በወልቃይት ቃብትያ አካባቢ አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ

ሰሞኑን በትግራይ ክልል ስር በሚገኘው የቃብትያ አካባቢ የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆች በክልሉ ላለመተዳደር የወሰዱትን የቃለ መሃላ ውሳኔ ተከትሎ በአካባቢው አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ። ትላንት እሁድ የወልቃይት ተወላጆች በውሳኔያቸው ዙሪያ ለመምከር በተሰባሰቡ ጊዘ የአካባቢው የጸጥታ ሃይሎች የማስፈራሪያ የተኩስ እርምጃ መውሰዳቸውን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። የጸጥታ ሃይሎች በነዋሪዎች ላይ የወሰዱትን እርምጃ ተከትሎም በአካባቢው ትምህርትና የሌሎች የመሰረታዊ አገልግሎቶች መቋረጡን ነዋሪዎች አስታውቀዋል። […]