የተክሌ አቋቋም ሊቁ መምህር እንደሥራቸው ከተሰወሩ እነኾ 24 ዓመት ኾነ፤ ዳግማዊ አለቃ ተክሌን መልሱልን

አሁን ያሉን መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ መምህር እንደሥራቸው በታሰሩበት ቦታ በቅርቡ አንድ ልኡክ ጉብኝት አድርጎ ነበር፡፡ መምህር እንደ ሥራቸው፣ መመንኮሳቸውንና አዘውትረው የሚጸልዩትም በአንድ እግራቸው ቆመው መኾኑን አመልክተዋል፡፡ አሁን ዕድሜያቸው ወደ 74 ዓመት የተጠጋውን እኒህን አረጋዊ የተክሌ ምትክ እባካችሁ ፍቱልን፡፡ ~~~~~~ /ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት/ “አራቱ ኃያላን” የተባለውን መጽሐፍ በ2006 ዓ.ም. ጎንደር ላይ ስንመርቅ፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ …