Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


A timely call to all Ethiopians!

Postby revelations » 29 Apr 2012, 13:00


By negashi,on April 28th,2012

ለወገኖቻችን ስቃይ እኛ ካልጮህን ማን?
ዛሬ ካልጮህንስ መቼ?


Image

አዎ! የዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ ቡድን በወገኖቻችን ላይ እየፈጸመ ያለውን በደልና ስቃይ የእንግልቱ ሰለባ የሆኑት ኢትዮጵያዊያን በእየዕለቱ ከሚያሰሙን የድረሱልኝ ጥሪ በተጨማሪ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም ይህንኑ የወገን ያለህ ጥሪ እየዘገቡት ይገኛሉ። ይህ የህዝባችን ሲቃ እንዲያበቃ ደግሞ ዛሬ ልናደርግ ከሚገባን በርካታ ተግባራት መካከል በተባበረ ድምፅ ስቃዩና ማፈናቀሉ በኢትዮጵያውያኑ ላይ በአስቸኳይ እንዲቆም ተባብረን የቁጣ ድምጻችንን ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ማሰማት አንዱ ጉዳያችን ነው ብለን እናምናለን። ስለዚህም የአገዛዙ ደጋፊዎችና ቀለብ ሠፋሪዎች የሆኑ መንግስታት ለወያኔ እየሰጡት ባለው ድጋፍ በህዝባችን ላይ ምን እየተፈጸመ መሆኑን እንዲገነዘቡት ለማድረግና ተቃውሞአችንንም ለመግለጽ፣ ለየተወካዮቻቸውም ማስረዳት አስፈላጊ ስለሆነ የመጀመሪያውን የተቃውሞ ድምፃችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ልናሰማ ቀጠሮ ይዘናል። ዋሽንግተንም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ /ስቴት ዲፓርትመንት / በር ላይ ተቃውሟችንን እናደርጋለን።

በዚህም የተቃውሞ ሰልፍ ላይ፤ ከ 78 000 በላይ አራሽ ገበሬዎች ከደቡብ ኢትዮጵያ የሃገራችን ክፍል አማራ በመሆናቸው ብቻ በጎሳ ፅዳት እየተፈናቀሉ ስለሆነ ይህ ህገውጥ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም፣
 በተመሳሳይ ጥቃት ከ 70 000 በላይ የጋምቤላ ነዋሪዎች ተፈናቅለው መሬታቸው ለሳውዲ ቱጃሮች የመሸጡን ተግባር ለማውገዝና ማፈናቀሉ ዛሬም ቀጥሎ በአፋር ህዝብ ላይ ያለው አዲስ ማፈናቀል በአስቸኳይ ቆሞ ነዋሪው ህዝብ ዋስትና እንዲያገኝ ለመጠየቅ፣
ክርስትናን ከኢትዮጵያ ለመንቀል በዝቋላ፣ በአሰቦት ገዳማትና በሌሎቹም ላይ ሆን ተብሎ የሚለቀቀው እሳት በአስቸኳይ እንዲቆምና የዓለም አብያተ ክርስቲያናትና ቅርስ ተንከባካቢ ድርጅቶች ጉዳዩን አውቀውት የመፍትሄ ርምጃ እንዲወስዱም ለመጠየቅ፣
 በዋልድባና በሌሎቹም ገዳማቶቻችን ላይ በልማት ስም ሃይማኖትና ቅርስ እንዴት እየተናደ እንደሆነ ለሚመለከተው ሁሉ ለማስገንዘብና ድርጊቱም በአስቸኳይ እንዲቆም ለመጠየቅ፣
 የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን የራሴ የሚሉትን እምነታቸውን በሰላም እንዳያራምዱ፣ ይልቁንም መጤ ሃይማኖትን ያለፈቃዳቸው እንዲቀበሉ በአገዛዙ በተፈጠረባቸው ጫና እየተሰቃዩ መሆናቸውን ማጋለጥና ድርጊቱም እንዲቆም ለመጠየቅ፣
 በህዝባችን ላይ በአጠቃላይ እየተፈጸመ ያለውን ህገ ወጥ የመሬት ነጠቃ፣ የዘረፋ ሊዝ ፖሊሲና ኢትዮጵያን ለባዳን ኢንቬስተሮች የመቸብቸቡ ጉዳይ በአስቸኳይ እንዲቆም ለመጠየቅ፣
 ቁጥራቸው ከ35 ሺህ በላይ የሚሆኑት በወያኔ እሥር ቤቶች የሚማቅቁት ኢትዮጵያዊያንን ዓለም እንዲታደጋቸው ለማስገንዘብ፣ እና 
በየሃገራቱ ያለውን ኢትዮጵያዊ ስደተኞችን የማንገላታት ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲቆም ለመጠየቅ ተዘጋጅተናል።

የህዝባችን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሀገራችን የነገ እጣ ፋንታ የሚሰማችሁ ወገኖቻችን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ፤ ጎሳ፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ እንዲሁም የቡድን ስሜት ሳያጥራችሁ፥ የመለየትን አጥርን አፍርሳችሁ፥ ስለወገኖቻችን መከራ ጊዜ አጣን ሳትሉ ለሁለትና ሦስት ሰዓት ሁላችንም ወጥተን በወገኖቻችን ላይ የሚፈፀመው ሰቆቃ እንዲያበቃ በአንድነት እንድንጮህላቸው ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ቦታ፤ ስቴት ዲፓርትመንት አድራሻ፤ 22ተኛውና (ሲ) ስትሪት ኖርዝ ዌስት ዋሽንግተን ዲሲ

ቀን፤ ሰኞ ሜይ 7 ቀን 2012 (እ.አ.አ)

ሰዓት፤ ከጠዋቱ 9፡00 ኤ ኤም

የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ

http://blog.ethiopianmuslims.net/?p=2155#more-2155Re: A timely call to all Ethiopians!

Postby revelations » 29 Apr 2012, 13:29


ImageRe: A timely call to all Ethiopians!

Postby Aba-Dula » 29 Apr 2012, 15:43


This is indeed a timely call for those thet would heed to the call. There is no better time than today to have that galvanize effect to bring TPLF junta down.Re: A timely call to all Ethiopians!

Postby Conformist » 29 Apr 2012, 15:54


The missing ingredient is the one leader that can galvanize all, without a leader there really can be no coordinated fight. I think we all have to bear it and grin until one competent leader emerges. If Ethiopians can find a man the caliber of Isaias, then we're talking business.Return to Ethiopian News & Opinion

Who is online

Registered users: AbebeB, Bing [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, Majestic-12 [Bot], MSNbot Media, Superior ER, Yahoo [Bot]