Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11187
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የኦሮሙማ ተረኞች ምን ተበደልን ብለው ነው ኡኡ ጆባይደንዬ ከትግሬ ኮርጀው የሚንከባለሉት? ወለጋ፤ አሩሲ ወዘተ አማራ ሲታረድ የትነበሩ?! ፍትህን አንቆ የገደለ ኦሮሙማ ፍትህ ከየት ይምጣ

Post by Abere » 19 Apr 2024, 16:23

ደግሞ የኦሮሙማ ተረኞች ምን ተበደልን ብለው ነው ኡኡ ጆባይደንዬ ከትግሬ ኮርጀው ውጭ አገር የሚንከባለሉት? የአየሁት አይቀረኝ። ወለጋ፤ አሩሲ ወዘተ አማራ ሲታረድ የትነበሩ?! ፍትህን አንቆ የገደለ ኦሮሙማ ፍትህ ከየት ይምጣለት። የትግሬ ተራ ይደርሰዋል - አይቀርም።

I have Zero doubt reluctant Oromos who enjoyed in the suffering of innocent Amhara, most of whom their next neigbour, will taste what Tigres tasted after the ignominious defeat of rag tag Woyane. Tigres were silent about TPLF for over 27 years when Amhara in Raya and Humera were murdered and took over the victims land and wealth. God graciously in the end paid them, the same will happen to fanatic Oromos now harassing innocent Amhara people. To see those fanatic Orommuma thugs rolling on the ground and crying foul is very disgusting - they have been emboldening child and women killer OLF. These fanatics were dancing when innocent Ethiopians in Burayo were murdered to receive bloody Dawud Ibssa from Asmara, where he had been training how to cleanse Ethiopians. The most disgusting rag tag OLF-PP

Abere
Senior Member
Posts: 11187
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የኦሮሙማ ተረኞች ምን ተበደልን ብለው ነው ኡኡ ጆባይደንዬ ከትግሬ ኮርጀው የሚንከባለሉት? ወለጋ፤ አሩሲ ወዘተ አማራ ሲታረድ የትነበሩ?! ፍትህን አንቆ የገደለ ኦሮሙማ ፍትህ ከየት ይ

Post by Abere » 20 Apr 2024, 09:27

ይሉኝታ የሰውን ቤት የፈታ - የሚል የአማርኛ አባባል በዚህ ትውልድ ዘመን እውነትነት ያለው ምሳሌያዊ አገላለጽ ነው። ለበርካታ አሥርት አመታት የትግሬ እና የኦሮሞ አክራሪዎች ስለ ኢትዮጵያ ያላቸውን ጥላቻ እና በአማራ ላይ በጠቆረ ልባቸው የታመቀውን መሪር ጥላቻ ጊዜያዊ እና ምናልባትም በአንድ አንድ የተሳሳቱ ግለሰቦች የሚናፈስ አድርጎ በማየት የፓለቲካ ትክክለኝነት አስተያየት ይሰጥ ነበር። ይህ አይነቱ መቻል እና ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ ለጥቂት አመታት መልካም ነበር - ምክንያቱም ሰዎች በቶሎ ወደ በጎ ህሌና ሊመለሱ ይችላሉ - ወቅታዊ ሁኔታ ነው በሚል እሳቤ። ዳሩ ግን ለ3 እና ከዚያ በላይ አስርት አመታት የቆየ ልማድ ከሆነ ደግሞ የትውልድ ለወጥ የተዛባውን አመለካከት ነባር አድርጎ ስለሚጓዝ በይሉኝታ ደበሎ ተጀብኖ መኖር አደገኛ እና እራስን በማታለል እራስን ለአደጋ መጣል ነው።

ዛሬ እራስ ቅል ጠጉራቸው ጥጥ መስሎ የሸበቱ በርካታ ኦሮሞዎች እና ትግሬዎች ምናልባትም በ60ዎቹ እና ከዚያ በላይ ያሉ በየምዕራቡ አለም የወያኔን አስቀያሚ ቅዘንማ ጨርቅ እና የኦነግን ጎመኔ አርማ በማውለብለብ በመንገድ ላይ የሚንከባለሉት እና ኡኡታ የሚያቀልጡትን ስንመለከት በይሉኝታ መታለል ከፍተኛ ስህተት ነው ። ትግሬ ወያኔ አይደለም ኦሮሞ ኦነግ አይደለም ብሎ ከመዘናጋት ትግሬ ወያኔ የመሆን ኦሮሞ ኦነግ የመሆን ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ይህን በዘመናት የትውልድ ለውጥ እና ስህተት ትርክት የተመረዘ ትውልድ ለመቀየር የግደታ አብዮት ያስፈልጋል።ይህ አብዮትም ለዚህ መርዝ ምክንያት የሆኑትን ኦነግ እና ወያኔን መደምሰስ ብቻ ነው። አብሮ መኖር የሚቻለው የኦነግ እና የወያኔ ድርጅት አሸንፎ በመደምሰስ እንጅ በይሉኝታ አይደለም። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል በርካታ አማራዎች ምንም አይነት ፓለቲካ ይሁን የክፍለ ሀገር አውራጃ እንኳን በቅጡ ለይተው የማያውቁ አማራ ስለሆኑ ብቻ በኦሮሞ ጽንፈኛ ሲገረፉ፤በጥፊ ሲመቱ፤ በጥይት ሲገደሉ፤ ጸያፍ ሲሰደቡ ወዘተ ማዬት የዘወትር ክስተት ነው። ለብዙ ዘመን በትግሬ ኢትዮጵያዊነት ስንቶች እንዳልተመጻደቁ ( ትግሬን ለማናደድ አንተ ኢትዮጵያዊ አይደለህም በለው እንዳላሉ) እውነተኛ ሰዐት ሲመጣ ግን ጥቂት የማይባሉ ትግሬዎች ሱዳናዊነን፤ በሚያሳዝንም ሁኔታ ወገናቸው የሆነውን የጎንደር ማይካድራ አማራ ሆዳቸው ችሎ አረዱ። በርካታ የሽማግሌ ቀላል ትግሬዎች የወያኔ ቅዘንማ ዐርማ ይዘው ክቡር የኢትዮጵያን ሰንድቅ ጥለው በአለም አደባባይ ይጮኻሉ።

አሁን እየሆነ ያለው 2 ልዋላዊ አገር ( ትግራይ ሪፓብሊክ እና ኦሮምያ ሪፓብሊ የሚባሉ ለመፍጠር የሚደረግ ግብግብ ነው። እነኝህ ከታዳጊ እስከ ልሌታም ሸበቶ አረጋዊ ድረስ በውጭ አገር አፋቸውን ከፍተው ኡኡታ የሚያሰሙት ኢትዮጵያዊ ሁነው ሳይሆን የሌላ አገር ዜጋ ሁነው የሌላ ተምኔታዊ አገር እወቁልን ሰንደቅ አላማ እያውለበለቡ ነው። በዚህ ትዕይንት ውስጥ ማን ነው ላሜ ቦራ የሆነው ነው? 1 ቁጥ አማራ ነው። ሌሎች ጎሳዎችን ለመንገዳቸው እንቅፋት አድርገው አያዩቸውም - በቀላሉ አወራርደው ይሰለቅጧቸዋል። እንደ ዝሆን ገዝፎ ይህን ያህል ዘመን አልወድቅ ያላቸው አማራ ነው - አረብ እና ምዕራብ እረዷቸው አሁንም አልቻሉም። ይበልጡንም አማራ እየደመሰሳቸው ነው። አማራ ደግሞ ይህን አቅሙን በሚገባ መረዳት አለበት። አማራ በምዕራብ አገር በአደባባይ መጮህ ሳይሆን በትግል ሜዳ መፋለም ብቻ ነው ውጤት የሚያመጣው። የምዕራብ አለም አማራን ማዳመጥ አይፈልግም። የሚፈልገው ህዳጣን ትግሬ ወያኔ ወይም እንደነ ተስፋየ ገብረእባብ በስህተት ይውሸት ታሪክ ቅዠት ያሰከሩትን ኦነግ ኦሮሙማ ነው።

አማራን የሚያወጣው እጁ ( አማራ) እንጅ ማንም ነጻ አያወጣውም። በየምዕራቡ አለም ሰልፍ በመውጣት አይሆንም ወይም ለከንቱ ዝና ከዚህ ወይም ከዚያ ተወካይ ጋር አክቲቪስት ወዘተ ተነጋገረ አይሰራም። የ50 አመታቱ የኢትዮጵያ ጦርነት ኢላማ ያደረገው አማራን ነው። አማራ ነው ታዳኙ።

Post Reply