም 55‚950 ነው
እርቅ የፈጸሙበት ጉዳይ አለመታወቁ እያነጋገረ ነው ሰሞኑን በሃይማኖት አባቶች አሸማጋይነት የአማራና የትግራይ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እርቅ የፈጸሙ ሲሆን ጉዳዩ ያልተገለፀ ስምምነትም ተፈራርመዋል፡፡ የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤልም ሆኑ የብአዴን ም/ሊቀመንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፤ በሁለቱ ክልሎች መሃከል በጥርጣሬ የመተያየት አዝማሚያ መፈጠሩን ጠቁመው፣ ይህም የሆነው በራሳቸው በፖለቲከኞቹ ስህተት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ “ህዝብ አልተጋጨም አልተጣላም፤ ችግሩ ያለው እኛ ጋ ነው” ያሉት የክልሎቹ መሪዎች፤ ”እኛ ፖለቲከኞች የሚጠበቅብንን ባለመስራታችን ለዚህ አሳዛኝ የታሪክ ምዕራፍ በቅተናል” ብለዋል፡፡ ሁለቱ መሪዎች ለእርቅና ስምምነቱ ፈቃደኛ ሆነው እርቅ በማውረዳቸው የሽምግልና ቡድኑ ምስጋና ያቀረበላቸው ሲሆን ፖለቲከኞች ችግሮቻቸውን በእርቅ መፍታት መጀመራቸው የአገሪቱ ፖለቲካ እየተለወጠ መምጣቱን ጠቋሚ ነው ሲሉ አስተያየት የሰጡ ወገኖች አሉ፡፡ አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው ፖለቲከኞችና ምሁራን ደግሞ በዚህ አይስማሙም፡፡ ያልተግባቡት በምን እንደሆነ ባልተገለጸበት ሁኔታ የመሪዎቹ እርቅ መፍጠር ውጤት ያመጣል ብለው እንደማያምኑ ይገልጻሉ፡፡ በዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረሰው ስምምነት በምን ጉዳይ ነው የሚለው በግልፅ ለህዝብ ይፋ አለመደረጉ ጥርጣሬዎች
በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተፈጠሩ ግጭቶችና በተሰነዘሩ ጥቃቶች ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ 256 ዜጐች መገደላቸውን የሠብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሠመጉ) አስታወቀ፡፡ የተለያየ መነሻ ምክንያት ባላቸው ብሔር ተኮር ግጭቶች ሳቢያ የሰው ህይወት በከንቱ እየጠፋ መሆኑ እንዳሳሰበው የገለፀው ሠመጉ፤ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ክልሎችና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በህዳርና ታህሳስ 2011 ዓ.ም በተፈጠሩ ግጭቶች 256 ሰዎች መገደላቸውንና በአስር ሺዎች መፈናቀላቸውን ጠቁሟል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በጋሪና በቦረና ጐሣዎች መካከል ከህዳር ጀምሮ በተነሳ ግጭት ከ50 በላይ ዜጐች ህይወታቸውን አጥተዋል ያለው የሰመጉ ሪፖርት፤ ታህሳስ 8 ቀን 2011 በሞያሌ ከተማ በቀለ ሞላ ሆቴል ውስጥ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት የ12 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ብሏል፡፡ በነቀምት፣ በነጆ፣ ጋሆ ቀቤ፣ በሀሮ ሊሙ አካባቢ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በተፈፀሙ ጥቃቶች ደግሞ ከ30 በላይ ሰዎች ህይወት ሲጠፋ፣ የጊቶ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ባልታወቀ አካል በነቀምቴ ከተማ ተገድለዋል፡፡ በዚሁ እለት ማለትም ታህሳስ 17 ቀን 2011 በነቀምቴ ከተማ ተጨማሪ ሁለት የፀጥታ ሃይሎች ተገድለዋል ብሏል- የሰመጉ
ህዝቡ በጉጉት ይጠብቃቸዋል ተብሏል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ዛሬ ጐንደር የሚገቡ ሲሆን ከ27 ዓመታት በኋላ የጐንደርን መሬት ይረግጣሉ ተብሏል፡፡ የአቀባበሉ ኮሚቴ አባል ዲያቆን አደራጀው አዳነ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው የጐንደር ህዝብ በጉጉት ነው የሚጠብቃቸው፡፡ ለፓትሪያሪኩ ከጐንደር አፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ፋሲል ግንብ አጠገብ እስከሚገኘው አደባባይ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ድረስ በበርካታ ህዝብና ተሽከርካሪዎች ታጅበው እንደሚጓዙ የተገለፀ ሲሆን፤ ዘጠኝ ሊቀጳጳሳትም ከአዲስ አበባ አጅበዋቸው እንደሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ በአቀባበሉ ላይ የጐንደር ሁሉም አድባራት፣ የአድባራቱ አስተዳዳሪዎች፣ ካህናት፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ የማህበረ ቅዱሳን አባላት፣ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎችና ሌሎችም የማህበረሰብ አባላት በድምቀት ይቀበሏቸዋል ተብሏል፡፡ አቡነ መርቆሪዮስ በአደባባይ ኢየሱስ እረፍት ካደረጉ በኋላ በመስቀል አደባባይ በተዘጋጀላቸው የአቀባበል መርሃ ግብር ላይ እንደሚታደሙ ታውቋል፡፡ አቡነ መርቆሪዎስ ከዛሬ ጀምሮ የጐንደርን ህዝብ ለመባረክና ለመጐብኘት እቅድ እንደያዙና ዘንድሮም በድምቀት በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ እንደሚታደሙ የገለፁት ዲያቆን አደራጀው ህዝቡ ላለፉት 27 ዓመታት የተለያቸውንና የናፈቃቸውን እኒህን ትልቅ አባት በአካል ለማየት በጉጉት እየጠበቀ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ
በኦሮሚያ ክልል መንግስትና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር መካከል ተፈጥሮ የቆየውን ግጭትና ውዝግብ በእርቅ ስርአት ለመፍታት የአባገዳዎች ም/ቤት ለዛሬ ቀጠሮ መያዙን የቀድሞ የአባ ገዳዎች ም/ቤት ሠብሳቢ አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ በዚህ የእርቅና ሽምግልና ሂደት ላይ ከመንግስት በኩል የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ከፍተኛ ኃላፊዎች እንዲሁም ከኦነግ መሪው አቶ ዳውድ ኢብሣና አጋሮቻቸው ፊት ለፊት ተገናኝተው አባገዳዎች ባሉበት ከዚህ ቀደም የተስማሙባቸውን ጉዳዮች ይነጋገራሉ፤ ስምምነታቸውንም ያድሳሉ ተብሏል፡፡ የሃይማኖት አባቶች ጉዳዩን በእርቅ ይፈታሉ ብለን በማሰብ ነበር ጣልቃ ሳንገባ የቆየነው ያሉት አባገዳ በየነ ሰንበቶ፤ አሁን ግን አባገዳዎች ወሳኙን ድርሻ ሊወጡ ይገባል በሚል መተማመን ወደ ሽምግልናው ሂደት እንደተገባና ከሁለቱም ወገን በጐ ምላሽ እንደተገኘ ጠቁመው፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል የቆየው ውዝግብና አለመግባባት ዛሬ በእርቅ እንደሚፈታ እተማመናለሁ ብለዋል፡፡ የእርቅና ሽምግልና ሥነ ስርዓቱም በኦሮሞ ባህል ማዕከል እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡ በምዕራብ ወለጋ ከኦነግ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ያለውን ሁኔታ ሰሞኑን ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያብራሩት የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር በገንዳ ውሃ ከተማ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ህፃናትን ጨምሮ 8 ሰዎች የሞቱበትን ሁኔታ የሚያጣራ ቡድን ወደ ሥፍራው እንደሚላክ የገለፀው የአማራ ክልል መንግስት፤ ያልተመጣጠነ ኃይል የተጠቀሙ በህግ ይጠየቃሉ ብሏል፡፡ በአካባቢው በመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ላይ ተሰማርቶ የነበረው ሱር ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ተሽከርካሪዎቹን ለማንቀሳቀስ በሞከረበት ወቅት በተፈጠረ አለመግባባት ክስተቱ መፈጠሩን የጠቆሙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፤ በግጭቱ የንፁሃን ህይወት መጥፋቱ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ የኮንስትራክሽን ድርጅቱን ከአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ አንፃር መከላከያ ሰራዊት አጅቦት መጓዙ ተገቢ እንደነበር የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የተፈጠረው ሁኔታ ግን መሆን ያልነበረበት ነው ብለዋል፡፡ ችግር እንኳ ቢያጋጥም በትዕግስትና በውይይት ጉዳዩን ለመፍታት ጥረት ማድረግ ይገባ እንደነበርም ገልፀዋል፡፡ በቀጣይ የጉዳቱ ዝርዝር ተጣርቶ፣ ያልተገባና ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ የወሰዱ አካላት በህግ እንደሚጠየቁ አቶ ገዱ አስታውቀዋል፡፡ በገንዳ ውሃና በኮኪት ቀበሌ ላይ ላጋጠመው አደጋ መነሻ ምክንያቶቹን ያብራሩት የክልሉ የፀጥታና ደህንነት ኃላፊ ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ፤ ህዝብ ሱር ኮንስትራክሽን የተባለውን ኩባንያ መሳሪያ አቀባባይና አስታጣቂ ነው ብሎ
ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በግጭት ምክንያት በየሳምንቱ፣ በአማካይ 320 ያህል የአማራ ተወላጆች እየተፈናቀሉ ወደ አማራ ክልል እንደሚገቡ የገለፀው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፤ ተፈናቃዮቹን ለመርዳት በክልሉ መንግስት በኩል የ8 ሚሊዮን ዶላር (280 ሚ. ብር ገደማ) አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ መቅረቡን አስታውቋል። የክልሉን መንግስት መረጃ ዋቢ ያደረገው ፅ/ቤቱ፤ የአማራ ተወላጆች በአመዛኙ ከአፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያና ሶማሌ ክልል የተለያዩ ጥቃቶችን በመሸሽ ወደ አማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች እየተሰደዱ ነው ብሏል። ክልሉ በየሳምንቱ በአማካይ 320 ያህል ስደተኞችን ያስተናግዳል ያለው ሪፖርቱ፤ በአሁኑ ወቅት የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከ14 ሺህ በላይ መድረሱን ጠቁሞ፣ ለሚቀጥሉት 6 ወራት የምግብና መሰረታዊ ፍላጎቶች አቅርቦት 8 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ አመልክቷል፡፡ ተፈናቃዮቹ በማዕከላዊ፣ ደቡብና ምዕራብ ጎንደር፣ በምዕራብ ጎጃም፣ በኦሮሞ ዞን፣ በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ በባህርዳር፣ በሰሜን ሸዋ፣ በዋግኧሞራና አዊ ዞን ውስጥ በተለያዩ ካምፖች ተጠልለው እንደሚገኙም ሪፖርቱ ጠቁሟል። የተፈናቃዮች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱ ለክልሉ መንግስት አዳጋች ሁኔታዎች መፍጠሩን ያመለከተው ሪፖርቱ፤የረድኤት ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡን አስታውቋል፡፡ በአሁኑ
አገልግሎቱ በአይነቱ በአገሪቱ የመጀመሪያው ነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ከውጭ አገራት የሚላክላቸውን ገንዘብ በሲቢኢ ብር አማካይነት በቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው እንዲደርሳቸው የሚያደርግና በአይነቱ በአገሪቱ የመጀመሪያው የሆነ አዲስ አሰራር ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ወርልድሪሚት ከተሰኘ ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት ጋር በመተባበር ህብረተሰቡ በአገሪቱ በአይነቱ የመጀመሪያው የሆነው የዚህ ምቹና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪውን ያቀረበው ባንኩ፣ የአገልግሎቱን መጀመር የሚያበስር ልዩ ስነስርኣት በመጪው ማክሰኞ የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የወርልድሪሚት የምስራቅና ማዕከላዊ አፍሪካ ቀጠና ኃላፊን ጨምሮ ሌሎች ተወካዮች በሚገኙበት እንደሚከናወንም ለአዲስ አድማስ በላከው መረጃ አክሎ ገልጧል፡፡የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየጊዜው ዘመኑ ያፈራቸውን የባንክ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ደንበኞቹ ቀላል፣ ቀልጣፋና ምቹ በሆነ መንገድ የባንክ አገልግሎትን እንዲያገኙ ሲያደርግ እንደቆየም አስታውሷል፡፡
ህገ መንግስት፣ ሰንደቅ ዓላማ፣ የአዲስ አበባ ጉዳይ … በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በቀጣይ የሚደረገው ውይይት የሚመራበት ስርአትና ደንብ ሰሞኑን የፀደቀ ሲሆን የህገ መንግስት ሰንደቅ አላማ፣ የክልሎች አወቃቀርና የአዲስ አበባ ጉዳይ በድርድር አጀንዳነት ቀርቧል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከረቡዕ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ውይይቱ በሚመራበት ህገ ደንብ ላይ ውይይት ሲያደርጉ የሰነበቱ ሲሆን ትናንት ሁሉም በደንቡ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰው አፅድቀዋል፡፡ ደንቡ በህግ ባለሙያዎች የተዘጋጀና በፓርቲዎች ውይይት የዳበረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ፓርቲዎች በውይይቱ ወቅት የሚመሩበትን መርሆዎች፣ ውይይቱ የሚካሄድበትን ስርአት፣ ከውይይቱ ተሳታፊዎች የሚጠበቅ ኃላፊነት፣ የአወያዮቹ ኃላፊነትና ግዴታ፣ የመገናኛ ብዙኃን ሚናና ግዴታን ያካተተ ነው፡፡ 16 አንቀፆች ያለው ደንቡ ውይይቱ በገለልተኛ ወገኖች እንዲመራና ገለልተኛ አካላቱ በፓርቲዎቹ የጋራ ስምምነት እንደሚመረጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ታዛቢዎችም ከሙያ ማህበራት እንዲሁም ከንግድና ስራ ማህበራት ይመረጣሉ ተብሏል፡፡ ፓርቲዎቹ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ውይይት ካደረጉ በኋላ የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ በአጀንዳው ላይ የሚተላለፈው ውሳኔ በአብላጫ ድምፅ እንዲሆንም ተስማምተዋል፡፡ ለሁለት ቀናት በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ
በደቡብ ክልል ሰገን ህዝቦች ዞን፣ በአባሎቼ ላይ የግድያ ሙከራን ጨምሮ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እየተፈፀመ ነው ያለው መኢአድ፤ ድርጊቱን የፈፀሙና ያስፈፀሙ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎችን ጨምሮ የዞንና የወረዳ አመራሮች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡ “ለውጡን የማይደግፉ የዞንና የወረዳ አመራሮች በአባሎቻችን ላይ እያደረሱ ያለው ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን” በሚል መግለጫ የሰጠው ፓርቲው፤ የሰገን ህዝቦች ያነሱትን የልማት ጥያቄ ተከትሎ ጥያቄውን ያስተባበሩት የመኢአድ አባላት ናቸው በማለት አባላቱ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማድረግ አለብን በሚል መነሻ፣እስርና ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ጠቁሟል፡፡ በዚህ ጥቃት ከክልሉ የፀጥታ ኃይል በተተኮሰ ጥይት 3 ሰዎች በፅኑ ቆስለው ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን፣ 22 ሰዎች ደግሞ መታሰራቸውንና መደብደባቸውን መኢአድ አስታውቋል፡፡ መንግስት ለውጡን በተቀላጠፈ መልኩ ለማስቀጠል እየሰራ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ለውጡን የማይፈልጉ የዞንና የወረዳ አመራሮች በህዝብ መካከል ክፍፍልና መጠራጠሮችን እየፈጠሩ ነው ያለው ፓርቲው፤እነዚህ አመራሮች ላይ መንግስት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡ መኢአድ በህዝቡ የተገኘው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያልተቋረጠ ድጋፍ ያደርጋል ያሉት የፓርቲው አመራሮች፤ ለውጥን የማይቀበሉ በየአካባቢው ያሉ ባለስልጣናት ግን የህዝቡን የመብት ጥያቄ
የደንብ ልብስ በመልበስና የጦር መሳሪያ በመያዝ ዘረፋ የሚያካሂዱ የፖሊስ አባላት እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በከተማችን አዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች የደንብ ልብስ የለበሱና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት የሆኑ ፖሊሶች፣ ግለሰቦችን በጦር መሳሪያ በማስፈራራትና በማስገደድ ዘረፋ እያካሄዱ መሆኑን ከፖሊስ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ዘራፊዎቹ በተለያዩ ቀናትና በተለያዩ ስፍራዎች በመዘዋወር “ዶላር እንመነዝርላችኋለን”፣ በማለትና መንዛሪዎቹን በጦር መሳሪያ በማስገደድ፣ የያዙትን ዶላርና ሞባይል ስልክ ይዘው ይሰወራሉ ተብሏል፡፡ ከፖሊስ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ታህሳስ 6 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 አምስት የፌደራል የወንጀል መከላከል ፀጥታ ህግ ማስበር ዳይሬክቶሬት ቲም አዛዥ የሆኑና ሁለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ልዩ ቦታው ሳሪስ አቦ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ አንድ ግለሰብን “ዶላር እንመንዝርልህ” በማለት ይዘውት ከገቡ በኋላ ለመመንዘር የያዘውን 160ሺ ብር በጦር መሳሪያ አስፈራርተው በመቀማት ላዳ ታክሲ ይዘው ከተሰወሩ በኋላ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት የሆኑ
የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ብ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ ሌሎች ኃላፊዎችና ግለሰቦች 319,475,287 (ሶስት መቶ አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሰባት) ብር በማባከን የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ አቃቤ ህግ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሰረተባቸው ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው፣ የቀድሞ ም/ዋ/ዳይሬክተርና የግብይትና ሽያጭ ኃላፊ ብ/ጀነራል ጠና ቁርንዲ፣ የአዳማ እርሻ መሳሪያዎች ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የቀድሞ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮ/ል ደሴ ዘለቀ፣ የአዳማ እርሻ መሳሪያዎች ኢንጂነሪንግና ኢንዱስትሪ የቀድሞ ም/ዋ/ዳይሬክተርና የኮርፖሬሽኑ ማርኬቲንግ ሰፕላይ ኃላፊ ኮ/ል ጌትነት ጉድያ፣ የአዳማ እርሻ መሳሪያዎች ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የቀድሞ ም/ዋ/ዳይሬክተርና የኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮ/ል ጎይቶም ከበደ እንዲሁም በንግድ ስራ የሚተዳደሩት ቸርነት ዳና፣ እሌኒ ብርሃንና ረመዳን ሙሳ ናቸው፡፡ በእነዚህ ስምንት ባለስልጣናትና ግለሰቦች ላይ ሰባት ክስ የቀረበባቸው ሲሆን ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የመንግስት ህዝብን ሃብት አባክነዋል፣ የሙስና ወንጀልም ፈፅመዋል ብሏል - አቃቤ ህግ በክሱ፡፡ ኃላፊዎቹ ለአዳማ እርሻ መሳሪያዎች
ህገ መንግስቱን ለዜጐች ማስተማር ለአገሩ የሚቆረቆር፣ ያገባኛል የሚልና በአስተሳሰቡና በአመለካከቱ የተቀየረ ዜጋ መፍጠር ነው ተባለ። አገሩንና ወገኑን የሚወድና ለአገሩ የሚቆረቆር ትውልድ ከራሱ ባሻገር ሌሎችን መመልከት ስለሚችል፣ ለአገር ግንባታው አሻራውን ማኖር እንደሚችልም ተገልጿል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት የቀረበውና አባላቱ በስፋት እየተወያዩበት የሚገኘው የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ እንደተመለከተው፤ ከዚህ ቀደም የነበረው የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ባልተደራጀ መልኩ የሚከናወን፣ ወጥነት ያለው አሰራርና አደረጃጀት ያልነበረው፣ ዜጐችን ተደራሽ ያላደረገና አሳታፊ እንዳልነበረ ተገልጿል፡፡ ዜጐችን ህገ መንግስት ማስተማር በቅብብሎሽ አገር የመገንባት አንዱ ገጽታ እንደሆነ ያመለከተው ይኸው ረቂቅ አዋጅ የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮን በስርዓትና በስልት ለመምራት ታስቦ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱም ተጠቁሟል፡፡ ዜጐች ህገ መንግስታቸውን እንዲያውቁና እንዲገነዘቡ በማድረጉ ረገድ እስከ አሁን የተሰራው ሥራ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ያልሆነ፣ በቅንጅትና በትስስር ያልተመራ እንደነበር ያመለከተውና ለምክር ቤቱ አባላት የቀረበው የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ እንደሚያመላክተው፤ ባለቤትና ተጠያቂነት ያለው ህጋዊ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም ማቋቋም ተገቢ ሆኖ መገኘቱን
ከኃላፊዎች ውጭ ሞባይል ይዞ መግባት አይፈቀድም በአዲስ አበባ የቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤትና ቂሊንጦ የቀጠሮ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች በድብቅ የሚገቡ ሞባይል ስልኮች መበራከታቸውን ምንጮች ገለፁ፡፡ ወደ ሁለቱም ማረሚያ ቤቶች ሞባይል ይዞ መግባት የሚፈቀድላቸው ለአመራሮቹ ብቻ ቢሆንም በርካታ ታራሚዎች ግን ሞባይል አስገብተው እንደሚጠቀሙ የገለፁት ምንጮች፤ አንድ ሞባይል ስልክ ለማስገባት እስከ 20 ሺ ብር እንደሚከፍሉ ተናግረዋል፡፡ ሞባይሎቹን ቻርጅ የሚያደርጉላቸው ደግሞ ቢሮ ውስጥ የሚሰሩ የማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ለአንድ የሞባይል ቻርጅ ማድረጊያ 150 ብር እንደሚያስከፍሉ የጠቆሙት ምንጮቻችን፤ አንድ የመቶ ብር ካርድም እስከ 500 ብር እንደሚሸጥ ተናግረዋል፡፡ ቀደም ሲል የማረሚያ ቤቱ ጥቂት ፖሊሶች ለአንድ ደቂቃ 30 ብር እያስከፈሉ ታራሚዎችን ያስደውሉ ነበር ያሉት ምንጮች አሁን ሞባይል የገባላቸው ታራሚዎችም ለአንድ ደቂቃ 20 ብር እያስከፈሉ እንደሚያስደውሉ ታውቋል፡፡ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገረመው አያሌው ስለ ጉዳዩ ከአዲስ አድማስ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፤ ስለ ጉዳዩ በጭምጭምታ ከመስማት በቀር የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ጠቁመው፣ ከኃላፊዎች ውጪ
በአዲስ አበባ ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ጉለሌና ቦሌ የግዴታ ጋብቻ በብዛት እንደሚፈፀምባቸው ተገለጸ፡፡ ባለፈው ሐሙስ በኢንሽየቲቭ አፍሪካ አዘጋጅነት፣ “ለውጥን በመለወጥ መተግበር” በሚል መሪ ሃሳብ በሞዛይክ ሆቴል ለአንድ ቀን በተካሄደ ስብስባ ላይ 20 የሁለተኛ ደረጃና የልዩ ፍላጐት ትምህርት ቤቶች መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሴት ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ የኢንሽየቲቭ አፍሪካ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ክቡር ገና በስብሰባው ላይ እንደገለጹት፤ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ጋር በመተባበር ባካሄደው ጥናት፤40 በመቶ በሚሆኑት ተማሪዎች ላይ ልዩ ልዩ ፆታዊ ጥቃት እንደሚፈጸም አረጋግጠዋል፡፡ ጥቃቱ በሁለቱም ፆታዎች ላይ የሚደርስ ቢሆንም ይበልጥ ተጐጂዎች ልጃገረድ ተማሪዎች ናቸው ብለዋል፤ጥናቱን በመጥቀስ፡፡ የስብሰባው ዋና አላማ በትምህርት ቤት አካባቢ በተማሪዎች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ለመቀነስ ምን ማድረግ እንደሚቻል ሃሳብ ለማመንጨት መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ችግሩን ፈጥኖ መከላከል ካልተቻለ የሚያስከትለው ጉዳት ቀላል እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡ ለተሰብሳቢዎቹ የውይይት መነሻ መረጃዎችን ያቀረቡት፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሥርዓተ ፆታ ኃላፊ፣ ወ/ሮ አበባ ዘውዴ፤የግዴታ ጋብቻ በአንዳንድ ክፍለ ከተሞች የሚታይ ቢሆንም በቦሌና ጉለሌ ክፍለ
በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የተለያየ አካባቢ እንዲሁም በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞንና በሃዋሳ በሲዳማና በወላይታ ብሔረሰብ መካከል ተፈጥረው የነበሩ ግጭቶችን በተመለከተ ምርመራ አከናውኖ ሪፖርት ያጠናቀረው የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)፤ በእነዚህ ግጭቶች በጠቅላላው 207 ሰዎች መገደላቸውንና አንድ ሚሊዮን ያህል ዜጎች መፈናቀላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ በጌዲኦ ዞን ከሚያዚያ 25 ቀን 2010 እስከ ሚያዚያ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በብሔር ተኮር ግጭት 8 ሰዎች መገደላቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ከእነዚህም አራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ማለትም ባልና ሚስት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር የተገደሉበት መሆኑን አመልክቷል፡፡ ሰመጉ በዚሁ በጌዲኦ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ማለትም በገደብ፣ በኮቸሬ፣ በ7/ጨሎ እና በወናሳ ወረዳዎች ተጨማሪ 74 ሰዎች መገደላቸውን የጌዲኦ ዞን ፖሊስ መምሪያን መረጃ ዋቢ አድርጎ በሪፖርቱ አጠናቅሯል፡፡ በምዕራብ ጉጂ ዞን በጉጂና በጌዲኦ ብሔረሰብ መካከል በተፈጠረው ግጭት ደግሞ ከሚያዚያ 3 ቀን 2010 እስከ ሚያዚያ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ብቻ 103 ሰዎች መገደላቸውን የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት መረጃን ዋቢ አድርጎ በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ በሃዋሳ ከተማ ከጨንበላላ
ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ውህደትና ህብረት እንዲመጡ ያስተላለፉትን ጥሪ ተከትሎ 12 ያህል ፓርቲዎች በተለያየ አግባብ ለመዋሃድ በሂደት ላይ ናቸው፡፡ የአራት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው “የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ” ሰሞኑን ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤው፣ የግንባሩን አባል ፓርቲዎች አቋም በማጠናከር፣ ጠንካራ ግንባር ሆኖ ለመውጣት የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ነድፎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል፡፡ በውህደት ሂደት ላይ የሚገኙትና የዜግነት ፖለቲካ እንደሚያራምዱ የገለፁት አርበኞች ግንቦት 7፣ ኢዴፓ፣ ሠማያዊ እና የቀደሞ አንድነት አመራሮችና አባላት እስከ መጋቢት መጨረሻ ውህደታቸውን ለማጠናቀቅ ያቀዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ፓርቲው እንዴት ይመስረት፣ የሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ምን ይመስላል?... የሚሉ ጉዳዮችን የሚያጠና 50 አባላት ያሉት የኤክስፐርቶች ቡድን ተቋቁሞ ስራ መጀመሩ ታውቋል፡፡ የታለመውን ውህደት እውን ለማድረግ ከተመሠረተ 7 አመት ያስቆጠረው ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው እሁድ ሙሉ ለሙሉ ህልውናውን አፍርሷል፡፡ በተመሳሳይ ኢዴፓ እና አርበኞች ግንቦት 7 ራሳቸውን የማክሰም እርምጃ እንደሚወስዱም ይጠበቃል፡፡ በሌላ የውህደት ስብስብ ውስጥ የተካተቱት 8 ፓርቲዎች በበኩላቸው፤ ተግባራዊ የውህደት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የገለፁ ሲሆን በቅድሚያ
በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊትና በተለያዩ ታጣቂ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት በእጅጉ እንዳሳሰበው የገለፀው ኦፌኮ፤ መንግስት ንፁሃንን እየገደሉ ያሉትን እንዲከላከል፤ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ደግሞ ለተፈጠሩ ችግሮች መፍትሄዎችን እንዲያመነጩ ጠይቋል፡፡ በመከላከያ ሰራዊትና በታጠቁ ኃይሎች መካከል ያለው ግጭት የንፁሃንን ህይወት እየቀጠረ መሆኑን የጠቆመው ፓርቲው፤ በቅርቡ በምዕራብ ጉጂ ዞን ፊንጫ አካባቢ በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የ13 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሌሎች ክልሎች ታጣቂ ኃይሎች ወደ ኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች (ወለጋ፣ ቦረና፣ ጉጂና ሐረርጌ ዞኖች) ውስጥ በመግባት ዜጎችን እየገደሉና እያፈናቀሉ መሆኑን ፓርቲው አስታውቋል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ተባብሰው ህዝብ ለበለጠ አደጋ እንዳይጋለጥ በመንግስትና በኦነግ ግንባር መካከል ያለው ልዩነት በውይይት በአስቸኳይ እንዲፈታ እንዲሁም ሁለቱ አካላት ያደረጉት ስምምነት ለህዝብ ይፋ እንዲደረግና ስምምነቱ ያለመሸራረፍ እንዲተገበር ጠይቋል፡፡ የፌደራል መንግስት ከሌሎች ክልሎች ወደ ኦሮሚያ በመግባት ንፁሃን ዜጎችን እየገደሉ፣ እየዘረፉና እያፈናቀሉ ያሉትን ታጣቂዎች እንዲከላከልም ኦፌኮ በመግለጫው ጠይቋል፡፡ የሃይማት ተቋማት፣ የሃገር ሽማግሌዎች አባገዳዎችና የማህበረሰብ መሪዎች በህዝቡ መሃል በመሰራጨት
ተጠርጣሪ ወንጀለኛን የደበቁ በህግ መጠየቅ አለባቸው” በየትኛውም የኢትዮጵያ መንግስት በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩትና መቀሌ ተሸሽገዋል የሚባሉት አቶ ጌታቸው አሰፋ ጉዳይ በፓርላማ ጭምር እያነጋገረ ነው፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሰፊ ማብራሪያ ያቀረቡት ዋና አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፤ ተጠርጣሪው በትግራይ ክልል እንደሚገኙ ነገር ግን ክልሉ ተጠርጣሪውን አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዋነኛ ተጠርጣሪው አቶ ጌታቸው አሰፋ በትግራይ ክልል ተሸሽገው እንደሚገኙ ፖሊስ በቂ መረጃ እንዳለው የጠቆሙት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ፤ በሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ የሌላ አካባቢ ተወላጆች ሳይቀሩ በትግራይ ክልል ተሸሽገው እንደሚገኙ ለም/ቤቱ አባላት ገልፀዋል፡፡የፌደራል መንግስቱ አንድ አካል የሆነው የትግራይ ክልል፣ አንድን የህግ ተጠርጣሪ መደበቁ ከፍተኛ የህገ መንግስትና የህግ ጥሰት ነው ይላሉ - የህግ ባለሙያው አቶ አመሃ መኮንን፡፡ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን የደበቀ፣ ከለላ የሰጠ፣ ወይም ተጠርጣሪ መሆኑን እያወቀ ወደ ሌላ ቦታ ያሸሸ አካል በግልፅ በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ የወንጀል ተጠያቂነት እንዳለበት ያስረዱት አቶ አመሃ፤ የትኛውም አካል በህግ ፊት እኩል እንደመሆኑ ተጠርጣሪን
የኢዴፓ አመራርነት ይገባኛል ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ፓርቲውን አፍርሶ ከሌሎች ጋር ውህደት ለመፈፀም የሚደረግን እንቅስቃሴ እንደሚቃወሙ የገለፁት እነ አቶ ልደቱ አያሌው፤ የመጨረሻ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የኢዴፓ የቀድሞ ፕሬዚዳንትና ከፍተኛ አመራር አቶ ልደቱ አያሌው ቀደም ብሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በፓርቲው ውስጥ በተፈጠረው ውዝግብ ዙሪያ ውይይት አድርገው እንደነበር ለአዲስ አድማስ ያስረዱት አቶ አዳነ ታደሰ፤ ጠ/ሚኒስትሩም ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን አጣርቶ እንዲፈታ እማከራለሁ የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው አስታውሰዋል፡፡ የቀድሞ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያም ጉዳዩን እየመረመሩና እንደነበርና መፍትሄ ያበጃሉ ተብለው እየተጠበቁ ሳለ ከኃላፊነታቸው ተነስተው በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ መተካታቸውን የጠቀሱት አቶ አዳነ፤ አሁን አዲሷ የቦርድ ሰብሳቢ ጉዳዩን ተመልክተው የመጨረሻ እልባት እንዲሰጡ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረውል፡፡ የፓርቲው እጣ ፈንታ ባልለየበት ሁኔታ አፍርሰነው ከሌሎች ጋር እንዋኃዳለን የሚለው ተቀባይነት እንዳያገኝም በደብዳቤያቸው መጠየቃቸውን አስታውቀዋል፡፡ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ከተሸሙ በኋላ ውሳኔ የሚሰጡበት የመጀመሪያ ውዝግብ የኢዴፓ ጉዳይ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ የፓርቲያችን መተዳደሪያ
በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ፖለቲካ ከነበረበት አስፈሪ ድባብ ወደ ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ተለውጧል ያለው አርበኞች ግንቦት 7፤ ከእንግዲህ አመጽ ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ትግል አማራጭ መሆን የለበትም ብሏል፡፡ ንቅናቄው ሰሞኑን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው መግለጫ፤የህዝቡ ትግልና በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠሩ የለውጥ ሃይሎች ጥምረት፣ የሃገሪቱን ፖለቲካ ከአስፈሪ ድባብ ወደ ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንዳሸጋገሩት ጠቁሞ፤ ይህን ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ለማጨለም ያቀደ አመጽ ከእንግዲህ ተቀባይነት እንደሌለው አስገንዝቧል፡፡ በለውጡ ተስፋ አድርጐ ማንኛውንም የአመጽ መንገድ በማቆም ወደ ሠላማዊ ትግል መመለሱን የጠቆመው አርበኞች ግንቦት 7፤ ሌሎች የፖለቲካ ሃይሎችም ተመሳሳይ መንገድ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡ቀደም ሲል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩ አባላቱ በምንም አይነት የትጥቅና የአመጽ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዳይሳተፉ ግልጽ መመሪያ ማስተላለፉን ያስታወሰው ንቅናቄው፤ እስካሁን ድረስ አባላቱ ለሠላም መስፈንና ለህግ የበላይነት መከበር ቀናኢነት ማሳየታቸውንና ምንም አይነት የአመፃና የትጥቅ እንቅስቃሴ ውስጥ አለመሳተፋቸውን አረጋግጧል፡፡ “ለወደፊትም ምንም አይነት አመፃ ውስጥ አባሎቼ እንደማይሳተፉ እርግጠኛ ነኝ” ያለው ንቅናቄው፤ ሌሎች ሃይሎችም በዚህ መንገድ የሀገሪቱ ለውጥ የማይደናቀፍበትን ሁኔታ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባርና መንግስት የገቡበት እሰጣ ገባ በአስቸኳይ በውይይትና በድርድር ሊፈታ ይገባል ያሉት የፓርቲዎች፤ የኦነግ የፖለቲካ አካሄድ ለሀገር ቀጣይ የለውጥ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ ከተመሠረተ ከ40 አመት በላይ ያስቆጠረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፤ ከምስረታው ጀምሮ ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነት ሲታገል የቆየ ድርጅት መሆኑን የገለፁት ፖለቲከኞች፤ የህዝቡ ትግል ፍሬ እያፈራ ባለበት በዚህ ወቅት የግንባሩ አመራሮች ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ገዥ ፓርቲ ኦዴፓ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ምንም የፖለቲካ ትርፍ አያስገኝም ብለዋል፡፡ የኦነግ የፖለቲካ አመራርና ልሂቃንም ሆኑ የኦዴፓ አመራሮች ጉዳዩን በሰከነ መንገድ ተወያይተው መፍትሔ ካላበጁ፣ ውዝግቡ ለሀገሪቱ የለውጥ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሊሆን ይችላል ይላሉ - ፖለቲከኞቹ፡፡ በኦነግ እና በኦዴፓ (መንግስት) መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት ምክንያቱ ሁለቱም በተደራደሩበት መንገድ ያለ መጓዛቸው ነው የሚል እምነት እንዳላቸው የገለፁት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕ/ር መረራ ጉዲና፤ “ሶስተኛ ወገን በሌለበት የሚደረጉ ማናቸውም ስምምነቶች እንዲህ ያሉ ችግሮችን መፍጠራቸው እንደማይቀር ይታወቃል” ብለዋል፡፡ ለተፈጠረው ውዝግብ አንዱ መፍትሔ ሁለቱም ወገኖች በአስመራ የተስማሙበትን ጉዳይ በጋራ ተቀምጠው
