Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


Breaking፡- Patriotic Ginbot 7 rebel groups advanced against Ethiopian government troops in the outskirts of Gondar

Postby MatiT » 18 Nov 2016, 17:14


Patriotic Ginbot 7 rebel groups advanced against Ethiopian government troops in the outskirts of Gondar http://abbaymedia.com/patriotic-ginbot- ... of-gonder/ via @abbaymediaRe: Breaking፡- Patriotic Ginbot 7 rebel groups advanced against Ethiopian government troops in the outskirts of Gondar

Postby MatiT » 18 Nov 2016, 18:25


በአማራ ክልል እራሳቸውን ባደራጁ ወጣት ግብረ ሃይሎች የተላከ መልክት
#EthiopianRevolution : ፕወዛ የወያኔ ቡድን ጭንቅ የሚይዝ የሚጨብጠው አጥቷል ። በአማራ ክልል የሚገኙ የፖሊስ አባላትን በየአካባቢያቸው በጥልቅ ተሃድሶ ቀመር በግምገማ ሲንጣቸው ሰንብቷል። መደምደሚያውም "ከወገኖቻችሁ ጋር ቁጭ ብላችሁ ምንም አልሰራችሀም "የሚል ሁኗል። የአፉኙ ወያኔ ስራ ህብረተሰቡን ማገልገል አይደለም ፤ከህዝብ ጎን መቆም አይደለም የህዝብን ጥያቄ መመለስ አይደለም ። ይልቅስ አብይ ስራ የሚለው ህዝብን መደብደብ ማሰርና መግደል እንዲሁም ወያኔን የሚኮንኑትን የራሱም አባሎች ይሁኑ ማስወገድ ና ማፈን እንዲሁም የህዝብን ጥያቄ በሃይል ማፈንና መቆጣጠር ነው ። በአማራ ክልል ከወራት በፊት በተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት ና አመፅ በተለያዩ ቦታወች የተወሰኑት የፖሊስ አባላት ከህዝብ ጎን ሁነው ወገናዊነታቸውን ሲያሳዩ በማየቱ የተበሳጨው ወያኔ እንደ ህልሙ ያልሄዱትን መኮነንና ጫና መፍጠሩን ተያይዞታል ። ለዚህም ይመስላል "ፕወዛ " እንደአማራጭ ይዞ የመጣው ። በየተውልድ ሃገራቸው የሚገኙ የፖሊስ አባላትን ወደ ሌላ የክልሉ ክፍል ማዘዋወርና መፕወዝ አልሞ ተነስቷል ።ለማጥፉት እንጂ ለማልማት ከቶውኑ ያልቆመው ወያኔ ከአሁኑ በፖሊስ አባላት ላይ ጉርምርምታንና ተቃውሞን እያስተናገደ ይገኛል ።ይህ ተቃውሞም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ወያኔ በራሱ ጊዜ መታነቂያውን ገመድ እንዳዘጋጀ መረጃውን የላከልኝ የፖሊስ አባል ይናገራል ። ነገ ደግሞ ምን ይሆን? አብረን የምናየው ይሆናል ።Re: Breaking፡- Patriotic Ginbot 7 rebel groups advanced against Ethiopian government troops in the outskirts of Gondar

Postby MatiT » 18 Nov 2016, 18:26


Patriotic Ginbot 7 rebel groups advanced against Ethiopian government troops in the outskirts of Gondar
By posted by Surafel - November 17, 20160
Share on Facebook Tweet on Twitter

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy, an organization which is led by Berhanu Nega, a former Bucknell University professor turned to rebels leader, claimed that the military wing of the movement have advanced against the Ethiopian government troops in the area of Gondar.

Abbay Media sources who reside in Eritrea and have knowledge of this specific military operation told us that there were a fierce fight between Patriotic Ginbot 7 rebel groups and government troops for the past ten days. One of the sources who is not authorized to speak on record with this very sensitive information has confirmed to us that the fight between the rebels and government troops is still ongoing in the outskirts of Gondar. There is no official statements given either from the government or Patriotic Ginbot 7 regarding this matter.Re: Breaking፡- Patriotic Ginbot 7 rebel groups advanced against Ethiopian government troops in the outskirts of Gondar

Postby MatiT » 18 Nov 2016, 19:05


ሰውየው ---ብርሃኑ ነጋ ( ሄኖክ የሺጥላ )
አጭር ፍቅር (አንድ ሰሞን from my file)
ሰውየው ሕልም አለው ። የአንደበቱ ርትዖነት ካለው የቃላት አጠቃቀም እና ልቀት ሳይሆን የሚመነጨው ከሃሳቡ ጠጣርነት እና ከቆመለት ትልቅ እውነት እንጂ !
ሰውየው ሕልም አለው ፣ ለዚያውም በሞቀ ቤት እና በቀዘቀዘ ቢራ ውስጥ በሚደረግ የሳይበር ጦርነት የሚጸና ሳይሆን ፣ የማሽላ እንጀራ እየበላ አፈር ላይ እየተኛ ፣ ከእባብ እና ገጊንጥ ጋ እየተታገለ ፣ በሞርታር እና በፈንጂ ወረዳ ውስጥ ውድ ነብሱን አቁሞ የሚሞትለት እጹብ ሕልም ።
ሰወየው ትሁት ነው ፣ የትልቅነት ሚስጥሩ ምን እንደሆነ የገባው ትሁት ። ሕልሙ ባለ ወፍራም ቆዳ ያደረገው እንደራሴ ፣ አላማው ለትንንሽ ነገሮች እና በትንንሽ ነገሮች ከማኩረፍ እና ከመኮፈስ ነጻ ያወጣው የኔ ዘመን በትረ አሮን ። በግልምጫ እና በእርግጫ ፖለቲካ ውስጥ ሊባክን የሚችል ታል-ኢት ( የሰኮንድ ግማሽ ) የሌለው ሰው ። ሰውየው አፋር ነው ሃገሩ ፣ ጎጃሜም ነው ፣ በኦሮሞነቱ አይታማም ፣ ጥርት ያለ ጉራጌ ነው ፣ ዘሩን የቆጠሩ ሱማሌ ስለመሆኑ ይናገራሉ ፣ አብረውት ያደጉት እና በቅርብ የሚያውቁት ስለመንዜነቱ የሚያውቁትን ሁሉ ሳይደብቁ ያወራሉ ፣ እርግጥ ሰውየው ኢትዮጵያዊ ነው ። ማነስ አይችልም ፣ በጎጥ እና በጎሳ ፣ በአውራጃ እና ወረዳ ፣ ተቆርሶ እና ተሰባብሮ የሚነገር ማንነትም ሆነ ፣ የሚቆጠር ደም የለውም ። ሕሉሙ ከደሙ ጋ አንድ አይነት ነው ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና ዘረ ኢትዮጵያዊ ፣ ሰወየው !
ስለ ሰውየው ሳስብ ኩራት ይሰማኛል ፣ ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት እንደማይሞት ምሳሌ ሆኗልና ፣ ቃሉን አላጠፈምና ፣ የሚኖርለት ሰው ባይኖር እንኳ የሚሞትለት ክብር እና ነጻነት ያለው ስለሆነ ። በቅርቡ ዋሽንግተን ዲስ ባደረገው ንግግር " እዚህ ውስጥ ብዙ የማውቃችሁ ጓደኞቼን ወዳጆቼን አይቻለሁ ፣ ሁሌ አስባችሗለሁ ፣ ላናንተ ብዬ ግን ከምሄድበት አልቀርም " የምትለዋን ሐረግ ድግሜ ደጋግሜ አደመጥኩ ፣ በእድሜ የሱ እኩዮች የሆኑ ፣ እንደሱ ወይም ከሱ በላይ የተማሩ ፣ ሀገር ሀገር የሚሉ ግን አንዳች ቁም ነገር ያለው ሥራ መስራት ያልቻሉት ወዳጆቹ ምን ይሰማቸው ይሆን ? እነዚህ በጥላቻ እና በማጥላላት የፖለቲካ ቁማር የሰከሩ << የፖለቲካ ቁሞ ቀሮች >> ወይም ዊዶዎች ይህንን ሲሰሙ ምን ይሉ ይሆን ?
እርግጥ ይህንን ጽሑፍ ከምታነቡት ሰዎች ውስጥ ኣንዳንዶቻችሁ እያሽቃበጥኩ ሊመስላችሁ ይችላል ። አልተሳሳታችሁም ፥ ኣዎ እያሽቃበጥኩ ነው!! ሰው እንኳን ለብርሃኑ ነጋ ለወያኔ ያሽቃብጥ የለ ?! ታዲያ ምን ሽግር ኣለው ?
ሺዎች ከጎንህ ነን ። ከጎንህ ያቆመን ደሞ የቆምክለት አላማ ነው !
ሄኖክ የሺጥላ
I just got this short article from my file which was written by #Henok Yeshitila የዛሬውን አያድርገውና!
ለትዝብት አንብቡት##EthiopianRevolution #OromoProtest #AmharaProtest #AG7 aka #ENM2016Re: Breaking፡- Patriotic Ginbot 7 rebel groups advanced against Ethiopian government troops in the outskirts of Gondar

Postby MatiT » 18 Nov 2016, 20:02


EthiopianRevolution : አርበኞች ግንቦት ሰባት ወይኔ ላይ የጀመረው ጥቃት ለሶስተኛ ቀን እደቀጠለ ነው ዝርዝሩን ይዤ እመለሳለው
ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር በመሆን ኢትዮጵያዊነት ይዞ ወደፊት❗️Re: Breaking፡- Patriotic Ginbot 7 rebel groups advanced against Ethiopian government troops in the outskirts of Gondar

Postby MatiT » 18 Nov 2016, 20:03


EthiopianRevolution : (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
***********************
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ፡፡ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡
**********************
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ህዳር 07 ቀን 2009 ዓ.ም ከትናነት ወዲያ ቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይ ነብሪ የተባለ ቦታ ለረጅም ሰአት የፈጀ ውጊያ ያደረገ ሲሆን በወያኔ ሰራዊት ላይም ብዛት ያለው ሙትና ቁስለኛ እንዳስቆጠረ ከስፍራው አርበኛ ታጋዩ ሪፖርተራችን ካደረሰን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በትናንትናው ዕለትም ቃፍታ ሁመራ ርዋሳ አካባቢ ልዩ ስሙ ማይጐነጥ የተባለ ቦታ ተመሳሳይ ጥቃት የፈፀመ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰአትም ውጊያው የቀጠለ መሆኑ ሲታወቅ የአርበኞች ግንቦት 7 የተገኘውን ወታደራዊ ድል በአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ በእሁድ ዜና እወጃችን ላይ ዝርዝሩን ይዘን የምንቀርብ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እስከ አሁን ባደረገው እንቅስቃሴ የአካባቢው ነዋሪ ከጐኑ የተሰለፈ መሆኑን ያሳወቀው ሪፖርተራችን፤ በአካባቢው ያለው የወያኔው ሚሊሽያ ኃይልም ከወንድሞቻችን ጋር ውጊያ አንገጥምም በማለት እንዳመፁና ብዛት ያላቸው የሚሊሽያ አባላትም ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጐን መሰለፋቸውንም ዘግቧል፡፡Return to Ethiopian News & Opinion

Who is online

Registered users: Awash, Bing [Bot], densa, Google [Bot], Google Adsense [Bot], Lilay, Majestic-12 [Bot], Superior ER, Yahoo [Bot]