የህወሀት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አሜሪካ በመምጣት ከትግራይ ተወላጆች ጋር ሊመክሩ ነው - Amharic News

የህወሀት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አሜሪካ በመምጣት ከትግራይ ተወላጆች ጋር ሊመክሩ ነው

News, analysis and views in Amharic

የህወሀት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አሜሪካ በመምጣት ከትግራይ ተወላጆች ጋር ሊመክሩ ነው

Postby Admas » 28 Dec 2012, 00:37

ኢሳት ዜና:-ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ደብረ-ጽዮን ገብረሚካኤል፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሀኖም እና አቶ አባይ ወልዱ በመጪው ጥር ወር አሜሪካ በመምጣት ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ብቻ እንደሚመክሩ ተመለከተ።

የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናቱ በ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር እንዲመካከሩ መድረኩን ያመቻቸው የትግራይ ልማት ማህበር ነው።

ደብረብርሀን ብሎግ እንደዘገበው የትግራይ ልማት ማህበር በዲያስፓራ ራሱን የቻለ የትግራይ መንግስት እየፈጠረ ያለ ድርጅት ነው።

አንድ የትግራይ ተወላጅ ወደ ውጪ አገር በሚመጣበት ጊዜ ወዲያው በመመዝገብ ታክስ እንደሚሰበስብ የጠቀሰው ብሎጉ፤ ማህበሩ ከረዥም ጊዜ አንስቶ በዲያስፖራ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻቸው ለመለየት እየደከመ የሚገኝ ጽንፈኛ ማህበር መሆኑን ጠቁሟል።

ይህ ጽንፈኛ ማህበር ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ የትግራይ ብሄርተኝነትን ለማስፋፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በማውሳትም፤ በመጪው ጥር ወር ወደ አሜሪካ የሚመጡት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በ አገር ጉዳይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ብቻ እንዲሰበሰቡ የግብዣ ጥሪ ያቀረበውና ፕሮግራሙን ያዘጋጀውም ይኸው የትግራይ ልማት ማህበር መሆኑን አመልክቷል።

በሚኒሶታና አካባቢው የሚኒሩ የትግራይ ተወላጆች በተደጋጋሚ ባወጧቸው መግለጫዎች ፦የመንግስት ባለስልጣናት ወደ ወጪ አገር ሲመጡ የትግራይ ተወላጆች ጋር ብቻ ስብሰባ ማድረጋቸውን በማውገዝ፤ የህወሀት መሪዎች የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለመለያዬት ከሚከተሉት ጠባብ የጎሰኝነት መንገድ እንዲታረሙ ማሻሰባቸው ይታወሳል።
Admas
Junior Member
 
Posts: 683
Joined: 14 Jul 2007, 14:56

 
Post details

Re: የህወሀት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አሜሪካ በመምጣት ከትግራይ ተወላጆች ጋር ሊመክሩ ነው

Postby Tigre » 29 Dec 2012, 08:57

The only thing we are about to tell them during the "memekaker" is stay here, they know it already + we know it.
Tigre
 

Re: የህወሀት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አሜሪካ በመምጣት ከትግራይ ተወላጆች ጋር ሊመክሩ ነው

Postby solomon11 » 30 Dec 2012, 00:12

we have the right to do so....why did you guys keet quite while otheres did the same...ye Gondar lijoch,ye Adere, ye Oromia ...have had meetings, but no one has complained, why on Tigrayans? ??come'on America is a nation of freedom..unless you accept fedarelism you can not win for the next 1000 years!!!
solomon11
 


Return to Amharic

Who is online

Registered users: Bing [Bot], Degnet, Google [Bot], Google Adsense [Bot], Majestic-12 [Bot], minilikze3rd, MSNbot Media, Tintagu wolloye, Yahoo [Bot], Zmeselo