መቼ ይሁን ሄጄ የማየዉ፣ ቅዱስ ላሊበላን ነበር ምኞቴ፣
ምቼስ ይሁን ወደ ሰሜ አቅንቶ የአክሱም ጉብኝቴ፣
ከዛም ወደያ መለስ ብዬ ወደ ፋስለዳስ አቅንቼ እዛ መገኘቴ
አሁን በዛብኝ የምጎበኛቸዉ የኢትዮጵያ መስብ ና መደረሻዬ
እንዴት አድርጌ ነዉ፣ ህዳሴን ሳላይ፣ ብዬ ስዘጋጅ፣ ለምቀጥለዉ ጉዞዬ
መጣ ና በለጠብኝ አዲሱ፣ የአገሪቷ ትልቁ ቅርስ፣ አድዋ መታሰባዬ
እንዴት ሆኜ ነዉ እሱን ሳልጨምር፣ ለምቀጥለዉ መዳራሻዬ?
ይብዛልሽ ብልፅግና፣ ይመርብሽ፣ ደርቦ ዳራርቦ ለወደፊትም አገሬ
የአንቺ መነሳት፣ ይቸግራቸዉ፣ ይጭነቀቻዉ፣ የዉጪም፣ የዉስጥ ቡራቡሬ
የንቺ ነጥቆ መሄድ እንደሆን ደግሞ ደጋጎም ታይቶዋል ሆኖ አይቀሬ..