Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Member
Posts: 4196
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን የማታቆም ከሆነ እናፈነዳቸዋለን

Post by MINILIK SALSAWI » 05 Mar 2014, 15:10

XXX
እስከዛሬ ብዙ ቀልዶችን ሰምቻለው አንደዚህ ግን ያዝናናኝ ቀልድ የለም አንድ የቀድሞ የግብጽ ጀነራል ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን የማታቆም ከሆነ እናፈነዳቸዋለን አሉ ለአንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ እንድታቆም ሶስት አማራጮች አሉ ብለዋል።

የቀድሞው የግብጽ ጀነራል በቀዳሚነት ያስቀመጡት አማራጭ በኢትዮጵያ ፣በሱዳን እና በግብጽ 20 ሚልዮን የሚደርስ የሙዝ እና የዛፍ ችግኝ በመትከል እና የዝናብ ሁኔታው እንዲስተካከል በማድረግ እና አማራጭ በመስጠት ኢትዮጵያ ግድቡን የምታቆምበትን መንገድ ማመቻቸት ነው ብለዋል።

ሁለተኛው አማራጭ የቀድሞ የግብጽ ንጉስ ሱልጣን አብዱል ሃሚድ የኢትዮጵያን አንድ ሶስተኛ መሬት ያስተዳድር ስለነበር ይህን መሬት አንዲሰጠን መጠየቅ ነው ያሉት የቀድሞ ጀነራል የዩጋንዳ አንድ ሶስተኛ መሬትም የግብጽ ንብረት እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህንንም ለማድረግ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደተዘጋጁ ነው የሚናገሩት። ሁለቱ አማራጮች የማይሰሩ ከሆነ ግን « በመሬታችን መሞት የለበንም መሞት ካለብንም ግድባቸው ስር ነው መሞት ያለብን ስለዚህ እዛው ሄደን ልንፈነዳቸው ይገባል በመሆኑም ኢትዮጵያ ከሶስቱ አማራጮች አንዱን መምረጥ አለባት» ብለዋል።
እንኳንስ ለሙቅ ለገንፎም አልደነግጥ አለ የሃገሬ ሰው!! አፈነዳለሁ በሎ ፈነድቶ የአሞራ እራት መሆን እንዳለ አያውቁም እንዴ ጀነራል? ቂቂቂ ቂቂቂ ቂቂቂ ቂቂቂ በነገራችን ላይ ጀነራል ሶስቱም የኛ ምርጫ አይደሉም የኛምርጫ ወንዛችንን መገደብ ነው…እኔ የሚገርመኝ ኧረ ግብፅ በጣም አበዛችው
አንድ ሰሞን ክቡር ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ እንዲህ ሲሉ ሰምቼ ነበር " ለሚያስፈራራክ ሰው መፍትሄው አለመፍራት ነው " ሳስበው ሳስበው ይህ ሰው ጅል እንጂ ጄነራል አይደለም!! ቂቂቂ ቂቂቂ ደስ የሚለው ነገር ጅነራሉም ሆኑ አንዋር ሳዳት አንድ አይነት እምነት አላቸው እዚያው ሄደን እንሙት !! እኛ መግደል መገዳደል ሰልችቶናል ሁላችንም በህይወት እንኑር ነው አቋማችን እግድህ የኛ መሬት ለባዐዳን መቀበርያ ይመች ይመስል የአሁኑ ትውልድም እንደ ድርቡሽ እዚያው እንሙት ቢያንስ እንደ ጣልያኖቹ የገዳዮችና የሟቾች ሃውልት በኢትዮጵያ ምድር ይኑረን አጥንታችን በኢትዮጵያ መሬት ካልተቀበረ የሞትን አይመስለንም ካሉ ባንወደውም ባንፈልገውም ሙትን ለመቅበር ከሟቹ ይልቅ ጉልበትና አቅም ይጠይቃልና ለዚያው መዘጋጀት ነው አንድም ሞት የናፈቃቸው ግብጻውያንን እዚየው ጣሕሪር አደባባይ ላይ ሞታቸው እንድከናወን መጸለይ ነው ካልሆን ግን ምን ይደረግ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደር ? ይስሙኝ እማ ጀኔራል በአባይ የመጣ እንኳን የኢትዮዻያ ወጣት እማማ አያቴ ትዘምታለች.ቂቂቂ እንዳዉም አረፈዳችሁ ቂቂቂቂቂቂ ቂቂቂ
ጀነራል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ''ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥'' ይላል እግዚአብሔር።
ትንቢተ ኢሳይያስ 19;1-10 ላይ
ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እይበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።
2፤ ግብጻውያንን በግብጻውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድምም ወንድሙን፥ ሰውም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።
3፤ የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፥ ምክራቸውንም አጠፋለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን በድግምት የሚጠነቍሉትንም መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ጠንቋዮቻቸውንም ይጠይቃሉ።
4፤ ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
5፤ ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል።
6፤ ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም፤ ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ።
7፤ በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም።
8፤ ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ።
9፤ የተበጠረውንም የተልባ እግር የሚሠሩ፥ ነጩንም ልብስ የሚሠሩ ሸማኔዎች ያፍራሉ።
10፤ ደገፋዎችዋም ሁሉ ይሰባበራሉ፥ የደመወዘኞችም ነፍስ ትተክዛለች።

ይስሙኝ እማ ጀኔራል በነገራችን ላይ ይኼን ግድብ ማፈንዳት አይደለም መገላመጥ በነፍስ ያወራርዳል፡፡ግድቡ የኢህአዴግ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ ኢጣሊያንን ያየ በእሳት አይጫወትም" አለች እማማ አያቴ . ቂቂቂ ቂቂቂ ቂቂቂ አይ አቅምን አለማወቅ ያሳዝናል የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫ መታጠቅ እንዲህ የሚያስፈነጭ መስሏቸው ከሆነ ከጣሊያን ይማሩ፡፡ጦርነት ሚጠይቀው ወኔና አላማ ነው ፡፡እንኳን ለግድባችን ….ይሞታል፡፡ታሪክ ጠይቁ የማን ልጆች እንደሆንን የሚኒልክ እና የቴድሮሥ አንፈራም ነገርዬው ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ አይነት ነው ግድቡ ስር ለመሞት መጀመሪያ መድረስ ይጠይቃል፤ ማፈንዳቱ ሳይሻላችሁ አይቀርም? ግን ልታፈነዱ ስትመጡ ልትፈነዱ አንደምችሉ አስባችሁ ግቡ! አገሪቱ ኢትዮጵያ, ህዝቡ ደግሞ የአድዋ ባለ ታሪክ ጀግና አንደሆነ ለአፍታም አንዳትዘነጉ! ቀልደኞች ቂቂቂ!! ጋሸ ጀነራሉ ወግ ከወግነቱ አልፎ አያውቅም ሞያ በልብ ነው ካወራህ ይበቃህል ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ለጠላት የተንበረከኩበት ዘመን የለም የታሪክ አሻራውን ማየት ከፈለክ ሜዳውም ፈረሱም ይህው። ጋሸ ጀነራሉ እንደዚህ አይነት ቀልድ ግብፅም ጀመረች እኛ ማን እንደሆን አታቅም እንዴ? ካላወቀች ጣሊያንን ትጠይቅ! ጀግኖቹ ኢትዮዽያኖችነን!!! ከእሳት እንዴት ችላ ትጠጋለች!! እኛ እኮ ለሚጠሉን እሳት ነን ለሚወዱን ደግሞ ዉሀ ነን.. እ!