ፓርቲው ከሌሎች ጋር የመዋሃድ እቅዱ በጉባኤው ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል ሰማያዊ ፓርቲ ነገ በሚያደርገው 2ኛ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ከአርበኞች ግንቦት 7 እና ከኢዴፓ ጋር ውህደት ለመፈፀም የተያዘውን እቅድ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ የሸዋስ አሰፋ አስታወቁ፡፡ “ተፎካካሪ ፓርቲዎች አንድ ሆነው ተጠናክረው መውጣት አለባቸው የሚል እምነት ከመነሻውም ፓርቲያችን ነበረው” ያሉት ሊቀ መንበሩ፤ “ይህ ጥረቱ ፍሬ አፍርቶ በአሁን ወቅት ከአርበኞች ግንቦት 7 እና ከኢዴፓ ጋር ውህደት በመፈፀም ለኢትዮጵያ ህዝብ የቆመ፣ ጠንካራ መሰረት ላይ የተዋቀረ ፓርቲ ለመመስረት በዋዜማው ላይ እንገኛለን” ብለዋል፡፡በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የፓርቲው አመራሮች፤ አዲስ የሚመሰረተው ሁሉን አቀፍ ፓርቲ ግዙፍና ጠንካራ ሆኖ ገዥውን ፓርቲ የሚገዳደር ይሆናል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት አስታውቀዋል፡፡ መሰረቱን በዜግነት ፖለቲካ ላይ አድርጎ የሚቋቋመው አዲሱ ፓርቲ፤በዋናነት በሃገሪቱ በዜጎች መካከል ያለውን የኑሮ አለመመጣጠን የማስተካከል አላማ ያነገበ ሲሆን ርዕዮተ ዓለሙን በማህበራዊ ፍትህ ላይ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመራሮቹ ጠቁመዋል። ነገ እሁድ ታህሳስ 21 የሚካሄደው የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ምናልባትም የመጨረሻው የፓርቲው
“ኮሚሽኑ የተቋቋመው በህገ መንግሥቱ ፍልስፍና ላይ ተመስርቶ ነው” ባለፈው ሳምንት የፀደቀው የማንነትና የድንበር ጉዳዮች አጣሪ ኮሚሽን፤ በየትኛውም መንገድ ህገ መንግስቱን እንደማይጥስ የገለፁት የህግ ባለሙያዎች፤ በፓርላማ አባላት የተነሳው ክርክርም የህግ መሰረት የሌለው ነው ብለዋል፡፡ የትግራይ ክልል ተወካዮች በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አዋጁ ህገ መንግሥቱን ይፃረራል ሲሉ የሞገቱ ሲሆን ተመሳሳይ ተቃውሞና ሙግትም በትግራይ የፖለቲካ ልሂቃን ሲስተጋባ ሰንብቷል፡፡ የትግራይ ክልል የህገ መንግስት ተርጓሚ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሰሞኑን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ኮሚሽኑ ህገ መንግስቱን የሚጥስና ለክልሎች የተሰጠውን ሥልጣን የሚጋፋ መሆኑን በመግለፅ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም መምህሩ ሜ/ጀነራል አበበ ተ/ሃይማኖትም፤ የኮሚሽን አዋጁ ህገ መንግስቱን ይጥሳል ሲሉ ይሞግታሉ፡፡ ህገ መንግሥቱ የማንነትና የድንበር ጉዳይን የመፍታት ብቸኛ ስልጣን የሚሰጠው ለፌዴሬሽን ም/ቤት ነው የሚሉት ጀነራሉ፤ የኮሚሽኑ መቋቋም ህገ መንግስቱ በግልፅ ለፌዴሬሽን ም/ቤት የሰጠውን ስልጣን መጋፋት ነው ብለዋል፡፡ የድንበር ወይም የማንነት ጥያቄ ሲቀርብ፣ የፌዴሬሽን ም/ቤት በህገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን አጣሪ ጉባኤ ያቋቁማል የሚሉት ሜ/ጀነራል አበበ፤ መሆን የነበረበትም በፌዴሬሽን ም/ቤት
የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ወደ 8 ሚሊዮን እንደሚያሻቅብ ተጠቆመ በቤኒሻንጉልና በምዕራብ ወለጋ አዋሳኝ ሰሞኑን የፀጥታ ኃይሎች የወሰዱትን የህግ ማስከበር እርምጃ ተከትሎ አንፃራዊ መረጋጋት በመስፈኑ ለተፈናቃዮች እርዳታ ማቅረብ መጀመራቸውን የረድኤት ድርጅቶች አስታወቁ፡፡ ቀደም ሲል በግጭቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተፈናቀሉ ለማወቅ አስቸጋሪ እንደነበር የጠቆመው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት፤የተፈናቃዮች ቁጥር ሩብ ሚሊዮን መድረሱን አስታውቋል፡፡ ለእነዚህ ተፈናቃዮች አስቸኳይ እርዳታ ለማቅረብም 25.5 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል። ከተፈናቀሉት 255 ሺ ያህል ዜጎች መካከል 57 ሺህ የሚሆኑት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ አሶሳና ከማሺ ዞን ውስጥ የሚገኙ ሲሆን 200 ሺ ያህሉ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው፣ በምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ውስጥ የሰፈሩ መሆናቸውን ጽ/ቤቱ በሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ ከሰሞኑ ተፈናቃዮች ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ የረድኤት ድርጅቶች ምልከታ ያደረጉ ሲሆን ተፈናቃዮቹ አስቸኳይ የህክምና፣የተመጣጣኝ ምግብና የመጠለያ አቅርቦት እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቀዋል፡፡ ተማሪዎችም ትምህርት ማቋረጣቸውም በሪፖርታቸው ተመልክቷል፡፡ ይህን እርዳታ በአስቸኳይ ለማቅረብም 25.5 ሚሊዮን ዶላር ለህክምና ቁሳቁስ፣ለምግብ፣ ለህፃናትና እናቶች አልሚ ምግብ እንዲሁም ለዘይት መግዣ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት
በዜጋ ፖለቲካ የሚያምን ሁሉ ሊቀላቀል ይችላል ተብሏል በፓርቲ ጥምረት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ቦታ የነበረውን የ1997ቱን ቅንጅት የፈጠሩ ፖለቲከኞችና ፓርቲዎች በድጋሚ ሊሰባሰቡ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የሚሰባሰቡት ደግሞ እንደከዚህ ቀደሙ በ“ቅንጅት” ወይም በጥምረት ሳይሆን በውህደት ነው፡፡ ውህደቱም የአመራሮችን በጎ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ ዋነኛው የውህደቱ ፈፃሚዎች የየፓርቲዎቹ አባላት ይሆናሉ ተብሏል፡፡ ፓርቲዎቹ የሚዋሃዱት በአመራር ደረጃ ሳይሆን ከስር ጀምሮ ባሉ አባላት ነው፡፡ የዚህ ውህደት ፈፃሚዎች ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7፣ ሰማያዊ፣ ኢዴፓ፣ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ ሌሎችም በዜግነት ፖለቲካ የሚያምኑ የዚህ ውህደት አካል መሆን ይችላሉ ተብሏል፡፡ ሠማያዊ ፓርቲ ላለፉት ሁለት አመታት በአላማ ከሚመሳሰሉት ጋር ለመዋሃድ ሌት ተቀን ባለመታከት ሲሰራ መቆየቱን የጠቆሙት ሊቀመንበሩ አቶ የሸዋስ አሠፋ፤ “ጥረታችን ፍሬ አፍርቶ አሁን ለኢትዮጵያ ህዝብ የቆመ፣ ጠንካራ ስረ መሠረት ያለው ፓርቲ በጋራ ለመመስረት በዋዜማው ላይ እንገኛለን” ብለዋል፡፡ አዲሱን ፓርቲ ለመመስረት ነባር ፓርቲዎች ህልውናቸው ሙሉ ለሙሉ እንደሚከስም የሚገልፁት አቶ የሸዋስ፣ ሊቀመንበሩን ጨምሮ በተለያየ ደረጃ ያሉ አመራሮችም ወደ የወረዳቸው ሄደው ከህዝብ
በተረጋጋ አንደበት ነገሮችን የማስረዳት ችሎታውና ገለፃው ትኩረትን የመሳብ አቅም አለው፡፡ አንደበተ ርቱዕ ነው፡፡ ምናልባት የሬዲዮ ጋዜጠኛና የሥነ ፅሁፍ ባለሙያ መሆኑ ሳይጠቅመው አልቀረም፡፡ “ስለ ኢትዮጵያ ክፉ ክፉውን ሳይሆን ቀናውን ማሰብ ይበጃል” የሚል ፅኑ እምነት አለው፡፡ በእድሜም በእውቀትም መብሰሉ ያመጣው ድምዳሜ ይመስላል። መንፈሰ ጠንካራ እንደሆነ ሁለመናው ይመሰክራል፡፡ ጋዜጠኛና መምህር ደምስ በለጠ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአገሩን መሬት የረገጠው ከ32 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ በገባ በሳምንቱም በአዲስ አድማስ ቢሮ ተገኝቶ፣ ሰፊ ቃለ ምልልስ አድርጓል፡፡ የስደት ህይወቱን፣ የወደፊት ህልሙንና ራዕዩን፣ ለአገሩ ያለውን በተስፋ የተሞላ ምኞት አውግቶናል - በቃለ ምልልሱ፡፡ በሳምንቱ ድንገተኛ ህልፈቱ ተሰማ፡፡ ለብዙዎች እጅግ አስደናጋጭና አሳዛኝ ነበር፡፡ ለ7 ዓመታት ያህል በሩሲያ በትምህርትና በተለያዩ የሚዲያ ስራዎች የቆየው ጋዜጠኛ ደምስ፤ በሰሜን አሜሪካ በሬዲዮ ጋዜጠኝነትና በመምህርነት ስራ ላይ ተሰማርቶ ለ25 ዓመታት ኖሯል፡፡ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢንተርኔት የአማርኛ ሬዲዮ መስራቹ ጋዜጠኛ ደምስ፤ ወደ አገሩ የተመለሰው ባዶ እጁን አልነበረም፡፡ ብዙ ተስፋና ራዕይ ሰንቆ ነበር፡፡ በሚዲያው ኢንዱስትሪ በርካታ ተግባራትን
አቶ በረከትና አቦይ ስብሃት ሃሳብ ክፉኛ ተተቸባለፈው ሳምንት ቅዳሜና እሁድ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በሃገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በተካሄደው ውይይት በአቶ በረከት ስምኦንና በሌሎች ምሁራን የመነሻ ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን የአቶ በረከትና የአቦይ ስብሃት ሃሳብ ጠንካራ ትችትና ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡በዚህ ውይይት መድረክ ላይ አቶ በረከት ባለፉት 27 ዓመታት የገዥው ፓርቲ ሊቀመንበርና የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ሆነው የመሩትን የአቶ መለስ ዜናዊን፣ የአቶ ኃ/ማርያምን ደሳለኝና የዶ/ር ዐቢይን የአመራር ዘመን እያነፃፀሩ ገምግመዋል፡፡ በአቶ መለስ አመራር ውስጥ ህግ የተከበረባት፣ ልማት የተሳለጠባትና አመራሩም ጠንካራ የነበረበት መሆኑን ያወሱት አቶ በረከት፤ በአንፃሩ በአቶ ኃ/ማርያም ዘመን “ልፍስፍስ” አመራር የነበረበትና አገሪቱ የኋልዮሽ ጉዞ የጀመረችበት ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡ አሁን ያለውን የዶ/ር ዐቢይ አመራር ደግሞ ህገ መንግስቱን የሚጥስ፣ ህግን ማስከበር ያልቻለና ሰላም የደፈረሰበት ሲሉ ገልፀውታል አንዳችም በጎ ነገር ሳይጠቅሱ፡፡ በአቶ መለስና በአቶ ኃይለማርያም የጠ/ሚኒስትርነት ዘመን ቁልፍ ስልጣን ላይ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን፤ እሳቸው በአመራሩ ውስጥ የነበራቸውን ሚና በግምገማቸው አይጠቅሱም፡፡ በትግራይ ዋነኛውን ተቃዋሚ ፓርቲ “አረና” የሚመሩት
ከ6ሺ ብር ወደ 71 ሺ ብር፣ ከ7 ሺ ብር ወደ 140 ሺ ብር አሻቅቧልየፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፤ ለንግድና ለድርጅት አገልግሎት በሚያከራያቸው ቤቶች ላይ ከ500 እስከ 2200 ፐርሰንት የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ ያደረገ ሲሆን ከሁለት ሺህ በላይ ተከራዮች ጭማሪው ፍትሃዊ አይደለም ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በበኩሉ፤ የክፍያ ተመን ማስተካከያውን ያደረገው ቤቶቹ በሚገኙበት አካባቢ የሚገኙ ተመሳሳይ የግለሰብ ህንፃዎች የሚከራዩበትን ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ለረጅም ጊዜ ሲያካሂድ የቆየውን ጥናት ተንተርሶ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የዋጋ ጭማሪው ከሚቀጥለው ጥር ወር 2011 ጀምሮ የፀና እንደሚሆን የገለጸው ኮርፖሬሽኑ፤ በማስተካከያ ዋጋው ላይ ቅሬታ ያላቸው አካላት ደብዳቤው በደረሳቸው በ5 ቀናት ውስጥ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቆ፤ ደንበኞች እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2011 ድረስ በተሻሻለው ዋጋ መሠረት አዲስ ውል እንዲዋዋሉ አሳስቧል፡፡ “የዋጋ ጭማሪው ወቅቱን ያላገናዘበና የቤቶቹን ውስጣዊ ገጽታ ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው” ያሉት ማሻሻያውን የተቃወሙ ተከራዮች፤ መንግስት አቅማቸውን ታሣቢ ባደረገ መልኩ ጉዳያቸውን በድጋሚ እንዲያጤን ጠይቀዋል፡፡ አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ በአፄ ኃይለስላሴና በደርግ ዘመን
- “አዋጁን ማጽደቅ ልንወጣ የማንችለው አደገኛ ችግር ውስጥ ያስገባናል”- “ህገመንግስቱን ሽፋን አድርገን ስንሰራ የኖርነውን ሃጢያት የምንታጠብበት አዋጅ ነው”- አዋጁ በ33 የተቃውሞ ድምፅ፣ በአራት ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ ድጋፍ ፀድቋል• የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላቱን ያወዛገበው የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ በአብላጫድምጽ ፀደቀ፡፡ 33 የምክር ቤቱ አባላት የአዋጁንመጽደቅ የተቃወሙት ሲሆን አራቱ ደግሞ ድምጽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ምክር ቤቱ ከትላንት በስቲያ ሃሙስ ባካሄደው ዘጠነኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ቀርቦ የነበረውን የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና ለህግ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ለዝርዝር እይታ መርቶት ነበር፡፡ ሁለቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ረቂቅ አዋጁን በዝርዝር ካጠኑና ለሣምንታት ከተወያዩ በኋላ ማሟላት ይገባዋል ብለው ያመኑባቸውን ጉዳዮች በማካተት ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ ታህሳስ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ለውሣኔ በቀረበው በዚህ የማቋቋሚያ አዋጅ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ከዚህ ቀደም በምክር ቤቱ ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ ውዝግብና ክርክር አካሂደውበታል፡፡ የትግራይ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር
ደራሲ - ተክለማሪያም መንግስቱ ዘውግ - ግለ-ታሪክና ታሪክ ይዘት - የወታደርነት ህይወት እስከ ምርኮነት፤ ደርግ ከአነሳሱ እስከ ውድቀቱ (ከ1967-1983) የገፅ ብዛትና ዋጋ - 312፤ 150 ብር
በቱርካውያን ባለሃብቶች በሠበታ ከተማ የተቋቋመው አይካ አዲስ የጨርታ ጨርቅ ፋብሪካ ከትናንት ጀምሮ ሥራ ማቆሙን ለሠራተኞቹ አስታወቀ፡፡4000 (አራት ሺ) የሚሆኑ የፋብሪካው ሠራተኞች ከረብዕ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ላይ የሠነበቱ ሲሆን አርብ ጠዋት ወደ ፋብሪካው ሲመለሱ በማስታወቂያ ቦርድ ላይ “ሳይሰራ የሚከፈል ደሞዝ ስለሌለ፣ ፋብሪካው ለጊዜው ስራ አቁሟል” የሚል ማስታወቂያ ተለጥፎ፣ ሠራተኛው እንዲመለስ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የፋብሪካው ባለቤት ቱሪካዊው ዩሱፍ ሃይዲኒ ፋብሪካውን ጥለው ከተሠወሩ ከ6 ወር በላይ መሆኑን የገለፁት ሠራተኞች፤ “ፋብሪካውን የሚያስተዳድረው” ልማት ባንክ ነው የሚል መረጃ እንደደረሳቸው፤ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ፋብሪካውን የሚያስተዳድረው አካል በውል እንደማይታወቅ ተናግረዋል፡፡ ሠራተኛው የስራ ማቆም አድማ ላይ የሰነበተውም “የፋብሪካው የወደፊት እጣ ፈንታና የስራ ዋስትናችን ይረጋገጥልን” በሚል ጥያቄ እንደነበር የገለፁት ሠራተኞቹ፤ ከአርብ ጀምሮ ግን ፋብሪካው ላልተወሰነ ጊዜ ስራ ማቆሙ በማስታወቂያ እንደተገለፀላቸው ተናግረዋል፡፡ ላለፉት 6 ወራት የፋብሪካው መደበኛ ስራ ተቀዛቅዞ መቆየቱን የጠቆሙት ሠራተኞቹ፤ ይሁን እንጂ ሠራተኛው የሚያገኘው ወርሃዊ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም አልተቋረጠም ነበር ብለዋል፡፡
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት “ይቅር ተደርጐልን መፈታት አለብን” የሚሉ እስረኞች ከትናንት በስቲያ ከሐሙስ ጀምሮ ረብሻ በማስነሳት የእርስ በርስ ግጭት መፈጠሩ ታውቋል፡፡ በማረሚያ ቤቱ ዞን ሁለት በተባለው ክፍል ከአዲስ አበባና ከፌደራል የፍትህ አካላት የተውጣጡ አስተዳዳሪዎች የታራሚዎችን አያያዝ በተመለከተ በአካል ተገኝተው ለመታዘብ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ ረብሻው መቀስቀሱን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ታራሚዎቹ በዋናነት “የይቅርታ ማመልከቻ አስገብተን፣ እንዴት እስካሁን ሳንፈታ ቆየን፤ ልንፈታ ይገባል” በሚል ተቃውሞ መጀመራቸውን የገለፁት ምንጮች፤ ይኸም ወደ እርስ በእርስ ግጭት አምርቶ በድንጋይና በተለያዩ ቁሳቁሶች በመታገዝ፤ በርካቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል፡፡ ረብሻው መፈጠሩን ለአዲስ አድማስ ያረጋገጡት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ገረመው አያሌው፤ ግጭቱና ረብሻው ብዙም ሳይስፋፋ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ ታራሚዎቹ ዞን ሁለትን ከዞን ሶስት የሚለየውን አጥር በማፍረስ ሁለቱን ዞኖች የቀላቀሉ ሲሆን ወደ ሴቶች ማረፊያ ለመግባትም ሙከራ ማድረጋቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
በፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ፓርቲና ኢህአፓን ጨምሮ 16 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰሞኑን በጋራ ባወጡት መግለጫ፤በትግራይ ክልል “በህውሓት” የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችን አውግዘዋል፡፡ ባለፉት 27 አመታት ህወሓት/ኢህአዴግ አገሪቱን ሲያስተዳድር፣ከ1 ትሪሊዮን ብር በላይ በላይ ከኢትዮጵያ በህገ ወጥ መንገድ ወጥቶ፣ በውጭ ሃገር ባንኮች መከማቸቱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱ የጠቆሙት ፓርቲዎቹ፤"በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ዲሞክራሲና ነፃነታቸውን በመጠየቃቸው ምክንያት አካላቸው ጎድሏል፣ ተገድለዋል፣ ተሰቃይተዋል" ብለዋል፤በመግለጫቸው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ አገሪቱን በሚያስተዳድርበት ወቅት ለማመን የሚያዳግቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውንና ከፍተኛ የሆነ የሃገሪቱ ሃብት መመዝበሩን የጠቆሙት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ፤ ሁለቱም የተፈጸሙት በዋናነት "በህወሓት ዘራፊዎችና ገራፊዎች ነው” ብለዋል፡፡ "የድርጊቱ ፈፃሚዎች ግን ፈጽሞ የትግራይን ህዝብ አይወክሉም" ብለዋል - ፓርቲዎቹ፡፡ "ገራፊዎችና ዘራፊዎች" የትግራይ ህዝብን ጋሻ ለማድረግ "የትግራይ ህዝብና ህውሓት አንድ ናቸው" የሚለውን ለማስረገጥ ታህሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም የተቀነባበረ ሰልፍ በማድረግ፣"እኛን ከነካችሁ ሃገር ትበታተናለች" እያሉ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰሙ መሆኑን አጥብቀን እንቃወማለን፤በቁርጠኝነት እንታገላለን ብለዋል - በመግለጫቸው፡፡"በተቃዋሚ ፓርቲ ስም ተደራጀተው ከህውሓት ዘራፊዎችና ገራፊዎች ጎን ቆመው ለውጡን ለማደናቀፍ የሚሯሯጡትን እናወግዛለን"
• መከላከያ ሰራዊት የተጠናከረ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል በሞያሌ በቤኒሻንጉልና በኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች በግጭትና በጥቃት በሳምንት ውስጥ ከ23 በላይ ዜጎች የሞቱ ሲሆን የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ ህግ ለማስከበር አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ከኬንያ ጋር አዋሳኝ በሆነችውና በተደጋጋሚ የቀውስ ቀጠና ሆና የዘለቀችው ሞያሌ ከተማ ባለፈው ማክሰኞ በበቀለ ሞላ ሆቴል በስብሰባ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ 13 ያህል መገደላቸውን ምንጮች ያመለከቱ ሲሆን በርካቶች ወደ ጎረቤት ኬንያ እንደተሰደዱም ተጠቁሟል፡፡ ከጥቃቱ በኋላ የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን መቆጣጠሩን የሚገልፁት የአካባቢው ምንጮች፤ አሁንም አለመረጋጋቱ እንደቀጠለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ከጥቂት ሳምንት በፊት በአካባቢው በተፈጠረ የእርስ በእርስ ግጭት 21 ሰዎች መገደላቸውና 61 የሚሆኑት በፅኑ መቁሰላቸውንም ምንጮች አስታውሰዋል፡፡ ለ “አፍሪካን ሞኒተር” አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ የአካባቢው ነዋሪ፤ በሞያሌ ያለው ሁኔታ ከእለት ወደ እለት አስጊ እየሆነ ነው፤ የፌደራል መንግስት የመጨረሻ የሚለውን እልባት መስጠት አለበት ብለዋል፡፡ ባለፉት 10 ወራት ውስጥ በሞያሌ ከተማ ካጋጠሙ ተመሳሳይ ጥቃትና ግጭቶች ጋር በተያያዘ ከአካባቢው ተሰድደው ኬንያ የሚገኙ
- የሺሻ ምርትን ማምረትት ማስመጣት፣ መሸጥ፣ ማስጨስ የተከለከለ ነው- ቢራን ጨምሮ ማንኛውንም የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያዎች ማስተዋወቅ የሚቻለው ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ ብቻ ነውየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትምባሆና በአልኮል መጠጦች ማስታወቂያዎች ላይ ገደቦችን ለመጣል በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ እየመከረ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ሰሞኑን ለውይይት ባቀረበውና የምክር ቤቱ አባላት በስፋት እየተወያዩበት በሚገኘው በዚሁ ረቂቅ አዋጅ ላይ እንደተገለፀው፤ ማንኛውንም የአልኮል መጠጥ በህዝብ መሰብሰቢያና መገልገያ ቦታ፣ በስፖርት ማዘውተሪያ፣ በአውራ ጐዳና ላይ፣ በጋራ የመኖሪያ ቤቶችና በመሰል ቦታዎች ላይ ማስተዋወቅ አይቻልም፡፡ ማንኛውም የአልኮል ይዘቱ ከ10% በላይ የሆነ አልኮል አምራች፣ አስመጪ ወይም አከፋፋይ የህዝብና የመንግስት በዓላትና ስብሰባዎችን፣ የንግድ ትርኢቶችን፣ የስፖርት ውድድሮችን፣ የትምህርት ቤት ዝግጅቶችን እንዲሁም ወጣቶች የሚሳተፉባቸውን ፕሮግራሞች በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ስፖንሰር ማድረግ አይችሉም፡፡ ቢራን ጨምሮ የአልኮል ይዘቱ ከ10% በታች የሆነ አልኮል በብሮድካስት አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚቻለው ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ እንደ ረቂቅ ህጉ፤
*የቀብር ሥነሥርዓታቸው የፊታችን ረቡዕ ይከናወናልከቀዳማዊ ንጉስ ሃይለሥላሴ ዘመን ጀምሮ ረዥም ዕድሜያቸውን በተለያዩ የመንግስት ሃላፊነት ያገለገሉትና በአሁኑ የኢህአዴግ መንግስት ለ12 ዓመታት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፤ባደረባቸው ህመም በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው፣ በ94 ዓመት ዕድሜያቸው ትላንት ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው የፊታችን ረቡዕ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤ/ክርስቲያን የሚፈጸም ሲሆን የአንድ ቀን ሃዘን እንደሚታወጅም ታውቋል፡፡ በንጉሱ ዘመን፣ በኤርትራ የሲቪል አቬሽን ሃላፊ በመሆን የመንግስት ሥራቸውን የጀመሩት መቶ አለቃ ግርማ፤ ከ3 ዓመት በኋላም የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል፡፡ ለሁለት ዓመትም የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዋና ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል፡፡ የፓርላማ አባልም ነበሩ፡፡ የደርግ መንግስት ከወደቀ በኋላ ሥልጣን በተቆጣጠረው ኢህአዴግ መንግስት ለመመስረትና አዲስ ህገመንግስት ለመቅረጽ በተደረገ ስብሰባ ላይ ተጋብዘው ነበር፡፡ በ77 ዓመት ዕድሜያቸው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት መቶ አለቃ ግርማ፤ለሁለት የሥልጣን ዘመን - ለ12 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ቀጥተኛና ግልጽ ባህርያቸው እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋችነታቸው በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን እንዳተረፈላቸው የሚነገርላቸው የእድሜ ባለጸጋው፤
በቅርቡ ለተቋቋመው የብሔራዊ ዕርቅ ኮሚሽን አባልነት ከ50 በላይ ታዋቂ ግለሰቦችና የአገር ሽማግሌዎች ተመለመሉ፡፡ የብሔራዊ እርቅ ኮሚሽን አባላትን በተመለከተ ለውይይት በቀረበው ሰነድ ላይ እንደተጠቀሰው፤ ለኮሚሽኑ ከምሁራን፣ ከስነጥበብ ባለሙያዎች፣ ከታዋቂ የህግ ባለሙያዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከአክቲቪስቶች፣ ከአትሌቶች እና ከአባገዳዎች የተውጣጡ አባላት ተመልምለዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኮሚሽኑ አባልነት ተመርጠው ከቀረቡት መካከል የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝና የቀድሞ የደርግ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኮ/ል ጐሹ ወልዴ ይገኙበታል፡፡ ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም፣ ልኡል በእደ ማርያም መኮንን፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ፣ ቀደማዊ መፍቲ ሐጂ ሁመር ኢድሪስ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጂበል፣ ዶ/ር ምህረት ደበበ፣ መጋቢ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፣ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ፣ ፕ/ር አህመድ ዘካሪያ፣ አባገዳ በየነ ሰንበቶ፣ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የጋሞ፣ የሲዳማና የሌሎች አካባቢ የሀገር ሽማግሌዎች በእርቅ ኮሚሽኑ አባል እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል ለውይይት ከቀረበው ሰነድ ዝርዝር
“መገንጠል የትግራይ ህዝብ አጀንዳ አይደለም” መቀሌን ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ከሰሞኑ ለሁለተኛ ጊዜ “ህገ መንግስቱ ይከበር፣ የማንነት የድንበር ኮሚሽን ሊቋቋም አይገባም፤ ዘርን ለይቶ የሚያጠቃ የህግ ማስከበር ሂደት ተቀባይነት የለውም” የሚሉ መፈክሮች ተንፀባርቀዋል፡፡ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል “የትግራይ ወጣቶች በቀጣይ ለማንኛውም ነገር እንዲዘጋጁ አበክረው ያሳሰቡ ሲሆን፤ የህዝቡ ድምጽ ሊደመጥ እንደሚገባውም ተናግረዋል - በሰልፎቹ፡፡ ሠላማዊ ሰልፉ አስፈላጊ እንደሆነ የሚገልፀው የአረና ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ፤ በተለይ “ህገመንግስቱ ይከበር” የሚለው መርህ የምስማማበት ጉዳይ ነው ይላል፡፡ ከዚህ ቀደም በትግራይ ህገ መንግስት ይከበር ብሎ ሠልፍ መውጣት እንደ ሃጢያት ይቆጠር እንደነበር ያስታወሰው አብርሃ፤ “አሁን ህወሓት በራሱ ደርሶ ሲያየው ያደረገው ቢሆንም የምደግፈው ጉዳይ ነው” ብሏል፡፡ “ሠልፍ በዋናነት ትክክለኛ ጥያቄ የያዘ ቢሆንም ልክ ህወሓትን የሚደግፍ ተደርጐ መቆጠር የለበትም” ያለው ሊቀመንበሩ፤ የትግራይ ህዝብ አጥፊዎችን ከህግ ለመከላከል ያደረገው ሠልፍ ተደርጐ መውሰድም እንደሌለበት ይገልፃል፡፡ የህወኃት ባለስልጣናት ህዝቡ ከጐናቸው የተሠለፈ በማስመሰል ከፌደራል መንግስት ጋር ለመደራደሪያነት ሊጠቀሙበት ይፈልጉ ይሆናል ያለው
ባለፉት 27 ዓመታት በመንግሥት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለተፈፀመባቸው ዜጎች ካሳ የሚጠይቅ የህግ ባለሙያዎች ማህበር እየተቋቋመ ሲሆን የሰብአዊ መብት በተፈፀመባቸው ወገኖች ላይ ጥናት እየተካሄደ መሆኑም ታውቋል፡፡ በዜጎች ላይ ለተፈፀመ የሰብአዊ መብት ጥሰት መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ተጠርጣሪዎችን ወደ ህግ እያቀረበ መሆኑን ያደነቁት የህግ ባለሙያው አቶ አመሃ መኮንን፤ “መወሰድ ካለባቸው እርምጃዎች እስካሁን ግማሽ መንገድ ነው የሄድነው፤ ቀሪ ለህግ መቅረብ ያለባቸው ተጠርጣሪዎችና ጉዳዮች አሉ” ብለዋል፡፡ መንግሥት ለተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እውቅና መስጠቱና ፈፃሚ ተጠርጣሪዎችን ለህግ ማቅረብ መጀመሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡት አቶ አመሃ፤ “አካላቸውን ለተጎዱ፣ አካላቸውን ላጡ፣ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው፣ እንዲሁም ኑሮአቸውና ቤተሰባቸው ለተበተነባቸው ተገቢው ካሳ ሊከፈላቸው ይገባል” ብለዋል፡፡ ለተፈፀመ ጉዳት ሁሉ ካሳ በህግ መሰጠት አለበት የሚሉት የህግ ባለሙያው፤ ይህን ካሳ ለማሰጠትም በመመስረት ላይ ያለው “የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብት ማህበር” በጥናት ተደግፎ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡ ተጎጂዎች ወደ መደበኛ ህይወታቸው የሚመለሱበት በቂ ህክምና የሚያገኙበት፣ የስነ ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ
የመንግሥት ተቋማት አመራሮች ማዕከሉን እየጎበኙ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጥቅምት 25 ቀን 2011 ዓ.ም መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን መጎብኘታቸውን ተከትሎ፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከ164 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን የመጠለያ ህንፃዎች ለመገንባት ቃል ገብተዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ፤ ከህብረተሰቡ በአጭር የ8151 መልዕክት ሲሰበስብ የቆየውን 74,718,165 (ሰባ አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ አምስት) ብር አስረክቧል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማዕከሉ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት፣ ዜጎች በአጭር መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ፣ ተቋማት ደግሞ ማዕከሉን እየጎበኙ ድጋፍ እንዲያደርጉ መልዕክት ማስተላለፋቸው የሚታወስ ሲሆን ለዚህ ፈጣን ምላሽ የሰጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሰራተኞች አዋጥተው ከሰጡት 10 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ አንድ ባለ 5 ፎቅ ህንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል ገብቷል፡፡ 100 ነፃ የደርሶ መልስ ቲኬቶችን ጨምሮ የተለያዩ የዓይነት ድጋፎችንም እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም የ15 ሚሊዮን ብር ልገሳና አንድ የህንፃ ወለል በ56 ሚሊዮን ብር ገንብቶ ለማስረከብ ቃል
ከታሰሩ በኋላ ሃብታቸው በ6 በመቶ ጨምሯል ተብሏል በሳዑዲ አረቢያ መንግስት በቁጥጥር ስር የዋሉትና ከአንድ አመት በላይ በቁም እስር ላይ የሚገኙት ሼክ መሃመድ አል አሙዲ በሙስና ወንጀል ክስ እንደተመሰረተባቸውና ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ አንድ የአገሪቱ ባለስልጣን ከትናንት በስቲያ ማስታወቃቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡በሳዑዲ አረቢያ ባለሃብቶች አካባቢ ሼክ አል አሙዲ በህይወት የሉም በሚል በስፋት ሲናፈስ የነበረው አሉባልታ ፍጹም ሃሰት መሆኑን የገለጹት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት ባለስልጣኑ፣ አል አሙዲ በህይወት እንዳሉና አሁንም ድረስ በእስር ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ የሰጡ ሲሆን፣ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ቢያረጋግጡም የችሎቱ ትክክለኛ ቀን ግን ገና አለመወወሰኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡የሼክ አል አሙዲ ቃል አቀባይ ቲም ፔንድሪ በበኩላቸው ባለሃብቱ በምንም አይነት የወንጀል ድርጊት በይፋ ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ከመግለጽ ውጭ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር አስተያየት ለመስጠት አለመፍቀዳቸውን ዘገባው ገልጧል፡፡አል አሙዲን በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጊዜ አንስቶ ባሉት ጊዚያት የተጣራ የሃብት መጠናቸው በ6 በመቶ እድገት በማሳየት 8.3 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የጠቆመው ብሉምበርግ፣ ባለሃብቱ በእስር ላይ ቢገኙም አለማቀፍ ቢዝነሳቸው ትርፋማ
ሰሞኑን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና የተሰጠው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮች፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በአማራ ህዝብና በኢትዮጵያ ጉዳይ እንዲሁም በህግ የበላይነት ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ የአብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ስለውይይቱ ለአዲስ አድማስ በሰጡት ማብራሪያ፤ አመራሮቹን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ቢሮአቸው ጠርተው ለሰአታት የቆየ ውይይት ማካሄዳቸውን ጠቁመዋል፡፡በውይይቱ በዋናነት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው ፍትህን የማስፈን ጉዳይ፣ በየአካባቢው እየተነሱ ስላሉ ግጭቶች እንዲሁም የሀገር አንድነትንና በህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት አስጠብቆ ወደፊት መጓዝ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸውን አቶ ክርስቲያን አስታውቀዋል፡፡ በአብን በኩል በዋናነት የአማራ ህዝብ የማንነት፣ የፍትሃዊ ተጠቃሚነትና የህልውና ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎች መቅረባቸውን ያወሱት ኃላፊው፤ ጠ/ሚኒስትሩም እነዚህን ጉዳዮች በአግባቡ እንደሚረዱ ገልፀው፣ ነገር ግን ችግሮቹ በሰከነ መልኩ ዘላቂ በሆነ መንገድ መፍታት እንደሚገባ መግለፃቸውን ጠቁመዋል፡፡ እርቅ፣ ህገ መንግስት መቀየር፣ የህዝብ ቆጠራ ጉዳዮችም በውይይቱ ላይ ተነስተዋል፡፡ህገመንግስቱን ማሻሻል እንደሚገባ መግባባት ላይ መደረሱን ነገር ግን ም/ቤቶች በሙሉ በገዥው ፓርቲ ስለተያዙ በአጭር
ለገናና ለፋሲካ ኤክስፖ 65 ሚ. ብር በጀት ተይዟል የተለያዩ ትልልቅ ኤክስፖዎችንና የመዝናኛ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ሀበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን ያዘጋጀው “ሀበሻ የገና ኤክስፖ” የዛሬ ሳምንት በኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚከፈት የሀበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡ የኩባንያው ኃላፊዎች በሳምንቱ አጋማሽ ላይ በሳፋየር አዲስ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የገናና የፋሲካ በዓል ኤክስፖን ለማዘጋጀት የኤግዚቢሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ባወጣው ጨረታ ሀበሻ ዊክሊ በ47 ሚ. ብር ጨረታውን ማሸነፉን ተናግረዋል፡፡ ለሁለቱ ኤክስፖዎች ጨረታና ዝግጅት 65 ሚሊዮን ብር ማስፈለጉንና በጀቱ መያዙን የገለፁት የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አዶኒክ ወርቁ፤ ለ23 ቀናት በሚዘልቀው በዚህ ኤክስፖ ከ500 በላይ የውጭና የአገር ውስጥ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበትና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይጎበኘዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ለመዝናኛው ዘርፍ ትኩረት ሰጥቻለሁ ያለው ሀበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን፤ በ23 ቀናት 23 የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ለታዳሚ የሚያቀርብ ሲሆን 100 ወጣትና አንጋፋ ድምፃዊያን፣ 7 የተመረጡ ተወዳጅ ባንዶች፣ 13 ያህል ዲጄዎች፣ አራት እውቅ ኮሜዲያኖችና ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ሶስት የሰርከስ ቡድኖች ዝግጅቱን ያደምቁታል ተብሏል፡፡ ለህፃናት መዝናኛ
- “ኢህአዴግ አገራዊ እርቅና መግባባት አያስፈልግም ብሎ ጽንፍ ይዞ ሲከራከር ነበር” - “በሁሉም ዜጐች የሚከበሩና ስማቸው በመጥፎ የማይነሱ ዜጐች በኮሚሽኑ ውስጥ በአባልነት ይታቀፋሉ” ለግጭትና ቁርሾ ምክንያት የሆኑ ችግሮች፣ ምክንያቶችና የስፋት መጠናቸውን አጣርቶ እውነታውን በማውጣት ተመልሰው እንዳይመጡ በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ፣ ተግባራዊ እርምጃዎችን የሚወስድና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን የሚያመነጭ ገለልተኛና ነፃ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሊቋቋም ነው፡፡ የእርቀ ሰላም ኮሚሽኑን ማቋቋም አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት የሚዘረዝረውና ለምክር ቤቱ የቀረበው መግለጫ እንደሚያመለክተው፤ ኢህአዴግ አገራዊ እርቅና ይቅርታ አስፈላጊ አይደለም የሚል ጽንፍ ይዞ ሲከራከር መቆየቱን ይጠቁማል፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ግለሰብ ፖለቲከኞች አገራዊ እርቅ ለአገራዊ ችግሮቻችን እንደቁልፍ መፍትሔ የሚታዩ ጉዳዮች እንደሆኑና ኢትዮጵያ ከገባችበት ፖለቲካዊ ችግር መሰረታዊ በሆነ መልኩ እንድትወጣ አገራዊ እርቅና መግባባት በጣም አስፈላጊ እንደሆነ በመጥቀስ ሲሟገቱ ቆይተዋል፡፡ ላለፉት በርካታ አመታት እርስ በርሳችን ስንዋጋ፣ አንዱ ሌላውን ሲበድልና ሲያቆስል በመቆየታችን የውጪ ወራሪዎች ካደረሱብን ሰብአዊና ቁሳዊ ጥቃት ይልቅ እርስ በርሳችን አንዱ በሌላው ላይ ያደረሰው ጉዳት በብዙ እጥፍ ይበልጣል ያለው መግለጫው፤ በሃሳብ ልዩነትና በብሔር
በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ብቸኛዋ አፍሪካዊት ናቸው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በታዋቂው ፎርብስ መጽሄት የአመቱ የአለማችን 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ተብለው ከተመረጡት እውቅና ዝነኛ ሴቶች መካከል አንዷ ሆነው የተመረጡ ሲሆን፣ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሆነዋል፡፡ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ 100 የአለማችን ሴቶች በተካተቱበት የፎርብስ የአመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ የ97ኛ ደረጃን የያዙ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ብቸኛ ሴት ፕሬዚዳንት የሆኑት ሳህለ ወርቅ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው በአገሪቱ የጾታ እኩልነትን በማስፈን ረገድ በጎ አንድምታ ያለው ፈር ቀዳጅ እርምጃ መሆኑን ፎርብስ ገልጧል፡፡ፕሬዚዳንቷ በተመድ ቆይታቸው ጉልህና ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ ማከናወናቸውን የጠቆመው ፎርብስ፣ በበዓለ ሲመታቸው ወቅት በአገሪቱ ሰላምና አንድነት ለማስፈን በትጋት እንደሚሰሩ ማስታወቃቸውንም አስታውሷል፡፡የዘንድሮውን የፎርብስ 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር በቀዳሚነት የመሩት የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ መርኬል ሲሆኑ፣ የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ በሁለተኛ፣ የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስቲያን ላጋርድ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡በአመቱ የአለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ
የማሻሻያ አዋጁ ለውይይት ቀርቧል በመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ቁጥር 809/2006 ላይ በተመለከቱ ከ28 በላይ የአዋጁ አንቀፆች ላይ ማሻሻያ ሊደረግ ነው፡፡ በአዲሱ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በወታደራዊ ካምፖች፣ ቢሮዎች ወይም በግል የሠራዊት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ጊዜ የማይሰጥና አደገኛ ወንጀል ወይም የፀጥታ መደፍረስ ሲከሰት ወይም ይከሰታል የሚል በቂ ጥርጣሬ ሲኖር በየደረጃው ያለ አዛዥ እስር ወይም ብርበራ ማካሄድ ይችላል ይላል፡፡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ፣ ለውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመራው ይኸው ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ፤ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሟል ተብሎ በሚታመንበት ጊዜ ምርመራውን የማስጀመርና የመጀመር ኃላፊነትን ለጦር አዛዥና ለወንጀል መርማሪው ሰጥቷል፡፡ በወንጀል መርማሪውና በአዛዥ መካከል ምርመራን ስለመጀመር ወይም ስለማቋረጥ ልዩነት ከተፈጠረ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ያለ አዛዥ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ አዛዥ ምርመራን ለማቋረጥ የሰጠው ትዕዛዝ ህገወጥ ሆኖ ከተገኘ ተጠያቂ ይሆናል። ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 2/2011 ሆኖ ለውይይት በቀረበው በዚሁ የማሻሻያ አዋጅ ላይ እንደተገለፀው፤ በሚኒስትሩና በጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ አቅራቢነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገራዊ ጥቅምና ደህንነትን ለመከላከል ሲባል እጅግ
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች በአል አስመልክቶ ለኢትዮጵያውያን መልዕክት ያስተላለፉት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤ “ቀኑ የኢትዮጵያዊነት በዓል ነው” ብለዋል፡፡ “ውድ የሀገሬ ህዝቦች፤ይህ ቀን የኢትዮጵያዊነት ቀን ነው፤ ይህ ቀን የኃብራዊ አንድነታችን ማክበሪያ ቀን ነው፤ ይህ ቀን ሀገራችን አንድ፤ጸጋዎቿ ግን ብዙ መሆናቸውን የምንገልጽበት ቀን ነው፡፡” በማለት ነው ጠ/ሚኒስትሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን የከፈቱት፡፡ በዓሉ ለይስሙላ የምናከብረው ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የምናደርግበት ትርጉም ያለው በአል ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ ሁላችንም “ሆ” ብለን ወጥተን የኢትዮጵያዊነትን ልዩ ልዩ ጸጋዎች እያሳየን፣ እያከበርንና እየጠበቅን የምናከብረው የህብራዊ አንድነታችን መገለጫ፣ እንዲሁም ልዩነቶቻችን የአንድነታችን ፀጋ፣ አንድነታችንም የልዩነቶቻችን ተደማሪ ዋጋ መሆኑን የምንገልጥበት ታላቅ በአል ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያችን ከሰጠችን ፀጋዎች አንዱ ብዙም አንድም ሆነን ለመኖር መቻላችን ነው፤ ብዙውነታችን ሳይነጣጥለን፣ አንድነታችን ሳይጠቀልለንና ሳይውጠን በዝተን ኖረናል ብለዋል - ዶ/ር ዐቢይ በመልዕክታቸው፡፡“ኢትዮጵያዊነት እንደ ኩሬ ውሃ ፀጥ ብሎ የተኛ አይደለም” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤በብሔረሰቦች መስተጋብር እንደ ባህሪ የሚታደስ እያደገ፣ እየዳበረና እየጠነከረ የሚሄድ የህዝቦች እሴት ነው ብለዋል፡፡ “በኢትዮጵያውያን
ግጭቶች በጊዜ አልባት እንዲበጅላቸው ተጠይቋል በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ህይወት እየቀጠፉና በርካቶችን እያፈናቀሉ ያሉ ግጭቶችን በጥልቀት እንደሚመረምር የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያስታወቀ ሲሆን ግጭቶች ለሃገሪቱ ስጋት ከመሆናቸው በፊት መቋጫ እንዲያገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችና አለማቀፍ ተቋማት አሳስበዋል፡፡ በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከሰሞኑ በተፈጠሩ ብሄር ተኮር ግጭቶች የሰው ህይወት መጥፋቱና መፈናቀል ማጋጠሙ የተገለፀ ሲሆን በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ (ምዕራብ ወለጋ) አዋሳኝ በተፈጠሩ ተመሳሳይ ግጭቶችም ሰዎች ሞተዋል፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል። በእነዚህ አካባቢዎች የረድኤት ድርጅቶች ከፀጥታው አስተማማኝ አለመሆን ጋር ተያይዞ ሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ እንዳልቻሉም አስታውቀዋል፡፡ በምዕራብ ወለጋ የተፈጠሩ ግጭቶችን ተከትሎም በዋና ዋና የኦሮሚያ ከተሞች መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብር፣ ዜጎችን ከሞትና መፈናቀል እንዲታደግ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ የአለማቀፉ የቀይ መስቀል ድርጅት እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በተለይ በምዕራብ ወለጋና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን ብዛት በውል አውቆ ዕለታዊ ሰብአዊ ድጋፍም ማድረስ እንዳልቻሉ ገልፀዋል፡፡ መንግስት በየአካባቢው እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶችን እንዲያስቆምና ሰብአዊ ድጋፍ የሚደርስበትን መንገድ
ኢትዮጵያ ከሌሎች ጎረቤት ሃገራት ተጨማሪ ወደቦችን ለመጠቀም የምታደርገውን እንቅስቃሴ በበጎ መልኩ እንመለከተዋለን ያለው የጅቡቲ መንግስት፤ በኢትዮጵያ በኩል በወደብ መጠቀሚያ ታሪፍ ላይ ቅናሽ እንዲደረግ የቀረበውን ጥያቄ መቀበሉንና በወደቡ የታሪፍ መጠን ላይም ማሻሻያ ለማድረግ ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ እርቅ መፈፀማቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ ወደቦች ማማተሯ አያስከፋንም ያሉት የጅቡቲ የወደብ ኃላፊ ዋሂብ ዳሂር፤ 100 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሃገር ተጨማሪ ወደብ ማፈላለጓ ተገቢ ነው” ብለዋል፡፡ 95 በመቶ የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ሸቀጥ በጅቡቲ ወደብ እንደሚስተናገድ ያወሱት ኃላፊው፤ ሸክሙ መቃለሉ የወደቡን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ ያግዘናል እንጂ አይጎዳንም ብለዋል፡፡ ተጨማሪ ወደቦችን በመገንባት እያደገ የመጣው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን የውጪ ንግድ እንቅስቃሴ ለማስተናገድ ሃገራቸው መዘጋጀቷንም ዋሂብ ዳሂር አስታውቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከጅቡቲ ወደብ በተጨማሪ የሶማሊያ በርበራ ወደብንና የሱዳን ወደብን ለመጠቀም ከየሃገራቱ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወቃል፡፡
ግጭቶች በጊዜ አልባት እንዲበጅላቸው ተጠይቋል በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ህይወት እየቀጠፉና በርካቶችን እያፈናቀሉ ያሉ ግጭቶችን በጥልቀት እንደሚመረምር የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያስታወቀ ሲሆን ግጭቶች ለሃገሪቱ ስጋት ከመሆናቸው በፊት መቋጫ እንዲያገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችና አለማቀፍ ተቋማት አሳስበዋል፡፡ በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከሰሞኑ በተፈጠሩ ብሄር ተኮር ግጭቶች የሰው ህይወት መጥፋቱና መፈናቀል ማጋጠሙ የተገለፀ ሲሆን በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ (ምዕራብ ወለጋ) አዋሳኝ በተፈጠሩ ተመሳሳይ ግጭቶችም ሰዎች ሞተዋል፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል። በእነዚህ አካባቢዎች የረድኤት ድርጅቶች ከፀጥታው አስተማማኝ አለመሆን ጋር ተያይዞ ሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ እንዳልቻሉም አስታውቀዋል፡፡ በምዕራብ ወለጋ የተፈጠሩ ግጭቶችን ተከትሎም በዋና ዋና የኦሮሚያ ከተሞች መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብር፣ ዜጎችን ከሞትና መፈናቀል እንዲታደግ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ የአለማቀፉ የቀይ መስቀል ድርጅት እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በተለይ በምዕራብ ወለጋና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን ብዛት በውል አውቆ ዕለታዊ ሰብአዊ ድጋፍም ማድረስ እንዳልቻሉ ገልፀዋል፡፡ መንግስት በየአካባቢው እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶችን እንዲያስቆምና ሰብአዊ ድጋፍ የሚደርስበትን መንገድ
ሰባት የፖለቲካ ድርጅቶች ለመዋሃድ ተስማሙኢራፓን ጨምሮ በሃገር ውስጥና በውጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 7 የፖለቲካ ድርጅቶች ለመዋሃድ መስማማታቸው ታውቋል፡፡ ሰሞኑን ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በተወያዩበት ወቅት፤ በውይይቱ ላይ 70 ፓርቲዎች መገኘታቸውን የጠቀሱት ዶ/ር ዐቢይ፤ በሃሳብ ተሰባስበው 4 ወይም 5 እንዲሆኑ ምክረ ሃሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ ሰሞኑን ውህደት ለመፈፀም የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙት በሀገር ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት እና በቅርቡ ወደ አገር ቤት የተመለሱ አምስት የፖለቲካ ድርጅቶች ናቸው፡፡ በወ/ሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታና በፕ/ር አቻሜለህ ዲባባ የሚመራው “የኢትዮጵያ መድህን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (መድህን)”፣ በአቶ ስለሺ ጥላሁን የሚመራው “የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ም/ቤት (ሽግግር)”፣ በዶ/ር አክሎግ ቢራራ የሚመራው “ብሩህ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብሩህ)”፣ በአቶ በርገና ባሣ የሚመራው “ቱሣ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ዲሞክራሲያዊ ድርጅቱ (ቱሣ)” እና በአቶ ነሲቡ ስብሃት የሚመራው “ኢትዮጵያችን ንቅናቄ” የውህደቱ አካል ናቸው ተብሏል፡፡ ድርጅቶቹ ለመዋሃድ የተስማሙት ላለፉት 6 ወራት ሠፊ የመጠናናት ውይይት ካደረጉ በኋላ መሆኑን ለአዲስ አድማስ የገለፁት የኢራፓ
ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ገደማ በአገሪቱ ላይ 5 አገራዊ ምርጫዎች ተካሂደዋል - ከአንዱ ምርጫ በስተቀር የተቀሩት በአብላጫዎቹ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቅቡልነት ያላገኙ መሆናቸው ከተደጋጋሚ ንግግራቸውና እሳቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡በዚህም ረገድ የሚበዙት የፖለቲካ ተንታኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ከፓርቲዎቹ ጐን ነው የሚቆሙት፡፡ ባለፉት 27 ዓመታት ገዢው ፓርቲና ተፎካካሪዎች ለ4 ጊዜያት ያህል ለድርድር መቀመጣቸውን ፓርቲዎቹ ያስታውሳሉ፡፡ አብዛኞቹ ድርድሮች በቅድመ - ምርጫ እንደ ዝግጅት የተካሄዱ ነበሩ፡፡ በ2008 ተጀምሮ የተቋረጠው ድርድር ግን በሃገሪቱ አጠቃላይ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ የሚያጠነጥን ነበር፡፡ እንደምርጫው ሁሉ የፓርቲዎቹ ያለፉት ዓመታት ውይይቶችና ድርድሮችም የከሸፉ እንደነበሩ ተፎካካሪዎቹ አስረግጠው ይናገራሉ፡፡ከ20 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩትን ኦፌኮ እና ኢዴፓ የሚመሩት ፕ/ር መረራ ጉዲና እና ዶ/ር ጫኔ ከበደ እንዲሁም ከተመሰረተ አመት ያልሞላውን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ክርስቲያን ታደለ ሰሞኑን ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር በተደረገው ውይይት ላይ ከተሳተፉት መካከል ይገኙበታል፡፡ ከዚህ ቀደም ከኢህአዴግ ጋር ለበርካታ ጊዜያት ለድርድር መቀመጣቸውን የሚያስታውሱት የኦፌኮ ሊቀ መንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ውይይቶቹና ድርድሮቹ እርባና ቢስ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት 50 የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙሀንን በኮሮስፖንዳንትነት የመረጠ ሲሆን ከዚህ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በሚመለከታቸው ባለስልጣናት የሚሠጡ መግለጫዎች የቀጥታ ስርጭት ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የፕሬስ ሴክሬተሪያት ትናንት በኮሮስፖንዳንትነት ለተመረጡ መገናኛ ብዙኃን በሰጠው ማብራሪያ፤ በሃገሪቱ ያሉ መገናኛ ብዙኃንን በተለያዩ መስፈርቶች በመመዘን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ተከታታይ ዘጋቢነት መምረጡን አስታውቋል። የብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን በዋናነት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዮችን በዜና እና ወቅታዊ ሁነቶች በመዘገብ፣ በወጥነት መስራትን በመስፈርትነት መጠቀሙ የተጠቆመ ሲሆን ለህትመት መገናኛ ብዙኃን ደግሞ የጋዜጣው ስርጭት ከ5 ሺህ ኮፒ በላይ መሆኑና ከአንድ ዓመት በላይ በስርጭት መቆየቱ እንዲሁም በስርጭት ቆይታው 1 ዓመት ባይሞላው እንኳ ከ8 ሺህ ኮፒ በላይ እያሳተመ መሆኑ መስፈርት ሆኖ ተቀምጧል፡፡ በዚህ መስፈርት መሰረት ከግልና ከመንግስት ህትመቶች ስምንት የተመረጡ ሲሆን አዲስ አድማስ ጋዜጣ አንዱ ነው፡፡ በኮሮስፖንዳንትነት የተመረጡ መገናኛ ብዙኃን፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በሚሰጡ መግለጫዎች ላይ በመገኘት ጥያቄ የማቅረብ እድል ያገኛሉ፡፡ የሚሰጡ ዋና ዋና መግለጫዎችም በተለያዩ ቴሌቪዥኖች የቀጥታ ስርጭት ያገኛሉ
“ሂውማን ራይትስዎች” እና “አርቲክል 19”ኝን ጨምሮ 12 ዓለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አዲሱን የበጐ አድራጐት እና ሲቪክ ተቋማት ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ደብዳቤ ፃፉ፡፡ ተቋማቱ በሀገሪቱ የማህበራትንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ነፃነት ለማስጠበቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው፣ አዲስ የተረቀቀው አዋጅ አለማቀፍ የሠብአዊ መብት አጠባበቅ ህግጋትን ጠንቅቆ ያሟላ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡ “አዲስ የተረቀቀው አዋጅ በዋናነት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሲቪል ማህበራት ስለሚኖራቸው የፋይናንስ ምንጭ፣ ያለ ውጣ ውረድ በቀላሉ ምዝገባ ስለማያከናውኑበት ሁኔታ አብዝቶ የተጨነቀ ነው” ያሉት ተቋማቱ፤ “ለሰብአዊ መብት ተከራካሪ ቡድኖች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር አይደለም የሚል ስጋት አለን” ብለዋል፡፡ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ በተለይ የአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብት አጠባበቅ በነፃነት የመሰብሰብና ማህበር የመመስረት መብቶችን በተመለከተ የደነገጋቸውን ማሟላቱን የሚኒስትሮች ም/ቤት እንዲያረጋግጥ ተቋማቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡ “ረቂቅ ህጉ፤ ሁሉ ማህበራትና ተቋማት እንደ አዲስ ሊመዘገቡ ይገባል ማለቱም ተገቢ አይደለም” ያለው ደብዳቤው በተለይ የሰብአዊ መብት ተቋማትን እንቅስቃሴ የሚገድብ ድንጋጌ በመሆኑ ሊሻር ይገባዋል ብሏል፡፡ አዲስ
በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ የመንግሥታቸው የመጀመሪያው ግብ ምርጫውን ዲሞክራሲያዊ ማድረግ ሲሆን በምርጫው ማሸነፍ ሁለተኛ ግባቸው እንደሆነ ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡ “ዲሞክራሲንና የዲሞክራሲ ባህልን ለመገንባት የጀመርነውን ለውጥ ተቋማዊ መሠረት ማስያዝ ይገባል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የዲሞክራሲ ዋነኛው ተቋም ምርጫ ቦርድ በገለልተኛ ሰዎች መደራጀቱ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ “በመንግሥትና በህዝብ መካከል ያለው ውል በነፃ ሊመሠረት የሚችለው ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ተቋም ሲኖር ነው” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ “ዲሞክራሲን ለመገንባት ቀጣዩ ምርጫ ትልቁ ምሰሶ ነው” ብለዋል፡፡ አክለውም፤ “ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድን እንደ መጀመሪያ ግብ ወስደን፣ ማሸነፍን ሁለተኛ ግብ እናደርጋለን፣ ማሸነፍን የመጀመሪያ ግብ ካደረግን ምርጫውን ፍፁም ዲሞክራሲያዊ የማድረግ ቁርጠኝነት አይኖረንም” ብለዋል፡፡ “የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲን የተራበ ነው” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ “ሁላችንም ቀጣዩ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን በጋራ መቆም ይኖርብናል” ብለዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ ተሿሚዋን ወ/ት ብርቱካንን እጩ አድርጐ ለማቅረብም ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከፖለቲካ ምሁራን ጋር ምክክር ማድረጋቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ወ/ሪት ብርቱካን ለመንግስትም ቢሆን እጅ የማይሠጡ፣ ለፍትህ፣ ለህግ የበላይነትና ለዲሞክራሲ ዋጋ ለመክፈል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤ ከህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የክልል መንግስታት የፌደራል መንግስቱን አካሄድ መቃወማቸው መብት መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባ አስታወቁ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ከትላንት በስቲያ በፓርላማ ተገኝተው የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን ሹመት በም/ቤቱ አባላት ባፀደቁበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ሰሞኑን የፌደራል መንግስት በሙስናና የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠርጣሪዎች ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ፣ የክልል መንግስታት መቃወማቸው መብታቸው መሆኑን ጠቁመው ይሄን መብታቸውን መቃወምና አለመቀበል ስህተት መሆኑን አስረግጠው ገልፀዋል - ለውጡ የመጣው ሰዎች ያልመሰላቸውንና ያላመኑትን በግልጽ እንዲቃወሙ መሆኑን በመጠቆም፡፡ “ክልሎች ማንኛውንም የፌደራል መንግስት ውሳኔ እጃቸውን አውጥተው አጨብጭበው እንዲቀበሉ አንጠብቅም” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ “ያልመሰላቸውን የመቃወም፤ መቃወማቸውንም በሚዲያ በይፋ የመግለፅ መብት አላቸው” ብለዋል፡፡“የኛን ንግግር የሚደግም ሳይሆን ትክክል አይደለም ብሎ ሲያስብ ተቃውሞውን በይፋ መግለፅ የሚችል ክልል፣ ምክር ቤትና የምክር ቤት አባል ነው የምንፈልገው” ያሉት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ፤ “በዚህ መሃል ግን ባለን ስልጣን ልክ ህግን ማስከበር ግዴታችን ነው፤ እየተናገርን ነገር ግን ህግን የማናስከብር ከሆነ ነው ግጭት የሚፈጠረው በማለት አብራርተዋል፡፡“ባለፉት 30 ዓመታት የተፈፀሙ
መንግስታዊ ያልሆነው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም፣ “የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ” ከ10 ዓመት በፊት በመንግሥት የታገደበት 9 ሚሊዮን ብር ገደማ ገንዘብ እንዲለቀቅለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል፡፡ ላለፉት 27 አመታት በሀገሪቱ ይፈፀማሉ የሚባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመንግስት በሚደርስበት ተጽእኖ ምክንያት በውስን አቅም ሲመረምር መቆየቱን የጠቆመው ሰመጉ፤ በ2001 ዓ.ም የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ መታወጁን ተከትሎ፣ በንብ ባንክ፣ በአዋሽ ባንክ፣ በህብረት ባንክና በአቢሲኒያ ባንክ ውስጥ ተቀማጭ የነበረ በድምሩ ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ አራት ብር (8,797,184.28) በመንግስት እንደታገደበት ይገልፃል - በደብዳቤው፡፡ በወቅቱ የታገደበትን ገንዘብ ለማስለቀቅ ክስ መስርቶ እንደነበረ አስታውሶ፤ “በዳኝነት ነፃነት እጦት ምክንያት” እንዳልተሳካለት ሰመጉ ጠቁሟል፡፡ በዚህም የተነሳ ተቋሙ ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ችግር በመዳረጉ፣ በ13 ከተሞች ላይ ከነበሩት ጽ/ቤቶች አስሩን ለመዝጋት መገደዱንና ከ80 በመቶ በላይ ሠራተኞቹን ማሰናበቱን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፈው አቤቱታ ጠቁሟል፡፡ እስካሁንም በፋይናንስ እጦት ሳቢያ የተዘጉ ቢሮዎቹን መልሶ መክፈትና ሠራተኞቹን መተካት እንዳልቻለ የጠቀሰው ሰመጉ፤ አሁን
አራት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማኔጅመንት አባላት በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ባንኩ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫው አረጋግጧል፡፡ በራሳቸው ፍቃድ ከኃላፊነታቸው የለቀቁት በባንክ ዋና የብድር መኮንን አቶ አባይ መሃሪ፣ የባንኩ የሰው ሃብት መኮንን አቶ ሰይፉ ቦጋለ፤ የባንኩ ዋና የኦፕሬሽን መኮንን አቶ አታክልቲ ኪዳነማሪያም እንዲሁም የባንኩ የጠቅላላ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሠረት አስፋው መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ቀደም ብሎም የባንኩ ዋና የቢዝነስ መኮንን የነበሩት አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ በራሣቸው ፍቃድ ከስራ መልቀቃቸውን ባንኩ አስታውቋል፡፡ በራሳቸው ፍቃድ ከስራ የለቀቁት የማኔጅመንት አባላት አቶ አባይና አቶ አታክልቲ ኪዳነማሪያም እያንዳንዳቸው ከ30 አመት በላይ በባንኩ ያገለገሉ ሲሆን አቶ ሰይፈ ቦጋለና ወ/ሮ መሠረት አስፋው ደግሞ ለ18 አመት መስራታቸው በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡ የማኔጅመንት አባላቱ ለምን በፍቃዳቸው ከስራ እንደለቀቁ ያለው ነገር የለም፡፡ አባላቱ የለቀቁበትን ምክንያት ራሳቸው ተጠይቀው ቢገልፁ የተሻለ መሆኑን የባንኩ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ በልሁ ታከለ አስረድተዋል። የመልቀቂያ ጥያቄያቸውን ያስገቡትም ሁሉም በተለያየ ቀን መሆኑን አቶ በልሁ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቀይ ባህርና በህንድ ውቅያኖስ መካከል የባህር ኃይል ጦር ሰፈር ልትገነባ መሆኑን የመከላከያ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ፡፡ የባህር ኃይል ጦር ሰፈሩ የሚገነባው ከቀይ ባህር ዳርቻ ወደ ውስጥ 60 ኪ/ሜትር ገብቶ በውሃው አካል ላይ ይሆናል ተብሏል፡፡ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ፑንትላንድና ኤርትራን ጨምሮ በርካታ አገሮች የባህር ኃይል ጦር ሰፈር ለመገንባት መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት ጀነራሉ፤ “ኢትዮጵያ የባህር በር ባይኖራትም የግዴታ የባህር ኃይል ጦር ያስፈልጋታል፤ ይህን እውን ለማድረግም እየተንቀሳቀስን ነው” ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ እስካሁን የቀይ ባህርን ለሸቀጥ ማጓጓዣ ብቻ ስትጠቀምበት ነው የኖረችው ያሉት ጀነራሉ፤ ይህ ሁኔታ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ይቀየራል፤ በቀይ ባህር ላይ የራሷ የባህር ኃይል ይኖራታል ብለዋል፡፡ በቀይ ባህር ላይ የባህር ኃይል መገንባቱ ሃገሪቱ በአካባቢው ላይ ያላትን ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅና ራሷን ከሚቃጡባት የውጭ ጥቃቶች ለመከላከል በእጅጉ አጋዥ መሆኑንም ጀነራሉ ገልፀዋል፡፡ አሁን የሚገነባው የባህር ኃይል ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሙሉ ለሙሉ ያሟላ፣ በእጅጉ የዘመነና የ100 ሚሊዮን ህዝብ ኃያል ሃገር መሆኗን የሚያሳይ ይሆናል ተብሏል፡፡
የኤርትራው ፕሬዚዳንት በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃልየተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት ላለፉት ዘጠኝ አመታት በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ባለፈው ረቡዕ ማንሳቱን ተከትሎ፣ ኤርትራውያን ደስታቸውን በአደባባይ የገለፁ ሲሆን የሃገሪቱ መንግስት “የትዕግስታችንን ውጤት በመጨረሻ አግኝተናል” ብሏል፡፡ በአለማቀፍ ደረጃ አሸባሪ ከተሠኘው አልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለትና በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰውን አልሻባብን ትደግፋለች፤ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን ለማተራመስ እየሠራች ነው በሚል ከዘጠኝ አመት በፊት በኤርትራ ላይ የጦር መሣሪያ ግዥና የባለስልጣናት ጉዞ ላይ ማዕቀብ ተጥሎባት እንደነበር ይታወቃል፡፡ ለ20 አመታት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የዘለቀው ጦርነትና ግጭት በቅርቡ መፈታቱን ተከትሎም በኤርትራ ላይ ተጥሎ የቆየው ማዕቀብ እንዲነሣ የኢትዮጵያ መንግስት የፀጥታው ም/ቤት አባል ሀገራትን ሲያግባባ ቆይቷል፡፡ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በቀጥታ ለፈረንሳይ፣ ለጀርመንና ለእንግሊዝ መንግስታት ማዕቀቡ እንዲነሣ እገዛ ያደርጉ ዘንድ መጠየቃቸውም ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎ ባለፈው ረቡዕ ህዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም ኒውዮርክ ላይ የተሠበሰበው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት በሙሉ ድምጽ ማዕቀቡ እንዲነሳ ወስኗል፡፡ የማዕቀቡን መነሣት ይፋ ከተደረገ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት
ህዝቡ ከመንግሥት ጋር እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል በሰብአዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦችና የመንግስት ባለስልጣናት ላይ መንግስት ከሰሞኑ መውሰድ የጀመረውን እርምጃ እንደሚደግፉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገለፁ፡፡ ባለፉት አመታት የመንግስትና የህዝብ ሃብትና ንብረት ላይ የተደራጀ ዘረፋ የፈፀሙ እንዲሁም በዜጎች ላይ ሰቅጣጭ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙና ከህግ ውጪ የተንቀሳቀሱ አካላት ላይ መንግስት እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ያደነቀው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ተጠርጥረው የተያዙ ግለሰቦች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ አሳስቧል፡፡ “አቃቤ ህግ የወሰደው እርምጃ በእጅጉ የሚደገፍ ነው” ያለው ፓርቲው፤ ከዚህ ቀደም በአባላቱና በሌሎች መብታቸውን በሚጠይቁ ዜጎች ላይ ይደርሱ የነበሩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ በርካታ መግለጫዎችን በማውጣት ሲያስገነዝብ ቢቆይም ሰሚ ሳያገኝ መቅረቱን አስታውሷል ሰማያዊ ፓርቲ፡፡ ዛሬ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ህግ ፊት መቅረባቸውን ያደነቀው ፓርቲው፤ ምንም እንኳ የዘገየ ፍትህ ቢሆንም የጠቅላይ አቃቤ ህግ እርምጃ የሚደገፍና የሚበረታታ ነው ብሏል፡፡ ሰብአዊ መብት ጥሰት በፈፀሙ ሰዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ለቀሪዎቹም አስተማሪ እንደሚሆን የጠቆመው ፓርቲው፤ ከሜቴክ ጋር ተያይዞ የተፈጠረው “መንግስታዊ ሌብነት” ጊዜውን ጠብቆ መጋለጡ የሚደነቅ ነው
“ኢትዮጵያ ወንጀለኞች በኩራት የሚኖሩባት አገር መሆን የለባትም” በከፍተኛ የሙስና እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 70 የደረሰ ሲሆን፤ ፖሊስ አሁንም ቀሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የተጠርጣሪዎችና የተጠርጣሪ ቤተሰቦችን ጨምሮ የ206 ግለሰቦች የባንክ ሂሣብ መታገዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡በቁጥጥር ስር የዋሉት የሜቴክ ከፍተኛ አመራሮችና የደህንነትና የፖሊስ ሃላፊዎች ከማክሠኞ ህዳር 4 ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ በተከታታይ ፍ/ቤት ቀርበው፣ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የጠየቀባቸው ሲሆን፤ አቃቤ ህግ የተጠርጣሪዎችን ንብረትና የባንክ ሂሣብ በማሳገድ ሥራ ተጠምዶ ሰንብቷል፡፡ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባለፉት 6 ወራት ከሙስናና የሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ በስኳር ኮርፖሬሽን፣ በብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ)፣ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሣ) እንዲሁም በደህንነትና የፀጥታ ተቋማት፤ ማረሚያ ቤቶች ላይ ምርመራ ሲያካሂድ እንደቆየ ተጠቁሟል፡፡ እስከ ትናንት ድረስ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የቀድሞ የሜቴክ ከፍተኛ አመራሮች፣ የደህንነትና የፀጥታ ተቋማት ሃላፊዎችና ባልደረቦች በተጨማሪ በቀጣይ የስኳር ኮርፖሬሽንና የኢንሣ የቀድሞ የስራ ኃላፊዎችን ለህግ የማቅረብ ስራ እንደሚከናወን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ከሜቴክ
· አየር መንገድ ለማዕከሉ ህንፃ ሊገነባ ነው· ፓይለቶች 10ሚ. ብር ለመለገስ ቃል ገብተዋል መቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የከተማ አስተዳደሩ በ10ሩም ክፍለ ከተሞች ሊሰጥ ቃል በገባው ቦታ ላይ ተጨማሪ ማዕከላትን ለመገንባት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ፤ አንድ ህንፃ በነፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል ገብቷል፡፡ በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማዕከሉ በ10ሩም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ቦታ ለመስጠት ቃል መግባቱን ያስታወሱት የማዕከሉ መስራችና ስራ አሥኪያጅ አቶ ቢኒያም በለጠ፤ ሊሰጥ የታሰበው ቦታ ፕሮጀክቱን የበለጠ ለማስፋፋት ወሳኝ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በአሁን ወቅት በማዕከሉ 2 ሺህ ያህል ዜጎች ድጋፍ እየተደረገላቸው ሲሆን በአጭር ጊዜያት ውስጥ የማዕከሉን አጠቃላይ የመቀበል አቅም 10 ሺህ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ለዚህ ፕሮጀክት ተግባራዊነት ህብረተሰቡና የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚያደርጉት ድጋፍ ቀጣይነት ወሳኝ መሆኑን አቶ ቢኒያም ጠቁመው፤ ህብረተሰቡ አሁንም ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማዕከሉ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ ሰርግ፣ ተዝካርና ልደት ደጋሾች በማዕከሉ እየመጡ ከማዕከሉ ነዋሪዎች ጋር ቆይታ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል፡፡ ጠቅላይ
ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሁንም አስተማማኝ ባለመሆኑ በግጭት ለተፈናቀሉ ከ57 ሺህ በላይ ዜጐች አስፈላጊውን ዕለታዊ እርዳታ ለማድረስ መቸገራቸውን ዓለማቀፉ የረድኤት ድርጅቶች ገልፀዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሠብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው፣ በቅርቡ ተፈጥሮ በነበረው ብሔር ተኮር ግጭት ተፈናቅለው ኦዳ አካባቢ ለሚገኙ 15 ሺህ ያህል እንዲሁም ካማሺ ዞን ውስጥ ለሚገኙ 42 ሺህ ያህል በድምሩ ለ57 ሺህ ያህል ተፈናቃዮች የእለት ደራሽ እርዳታ ለማቅረብ በአካባቢው ግጭት ባለመቆሙና የፀጥታው ሁኔታ አስተማማኝ ባለመሆኑ የተነሣ መቸገሩን ጠቁሟል፡፡ ዜጐቹ ከተፈናቀሉ 2 ወር ያህል ቢሆናቸውም እስካሁን እርዳታ የቀረበላቸው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ያለው ጽ/ቤቱ፤ አሁንም መንግስት የራሱን መዋቅር ተጠቅሞ በወታደራዊ ከለላ ነው ያቀረበው ብሏል። በሁለቱ አካባቢዎች የሚገኙ ከ57ሺህ በላይ የሚሆኑት ተፈናቃዮች አሁን ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዳልተቻለ የገለፀው ጽ/ቤቱ፤ መንግስት ለሁኔታው ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡ በወቅቱ ተፈጥሮ በነበረው ብሔር ተኮር ግጭት በአጠቃላይ ከተፈናቀሉ 240 ሺህ ዜጐች ውስጥ 182 ሺህ ያህሉ በኦሮሚያ በምስራቅና ምዕራብ ወለጋ መጠለላቸውንና
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ውስጥ “ራሳችንን ችለን ክልል እንሁን” የሚሉ ጥያቄዎች እየተበራከቱ መምጣታቸው ታውቋል፡፡ በ13 ዞኖች በ8 ልዩ ወረዳዎችና በ22 የከተማ አስተዳደሮች የተደራጀውና 56 ብሔር ብሔረሰቦችን በያዘው በዚህ ክልል ውስጥ እስካሁን የሲዳማ፣ የወላይታና የከፋ ክልል የመሆን ጥያቄዎችና የውሳኔ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡ የከንባታ ጠንባሮ ዞንም “የክልል ጥያቄ” ማቅረቡን የጠቆሙ ምንጮች፤ በሌላ በኩል በዚሁ በከንባታ ጠንባሮ ዞን ውስጥ “ጠንባሮ ለብቻው ዞን ይሁን” የሚል ጥያቄም መቅረቡን አመልክተዋል፡፡ የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ በሲዳማ ዞን ም/ቤት በሙሉ ድምፅ ከፀደቀ በኋላ ለክልሉ ም/ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ማግኘቱ የታወቀ ሲሆን ከሰሞኑ የወላይታ “ክልል እንሁን” ጥያቄም በወላይታ ዞን ም/ቤት ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ የከፋ ዞን ም/ቤትም “ከፋ ራሱን ችሎ ክልል መሆን አለበት” የሚለውን የውሳኔ ሃሳብ ከትናንት በስቲያ ሐሙስ አፅድቋል፡፡ የከንባታ ጠንባሮ ዞን ም/ቤትም በዞኑ “ክልል ልሁን” ጥያቄ ላይ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቦ ለመወያየት ማቀዱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በቅርቡ በክልሉ የዞን፣ የልዩ ወረዳና የወረዳ አወቃቀር ላይ የህዝቡን ጥያቄ በሚመልስ መልኩ ተዘጋጅቷል የተባለው ጥናት፤ ለክልሉ ም/ቤት
ከሰባት ዓመታት የአሜሪካ የስደት ህይወት በኋላ ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ወደ አገራቸው የተመለሱት የህግ ባለሙያዋና ፖለቲከኛዋ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፤ የተጀመረውን አገራዊ ለውጥ ለማስቀጠል ሁሉም የድርሻውን ማበርከት እንዳለበት ጠቁመው፤ በዲሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ላይ ለመሥራት እንደሚሹ ተናግረዋል፡፡ ለሁለት ጊዜያት ያህል በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ለእስር የተዳረጉት ወ/ት ብርቱካን፤ በስደት ከሚኖሩበት አሜሪካን ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት በሃገሪቱ የተጀመረው ፖለቲካዊ ለውጥ አነሳስቷቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ “በተለያየ ደረጃ በሙያዬ በህግ እውቀት ወገኖቼን ለማገልገል ሙከራ ሣደርግ ነበር” ያሉት ወ/ት ብርቱካን፤ “አሁን በሃገሪቷ የመጣው ለውጥና ሃገሪቷ ባለችበት ሁኔታ ይህን ፍላጐቴን ለማሳካት እድሎች እንዳሉ ስለተመለከትኩኝ፣ የአቅሜን በሙያዬ፣ በልምዴ፣ በእውቀቴ ለማድረግና ለማዋጣት ነው የመጣሁት” ብለዋል፡፡ “እኔ ማተኮር የምፈልገው በዲሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ላይ ነው” ያሉት ወ/ት ብርቱካን፤ “የትኛው ተቋም ላይ እንደምሳተፍ በቀጣይ የምወስነው ይሆናል” ብለዋል፡፡ “በአሜሪካን ሃገር ከጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በተገናኘንበት ወቅት ለለውጥ ተነሣሽነት ያላቸው መሆኑን ተረድቻለሁ፤ ለዚህም ነው ወደ ሀገር ቤት ተመልሼ፣ በዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ላይ ለመሳተፍ የወሰንኩት” ይላሉ፡፡ የህግ ባለሙያዋ፣
የ200 ሰዎች የጅምላ መቃብር በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል አዋሣኝ አካባቢ መገኘቱን የገለፀው የፌደራል ፖሊስ፤ በጅምላ ተቀብረው የተገኙትን አስከሬኖቹ ማንነት ለመለየት እያደረገ ምርመራ እያደረገ መሆኑም አስታውቋል፡፡ ፖሊስ የጅምላ መቃብሩን ያገኘው በአሁን ወቅት በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሐመድ ኡመር ላይ ተጨማሪ ምርመራዎች በሚያከናወንበት ወቅት መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በሰዎች ግድያና ኢ-ሠብአዊ ድርጊቶች በመፈፀም ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አብዲ መሐመድ፤ በሥልጣን ላይ በቆዩባቸው ላለፉት 13 አመታት በክልሉ በርካታ ኢ-ሠብአዊ ተግባራት በዜጐች ላይ መፈፀማቸውን ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት በተለያዩ ጊዜያት ባወጧቸው ሪፖርቶች መጠቆማቸው ይታወሳል፡፡ አሁን ፖሊስ አግኝቸዋለሁ ያለው የጅምላ መቃብር አቶ አብዲና አስተዳደራቸው ከሚወቀሱባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር ስለመያያዙ ተጣርቶ ውጤቱ ለፍ/ቤት እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡ በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈርና ዜጐችን በተለያየ ዘዴ ማሰቃየትና ቶርች መፈፀም ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየተጣራ የሚገኘው የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት፤ ከትናንት በስቲያ ፍ/ቤት ቀርበው ተጨማሪ የአሥራ አራት ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
“መንግሥት ይጠቀምብን፤ ሃገራችንን ማገልገል እንፈልጋለን” የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት አባላት፤ ሃገር አቀፍ ማኅበር መመስረቱን አስታወቁ፡፡ ባለፈው እሁድ በርካታ የቀድሞ የጦር ሰራዊት አባላትና አመራሮች በአዲስ አበባ ተሰብስበው ስለማኅበሩ ምስረታ ምክክር አድርገዋል ተብሏል። በዚህ ማኅበር የቀድሞ ምድር ጦር፣ አየር ኃይልና ባህር ኃይል አባላት መካተታቸውን የጠቆሙት የማኅበሩ ምስረታ አስተባባሪ መቶ አለቃ ሰለሞን አደመ፤ በቀጣይ ማኅበሩ አድማሱን በማስፋት በየቦታው በተለያየ ሁኔታ ላይ የሚገኙ የጦሩን አባላት ያሰባስባል ብለዋል፡፡ ማኅበሩ በዋናነት የሰራዊቱ አባላት የጋር ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁበት፣ እርስ በእርስ የሚረዳዱበት እንዲሁም መንግስት ሙያዊ እገዛቸውን በፈለገ ወቅት ለሃገራቸው የሚያገለግሉበት እንደሚሆን መቶ አለቃ ሰለሞን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በማኅበሩ ምስረታ ላይ ተጋብዘው የተገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አዛዥ ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ በበኩላቸው፤ መንግስት የቀድሞ ሰራዊት አባላትን እውቀትና አቅም ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡
በአገሪቱ የፍትህ ነፃነትን ለማረጋገጥ እንደሚታገሉና ህዝቡ በፍትህ ስርዓቱ ላይ እምነት እንዲያድርበት እንደሚሰሩ አዲሷ የመጀመሪያዋ የጠቅላይ ፍ/ቤት ሴት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ገለፁ፡፡ ታዋቂዋ የሴቶች መብት ተሟጋችና የሰብአዊ መብት ጠበቃዋ ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ከሹመታቸው በኋላ ለቢቢሲ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ “ይህ አሁን ለእኔ የተሰጠኝ ክብርና ልዩ እድል ለአገሬ አዲስ ምዕራፍ ነው” ብለዋል፡፡ የፍትህ ነፃነት እንዲከበር ለማድረግ እተጋለሁ ያሉት አዲሷ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት፤ ለዚህ እንቅስቃሴዬም ከመንግስቴ ሙሉ ድጋፍ እንደማገኝ አምናለሁ” ብለዋል፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት በአገራችን የህግ ስርዓቱ የመንግስት የመ;; ኃይል ሆኖ ሲያገለግል መቆየቱን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቷ፤ ይህም ህዝቡ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሸር አድርጐታል ብለዋል፡፡“በተሰጠኝ ሹመት በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ሴት ልጅ መድረስ የምትችለው እዚህ ጋ ነው ተብሎ የተከለለው ድንበር ተሰብሯል” ያሉት ወ/ሮ መአዛ፤ አሁን “ሴት ልጆቼ መሆን የሚፈልጉትንና የሚመኙትን ለመሆን ይችላሉ፤ ይህ ለአገሬ አዲስ ምዕራፍ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “ዜጐች ፍትህ እንዲያገኙ አበክሬ እሰራለሁ” ያሉት የ55 ዓመቷ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት፤ “በፍ/ቤቶች ላይ የተሸረሸረው የህዝብ
መንግሥት በያዝነው ዓመት የሀገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋትና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ትኩረት አድርጎ የሚሰራባቸውን ዋና ዋና እቅዶች ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡ በሀገሪቱ ሰላምና ፀጥታን፣ ፍትህና ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሻውን ዲሞክራሲ ለማስፈን መንግስታቸው ተከታታይ መዋቅራዊና ተቋማዊ ማሻሻያዎችን በዘንድሮ ዓመት እንደሚያከናውን ጠ/ሚኒስትሩ ሰሞኑን በፍራንክፈርት ከኢትዮጵያውያን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ አብራርተዋል፡፡ ፍትህና ዲሞክራሲን ሊያሳልጡ የሚችሉ ተቋማትን በመገንባት ላይ እንገኛለን ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ በተጓዳኝም ተቋማቱን በገለልተኝነት የሚመሩ ባለሙያዎችን የመምረጥ፣ የማሰልጠንና የመመደብ ስራዎች ተጀምሯል ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድን ነፃ፣ ገለልተኛና ተአማኒ ለማድረግ የህግና የመዋቅር ማሻሻያ በመሰራት ላይ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ዐቢይ፤ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት በሰለጠነ መንገድ የዜጎችን መብትና ክብር ጠብቀው ስራቸውን እንዲሰሩ ጠንካራ ሪፎርም በመካሄድ ላይ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ መከላከያውን የማዘመንና የማጠናከር ስራ እየተሰራ መሆኑንም ጠ/ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡ የፍትህ ተቋማት በገለልተኝነት የሚሰሩና ለዜጎች መብት ብቻ የቆሙ ለማድረግ፣ ዳኞች በህግ ልዕልናና በህሊናቸው ብቻ የሚዳኙ እንዲሆኑ ማድረግም የዚህ ዓመት ዋነኛ ትኩረት ነው ብለዋል። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ በፍትህ ዘርፉ ላይ ተከታታይ የሪፎርም እርምጃዎች
የፖለቲካ ፕሮግራሙንና ህገ ደንቡን እንደሚያሻሽል ጠቁሟል በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተጀመሩ የፖለቲካ ለውጦች አበረታች መሆናቸውን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች ማብራራቱን የገለጸው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ከለውጡ ጋር አብሮ ለመጓዝ የፖለቲካ ፕሮግራሙንና ህገ ደንቡን እንደሚያሻሽል ጠቁሟል፡፡ ዶ/ር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በሀገሪቱ አያሌ አበረታች የፖለቲካ ለውጦች መካሄዳቸውን ያብራራው ፓርቲው፤ በተለይ የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸው፣ ትጥቅ አንስተው ሲታገሉ የነበሩ ተቃዋሚ ኃይሎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸው፣ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘንድ አንድነትና ህብረት መፈጠሩ እንዲሁም ለ20 ዓመታት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የዘለቀው ግጭት ተወግዶ፣ እርቅ መፈፀሙ፣ ትልቁ የለውጡ ስኬት መሆኑን ለዲፕሎማቶቹ አስረድቷል፡፡ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዛወር መወሰኑ፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲታረቁ መደረጉ፣ ሴቶች ወደ ከፍተኛ ስልጣን መምጣታቸው እንዲሁም የፀረ ሽብር ህጉን ጨምሮ አፋኝ ህጎችን ለማሻሻል ሥራ መጀመሩም የለውጡ ትሩፋት መሆኑን ፓርቲው አብራርቷል፡፡ የዶ/ር ዐቢይ አመራር በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ የሀገሪቱን የለውጥ ጉዞ እየመራ እንደሚገኝ የገለፀው ፓርቲው፤
ከ250 በላይ የተሽከርካሪዎች ፍሰት ተገትቷል የትግራይ ክልልን ከአማራ ክልል የሚያገናኘው የአላማጣ ቆቦ መንገድ ተዘግቶ በመሰንበቱ የትራንስፖርት ፍሰት የተገታ ሲሆን ተሽከርካሪዎች መጉላላታቸው ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡ መንገዱ ካለፈው ሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2011 ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ ያልተከፈተ ሲሆን ከትግራይ ክልል ወደ አማራ ክልል ለመግባት የተንቀሳቀሱ ከ250 በላይ የህዝብና የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ቆመው መሰንበታቸው ታውቋል፡፡ መንገዱ በዋናነት ከቆቦ ከተማ ወጣ ብሎ ሰቀላ ወንዝ አካባቢ የሚገኝ ነው ያሉት ምንጮች፤ የመዘጋቱ ምክንያትም በአካባቢው ከተከሰተው ተቃውሞና ግጭት ጋር ተያይዞ የሰው ህይወት በመጥፋቱ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ “የትግራይ ልዩ ሃይል ሊያጠቃን ይችላል” በሚል ስጋት ነው መንገዱ የተዘጋው ብለዋል - ምንጮች፡፡ መንገዱን ለማስከፈት ከአካባቢው ወጣቶችና ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ትናንት ለቢቢሲ የገለፀ ሲሆን፤ ከውይይቱ በኋላ መንገዱ በአፋጣኝ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
የዓለም ባንክ ከፍተኛ የሚባለውን የ1.2 ቢሊዮን ዶላር ብድርና እርዳታ ለኢትዮጵያ የፈቀደ ሲሆን ገንዘቡ በሀገሪቱ በተጀመረው ለውጥ ውስጥ የኢኮኖሚ እድገቱን ለማፋጠን በቀጥታ የሚውል ነው ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚገኝ መገንዘቡን የገለፀው የአለም ባንክ፣ ከኤርትራ ጋር ሰላም መፍጠሩን፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት አበረታች እርምጃዎች መውሰዱንና በአካባቢው ሰላምን መሰረት ያደረገ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ተግባር በማከናወን ላይ መሆኑን እንዲሁም በመንግስት ተይዘው የነበሩ የልማት ተቋማትን ወደ ግል ዘርፍ ለማዛወር እንቅስቃሴ መጀመሩን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከፍተኛውን ብድርና እርዳታ ለኢትዮጵያ ለመስጠት መወሰኑን አስታውቋል፡፡ በብድርና እርዳታ መልክ የሚሰጠው ገንዘብ በዋናነት ሶስት ጉዳዮችን ለማስፈፀም እንደሚያግዝ የጠቆሙት የአለም ባንክ የፕሮጀክት ቡድን መሪዋ ናታሊያ ሚዮሌንኮ፤ ገንዘቡ በዋናነት ለልማት የሚመደበውን በጀት ለመደጎም፣ የኢንቨስትመንት ግንኙነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት በቀጥታ ይውላል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠትና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍም እርዳታና ብድሩ ያግዛል ተብሏል፡፡ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከፈቀደው 1.2 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ግማሹ (600 ሚሊዮን ዶላር ያህሉ) በእርዳታ የሚሰጥ መሆኑም
ሃይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ) የታክሲ አገልግሎት ድርጅት፤ ሕጋዊና ዓለምአቀፍ የጥራት ደረጃ ያለው አገልግሎት እየሰጠሁ ቢሆንም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሕገ-ወጥ ናችሁ በሚል በደል እያደረሰብኝ ነው ሲል አማረረ፡፡ ድርጅቱ ትናንት በሸራተን አዲስ ሆቴል ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፤ “የትራንስፖርት መጥሪያ ቴክኖሎጂ አገልግሎት ለመስጠት ሕጋዊ ፈቃድ ያለን ብንሆንም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አብረውን ለኅብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን ከ900 በላይ ኮድ 3 የኪራይ መኪኖች ሕገ-ወጥ ናችሁ እያለ በሞተር እያሳደደ፣ በብጣሽ ወረቀት እየከሰሰና መኪኖችን እያሰረ ነው” ብሏል። “ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ግብር እየከፈሉ በግልጽ አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን ኮድ 3 የኪራይ መኪኖች ሕገ -ወጥ ናቸው በማለት ለ10ሩም ክፍለ ከተሞች ደብዳቤ መጻፉና በሚዲያ ማስነገሩ ትክክል አይደለም” ያለው ድርጅቱ፤ “በዚህ አገልግሎት አሰጣጥ ክልከላ ላይ ጥቅማቸው የተነካ ቡድኖች ከጀርባው ያሉ ይመስለናል” ብሏል፡፡ “እኛ ሕጋዊ ፈቃድ ያለን በቴክኖሎጂ አገልግሎት በመስጠት በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል፣ ኮድ 3 መኪኖች ካላቸው ወጣቶች ጋር እየሠራን ነው” ያለችው የሃይብሪድ ዲዛይንስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሳምራዊት ፍቅሩ፤
“ሰላምና ኢትዮጵያ አንድና ያው እስኪኾኑ መሥራት ይገባናል”ከትናንት በስቲያ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው በለቀቁት የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ምትክ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያዋ የአገሪቱ ሴት ርዕሰ ብሔር ሆነው ተሾመዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዚዳንት በመሾም በምስራቅ አፍሪካ ፈር ቀዳጅ ያደርጋታል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ተወልደው ያደጉት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሊሴ ገብረማሪያም የተከታተሉ ሲሆን፤ በ17 ዓመት ዕድሜያቸው ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝተው ወደ ፈረንሳይ በማቅናት፣ በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሞንቸፔለየር፣ በተፈጥሮ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ በአገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአምባሳደርነት ከተሾሙት ዮዲት እምሩ ቀጥሎ የአምባሳደርነት ሹመት ያገኙት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመደቡትም በሴኔጋል ሲሆን፤ የአምባሳደርነት ስልጣናቸው ማሊን፣ ኬፕቨርዲን፣ ጊኒቢሳዎን፣ ጋምቢያንና ጊኒን የሚያቃጠልል ነበር፡፡ ከዚያም በጅቡቲ፣ ቱኒዚያ፣ ሞሮኮና ፈንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከአምባሳደርነታቸው በተጨማሪም በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ፣ በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ተወካይ፣ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ተወካይ፣ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር፣ በተባበሩት መንግስታት
የሶማሌ ህዝብ ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር በሰላም ለመኖር የሚፈልግ ህዝብ በመሆኑ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ጉዳይ የማይታሰብ ነው ሲሉ አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር አስገነዘቡ፡፡ “ሰሞኑን ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ጋር በአስመራ በተፈፀመ ስምምነት የሶማሌ ህዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብቱን ተጠቅሞ፣ ህዝበ ውሳኔ እንዲያደርግ ከስምምነት ላይ ተደርሷል” በሚል በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የቀረበው ዘገባ ሃሰተኛ መረጃ መሆኑን የገለጹት አቶ ሙስጠፋ፤ “በስምምነቱ ወቅት ስለ ህዝበ ውሳኔም ሆነ ስለ መገንጠል ጉዳይ ለውይይት አልቀረበም፤ ስምምነትም አልተፈረመበትም” ብለዋል፡፡ አስመራ ላይ በተደረገው ስምምነት ኦብነግ እንደ ሌሎቹ ትጥቅ ይዘው ሲንቀሳቀሱ እንደነበሩ ተቃዋሚዎች የትጥቅ ትግሉን አቁሞ በሰላማዊ መንገድ፣ በሃገር ውስጥ ገብቶ እንዲንቀሳቀስ ነው የተስማማው ያሉት የክልሉ ፕሬዚዳንት፤የህዝበ ውሳኔና የመገንጠል ጉዳይ ፈፅሞ አለመነሳቱን አስታውቀዋል፡፡ በምስራቅ ኢትዮጵያ በኩል ያለው ሉአላዊነት የሚጠበቀው በሶማሌ ህዝብ ፍቃድና ፍላጎት ብቻ መሆኑን ያስገነዘቡት ፕሬዚዳንቱ፤ በቅርቡ በጅግጅጋ ተፈጥሮ የነበረውን ግጭትና ግድያ ከቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ መሃመድ ጀርባ ሆነው ያነሳሱ ኮንትሮባንዲስቶች አሁንም አካባቢውን ለመረበሽ ፍላጎት እንዳላቸው
“በመብት ጠያቂዎች ላይ የሚፈፀም ግድያ አለመቆሙ አሳሳቢ ነው”በራያ እና በወልቃይት ለዜጎች ሞትና እንግልት ምክንያት የሆኑ የማንነት ጥያቄዎች በፌደራል መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው የጠየቀው ሰማያዊ ፓርቲ፤ መብታቸውን በተለያየ አግባብ በሚጠይቁ ዜጎች ላይ የሚፈፀመው ግድያ አሁንም አለመቆሙ አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡ ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው፤ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች የአስተዳደርና የማንነት ጥያቄ በሚያነሱበት ወቅት በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የሚወሰደው የኃይል እርምጃ የዜጎችን ሰብአዊ መብት የሚጥስ በመሆኑ ከእንግዲህ መደገም እንደሌለበት አሳስቧል፡፡ በየአካባቢው ለሚነሱ የአስተዳደርና የማንነት ጥያቄዎች፣ በምክክርና በውይይት፣ የህዝብን ፍላጎት መሰረት አድርጎ፣ በመንግስት በኩል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥም ጠይቋል - ፓርቲው፡፡ጥያቄ አንግበው አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ የሰጡና ነፍስ ያጠፉ የፀጥታ ኃይሎች በህግ እንዲጠየቁና ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች ተገቢው ካሣ በአስቸኳይ እንዲሰጣቸው የጠየቀው ሰማያዊ ፓርቲ፤ “በሀገሪቱ እየተደረገ ያለውን ለውጥ የምደግፈው በየትኛውም መልኩ ዜጎችን በእኩልነት የሚያይና ሰብአዊ መብቶችን የሚያከብር ስርአት እስከሰፈነ ድረስ ብቻ ነው” ብሏል፡፡ “የትኛውንም የህዝብ ጥያቄ በኃይል ማፈን አይቻልም” ያለው
የፌደራል መንግስት ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ጉዳት እያጋጠማቸው ላሉት የጣና ኃይቅና የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ትኩረት እንዲሰጥ እንዲሁም የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ዜጎች ላይ የሚደርስ የኃይል እርምጃ እንዲቆም የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር፣ በደብረ ታቦር፣ በባህር ዳር፣ በወልዲያና በሌሎች የአማራ ከተሞች ይካሄዳል ተብሏል፡፡ የጎንደሩ ሰላማዊ ሰልፍ “በአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር” አስተባባሪነት እንደሚካሄድ የማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት ይሁኔ ዳኛው ለአዲስ አድማስ የገለፀ ሲሆን ሰልፉን አስመልክቶም ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ቤትና ከፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ምክክር ተደርጎ፣ እውቅና መገኘቱን ጠቁሟል፡፡ በእንቦጭ አረም የተወረረው የጣና ኃይቅ አስቸኳይ እልባት እንዲያገኝ፣ በላዩ ላይ በተሰራው መጠለያ ምክንያት አደጋ የተጋረጠበት የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በአስቸኳይ ይጠገን ዘንድ የፌደራል መንግስት ትኩረት እንዲሰጠው በሰላማዊ ሰልፉ እንጠይቃለን ያለው ወጣት ይሁኔ፤ በራያ፣ በወልቃይትና በሌሎች አካባቢዎች የአማራ ማንነት ጥያቄን ያነሱ ዜጎች ምላሽ እንዲሰጣቸውም የምንጠይቅበት ይሆናል ብሏል፡፡ ሰላማዊ ሰልፉን ፍፁም ሰላማዊ ለማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉንም አስታውቋል፡፡ ደብረ ታቦር የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ከሚያስተባብሩ ወጣቶች አንዱ የሆነው ወጣት
• ሁለንተናዊ ለውጥ ያመጣል የተባለ መሪ ዕቅድ እንዲተገበር ተወስኗል• ኅብረቱ በትግበራው ለመሳተፍና እስከ ግንቦት ለውጡ እንዲታይ ጠይቋል ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመዋቅርና የአሠራር ችግሮች ኹነኛ መፍትሔ በመስጠት ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘውና በአምባሳደር ካሳ ከበደ የሚመራው የአእላፋት ድምፅ የካህናትና ምእመናን ኅብረት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፊት ቀርቦ የአስተዳደር ለውጥ አቋሙን አስረዳ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱም በጥያቄዎቹ ላይ መክሮ ምላሽ እንደሚሰጥ ለኅብረቱ ተወካዮች አስታውቋል፡፡ የብዙ ሺሕ ካህናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ መንፈሳውያን ማኅበራት፣ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ምእመናን ተወካዮች የኾኑና በአምባሳደር ካሳ ከበደ የሚመሩ 9 የኅብረቱ ልኡካን፣ ትናንት፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በመሪ ዕቅድ በመመራትና የምእመናንን ከፍተኛ ተሳትፎ በማረጋገጥ ማምጣት ስላለባት አስተዳደራዊ ለውጥ ያላቸውን አቋም በመካሔድ ላይ በሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ማስረዳታቸውን ምክትል ሰብሳቢው አርክቴክት ዮሐንስ መኰንን ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡ “ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ለውጥ የካህናትንና የምእመናንን አቤቱታ ስለማቅረብ” በሚል ርእስ በንባብ በተሰማው ጽሑፍ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ችግሮች በጥናት የተደገፈ አስቸኳይ እርምት አለመስጠት፣ ተግባራዊ እንዲኾኑ
· በወንጀል የተጠረጠሩ ባለሥልጣናት በመጪው ሣምንት ይፋ ይሆናሉ · ህግን ማስከበር፤ ጡንቻን ከማሳየት ጋር አንድ አድርጎ ማየት ተገቢ አይገለም · የታጠቀና የተቆጣ ወታደርን ስሜት አብርዶ መመለስ ትልቅ ፈተና ነበር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከትናንት በስቲያ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው የምክር ቤቱ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ላይ ተመስርቶ ከምክር ቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ የሰጡት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤የምክር ቤቱ አባላት የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ለማስቀጠል ከፍተኛ ስራ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ አሁን አገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ከፍተኛ ጥንቃቄና እርጋታን የሚፈልግና የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ ወቅት መሆኑን ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ የሥርዓት አልበኝነት ዳፋ በተለያዩ አካባቢዎች ሁከት በመቀስቀስ የዘር ማጥፋት በፈፀሙ ወንጀለኞች ላይ የተወሰደ አስተማሪ እርምጃ ካለ እንዲገለፅና ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ ላይ ቦንብ በማፈንዳት በሰዎች ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙ ወንጀለኞች ጉዳይ ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ ማድረግ ያልተቻለበት
“አዲስ አበባ በልጆቿ መመራት አለባት” በሚል በአሁኑ የከተማዋ አመራር ላይ አሲረዋል ተብለው የታሰሩት የህግ ጠበቃና የሰብአዊ መብት ተከራካሪው አቶ ሄኖክ አክሊሉ፤ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲለቀቁ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ፡፡ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ እና ሌላው ታሳሪ አቶ ሚካኤል መላኩ መታሰር፤ አሁንም በሀገሪቱ መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች ተሟልተው እየተከበሩ እንዳልሆነ ጉልህ ማሳያ ነው ብሏል የሰብአዊ መብት ተቋሙ፡፡ “እስሩ መንግስት የጀመረውን የፖለቲካ ምህዳር ማስፋት እንቅስቃሴን በእጅጉ የሚጎዳ ነው” ያለው አምነስቲ፤ “ፖሊስ የመብት ተሟጋቾችን ከማሰር ይልቅ መብታቸውን ሙሉ ለሙሉ የሚጠቀሙበትን አስቻይ ሁኔታ መፍጠር ይገባዋል” ብሏል፡፡ በሀገሪቱ ሃሳብን የመግለፅና የመደራጀት መብት ተሟልቶ እንዲከበር መንግስት ያለውን ቀናኢነት ሁለቱን ግለሰቦች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር በመፍታት ማሳየት አለበት ብሏል - አምነስቲ ኢንተርናሽናል፡፡ ለበርካታ የሽብር ተከሳሾች በነፃ ጭምር ጥብቅና በመቆም የሚታወቁት የህግ ባለሙያና ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ፤ “አዲስ አበባ በልጆቿ ብቻ ነው መመራት ያለባት” ሲሉ አሲረዋል በሚል ተጠርጥረው መታሰራቸውን ፖሊስ ለፍ/ቤት አስታውቋል፡፡ ረቡዕ እለት በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት ተጠርጣሪው፤ ሐሙስ ፍ/ቤት
የካቢኔያቸውን እኩሌታ በሴቶች በማዋቀር፣ በሴቶች የለውጥ ኃይልነት እምነት ያሳደሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ የፆታ እኩልነትን በሚያረጋግጠው አዲስ የሴቶች ሹመታቸው አለማቀፍ ተቋማት አድናቆት የተቸራቸው ሲሆን ብዙዎቹ የዓለም መገናኛ ብዙኃንም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው ዘግበውታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሴቶችን ለከፍተኛው የፖለቲካ ስልጣን በማብቃት ረገድ ከአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ቀዳሚነቱን በመያዝ ፈርቀዳጅነታቸውን አስመስክረዋል ተብሏል፡፡ የመከላከያ ሚኒስትር እና በስሩ የደህንነትና የፀጥታ ኃይሎችን የያዘውን የሰላም ሚኒስትር በሴቶች እንዲመሩ ማድረጋቸውን በአድናቆት የዘገበው አሶሴትድ ፕሬስ፤ ይህም መሰረታዊ ለውጥ በማምጣት፣ ሀገሪቱን በአፍሪካ ጠቃሚና ስትራቴጂያዊ ሃገር ለማድረግ ያግዛታል ብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህን መሰረታዊ ለውጦች በራሳቸው ቀና አድርጓቸዋል ፖለቲካዊ ውሳኔ ማምጣታቸውን ዘገባው ጠቁሞ ይህ የለውጥ እርምጃቸውና አቅጣጫቸው በአመራር ዘመናቸው ተወዳጅነትና ታዋቂነትን ካተረፉት የደቡብ አፍሪካው ኔልሰን ማንዴላ፣ የአሜሪካው ባራክ ኦባማ እና የሩሲያው ሚኻኤል ጎርቫቾቭ ጋር እንዲመሳሰሉና እንዲነፃፀሩ አድርጓቸዋል ብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሴቶችን ወደ ፖለቲካ ስልጣን በማምጣት ሩዋንዳ እና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ ሩዋንዳ ከፓርላማ አባሏ ከ60 በመቶ በላይ ሴቶች ሲሆኑ ኢትዮጵያ ዋናው የመንግስት
ለአፍሪካ ሃገራት ነፃነትና ለአፍሪካ ህብረት ምስረታ፣ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካበረከቱት የአፍሪካ መሪዎች በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ፤ በአፍሪካ ህብረት ግቢ ውስጥ የመታሰቢያ ሃውልት ሊቆምላቸው መሆኑ ተገለጸ፡፡ በቻይና መንግስት ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ለአፍሪካ ህብረት የተበረከተው አዲስ ህንጻ በተመረቀበት ወቅት የአፍሪካ አንድነትን ከመሰረቱት አፍሪካውያን መሪዎች መካከል የጋናው መሪ የመታሰቢያ ሃውልት ቢቆምም፣ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሃውልት ግን መዘንጋቱ ብዙዎችን ማሳዘኑ የሚታወስ ሲሆን ጉዳዩ በኢትዮጵያ መንግስት ደረጃ ተነስቶ ለውይይት የቀረበበት ጊዜ የለም፡፡ ለቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የመታሰቢያ ሃውልት በሚቆምበት ሁኔታ ላይ በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ተወካይ ከሆኑት አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ ጋር ምክክር ማድረጉን የገለፀው ህብረቱ፤ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል አዎንታዊ ምላሽ መገኘቱን አስታውቋል፡፡ በህብረቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የንጉሱን ሃውልት የማቆም ስራም እስከ ቀጣዩ የፈረንጆች 2019 ዓ.ም መጀመሪያ ድረስ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡ ለቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ የሚቆመው ይህ ሃውልት፤ንጉሡ ለአፍሪካ ሃገራት ነፃነትና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ ላበረከቱት ወደር የለሽ አስተዋፅኦ፣ እውቅና ለመስጠት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት ምስረታ የጎላ
ቤተ ክርስቲያንን ከፖለቲካ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት የሚከላከል አካል በቀጣይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዕተ ጉባኤ እንዲሰየም እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱ የአማኞች ቁጥር የቀነሰበትን ምክንያት የሚመረምርና መፍትሄ የሚያስቀምጥ ራሱን የቻለ አካል እንዲቋቋም የሰሜን አሜሪካ የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን ማህበረ ካህናት ጠየቁ፡፡ ማህበረ ካህናቱ “ከተዋሃደው ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዕተ ጉባኤ ምን እንጠብቅ?” በሚል ባወጡት የአቋም መግለጫ፤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ከተዋኃዱ በኋላ የሚደረገው ምልዕተ ጉባኤ፤ ለቤተ ክርስቲያኒቱ መሰረታዊ ችግሮች መፍትሄ ሊበጅ የሚገባውን ጉዳይ አመላክተዋል፡፡ “ታላቅና ገናና ስም የነበራት ቤተ ክርስቲያናችን፤ የአማኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ፣ ተደማጭነቷ እየቀነሰ፣ ልዕልናዋ እየተደፈረ፣ ክብሯ እየተሸረሸረ መጥቷል” ያሉት ማህበረ ካህናቱ፤ “የሰው ኃይል፣ የገንዘብ አቅምና የእውቀት ችግር የሌለባት ቤተ ክርስቲያን፤ እንደ ተራ ተቋም፣ ለቁጥር በሚያዳግት ችግሮች ተተብትባ ልትቀጥል አይገባትም” ብለዋል፡፡ ይህን ለማረቅም የተዋኃደው ቅዱስ ሲኖዶስ ከምንግዜውም በላይ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበትና በመሰረታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግሮች ላይ አተኩሮ ሊወያይ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡ ከዚህ በፊት የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በተለያየ ጊዜ ታላላቅ ውሳኔዎችን ያሳልፍ የነበረ ቢሆንም ውሳኔዎቹ
