በአሳሳቢው የሥነ ምግባር ጉዳይ: ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ለትውልዱ ሓላፊነት አለባቸው፤7ኛው ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች ጉባኤ እየተካሔደ ነው

ግብረ ገብ የለሽ ዓለማዊነትና የማንነት ነጠቃ ባህል፣ከተደቀኑባቸው ፈተናዎች ቀደምቱ ናቸው የሰብአዊ መብቶች እና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ኾነው፣ዓለማችንን በነውረ ኃጢአት እየዘፈቋት ነው በገንዘብ፣በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ የታገዙ ናቸውና የቤተ ክርስቲያንን የተደራጀ ምላሽ ይሻሉ በ“ክርስቲያናዊ ሉላዊነት” ዓለምን ኹሉ ደቀ መዝሙር የማድረግ አቅሙን ልናዳብር ይገባል፤ ††† ኦርቶዶክሳውያን የሰንበት ት/ቤት አባላት፣ “በዓለም እንደሐዋርያት ተብተነው ይገኛሉ፤” ቤተ ክርስቲያን፥በዓለም ያላትን ተሰሚነት የሚያረጋግጡ“ሚሊዮን ድምፆች” …