ስሙኝማ በነገራችን ላይ አረብ ሲባል የሻገተና የአስተሳሰብ ደኃ ነው፡፡ እንደልማዳችሁ እናፈነዳለን ብልችሁ ስትነሱ እራሳችሁ ላይ አፈንድታችሁ ታልቃላችሁ፡፡ አሁን የጨዋታው ህግ ተቀይሯል፤ እንኳንስ የኃይል እጥረት እያለብን ይቅርና ቢተረፈረፈንም ግድቡ አይቆምም ፡፡ ደግሞ እንዳይገርማችሁ ፤ ይህ ከአራቱ ግዶቦች የመጀመሪያው ነው 3ቱ በቅርብ ጊዜ በቅደም ተከተል ግንባታ ይጀመራል፡፡ ስለሆነም ውኃችን ነዳጃችን ነው ፡፡ ነዳጂ በነፃ አለ እንዴ??? በነገራችን ላይ ጀኔራል ሙዝ እና ችግኙም አሪፍ ሀሳብ ነው። ከግድቡ በኃላ ወደዛም እንዘምታለን ቂቂቂ ቂቂቂ በነገራችን ላይ ጀኔራል ይልቁንም ለብዙ ሺህ አመታት ያለከልካይ የአባይን ውሃ ተጠቅመዋል ስለዚህ ለኢትዮጵያ በርካታ በሊዮን ዶላር ሊከፍሉ ይገባቸዋል!!!!
አሁን ነው መበቀል አረብን እስካሁን በትንሽ ሳንቲም የአበሻን ጉልበት የበዘበዙበት ሳያሳቸው በዚም መጡ ይሄ ግድብ ክብራችንን ከፍ የሚደርግልን ነው በዛውም ልክ ግድቡ ላይ ጥቃት ደርሶ ማለባበስ በቁም እንደመሞት ነው ለአገራችን ክብር መንግስት ራሱን ሊዘጋጅበት እና በማንኛውም እንቅስቃሴ አፀፋዊ መልስ ሊሰጥ ይገባል የስካሁኑ ውርደት በአረቦች ይብቃ ካለበለዚያ ሀገርንም በማስደፈር እስካሁን ከነበሩት መንግስት ቀዳሚው የትውልድ ተወቃሽ መሆኑ ማይቀር ነው እናም መንግስት በሁሉም ነገር አፀፋዊ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆን ይገባል፡