“ያለአግባብ የታሰሩና የተቀጡ ካሉ፣ ለለውጡ እንደከፈሉት ዋጋ ሊያዩት ይገባል” - ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ለአንድ ወር ያህል በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ታስረው ሲሰለጥኑ ነበር የተባሉ 1ሺ174 የአዲስ አበባ ወጣቶች፤ ከትላንት በስቲያ ከእስር የተለቀቁ ሲሆን የወጣቶቹ እስርም ሆነ የግዳጅ ስልጠና ህጋዊ መሰረት የሌለው ነው ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ተችተዋል፡፡ ወጣቶቹ በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በቆዩባቸው ጊዜያት በህገ መንግስት፣ በሰላም አስፈላጊነት፣ እራስን ከወንጀል ስለ ማራቅና ተያያዥ ስልጠናዎች ወስደው ማጠናቀቃቸው የተገለፀ ሲሆን ከማሰልጠኛው ሲወጡም፤ “ሰላም ለሁላችንም ስለሆነች እንጠብቃለን” የሚል ቲ-ሸርት ለብሰው ታይተዋል፡፡ የወጣቶቹ እስርና ስልጠና የህግ አግባብነት ያለው መሆኑን የተጠየቁ የህግ ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት፤ የመንግስት ድርጊት የሀገሪቱን ህገ መንግስትም ሆነ የወንጀለኛ መቅጫ ህጉን የተፃረረ ነው ብለዋል፡፡ መንግስት በወንጀል የጠረጠረውን ግለሰብ፣ በ48 ሰዓት ውስጥ ለፍ/ቤት የማቅረብና በማስረጃ ከስሶ የማስቀጣት መብት እንጂ ሰዎች በኃይል ሰብስቦ፣ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ውስጥ በማስገባት የግዳጅ ስልጠና የመስጠት ህጋዊ መብት እንደሌለው ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡ መንግስት ለዚህ የህግ ጥሰት ወጣቶቹንና የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበትና ወጣቶቹ ላባከኑት ጊዜና
በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ)፤ የታሰሩበትን ክፍል መስኮት በመስበርና ከጥበቃ ጋር በመተናነቅ የማምለጥ ሙከራ አድርገው ነበር ሲል ፖሊስ ትናንት ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተናገረ ሲሆን ግለሰቡ ግን ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን ለችሎቱ መግለጻቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡አብዲ ሞሃመድ ኡመር፤ በምርመራ ወቅት ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንደነበረባቸውና የአእምሮ ጤና ችግር ካለበት አንድ ታሳሪ ጋር በአንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ ታስረው እንደነበር ለችሎቱ አቤቱታቸውን ማሰማታቸውን ተከትሎ ፖሊስ በሰጠው ምላሽ፣ ግለሰቡ የጤና ችግር እንዳለባቸው በመግለጻቸው ለቢሮ በሚያገለግል ክፍል ውስጥ ታስረው እንደነበርና የማምለጥ ሙከራ ካደረጉ በኋላ ግን፣ ወደ መደበኛ የእስረኞች ክፍል ተዛውረው ለብቻቸው እንዲታሰሩ ተደርጓል ማለቱን ዘገባው አመልክቷል፡፡
· ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ይጣመራሉ፤የካቢኔ አባላት ከ28 ወደ 20 ዝቅ ይላሉ· ሰላምና የህግ የበላይነት እንዲሰፍን የሚሰራ “የሰላም ሚኒስቴር” ሊቋቋም ነውየጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ አባላት ቁጥር ከ28 ወደ 20 ዝቅ የሚደረግ ሲሆን በርካታ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ይጣመራሉ ተብሏል፡፡ አዲስ “የሰላም ሚኒስቴር” መስሪያ ቤትም ይቋቋማል፡፡ የፌደራል መንግስት አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን የጠቆሙት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ፤ ስድስት ያህል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ይዋሃዳሉ ብለዋል፡፡ በረቂቅ አዋጁ መሰረት፤የንግድ ሚኒስቴር እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተዋህደው፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሆን፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተዋህደው፣ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡ በተጨማሪም የከተማ ልማት ሚኒስቴር እና የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተዋህደው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን በየሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስር ያሉ ተጠሪ ተቋማትም በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲዋሃዱ ይደረጋል ተብሏል፡፡በሀገር ውስጥ ሰላምና የህግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ በህዝቡ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ መገንባት ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ “የሰላም
የሠራዊት አባላቱ ጠ/ሚኒስትሩንና ህዝቡን ይቅርታ ጠይቀዋባለፈው ረቡዕ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም ተሲያት ላይ፣ 240 የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ያመሩት ለግዳጅ አልነበረም። ይልቁንም ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ለመወያየት ፈልገው ነው፡፡ የሰራዊት አባላቱ ያልተለመደ አመጣጥ እንግዳ የሆነባቸው የቤተ መንግስት ጸጥታና ደህንነት ሃላፊዎች፤ ከሁሉ አስቀድመው አባላቱን ትጥቅ እንዳስፈቷቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው ቤተ መንግስት እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ተብሏል፡፡ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የዚያኑ ዕለት ምሽት ለኢቴቪ በሰጡት መግለጫ፤ ነገሩን ቀላል አድርገው ነው የገለጹት፡፡ በወታደሮቹ ቤተ መንግስት መከሰት የደነገጡ ወይም የተበሳጩ አይመስሉም፡፡ እንደውም ከሰራዊቱ አባላት ወደ ቤተ መንግስት መግባት ጋር ተያይዞ፣ በፌስቡክ ላይ በተሰራጩ የ”መፈንቅለ መንግስት ሙከራ” እየተደረገ ነው ዓይነት አሸባሪ የፈጠራ ወሬዎች ሳይደነግጡ አልቀሩም፡፡ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም ራሳቸው ለቲቪ መግለጫውን የሰጡት። “የውሸት ዘመቻ ተቀብለን ካስተናገድን ያው መበላላት ነው” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ ”በሃይማኖት፣ በዘር፣ በሥልጣን---ክፉ ሰዎች እንዲህ እየፈጠሩ ነው የሚያሰራጩት--” በማለት ህብረተሰቡ፣ ከፌስቡክ ዘመቻ ራሱን እንዲያቅብ መክረዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ነገሩን ቀለል
በጠቅላይ አቃቤ ህግ ሥር የተቋቋመው የፍትህ እና ህግ ማሻሻያ ም/ቤት ኮሚቴ ሰሞኑን በአዋጁ ላይ ያደረገውን ጥናት ውጤት ለውይይት አቅርቧል፡፡ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ተቋማትና የማህበረሰብ ኮሚቴዎች በፀረ ሽብር ህጉ ላይ የተወያዩ ሲሆን “የፀረ ሽብር ህግ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል አያስፈልግም” በሚለው ላይ ሰፊ ክርክርና ውይይት ተካሂዷል፡፡ አብዛኛው አስተያየት ሰጪ አገሪቱ ከምትገኝበት ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታ አንፃር፣ የፀረ ሽብር ህግ ያስፈልጋታል የሚለውን ሃሳብ ያንፀባረቀ ሲሆን ላለፉት 8 ዓመታት የተተገበረው የፀረ ሽብር ህግ ግን ለፖለቲካዊ ማጥቂያ ውሏል በሚል ክፉኛ ተተችቷል፡፡ የፍትህና የህግ ማሻሻያ ም/ቤት አባሉ፣ ጠበቃና የህግ አማካሪ አቶ አመሃ መኮንን ባቀረቡት ጥናት ላይም፤ በተለይ የተለየ አመለካከትና ሃሳብ ያላቸው፣ የያዙት ሃሳብ ለመንግስት ስጋት ነው ተብለው የሚገመቱ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የነበረው የፀረ ሽብር ህግ እንደማጥቂያ መሳሪያ አገልግሏል ብሏል፡፡ በርካቶችም በዚህ ህግ ምክንያት ለሰብአዊ ጉስቁልና እና ጉዳት እንዲሁም ለህሊናዊና ሞራላዊ ጉዳት መዳረጋቸውን በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ ለኢትዮጵያ “የፀረ ሽብር ህግ ያስፈልጋል አያስፈልግም” በሚለው ጉዳይ ላይ በተደረገው ውይይት እንደቀድሞ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ኢላማ
“ፖለቲከኞች ከሃገር ሽማግሌዎች መማር አለባቸው” - ሰማያዊ ፓርቲበቅርቡ ከውጭ የተመለሱና ነባር የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ከገዥው ፓርቲ ጋር በጋራ በሀገሪቱ የወደፊት አቅጣጫዎችና የህግ የበላይነት ጉዳይ ላይ የሚመክሩበትን መድረክ፤ መንግስት ኃላፊነት ወስዶ እንዲያመቻች ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ትናንት በሰጠው መግለጫ፤ በሀገሪቱ የሚታዩ የህግ አለመከበርና የዜጎች እንግልት እንዲገታ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገሪቱ ሁኔታ ላይ የጋራ አቋም ይዘው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል ውይይት ማካሄድ ያስፈልጋል ብሏል። ይህን የውይይት መድረክም የሀገርን ሰላምና መረጋጋትን የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለበት የሀገሪቱ መንግስት እንዲያዘጋጅ ፓርቲው በመግለጫው ጠይቋል፡፡ ይህ መድረክ ቢዘጋጅ “ትጥቅ ፍታ አልፈታም የሚል ውዝግብን በማስቀረት በሀገሪቱ ጉዳይ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝም አጋዥ እንደሚሆን ሰማያዊ ጠቁሟል፡፡ “የሀገርና ህዝብን ሰላምና መረጋጋት ከማስፈን አንፃር፤ የፓርቲ ርዕዮተ ዓለም ልዩነቶች ሊገድቡን አይገባም” በሚል መርህ ፓርቲው ባወጣው የአቋም መግለጫው፤ “ይሄ የኔ ሀገር ነው፤ ያ ያንተ ነው መባባሉ ቀርቶ፣ የጋራ ሃገራችንን ወደ መገንባት ሂደት መግባት አለብን” ብሏል፡፡ “ፖለቲከኞች ከጋሞ ሃገር ሽማግሌዎች መማር አለባቸው” ያለው ፓርቲው ለፀብ መነሻ የሚሆኑ አጀንዳዎችን በመተው፣
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውና የበርካታ ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ያለውን የካንሰር ሕመም ለመከላከል ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል ተገቢ ነው ያለው ሲኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል በኅብረተሰቡ ዘንድ ስለ በሽታው ግንዛቤ መፍጠር እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡ ከተመሰረተ 18 ዓመታትን ያስቀጠረው ሆስፒታሉ፣ የጡት ካንሰርን አደገኛነት ለማስገንዘብ እየሰራ ከመሆኑም በላይ ከጥቅምት 5-17 ቀን 2011 በዘመናዊ መሳሪያ (Mamography) በመታገዝ ዕድሜአቸው ከ40 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ነፃ የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ የጡት ካንሰር፣ መደበኛ የጡት ሴሎች ከቁጥጥር ውጭ በመሆን መልኩ በሚበዙበትና ጤናማ አካልን በሚወርሩበት ጊዜ የሚፈጠር ሲሆን፣ በበለፀጉት አገሮች ከ8 ሴቶች አንዷ በጡት ካንሰር የተያዘች እንደሆና ሴቶች በካንሰር የመያዝ ዕድላቸው 150 እጥፍ እንደሆነ ሆስፒታሉ ገልጿል። የጡት ካንሰር ምልክቶች፤ በጡት ላይ እብጠት ወይም ዕጢ፣ የጡት መጠን መጨመር ወይም መቀነስ፣ የጡት ቆዳ መሰርጎድ፣ መቁሰል፣ የጡት ላይ ህመም ሲሆኑ፣ በጡት ላይ የሚታዩ ምልክቶች ሁሉ የካንሰር ምልክቶች ናቸው ማለት እንደማይቻል ተነግሯል፡፡ ማንኛዋም ከ40 ዓመት በላይ የሆናት ሴት በዓመት አንድ ጊዜና
የምርጫ ህጉን በተመለከተ የማሻሻያ ሃሳቦችን ያቀረበው ከፓርቲዎች የተውጣጣው የምርጫ ጉዳዮች ማሻሻያ ሃሳቦች አቅራቢ ኮሚቴ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ምዝገባ አዋጅን ለማሻሻል ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ ያስፈልጋል አለ፡፡ ኮሚቴው በፖለቲካ ድርጅቶች ምዝገባ አዋጅ እና በፓርቲዎች የስነ ምግባር አዋጅ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ማሻሻያ አጠናቆ ለፓርቲዎች ውይይት ዝግጁ ማድረጉን የኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ የተመለሱ የፖለቲካ ድርጅቶች አብዛኛው አመራሮቻቸው ከዜግነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምዝገባ ማከናወን እንዳልቻሉ ባለፈው ሳምንት ለአዲስ አድማስ መግለፃቸው የሚታወስ ሲሆን የፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ማሻሻያ ሀሳብ አቅራቢ ኮሚቴውም፤ በጉዳዩ ላይ ውይይት ማድረጉ ተገልጿል፡፡ በጉዳዩ ላይ ለውይይት የሚቀርቡ የተለያዩ አማራጮች መቅረባቸውን የጠቆሙት አቶ ዋሲሁን፤ ኢትዮጵያዊ ባልሆኑ ግለሰቦች የተቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት ይስተናገዱ የሚለው ራሱን ችሎ ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው በጥናት ታግዞ በቀረበው የማሻሻያ ሃሳብ መመላከቱን አስረድተዋል፡፡ በቀጣይ ለፖለቲካ ድርጅቶች ውይይት በሚቀርበው የፓርቲዎች የስነ ምግባር አዋጅ ላይም ከዚህ ቀደም የፓርቲዎችን ነፃነት የሚገድቡ የተለያዩ አንቀፆች መሻሻላቸውን እንዲሁም በውጭ ሀገር የሚኖሩ
ገንዘብ ከማንኛውም ህጋዊ ምንጭ እንዲያሰባስቡ ይፈቅዳልማህበራትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤ ከየትኛውም ህጋዊ ምንጭ ገንዘብ መሰብሰብ የሚያስችላቸው አዲስ ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀ ሲሆን አዋጁ የድርጅቶችን ነፃነት የሚያስጠብቅ ነው ተብሏል፡፡በጠቅላይ አቃቤ ህግ ስር የተቋቋመው የፍትህና የህግ ማሻሻያ ምክር ቤት፤ በ2001 ዓ.ም የወጣውና ለበርካታ ማህበራትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መዳከም ምክንያት ሆኗል በሚል ሰፊ ትችት ሲቀርብበት የነበረውን አዋጅ አሻሽሎ እንዳጠናቀቀ ታውቋል፡፡ አዲስ በተዘጋጀው ረቂቅ ላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (ማህበራትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች) በፈለጉት ጉዳይ ላይ የመስራትና የመንቀሳቀስ መብታቸው ያለምንም ገደብ መጠበቁ ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ ቀደም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከውጪ የሚያገኙት ገንዘብ ከ10 በመቶ መብለጥ እንደሌለበትና በዋናነት ገቢያቸው ከሀገር ውስጥ እንዲሆነ የሚያስገድደው አንቀፅም ሙሉ ለሙሉ ተሻሽሎ ድርጅቶች ከየትኛውም ህጋዊ ምንጭ ገንዘብ ማሰባሰብ እንዲችሉ ይፈቅዳል ተብሏል፡፡ ይህን አዋጅ አስመልክቶም ከትናንት በስቲያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ አዲሱ የተሻሻለው ህግ፤ በሀገሪቱ የተጀመረውን የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታን ተቋማዊ ለማድረግ በእጅጉ ይረዳል ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያና የኤርትራ እርቅን ተከትሎ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ማሻሻያ እያደረገች ነው የተባለችው ኤርትራ፤ የፖለቲካ እስረኞችን እንድትፈታ ሂውማን ራይትስ ዎች ጠይቋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዳግም ከተጀመረ በኋላ የኤርትራ መንግሥት በተለይ በዲፕሎማሲው ረገድ ከፍተኛ ማሻሻያ ማድረጉን፣ የህገ መንግስት ረቂቅ ማዘጋጀት መጀመሩን፣ በሃሳብ ልዩነትና በፖለቲካ አመለካከት የተሰደዱ ኤርትራውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡን የገለፀው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ፤ ከእነዚህ ማሻሻያዎች ጎን ለጎን የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት አለበት ብሏል፡፡ በ2001 (እኤአ) 21 ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናትና ጋዜጠኞች በግፍ መታሰራቸውንና በእስር ላይ የተለያዩ ኢ - ሰብአዊ ተግባር እየተፈፀመባቸው መሆኑን የጠቆመው ድርጅቱ፤ እነዚህን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡ የሀገሪቱ መንግስት በህግ የበላይነትና በእስረኞች ጉዳይ ማሻሻያ ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ በቅርቡ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት የሀገሪቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዘብጥያ መወርወሩ “ተገቢነት የጎደለው ኢ-ፍትሃዊ ድርጊት” ነው ሂውማን ራይትስ ዎች ሲል በፅኑ ኮንኗል፡፡የኤርትራ መንግስትና የኢትዮጵያ መንግስት፤ የተባበሩት መንግስታት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ መጠየቃቸው የሚታወቅ ሲሆን ሂውማን ራይትስ ዎች በበኩሉ፤ የመንግስታቱ ድርጅት የሃገሪቱን
“ከዜግነት ጋር የተያያዘው ህግ እንቅፋት ሆኖብናል”በመንግስት ጥሪ ተደርጎላቸው ከውጭ አገራት ወደ ሃገር ቤት የተመለሱ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች እስካሁን በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ህጋዊነትን ያላገኙ ሲሆን የፖለቲካ ድርጅቶቹ እንዲመዘገቡ ምርጫ ቦርድ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም አባይ ለአዲስ አድማስ በሰጡት ማብራሪያ፤ ቦርዱ ቀደም ሲል ለፖለቲካ ድርጅቶቹ ጥሪ በማድረግ፣ በአመዘጋገብ ስርአቱና ሂደቱ ላይ ገለፃ መስጠቱንና እንዲመዘገቡም ማስታወቁን ጠቁመው፤ እስካሁን ከ“አፋር ህዝብ ፓርቲ” በስተቀር ወደ ጽ/ቤቱ ቀርቦ አቅርቢ እውቅና ለማግኘት ያመለከተ ፓርቲ የለም ብለዋል፡፡ የሀገሪቱ ህግ፤ “ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት በሃገር ውስጥ ህጋዊ ሆኖ ነው መንቀሳቀስ አለበት” ይላል ያሉት አቶ ተስፋለም፤ ድርጅቶቹ ወደ ምዝገባ ስርአቱ እንዲገቡ ቦርዱ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ቦርድ በህጋዊነት የመዘገባቸው 22 ሀገር አቀፍና 40 ክልላዊ፣ በድምሩ 62 ፓርቲዎች መሆናቸውንም ዳይሬክተሩ ጠቁመው፡፡ ቦርዱም በሀገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲነት የሚያውቃቸው እነዚህኑ ድርጅቶች ብቻ ነው ብለዋል - አቶ ተስፋለም፡፡ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ወደ
· “ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ ነው” · ግጭቱ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን ተሰግቷል እየተፈፀመ ነው”በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የተደራጁ ታጣቂዎች በሰነዘሩት ጥቃት ከ60 በላይ ዜጎች መገደላቸውን ተከትሎ፣ በተከሰተ ግጭት በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞና አማራ ተወላጆች የተፈናቀሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ፤ በክልሉ ከፍተኛ መፈናቀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ መሆኑን ጠቁሞ፤ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ ካልወሰደ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ በአካባቢው ግጭቱና የሰብአዊ መብት ጥሰቱ መቀጠሉንም ኮሚሽኑ አስታውቋል። በሌላ በኩል፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንገድ በመቆረጡና በታጣቂዎች በመዘጋጋቱ ምክንያት ተፈናቅለው ለሚገኙ ከ82 ሺህ በላይ ዜጎች ተገቢውን ሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ አለመቻሉን የክልሉ መንግስት ለአዲስ አድማስ አስታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያሱ እና ሊጃንፎ በተባሉት የክልሉ ሁለት ወረዳዎች፣ አንፃራዊ መረጋጋት በመስፈኑ የተወሰኑ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን የተናገሩት የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዘላለም ያደታ፤ በአንፃሩ አጋሎሜቲ በተባለው ወረዳ ትንኮሳዎችና ግጭቶች አሁንም አልፎ አልፎ እየተከሰቱ ነው ብለዋል፡፡መረጋጋት ባለባቸው አካባቢዎች የበለጠ የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መሆኑን
· ምርጫ ቦርድ፤ በገዥው ፓርቲና በተቃዋሚዎች እኩል ውክልና ይመራል· ቅሬታዎችን የሚያስተናግድ የምርጫ ፍ/ቤት ይቋቋማል· በአዲሱ ህግ፤ ጠ/ሚኒስትሩ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን የመምረጥ ስልጣን የላቸውምየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከገዥው ፓርቲና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በእኩል መጠን በተውጣጡ አባላት እንደሚመራ አዲሱ የምርጫ ህግ ሪፎርም ሰነድ አመልክቷል፡፡ በምርጫ ውጤት ቅሬታ የሚያቀርቡ ተወዳዳሪዎችን ለመዳኘትም በምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ “የምርጫ ፍ/ቤት” ይቋቋማል ተብሏል፡፡ የሀገሪቱን የምርጫ ስርአት ለመቀየር የግድ ህገ መንግስቱ መሻሻል እንደሚገባውም ይኸው ለፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት የቀረበው የምርጫ ህግ ሪፎርም ይጠቁማል፡፡ባለፉት 27 ዓመታት በሀገሪቱ በተደረጉት 5 ብሔራዊ ምርጫዎች ላይ በህገ መንግስቱ ተደንግጎ ያገለገለው የአብላጫ ምርጫ ስርአት፣ ህገ መንግስቱ ተሻሽሎ በቅይጥ ትይዩ አሊያም በተመጣጣኝ ውክልና የምርጫ ስርአት መተካት እንዳለበት ረቂቅ ሰነዱ ያመለክታል፡፡ ምርጫን በበላይነት የሚያስፈፅመው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ቀደም ሲል ዘጠኝ አባላት የነበሩት ሲሆን በአዲሱ ማሻሻያ ቁጥራቸው ወደ 15 ከፍ ብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቦርዱን ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ መርጦ ለሹመት ያቀርባል የሚለውን የቀድሞ ህግ በማሻሻል የቦርዱ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ከቦርዱ አባላት
“በዶ/ር ዐቢይ አመራር አለምን ያስደነቀ ለውጥ መጥቷል” - ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሐዋሳ ከተማ ላለፉት ሦስት ቀናት ጉባኤውን ሲያካሂድ የቆየው ኢህአዴግ፤ ዶ/ር ዐቢይ አህመድንና አቶ ደመቀ መኮንንን በሊቀ መንበርነትና በም/ሊቀመንበርነታቸው እንዲቀጥሉ የመረጠ ሲሆን ኢህአዴግ የርዕዮተ ዓለም ለውጥ አለማድረጉ ታውቋል፡፡ በጉባኤው በዋናነት ባለፉት 6 ወራት በዶ/ር ዐቢይ አህመድ አመራርነት የመጡ ፖለቲካዊ ለውጦች የውይይት አጀንዳ እንደነበሩ የጠቆሙት የስብሰባው ተሳታፊዎች፤ ጠ/ሚኒስትሩ የሰጧቸው አመራሮች ውጤታማና ስኬታማ ነበሩ በሚል መገምገሙን ጠቁመዋል፡፡ የህውሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጉባኤው ላይ በሰጡት አስተያየት፤ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አመራርነት ባለፉት 6 ወራት በሀገሪቱ የመጣው አዎንታዊ ፖለቲካዊ ለውጥ እውቅና ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ “ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡት አለምን ያስደነቁ ለውጦች ዶ/ር ዐቢይ እንደ መንግሥት መሪ የራሱን ፈጠራ፣ ድፍረት፣ ጥበብና ሁለንተናዊ የአመራር ብቃት ተጠቅሞ ያመጣው ለውጥ ነው፣ ለዚህም ተገቢውን እውቅናና ክብር መስጠት ያስፈልጋል” ማለታቸውን አንድ በስብሰባው የተሳተፉ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል፡፡ በጉባኤው ሌላው ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የህግ የበላይነት ጉዳይ ሲሆን
- “ጥቃቱን ያቀነባበረችው ግለሰብ ነዋሪነቷ በኬንያ ነው” - ዐቃቤ ሕግ - ኦነግ ጉዳዩ አይመለከተኝም ብሏል ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተጠራው የድጋፍና የምስጋና ህዝባዊ ሰልፍ ላይ የተፈፀመው የቦንብ ጥቃት ጠ/ሚኒስትሩን ለመግደል ያለመ መሆኑን ዐቃቤ ሕግ የገለፀ ሲሆን ጥቃቱን ያቀነባበረችው ግለሰብ ነዋሪነቷ በኬንያ መሆኑን ለፍ/ቤት ተናግሯል፡፡ ትናንት አርብ ዐቃቤ ሕግ በአምስት ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብርተኝነት ክስ የመሠረተ ሲሆን፤ ተከሳሾቹም አቶ ጌቱ ግርማ፣ አቶ ብርሃኑ ጃፋር፣ አቶ ጥላሁን ጌታቸው፣ አቶ ባህሩ ቶሎሳና አቶ ደሣለኝ ተስፋዬ ናቸው፡፡“ተከሳሾቹ ጥቃቱን ለመፈፀም ያነሳሳቸው የአገሪቱ መንግስት መመራት ያለበት ቀድሞ በተመሠረተው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነው” የሚል አላማ ይዘው መሆኑን ዐቃቤ ሕግ አስረድቷል፡፡ ዶ/ር ዐቢይ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም በማለት ተከሳሾቹ ለድርጊቱ መነሳሳታቸውን የጠቆመው ዐቃቤ ሕግ፤ ጠ/ሚኒስትሩ የኦሮሞ ህዝብን ፍላጐት አያስፈፅሙም የሚል እምነት ሰንቀው ለጥቃቱ መንቀሳቀሳቸውን ከምርመራ ግኝቱ ማረጋገጡን አሰታውቋል፡፡ የቦንብ ጥቃቱን ያቀነባበረችውም ነዋሪነቷ በኬንያ ናይሮቢ የሆነች ገነት ታምሩ
በሃገሪቱ የሚካሄደው ፖለቲካዊ ለውጥ ከስሜት የፀዳ እንዲሆን አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግ የጠየቁ ሲሆን፤ ዜጐች የለውጥ ኃይሉን ተግባር ለማደናቀፍ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲታቀቡ አሳሰቡ፡፡ የሁለቱ ድርጅቶች አመራሮች ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ዜጐች ሕገወጥ በሆኑ ሰልፎች ከመሳተፍ፣ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ መፈክሮችን ከማሰማትና የለውጥ ሂደቱን ከሚያደናቅፉ እንቅስቃሴዎች መታቀብ አለባቸው ብለዋል፡፡ የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሣ፤ “ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ወስነን የመጣን እንደመሆኑ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን በትዕግስት እንዲንቀሳቀሱ እንመክራለን፤ እየመከርንም ነው” ብለዋል፡፡ መንግስት የህዝብን ሠላም የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት ያስታወሱት ሊቀመንበሩ፤ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚፈጠሩ አለመረጋጋቶች መንግስት መፍትሄ ለማበጀት የሚያደርገውን ጥረት እንደግፋለን ብለዋል፡፡ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ መፈክሮችና ሰልፎች እንዲታቀቡ እየመከርን ነው ያሉት የአርበኞች ግንቦት 7 የህዝብ ግንኙነት አቶ አበበ ቦጋለ በበኩላቸው፤ በቅርቡ በአዲስ አበባ በተደረገ ድንገተኛ ሠልፍ ላይ የተሰሙ “የኦሮሞ መንግስት ከአዲስ አበባ ይውጣ”፣ “ከንቲባ ታከለ ኡማ ከስልጣን ይልቀቁ”፣ “ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከስልጣን ይውረዱ” የሚሉ መፈክሮች የትኛውንም የፖለቲካ ድርጅት የማይወክሉ፣ ተገቢነት የሌላቸው መፈክሮች
በቅርቡ ወደ ሃገር ቤት የተመለሰውን “አርበኞች ግንቦት 7” ጨምሮ 11 የፖለቲካ ድርጅቶች “የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና” በሚል ርዕስ በባህር ዳር በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በመድረኩ ጥናት፤ ያቀረቡ ምሁራን፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች መብዛት ለግጭትና መከፋፈል ምክንያት እየሆነ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ሠማያዊ፣ ኢዴፓ፣ መኢአድ፣ አብን ጨምሮ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ በምሁራን ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጐበታል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶ/ር ዳዊት መኮንንና አቶ ኢያሱ በካፋ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ሚናቸውን ሊወጡ የሚችሉባቸውን አቅጣጫዎች ጠቁመዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የተሳተፉት የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮች ስለ ውይይቱ ለአዲስ አድማስ እንዳብራሩት፤ “በሃገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መብዛት ለግጭትና መከፋፈል ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው ፓርቲዎች ወደ አንድነት መምጣት አለባቸው” የሚል ሃሳብ ከጥናት አቅራቢዎቹ ተሰንዝሯል፡፡ በፖለቲካ ውድድር ውስጥም ፓርቲዎች ጥላቻና ሃይልን በማስወገድ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ አካሄዶችንና አማራጮችን ሊያዳብሩ እንደሚገባ ለማስገንዘብም የተለያዩ ሃገራት ተሞክሮ በማሳያነት መቅረቡንም የውይይቱ ተሳታፊዎች
ላለፉት 20 ዓመታት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ዝግ ሆኖ የቆየው ድንበር መስከረም 1 ቀን 2011 ዓ.ም መከፈቱን ተከትሎ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አቋርጠው መግባታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒሰትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያን ዘመን መለወጫ ምክንያት በማድረግ በቡሬና በዛላምበሳ ዝግ የነበረውን ድንበር ማስከፈታቸውን ተከትሎ፣ የሰዎች ዝውውር ከፍተኛ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል፡፡ አብዛኞቹ ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ያሉት ኤርትራውያን ኑሮአቸውን በኢትዮጵያ ለማድረግ መሆኑን የጠቆመው የተቋሙ ሪፖርት፤ ቀሪዎቹም በኢትዮጵያ የሚገኙ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ በማሰብ መምጣታቸውን አመልክቷል፡፡ ለንግድ የሚመላለሱ ኤርትራውያን ነጋዴዎች ቁጥርም ቀላል እንዳልሆነ ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡የሁለቱ ሃገራት ድንበር ከተከፈተ በኋላ ቀድሞ የኤርትራን መንግስት ጭቆና ሽሽት በድብቅ ይመጡ የነበሩ ኤርትራውያን አሁን በይፋ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት መጀመራቸውን የጠቆመው ተቋሙ፤ በየቀኑ 500 ያህል ስደተኞች ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው ብሏል፡፡ በዚህም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ፈላጊዎች ቁጥር ወደ 175 ሺህ ከፍ ማለቱን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡
ከተመሠረተ ከአራት አሰርት ዓመት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) አመራሮች ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ እንደሚገቡ የአቀባበል ስነ ስርዓት አዘጋጆቹ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ ባለፉት 46 ዓመታት በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር በሚገኙ አባላቱ አማካኝነት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍን ሲታገል መቆየቱን የገለፀው ኢህአፓ፣ አሁን የተፈጠረውን ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ በመጠቀም፣ አመራሮቹ ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ መወሰናቸውን አስታውቋል። “በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን እየታየ ያለው የለውጥ ብልጭታ፣ ለዘመናት ስታገልለት የቆየሁለት አቋሜ ውጤት ነው” ያለው ኢህአፓ፤ ይህን የለውጥ ሂደት ለመደገፍና የተጀመረውን የሰላም የዴሞክራሲና የአንድነት ጭላንጭል እንዳይደበዝዝ፣ የድርሻቸውን ሊወጡ፣ አመራሮቹ ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስታውቋል፡፡ ኢህአፓ በዋናነት የሚታገልላቸው አላማዎችም፤ የአዲሱ ትውልድ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ፣ የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባና ነው ብሏል ለህዝብ መብት መሞት አኩሪ ታሪክ መሆኑን በተግባር ማሳየት ጠቁሟል፡፡ ዛሬ ለረጅም ዓመታት በስደት ከኖሩበት ወደ ሃገር ቤት ከሚመለሱ ከፍተኛ አመራሮቹ መካከል ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም፣ አቶ መሐመድ ጀሚል፣ ሊቀመንበሩ አቶ መርሻ ዮሴፍና ኢ/ር
ከተመሠረተ ከአራት አሰርት ዓመት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) አመራሮች ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ እንደሚገቡ የአቀባበል ስነ ስርዓት አዘጋጆቹ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ ባለፉት 46 ዓመታት በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር በሚገኙ አባላቱ አማካኝነት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍን ሲታገል መቆየቱን የገለፀው ኢህአፓ፣ አሁን የተፈጠረውን ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ በመጠቀም፣ አመራሮቹ ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ መወሰናቸውን አስታውቋል። “በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን እየታየ ያለው የለውጥ ብልጭታ፣ ለዘመናት ስታገልለት የቆየሁለት አቋሜ ውጤት ነው” ያለው ኢህአፓ፤ ይህን የለውጥ ሂደት ለመደገፍና የተጀመረውን የሰላም የዴሞክራሲና የአንድነት ጭላንጭል እንዳይደበዝዝ፣ የድርሻቸውን ሊወጡ፣ አመራሮቹ ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስታውቋል፡፡ ኢህአፓ በዋናነት የሚታገልላቸው አላማዎችም፤ የአዲሱ ትውልድ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ፣ የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባና ነው ብሏል ለህዝብ መብት መሞት አኩሪ ታሪክ መሆኑን በተግባር ማሳየት ጠቁሟል፡፡ ዛሬ ለረጅም ዓመታት በስደት ከኖሩበት ወደ ሃገር ቤት ከሚመለሱ ከፍተኛ አመራሮቹ መካከል ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም፣ አቶ መሐመድ ጀሚል፣ ሊቀመንበሩ አቶ መርሻ ዮሴፍና ኢ/ር
በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ በግጭና ብሔር ተኮር ጥቃቶች፤ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የ215 ዜጐች ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፉን የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ከትናንት በስቲያ ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል፡፡ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ብሔር ተኮር ግጭቶችና በቡድን የተደራጁ ኃይሎች እየፈፀሟቸው ያሉትን ከባድ ጥቃቶች መንግስት በአስቸኳይ ሊያስቆም እንደሚገባ ሰመጉ አሳስቧል። በተለያዩ አካባቢዎች ግድያዎች፣ ዘርን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችና ግጭቶች፣ የመንጋ ፍትህና ሥርዓት አልበኝነት እየተንሰራፋ መሆኑን የጠቆመው የሰመጉ ሪፖርት፤ በአደባባይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችም በባህሪያቸው ዘግናኝ ናቸው ብሏል፡፡ ካለፈው ሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች 215 ያህል ዜጐች በግጭትና በጥቃት መሞታቸውን ያስታወቀው ሪፖርቱ፤ እነዚህ ግጭቶችና ጥቃቶች በከፍተኛ መስዋዕትነት የተገኘውን የዴሞክራሲ ጭላንጭል ያጨልም ስር የሰደዱ ችግሮች እየተገዳደሩት ይገኛሉ ብሏል፡፡ በግጭት በቃትና በመንጋ ፍትህ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉባቸው አካባቢዎች መካከልም፤- በደቡብ ክልል ፔፒ ከተማ 5 ሰዎች፣ በኦሮሚያ ክልል ባሌ-ጐባ 10 ሰዎች፣ በደቡብ ክልል የም ወረዳ 6 ሰዎች፣ እንዲሁም ዳውሮ ዞንሪ ተርጫ ከተማ 5 ሰዎች፣ በሻሸመኔ 4 ሰው፣ በድሬዳዋ 15 ሰዎች፣
- ሲሚንቶ ወደ ኤርትራ፤ አልባሳት ወደ ኢትዮጵያ … - ኤርትራ በድንበር አካባቢ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥላለች በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ባለፈው ሳምንት ሚኖረውን ግንኙነት የሚደነግግ ባለ 7 አንቀጽ ስምምነት፣ የሁለቱ ሃገራት መሪዎች የተፈራረሙ ሲሆን፤ በሳዑዲ አረቢያ ጂዳ የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ፣ በሁለቱ ሃገራት ድንበር ከወዲሁ የንግድ እንቅስቃሴ መጧጧፉ ታውቋል፡፡ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ ነው የተባለው ስምምነት፤ በሁለቱ ሃገራት መካከል የጋራ የኢኮኖሚ ትስስር እንዲፈጠር የሚያግዝ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ ሁለቱ ሃገራት በጋራ የኢኮኖሚ ዞን ለመመስረት፣ የንግድ እንቅስቃሴውም ነፃ እንዲሆን የተስማሙ ሲሆን ስምምነቱን ተከትሎም፣ በድንበር አካባቢ ከሰሞኑ የንግድ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መታየቱን ኤርትሪያን ፕሬስ ዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ ሲሚንቶ የኤርትራን ገበያ ማጥለቅለቁን፣ በአንፃሩ የኤርትራ የአልባሳት ምርት ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ፣ የኤርትራ መንግስት፤ ለደህንነት ሲል ድንበር ማቋረጥ የሚቻለው ከጠዋቱ 12 ሠዓት እስከ ምሽቱ 12 ሠዓት ብቻ እንዲሆን የሰዓት እላፊ ገደብ መደንገጉን ኤርትሪያን ፕሬስ ዘግቧል፡፡ የሁለቱ ሃገራትን ነፃነት፣ ሉአላዊነትና የድንበር
