ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ወሳኔ ለመተግበር ወሰነች

ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴዉ የአልጀርሱን ስምምነት እና በአልጀርሱ ሥምምነት መሠረት የተሰየመዉ የድንበር አካላይ ኮሚሽን ዉሳኔን ገቢራዊ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት «ያለማመንታት በቁርጠኝነት» የሚሰራ መሆኑን ገልጧል። መንግሥት የሚቆጣጠራቸውን ትላልልቅ ኩባንያዎች እና ድርጅቶች በተወሰነ ደረጃ በአክስዮን ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ መታቀዱንም አስታውቋል።…