በኦሮሚያ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ስራቸውን እየለቀቁ ነው - Amharic News

በኦሮሚያ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ስራቸውን እየለቀቁ ነው

News, analysis and views in Amharic

በኦሮሚያ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ስራቸውን እየለቀቁ ነው

Postby Admas » 28 Dec 2012, 04:31

ኢሳት ዜና:- በኦሮሚያ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ነው ስራቸውን የሚለቁት። አምና ከ100 በላይ ዳኞች ስራቸውን የለቀቁ ሲሆን በያዝነው አመት ደግሞ ቁጥሩ በእጥፍ ጨምሯል።

ከአንድ ወር በፊት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ታደለ ነጊሾና አቶ ሰይድ ጁንዲን ስልጣናቸውን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እንዲለቁ ከተደረጉ በሁዋላ፣ ችግሩ መባባሱ ተገልጾአል።

ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች አሁን ባለው የፌደራል ስርአትና በክልሉ መንግስት ላይ አመኔታ ስለሌላቸው ከስልጣን እንዲለቁ መደረጋቸውን ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ዳኞች ለኢሳት ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር140/99 ፕሬዚዳንቱና ምክትሉ ከስልጣን የሚወርዱት በፈቃድ፣ በህመም ፣ በጡረታ ወይም ቅሬታ ካለ ቅሬታው ለምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ቀርቦ አስፈላጊው ማጣራት ከተደረገ በሁዋላ መሆኑን ቢደነግግም፣ አቶ ታደለና አቶ ሰይድ እንዲወርዱ የተደረገበት አካሄድ ግን ከዚህ የተለየ ነው ብለዋል።

ከሶስት ሳምንት በፊት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት አቶ ሙዜማም በኦህዴድ አመራር አባልነታቸው የሚታወቁና ገዢውን ፓርቲ ደግፈው በመገናኛ ብዙሀን ሲከራከሩ የነበሩ ናቸው።

ከዚህ ቀደም በዳኞች ላይ ይፈጸሙ የነበሩት የመብት ጥሰቶች አሁንም ተጠናክረው በመቀጠላቸው ዳኞች ተቃውሞአቸውን ለማሳየት ስራቸውን በገፍ እየለቀቁ ነው።

የአዲሱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሹመት ” ህዝብን መናቅ፣ ህዝብ ምን ይመጣል?” በሚል የተደረገ መሆኑን አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ተናግረዋል። “ትናንት ድርጅቴ ኢህአዴግ እንዲህ አድርጎአል እያሉ በሚዲያ ሲናገሩ የነበሩ ሰው ዛሬ ፍትሀዊ ዳኝነት ይሰጣሉ ብሎ ማሰብ አይቻልም” ያሉት ዳኛው፣ ዳኞች ሃላፊነታቸውን እየለቀቁ ከመሄድ ውጭ ሌላ አማራጭ የላቸውም ብለዋል።

ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ስልጣናቸውን እንዲለቁ የተደረጉት ፕሬዚዳንቱ ፣ የተረከቡትን እቃ አላስረክብም በማለታቸው በደህንንቶች ክትትል ስር እንደነበሩ ለማወቅ ተችሎአል።

በክልሉ የሚታየው ጎሰኝነት እየጨመረ መሆዱም ዳኞች ስልጣናቸውን እንዲለቁ ተጨማሪ ምክንያት መሆኑም ታውቋል።
Admas
Junior Member
 
Posts: 685
Joined: 14 Jul 2007, 14:56

 
Post details

Re: በኦሮሚያ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ስራቸውን እየለቀቁ ነው

Postby Guest1 » 28 Dec 2012, 11:44

gobbledygook! 8)

Oromo oppressing oromo, increased racism in Oromia? laughable!

Oromo judges are leaving their position as a protest against EPRDF's unbalanced federal system? Are you telling us this is a novel oromo way of protest. leaving jobs? It is similar to what OLF did in 1993 when they left by the airport. foolish! have they gone into exile or back to farming? lol

ay Esat!

equal power sharing within EPRDF is essential for democracy. But the most important part of democracy is respecting minority rights? Are minority rights respected in Oromia? This is what you have to find out and work with!!! you idiots!
Guest1
Junior Member
 
Posts: 1353
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: በኦሮሚያ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ስራቸውን እየለቀቁ ነው

Postby kk » 29 Dec 2012, 01:54

All present judges should be swept and be imprisoned as they all are unjust & corrupted and against the rule of law.Who cares for them?
kk
 

Re: በኦሮሚያ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ስራቸውን እየለቀቁ ነው

Postby kk » 30 Dec 2012, 10:15

If all judges from the supreme court down to the first instance court including their bosses are to be displayed via free TV one by one and the people of Ethiopia are allowed to criticize each of them directly using TV such as ESAT TV, you will not find a single judge who stands before. It is pity. They are there because they don't have the impetus other than being puppet. Please, you ESAT TV, use this and display them. How do you expect them to struggle for the rule of law after they bow for breaching the law? Even they never follow Birtukan who spearheads the struggle by standing on the sharp blade of the sword.
kk
 


Return to Amharic

Who is online

Registered users: BigBreak, Bing [Bot], EthiopianPride, Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, MSNbot Media, Yahoo [Bot]

cron