Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11189
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ኢህአፓ፤ ወያኔ፤ ኦነግ ፤ ሻዕብያ ሲፈጠሩ የአይን ጥቅሻ ያህል የዕድሜ ልዩነት ነበራቸው? በእኔ ግምት አንድ ላይ የፈሉ እና ኢትዮጵያን ለውድቀት የዳረጉ ይመስለኛል።

Post by Abere » 03 Apr 2024, 13:14

ኢህአፓ፤ ወያኔ፤ ኦነግ ፤ ሻዕብያ ሲፈጠሩ የአይን ጥቅሻ ያህል የዕድሜ ልዩነት ነበራቸው? በእኔ ግምት አንድ ላይ የፈሉ እና ኢትዮጵያን ለውድቀት የዳረጉ ይመስለኛል። እያንዳንንዳቸው ለኢትዮጵያ እና ለህዝቧ አንዳች የሚፈይድ ነገር ያላመጡ ዳሩ ግን ስዴት፤ ውርደ፤ እልቂት ያመጡ ናቸው ባይ ነኝ።

Axumezana
Senior Member
Posts: 13697
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ኢህአፓ፤ ወያኔ፤ ኦነግ ፤ ሻዕብያ ሲፈጠሩ የአይን ጥቅሻ ያህል የዕድሜ ልዩነት ነበራቸው? በእኔ ግምት አንድ ላይ የፈሉ እና ኢትዮጵያን ለውድቀት የዳረጉ ይመስለኛል።

Post by Axumezana » 03 Apr 2024, 13:54

ኢህእፓ፥ እትዮጵያን፥ ለማዳከም፥ በፉሊስጤሞች፥ እና፥በአልጀርያዎች፥ድጋፍ፥የተመሰረተ፥ ሽብርተኛ፥ ሲሆን፥ የከተማ፥ ሽብር፥ በመጀመር፥የዘመኑን፤ አስኳል፤ ወጣቶች፥ ያስፈጀ፥ ነው። ኦነግም፥እድሜ፥ ልኩን፥ አድሮ፥ ጥጃና፥ጥገኛ፥የነበረ፥ ድርጅት፥ ነው። ሻእብያ፥ ደግሞ፤ በግብፆች፥ከተወለደው፥ የጀብሃ፥ሊጅ፥ ሲሆን፥ ኢትዮጵያንና፥ ኤርትራን፤ ያጠፋ፥ ድርጅት፥ ነው።
ወይን፥ ኢትዮጵያን፥ ከአዘቅት፥ አውጥቶ፥አረጋግቶና፥ሰላም፥ አስፍኖ፥ በአለም፥ ፈጣን፥ እድገት፥ ካላቸው፥ አገሮች፥ ተርታ፥ ያሰለፈና፤ አይነኬውን፤ የአባይ፥ ግድብ፥አስጀምሮ፥ 68% ድረስ፥ ያስጨረሰ፥ ነው። ከስድስት፥ አመት፤ በፊት፥ በውስጥ፥ የስልጣን፥ ጥመኞችና፥በእነ፥ግብፅ፥ቅንብር፥ለተነሳው፥ አመፅ፥ ስልጣኑን፥ አስረክቦ፥ መቀሌ፥ ቢከትምም፥በግብፆች፥በኢሳያስና፥ በአብይ፥ የሞት፥ ፍርድ፥ ተፈርዶበት፥ በእግዚአብሔር፥ ጥበቃና፥ በከፍተኛ፥ የትግራይ፥ ህዝብ፥ መስእዋትነት፥ በከፍተኛ፥ አልሞት፥ ባይ፥ተገዳይነት፥፥ ህልውናውን፥ አስጠብቆና፥ ዛሬም፥ እንደትናንቱ፥ የኢትጵዮጵያ፥ የመረጋጋት፥ ተስፋ፥ ሆኖ፥ እየቀጠለ፥ይገኛል። ብር፥ ላበደረ፥ ጠጠር፥ እንደሚባለው፥ ከከሰሩት፥ ድርጅቶች፥ ጋር፥ ወይንን፥ጨፍልቆ፥ ለማዬት፥ መሞከሩ፥ ከጭፍን፤ ጥላቻ፥ የመነጨ፥ ነው።
Last edited by Axumezana on 03 Apr 2024, 14:35, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30981
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢህአፓ፤ ወያኔ፤ ኦነግ ፤ ሻዕብያ ሲፈጠሩ የአይን ጥቅሻ ያህል የዕድሜ ልዩነት ነበራቸው? በእኔ ግምት አንድ ላይ የፈሉ እና ኢትዮጵያን ለውድቀት የዳረጉ ይመስለኛል።

Post by Horus » 03 Apr 2024, 14:08

አበረ፣
ባለፉት ስርዓቶች የየተኛው አመለካከት አባል እንደ ነበርክ ባላውቅም ያልከው ስህተት ነው። ኢ ሕ አ ፓ ሾቪኒስት ያማራ ፓርቲ ተብሎ በወያኔ በሻቢያ በኦነግ ተወግቶ ከሰሜንም ከደቡብም የተባረረ ድርጅትና ደርግ ወታደራዊ አገዛዝ ብቸኛ ለማረግ ጨፍጭፎ ያጠፋው ድርጅት ነው ። ታሪክን ወደ ተመልሰ በውጤቱ እንገምግም ከተባለ የኢትዮጵያ መከራ የተጀመረው በጎሳ ድርጅቶች እና በወታደራዊ መንግስት ተመትቶ ኢ ሕ አ ፓ የወደቀ ቀን ነው የዚህች አገር መከራ የጀመረው ። ወደፊትም ይህ መከራ የሚቆመው እንደ ኢ ሕ አ ፓ ኢትዮጵያ የሚወድ ለሕዝብ መብት የሚሞት ድርጅት ሲፈጠር ብቻ ነው። የኢሕአፓ መጥፋት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ያስከተለው መዘዝ ገና ለብዙ ዘመን የሚታይ ነው።

Post Reply