የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወንበሮች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጠዋት ወደ ቢሯቸው ማልደው ሲገቡ የእንግዳ መቀበያ ክፍሉ ወንበሮች ተሰልፈው ጠበቋቸው፡፡ ነገሩ እንግዳ ሆነባቸው፡፡ የዚህን ቤተ መንግሥት ባሕል ገና አልለመዱትም፡፡ የተለመዱ ችግሮችን ባልተለመደ መንገድ እፈታለሁ ብለው ለተነሡት ጠቅላይ ሚኒስትር ነገሩ ከተለመደውም የወጣ መሰላቸው፡፡‹ምንድን ነው?› አሉ ሳቅ ይዟቸው፡፡‹አሰናብቱን› አለ ደንዳሳ ትከሻ ያለው የቆዳ ወንበር፡፡…