​​​​​​​ ስፖርት፤ ግንቦት 27 ቀን፣ 2010 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአስመራጭ ጠቅላላ ጉባኤ እያወዛገበም፣ እያነታረከም ትናንት እስከ ምሽቱ አምስት ሰአት ድረስ ዘልቋል። ፌዴሬሽኑ ራሱ ያወጣውን መመሪያ ራሱ ሲጥሰውም ተስተውሏል። በስተመጨረሻ ግን ፕሬዚዳንቱንም፣ ምክትሉንም ሌሎች አስተዳዳሪዎችንም መምረጡን ይፋ አድርጓል።…