በመጪው ዓመት 2012 ለሚደረገው ብሔራዊ ምርጫ አጋዥ የሆኑ ተቋማትን የመመስረትና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል አስቸኳይ ድርድር ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር እንዲጀመር በፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው “የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ” ጠየቀ፡፡ ፓርቲው በወቅታዊ መግለጫው፤ የተጀመረው ለውጥ ህዝቡ የሚፈልገውን መቋጫ እንዲያገኝ፣ በቀጣዩ ምርጫ ዙሪያ ከወዲሁ ድርድር መጀመር አለበት ብሏል፡፡ “በምርጫ ጉዳይ ለሚደረገው ድርድር ጊዜ ሊሰጠው አይገባም” ያለው ፓርቲው፤ “በገዥው ፓርቲ እየተደረገ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ ጊዜያዊ ማስታገሻ ከመሆን የዘለለ አይደለም፤ ሁሉን አሳታፊና ብሔራዊ መግባባትን የሚፈጥር ሥርዓት በምርጫ መመስረት ያስፈልጋል” ብሏል።በሃገሪቱ መሠረታዊ በሆኑ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እጅግ የተራራቁ ሃሳቦችን የሚያራምዱ ኃይሎችን የሃሳብ ልዩነቶቻቸውን ለማቀራረብና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችሉ ውይይቶች መካሄድ አለባቸው ብሏል - ፓርቲው። በሃገሪቱ መሠረታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ድርድሮች ተካሂደው ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ እንደሚያስፈልግ ያስታወቀው ኢሶዴፓ፤ የተጀመረውን የለውጥ ሂደትም በገዥው ፓርቲ አመራርነት ብቻ ማሳካት አይቻልም ብሏል። ለዚህም የሃገሪቱን ፖለቲካዊ ለውጥ ወደፊት ሊያሸጋግር የሚችል የብሔራዊ አንድነት መንግስት በአስቸኳይ ተመስርቶ፣ የለውጡን ሂደት መምራት አለበት ሲል
በሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ኢትዮጵያ ከዓለም በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሪፖርት አመልክቷል፡፡ሰሞኑን ይፋ በሆነው በዚህ ሪፖርት በ2018 እ.ኤ.አ. ግማሽ ዓመት በእርስ በርስ ግጭት ምክንያት ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ዜጐች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን፣ ይህም በዓለም ሃገራት ያልተለመደ መሆኑን ጠቁሟል - ሪፖርቱ፡፡ ዜጐች የተፈናቀሉባቸው ግጭቶችም በደቡብና በኦሮሚያ ድንበር አዋሳኝ፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ፣ በቤኒሻንጉልና በአማራ ክልል እንዲሁም በደቡብ ክልል የወረዳ ለወረዳ ግጭቶች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ ለግጭቶቹ መበራከትና መስፋፋት በኢህአዴግ መካከል የተፈጠረው አለመግባባትና የመንግስቱን ድክመት በምክንያትነት የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ ለተፈጠሩት ግጭቶችና መፈናቀሎች የመንግስትን ስልጣን የያዘው ኢህአዴግ ቀዳሚ ተጠያቂና ተወቃሽ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ የተፈናቃዮች ጉዳይ አስቸኳይ እልባት ካላገኘ የከፋ ሰብአዊ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል ያለው ሪፖርቱ፤ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ በተፈጠረ ግጭት 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ከቀዬአቸው የመፈናቀላቸውን ጉዳይ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በቸልታ መመልከታቸው አግባብ አይደለም ሲልም ወቅሷል፡፡ በአሁን ወቅት ውስን የእርዳታ ድርጅቶችና መንግስት ለተፈናቃዮች እርዳታ ለማቅረብ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን የመንግስታቱ
ላለፉት 27 ዓመታት የአማራ ክልልን ሲያስተዳድር የቆየው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)፤ ስያሜውንና አርማውን እንደሚቀይር አስታወቀ፡፡ የአማራ ህዝብ ትግል የደረሰበትን ደረጃ መሠረት በማድረግ፣ አርማና ስያሜውን ለመቀየር መወሰኑን የገለፀው ብአዴን፤ አዲሱን መጠሪያውንና አርማውን ከሳምንት በኋላ በሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባኤው ይፋ ያደርጋል ተብሏል፡፡ የድርጅቱን ቀጣይ ስያሜና አርማ በተመለከተም አማራጮችን አቅርቦ እስከ ወረዳ ባለው መዋቅሩ እያወያየበት መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ ለድርጅቱ መጠሪያነት አራት አማራጮችን ለውይይት ማቅረቡም ታውቋል፡፡ለውይይት የቀረቡት አማራጮችም፤ “የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” (አህዴፓ)፣ “የአማራ ክልል ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ” (አህዴፓ)፣ “የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት” (አህዴድ)ና “የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ” (አህዴን) የሚሉ ናቸው፡፡ የአርማ አማራጮችም ተዘጋጅተው ለንቅናቄው አባላት ውይይት ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ፤ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ስያሜውን፣ አርማውንና ድርጅታዊ መዝሙሩን ለመቀየር እንዳቀደና ይህም ከመስከረም 8 እስከ 10 በጅማ ከተማ በሚካሄደው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ውሣኔ እንደሚያገኝ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ መላውን ዓለም ያስደመመ ፖለቲካዊ ለውጥ እያደረገች መሆኑን ሰሞኑን አመራሮቹ ወደ አገር ውስጥ የገቡት “አርበኞች ግንቦት 7” ባወጣው የአቋም መግለጫው አስታወቀ፡፡ የንቅናቄው አመራሮች ወደ ሃገር ቤት ከገቡ በኋላ ባወጣው በዚህ የመጀመሪያው የአቋም መግለጫው፤ ዛሬ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴና የለውጡ ሂደት ቀጥተኛ ባለቤት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ብሏል፡፡ “በሃገሪቱ የተካሄደው ለውጥም የኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የናፈቀውን መላውን የዓለመ ህዝብ ያስደመመ ነው” ብሏል - ንቅናቄው፡፡ ባለፉት ሁለትና ሦስት ወራት ውስጥ ለውጡን በመደገፍ፣ ለውጡን ወደፊት ለማራመድ የሚፈልጉ የሰብአዊ መብት ታጋዮች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሃይማኖት አባቶች ለብዙ ዓመታት በስደት ከኖሩባቸው ሃገሮች ወደ ሃገራቸው መመለሳቸውን ያስታወሰው የንቅናቄው መግለጫ፤ ለተመለሱት ሁሉ እኩል ክብር እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡ በዜግነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካን አራምዳለሁ ያለው አርበኞች ግንቦት 7፤ “ለወደፊት የምንገነባው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከሚፈልጋቸው ቅድመ ሁኔታዎች አንዱና ትልቁ የፖለቲካ አካሄዳቸው ከማይገጥመንና በሃሳብ ከምንለያያቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ተከባብሮና ተቻችሎ መኖር መቻል ነው” ሲል አስገንዝቧል፡፡ህዝቡ ለአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ፣ በመከባበርና በፍቅር
በመላ ሃገሪቱ ከአርማና ባንዲራ ጋር በተያይዞ እየተፈጠሩ ያሉ ውዝግቦች ዘላቂ ሕጋዊ መፍትሄ እንደሚያሻቸው የገለፁት ሰማያዊ ፓርቲና ኦፌኮ፤ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ ወጥተው ወደ ሁከትና ብጥብጥ ከማምራታቸው በፊት መንግስት አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል። ከአርማና ሠንደቅ አላማ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ሁከቶችን ለማስቆም የሃይማኖት አባቶችና፣ አባገዳዎች፣በየአካባቢው ወጣቶችን የማረጋጋት ስራ እንዲሰሩም ፓርቲዎቹ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠይቀዋል፡፡ “የለውጡን ሂደት መደገፍና አገሪቱን እንደ አገር የማስቀጠል ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው ሲገባ፤ በየአካባቢው የሚታዩ ግጭቶችና ሥርአት አልበኝነት አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል” ያሉት ፓርቲዎቹ፤ “በተለይ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከባንዲራ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ውዝግብ ከምንም በላይ አሳሳቢ ነው፤ አስቸኳይ እልባት ያስፈልገዋል” ብለዋል፡፡ ሁሉም አካል የሌላውን ባከበረ መልኩ የየራሱን አርማ መያዝ እንደሚችል የተረጋገጠ ሁኔታ መፈጠሩን የጠቀሱት ፓርቲዎቹ፤ በዚህ ሰበብ የሚፈጠሩ ግጭቶችን በፅኑ እናወግዛለን ብለዋል፡፡ በሃገሪቱ በአሁን ወቅት እየታየ ያለው ፖለቲካዊ ለውጥ ተስፋ ሰጪ መሆኑን የጠቆሙት «ሰማያዊ» እና «ኦፌኮ»፤ ሁሉም የፖለቲካ ቡድን ይህን ተስፋ ወደተሻለ ለውጥ የማሸጋገር ኃላፊነት አለበት ብለዋል፡፡ ወደ ሃገር ውስጥ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታን ለመቀየር የወሰዷቸውን እርምጃዎችና ለውጡን ለማምጣት የሄዱበትን ርቀት የአሜሪካ መንግስት አደነቀ፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ቲቦር ናጋይ፤ በዶ/ር ዐቢይ አህመድ አመራር በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎች አድናቆት የሚቸራቸው ናቸው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የሃገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር እንዲሰፋ የሚያደርጉ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆኑን የጠቆሙት ቲቦር ናጋይ፤ በዚህም ለበርካታ ችግሮች መፍትሄ ማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡ በሃገሪቱ የተጠራቀሙ ፖለቲካዊ ችግሮችም እልባት እያገኙ መሆኑን መረዳታቸውን የጠቆሙት ኃላፊው ፤ ለመጣው ለውጥም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የአመራር ሚና አድናቆት የሚቸረው ነው ብለዋል፡፡ መንግስታቸውም በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተደረጉ ያሉ ለውጦችን በአድናቆት እንደሚመለከተው ጠቁመው፤ ለዘላቂነቱም ድጋፍ ይቸረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵና በኤርትራ መካከል ላለፉት 20 ዓመታት የዘለቁ ችግሮን በሰላም ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያከናወኑት የዲፕሎማሲ ሥራ የሚደነቅና ያልተለመደ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፤ በቀጣይ አፋኝ የሚባሉ አዋጆችን በማሻሻል የፖለቲካ ምህዳሩን የሚያሰፋ ተጨማሪ እርምጃዎች እንዲወስዱም ጠይቀዋል፡፡
ከህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ጋር ተያይዞ “ስለተፈፀመው ከፍተኛ ዘረፋ” ለህዝብ ማብራሪያ እንዲሰጥ የጠየቀው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፤ በዘረፋውና ምዝበራው የተሳተፉ የመንግስት ኃላፊዎች በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡ ለሃገሪቱ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ልማት ዘርፍ ብዙ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ለተደራጀ ዘረፋ ተጋልጦ እንደነበር ከቀረቡ ዘገባዎች መረዳት መቻሉን የጠቆመው አብን፤ መንግስት የፕሮጀክቱ ባለቤት ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ዝርዝር መረጃ መስጠት እንዳለበት ገልጿል፡፡ በግድቡ ግንባታ ወቅት መጓተትን የፈጠሩ፣ በህዝብ ሃብትና ገንዘብ ምዝበራ የተሳተፉ እንዲሁም ምዝበራው ሲፈፀም ማስቆም ሲገባቸው ያላስቆሙ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ተጠያቂ እንዲደረጉ ንቅናቄው ጠይቋል፡፡ በቀጣይም ግልፅ የፋይናንስ ሥርዓት ተዘርግቶ፣ ግንባታው በአስቸኳይ እንዲጠናቀቅ መደረግ አለበት ብሏል አብን ባወጣው መግለጫው፡፡ የግድቡን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግንባታ ኮንትራት የወሰደው ሜቴክ፤ ስራውን በአግባቡ ባለማከናወኑ “ለኪሳራ ተዳርጌያለሁ” ያለው የሲቪል ግንባታ ኮንትራክተሩ ሳሊኒ መንግስትን 3.5 ቢሊዮን ብር እና 338 ሚሊዮን ዩሮ መጠየቁ ይታወቃል፡፡
መቐለ በምጽዋ አገልግሎት መጀመሯ “የአዲስ ዓመት ገጸበረከት ነው” - ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ሰሞኑን በአስመራ ተገናኝተው በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩት የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች፤ በአካባቢው የፀጥታ ጉዳይ ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሶማሊያው ፕሬዚዳንት አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዚደንት ሙሐመድ ፎርማጆ ስለ ውይይታቸው በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ማስታወሻ፤ሶስቱን ሃገራት በኢኮኖሚ ለማስተሳሰርና በፀጥታ ጉዳይም በጋራ ለመስራት ታሪካዊ ስምምነት ተፈርሟል ብለዋል፡፡ የኤርትራ መንግስት በበኩሉ፤ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን በሙሉ አቅሙ ለመጠቀም እንዲያስችላት በሚል ከወደቡ እስከ ቡሬ ከተማ የሚደርስ የ71 ኪሎ ሜትር ዘመናዊ አስፓልት መንገድ መገንባት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ መንገዱ በአንድ ጊዜ አራት ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ አስፓልት መሆኑን የጠቆመው የኤርትራ መንግስት፤ይህም የሁለቱ ሃገራትን የኢኮኖሚ ትስስር ወደተሻለ ደረጃ ያሻግራል ብሏል፡፡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን ለሁለተኛ ጊዜ በኤርትራ ባደረጉት ጉብኝትም “መቐለ” የተሰኘችው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ፣ ከ20 ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ከምፅዋ ወደብ የኤርትራን የወጪ ንግድ እቃ በመጫን፣ ወደ ቻይና ያደረገችውን ጉዞ አስጀምረዋል፡፡ መርከቧ በምጽዋ አገልግሎት መስጠት መጀመሯ በእጅጉ ያስደሰታቸው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ፤ ለመላው
ሰሞኑን ከ15 ዓመታት የውጭ አገር ስደት በኋላ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት የሰብአዊ መብት ተሟጋቹና የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኙ አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ብሔራዊ እርቅና መተማመን ያስፈልጋል አሉ፡፡ አቶ ኦባንግ ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ወደ ሃገር ቤት የተመለሱት በዋናነት የጀመሩትን የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የበለጠ ለማጠናከር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ “ላለፉት 27 ዓመታት ከገባንበት መከፋፈል፣ መጠፋፋትና የጨለማ ጊዜ እየወጣን ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ፤አሁን የሚታየው ለውጥ የብዙዎች ደም ፈሶ፣ በርካቶች ለአካል ጉዳትና፣ ለስደት ተዳርገው ያመጡት እንደመሆኑ፣ ሁሉም ሰው ለውጡ እንዳይቀለበስ ሊጠብቀው ይገባዋል” ብለዋል፡፡ “ሰው መሆናችን ብቻ በቂ ነው፤ ደማችን አንድ ነው” ያሉት የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ፤ በዘር መከፋፈል ቀርቶ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር መሰባሰብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ “ከገባንበት የጐጠኝነት ፖለቲካ ወጥተን ወደተሻለው አገራዊ አንድነት አስተሳሰብ መሻገር አለብን” ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚሉ ወገኖች በሙሉ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው፣ “ቀጣይዋ ኢትዮጵያ ምን ትምሰል? ምን አይነት ኢትዮጵያን ነው ለአዲሱ ትውልድ የምናሻግረው?” በሚለው ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት ማድረግና መወሰንም እንደሚገባ አሳስበዋል - አቶ
ነገ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ 250 አመራሮች ይገባሉ ነገ ማለዳ አዲስ አበባ ለሚገቡት የ”አርበኞች ግንቦት 7” ንቅናቄ አመራሮች፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የመዲናዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ያደርጉላቸዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን መዲናዋ ለዚሁ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት፣በባንዲራና በፖስተሮች ደምቃለች፡፡ ለአመራሮቹ የሚደረገው አቀባበል ከጠዋቱ 12፡30 እስከ ቀኑ 9 ሰዓት በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚፈፀምም ታውቋል፡፡ የንቅናቄው አመራሮች ከሚኖሩባቸው የተለያዩ የአሜሪካና አውሮፓ ሃገራት በተለያዩ በረራዎች ከጠዋቱ 12፡30 ጀምሮ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚደርሱ ለአዲስ አድማስ የጠቆሙት የአቀባበል ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፤ ሁሉም አመራሮች ከገቡ በኋላ ዋናው የአቀባበልና የዕርቅ ማብሰሪያ ሥነ ሥርዓት ወደ ሚካሄድበት አዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚያመሩ አስታውቀዋል፡፡ በነገው ዕለት በመላው ዓለም የሚገኙ የንቅናቄው አመራሮች ተጠናቀው ወደ ሃገር ቤት እንደሚገቡ ያመለከቱት አስተባባሪው፤ ንቅናቄውም ቀደም ሲል ሲያራምድ የነበረውን በትጥቅ የታገዘ ሁለገብ ትግል ፈትሾ፣ በሃገር ውስጥ በሠላማዊ መንገድ ለመታገል የሚያስችለውን ስትራቴጂ ነድፏል ብለዋል፡፡ በቅርቡም ንቅናቄው በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ለምርጫ ውድድር እንደሚቀርብ የጠቆሙት አቶ ብርሃኑ፤ ወደ ሃገር ቤት
- ተቃዋሚዎች ስድስት አንቀፆች እንዲሠረዙ ጠይቀዋል - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የመድረክ አመራሮችን ሊያነጋግሩ ነው ለበርካታ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች እስር ምክንያት የሆነው የፀረ ሽብር አዋጅ እንደሚሻሻል መንግስት ያስታወቀ ሲሆን ተቃዋሚዎች ስድስት አንቀፆች ከአዋጁ ላይ ሙሉ ለሙሉ እንዲሠረዙ ጠይቀዋል፡፡ የፀረ ሽብር አዋጁ ማሻሻያ በህግ ባለሙያዎች እየተሠራ መሆኑን የገለፀው መንግስት፤ ሊካተቱ የሚችሉ አዳዲስ አንቀፆችም ይኖራሉ ተብሏል። ተቃዋሚ ፓርቲዎችም አምስት አንቀፆች እንዲጨመሩ፣ ስድስት ነባር አንቀፆች እንዲሠረዙና አራት አንቀፆች ማሻሻያ እንዲደረግባቸው የጠየቁ ሲሆን ኢህአዴግም በአብዛኛው መስማማቱ ታውቋል፡፡ ይሠረዛሉ ተብለው ከሚጠበቁት አንቀፆች መካከል አንቀፅ 14 ላይ የተደነገገው “ተጠርጣሪዎች አሻራ በግዳጅ መስጠት” የሚለውን ጨምሮ የግለሠቦችን ስልክና ማናቸውንም የግንኙነት አውታር የመጥለፍ ስልጣን ለደህንነት ሃይሉ የሚሠጠው አንቀፅ ይገኝበታል፡፡ በፀረ ሽብር አዋጁ ይሻሻላሉ ተብለው ከሚጠበቁት አንቀፆች መካከልም የቅጣት አወሣሠን ጉዳይ ይገኝበታል፡፡ ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚዎች ባደረጉት ድርድር ላይ በአዋጁ ከእድሜ ልክ እስከ ሞት የተደነገገው የቅጣት ደረጃ ተሻሽሎ፣ “አንድ በእስር የሚፈረድበት ሰው ከ10 ዓመት በማይበልጥ እስራት ብቻ እንዲቀጣ” የሚለው ሃሣብ ጎልቶ መውጣቱ ታውቋል፡፡በአዋጁ
ሁሉም አፍሪካውያን ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት እድል ሊመቻች እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለፁ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሰሞን በኢትዮጵያ የ2 ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ካደረጉት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በነበራቸው ውይይት፣ ሩዋንዳ ሁሉም አፍሪካውያን ያለ ቪዛ ወደ ሃገሯ እንዲገቡ ያስተላለፈችውን ውሣኔ አድንቀው፣ ኢትዮጵያም በቅርቡ የሩዋንዳን በጎ ተሞክሮ ትከተላለች ብለዋል፡፡ የአፍሪካ መዲና ወደ ሆነችው አዲስ አበባ፣ አፍሪካውያን ያለ ቪዛ እንዲገቡ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሃገሪቱን የቱሪስት ፍሠት የሚጨምር ከመሆኑም በላይ ለኢኮኖሚዋም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም አፍሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ቪዛ እንዳይጠየቁ ሊደረግ እንደሚችል ከመጠቆማቸው ውጭ እንዴትና መቼ ተግባራዊ ይደረጋል በሚለው ላይ ያሉት ነገር የለም፡፡
ሠኞ ከንቲባው ቅሬታ አቅራቢዎችን ያነጋግራሉ በከተማዋ በሁለት አመት ውስጥ 36 ሺህ ህገወጥ ቤቶች ፈርሠዋል በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሃና ማርያም አካባቢ ከሁለት አመት በፊት “ህገ ወጥ ናችሁ” በሚል ቤት ለፈረሠባቸው ነዋሪዎች የአዲስ አበባ አስተዳደር መፍትሄ እንዲሠጥ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አሣሠበ፡፡በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 እና ወረዳ 11 ውስጥ በሚገኙ ቀርሳ ኮንቶማ፣ ማንጎ በሚባሉ አካባቢዎች ቤታቸው በሃይል የፈረሠባቸው ዜጎች፤ ላለፈው አንድ አመት ተኩል ለአስተዳደሩ አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ ቢቆዩም ምላሽ ባለማግኘታቸው፣ በሠላማዊ ሠልፍና በደብዳቤ ከሠሞኑ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢ፤ የቅሬታ አቅራቢዎቹን ተወካዮች ከትናንት በስቲያ በፅ/ቤታቸው ያጋገሩ ሲሆን እስካሁን መፍትሄ ሳያገኙ መንገላታታቸው ተገቢ አለመሆኑንና አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመው፤ ለዚህም ከንቲባው ከነገ በስቲያ ሠኞ ግንቦት 27 ቀን 2010 ዓ.ም አቤቱታ አቅራቢዎቹን ሰብስበው እንዲያነጋግሩ ቀጠሮ ማስያዛቸውን እንደነገሯቸው ተወካዮቹ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከሁለት አመት በፊት በከተማዋ የሚገኙ 36 ሺህ ህገ ወጥ ቤቶችን ማፍረሡን በመግለፅ፤ ለዚህ
ከአንድ ወር በኋላ በሰሜን አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ፣ ለ35ኛ ጊዜ በሚካሄደው በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለመገኘት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም ተባለ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሣምንት በፊት ለስፖርት ፌስቲቫል አዘጋጁ ፌዴሬሽን፤ “በፕሮግራማችሁ ላይ ከኢትዮጵያውያን ጋር ልገናኝ” የሚል ደብዳቤ መፃፋቸው የታወቀ ሲሆን ፌዴሬሽኑም ይገኙ አይገኙ የሚለውን የወሠነው በአባላቱ ድምፅ ነው ተብሏል፡፡ 14 የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት “ዶ/ር አብይ መገኘት የለባቸውም” የሚል ድምፅ ሲሠጡ፣ “11 ደግሞ ይገኙ” ብለዋል፡፡ 8 ድምፀ ተአቅቦ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ ፌዴሬሽኑ በድረ ገፁ በሠጠው መግለጫ፤ “አብዛኛው አመራር አይገኙ የሚል ውሣኔ ያሣለፉት እንዳይገኙ ከመፈለግ ሣይሆን ጥያቄው የቀረበበት ጊዜ አጭር በመሆኑ፣ ሁኔታዎች አገናዝቦ ለመወሰን አመቺ ባለመሆኑ ነው” ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፤ በቀጣይ በሚደረገው ተመሣሣይ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የመገኘት እድል እንዲሰጣቸው መመቻቸቱንና ጥያቄያቸው ለቀጣይ መሸጋገሩንም ፌደሬሽኑ አስታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ በሠሜን አሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሚሰባሰቡበት የስፖርት መድረክ ላይ ልገኝ ብለው የጠየቁ
የመሬት መንሸራተት አስጊ ሆኗል በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እየጣለ ባለው መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ በሆነ ዝናብ ምክንያት በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት 39 ሰዎች መሞታቸው የታወቀ ሲሆን በቀጣዩ ክረምት 1.5 ሚሊዮን ዜጎች ለጎርፍ አደጋ ተጋልጠዋል ተባለ፡፡ ከሠሞኑ በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን፣ ከባድና ተከታታይ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት 7 ሰዎች፣ በደቡብ ክልል ጋሞ ጎፋ በተመሣሣይ አደጋ ዘጠኝ ሰዎች እንዲሁም በደቡብ ክልል በሲዳማና በአርሲ ዞን አዋሳኝ አካባቢ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉን፣ ከፌደራል የአደጋ መከላከልና ስጋት አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህ ሁኔታ በቀጣይ ምን መልክ ይኖረዋል በሚለው ጉዳይ ለአዲስ አድማስ መረጃ የሰጡት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሣ፤ በሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት የመሬት መንሸራተት አንዱ የአደጋ ዘርፍ እየሆነ ነው ብለዋል፡፡ ችግሩም አሣሣቢ ደረጃ መድረሡን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ የሰዎች ህይወትም እየቀጠፈ ነው ብለዋል፡፡ ለመሬት መንሸራተት አስጊ እየሆነ መምጣት በአካባቢ ጥበቃ ጉድለት ደን መራቆት መከሠቱ፣ ሠዎች ተዳፋታማ አካባቢዎች መስፈር መጀመራቸው እንዲሁም የአፈር አይነት ምክንያት መሆናቸውን አቶ ምትኩ ለአዲስ
ከ50 በላይ አመራሮቹና አባላቱ በትግራይ ክልል በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ታስረው እንደሚገኙ የገለፀው አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉአላዊነት (አረና) ፓርቲ፤ የክልሉ መንግስት እስካሁን ዋነኛ የፖለቲካ ሰዎችን ከእስር አለመልቀቁን አስታወቀ፡፡ በቅርቡ ከ2 ሺህ በላይ እስረኞች በክልሉ መለቀቃቸውን ያስታወሡት የፓርቲው ም/ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ፤ ከተለቀቁት መካከል አንድም ፖለቲከኛ አለመኖሩን ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ከ50 በላይ የሚሆኑ በፓርቲው ውስጥ ሠፊ ተሣትፎ የሚያደርጉ አባላትና አመራሮች በተለያየ ሰበብ በእስር ላይ እንደሚገኙ የገለፁት አቶ ጎይቶም፤ ፓርቲያቸው ታሣሪዎች እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ቀና ምላሽ አለማግኘቱን ጠቁመዋል፡፡ ከፓርቲው አባላት በተጨማሪም መሠረቱን ኤርትራ አድርጎ፣ የኢትዮጵያን መንግስት በመቃወም ከሚንቀሳቀሰው የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የታሠሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች ከእስር አለመፈታታቸውን አቶ ጎይቶም አስታውቀዋል፡፡
- “ኢትዮጵያ እንዲህ ይቅር ባይ መሪ ያስፈልጋታል” - ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ- “የኢትዮጵያ ትንሣኤ መቅረብ ምልክት ነው” - ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ- “ይህቺ ሃገር ሊያልፍላት ይሆን እንዴ?” - ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሃይሉ ከእስር የተፈቱት የአርበኞች ግንቦት 7 ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተገናኝተው መወያየታቸው ብዙዎችን ያስደሰተ ሲሆን የአውሮፖ ህብረትና የእንግሊዝ መንግስት የሚበረታታ እርምጃ ነው፤ እንደግፈዋለን ብለዋል፡፡ ማክሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2010. ዓ.ም ከ4 ዓመት እስር በኋላ በይቅርታ ተፈትተው ቤተሠቦቻቸውን የተቀላቀሉት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፤ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡በውይይታቸውም የተለያዩ ፖለቲካዊና ሃገራዊ ጉዳዮች መነሣታቸውን በጥቅሉ የገለፁት አቶ አንዳርጋቸውም የተወያዩባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በብሄራዊ ቤተ መንግስት የተነሱትና በጠ/ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ድረገፅ የወጣው ፎቶ ግራፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች ከተሠራጨ በኋላ በርካቶች የተሠማቸው ደስታ ገልፀዋል፡፡የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህሩና የመብት አራማጁ ስዩም ተሾመ በፌስ ቡክ ላይ ባሰፈረው አስተያየት፤ የቂም በቀልና
በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ውስጥ የሠብአዊ መብት ጥሰቶችን እየፈፀመ ነው ያለውን የሶማሌ ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ መንግስት በአስቸኳይ እንዲበትን የሠብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ፡፡ አምነስቲ ትናንትና ባወጣው መግለጫው፤ የሶማሌ ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ ተደጋጋሚ የሠብአዊ መብት ጥሠትና ግድያዎችን እየፈፀመ መሆኑን ጠቅሶ፤ ከሠሞኑም በክልሉ 48 ቤቶችን በማቃጠል፣ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ጥለው እንዲሠደዱ አድርጓል ብሏል፡፡ መንግስት ይህን ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ በአስቸኳይ በመበተን፣ ለአለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ተገዥ የሆነ መደበኛ የፖሊስ ሃይል እንዲደራጅ ጠይቋል፡፡ “ከዚህ በኋላ የሶማሌ ልዩ ሃይል አባላት እንዳሻቸው በህዝብ ላይ ግፍ እንዲፈፅሙ መፈቀድ የለበትም” ያለው ተቋሙ፤ “መንግስት ይሄ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያበቃ ማድረግ አለበት” ብሏል፡፡ በአከባቢው ላለው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠትም ልዩ ሃይሉን በማፍረስ፣ የክልሎችን ድንበር በተገቢው ሁኔታ ማካለል ያስፈልጋል ብሏል- አምነስቲ፡፡
ህገ ወጥ ግንባታ ነው በሚል ከሁለት አመት በፊት በአዲስ አበባ ቤታቸው የፈረሠባቸው አስር ሺህ ያህል አባ ወራዎች፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አቤቱታቸውን በደብዳቤ አቀረቡ፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ገቢ በተደረገው የአቤቱታ ደብዳቤ ላይ፤ አባወራዎቹ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፣ ማንጎ ጨፌ ግራር በተባለ አከባቢ በተለያየ አግባብ መኖሪያ ቤት ሠርተው መኖር መጀመራቸው ተገልጿል፡፡ በወቅቱ ነዋሪዎቹ ያለ ማስጠንቀቂያ በቡልዶዘር ቤታቸው በጅምላ እንዲፈርስ ተደርጎ ጎዳና ላይ መበተናቸውን የሚጠቅሰው ደብዳቤው፤ በኋላም በአካባቢው በነበረው የቤቶቻቸው ፍርስራሽ ላይ በላስቲክና በሸራ ድንኳን ወጥረው መኖር እንደጀመሩ ደብዳቤው ይጠቁማል፡፡ ይሁን እንጂ ሠሞኑን (ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 3) ወደ ፕላስቲክ መኖሪያ ቤቶቻቸው እንዳይገቡ ተከልክለው ሜዳ ላይ መውደቃቸውን፤ ልጆቻችውም ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀላቸውን አቤቱታ አቅራቢዎቹ ገልፀዋል፡፡ህብረተሠቡ መብቱን ሲጠይቅ በዱላ እየተደበደበ ይታሠራል የሚሉት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፤ የውጭ ሃገር ስደተኞችን ተቀብላ በክብር የምታኖር ሃገራችን፣ እንዴት ለኛ ለዜጎቿ ቦታ ታጣለች ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ በ2005 ዓ.ም ገንዘብ አዋጥተን፣ መንገድ፣ መብራትና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ
የግል ኩባንያዎች የሙስና ክስም ተቋርጧል ከአምስት አመት በፊት በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት የገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ፣ ምክትላቸው አቶ ገብረዋህድ ገ/ጊዮርጊስና ባለቤታቸው ኮ/ል ሃይማኖት ተስፋዬን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ክሳቸው ተቋረጠ፡፡ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክሱን ያቋረጠው የግንቦት 20ን በአል ምክንያት በማድረግ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ክሣቸው ከተቋረጠላቸውም መካከልም አቶ መላኩ ፋንታ፣ አቶ ገብረዋህድ ገ/ጊዮርጊስ እንዲሁም አብረዋቸው ታስረው የነበሩት የነፃ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሄር፣ የኬኬ ኩባንያ ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ፣ የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤት አቶ ስማቸው ከበደ እንዲሁም ባለሃብቱ አቶ ጌቱ ገለቴና፣ አቶ ገብረስላሴ ገብሬ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በቅርቡ ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የኢሊሊ ሆቴል ባለቤት አቶ ገምሹ በየነም ክሳቸው ተቋርጧል፡፡ ከባለስልጣናትም የኢንዱስትሪ ሚ/ር ዴኤታ የነበሩ አቶ አለማየሁ ጉጆ፣ አቶ ዋሲሁን አባተ፣ አቶ አክሎክ ደምሴ፣ አቶ ዛይድ ወ/ገብርኤል (የቀድሞ የመንገዶች ባለስልጣን ዳይሬክተር)፣ አቶ መስፍን ወርቅነህ፣ ወ/ሮ ሰኙን ጎበና፣ አቶ ጌታቸው ነገሪ፣ አቶ ነጋ መንግስቱና አቶ ሙሣ መሃመድ ክሳቸው ተቋርጧል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም ጂኤች
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መውጣቱን ተከትሎ፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከተቃውሞ ጋር በተያያዘ ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ከ2ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኮማንድ ፖስት፣ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች 1600 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በአማራ ክልል፣ ጎንደር 93 ሰዎች በገዛ ፍቃዳቸው እጃቸውን ለፖሊስ ሰጥተዋል ብሏል - ኮማንድ ፖስቱ፡፡ በሰበታ ከተማ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ላይ ለደረሰው ቃጠሎና ውድመት እጃቸው አለበት የተባሉ 1 ሺ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ባለፈው ሳምንት ፖሊስ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ ብቻ 450፣ በአካባቢው ባሉ ወረዳዎች 670 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የገለጸው ኮማንድ ፖስቱ፤ በቄለም ወለጋ ዞን 110 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብሏል። በኦሮሚያ ከተዘረፉት 513 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች 384 ያህሉ መመለሳቸውን አመልክቷል፡፡ ሌሎች በግጭቱ ወቅት የተዘረፉ የመንግስትና የግለሰብ ንብረቶችም በስፋት እየተመለሱ ነው ብሏል - ኮማንድ ፖስቱ፡፡ በአማራ ክልል በጎንደር ከተማና አካባቢው “ሸፍተው” ጫካ የገቡና ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ከነበራቸው መካከል 93 ሰዎች እጃቸውን የሰጡ