ስሙኝማ ነገርዬው ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ አይነት ነው፡፡ ግብፆች ከድርድር ውጪ የጦርነት አማራጭ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ የተያያዙት ተራ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ነው፡፡ ያው ማስፈራራት ነው፡፡ ቢሆንም በደካማ ጎናችን አይጠቀሙም ማለት አይታሰብም፡፡ የግብፅ ግብረሰናይ ድርጅቶችም ሆኑ ማናቸውም የግብፅ መሰረት ያላቸው የኢንቨስትመን ስራዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ካልተደረገ ሊጎዱን ይችላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ሊሰራ የሚችል ወታደራዊም ሲቪል ደህንነት ተቋም ሊመሰረት ይገባል፡፡ መስራት ከባድ ነው፡፡ ማፍረስ ቀላል ነው፡፡ የቁማር ጨዋታው ውጤት ግልጽ ስላይደለ መዘጋጀቱ አይከፋም፡፡ በድንበር አካባቢ ያለንን የፀጥታ አጠባበቅ ማጥበቅም ግድ ይለናል፡፡
ግድቡ ተዓምር ባያመጣልን እንኳ ግብፅ ለዘመናት ያፈራረሰችንን ማካካሻ ስለሚሆን ለእኔ ልዩ ትርጉም አለው፡፡ ለብዙ ላልተገለፁ ነገሮችም መሰረት ይሆናል፡፡ አይደለም 6ሺ 200 ሜጋ ዋትም ካመነጨ በድል አድራጊነት እንዳጠናቀቅን እቆጥራለሁ፡፡የግብፅን የውስጥ መተራመስ ፈጣሪ ለኛ ብሎ ያደረገው እንደሆነስ ማን ያውቃል! ባይሆን ኖሮ የሚተኙልን አይመስለኝም፡፡ በዚህ ምስቅልቅል ጊዜ ይህን ያህል ከተንፈራገጡ ደህና ቢሆኑ ውጤቱን ገምቱ…መንግስትም ለማናቻውም ማስፈራራት ተመጣጣኝ ምላሽ መስጠት ይኖርበታል፡፡ ግድ ነው፡፡
ይስሙኝ እማ ጀኔራል በትምቢቱ ኢሳያስ መዝ67:31 ኢትዮጵያ ላይ ጦርን እንዳታነሱ ትደቃላችሁ ብሏል።በደንብ ይወቁን ይምጡ ሙዝ እንዳሉ የርሳስ ሙዝ በልተው ይሄዳሉ።
ቂቂቂ ቂቂቂ
ህዝብ ሆይ ስማ እንደወርቅ የነጠረ እንደ ብር የነጣ ሀበሻዊ ማንነትህ በሙዝ ተቀይራል እና መሳሪያም ያለህ መሳሪያ ጀገሪያም ያለህ ጀገሪያ አንካሴም ያለህ አንካሴ እነኚህ የሌላችሁ ወኔአችሁን ይዛችሁ ወደ አባይ ውጡ ይህን ማድረግ ያልቻለ ሀበሻ ቢኖር እንጣላለን ማርያምን!!!!!!!
አሁንስ ትግስቴ እያለቀ ነዉ ያአባቴን ak-47 መሳሪያ ይዤ ልሸልል ነዉ ያበጠ ይፈንዳ ምነዉ ሸዋ
አረ ጎራው አረ ጎራው ንቡ ወለደና ቀፎውን ጨነቀው፣
ማር ብቻ መስሎታል መርዙን አላወቀው፣
የማን ዘር ነኝና ከማስ ተወልጄ
ሚኒልክ ያወረሰኝ ዛሬም አለ በጀ።
ዘራፍ ዘራፍ የማንን ሀገር ማን ይነካታል፣
ካለ ሀበሻ ያስከብራታል።
የማን ቤት ጠፍቶ የማን ሊበጅ፣
የአውሬ መውለጃ ይሆናል እንጂ።
ዘራፍ ዘራፍ!!! ዘራፍ!!! ዘራፈ!!
የምኒሊክ ልጅ ነኝ የበላይ የዛ ሳተና
ለጣልያንም ያልተኛ ቆራጡ ጀግና እኔነኝ ያለ ይሞክረኛ !!! ዘራፍ ዘራፍ!!!ተተተተተተተተተ ''ኢትዮጵያ ታበፅእ እደዊሀ ሀበ እግዚአብሄር
እንግዲ እነሱ በሚፈልጉት አማራጭ መሄድ ይችላሉ መብታቸው ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ያለን አንድ እና አንድ ነው ያለን ያም የኃያላን ኃያል የነገስታት ንጉስ በረዶ የሚያዘንብ ፈርኦንን ከነሰራዊቱ በባህር የጣለ ድንቅ መካር እና ኃያል አምላክ ነው እሱም እጃችንን ዘርግተን ለምነን ከኛ ጋር ነው ስለዚህ ቀድመን አሸንፈናቸዋል
እኛስ እንሙት ችግር ብርቃችን አይደለምና መጪው ትውልድ ግን እኛ ያየነዉን ችግር እኛ ያለፍንበትን የድህነት ህይወት መቅመስ የለበትም ብሔር ሀይማኖት ሳይለየን ሁላችንም በአንድነት ለመጪው ትውልዳችን መስዋት ከፍለን ማለፍ አለብን ስም አይሞትም ታሪክም አይሞትም::እነሱ ያውሩ እኛ እንሰራለን ©2014 ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከ Love on The way