በቴሌኮም ማስፋፋትና በኔትወርክ ዝርጋታ ስራ የተሰማራው ህዋዌ፤ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለ‹‹መሰረት በጎ አድራጎት›› ድርጅት የትምህርት መሳሪያ ድጋፍ አደረገ፡፡ ድርጅቱ 4500 ደብተሮችን፣ 1500 እርሳሶችን፣ 1500 እስክርቢቶዎችንና ላጲሶችን ለግሷል፡፡ በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት አዛገ ህዋዌ ስላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፣ ድጋፉ ‹‹አንድ እሽግ ለአንድ ልጅ›› በሚል የሚያካሂዱትን የትምህርት ቁሳቁሶች አቅም ለሌላቸው የማከፋፈል ፕሮጄክት፣ በእጅጉ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ ከህዋዌ ያገኙት ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከ50 ሺህ ብር በላይ እንደሆነ የገለፁት ወ/ሮ መሰረት፤ ድጋፉ ሌሎችም ድርጅቶች ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መነቃቃትን ይፈጥራል ብለዋል፡፡ከድጋፉ ጎን ለጎን መሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት የተመሰረተበትን አምስተኛ ዓመት ያከበረ ሲሆን በአምስት አመት ጉዞው ያከናወናቸውን፣ ያሳካቸውንና ያለፋቸውን ፈተናዎች በዘጋቢ ፊልም ለታዳሚዎቹ አቅርቧል፡፡ የህዋዌ ተወካዮችም ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ በዕለቱ ቃል ገብተዋል፡፡ በመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት ጽ/ቤት በተካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ ድርጅቱ አምባሳደር አርቲስት ሩታ መንግስተአብና አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ የውጭ አገር ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ የመጓዝ ፍላጎታቸው በእጅጉ መቀነሱን የገለፁ አስጎብኚ ድርጅቶች፤ ለችግሩ መላ ካልተገኘ አዋጁ በቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ተናገሩ፡፡ ‹‹አገር የማስጎብኘት ሥራ እንደ ማኑፋክቸሪንግ አይደለም፤ አንድ ፋብሪካ ቢቃጠል ወይም ሌላ ጉዳት ቢደርስበት በዓይን ይታያል። የቱር ኦፕሬሽን ሥራ፣ አገልግሎት ስለሆነ ጉዳት ሲደርስበት በዓይን አይታይም፡፡ አሁን በአገሪቱ በተፈጠረው ችግር ሳቢያ ዘርፉ ጉዳት ደርሶበታል›› ብለዋል፤ የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት፤ አቶ ያዕቆብ መላኩ፡፡አስጎብኚ ድርጅቶች ከመስከረም ጀምሮ እስከ ታህሳስ፣ ጥርና የካቲት ያሏቸውን ገበያዎች ሸጠው እንደጨረሱና ደንበኞችም ክፍያ መፈጸማቸውን ጠቅሰው፣ ለሆቴሎችና ለሌላ አገልግሎት አቅራቢያዎችም ክፍያ መፈፀማቸውን ይገልፃሉ። ሆኖም በተፈጠረው ችግር ምክንያት ቱሪስቶች ወደ አገራችን ለመምጣት ፍላጎት አላሳዩም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ አንዳንድ ቱሪስቶች የከፈሉት እንዲመለስላቸው እየጠየቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ የጉዞ አማካሪዎችና ኤምባሲዎች የሚያሰራጩት ወደ ክልከላ ያደገ ማስጠንቀቂያ፣ ለጉብኝት ፕሮግራሞች መሰረዝ ዋነኛ ምክንያት እንደሆኑ የጠቀሱት አቶ ያዕቆብ፣ ‹‹አንዴ ፕሮግራም አድርጌአለሁ፤ ሄጄ ያለውን ነገር አያለሁ›› ብለው የሚመጡ ጥቂት ቱሪስቶች ቢኖሩም
“የሰመጉን ሪፖርት አንቀበልም አላልንም” ባለፈው ጥቅምት 5 ቀን 2009 ዓ.ም ታትሞ በወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ከሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ብፅአተ ተረፈ ጋር በተደረገው ቃለ ምልልስ፤ ‹‹ከፕሬዚዳንቱ ፅ/ቤት ሁለተኛ ሪፖርታችሁን ወደ ፅ/ቤታችን እንዳትልኩ ተብለናል›› ሲሉ የተናገሩት የፕሬዚዳንቱን ፅ/ቤት ስም የሚያጠፋና ፈፅሞ ያልተባለ ነገር ነው፤ አንድም ቀን ሪፖርታችሁን አንቀበልም ብለናቸው አናውቅም፤ ልንልም የምንችልበት ምክንያት የለንም፡፡ የፕሬዚንዳንቱ ፅ/ቤት ሁሉንም የሃገሪቱን ዜጎችና ተቋማት በእኩልነት የሚያገለግል ተቋም ነው፡፡ አቶ አለምነህ ረጋሳ የፕሬዚዳንቱ የፅ/ቤት የፕሮቶኮልና ኮሚኒኬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፡፡
ለሚዲያዎች መስፋፋትና እድገት ማነቆ ሆኗልበሃገሪቱ ያለው የህትመት ኢንዱስትሪ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ መሆኑን አንድ ጥናት ያረጋገጠ ሲሆን ለሚዲያዎች መስፋፋትና እድገትም ማነቆ እየፈጠረ ነው ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ አሳታሚዎች አታሚዎች ማህበር ከትናንት በስቲያ በሸራተን አዲስ ሆቴል ባዘጋጀው የግማሽ ቀን ወርክሾፕ ላይ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር የቀድሞው ፕሬዚዳንት በአቶ ጌታቸው በለጠ የቀረበ ጥናት እንዳመለከተው፤መንግስት ለህትመት ኢንዱስትሪው ምንም አይነት ድጋፍ ስለማያደርግ ዘርፉ ከማደግ ይልቅ እየቀጨጨ ነው፡፡ በጥናቱ ላይ ተሳታፊ ከነበሩ የኢንዱስትሪ አንቀሳቃሾች በተሰባሰበ መጠይቅ፣ለህትመት ኢንዱስትሪው የሚደረግ የመንግስት ድጋፍ 0 % መሆኑ ተመላክቷል፡፡ መንግስት በሁለቱም የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዶቹ ኢንዱስትሪውን በተመለከተ ያስቀመጠው እቅድ፣ ጉዳዩን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል ብለዋል - ጥናት አቅራቢው፡፡ የህትመት ኢንዱስትሪው ትልቁ ተግዳሮት፣ ተደራራቢ ታክስ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡ በንጉሡ፣ በደርግና በአሁኑ መንግስት በህትመት ኢንዱስትሪው ላይ የታዩ ለውጦች በጥናቱ የተዳሰሱ ሲሆን በንጉሡ ዘመን የተሻለ የህትመት ኢንዱስትሪ መስፋፋት ታይቶ ነበር ተብሏል፡፡ በተለይ እንደ ማክሚላን ቡክስ፣ ኦክስፎርድ የመሳሰሉ የውጭ ትላልቅ የህትመት ኩባንያዎች በኢንዱስትሪው ተሳታፊ የነበሩ መሆናቸው መልካም አጋጣሚ እንደነበር በጥናቱ ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለሁለት “ሴት ቶፕ ቦክስ” አምራቾች፣ ለሦስት የግል ቴሌቪዥንና ለሦስት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስተር ድርጅቶች ፈቃድ ሰጠ፡፡ ባለፈው ረቡዕ በሸራተን አዲስ በተከናወነው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት፣ “ሴት ቶፕ ቦክስ” ለማምረት ከባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ከአቶ ዘርዓይ አስገዶም ጋር የተፈራረሙት ጣና ኮሙኒኬሽን ኃ.የተ. የግ.ማ እና ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሃይቴክ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ናቸው፡፡ የግል የቴሌቪዥን ብሮድካስት ፈቃድ የተሰጣቸው ሦስት ድርጅቶች፡- ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልና አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ኃ.ተ. የግ.ማ ናቸው፡፡ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ብሮድካስቲንግ ፈቃድ የተሰጣቸው ሦስት ድርጅቶች ደግሞ ኤዲስቴለር ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ (አሐዱ 94.3)፣ አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስና ዋን ላቭ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ኃ.የተ. የግ.ማ (ሉሲ 107.8) ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ናቸው፡፡ በዕለቱ የተሰጠው ሦስት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ፈቃድ፣ አሁን በአዲስ አበባና አካባቢያዋ አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን ሰባት ጣቢያዎች ጋር ቁጥር ወደ 10 እንደሚያደርሰው ታውቋል፡፡ “ሴት ቶፕ ቦክስ” ማለት አሁን ያለው አናሎግ የቴሌቪዥን ስርጭት ወደ ዲጂታል ሲቀየር ስርጭቱን መቀበል የሚያስችል
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መተግበሩን ተከትሎ፣ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ የተደረገው ጥረትና መንግስት ተገዶ ወደ እርቀ ሰላም እንዲገባ በማድረግ፣ በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ የተደረገው ጥረት መክሸፉን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጌታቸው አምባዬ አስታወቁ፡፡ አዋጁ ያስፈለገበትን ምክንያትና እስካሁን ያለውን አፈፃፀም ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ከትናንት በስቲያ በስፋት ያብራሩት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ፤ አዋጁ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ በአገሪቱ ላይ መረጋጋት እየተፈጠረ፣ የሰዎች ደህንነትና ቁሳዊ ሀብቶች ከውድመት እየተጠበቁ ነው ብለዋል፡፡ በተቃውሞ ወቅት በጦር መሳሪያ የታጀቡ ትንንሽ ቡድኖች ራሳቸውን በማደራጀት፣ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ፊት ለፊት ፍልሚያ የጀመሩበት ሁኔታ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጌታቸው፤ ሀገሪቱ የበለጠ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ በማሰብ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጁ ሀገሪቱ የተጋረጠባትን ስጋት እየቀለበሰ ነው ብለዋል፡፡ በኢሬቻ በአል ላይ የተፈጠረውን ግጭትና የህይወት መጥፋት ተከትሎ ከበአሉ የተበተነው ኃይል፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች ሰፍሮ እንደነበር የገለፁት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ፤ የተለያዩ ቡድኖችን በማደራጀት ሃዋሳን፣ አዳማንና አዲስ አበባን ወደ መሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች እንዲገቡ ጥረት ሲደረግ ነበር ብለዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ
ኢትዮ ቴሌኮም “ከደንበኞቼ ቅሬታ አልደረሰኝም” ብሏል በአዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ የኢንተርኔት ካፌ ከፍቶ መስራት ከጀመረ 7 ዓመታት ያስቆጠረው ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ወጣት፤ በየዓመቱ በዚህ ወቅት የአሜሪካን ዲቪ ሎተሪ በማስሞላት ዳጎስ ያለ ገቢ ያገኝ እንደነበር ይናገራል፡፡ ዘንድሮ ግን በከተማዋ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ተከትሎ፣ የተለመደውን አገልግሎት ለደንበኞቼ መስጠት እንዳልቻለ ይገልፃል፡፡ በአማራጭነት የዋይ ፋይ አገልግሎት መስጫ ቢኖረውም በአግባቡ የሚሰራ ባለመሆኑ፣ እንኳን ዲቪ ለማስሞላት ይቅርና የኢንተርኔት አገልግሎት በቅጡ ለመስጠት አዳግቶኛል ብሏል፡፡የኢንተርኔት አገልግሎት በመስጠት ብቻ በቀን በአማካይ ከ300-500 ብር ገቢ ያገኝ እንደነበር የሚናገረው የኢንተርኔት ካፌ ባለቤት፤ የኢንተርኔት መቋረጥ የሥራ ዘርፉን እንዳስቀየረው ይናገራል። “የኮምፒውተር ፅሁፍ፣ መጠረዝና፣ የፎቶ ኮፒ ስራዎችን ብቻ ለመስራት ተገድጄአለሁ” ብሏል። በየአመቱ ጥሩ ገቢ ያስገኝለት የነበረው ዲቪ የማስሞላት ስራም በኢንተርኔት መቋረጥ ሳቢያ መስተጓጎሉን ገልጿል፡፡ የዲቪ አመልካቾች በኢንተርኔት መቋረጥ የገጠማቸውን ችግር በተመለከተ ለአሜሪካ ኤምባሲ ላቀረብነው ጥያቄ፤ ችግሩ ከዲቪ ማመልከቻ ድረ ገፁ ሳይሆን ከኢንተርኔት መንቀራፈፍና መቆራረጥ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል፡፡“አመልካቾች የ2018 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ማመልከቻን በኢንተርኔት
- የወህኒ ቤቱ ጠባቂዎች እስረኞቹ እንዲያመልጡ ትብብር አድርገውላችዋል በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ገብተዋል በሚል በደቡባዊ የመን በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ታስረው የነበሩ 1 ሺህ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ባለፈው ረቡዕ ሌሊት አምልጠው መጥፋታቸውን አንድ የአገሪቱ የደህንነት ሃላፊ ማስታወቃቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡በህገወጥ መንገድ ወደ የመን ገብተዋል በሚል ሻባዋ በተባለቺው የአገሪቱ ግዛት ውስጥ ታስረው ከነበሩትና ወደ አገራቸው ሊመለሱ ከተዘጋጁት 1 ሺህ 400 ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል አንድ ሺህ የሚሆኑት ባለፈው ረቡዕ ሌሊት እስር ቤቱን ሰብረው በመውጣት መጥፋታቸውን ዘገባው ገልጧል፡፡የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ስደተኞቹ እንዲያመልጡ ትብብር እንዳደረጉላቸው ተረጋግጧል ያለው ዘገባው፤ ስደተኞቹ በተቀናበረ መንገድ ካመለጡ በኋላም በተዘጋጀላቸው መኪና በቡድን በቡድን እየሆኑ በአቅራቢያ ወደሚገኙት ማሪብ እና ባይዳ የተሰኙ ግዛቶች መሄዳቸውን አስታውቋል፡፡ የየመን መንግስት ባለፈው ወር ብቻ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ገብተዋል በሚል ከ220 በላይ አፍሪካውያን ስደተኞችን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ አገራቸው እንደመለሰ ያስታወሰው ዘገባው፤ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ጠቁሟል፡፡
(ወ/ሮ ሂክማ ኬይረዲን፤ የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ) የችግሩ ምክንያት በዲላ የንግዱ ማኅበረሰብና የጌዴኦ ዞን ሕብረት ሥራ ዩኒየን መካከል የቦታ ይገባኛል ክርክር ነበር፡፡ ባለፉት ጊዜያት ፍ/ቤቱ አክራክሮ ውሳኔም አስተሳልፎ ወደ አፈፃፀም ሂደት ሊገባ ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ቦታው ለዩኒየኑ ይገባል በሚል የተወሰኑ አካላት ማኅበረሰቡን አነሳስተው በንግዱ ማኅበረሰብ ላይ ጉዳት ደርሷል። የፍ/ቤቱን ውሳኔ መነሻ አድርጎ ነው ግጭቱ የተከሰተው፡፡ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ ንብረትም ወድሟል፡፡ 23 ሰዎች ሞተዋል፤ ቤት ንብረት የተቃጠለባቸውና የወደመባቸው አሉ፤ ጉዳቱ ሰፊ ነው፡፡ በዚሁ ሂደት መካከል ችግሩ ሲከሰት ደንግጦ ከቤቱ የወጣ፤ ቤትንብረቱ ሲቃጠል ከቤቱ የወጣ ሰው አለ፡፡ አንዳንድ ሰዎች የብሔር ግጭት ነው ይላሉ፡፡ ግን አይደለም፡፡ ጉዳቱ የደረሰው ከአካባቢው ብሔረሰብ ውጭ ብቻ አይደለም፡፡ ከአካባቢው ተወላጅ ሕይወቱ ያለፈ አለ፡፡ ስለዚህ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ብለን ነው መውሰድ የሚቻለው፡፡ የንግዱ ማኅበረሰብ ውስጥም የአካባቢው ተወላጆች አሉ፡፡ ንብረታቸው የወደመው የሁሉም ነው፡፡ ስለዚህ ግጭቱ የተወሰነ ብሔረሰብ ላይ በፍፁም ያነጣጠረ አይደለም፡፡ ለተጠቂዎቹ ቀድሞ የደረሰላቸውና ሕይወታቸውን
የቀብር ስነ ስርአታቸው ባለፈው ማክሰኞ በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለተፈፀመው አንጋፋው ፖለቲከኛ ኢ/ር ኃይሉ ሻወል በመኢአድ ፅ/ቤት በነገው እለት የመታሰቢያ ዝግጅት ይደረጋል። በመታሰቢያ ዝግጅቱ ላይ የፓርቲ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ ፖለቲከኞችን ጨምሮ የስራ አጋሮቻቸውና ቤተሰቦቻቸው እንደሚገኙ ከመኢአድ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። ነገ እሁድ ከ8 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው የመታሰቢያ ስነ ስርአት ላይ ኢ/ር ኃይሉ ሻወል፤ በተለይ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ባበረከቱት አስተዋፅኦ ላይ ሶስት ምሁራን ፅሁፍ አቅርበው ውይይት ይደረጋል ብለዋል፤ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አደና ጥላሁን፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ የስነ ፅሁፍ ፕሮግራሞችም እንደሚካተቱና ከ200 በላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
- የሰዓት እላፊ ተግባራዊ የሚሆንባቸው ቦታዎች አሁንም ይፋ አልተደረጉም- በሁከቱና ብጥብጡ ተሳታፊ የሆኑ ሰዎችን በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ እንደጥፋታቸው መጠን እርምጃ የመውሰድ ሥራ ይሰራል - በስራ ማቆምና በቤት ውስጥ መቀመጥ አድማዎች ላይ ተሳታፊ መሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስቀጣል- በኢንተርኔት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች፣ በአፍራሽ ተግባር ላይ ተሰማርተው የቆዩ በመሆኑ ገድቦ ማቆየቱ ተገቢ ነውየሰዓት እላፊ ተግባራዊ የሚሆንባቸው ቦታዎች አሁንም ይፋ አልተደረጉም በሁከቱና ብጥብጡ ተሳታፊ የሆኑ ሰዎችን በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ እንደጥፋታቸው መጠን እርምጃ የመውሰድ ሥራ ይሰራል በስራ ማቆምና በቤት ውስጥ መቀመጥ አድማዎች ላይ ተሳታፊ መሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስቀጣል በኢንተርኔት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች፣ በአፍራሽ ተግባር ላይ ተሰማርተው የቆዩ በመሆኑ ገድቦ ማቆየቱ ተገቢ ነው በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተነሳውን ተቃውሞና አመፅ ተከትሎ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የማስፈፀሚያ ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት ማውጣቱ ተገለፀ፡፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ
መንግስት ድርጊቱ ከአዋጁ መንፈስ ጋር አይገናኝም ብሏልየአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ የግል ማተሚያ ቤቶች፤ ጋዜጣና መፅሄት አናትምም በማለታቸው ህትመታቸው መስተጓጎሉን የ “ኢትዮ ምህዳር” ጋዜጣ እና “የሀበሻ ወግ” መፅሄት አሳታሚዎች ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአጠቃላይ አቃቤ ህግ ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ሃይማኖት ከሃይማኖት፣ ብሄርን ከብሄር የሚያጋጩና አመፅና ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ፅሁፎችን ማተም፣ ማሳተምና ማሰራጨት ሊከለከል ይችላል መባሉን መነሻ በማድረግ የግል ማተሚያ ቤቶች በተለይ ፖለቲካ ነክ ፅሁፎች ያሉባቸውን ጋዜጦች አናትምም ማለታቸውን አሳታሚዎቹ ተናግረዋል፡፡ ዘወትር ቅዳሜ ታትሞ የሚወጣው ሳምንታዊው “የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ባለቤት አቶ ጌታቸው ወርቁ፤ ቀድሞ ጋዜጣው ይታተምበት የነበረውን ማተሚያ ቤት ጨምሮ ከ3 በላይ ማተሚያ ቤቶች አዋጁ እንዳስፈራቸው በመግለፅ፣ ለማተም ፍቃደኛ እንዳልሆኑላቸው አስረድቷል፡፡ አዋጁ ገና ዝርዝሩ ወጥቶ እንዳልፀደቀና ጋዜጣቸው በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚሰራ ሚዲያ መሆኑን በመግለፅ ማተሚያ ቤቶቹን ለማግባባት ሞክረው እንደነበር የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፤ ማተሚያ ቤቶቹ ግን ፍቃደኛ ሊሆኑ እንዳልቻሉ ገልፀዋል፡፡ ማተሚያ ቤቶቹ ጋዜጣውን አናትምም ማለታቸውን ተከትሎ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ወዳሏቸው
“ነፃና ትችት ያዘሉ ድምፆችን ማፈንና ማሰር በራስ ላይ ውድቀትን መጋበዝ ነው” በቅርቡ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞና አመፅ ተከትሎ መንግስት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በእጅጉ እንዳሳሰባትና አዋጁ በዚህ ሁኔታ ተፈፃሚ የሚሆን ከሆነ ለተቀሰቀሰው የፖለቲካ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት እንደማያስችል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታወቁ፡፡ ቃል አቀባዩ ጆን ኪርቢ ከትናንት በስቲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያ መንግስት መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች የማይጥስ መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎችን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሰርና የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋት ጨምሮ ሃሳብን የመግለፅ ነፃነትን መገደብ፣ ህዝባዊ ስብሰባን መከልከል፣ የሰዓት እላፊ ገደብን መጣል እንዲሁም የመናገር መብትን መገደብ የመሳሰሉ ተፅዕኖዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ የቃል አቀባዩ መግለጫ ያመለክታል፡፡ የተቃውሞ ሰልፈኞቹና የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ተገቢ የሆኑ ብሶቶች ማዳመጥና ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው ያለው መግለጫው፤ መንግስት የዜጎቹን መብት እንዲያከብር፣ ህገ-መንግስቱ ያረጋገጠውን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅና የመደራጀት መብት እንዲያረጋግጥ እንዲሁም መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መስራችና ፕሬዚዳንት እንዲሁም በ97 ምርጫ የቅንጅት ሊቀመንበር የነበሩት አንጋፋው ፖለቲከኛ ኢ/ር ሃይሉ ሻወል በ80 አመታቸው ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል አስክሬናቸው ዛሬ አዲስ አበባ የሚገባ ሲሆን፡፡ የቀብር ስነስርዓታቸው መቼ እንደሚፈፀም አልተወሰነም ተብሏል፡፡ ኢ/ር ሀይሉ ሻወል በ1997 ምርጫ ማግስት በተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ታስረው ከተፈቱ በኋላ የጀርባና የእግር ህመምን ጨምሮ በተለያዩ ህመሞች ሲሰቃዩ እንደነበር ያስታወቀው ፓርቲያቸው፤ በተለይ ላለፉት ሁለት ዓመታት ህመማቸው ፀንቶ በታይላንድ ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ትናንት እዚያው ታይላንድ አርፈዋል ብሏል፡፡ ኢንጀነር ኃይሉ በ1984 ዓ.ም የመላው አማራ አንድነት ድርጅትን (መአዕድ) ከፕሮፌሰር አስራት ወ/የስ ጋር በመሆን ከመሰረቱ በኋላ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ለ10 ዓመት መርተውታል፡፡ መአዕድ ወደ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በ1995 (መኢአድ) ከተቀየረ በኋላ እስከ 2005 ዓ.ም ለ10 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ማገልገላቸው ይታወቃል። በ1997 አራት ድርጅቶች ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ የተሠኘውን ስብስብ ሲፈጥሩ ኢ/ር ሃይሉ ሊቀ መንበር በመሆን ከምርጫ ጋር ተያይዞ ለተለያዩ አለማቀፍ መገናኛ ብዙሃን በሚሠጧቸው መግለጫዎች የሚታወቁ ሲሆን ከታሰሩት የቅንጅት
የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ነው- ትላንት በአርሲ - ኦጄ፣ ከ30 በላይ ሰዎች ሞተዋል በኢሬቻ በዓል ላይ በደረሰው እልቂት በተቀሰቀሰው ቁጣ ምክንያት ሳምንቱን በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ከፍተኛ ተቃውሞና ግጭት ተከስቶ የበርካቶች ህይወት ጠፍቷል፡፡ በትላንትናው ዕለት በአርሲ ነገሌና አርሲአጄ አካባቢ፣ በተከሰተ ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ “በክልሉ በዚህ ሳምንት የሞቱ ሰዎችን በተመለከተ የሚደርሱን መረጃዎች አስደንጋጭና እርስ በእርስ የማይጣጣሙ ናቸው” ያለው የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ (ኦፌኮ)፤ የበለጠ ማጣራት “አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘነው ቁጥሩን ከመግለፅ እንታቀባለን” ብሏል፡፡ በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች በተነሳው ግጭት የሞቱ ሰዎችን አስመልክቶ ከክልሉ መንግስት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ ወርቁ ጫላ ያገኘነው መረጃ፤ ከሰኞ ጀምሮ በተለያዩ ወረዳዎች በተፈጠሩ ሁከቶች የፀጥታ አካላትን ጨምሮ የዜጎች ህይወት መጥፋቱን ቢገልፅም የሟቾች ቁጥርን ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል፡፡ የቢሾፍቱ እልቂት የቀሰቀሰው ቁጣ፤ በምዕራብ ጎጂ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በሆሮጉድሩ፣ ጊምቢ፣ በጅማ፣ በቦረና ያቤሎ፣ በቡሌ ሆራ፣ በምስራቅ ሀረርጌ፣ በአምቦ፣ ወሊሶ፣ በዝዋይ፣ በአርሲ -ነገሌና አርሲአጄ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ውስጥ
“ለደህንነታችን ዋስትና የሚሰጠን አካል የለም” ባለሀብቶች- “ቢሻን ጋሪ ሎጅ” ላይ በደረሰው ዘረፋና ቃጠሎ ፖሊስ ጥቃቱ እንዳይደርስ ከመከላከል ተቆጥቧል- ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ፍርድ ቤቶች፣ ማዘጋጃ ቤቶችና የመንግስት ተቋማት ወድመዋልበኢሬቻ በዓል አከባበር ወቅት የተከሰተውን የበርካቶች ህልፈተ ህይወት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ተቃውሞና አመፅ እያደረሰ ያለው የንብረት ውድመት ከመንግስት ጥበቃና ቁጥጥር ውጪ እየሆነ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት በክልሉ የተለያዩ ስፍራዎች በተቀሰቀሰው ተቃውሞና አመፅ በቢሊዮን ብሮች የሚቆጠር ንብረት ወድሟል ተብሏል፡፡ ሰሞኑን በቡራዩ፣ በሰበታ፣ በአዋሽ መልካሳ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በአለምገና እና ሌሎች የኦሮሚያ ክልሎች በተቀሰቀሰው ተቃውሞ፣ በሚሊዮኖች በሚቆጠር ገንዘብ የተቋቋሙ ፋብሪካዎች፣ የህዝብና የጭነት ማመላለሻ መኪኖች፣ የመንግስት ተቋማት፣ ፖሊስ ጣቢያዎችና የአበባ እርሻዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡ በላንጋኖ አካባቢ በ100ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ በተገነባው ቢሻን ጋሪ ሎጅ ባለፈው እሮብ በደረሰበት ዘረፋና ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋትም ሆነ ንብረቱን ከአደጋ ለመከላከል የተደረገ ሙከራ አለመኖሩ ተስፋ እንዳስቆረጣቸው የድርጅቱ ባለቤት አቶ ዑመር ባገርሽ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡ ሎጁ ላለፉት 17
የጀርመን መራሄ መንግስት አንጌላ መርኬል ማክሰኞ አዲስ አበባን እንደሚጎበኙና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ከስደት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የፊታችን ዘግቧል፡፡ከሶስት የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር በስደትና ሽብርተኝነትን በመታገል ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን ለማድረግ ያቀዱት መርኬል፤ ነገ ወደ ማሊ እንደሚያቀኑና ከዚያም በኒጀርና በኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን እንደሚቀጥሉ የጠቆመው ዘገባው፤ በአዲስ አበባ ቆይታቸው የአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤትን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡አንጌላ መርኬል በአፍሪካ አገራት ለቀናት የዘለቀ ጉብኝት ሲያደርጉ ከአምስት አመታት ወዲህ የአሁኑ የመጀመሪያው እንደሚሆን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
ፓሲፊክ ኢንዱስትሪዎች ኃ.የተ.ማ የሚያመርታቸው “ኤክሰል አሬንጅ ጁስ”ና “ማርች ማንጎ ጁስ” ለጤና ጎጂ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ ባለሥልጣኑ ሰሞኑን ለዝግጅት ክፍላችን ለድርጅታችን በላከው ደብዳቤ፣ ከኅብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት፤ ምርቶቹ ላይ በተደረገ የላቦራቶሪ ፍተሻ ለጤና ተስማሚ አለመሆናቸው በመረጋገጡ፣ ለኅብረተሰቡ ጤና ጎጂ መሆናቸውን ጠቁሞ፣ ድርጅቱ ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ችግር ምርቱ ገበያ ላይ እንደይውል መደረጉንና ከገበያም እንዲሰበሰብ መደረጉን፣ አሁንም ተመሳሳይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን አመልክቷል፡፡ አምራች ድርጅቱ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ምንም ዓይነት የብቃት ማረጋገጫ ያልተሰጠው በመሆኑ ምርቱ ተመርምሮ የሀገሪቱን የምግብ ደህንነትና የጥራት መስፈርት የማያሟላ፣ እንዲሁም ለጤና ጎጂና አደገኛ መሆኑን በማረጋገጥ እነዚህን ምርቶች ማንኛውም ሰው እንዳይጠቀም አበክሮ አሳስቧል፡፡ ባለሥልጣን መ/ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት፤ እነዚህን የተከለከሉ ምርቶች ሲሸጥ፣ ሲያጓጉዝ፣ ሲያከፋፍል የተገኘ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ላይ እርምጃ እንደሚወስድና አጥፊዎቹን በሕግ የሚጠይቅ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ኅብረተሰቡ ይህን መሰል ሕገ-ወጥ ተግባራትና ማንኛውም ሕገ ወጥ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና አገልግሎቶች ሲያጋጥሙት፣ በአካባቢው ላለ የሕግና የጤና
ኖርዝ ኢስት ኢንቨስትመንት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና ከብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በየዓመቱ የሚካሄድ ‹‹ሆሄ የኢትዮጵያ የሥነ ጽሁፍ ሽልማት›› ፕሮግራም ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡የሽልማት ዝግጅቱ ዓላማ በሀገራችን የንባብ ባህል እንዲጎለብት ማስቻል፣ በየዓመቱ የሚታተሙ መጽሐፍትን እንዲተዋወቁና የተሻሉት ደግሞ በተሸላሚነት እውቅና እንዲያገኙ እንዲሁም በልጆች ንባብ ላይ የተለየ ትኩረት በማድረግ ድጋፍ መስጠት ነው፡፡ የፈጠራ ፅሁፍ ስራዎቻቸውን ላበረከቱ ደራሲያንና ጸሐፍት እውቅና ከመስጠት ባለፈ የንባብ ባህል እንዲስፋፋ፣ በተፃፉ መፅሃፍት ላይ ህብረተሰቡ እንዲወያይባቸው ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ የንባብ ክበባት እንዲፈጠሩ እንዲሁም በየጊዜው የሚታተሙ መፅሀፍት ላይ ሂስና ትንታኔ በመስጠት ለመላው ህብረተሰብ የንባብ ትሩፋቶችን በማጋራት ለሚሰሩ ሀያሲያን የሽልማት ፕሮግራሙ እውቅና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ “ሆሄ የስነፅሁፍ ሽልማት” ፕሮግራም በዋነኛነት ሶስት የውድድር ዘርፎች የሚኖሩት ሲሆን እነዚህም የረጅም ልብ ወለድ መጻህፍት፣ የስነ ግጥም መድበሎችና የልጆች መጻህፍት ናቸው። ተወዳዳሪ መፃህፍት በዳኞች ኮሚቴ አማካይነት በተዘጋጀላቸው መስፈርቶች መሰረት የሚመዘኑ ሲሆን ውድድሩ በዳኞች ኮሚቴ ከሚሰጠው ውጤት በተጨማሪ በአንባቢያን ነፃ የስልክ መልእክትና በድረ ገፅ ኦን ላይን ከአንባቢያን የሚሰጠው ድምፅ
የትምህርት መጀመሪያ ቀን እስካሁን አልታወቀም ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ዘግይቶ ከትላንት በስቲያ የተጀመረውና ለ5 ቀናት እንደሚካሄድ የተጠበቀው የጎንደር ዩኒቨርስቲ የመምህራን ውይይት፤ ትላንት ሐሙስ ጠዋት በተቃውሞ የተቋረጠ ሲሆን ከሰዓት በኋላ በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ጉዳይ መምህራኑ ውይይት አድርገዋል፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል ከመስከረም 9 ጀምሮ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ውይይት፤ መምህራኑ በውይይቱ ሥፍራ ሳይገኙ በመቅረታቸው አለመካሄዱ የሚታወስ ሲሆን በድጋሚ በዩኒቨርሲቲው በወጣ ማስታወቂያ መሰረት ውይይቱ ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 24 እንደሚካሄድ ተገልፆ ነበር፡፡ ሁሙስ እለት የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል፤ “የሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት” በሚል ርዕስ ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፤ የመድረክ መሪውን የመነሻ ፅሁፍ ተከትሎ መምህራን በሶስት አዳራሽ ተከፋፍለው በቡድን ውይይት እንዲያደርጉ ቢሞከርም፣ በሁለቱ አዳራሾች የነበሩ መምህራን ራሳቸውን ከንግግር በማቀባቸው ውይይቱ ተበትኗል፡፡ በሌላኛው አዳራሽ ከነበሩ መምህራን አንደኛው ድንገት ተነስቶ፤ ‹‹ሰው እየተገደለ፣ ንብረት እየተቃጠለ ምን እንድንል ነው የምትፈልጉት?›› የሚል ዱብ ዕዳ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን የመድረኩ መሪ ንግግሩን ውይይቱ መበተኑ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ለአዲስ
ሳምንታዊ የግል ጋዜጦች ከማተሚያ ቤት ችግር ጋር በተያያዘ ከሚወጡበት መደበኛ ቀናቸው እስከ 5 ቀን ዘግይተው እየወጡ ሲሆን ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፤ የጋዜጦችን ዘግይቶ የመውጣት ችግር ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ነኝ ብሏል። ችግሩን ለመፍታት የጋዜጣ አሳታሚዎች እስከ መስከረም 30 ቀን 2009 ዓ.ም እንዲታገሱትም ጠይቋል-ማተሚያ ቤቱ፡፡ “አዲስ አድማስ” ን ጨምሮ ቅዳሜ ለአንባቢያን መድረስ የነበረባቸው ጋዜጦች እሁድ መውጣት የጀመሩ ሲሆን የእሁድ ሳምንታዊ ጋዜጦች እስከ 4 እና 5 ቀናት እየዘገዩ እንደሚወጡ የገለፁት አሳታሚዎች፤ መዘግየቱ ከማስታወቂያ ደንበኞቻቸው ጋር ቅራኔ ውስጥ እየከተታቸው መሆኑን ጠቁመው ለአንባቢያን በጊዜና በሰአቱ መድረስ ያለባቸው መረጃዎችም እየዘገዩ መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተካ አባዲ፤ ጋዜጦች ለምን በዕለታቸው እንደማይወጡ ከአዲስ አድማስ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ ‹‹ማተሚያ ቤቱ በ22 ሚሊዮን ብር የገዛውና በሰአት እስከ 20 ሺህ ኮፒ ጋዜጦች የማተም አቅም ያለው ዘመናዊ ማሽን የቴክኒክ እክል ስለገጠመው ነው›› ብለዋል፡፡ ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት ድርጅቱ ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለጹት አቶ ተካ፤ ማሽኑ ወደ ሀገር
ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የኦሮሚያ ወረዳዎች የ4 ሰዎች ህይወት በፀጥታ ኃይሎች ማለፉን ኦፌኮ ገለፀ፡፡ በነቀምት ላይ አንድ ወጣት መገደሉንና በምዕራብ መንዲ ወረዳ በመስቀል ደመራ ላይ የ15 ዓመት ታዳጊ መገደሉን የገለፀው ኦፌኮ፣ ነጆ በምትባል ከተማም አንድ ሰው ተገድሎ 5 ሰዎች በጥይት እንደቆሰሉ ጠቁሟል፡፡ በምዕራብ አርሲ አጄ፣ አንድ ሰው መሞቱን የተናገሩት የኦፌኮ ም/ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ፤ የማስፈራራትና ማዋከብ ዘመቻም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል፡፡ የኦህዴድ ሊቀ መንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ለማ መገርሳ፤ ከህዝብ ጎን እንደሚቆሙና ሰላም እንደሚፈጥሩ ቃል መግባታቸውን የጠቀሱት አቶ ሙላቱ፤ ይህ በተባለ ማግስትም በሰው ህይወትና አካል ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ካልቆሙ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡ ከክልሉ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡
በባህርዳር ከተማ መስቀል አደባባይ በተካሄደው የደመራ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙትና የሰሞኑ አገራዊ የመወያያ አጀንዳ የሆኑት የባህርዳር ምዕራብ ጎጃም አዊና መተከል አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አቡነ አብርሃምን የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ከትናንት በስቲያ አነጋገሯቸው፡፡ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሰረት፤ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ከሆኑት የመንግስት ባለስልጣናት መካከል የፌደራል አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃንና በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ህላዊ ዮሴፍ ናቸው፤ ጳጳሱን ያነጋገሩዋቸው፡፡ የንግግራቸው አጀንዳም በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይና መደረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደሆነም ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በባለስልጣናቱና በአቡነ አብርሃም መካከል የተካሄደውን ውይይት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ባንችልም፣ ባለስልጣናቱ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ መንግስት ምን ማድረግ እንደሚገባው አባታዊ ምክራቸውን እንዲሰጡ አቡነ አብርሃምን መጠየቃቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በባህርዳር ከተማ መስቀል አደባባይ ላይ በተከናወነው የደመራ በአል ላይ ለምዕምኑ ንግግር ያደረጉት አቡነ አብርሃም፤ ‹‹የምናገረው ፖለቲካ አይደለም፤ እንደዛ ነው የሚል እንደፈለገ ይተርጉመው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ችግር የሚፈጠረው በመሪ እንጂ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፡፡ ወታደሩ
በዲላ ዩኒቨርስቲ ‹‹የህሊና ፀሎት›› ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም በአገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መንግስት ከመምህራን ጋር እያካሄደ ያለው ውይይቶች በተቃውሞና በውዝግብ የታጀቡ ሆነዋል፡፡ በጎንደርና በባህርዳር ውይይቱ በወጣው መርሃ ግብር መሰረት አለመካሄዱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡መስከረም 4 በተጀመረው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የመምህራን ውይይት ለ2 ቀናት ብቻ ብቻ የተሳተፉ አንድ መምህር፤ እንደገለፁልን፤ መምህራኑ ተቀምጦ ከማዳመጥ ባለፈ ጥያቄም ሆነ አስተያየት በቀጥታ ማቅረብ አትችሉም መባላቸውን ተከትሎ ቅሬታዎች ተፈጥረው ነበር፡፡ በትግራይ ክልል ም/ርዕሠ መስተዳደር ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ አጋፋሪነት በተመራው ውይይት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው በየኮሌጆቹ ተወካዮች በኩል እንጂ መምህራን በቀጥታ ማቅረብ ተከልክለው ነበር። የሚሉት መምህሩ፤ ጥያቄዎች ለኮሌጅ መሪዎች ከተሰጡ በኋላ ተጨምቆ ለመድረክ ይቀርብ ነበር ብለዋል፡፡ በዩኒቨርስቲው ስብሰባው ላይ ተሳታፊ የነበሩ አንዳንድ ያነጋገርናቸው መምህራንም በቀሪ መቆጣጠሪያ መዝገብ ላይ እየፈረሙ ወጣ ገባ ከማለት በስተቀር ውይይቱን በአግባቡ እንዳልተከታተሉ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪና የዲላ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል ሰብሳቢነት ከመስከረም 5 ጀምሮ እስከ ትናንት በተካሄደው ስብሰባ ላይ እንደ አዲስ አበባ
ማልታ ጊነስ በአይነቱ ልዩ የሆነ የስኬት ቦርድ ውድድር ሰሞኑን በአዲስ ስኬት መዝናኛ ውስጥ አካሄደ፡፡ በ15 ተወዳዳሪዎች መካከል የተካሄደው የስኬት ቦርድ ውድድር፤ በአገራችን አምብዛም ያልተለመደውን የስኬት ስፖርት በስፋት እንዲለመድና ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለማፍራት የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጿል። ከአልኮል ነፃ በሆነው የማልታ ጊነስ ምርት ታጅቦ በተካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ከ1-3 የወጡ ተወዳዳሪዎች የማልታ ጊነስ ምርት አምራች በሆነው ዲያጆ ኢትዮጵያ የተዘጋጀላቸውን ሽልማቶች ተቀብለዋል፡፡ ውድድሩ በራሳቸው የሚታማመኑና ብቃት ያላቸው የስኬት ቦርድ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችል የማልታ ጊነስ ብራንድ ማናጀር አቶ አቤል አናጋው በውድድሩ ወቅት ተናግረዋል፡፡ በዚሁ የስኬት ቦርድ ስፖርት ውድድር ወቅትም ዲያጆ ኢትዮጵያ ለአዲስ ስኬት ፓርክ የ50ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
‹‹የህዝቡ ጥያቄ የስርአትና የፖሊሲ ለውጥ ነው›› በተሃድሶ ግምገማ ላይ ከሚገኙት አራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች ኦህዴድ ሊቀመናብርቱን ሰሞኑን ከሃላፊነት ያነሰ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች በየትኛውም ደረጃ የሚደረጉ የአመራር ለውጦች ለህዝብ መሰረታዊ ጥያቄ ምላሽ አይሆኑም ብለዋል፡፡ህዝብ የጠየቀው የስርዓትና የፖሊሲ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች መቀያየርን አይደለም፤ ይላሉ ተቃዋሚዎች፡፡የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ፤ የገዥውን ፓርቲ ተሃድሶ ብቻ ሳይሆን ሁሉም አስተሳሰቦች የተካተቱበት የፖሊሲ ለውጦች ነው የጠየቅነው ብለው፡፡ አሁን ባለው ፖሊሲ ላይ ግለሰቦችን መለዋወጥ ተሃድሶ እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡ ‹‹የህዝቡ ጥያቄም የአመራሮች መለዋወጥ›› አይደለም ያሉት ዶ/ር ጫኔ፤ ተሃድሶው በዚህ መልኩ ከቀጠለ ምንም ለውጥ አያመጣም፤ የህዝቡንም ጥያቄ በዚህ መንገድ መመለስ አይቻልም ብለዋል፡፡ በኦሮሚያ የኦህዴድ አመራሮች መቀያየራቸው ሌሎቹ ድርጅቶችም ከዚህ የተለየ አጀንዳ እንደሌላቸው ያሳያል፡፡ ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በኢዴፓ እምነት ይህ አካሄድ የበለጠ የህዝበን ጥያቄ የማፈኛ መንገድ ነው ብለዋል፡፡ አዴፓ አሁንም ብቸኛው መፍትሄ የብሄራዊ እርቅ መድረክ ማዘጋጀት ነው የሚል አቋም እንዳለውም ዶ/ር ጫኔ ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያም ቢሆን ህዝብ የአመራር ለውጥ አልጠየቀም ያሉት የሠማያዊ
በአማራ ክልል በተለይ በጎንደርና በባህርዳር ከተሞችና በአካባቢያቸው ባሉ ወረዳዎች ሠሞኑን ከቤት ያለመውጣት አድማ ሲደረግ መሠንበቱን የጠቆመው መኢአድ፤ በሌላ በኩል ወጣቶች በፀጥታ ሃይሎች እየተለቀሙ መታሠራቸው አስታውቋል፡፡ የፓርቲው ዋና ፀሃፊ አቶ ኪዳነ በጎንደር ከሠኞ መስከረም 9 ቀን ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ አንድም የንግድ ተቋም ሳይከፈት የቤት ውስጥ አድማ ሲደረግ መሰንበቱንና በደብረታቦር ማክሰኞ አድማው የተደረገ ቢሆንም በሃይል ህዝቡ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ነዋሪዎችም ደብረታቦር መታሰራቸውን አስታውቀዋል፡፡ ጋይንት፣ ንፋስ መውጫ፣ ሊቦ ኮምኮምና አዲስ ዘመን በተባሉ የጎንደር ከተሞችም እስከ ትናንት ድረስ የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል ተብሏል፡፡ ባህርዳር እስከ ሃሙስ እለት የንግድ መደብሮች ዝግ ቢሆኑም የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የትራንስፖርት አገልግሎት አልተቋረጡም ብለዋል ዋና ፀሃፊው፡፡ በወገራና ኮሶዬ በተባሉ ወረዳዎች ሠሞኑን የፀጥታ ሃይሎች ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር መጋጨታቸውን መኢአድ አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል፤ በባህርዳርና በወልቂጤ ዩኒቨርስቲዎች በተደረጉ የመምህራን ስብሰባዎች ለመንግስት ሃላፊዎች ጠንካራ ጥያቄዎች እንደቀረበላቸው መኢአድ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ በኮንሶ አካባቢ የተከሰተው ቀውስ አለመረጋጋቱን የጠቆመው መኢአድ፤ በአካባቢው ሰዎች
የኩሽ ህዝቦች በተለይም አሮሞዎች ፈጣሪያቸውን በሚያመሠግኑበት ሃይማኖታዊና ባህላዊ የኢሬቻ ስነስርአት ላይ ማናቸውም የፖለቲካ ሃይሎች ከዋዜማው ጀምሮ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ የኦሮም ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አሣሠበ፡፡መስከረም 22 የሚከበረው የኢሬቻ በአል የራሱ ሃይማኖታዊ ባህልና የአከባበር ስርአት እንዳለው በመግለጫው የጠቀሰው ኦፌኮ፤ የተለያዩ አካላት በዋዜማው ‹‹የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ›› እና ሌሎች ከባህሉ ጋር የማይገናኙ ፕሮግራሞችን ለማካሄድ ማቀዳቸው ተቀባይነት የለውም ብሏል፡፡ በአሉ የምስጋና ቀን በመሆኑ በመልከ መውረጃ መንገዶች ላይ የኪነት ቡድን አደራጅቶ ማስጨፈር፣ የፖለቲካ ንግግር ማድረግ የመሣሰሉትን ፓርቲው እንደሚቃወም አስታውቋል፡፡ በአሉ ከፖለቲካም ሆነ ባህሉን ከሚፃረር ማንኛውም ድርጊት ነፃ እንዲሆንና የህዝብ በአልነቱ እንዲከበር አሳስቧል ኦፌኮ፡፡
ወጋገን ኮሌጅ ላለፉት ሁለት ዓመታት በአካውንቲንግ፣ በፊልምና በቴአትር ጥበባት ያሰለጠናቸውን 120 ተማሪዎች ዛሬ ቦሌ አሮሚያ ታወር ላይ በሚገኘው ሰራዊት ሲኒማ አዳራሽ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ያስመርቃል፡፡ ኮሌጁ ከተቋቋመበት ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ሲያሰለጥን የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ የሚያስመርቅ መሆኑን የኮሌጁ ሬጅስትራር ኦፊሰር ወ/ሪት ሀመልማል በላይ አሞኘ ለአዲ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ወጋገን ኮሌጅ በ2008 የበጀት ዓመት የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 66 ያህል የግል ኮሌጆች መካከል የሰልጣኞቹን የብቃት መረጋገጫ ውጤት 81 በመቶ በማምጣት ለ2009 ዓ.ም የእውቅና ፈቃዳቸውን ካደሱ 12 ኮሌጆች የመጀመሪያው ሆኖ ማለፉንም ወ/ሪት ሀመልማል ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ኮሌጁ ዛሬ በሚያስመርቃቸው ሰልጣኞች የምረቃ በዓል ላይ የዩኒቨርስቲ ምሁራን፣ ታዋቂ የኪነ- ጥበብ ባለሞያዎች የተመራቂ ቤተሰቦችና የኮሌጁ ማህበረሰቦች እንደሚታደሙም ለማወቅ ተችሏል፡፡
አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን በነገው እለት በመኢአድ ፅ/ቤት ግቢ ሊያከናውን ቀጠሮ ይዞ የነበረው ሠማያዊ ፓርቲ፤ ከህግ አግባብ ውጪ በምርጫ ቦርድ ጉባኤውን እንዳያካሂድ መከልከሉን አስታወቀ፡፡ ፓርቲው ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ፤ በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ የነበረበትን የውስጥ ፓርቲ ችግር ለመፍታት አቅዶ እንደነበር ጠቅሶ፤ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት፤ ‹‹በፓርቲው ላይ የሚጣሩ ጉዳዮች በመኖራቸው የጉባኤው ቀን እንዲራዘም›› በሚል የማሳሰቢያ ደብዳቤ መላኩን አመልክቷል፡፡ የምርጫ ቦርድ ሃላፊነት ተወካይ በመላክ ሂደቱን መታዘብ እንጂ የጉባዔ ቀን መወሠን አለመሆኑን የጠቀሰው ፓርቲው፤ ጉባኤው በዚህ ምክንያት ከመደናቀፉ ባሻገር ለጉባኤው ፓርቲው ያወጣቸው ወጪዎች ለኪሣራ እንደዳረገው አስታውቋል፡፡ ለደረሰው ኪሣራም ፓርቲው ምርጫ ቦርድን በህግ እንደሚጠይቅ አስታውቆ፤ የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ይልቃል ጌትነትና ሌሎች አካላት ጉባኤውን ከማደናቀፍ ተግባር እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡ ጉባኤውንም በቅርቡ በድጋሚ እንደሚጠራም የፓርቲው ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሠጡን የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ፤ ‹‹የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ለማሠናከል አይደለም፤ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ይልቃል ጌትነት
“ጥያቄያችን በኦሮሚያ ክልል እስከመጠቃለል ይዘልቃል” አቶ ገመቹ ገንፌ፤ - የኮንሶ ኮሚቴ አባል“ጥያቄው የህዝብ ሳይሆን የጥቂቶች ነው” - የክልሉ መንግስት ከኮንሶ የዞንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግጭት የበርካቶች ህይወት ጠፍቶና በሺህ የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለው ዜጎች የተፈናቀሉሲሆን የኮንሶ ህዝብ ኮሚቴ፤ ጥያቄያችን ወደ ኦሮሚያ ክልል እስከመጠቃለል ይዘልቃል ብለዋል፡፡ በአካባቢው እስከ ትናንት ድረስ ግጭቶች መቀጠላቸውንና የታጠቁ የመንግስት ኃይሎች የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር የኮንሶ ኮሚቴ አባል አቶ ገመቹ ገንፌ ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን በሰሞኑ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና አስክሬናቸው እስከ ትናንት ድረስ ለቤተሰብ እንዳልተሰጠ ተገናግረዋል። የደቡብ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ አይረዲን በበኩላቸው፤ ግጭቱን ያስነሱትና በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉት የኮሚቴው አባላት ናቸው ይላሉ፡፡ “የፀጥታ ኃይሉ ጥፋቱ ከደረሰ በኋላ ነው ህዝቡን ለመታደግ ወደ አካባቢው የገባው፤ በአሁን ወቅት ግን በኮንሶ ምንም ግጭት የለም፤ ሰላማዊ ነው”፤ ብለዋል ኃላፊዋ፡፡ የኮሚቴው አባል አቶ ገመቹ፤ ጥያቄያችን በፌደሬሽን ምክር ቤት ተቀባይነት ካላገኘ በሪፈረንደም ወደ ኦሮሚያ
ባለፈው ዓመት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተቀሰቀሱት ተቃውሞዎች ወደ ግጭትና የፖለቲካ ቀውስ ሲሻገሩ ነበር አዲስ አድማስ የመፍትሄ ሃሳቦችን ከተለያዩ ወገኖች ማሰባሰብ የጀመረችው፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት የሃይማኖት መሪዎችን ጨምሮ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የተለያዩ ዕውቅ ኢትዮጵያውያንን አነጋግረን ለፖለቲካ ቀውሱ መፍትሄ ነው የሚሏቸውን ሃሳቦች ስናስተናግድ ቆይተናል፡፡የአገሪቱ ምሁራንም በችግሮቹ ዙሪያ ሀሳባቸውን የመፍትሄ አቅጣጫ ይሰጡን ዘንድ ጥረት ብናደርግም ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡ ከሶስት ምሁራን ውጭ አብዛኞቹ “ትንሽ ይቆየን፤ አሁን ይለፈን” በሚል ራሳቸውን አግልለዋል፡፡ ምሁራን በአገራቸው እንዲህ ያለ ፖለቲካ ቀውስ ተከስቶ፣ ለምን ራሳቸውን አገለሉ? ብዙዎች ፍርሃት ስላለባቸው ነው በሚለው ይስማማሉ፡፡ አገር በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ስትገባ፣ ምሁራን ቀዳሚ ሚና ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚናገሩት ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፤ ምሁራኑ ከማንም በፊት ለህዝብ መቆም አለባቸው ይላሉ፡፡ ችግሩ ግን በፍርሃት ተቀፍድደዋል ባይ ናቸው፡፡ በየትኛውም አገር ለህዝብ መብቶች በመታገል ጉልህ ሚና የሚጫወቱት ምሁራን፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና ሚዲያው እንደሆኑ የሚናገሩት ፕሮፌሰሩ፤ ሦስቱም ግን በፍርሃት ተሸብበዋል ይላሉ፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ፅሁፍ መምህሩ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራም የፕሮፌሰሩን
የስልጠናው ዋነኛ አጀንዳ ፌደራሊዝም ነው በአገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 4 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ቀናት ለመምህራን ሊሰጥ የታሰበው ስልጠና ውዝግብ አስነሳ፡፡ የግል ት/ቤት መምህራን ስልጠናው ከሙያቸው ጋር ፈፅሞ የማይገናኝ ከመሆኑም በላይ ለመንግስት ት/ቤቶች መምህራን የሚሰጠው የአበል ክፍያ የማይታሰብላቸው በመሆኑ ስልጠናውን አንካፈልም በማለት ጥለው ወጥተዋል ተብሏል፡፡ ሰሞኑን ተዘዋውረን ባየናቸው የግል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ መምህራኑ ስልጠናውን ለመካፈል የማይፈልጉ መሆናቸውን በመግለፅ አቋርጠው ወጥተዋል፡፡ በባሸዋም አንደኛ ደረጃና የፕሪፓራቶሪ ት/ቤት ውስጥ ስልጠናውን ለመካፈል ተሰባስበው የነበሩ የአምስት የግል ት/ቤቶች መምህራን፤ ስልጠናውን ለመካፈል ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ተበትነዋል፡፡ ለመምህራኑ ስልጠናውን ለመስጠት በሥፍው ለተገኙት የመንግስት ተጠሪ፤ ስልጠናውን የሚካፈሉት ለመንግስት መምህራን የተሰጠው የአበል ክፍያ ለእነሱም ሲታሰብ መሆኑን በመግለፅ ስልጠናውን አንሣተፍም ብለዋል፡፡ የመንግስት ተጠሪዋ ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመግለፅ፤ የግል ት/ቤቶች መምህራን የአበል ክፍያውን ከየትምህርት ቤቶቻቸው ያገኛሉ ተብሎ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “ስልጠናው ባይኖርም ሥራ ላይ መሆናችሁ አይቀርም ነበር፡፡ ስለዚህም አበል ሊከፈላችሁ አይገባም” መባላቸውን የሚናገሩት መምህራኑ፤ ከሥራችን ጋር ፈፅሞ የማይገናኝ
ከ292 ሺህ በላይ የአገሪቱ ስደተኞች በኢትዮጵያ ይገኛሉ ባለፈው ሳምንት ብቻ ከ11 ሺህ በላይ የሚሆኑ ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች በጋምቤላ ክልል በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣው ግጭትና ውጥረት በርካታ ዜጎች አገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት አገራት እንዲሰደዱ እያስገደዳቸው ነው ያለው ኮሚሽኑ፤ ባለፈው ሳምንት በስደት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ከ11 ሺህ በላይ ደቡብ ሱዳናውያን በኢትዮጵያ የሚገኙ የአገሪቱ ስደተኞችን ቁጥር ከ292 ሺህ በላይ እንዳደረሱት አስታውቋል፡፡አብዛኞቹ ስደተኞች ናስር፣ ማባን፣ ማቲያንግና ማዩት በተባሉት የደቡብ ሱዳን አካባቢዎች የተጠናከረ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በማየታቸውና አዲስ ግጭት ይከሰታል ብለው በመስጋት ስደትን የመረጡ ደቡብ ሱዳናውያን እንደሆኑም አስረድቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት በጋምቤላ ክልል ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች፤ አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት ናቸው ያለው ኮሚሽኑ፣ ብዙዎቹም የኑዌር ጎሳ ተወላጆች እንደሆኑና 500 ያህሉ ስደተኞች ያለ ወላጅ ብቻቸውን ስደት የወጡ ህጻናት እንደሆኑ ገልጧል፡፡በደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ሳቢያ ወደ ጎረቤት አገራት የተሰደዱ የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር ከአንድ
የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስቲያን ላጋርድ፣ ኢትዮጵያዊውን ኢኮኖሚስት አቶ አበበ አእምሮን የተቋሙ የአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ተቋሙ ከትናንት በስቲያ በድረ-ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ ላለፉት 22 አመታት በአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም የሰሩት አቶ አበበ አእምሮ በተቋሙ፣ በነበራቸው ቆይታ፣ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን የገለጸው ተቋሙ፤ በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ባከናወኗቸው ውጤታማ ተግባራት የካበተ ልምድ እንዳላቸውም ጠቁሟል፡፡“አቶ አበበ በተቋሙ በነበራቸው ቆይታ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ከአህጉሪቱ ፖሊሲ አውጪዎች ጋር በቅርበት ሲሰሩ እንደመቆየታቸው የአፍሪካን ፈተናዎች በተመለከተ ጥልቅ ግንዛቤ አላቸው፡፡ በአመራር፣ በማስተባበርና በሌሎች መስኮች ያላቸውን ብቃት በተግባር ማረጋገጣቸው ለዚህ የስራ ሃላፊነት እንዲመረጡ አድርጓቸዋል” ብለዋል የተቋሙ ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ ክርስቲያን ላጋርድ፡፡አቶ አበበ አእምሮ በተቋሙ ቆይታቸው፣ የአፍሪካ ክፍል የኡጋንዳ ከፍተኛ ተወካይና የደቡብ አፍሪካ ተልዕኮ ሃላፊ ሆነው ከመስራታቸው በተጨማሪ የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ትንበያን ጨምሮ በኮትዲቯር፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያና ሴራሊዮን በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ስኬታማ ስራ ማከናወናቸውንም ተቋሙ አስታውቋል፡፡በተቋሙ የስትራቴጂ፣ ፖሊሲና ግምገማ ክፍሎች በተለያዩ ሃላፊነቶች ላይ በነበራቸው የስራ ቆይታ የአመራር
በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ቃጠሎ 40 ሰዎች ሞተዋልበኢህአዴግ የሚመራው መንግስት የዘንድሮውን ያህል ህዝባዊ ተቃውሞ ደርሶበት አያውቅም ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ህዳር ወር የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም የተነሳው ተቃውሞ ማስተር ፕላኑ መሰረዙን መንግስት ቢያስታውቅም ተቃውሞው ግን አልበረደም። በርካታ የመብት ጥያቄዎችን የሚያቀርቡ ወጣቶች የሚበዙባቸው የተቃውሞ ጎርፎች የኦሮምያ ጎዳናዎች አጥለቀለቁት፡፡ ከ10 ወራት በላይ በዘለቀው የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞና ግጭት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ብዙ ሺዎችም ለእስር እንደተዳረጉ የተለያዩ ሪፖርቶች ጠቁመዋል፡፡በአማራ ክልለ ህዝባዊ ተቃውሞዎቹ ከ3 ወር የማይበልጥ ዕድሜ ቢኖራቸውም በእጅጉ የተጠናከሩና በህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ናቸው፡፡የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከሐምሌ 29 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን መረጃ መዝግቦ መያዙን የገለፁት የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አዳነ ጥላሁን፤ በአማራ ክልል ውስጥ እስከ ሐሙስ ድረስ 173 ሰዎች ሞተው፣ 130 መቁሰላቸውን ጠቁመዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ሐምሌ 30 ተጠርቶ በነበረ የተቃውሞ ሰልፍ፤ በአንድ ቀን የሞቱትን 60 ሰዎች ጨምሮ ከነሐሴ 18 እስከ 27 ድረስ
ከጳጉሜ 1 እስከ መስከረም 2 በኦሮሚያ በማህበራዊ የንግድ አድማ መጠራቱን ተከትሎ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ተግባራዊ መደረጉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ያስታወቀ ሲሆን መንግስት በበኩሉ፤ የአድማ ጥሪው በህብረተሰቡ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከሽፏል ብሏል፡፡ የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለአዲስ አድማስ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ “በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች የንግድም ሆነ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም፤ ሁሉም ነገር እንደታገደ ነው” ብለዋል፡፡ ሆቴል ቤቶች፣ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮችና የገበያ ስፍራዎች ዝግ ሆነው መሰንበታቸውን ኦፌኮ አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል በነቀምትና ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ ባለፈው ሰኞና ማክሰኞ 4 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው አቶ ሙላቱ ተናግረዋል፡፡ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሃመድ ሠኢድ ስለጉዳዩ ከአዲስ አድማስ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠሩት ችግሮች ከህገ መንግስቱ ጋር የማይጣጣሙ እንደሆኑ ጠቁመው ሁከቱ በዜጎች ህይወትና ንብረት ላይ ጥፋት ማስከተሉን አስታውቀዋል፡፡ “ህዝቡ በቅንነት የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከህዝቡ ከራሱ ጋር ተመካክሮ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነቱን መንግስት በመግለጫዎቹ አሳይቷል” ያሉት አቶ መሃመድ፤ ከዚህ በመነሳት የህብረተሰቡን አጀንዳ
- የሞቱ ዜጎች ጉዳይ በገለልተኛ አካል ይጣራ፤ የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ በህግ ይጠየቁ ብለዋል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ በአማራና ኦሮምያ ክልሎች ከተቀሰቀሱ ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ የታሰሩ ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአፋጣኝ እንዲፈታ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊት እንዲያደርግ በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰሩ 15 የተለያዩ ታዋቂ አለማቀፍ እና ብሄራዊ ተቋማት ጠየቁ፡፡ ተቋማቱ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በላኩት የጋራ ደብዳቤ፣ ምክር ቤቱ በቀጣዩ ሳምንት በሚያካሂደው አመታዊ ጉባኤው በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ቀዳሚ አጀንዳው እንዲያደርግና ጉዳዩን በተመለከተ መግለጫ እንዲያወጣ ጠይቀዋል፡፡መንግስት ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪዎች፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላትና ተቃዋሚዎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔ በአፋጣኝ እንዲፈታ እንዲሁም የጸጥታ ሃይሎች በሁለቱም ክልሎች ሆነ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በተቃዋሚዎች ላይ ያልተመጣጠነና ተገቢ ያልሆነ የሃይል ጥቃት መፈጸማቸውን እንዲያስቆም ግፊት እንዲያደርግም ምክር ቤቱን ጠይቀዋል፡፡መንግስት ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ የተገደሉና የሰባዓዊ መብቶች ጥሰቶች የደረሱባቸው ዜጎች ጉዳይ በአለማቀፍ ገለልተኛ ተቋማት እንዲጣራ እንዲፈቅድ፣ የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ አካላት
“ያለ ህግ አግባብ የታሰሩ ሰዎች በአስቸኳይ ይፈቱ”ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የተሠባሠቡ አባገዳዎች በክልሉ ባለው ተቃውሞና ግጭት ሳቢያ የበርካታ ሰዎች ህይወት እየጠፋ መሆኑን በመግለፅ ችግሩን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ በውይይት መንግስት እንዲያነጋግራቸው ጠይቀዋል፡፡ከነሐሴ 23 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሶደሬ ሆቴልና ሪዞርት ከ2 ሺ በላይ የሀገር ሽማግሌዎችና ሴቶች ባካሄዱት የ3 ቀን ጠቅላላ ጉባኤ በክልሉ ባለው ተቃውሞና ግጭት ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ ባለ 13 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የፌዴራል መንግስት ጦር የሃገሪቱን ዳር ድንበር የመጠበቅ ስራውን ትቶ በክልሉ መስፈሩን የጠቆሙት አባገዳዎች፤ ጦሩ የህዝቡን ቋንቋ የማያወቅ በመሆኑ ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን በመግለፅ በአስቸኳይ ከክልሉ እንዲወጣ ጠይቀዋል። ሰላማችንን ራሳችን እንጠብቃለን በማለት፡፡“የጦር ሰራዊቱ ኦሮሚኛ ቋንቋን ስለማያውቅ ከህብረተሰቡ ጋር በቅጡ እየተግባባ አይደለም፤ ክልሉን በአፋጣኝ ለቆ እንዲወጣ እንጠይቃለን” ብለዋል የቱለማ አባገዳ በየነ ሰንበቶ፡፡ አብዛኛው የኦሮሞ ማህበረሠብ አባገዳዎች ጋር እየቀረበ፣ የደረሰበትን በደል እየተናገረ መሆኑን የጠቀሱት አባገዳው፣ ግጭቶችን ተከትለው የኦሮሞ ልጆች ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ “በኦሮሞ ባህል እንኳን የሰው ልጅ የበሬ ደም እንኳ
የእርቅ መንግስት እንዲመሰረት ፓርቲው ጠይቋልባለፈው ሳምንት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ለደረሰው የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት መንግስትን ተጠያቂ ያደረገው የመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፤ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል፡፡ ፓርቲው ሰሞኑን በፅ/ቤቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፤መንግስት በአደጋው 23 ታራሚዎች መሞታቸውን ቢናገርም ቁጥሩ ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አለኝ ብሏል፡፡ መንግስት ለታራሚዎች ህገ መንግስታዊ ከለላ በመስጠት ደህንነታቸውን መጠበቅ ሲገባው፤ ይህ ሳይፈፀም መሞታቸውም ሆነ ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ለታሳሪ ቤተሰቦች ግልፅና የማያሻማ ፈጣን መልስ በመስጠት ፈንታ በቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ጭንቀትና አሳዛኝ መጉላላት እንዲደርስ መደረጉን በጥብቅ አወግዛለሁ ብሏል መኢአድ፡፡ በጉዳቱ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት ማዘኑንም ፓርቲው አስታውቋል፡፡ ፓርቲው በመግለጫው፤ በማረሚያ ቤቱ የደረሰውን ጉዳት ጨምሮ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የደረሡ ጉዳቶች በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ፣ ለጠፋው ህይወት መንግስት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና የደም ካሣና የዜጎች ማቋቋሚያ ካሣ እንዲከፍል ጠይቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሣለኝ ነሀሴ 24 የሠጡት መግለጫ ‹‹ጦርነት ከማወጅ የማይተናነስ አሳዛኝም አስደንጋጭም ተግባር ነው›› ያለው ፓርቲው፤ በአስቸኳይ ትዕዛዙ
በሃገሪቱ ያለው ውጥረት ይረግብ ዘንድ ብሄራዊ እርቅ እንዲፈጠር ኢዴፓን ጨምሮ 16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሠባሠቡበት ‹‹ጥምረት ለብሄራዊ መግባባትና አንድነት›› ሰሞኑን ጥሪ ያቀረበ ሲሆን መንግስት እርቁን ካልተቀበለ ሃገሪቱን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላታል ብሏል፡፡ ኢህአዴግ አሁን በጀመረው መንገድ ግጭቶቹ ሊፈቱ እንደማይችሉ የጠቆመው ጥምረቱ፤ የሃይል እርምጃዎች ከቀጠሉ ሃገሪቱ ከኢህአዴግ ቁጥጥር ውጭ ልትሆን ስለምትችል በጊዜ የብሔራዊ እርቅ መድረክ ተፈጥሮ ሠላምና መግባባት እንዲሰፍን ጠይቋል፡፡ የተፈጠረውን የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ ለማረጋጋት ብሄራዊ እርቅ ወሳኝ ነው ያለው የፓርቲዎች ጥምረት፤ እርቁ ለዘመናት ስር እየስደደ የመጣውን የጥላቻ፣ የመናናቅ፣ ያለመተማመን፤ የቂም በቀልና የመገዳደል ስሜትን ለማስወገድ ወሳኝ ነው ብሏል፡፡ በዋናነት በተቃውሞዎች የተንፀባረቀው ‹‹የህወሃት የበላይነት የተረጋገጠበትና የታየበት አሰራር እንዲለወጥ›› የቀረበ ጥያቄ ነው ያለው ጥምረቱ፤ የአንድ ፓርቲ የበላይነት ሠፍኗል የሚለው አመለካከት እንዲቀረፍ ከተፈለገ፤ በጉዳይ ላይ የመድረክ ላይ ክርክር ውይይት ወሳኝ ነው ብሏል፡፡ የፖለቲካ እስረኞች ተፈተው ብሄራዊ እርቁ እንዲከናወን የጠየቀው ጥምረቱ፤ በእርቅ መድረኩ የተለያዩ ሃገራት መንግስታት፣ ታዋቂ አለማቀፍ ድርጅቶችና የዲፕሎማቲክ ተቋማት የታዛቢነት ድርሻ እንዲኖራቸው ጠይቋል፡፡
በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የሚወሰድ አላስፈላጊ የኃይል እርምጃ እንዲቆምና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት እንዲከበር የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) የጠየቀ ሲሆን የመብት ጥሰቶችን በማጣራት ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎቹም በመንግስት እየታሰሩበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ ተቋሙ ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች የደረሱ የመብት ጥቃቶችን አጣርቶ ማቅረቡን በመጥቀስ፤ አሁንም በአማራ ክልል በጎንደርና ባህር ዳር ከተሞች ጨምሮ ተቃውሞና ግጭት በተፈጠረባቸው የክልሉ ከተሞች የበርካታ ሰው ህይወት ማለፉን ባገኘው መረጃ አንዳረጋገጠ መቁሞ መንግሥት የኃይል እርምጃ ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስቧል፡፡ሰላማዊ ተቃውሞዎችን ወደ ግጭት እየቀየረ ያለው በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የሚወሰድ ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ መሆኑን የጠቀሰው ሰመጉ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ኃይማኖትና ብሄርን አላማ ያደረገ ግጭት ለመፍጠር የሚደረጉ ሙከራዎች መኖራቸውን ጠቁሞ ሁሉም ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቋል፡፡ መንግስት፤ የፀጥታ ኃይሎችን ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ አስቁሞ ህዝብን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ የተፈፀመው የሰብአዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራና አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ እንዲሁም ህይወታቸው ላለፈ ዜጎች ቤተሰብና በግጭቱ ለተጎዱ ካሳ እንዲከፈል፣ ከህግ አግባብ ውጪ የታሰሩ እንዲፈቱ ሰመጉ
“መንግሥት የሀገሪቱን መሰረታዊ ችግር አልተገነዘበም” የሰሞኑ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ መግለጫ፤ የወቅቱን የሀገሪቱን ችግሮች በአግባቡ የፈተሸና ለውጥ ሊያመጣ የሚችል አለመሆኑን የገለፁት ተቃዋሚዎች፤ በሀገሪቱ በተከሰቱት ችግሮች ዙሪያ ያስቀመጧቸውን የመፍትሄ ሃሳቦች ከግምት ውስጥ ያስገባ የሰጠ አይደለም ብለዋል፡፡ መንግስት የአገሪቱን መሰረታዊ ችግር ባለመገንዘቡ፣ አሁንም መፍትሄ ለማምጣት ቁርጠኛ አለመሆኑን ከተሰጠው መግለጫ መረዳታቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስታውቀዋል፡፡ በሀገሪቱ በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለተፈጠሩት ችግሮች መፍትሄው ውይይትና ብሄራዊ እርቅ ማካሄድ ብቻ እንደሆነ ሲወተውቱ መቆየታቸውን የጠቆሙት ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ፤ መንግስት የመፍትሄ ሃሳቦቹን አለመቀበሉን እንዳልተቀበላቸው ከመግለጫው አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ “ኢህአዴግ እታደሳለሁ ማለቱ ጊዜውን ያልጠበቀ ነው፤ ከዚህ በኋላ ቢታደስም ለውጥ አያመጣም” ሲሉ ፓርቲዎቹ የተሃድሶ ፕሮግራሙን ነቅፈውታል። የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ፤ በሀገሪቱ ለተፈጠሩ ተቃውሞና ግጭቶች የብሄራዊ መግባባትና እርቅ ማካሄድ መፍትሄ እንደሆነ ፓርቲያቸው በተደጋጋሚ ሲያሳስብ እንደነበር አስታውሰው፤ መንግስት እንደተለመደው ማሳሰቢያዎቹን ችላ ማለት ውጤቱ የከፋ ነው ብለዋል፡፡ ኢዴፓ፤ የግጭት መንስኤዎች እንዲጠኑ፣ የኃይል እርምጃ እንዲቆም በተደጋጋሚ መጠየቁን የጠቀሱት ዶ/ር ጫኔ፤ መንግስት የመፍትሄ ሃሳቦቹን ያልተቀበለው አሁንም በጉልበት
አዲስ ኮሌጅ በዲግሪ ለ5 ዓመት በቲኢቪቲ ለ3 ዓመት ያስለጠናቸውን 520 ተማሪዎች ዛሬ በአምባሳደር ቴአትር ያስመርቃል፡፡በቲኢቪቲ ፕሮግራም በአይቲ በአካውንቲንግ፣ በሰርቬይ፣ በድራፍቲንግ፣ በኮንስትራክሽንና በኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የሚያስመርቅ ሲሆን በዲግሪ ፕሮግራም ደግሞ በአርኪተክቸርና በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና በማኔጅመንት ያሠለጠናቸው ናቸው፡፡የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ለማረጋገጥ በ2009 ዓ.ም የቴክኖሎጂና የቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል በማደራጀት በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በሮድ ኤንድ ትራንስፖርትና በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት ለመጀመር ለመንግሥት ጥያቄ አቅርቦ በመጠባበቅ ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